ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch @morhawassabranch Channel on Telegram

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

@morhawassabranch

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch (Amharic)

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch አዲስ እና የተሻሻለ ከሆነ ቅርንጫፎች ለሀዋሳ ሱጋም እና አንዴ ምሳሌ የተረዳችሁትን እና ወቅታዊ መዝናኛዎችን በቀን ገና ከተቀረ። ይህ አንዴ በጣም በሚከተለው የኳስ እድሳችን ላይ በተነሳን መረታኝ ላይ ያለውን ውጤት እና መፍትሄ ይቀላቀሉ። በሱጋም መቼ እቀርባለሁ? በእዚህ ምሳሌ ለሁሉም የቅርንጫፎች አካባቢ ያሉ እና ከሂደት ማከማቹ የተደጋጋሁ ሆነ ለሂደት ተደራሽ ከተደረገበት ቀን የሚገኝ ወቅታዊ መማከሙን ለመፍጠር በሚደረግበት ጥናት ላይ እንዳለ። ሁለቱን ከሆነ ካልታወቀ ?- የሚየላውን ወቅታዊ መሠዋልን የሚፈፅማችሁ ሁለቱንም ለቆሞታል፡፡

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

15 Nov, 04:22

"ገቢያችን ህልውናችን" (15ኛ ዓመት የመሰከረም ወር 2017 ዓ.ም ቁጥር 177 እትም ጋዜጣ)
ሕዳር 05/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
"ገቢያችን ህልውናችን"በገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት እየተዘጋጀች የምትሰራጭ ወርሃዊ ጋዜጣ ስትሆን ጋዜጣዋን ለማገኘት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ:- https://shorturl.at/s7MsF

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

14 Nov, 09:43

#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

የመመሪያውን ሙሉ ክፍል ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/JNqW7

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

14 Nov, 09:37

ሕዳር 05/2017 ዓ.ም
👉ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡
🙏ግብር÷ ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/MORBAHIRDARBRANCH2024
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/morbahirdar
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@m.o.r.bahirdarbranch
የሬዲዮ ፕሮግራም፡- ዘወትር እሮብ ከቀኑ 5፡30 ጀምሮ በአማራ ራዲዮ እና በአማራ ኤፍ ኤም ባህር ዳር 96.9
በወዳጅነት ይከታተሉን፡፡

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

13 Nov, 19:57

#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

የመመሪያውን ሙሉ ክፍል ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/JNqW7

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

12 Nov, 17:21

የአንድ ጊዜ ስልጠና ተሰጠ

ሀዋሳ (03/03/2017 ዓ.ም ):- በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት  ለመዳ ወላቡ  ዩኒቨርሲቲና  በስሩ ለሚገኙ ካምፓሶች ግዥ ፣ፋይናንስና ውስጥ ኦዲት ሰራተኞችና ኃላፊዎች  በባሌ ሮቤ ከተማ  በመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግብ ወቅታዊ ሁኔታን ያገናዘቤ የአንድ ጊዜ ሥልጠና በዛሬ ቀን  ሲሰጥ ውሏል።
 በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ከፋዮች ትምህርትና  መረጃ አቅርቦት ቡድን  አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዛሬ ስልጠና በተለያዩ የታክስ አዋጆች እና መመሪያዎች ዙሪያ  ስልጠና የተሰጠ  ሲሆን የእለቱን ስልጠና  የታክስ ከፋዮች ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ፍጹም እሸቱ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ፣ስለ ወጪ መጋራት ፣ስለቅድመ ግብር ክፍያ እና ቫት ዊዝሆልዲንግ ታክስን በተመለከተ  ሰፊ ገለጻ አደርገዋል። በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ  ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ይጫኑ፦

በቴሌግራም
https://t.me/MORHawassaBranch

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100080114927205

በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCtu9M68G_lQbTIsu1fzzjyw
ቀጣይ

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

12 Nov, 03:30

https://youtu.be/8yRZDS7z1Dw

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

12 Nov, 03:27

 የመመዘኛ ፈተና  ተሰጠ

በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአንደኛው ምዕራፍ 29ኛ ዙር የሞጁላር ስልጠና ለተከታተሉ ወላይታ ከተማ እና ዙሪያ ለሚገኙ ታክስ ከፋዮች  ህዳር 02/2017 ዓ.ም  የመመዘኛ ፈተና ተሰጥቷል፡፡
የመመዘኛ ፈተናው የተሰጠው ባለፈው ሳምንት ቀጥተኛ በሆኑ የታክስ ዓይነቶች ማለትም ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ፣ ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ፣ከንግድ ስራ የሚገኝ ገቢ፣ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና ቅድመ  ታክስ ላይ ስልጠና ለወሰዱ ግብር ከፋዮች ሲሆን
በዚህ ማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ  የተገኙት የታክስ ስርዓት ም/ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድአወል ወዳጆ ተገኝተው  ሰልጣኞችን ያወያዩ ሲሆን በውይይት ወቅት ከስልጠና  ጋር ተያይዞ ሞጁላር ስልጠና በአካል ብቻ ሳይሆን በርቀት እየተሰጠ እንዳለ በመግለጽ  ግብር ከፋዮች ከነዚህ አማራጮች የሚፈልገውን መርጦ በመጠቀም የታክስ ህግን በማወቅ ግዴታውን በተገብ መንገድ በመወጣት መብቱን መጠየቅ የሚችል ዜጋን ለመፍጠር እንደዚህ አይነት ስልጠና አይተካ ሚና መኖሩን አብራርተዋል። በተጨማሪም  ግብር ከፋዮች በተለያዪ ጉዳዮች ዙሪያ ላነሷቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት  ሰልጣኞች ስልጠናዉን በአግባቡ ተከታትሎ  በማጠናቀቃቸዉ ምስጋና በማቅረብ  በቀጣይ  ለሚሰጠው ስልጠናም በሚጠሩበት ጊዜ ተገኝተዉ የጀመሩትን  ስልጠና መጨረስ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ይጫኑ፦
በቴሌግራም

https://t.me/MORHawassaBranch

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100080114927205

በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCtu9M68G_lQbTIsu1fzzjyw

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

08 Nov, 15:40

ለቅ/ጽ/ቤታችን ግብር ከፋዮች በሙሉ

          ጥቅምት (29/2017 ዓ.ም
  በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት በነገ ዕለት ስድስቱን ታክስ ማዕከላት ጨምሮ የሙሉ ቀን አገልግሎት የሚንሰጥ  መሆኑን እያሳወቅን የ2016  በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ  ግብር ማሳወቂያ ጊዜ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም  ስለምጠናቀቅ  እስካሁን ግብራችሁን ያላሳወቃችሁ  እና ያልከፈላችሁ  ግብር ከፋዮች በሙሉ በቀረው አንድ ቀን ውስጥ  የታክስ ግዴታችሁን እንድትወጡ  እናሳስባለን።
        
                     ግብር ለሀገር ክብር!!
ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ይጫኑ፦
በቴሌግራም
https://t.me/MORHawassaBranch

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100080114927205

በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCtu9M68G_lQbTIsu1fzzjyw

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

08 Nov, 14:48

#1_ቀን_ብቻ_ቀረው!

ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ገቢ አሳውቆ ግብር የመክፈያ ጊዜ ነገ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

ስለሆነም ግብርን በወቅቱ አሳውቆ ባለመክፈል ምክንያት ከሚመጣ ቅጣትና ወለድ ለመዳን ዛሬውኑ አሳውቀው ይክፈሉ!

የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር

ግብር ለሀገር ክብር!

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

30 Oct, 08:00

https://youtu.be/1K3s_m2MrlY

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

29 Oct, 19:25

የሀሰት ወይም አሳሳች መግለጫዎች እና የተጭበረበሩ ሰነዶችን ማቅረብ የሚያስከትለው ቅጣት

የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 እና አስተዳደራዊ ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 9/2011 መሰረት የሀሰት ወይም አሳሳች መግለጫዎች እና የተጭበረበሩ ሰነዶች ለግብር ሰብሳቢ አካል ያቀረበ

1. ማንኛውም ሰው ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት፦

ሀ) ለባለሥልጣኑ ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መግለጫ የሰጠ፤ ወይም
ለ) ለባለሥልጣኑ ሊቀርብ የሚገባን መግለጫ አሳሳች ሊያደርግ በሚችል አኳኋን መካተት የሚገባቸውን ነገሮች ያለበቂ ምክንያት ያስቀረ እንደሆነ፤
ሐ) ለባለሥልጣኑ የተጭበረበሩ ሰነዶችን ያቀረበ እንደሆነ፤
ከብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) እስከ ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሦስት ዓመት እስከ አሥራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/6ilxf7

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

29 Oct, 19:21

29ኛ ዙር የክፍል አንድ ስልጠና  መሰጠት ተጀምረ

ሀዋሳ (19/02/2017 ዓ.ም) በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመጀመሪያው ምዕራፍ የ29ኛው ዙር የሞጁላር ስልጠና በትላትናው ቀን በወላይታ ሶዶ  ከተማና ዙሪያ ለሚገኙ ታክስ ከፍዮች ተሰጥተዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት ቡድን አዘጋጅነት በተሰጠው ስልጠና  ከመቀጠር የሚገኝ ገቢና የወጪ መጋራት በሚሉ ርዕሶች ላይ  የተሰጠ ሲሆን የዕለቱም ስልጠና የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት ቡድን አስተባባሪ  ወ/ሮ አለምጸሀይ ጭሻ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በስልጠና ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነት፣ከገቢ ግብር ነጻ ስለሆኑ ገቢዎች ፣በገደብ ነጻ ስለተደረጉ ገቢዎች፣አይነት ጥቅም እና ከወጪ መጋራት ጋር ተያያዞ ያሉ ጉዳዮችን በተመለከተ ስልጠና በመስጠት ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ይጫኑ፦
በቴሌግራም
https://t.me/MORHawassaBranch

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100080114927205

በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCtu9M68G_lQbTIsu1fzzjyw

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

25 Oct, 19:45

ማሳሰቢያ  ለቅ/ጽ/ቤታችን ግብር ከፋዮች በሙሉ
 ጥቅምት (15/2017 ዓ.ም)
በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም አዲስ ያስገነባውን ህንጻ አስመርቆ ስራ መጀመሩ ይታወቃል። ስለሆነም  ቢሮ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የቢሮ መደበኛ ስልክ ኔትወርክ ዝርጋታ ሂደት ላይ ስላለ ማንኛውም ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳረያ ጋር በተገናኘ ለሚቀርብ ጥያቄ ለምሳሌ፦ብልሽት ለማስመዝገብ፣መብራት ሲቋረጥ እና አመተዊ እድሳት ሲገባ ለማስመዝገብ ቀጥሎ በተገለጸው ስልክ ቁጥር  0912021226/0916933649 በመደወል መረጃ  መስጠት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። በተጨማሪም  ከታክስ ጋር ለሚነሱ ጥያቄዎች 0936162245 በመደወል መረጃና ማብራሪያ  ማገኘት  እንደምትችሉ እያሳሰብን የ2016 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ግብር ያላሳወቃችሁ እና ያልከፈላችሁ ግብር ከፋዮች በሙሉ በቀሩት ቀናት ውስጥ የታክስ ግዴታችሁን እንድትወጡ  እናሳስባለን።

         ግብር ለሀገር ክብር!!

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ይጫኑ፦
በቴሌግራም
https://t.me/MORHawassaBranch

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100080114927205

በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCtu9M68G_lQbTIsu1fzzjyw

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

25 Oct, 19:44

https://www.youtube.com/watch?v=6MPjCRb2G5Y&list=PPSV

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

25 Oct, 13:43

በገቢዎች ሚኒስቴር ለሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች  በሙሉ
ውድ ግብር ከፋዮቻችን
ከሐምሌ 1 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ የአመታዊ  ንግድ ትርፍ ግብር እንድሁም የመስከረም ወር ተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ ቲኦቲ ፣ ኤክሳይስ ታክሰ እና ሌሎች ግብር ዓይነቶች የሒሳብ ማሳወቂያና  መክፈያ ጊዜ መሆኑን ይታወቃል ፡፡
ስለሆነም ውድ ግብር ከፋዮቻችን  ወቅቱን ጠብቃችሁ በማሳወቅ እና በመክፈል ከአላስፈላጊ ወልድና ቅጣት ድርጅታችሁን እንድታድኑ፣ መብታችሁን በማስጠበቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ  እናሳስባለን፡፡

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

25 Oct, 13:40

https://youtu.be/QkAVDteYRGE?si=Fypxf3obQ1IwXcwi

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

22 Oct, 16:07

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የአድራሻ ለውጥ ለማድረግ መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ

ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

📢አዲስ የንግድ አድራሻ የተቀየረ የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፣

📢ለታክስ ባለ ስልጣኑ የአድራሻ ለውጥን ማሳወቅ ፣

📢የአድራሻ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል ከግብር ከፋዪ የታክስ ማዕከል የተጻፈ

የአድራሻ ለውጥ ደብዳቤ ለአቅራቢው መውሰድ፣

📢የተጨማሪ እሴት ታክስ ካላቸው ማቅረብ አለባቸው፡፡

በታደሰ ኢቢሳ

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

21 Oct, 11:42

የመመዘኛ ፈተና ተሰጠ
በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሶስተኛው ምዕራፍ 18ኛ ዙር የሞጁላር ስልጠና ለተከታተሉ ሰልጣኞች በወልቂጤ ከተማ  ጥቅምት  11/2017 ዓ.ም የመመዘኛ ፈተና ተሰጥቷል፡፡
የመመዘኛ ፈተናው ከሞጁል 9 እስከ 13 ድረስ ስልጠና ለወሰዱ ግብር ከፋዮች የተሰጠ
ሲሆን በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ የታክስ ስርዓት ም/ስራ አስኪያጅ  አቶ መሀመድአወል ወዳጆ ተገኝተው ሰልጣኞች በሁሉም ሞጁሎች ላይ ለስልጠና በተጠሩበት ጊዜ በመገኝት  ስልጠና መወሰዳቸውን በማመስገን ያገኙትን ዕውቀት ለሌሎች ተደራሽ  በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንድወጡ  እና የቀጣይ ስራዎችን ታክስ ህጉ በሚፈቅደው አግባብ በመስራት ትክክለኛውን ገቢ በመሰበሰብ የግብር ግዴታችሁን መወጣት አለባችሁ  በማለት ያሳሰቡ ሲሆን  ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።በተጨማሪም  የተቋማዊ ስነ ምግባርና ስራ አመራር ቡድን አስተባበሪ አቶ ሰላሙ ዮሐንስ በውይይት መድረኩ ላይ ለግብር ከፋዮች በሰጡት  አስተየያት ማንኛውንም  አገልግሎት  በምታገኙበት  ወቅት የስራ ስነ ምግባር ተላብሶ ተገልጋይን በተገቢው መንገድ የማያስተናግድ ሰራተኛ ካለ ለሚመለከተው ክፍል መረጃ በመስጠት  ትብብር እንድያደረጉና የገቢዎች ሰራተኛ ነን በማለት ሀሰተኛ ማንነት በመጠቀም ከሚያጨበረብሩ ህግ ወጦች  ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አስሳስበዋል።

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ይጫኑ፦
በቴሌግራም
https://t.me/MORHawassaBranch

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100080114927205

በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCtu9M68G_lQbTIsu1fzzjyw

ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ M.O.R Hawassa Branch

18 Oct, 19:03

የታክስ ዕዳ አከፋፈል ቅደም ተከተል
አንድ ታክስ ከፋይ የታክስ ግዴታውን በወቅቱ ባለመክፈሉ ምክንያት ቅጣት እና ወለድ መክፈል በሚኖርበት ጊዜ የአከፋፈል ቅደም ተከተሉ፦
👉በመጀመሪያ ዋናውን የታክስ ዕዳ፣
👉በሁለተኛ ደረጃ ክፍያው ለዘገየበት የሚከፈል ወለድ፣
👉በመጨረሻ ቀሪው የአስተዳደራዊ ቅጣት ይሆናል፡፡
ማንኛውም ታክስ ከፋይ በሚፈፀምበት ጊዜ ከአንድ በላይ የታክስ ዕዳ የሚፈለግበት ከሆነ ክፍያው የሚሸፍነው ዕዳ ቅደም ተከተል ዕዳው በተፈጠረበት ጊዜ ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል፡፡
በታደሰ ኢቢሳ
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ቅዳሜ አመሻሽ ከ 12፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።