Telkhis (هذه عقيدتنا) @telkhis Channel on Telegram

Telkhis (هذه عقيدتنا)

@telkhis


Telkhis (هذه عقيدتنا) (Arabic)

Telkhis (هذه عقيدتنا) هو قناة تيليجرام تقدم محتوى متنوع وشيق يتعلق بالعقائد والمعتقدات. تهدف القناة إلى توفير معلومات شيقة ومفيدة للجمهور حول مواضيع دينية وفكرية. من خلال تلك القناة، يمكنك الاطلاع على مقالات متنوعة تتناول قضايا هامة تتعلق بالعقيدة والإيمان. سواء كنت مبتدئًا في هذا المجال أو مهتمًا بتعميق معرفتك، ستجد في Telkhis (هذه عقيدتنا) ما يلبي احتياجاتك. انضم إلينا اليوم لتستفيد من محتوى ذو جودة عالية وتواكب كل جديد في عالم العقائد والمعتقدات.

Telkhis (هذه عقيدتنا)

28 Nov, 16:50


ሰው ሆኖ የማይረሳ የለምና አማኞችም ሶላትም ዉስጥ ሆነው መጨመር የሌለበባቸውን ረስተው ሊጨምሩ ይችላሉ። አንዳንዴ ደግሞ መፈጸም የነበረበትን ያልፋሉ። በሌላ ወቅት ደግሞ ምናልባት ምን እንደፈጸሙና ምን እንደቀራቸውም ጭምር ግራ ይጋባቸው ይሆናል። ለእነዚህና መሰል ተያያዥ ችግሮች ሸሪዓችን ያስቀመጠው ማስተካከያ አለ። እሱም ሱጁዱ'ሰህው (የመርሳት ሱጁድ) ይባላል።

>> ሱጁደ ሰህው ምንምን ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት?

>> በሱጁደ'ሰህው ሊስተካከሉ የሚችሉ ስህተቶችስ የትኞቹ ናቸው?

>> ሱጁደ'ሰህው የሚፈጸመው ከማሰላመት በፊት ወይስ በኋላ?

>> የትኞቹ ስህተቶች ናቸው ከማሰላመት በፊት የመርሳት ሱጁድ እንድናደርግ የሚያስገድዱን?

>> ከማሰላመታችን በፊት ማድረግ የነበረብንን የመርሳት ሱጁድ ብንረሳውስ?

>> ለየትኛዎቹ ስህተቶች ነው ካሰላመትን በኋላ ሱጁደ'ሰህው መፈጸም ያለብን?

>> ኢማም ተከትለን በምንሰግድበት ወቅት ረስተን የምንፈጽማቸው ስህተቶችስ በምን መልኩ ነው የሚስተካከሉት?

ይች በpdf  መልክ የተዘጋጀች ጽሁፍ እነዚህንና መሰል ጥያቄዎቻችንን የምትመልስ አጠር ያለች ማስታወሻ ነች።

እርሰዎ ያንብቧት። መልካም ነገርን ለሌሎች የጠቆመ  የአጅራቸው ተቋዳሽ ይሆናልና ለወንድምና እህቶቻችን ትደርሳቸው ዘንድ ደግሞ ያሰራጯት።

ያው ሰው ከስህተት አይነጻምና በጽሁl ዉስጥ ያገኙት ስህተት ካለ ደግሞ ያድርሱኝ።

t.me/telkhis

Telkhis (هذه عقيدتنا)

29 Oct, 17:47


https://drive.google.com/drive/folders/1Z0-9x5cTtBu83H-yCLOlgKaslnWThm7r

Telkhis (هذه عقيدتنا)

21 Sep, 06:52


አልሐምዱሊላህ ሀምደን ከሲረን ጦይበን ሙባረከን ፊህ

#አልሙለኸሱል_ፊቅሂይ ሚን ዑሉሚል ኢማሚል አልባኒይ

የዛሬ አመት September 25 -2023 የጀመርነውን ይህን ምርጥዬ ኪታብ
እነሆ በአመቱ September 20-2024 አጠናቀቅን። አላህ የበዛ የሆነ ዉዳሴና ምስጋና ይገባው። መልካም ስራችንን ይቀበለን። ስህተቶቻችንን ይቅር ብሎ ይለፈን።

Telkhis (هذه عقيدتنا)

11 Sep, 08:52


#አያህ_ወተፍሲር

በአላህ ላይ መመካት
ወደ እሱው መጠጋት
ያለ አንተ ምን ዋጋ አለኝ ማለት
ለስኬት መብቂያ እና ከመከራ መጠበቂያ አዋጩ መንገድ ነው። ሺንቂጢይ

{ وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ }
{ فَوَقَاهُ اللَّهُ سَيِّئَاتِ مَا مَكَرُوا }. [سُورَةُ غَافِرٍ: ٤٤-٤٥]

T.me/telkhis

Telkhis (هذه عقيدتنا)

10 Sep, 10:33


#አያህ_ወተፍሲር

በንጋትና በአመሻሹ ወቅት
ስግደታቸውን በትክክል የሚፈጽሙ እንድሁም በጥቅሉ ጌታቸውን በዱዓእ የሚማጸኑ ሰዎች ከሌሎች አማኞች ከፍ ያለ ልቅና አላቸው። ምክንያቱም እነኚህ ወቅቶች አብዛኛው የሰው ልጅ በስራ የሚወጠርባቸው፣ ወደ ስራ የሚሯሯጥባቸው እና ስራውን ለማጠናቀቅ ደፋ ቀና የሚልባቸው ሰአቶች ናቸው። በእነዚህ ወሳኝ የጥድፊያ ወቅቶች ላይ የጌታውን ትእዛዝ የጠበቀ አማኝ፣ በሌላው ወቅት ላይ ትእዛዙን የበለጠ ይጠብቃል ተብሎ ነው የሚታመነው።

ለዚህም ነው ጌታችን አላህ "እነዚያ የአምላካቸው ሽልማት ለመጎናጸፍ በማሰብ በጧቱና በአመሻሹ ወቅት ላይ ጌታቸውን በአግባቡ የሚያመልኩን ባልደረቦችህን በፍጹም እንዳትገፋቸው ብሎ ነብዩን صلى الله عليه وسلم ያስጠነቀቀው።

{ وَلَا تَطْرُدِ الَّذِينَ يَدْعُونَ رَبَّهُمْ بِالْغَدَاةِ وَالْعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجْهَهُ }. [سُورَةُ الأَنْعَامِ: ٥٢]

T.me/telkhis

Telkhis (هذه عقيدتنا)

08 Sep, 18:51


#አያህ_ወተፍሲር

ጫማህን ከሌሎች ሰዎች ጫማ ጋር ማነጻጸርህ
ልብስህን ከሌሎች ሰዎች አልባሳት ጋር ማነጻጸርህ እና የኔ ከእነሱ ጋር ለንፅፅርም የሚቀርብ መሆን የለበትም በሚል በላጭ በላጩን ካልገዛሁ ማለትህ

'''ይህችማ የዝንተ ዐለሟ ሀገር ነች። እሷንም በምድር ላይ የበላይነትን ለማይፈልጉትና ብልሽትን ለማያሰራጩት አማኞች ነው የምናደርጋት" ከሚለው የጌታችን ቃል ጋር የሚካተት ነው።

( تلك الدار الآخرة نجعلها للذين لا يريدون علوا في الأرض ولا فسادا والعاقبة للمتقين)

T.me/telkhis

Telkhis (هذه عقيدتنا)

02 Sep, 19:03


ለኡዱሂያ እርድ የተቀመጡ የተለያዩ መስፈርቶች ለዐቂቃ እርድ (ከልጆች መወለድ ጋር ተያይዞ የተደነገገ እርድ) ላይ ግን አይደነገጉም።

ለምሳሌ
1) የኡዱሂያን እርድ ስጋውን ለራስ መመገብ፣ ማስቀመጥና ለሚስኪኖች መስጠት ያስፈልጋል። ዐቂቃ ላይ ግን ሙሉ ስጋውን ለራስ ብቻ መመገብ ወይም ሙሉ ስጋውን ለሚስኪኖች ብቻ ማከፋፈል ይቻላል።

2) የኡዱሂያ እርድ የበግና የፈየሏን እድሜ በተመለከተ የተቀመጠ ወሳኝ ገደብ አለ። ለዐቂቃ ግን መታረድ የሚችሉን በየትኛውም እድሜ ላይ ያሉ በጎችንና ፍየሎችን ማረድ ይቻላል።

4) ለኡዱሂያ እርድ የሚቀርቡ እንስሳቶች ከተወሰኑ እንከኖች የነጹ መሆን አለባቸው። ለምሳሌ ግልጽ የማየት ችግር፣ ግልጽ ሽባነት፣ ግልጽ ስብራት እና ግልጽ የሆነ ህመም ያለባቸውን እንስሳት ለኡዱሂያ ማረድ አይቻልም። ለዐቂቃ ግን ይቻላል።

5) የኡዱሂያ እርድ ከፍየል፣ ከበግ፣ ከከብትና ከግመል መሆን ይችላል። የዐቂቃ እርድ ግን ከፍየልና ከበግ ዉጭ ማረድ አይቻል።

6) የኡዱሂያን እርድ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ብቻ ነው ማረድ የሚቻለው። በዒደል አድሃና ቀጣይ ባሉት ሶስት የአያመ ተሽሪቅ ቀናት ብቻ ነው ማረድ የሚቻለው። የዐቂቃ ግን በተወለደ በ7ኛው ቢሆን ሱንና ነው። ይህ ካልተሳካ በ14ኛው ይህም ካልተሳካ በ21ኛው ቀን መታረዱን የሚያበረታቱ የቀደምት አበዎች አስተያየት አለ። በእነዚህ ቀናት ካልተሳካም በየትኛውም በተመቸን ቀንና ጊዜ ዐቂቃን ማውጣት ይቻላል። ከ7ኛው ቀን በፊትም ከ21ኛው ቀን በኋላም በእነዚህ ቀናቶች መካከልም ዐቂቃን ማውጣት ይቻላል።

#ዱረሩል_አልባኒይ

T.me/telkhis

Telkhis (هذه عقيدتنا)

25 Aug, 20:12


#አያህ_ወተፍሲር

ከዚህ የቁርአን አንቀጽ
መልካም ሚስትን ያገባ ሰው ሀብትንና መብቃቃትን እንደተሰጠ ተደርጎ እንደሚቆጠር እንረዳለን።

"ደሃ ሆነህ ሳለህ ኸዲጃን በመዳር ሀብታም አደረግኩህ ማለት ነው ብለዋል ቁርጡቢይ በተፍሲራቸው።

{وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَىٰ}

T.me/telkhis

Telkhis (هذه عقيدتنا)

24 Aug, 19:32


#አያህ_ወተፍሲር

በቀንም ይሁን በሌሊት ሶላቱ ላይ ረጋ ብሎ በጽናት የቆመ
ለስግደቱ ሲል ለነፍስያው የሚከብዱን ፈተናዎች ተቋቁሞ በአምልኮቱ የጸና ሰው ነገ አላህ ፊት በሚቀርብበት ወቅት ምርመራው ይቀልለታል። ፈተናው ይገራለታል። በአግልባጩ ደግሞ በዱንያ ቆይታው ጨዋታንና እረፍትን የመረጠ፣ በቀልድና በዛዛታ ጊዜውን ያሳለፈ ነገ አላህ ፊት በሚቀርብበት ወቅት ፈተናው ይቆይበታል፣ መከራው ይወሳሰብበታል። አላህ ይሄን አስመልክቶ እንድህ ይላል።
{ وَمِنَ اللَّيْلِ فَاسْجُدْ لَهُ وَسَبِّحْهُ لَيْلًا طَوِيلًا (26) إِنَّ هَٰؤُلَاءِ يُحِبُّونَ الْعَاجِلَةَ وَيَذَرُونَ وَرَاءَهُمْ يَوْمًا ثَقِيلًا }

ኢብኑል ቀዪም رحمه الله

T.me/telkhis

Telkhis (هذه عقيدتنا)

23 Aug, 19:10


ለማንም ሰው ያለህ ውዴታም ይሁን ጥላቻ በልክ ይሁን ድንበር ያለፈ አይሁን!

ውዴታህም ያ የምትወደው ሰው ያልሰራውን ሰርቷል እንድትልና ከማይመጥነው ቦታ እንድታስቀምጠው አያድርግህ።

ጥላቻህም ያ የምትጠላው ሰው የሌለበትን እንድትቀጥፍበትና ውስጥህ የሚያውቀውን እውነታ እንድትክድ አያድርግህ።

በአጠቃላይ በሁሉም ነገር ላይ ፍትሓዊና መካከለኛ ሁን!


    🖌 ወንድማችሁ አቡ መርየም

  👉 t.me/AbuMeryemNeja 👈

Telkhis (هذه عقيدتنا)

22 Aug, 05:42


#አያህ_ወተፍሲር

"ልጅ ስጠኝ " ብቻ ብሎ ዱዓእ ማድረግ ትክክል አይደለም። መልካም የሆኑ ልጆችን ስጠኝ ብሎ መገደብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም አንዳንዱ ልጅ ሸክም ፣ መከራና ሰቆቃ ይሆንና ምናለ ባልወለድኩት ሊያሰኝ ይችላል። የነቢ ዘከሪያን ዱዓእ አስተውሉ እስኪ።

ጌታዬ ሆይ አንተ ለጋስ ነህና "መልካም የሆኑ ዝርያዎችን" ስጠኝ።

ከኢብኑ ዑሰይሚን ተፍሲር

Telkhis (هذه عقيدتنا)

20 Aug, 18:34


➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እንዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ።👇👇👇👇👇👇

1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ?
https://t.me/IbnuMunewor/893

2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ
https://t.me/IbnuMunewor/869

3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
https://t.me/IbnuMunewor/876

4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!}
https://t.me/IbnuMunewor/884

5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
https://t.me/IbnuMunewor/2227

6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ
https://t.me/IbnuMunewor/2214

7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ!
https://t.me/IbnuMunewor/2261

8, ዓሹራን ለመውሊድ?
https://t.me/IbnuMunewor/2269

9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ!
https://t.me/IbnuMunewor/2294

10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
https://t.me/IbnuMunewor/882

11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
https://t.me/IbnuMunewor/2298

12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው!
https://t.me/IbnuMunewor/886

13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል?
https://t.me/IbnuMunewor/2234

14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
https://t.me/IbnuMunewor/898

15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ
https://t.me/IbnuMunewor/2277

16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
https://t.me/IbnuMunewor/878

17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ
https://t.me/IbnuMunewor/34

18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
https://t.me/IbnuMunewor/1624

19, መውሊድ ተከሽኖ
https://t.me/IbnuMunewor/2309

20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
https://t.me/IbnuMunewor/918

21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ
https://t.me/IbnuMunewor/2302

➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵

Telkhis (هذه عقيدتنا)

20 Aug, 09:51


በአሁን ሰዓት በሱና ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት እንዲሰፋ ካደረጉ ነገሮች አንዱ ከዚህ በፊት በሱና የሚታወቅ ሰው ከሱና ሙሉ በሙሉ የማያስወጣ የሆነ ጥፋት ሲያጠፋ ወይም በሆነ ስህተት ሲወድቅ በዛ ሰው  ረድ/ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ ጭራሽ ሱና ውስጥ እንዳልነበረና  ከሱና እንደወጣ አድርገው ረድ ማድረጋቸው ነው።

     ✒️ወንድም አቡ መርየም

     👉
t.me/AbuMeryemNeja 👈

Telkhis (هذه عقيدتنا)

18 Aug, 13:57


አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ
=
በደሴ ከተማ በአዝሃር መስጅድ ሙአዚንና ጥበቃ ሆነው ያገለገሉት ሸይኽ ሰዒድ ዑመር በፅኑ ታመዋል። ህመማቸው የጉሮሮ ጫፍ ካንሰር ሲሆን ወደ ጉበትና አንጀት ተሰራጭቷል። በዚህም ሳቢያ በደሴ ሆስፒታል ለዘጠኝ ጊዜ የኬሞ ቴራፒ ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ጤንነታቸው እየተመለሰ ባለበት በቅርቡ ደግሞ የሚጥል አዲስ ነገር ተፈጠረባቸው። መንስኤው ካንሰሩ ወደ ጭንቅላታቸው መሰራጨቱ እንደሆነ ተነገራቸው።
ለዚህም የጨረር ህክምና ስለሚያስፈልግ ወደ ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ሪፈር ቢፃፍላቸውም ህክምናውን በአጭር ጊዜ ለማግኘት በፕራይቬት ካልሆነ በቀር ማገኘት አልተቻለም። በግል ለመታከም ደግሞ እጃቸው ላይ ገንዘብ የላቸውም። እንዲያውም እስከዛሬም የታከሙት በአብዛኛው ከሰው ተበድረው ነው። ስለዚህ ወንድም እህቶች ለአላህ ስትሉ በምትችሉት ሁሉ እንድትተባበሩን በአላህ ስም እንጠይቃለን።

ቤተሰቦቻቸው

የንግድ ባንክ አካውንት
1000429658512 አህመድ ሰዒድ ይመር

ስልክ ቁጥር 0935270839

Telkhis (هذه عقيدتنا)

01 Aug, 05:10


ለማንኛውም
ሳንቲምን #በሀዋላ መላክ የተፈቀደ ጉዳይ ነው። ሀራም አይሆብም። እጅ በእጅ ገንዘብን እንደመቀባበል ነው።
የአግልግሎት ክፍያ እንደሚያስከፍለው ልክ በባንክ እንደመላክ
ወይም ለሆነ ሰው እቃዬን ለቤተሰቦቼ አድርስልኝና ይህን ያክል ሳንቲም ልሰብልህ እንደማለት ነው።

ሀዋላ ከሪባ ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ የለም። አለ የሚባልበት ሁኔታ ቢኖር እራሱ ማህበሰረብ አቀፍ የሆነ የሁሉም ሰው ችግር በመሆኑ ሸሪዐዊ የሆነ ማቃለያ መንገድ ይቀመጥለታል።
በተለይም አሁን ላይ ዶላርን እንደፈለጉ መሸጥ የሚቻልበት ሁኔታ በመንግስትም ሳይቀር መፈቀዱ ሌላኛውን ሀራም ሊያደርገው ይችላል ተብሎ የሚሰጋውን ጉዳይ (መንግስት የከለከለውን መተግበር ወንጀል ነው የሚባለውን መከራከሪያም) ያስወግድልናል።
ስለዚህ በጣም ከፍ ያለ exchange rate በሚያቀርቡ ላኪዎች ሳንቲማችሁን ዘና ብላችሁ አስተላልፉ። ባይሆን ግን ሳንቲም የሰጣችሁበትን ደረሰኝ፣ የድምጽ ወይም የጽሁፍ መልእክቶች ያዙ።

Telkhis (هذه عقيدتنا)

25 Jul, 16:15


https://vm.tiktok.com/ZMr924S3M/

Telkhis (هذه عقيدتنا)

14 Jun, 17:05


እናት እና አባቷ ሳይጋቡ ወለዷት። እሷም ከተወለደች በኋላ አልተጋቡም። ተራራቁ ኧረ እንዳውን ልጅቷን እናቷ ሳትሆን አባቷ አሳደጋት። ከሚስቱ ከወለዳቸው ልጆቹ አብልጦ እየተንከባከበ፣ ወደአኼራ ሲሸጋገር ራሱ ይችው ልጁ እንዳትበደልበት ዉርስ ውስጥ እንድትካተት ኑዛዜን አስተላልፎ አለፈ። ልጅቱ አደገች። ለቁም ነገር ደረሰች። ትዳር ለመመስረት ብዙ ርቀትን ትሄዳለች። ሊያገቧት የሚሹ ወንድሞች ጉዳዪን ሲያውቁ በአባትሽ መጠራት የለብሽም። ስምሽን ቀይሪ ይሏታል። ጋሻና መከታ ሆነው ያሳደጓትን እነዚያን ወንድሞቿን እነሱኮ ባዳዎች ናቸው፣ አጅነብዮች። ከነሱ ጋር ብቻሽን መገኘት የለብሽም። እንደጸጉር፣ እጅ፣ እግር ፣አንገት--- ያሉ ሰውነቶችሽን ራሱ ሊያዩት አይፈቀድላቸውም ይላሉ። ለትዳር ወሊይ መሆን አይችሉምና አንች በነሱ ኒካህ ማድረግ አትችዪም ይላሉ። ለሷ ደግሞ እነኚህ ወንድሞች የሚያነሷቸውን ሀሳቦች መቀበል እጅግ በጣም ከባድ ነው። በዚሁ ምክንያት ጉዳይዋ ጫፍ ይደርስና እንደገና ዜሮ ይሆናል።

ሀቂቃ በዚህ ዙሪያ እንደጉድ የተሰራጩ የምሁራኖቻችን ፈተዋዎች መረጃዎችንም ተጨባጭ ግኝቶችንም ባካተተ መልኩ በደንብ ሊከለሱ ይገባቸዋል።

እንዴት ያለ አንዳች #ግልጽና_ትክክለኛ መረጃ አባት የለሽም፣ በእናትሽ ተጠሪ፣ ወሊይ አልባ ነሽ ይባላል?

Telkhis (هذه عقيدتنا)

08 Jun, 06:12


እስኪ 5ትም 100ቶም ብትሆን እንደአቅማችሁ ጣል አድርጉበት እህት ወንድሞች።

ለመጨረስ በጣም ረጂም አመታት ወሰደብንና አግዙን እስኪ

Telkhis (هذه عقيدتنا)

05 Jun, 11:13


እኛም
በወረዳችን ላይ ኹለፋኡ ራሺዲን የሚሰኝ መስጅድ በመስራት ላይ ከተሰማራን አመታት አለፉን። አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎች ይቀሩናል። መስጅዱን በዋነኝነት የሰሩት በአረብ ሀገር የሚኖሩ የኩታበር ወረዳ ተወላጆች ናቸው። በተጨማሪም ደግሞ በአሜሪካ የሲያትል ሙስሊሞች በቃላት የማይገለጽ ትልቅ ዉለታ አለብን።

አሁን ላይ የቀረን
ምንጣፍ
ሚናራ
የመብራትና የዉሃ መስመር ዝርጋታ
የመጸዳጃ ቤት ግንባታ
ደረጃዎች ናቸው
ሰሞኑ በዋትስ አፕ ተሰባስብን ሁላችንም የምንችላትን ያክል ሳንቲም እያሰባሰብን ነው።

እንደሚታወቀው እኛ ብዙ የሚድያ ሽፋን የለንም። ፕርጀክቱ በታዋቂ ሰዎችም አይደገፍም።

ግን እንድሁ እሱም ስሙም ከማይታወቁበት ቦታ ላይ መስጅድ በማሰራቱ ላይ #ሊላህ ብሎ የሚያግዝ ካለ ቢተባበረን ምንዳውን ከአላህ ዘንድ በዝቶ ተበራክቶ ያገኘዋል።

Telkhis (هذه عقيدتنا)

25 May, 12:32


#በለተሞ_መንጋ የምርቃና ስብከት ለተጠለፋችሁ ሁሉ!
~
1ኛ፦ እነዚህ ሰዎች የመንሀጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ፣ የግል አመላቸውንና ሰለፊያን የሚያምታቱ ስለሆነ የሰለፊያን ግንዛቤ ከነዚህ ሰዎች አትውሰዱ። ይልቁንም ጊዜው የሚመች ነውና ከነ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ፣ ... ኪታቦችና የድምፅ ቅጂዎች ተጠቀሙ። ከነሱም በላይ የቀደምት ዑለማዎችን አካሄድ በሚገባ ፈትሹ። እነዚህ ሰዎች ሰለፊያ ነው ብለው የሚያቀርቡላችሁ ከክፉ አመላቸውና ሸውራራ ግንዛቤያቸው ጋር የተቀላቀለ ቡድንተኛ አካሄድ ነው። የሱና ዑለማኦችን የሚያጣቅሱት ለሽፋን ያህል ነው።

2ኛ፦ ደዕዋችሁ የአካባቢያችሁን ተጨባጭ ያገናዘበ ይሁን። አዲስ ብሄርተኛ ይመስል መንሀጅ በተገነዘባችሁ ማግስት በትንሽ በትልቁ ሌሎች ጋር አትላተሙ። እነዚህ የሚያጋጯችሁ አካላት ከምትገቡበት አጣብቂኝ እንድትወጡ የሚያግዝ ይሄ ነው የሚባል ሃሳብ እንኳ ማቅረብ አይችሉም። እነሱ እንደሆኑ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን ካሜራ ውስጥ እንዳይገቡ እየተሹለከለኩ፣ ማስክ እያጠለቁ የሚጣዱ ናቸው። እነሱን ተከትላችሁ ደዕዋችሁ ቢሰናከል ብዙ ርቀት ወደ ኋላ ይመልሷችኋል።

3ኛ፦ ለፍረጃና ለተብዲዕ አትቸኩሉ። በቂ የመንሀጅ ግንዛቤ ያልያዘ ሰው ፈፅሞ ለተክ -ፊርና ለተብዲዕ ብቁ አይደለም። ነገሩ በሚገባ ተገልጦልናል ብላችሁ በምታምኑበት ጉዳይ ራሱ በመናገራችሁ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስሉ። የደመ ነፍስ አካሄድ ማንንም አይጠቅምም።

4ኛ፦ የለተሞ ጭፍራዎች ጋር መጓዝ መስጂዶቻችሁን ያሳጣችኋል። ከማህበረሰብ ጋር ያጋጫችኋል። በሂደት ደዕዋችሁን ወይ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋዋል። ወይ ደግሞ በእጅጉ ያቀጭጨዋል። ብዙ ካበላሻችሁ በኋላ ግራ ቀኝ አይታችሁ የተሻለ መስለሐ ያለበትን ውሳኔ ብትወስኑ ራሱ እነዚህ እባቦች ከማንም በላይ የሚናደፉት እናንተን ነው። የቻግኒው ሸይኽ ከማል አፍሪ ጉዳይ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። ቀድመው በነዚህ አካላት የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ነበር። አሁንም ምን ያህል እንደነቁ አላውቅም። የተሻለ መስለሐ አይተው መስጂድ ገብተው ሲያስተምሩ እድሜያቸውንም፣ ውለታቸውንም በማይመጥን መልኩ እያብጠለጠሏቸው ነው። "ያሳደጉት ውሻ፣ ያሳጣል መድረሻ!"

5ኛ፦ የአካባቢያችሁን መስለሐ ራሳችሁ ወስኑ። በሩቅ ያለ ሰው ያላችሁበትን ተጨባጭ ላያውቅ ይችላል። በተለይ እነዚህ ከህሊናቸው የተጣሉ አካላትን ፈፅሞ አታማክሩ። እንኳን ለናንተ ለራሳቸውም የሚሆኑ አይደሉም። አስፈላጊ ሲሆንና ከተቻላችሁ ዑለማኦችን አማክሩ። እነዚህ የሚጮሁትን የማይኖሩ ደናቁራን እንዳያሳስቷችሁ። ለተሞ በራሱ ምስክርነት ከ10 አመት በላይ ኢኽዋንን ሲያደንቅና አብሮ ሲጓዝ የኖረ ሰው ነው። አሁንም ከተወሰኑት ጋር ያፋጠጠው የጥቅም ግጭት ነው። እንጂ የጥቅም ቃል ሲገባለት እንኳን ከነዚህ ጋር ይቅርና ቀድሞ ተብዲዕ ካደረጋቸው ሰዎች ጋር ራሱ ሊታረቅ እልል ሲል ነበር። አሁንም የተሻለ ካየ ለሌላ ይፈርማል። ባህሩም ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ሲል ለዲን ተቆርቁሮ አይደለም። የራሱ አንዱ ጋሻጃግሬ ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር የመስጂድ ኮሚቴ አባል ነው። ኮሚቴው በመጅሊስ መዋቅር ስር እንደሆነ አስተውሉ። የባህርዳሩም ጭፍራ ዲን አይደለም ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር ያፋጠጠው። "ለኛ የተላከ ኪታብ ወስደውብን ..." እያለ ነው የህፃን ለቅሶ የሚያለቅሰው። ራሳቸው በቡኻሪ መስጂድ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ፕሮግራም አስተዋውቀው ሲያበቁ እነዚህ ከህዝቡ ብር ሲሰበስቡ ጊዜ ጨርቃቸውን ጣሉ። በቀናት ልዩነት ውስጥ ተነስተው አስጠነቀቁ። ስሜታቸውን የማይቆጣጠሩ፣ ይሉኝታ የማያውቁ ጉዶች ናቸው። እንጂ ዛሬ ለተብዲዕ የሚመዙትን ጉዳይ እየጠቀሱ ተብዲዕ ግን አናደርግም ሲሉ እንደነበር የድምፅ መረጃ አለ።

6ኛ፦ በደዕዋ ላይ ተመዩዝ አስፈላጊ ነው። ተመዩዝ ማለት ግን በራስ ላይ በር ዘግቶ መጮህ አይደለም። ከሆነላችሁ ያለ ንክኪ አስተምሩ። መድረክ ካገኛችሁ አቋማችሁ የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ በሱፊዮች መስጂድ እንኳ ቢሆን አስተምሩ። ታላላቅ መሻይኾች በሱፊያ መስጂዶች ያስተማሩበት ተጨባጭ አለ። ለምሳሌ ሸይኽ ረቢዕ ሱዳን ውስጥ በሱፊያ መስጂድ አስተምረዋል። "በአቋም ቢገናኙ ነው ከነ እንትና መስጂድ የሚያስተምሩት" የሚለው የነዚህ ሰዎች ጩኸት ዝቅ ቢል ድንቁርናቸውን ከፍ ቢል አታላይነታቸውን ነው የሚያሳየው። ለአመታት ሂዝቢዮች ላይ ቁጭ ብለው ሲማሩ ነው የኖሩት። ባህሩ፣ ሁሴን ሲልጢ እና ጠሀ ኸዲር ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። ራሳቸው የሳዑዲ ጃሚ0ዎች በሒዝቢዮች የተጥለቀለቁ እንደሆኑ ይገልፃሉ። ራሳቸው በንዲህ አይነት ተቋማት ቁጭ ብለው እየተማሩ እኛ ጋር መጥተው እንትናን ከእንትና ጋር አየነው እያሉ አድብተው ይጠብቃሉ።
በሰሜን ወሎ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ዞኖች የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። ለተሞ በሚያብጠለጥላቸው የየመን መራኪዝ የሚማሩ የለተሞ መንጋዎች አሉ። የመን መዕበር ድረስ ሄደው ሙሐመድ አልኢማም ዘንድ የሚማሩ ሁሉ አሉ። እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐረብኛ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙመይዐ ከሚሏቸው እና ኢኽዋኒዮች ዘንድ ቁጭ ብለው የሚማሩ አሉ። ከዚህም የባሰ ሱፊዮች ዘንድ ሳይቀር ሉጋ የሚማሩ አሉ። ራሳቸው በሚሰሩት ጉዳይ ሌሎችን ተብዲዕ የሚያደርጉ የማፊያ ስብስብ ናቸው።
ጩኸታቸው የእውነት መስሏችሁ እነሱን የተከተላችሁ በጊዜ ብትነቁ ይሻላችኋል። ጥሪዬ በተለይ መሬት የረገጠ ደዕዋ ላላችሁ ነው። ደዕዋችሁን ሳታጡት በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Telkhis (هذه عقيدتنا)

23 May, 10:25


ሱጁድ
እጅግ ያማረው የሶላት ክፍል ነው። ለዚህም ሲባል
የሚሰገድባቸው ቦታዎች ራሱ መስጅድ ነው የሚባሉት። መስጅድ ማለት ሱጁድ የሚደረግበት ቦታ ማለት ነው።
ይህም ሱጁድ እጅግ ወሳኙ የሶላት ክፍል ባይሆን ኖሮ
የመስገጃ ቦታዎች መስጅድ ሳይሆን መርከዕ ወይም መቃም የሚል መጠሪያ ይሰጣቸው ነበር። (የሩኩዕ ወይም የቂያም ቦታዎች)

ሶላት እንደጥቅልም ሱጁድ የሚል ስም የተሰጠው እንድሁ ወሳኝነቱን ለመግለጽ ነው።
ክቡር ነብያችንስ صلى الله عليه وسلم ቢሆኑ እስኪ ሱጁድ በማብዛት አግዘኝ ብለውት የለ ከርሳቸው ጋር በጀነት ስለመጎራበት የጠየቀውን ባልደረባቸውን ኸላድን رضي الله عنه ።
ሱጁድ አብዛ ማለታቸው ሶላትን አብዛ ለማለት አይደለ?

በሱጁድ ላይ እንበርታ!!

T.me/telkhis

5,689

subscribers

271

photos

151

videos