ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች @felsefna Channel on Telegram

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

@felsefna


የፍልስፍና እይታዎች

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች (Amharic)

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች በውስጤ እና በአንድነት እንዲሆን የጊዜ እይታዎችን መስለዋል። ዘላቂ ፍልስፍና ከእንግሊዙ አለም ያለው የአፍሪካ ቬሎቶፓላዊ ተማሪ ዝናብ ሬሳይት በድጋሚ በማከናወንበር ታሪክ እንደሚያቀርበው ነው። በአለም ግንባታ ተወዳዳሪ ሁኔታዎችን የተለያዩ ያልሆኑ ፓርቲዎችን ለማግኘት እና በቀላሉ ሲያስፈልግ የቀረቡ እንደሆናቹ ነው። ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች ከግንባታ ወደ ፍልስፍና ያገኙ ባለስለጥ ሁኔታዎችን እንዲሰብስበው ስናቀድ እንችላለን።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

02 Apr, 01:16


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 10 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

23 Mar, 18:57


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 19 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

15 Mar, 00:38


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 28 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


እንድታስታውሱ የምመክራቹሁ:- በህይወት እንድትኖሩ እና ህይወት ምን እንደሆነች ለማወቅ እንድትሞክሩ ነው። በሕይወት መኖራችሁ በጣም ውድ ነገር መሆኑ አስታውሱ ። ህይወትን አክብሩ ። ከህይወት የበለጠ የተቀደሰ ፣ ከሕይወት የበለጠ መለኰታዊ የሆነ ነገር የለም ።
#ህይወታችሁን አክብሩ ። ህይወታችሁን በማክበርም የሌሎችን ህይወት ማክበር ትጀምራላችሁ ። ዋናው ምክንያት ህይወትን ካከበራችሁ አበባን እንኳን መቅጠፍ ይከብዳችኃል። አበባው ያስደስታችኃል ፣
ትወዱታላችሁ ፣ትዳስሱታላችሁ፣ታሸቱታላችሁ ነገር ግን አበባውን መቅጠፍ ልክ እንደ እናንተ ህይወት ያለውን አካል ማጥፋት እና ማሰቃየት ነው።
:
➣ኦሾ
➣ኃይማኖትን መመርመ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


"ሁሉን ነገር መፈለግ፣ ሁሉን መሻት፣ ያለገደብ ለመኖር ማሰብ የዚህ ዓለም ጣጣ፣ የድካም ምንጭ ነው። የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ፤ የሚያጠግብህን ያክል ብቻ ብላ፤ የሚያረካህን ያክል ብቻ ጠጣ፤ ሁሉን ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም ሁሉን ነገር ማግኘትም ዕዳ ይሆናል፡፡ ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም ሁሉን ማወቅ ደግሞ ሸክምም ይሆናል።"

ምንጭ ፡- ዝጎራ በ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


በአንድ ዘመን ሀገረ-ህንድን የሚመራ ንጉስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ይሾማል።በወቅቱ የሀገሪቷን የደህንነት ጉዳይ ለሌሎች ሀገሮች መረጃ መስጠት በሞት ያስቀጣ ነበር።ታድያ የተመረጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በዚህ ወንጀል ይያዝና ሞት ይፈረድበታል።ቅጣቱ የሚፈፀምበት ቦታ በሰዋራ ስፍራ የሚገኝ አዳራሽ ውስጥ ነበር።ታዛቢዎች አዳራሹን ሞሉ።ሁለት የመሞቻ መንገድ ለወንጀለኛው ቀረበ።በቀኝ በኩል አንድ የጥንት ጠብ-መንጃ(ጠመንጃ)፣በግራ:- ጥቁር ቀለም የተቀባ የተዘጋ በር ይገኛል።የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የተዘጋውን በር ከፍቶ ለመግባትና ባልታወቀ የአሟሟት ሁኔታ ለመሞት ስላልደፈረ በጠመንጃ መሞትን መርጦ ተገደለ። ከንጉሱና ከንግስቷ በስተቀርም ሁሉም አዳራሹን ለቆ ሄደ። ንግስቷም ከጥቁሩ በር ጀርባ ስላለው የመግደያ አይነት ንጉሱን አጥብቃ ጠየቀች።ንጉሱም እንዲህ አለ"ከጥንት ጀምሮ ጠመንጃውም በሩም አለ ግን አንድም ተቀጪ በሩን አልመረጠም።ሁሉም የማያውቁትን ለማወቅ አልደፈሩም።ነይ ላሳይሽ"ይልና በሩን ከፈተ።ከበሩ በስተያ ልምላሜ ያለው ተራራ እንጂ ምንም አልነበረም።
/ህያውነት 1
/osho/ኦሾ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


" ......ተገቢውን ፍርድ ለመስጠት የምትሹ እናንተ ዳኞች ሆይ ...በስጋው ታማኝ ቢሆንም በመንፈስ ሌባ ለሆነ ሰው ምን ፍርድ ትሰጡታላችሁ ?......በስጋው ለሚያርድ በመንፈሱ ግን እርሱ ራሱ ለታረደውስ ምን ቅጣት ትጥሉበታላችሁ ?......እናስ በተግባር አታላይና ጨቋኝ ቢሆንም እርሱ ራሱ የተጨቆነውን የተዋረደውንስ እንደምን ትዳኙታላችሁ ?.....ገና ሳይፈረድባቸው ፀፀታቸው ከመጥፎ ድርጊታቸው በእጅጉ በልጦ የተገኘውንስ እንዴት አድርጋችሁ ነው ቅጣት የምትጥሉባቸው ?.......በአግባቡ እያገለገላችሁት የምትገኙት ያ ህግ በራሱ የሚሰጠው ፍትሀዊ ብይንስ ፀፀት አይደለምን ? እንደዚያም ሆኖ በንፁሃን ላይ ፀፀት ልታሳድሩ ወይም ከጥፋተኞች ልብ ላይ ፀፀት ነቅላችሁ ልታወጡ አይቻላችሁም ። ...." ገፅ ( 38 / 39 )

".....ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሐይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት ....በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ፣ አንፀባራቂ ድል አድራጊዎችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት ..... መሪው ቀበሮ ፈላስፋው ቀጣፊ ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት ..... አዋቂዎቿ በእድሜ መግፋት ዲዳ ለሆኑባት ፣ ብርቱ ልጆችዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት ..... ግዛቷ ለተበጣጠሰባትና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት ..... ገፅ ( 153 )
የጠቢባን መንገድ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


#የምስራቃውያን_ተረት

አንድ ኃያል ንጉስ ከአስፈሪ የሞት ፅልመት ጋር ተገናኘ። ለቀናትም ከፊቱ የተደቀነው የሞት ጥላ እንቅልፍ ነሳው። "ማነህ አንተ? ምንስ ትፈልጋለህ?" ሲል ጠየቀው በድንጋጤ። ጥቁሩ የጥላ ምስልም "እኔም ሞትህ ነኝ። የመጣሁትም በትክክለኛው ስዓት እና ስፍራ እንዳገኝህ ላስታውስህ ነው።" አለው። ከንጉሡ ፊት ከመሰወሩ በፊትም "ነገ በትክክለኛው ስፍራና ስዓት እንገናኝ " ብሎት ሄደ።


በማስጠንቀቂያው የተደናገጠው ንጉሥ፤ ጠቢባን አማካሪዎቹን፣ ኮከብ ቆጣሪዎችን፣ ህልም ፈቺና ጠንቋዮችን አስጠርቶ የህልሙን ምንነት እንዲያስረዱት ጠየቀ።

ጠቢባኑ በንጉሡ እልፍኝ ተሰብስበው መከራከር ጀመሩ። ንጉሱን ከህፃንነቱ ጀምሮ የሚያውቁት አንድ አዋቂ ወደ ጆሮው ተጠግተው እንዲህ ሲሉ መከሩት፦ "የጊዜህን አታባክን የነዚህ ጠቢባን ክርክር አያልቅም። ቀኑ ያልቅና በነጋው ዕለት ይተካል። ስለዚህ ፈጣኑን ፈረስ ጫንና ከዚህ ስፍራ አምልጥ!"

ንጉሱም ፈጣኑን ፈረስ እየጋለበ ህልሙን ካየበት ቤተ መንግሥቱ ራቀ። ከከተማዋ ብዙ ርቀት ጋልቦ ቆመና "ሞት እዚህ ድረስ ሊመጣብኝ አይችልም በትክክለኛው ሥፍራና ሰዓት አልገኝለትም" አለ።

ፀሀይ ለማጥለቅ ስትቃረብ ፈረሱን አሳርፎ ምግብ ሰጠው። በፈረሱ ፈጣንነትና ከሞት መራቁ ተደስቶ ሳር ላይ ሲቀመጥ ትከሻውን አንድ ነገር ዳበሰው። ዞሮ ሲመለከት የሞት ጥላው ከኋላ ቆሞ በፈገግታ ያየው ነበር። "ምን ያስቅሃል?" ሲል የተደናገጠው ንጉሥ ጠየቀው።
ሞትም "የቀጠሮአችን ጊዜና ቦታ ይህ ነው። በቶሎ አትደርስም ብዬ ሰግቼ ነበር። ሆኖም ግን ለፈረስህ ምስጋና ይግባውና አልዘገየህም" ሲል መለሰለት።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


•ንጉሱ በጣም ብርዳማ በሆነው ሌሊት ወደ ቤተመንግስቱ ሲገባ ስስ የሆነ ልብስ የለበሱ አንድ በእድሜ የገፉ የቤተመንግስቱን ጥበቃ ተመለከተ
.
ወደ እሳቸውም ተጠጋና አይበርዶትም? አላቸው
.
ሰውዬውም፦ይበርደኛል እንጂ ነገር ግን ብርድን የሚከላከል ልብስ የለኝም! አለ
.
ንጉሱ፦ወደ ህንጻው ከገባ በኋላ ከጠንካራው እና ብርድን የሚከላከል ከሱፍ የተሰራ ልብስ እንዲያመጣላቸው አንዱን አገልጋይ
ያዘዋል።
.
ጥበቃው፦በንጉሱ ቃል በጣም ተደሰቱ። ነገር ግን የንጉሱ አገልጋይ ረስቶት ሊያመጣላቸው አልቻለም።
.
ሌሊቱ ሲነጋ ግን ንጉሱ ከቤተመንግስቱ ሲወጣ ሰውዬው ሞተው ያያል።
.
አንድ ብጣሽ ወረቀትም በእጃቸው ይዘው ነበር ንጉሱን ወረቀቱም ማንበብ ጀመረ።
.
ደብዳቤውም እንዲህ ይላል
.
"ብርዳማ ሌሊቶችን መቋቋም እችል ነበር ነገር ግን ለኔ ብርድ የሚከላከል ልብስ #ቃል መግባትህ ሀይሌን ነጠቀኝ"
.
~~~~~~~ ~~~
ቃል የምትገባላቸው ሰዎች ቃልህን ከምታስበው በላይ ቦታ ሊሰጡት
ይችላሉና እናስታውስ ቃላችንን አንጠፍ።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


#የትኛውም እንሰሳ የተራክቦ ስሜቱን የሚወጣው የሴቷን ሽንት አሽትቶና እርጉዝ አለመሆኗን አረጋግጦ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ወቅትና የሴቷን ፈቃደኝነት ተከትሎ ነው።
#የሰው ልጅ ግን ስግብግብ በመሆኑ ያለ ሴቷ ፍቃድና አስገድዶ ደፋሪ ሆኖ ከእንሰሳ በታች የዘቀጠ የስብዕና ኖሮት አለማፈሩ አስገራሚ ፍጡር ያደርገዋል ።
ኦሾ/Osho

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


አለማችን ላይ ያሉ ሀገሮች ሁለት አይነት ሀብት አላቸው! የጭንቅላትና የመሬት
አፍሪካውያን የመሬቱ ተባርኮላቸዉ ጭንቅላት ላይ ግን ችግር አለ። እነ ጃፓን
ደግሞ መሬቱ በየአመቱ በሱናሚ የሚናወጥ ሀገር ነው። ነገር ግን ሱናሚ
የጃፓንን ህንፃዎች እንጂ የጃፓንን ጭንቅላት ማፍረስ አይችልም። ጃፓን ለኮንጎ
ዛዬር እርዳታ ትልካለች የሁለቱን ሀገር የተፈጥሮ ሀብት ልዩነት ካዬነዉ ልዩነቱ
የተአምር ያህል ነው። ዛዬር ነበረች እርዳታ መላክ የነበረባት ግን መሬቱ ተባርኮ
ጭንቅላት ስለጠፋ አስር ኩንታል ጤፍ እቤት ዉስጥ ቢኖር አስፈጭቶ ካልተበላ
ከርሃብ ማምለጥ አይቻልም። ስለዚህ አስተሳሰብ ላይ ትልቅ ስራ መስራት ይገባናል። ለዚህም ደግሞ ትልቁ መንገድ ማንበብ ነው። ያላነበበ ጭንቅላት ጥሩ ሀሳብና ጠቃሚ ነገር ማመንጨት አይችልም! የዘወትር ስራው አሲድ ማመንጨት ነው ስለዚህ እናንብብ! እናንብብ! እናንብብ!

#መጋቢ _ሀዲስ_እሸቱ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


💥ከተከማቸ እውቀት ይልቅ አንዲት ጠብታ ምናብ ምሉነትህን ትቀይራለች።
የምትጨብጠው ሰመመን ነው።የምትለብሰው ጥበብ ነው።
የህይወት መንገድ የሚጠፋብህ የምናብ ኦና ስትሆን ነው።
አንተነትህ ጠፍቶብህ የምትማስነው ምናብህ ሲደህይ ነው።
በሰዎች ፀጋ የምትቀናው ማለምህ ሲመክን ነው።
ምናብ ውስጥ ሁሌም ንጋት አለ።አዲስ ለውጥ አለ።
አዲስ መንገድ አለ። ከተከማቸ እውቀት ይልቅ አንዲት ጠብታ ምናብ ምሉነትህን ትቀይራለች።
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፨፨፨፨፨፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ደራሲ፦መሀመድ አሊ/ ብርሀን አዲስ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

07 Oct, 13:12


#ከህይወቴ ተምሬያለው
💥. አንዳንድ ሰው እንዲያፈቅራችሁ ማድረግ እንደማይቻል ተምሬያለሁ ፤ ማድረግ የሚቻለው ጥሩ አፍቃሪ መሆን ብቻ ነው ።

💥.ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን ተሞክሮዎች ዓይነትና ከተሞክሮዎቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጅ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምሬያለሁ ።

💥.እንዳንዴ የቱንም ያህል ለሌሎች ብጨነቅ እና ግድ ብሰጥ አንዳንዴ አንዳንዶች በመልሱ ግድ ላይሰጡ እንደሚችሉ ተምሬያለሁ ።

💥.ጓደኞች ምንም ያህል ጥሩ ቢሆን አልፎ አልፎ ማስቀየማቸው እንደማይቀር ተምሬያለሁ ። ባስቀየምናቸው ሰዎች ይቅር መባል በቂ ያለመሆኑንና ራስንም ይቅር ማለትም እንደሚያስፈልግ ተምርያለሁ ።

💥.መታመንን ለመግንባት ዘመናት እንደሚያስፈልግ ፤ ለማውደም ግን ሰከንዶች ብቻ እንደሚበቁ ተምሬያለሁ ።

💥.አንዳንድ ጊዜ ተንሸራትተህ ስትወድቅ ይረጋግጡኛል ብለህ የምትጠብቃቸውና የምትፈራቸው ሰዎች ብድግ አድርግው በማንሳት እንደሚያስገርሙህ ተምሬያለሁ ።

💥.እውነተኛ ጓደኝነት እንደዚህም እውነተኛ ፍቅር በቦታ ርቀት ሳይግደብ ማበብ መፍካቱ እንደማይቆም ተምሬያለሁ ።

💥.በአስተዋይነት "እምቢ" ማለት ሁልጊዜም የንፉግነት ምልክት ያለመሆኑን “እሺ” ማለትም ሁልጊዜ ምግባረ ሰናይነትን እንደማያሳይ ተገንዝቢያለሁ ።

💥.ራስን ከጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ከጥላቻ የምንገላገልበት ብቸኛ መንገድም የአለፈውን ጊዜ ረስተን ከአሁን ጋር እርቅ ማድረግ ስንጀምር እንደሆነ ተምርያለው ።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

06 Oct, 14:34


🌜በሌሎች ላይ እየፈረድን እኛ ግን ያንኑ መልሠን እናደርጋለን፡፡በሀሳባቸዉ ፣ በእምነታቸው ፣በድርጊታቸዉ ወዘተ ላይ እየፈረድን መልካም እና በጎ ፣ ብርሃን እና ጨለማ በማለት እንፈርጅዋለን፡፡ አስቀድማችሁ ከራሳቸሁ ጋር አንድነት ፍጠሩ። በጨለማ እና በብርሃን ፤ በህይወት እና በሞት መካከል መስማማትን አምጡ፡፡ ያን ጊዜ ዉስጣችሁ አንድ ይሆናል። የሰዉ ልጀ ግን እንኳን አንዱን ከሌላው ጋር ቀርቶ ከራሱም በውስጡ አንድነት የሌለው እና ዘወትር ሲናወጥ እና ሲከፋፈል የሚዉል ፍጡር ነው።🌛
#ኦሾ/Osho

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

06 Oct, 14:34


አንድ ጊዜ ታላቁ ሸህ ኢብን ዐረቢ ወደ ደማስቆ ተራራ ይወጣና ማስተማር ይጀምራል፡፡ በመሃል "ሰዎች ሆይ! የምታመልኩት ጌታ ከእግሬ ሥር ይገኛል" አላቸው፡፡ ሰዎቹ በጣም ከመናደዳቸው የተነሳ አሰሩት፤ ሊገድሉትም ዝግጁ ሆኑ፡፡
ኢብን ዐረቢ ሥራዎቹ ጥቃት የተቀላቀሉበት ውዝግቦችን ከማስነሳታቸው የተነሳ ከሞተ በኀላ የተቀበረበት እንዳይገኝ ሃውልቱን ሁሉ አፈራርሰው ድራሹን አጠፉት፡፡
ታዲያ ኢብን ዐረቢ የሚታወቅባቸው በርካታ ንግግሮች አሉት፡፡ አንደኛው "ሲን ሺን ሲገባ ቀብሬ ይገኛል" የሚለው ዋናው ነው፡፡
ኢብን ዐረቢ ከሞተ ወደ ሶስት መቶ ዓመታት ሊሞላው ሲል ዘጠነኛው የዑስማንያ ኸሊፋ ሰሊም ሁለተኛው ደማስቆን 1516 ይማርካል፡፡ ሰሊም ከላይ የተጠቀሰውን የኢብን ዐረቢ ንግግር በወቅቱ ከነበረው ዓሊም ዘምቢሊ ዓሊ ኢፈንዲ ከነትንቢቱ ይሰማል፡፡ ሸኽ ዘምቢሊም የትንቢቱን ፍቺ ይነግሩታል- ሲን ማለት ሰሊም ወደ ሺን ማለት ሻም ሲገባ የሙሂይዲን ሐውልት ይሠራል።
ታዲያ ሰሊም ከከተማዋ የነገረ መለኮት ዓሊሞች ኢብን ዐረቢ "የምታመልኩት ጌታችሁ ከእግሬ ሥር ይገኛል" ብሎ የተናገረበትን ቦታ ጠይቆ ከተረዳ በኀላ ማስቆፈር ይጀምራል፡፡ የወርቅ ሳንቲሞች ክምር ያገኛል፡፡ ፃድቁ ኢብን ዐረቢ ምን ለማለት እንደፈለገ ይገልፃል፡፡ የወርቅ ሳንቲሞቹ ከተገኙበት ቦታ ብዙም ሳይርቅ የተቀበረበትን ቦታ ያገኘዋል፡፡ ሰሊም በተገኘው ወርቅ በቦታው ላይ መስጊድ እና የኢብን ዐረቢን ሐውልት ያሠራል፡፡
መስጊዱና ዶሪሁ አሁንም በደማስቆ ይገኛል፡፡ ሳሊሂያ ይባላል፡፡ ቃሲዩን ከሚባለው ተራራ ተዳፋቱ ላይ ነው፡፡ አሁን በአገሪቷ እየተካሄደ ባለው የእርስ በእርስ ጦርነትም ጉዳት አልደረሰበትም፡፡
አላህ ሆይ! በታላቁ ሸኽ ይሁንብህ፤ እባክህን ወዳንተ አቃርበን!
ቀደሰላህ ሲረሁ

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

06 Oct, 14:34


ለሆዳቸው ሲሉ ሕሊናቸውን የጣሉ ትርፋቸው ምንድነው??
(እ.ብ.ይ.)

ወዳጆች ቅንነትን የሚያወድም፣ ደግነትን የሚያጠፋ፣ ፍቅርን አሽቀንጥሮ የሚጥል ልቡ በክፉ ሃሳብ የጠፋ ብቻ ነው፡፡ ብዙዎች በውስጣቸው ያለውን ቅንነት፣ በልባቸው የነበረውን ደግነት፣ በሕሊናቸው የኖረውን መልካምነት አሟጥጠው በመጨረስ ከሠውነት ጎዳና ይወጣሉ፡፡ ከትክክለኛው የሠውነት ምልክታቸው ያፈነግጣሉ፡፡ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ፣ ከደግነት ይልቅ ክፋት ዓይናቸውን ያውረዋል፡፡ ልባቸው በክፉ ሃሳብ ይጨልማል፡፡ በጨለማው ማንነታቸው ዓለሙን ይበይናሉ፡፡ በበየኑት ዓለም ውስጥ በድቅድቁ አመለካከታቸው ብቻ ነው የሚመላለሱት፡፡ ልቦናን መጣል፣ እውነትን ማርከስ፣ እምነትን ማጉደል ለነሱ ቀላል ይሆናል፡፡

ሠው ለእምነቱ፣ ለእውነቱ፣ ለሕሊናው መኖር ካልቻለ ታዲያ ለምን ሊኖር ነው?? ሠው በሆዱ፣ በቁስ ፍላጎቱ፣ በብልጭልጩ ዓለም እየታለለ እስከመቼ ይዘልቃል?? የሠውነት ውስጣዊ ዓለሙንስ የሚያረካው መቼ ነው?? የቱ ላይ ነው ሠውነቱ?? ለሆዳቸው ሲሉ አዕምሯቸውን የጣሉስ ትርፋቸው ምንድነው??

ታላቁ ቡድሃ ‹‹ምንም ዓይነት መርዝ ቀና አሳቢን አይገድለውም፡፡ ምንም ዓይነት ሕክምና ክፉ አሳቢን አያድነውም፡፡›› ይለናል፡፡

እውነት ነው! ክፉ ሃሳብን፣ ተንኮልን፣ ሌሎችን ማሳቀቅን፣ እኔ ብቻ ይድላኝ የሚል ስግብግበነትን፣ ሌሎች በየሜዳው ቢወድቁ እኔ ምን ተዳዬ የሚል ጨካኝ አመለካከትን ማከም መቻል እጅግ ከባድ ነው፡፡ በሽተኛው በሽታውንና ህመሙን ተረድቶ ለመፈወስ እስካልቆረጠ ድረስ ሊታከም የሚችል በሽታ አይሆንም፡፡

በዛው ልክ ደግሞ ቀና አስተሳሰብን የሚያወድም ምንም ዓይነት ሃይል የለም፡፡ ቀና አሳቢው ቢሞት እንኳን ቅንነቱን ሌሎች ላይ አጋብቶ ስለሚኖር በቅኖች ቅብብል ቀና አስተሳሰብ ዘላለም ይኖራል፡፡ ቀና አስተሳሰብ ባይኖር ክፉ ሃሳቦችን ለመመዘን አንችልም ነበርና፡፡

ኤሪክ ፎረም የተባለ ፀሐፊ You shall be as Gods በተባለ መፅሐፉ እንዲህ ይለናል፡-

‹‹ክፋት የሚመገብ አዕምሮ በክፋት ያድጋል፡፡ ደግነትም የሚመገብ እንዲሁ ይሆናል፡፡ የዕድገት ዋነኛ ምክንያት ግን የሠው ብቸኛ ችሎታ በሆነው ማሠብ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡›› ይለናል፡፡

እውነት ነው! ሠው ሆዱን ለሚመግበው እንደሚጠነቀቀው ሁሉ ለአዕምሮውም የሚመግበውን ሃሳቡን መፈተሸ አለበት፡፡ ያገኘውን ሁሉ አግበስብሶ የሚመገብ ከሆነ ጉዳቱ ለራሱ ነው፡፡ ቁንጣንም በሽታ ነው፤ በበቂ ሁኔታም አለመመገብ የምግብ እጥረት ነው፡፡ መጠን ግድ ይላል፡፡ መጠን እንወቅ ወዳጆች!

ለዚህም ነው ኤሪክ ፎረም፡- ‹‹የሠው ልጅ እጅግ ጨካኝም ሆነ እጅግ ደግ የሚያደርገው ዘወትር ሃሣቡን የሚመግበው ነገር እንጂ ሌላ የተለየ ምክንያት ኖሮት አይደለም፡፡›› በማለት ሠው ሃሳቡ ላይ ብዙ መስራት እንዳለበትና ሚዛን የሚደፋ ሃሳብ ተመግቦ እንዲያመርት ነው ፀሐፊው የሚመክረው፡፡

አንዳንድ ሠው ደግሞ ራሱን ለክፋት አስተሳሰብ እያጋለጠና በፍቃዱ ጨካኝ ሃሳብ በአዕምሮው እየሞላ ይሄን ያደረግኩት ሠይጣን አታሎኝ ነው እያለ ራሱን ያሞኛል፡፡ ራሱ ለፈጠረው ስህተት ከመናዘዝ ይልቅ ሠበብን ፍለጋ ይዳክራል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሠው ለሠራው በጎ ነገር ዕውቅናን ለማግኘት ደፋ ቀና ቢልም፤ ለሠራቸው ስህተቶች ደግሞ ሃላፊነትን መውሰድ አይሻም፡፡ ሌሎች ላይ ማላከክ፣ ሠበብ መፈለግ፣ የእምዬን ወደአብዬ ማድረግ ከስህተቱ ለመታረም ያለመቻላችን ውጤት ነው፡፡

አንድ የሱፊ ተረክ አለ፡፡ በኢራን አቡል ቢስታሚ የተባሉ በእምነታቸው ፅኑ እና የታወቁ ሱፊ ነበሩ፡፡ አንድ ቀን ምሽት ከደቀመዛሙርቶቻቸው ጋር ተቀምጠው ሲያወጉ የእምነት ጉዳይ ተነሣ፡፡ ደቀመዛሙርቱ ተራ በተራ የእምነታቸውን መላላትና ብሎም መጥፋት ከነገሯቸው በኋላ ለዚህም ምክንያቱ ሠይጣን እንደሆነ አስረግጠው አስረዷቸው፡፡

በዘመኑ ተዓምራትን ማድረግ ይችሉ ነበር የሚባልላቸው አቡል ቢስታሚ የደቀመዛሙርቱን ስሞታ ካዳመጡ በኋላ ሠይጣንን ጠርተው ጠየቁት፡-

‹‹እውን የደቀመዛሙርቶቼን እምነት ሠርቀሃል?›› አሉት፡፡ ሠይጣንም መለሠ፡- ‹‹እኔ የማንንም እምነት ለመስረቅ የሚያስችል ሃይል የለኝም፡፡ ምክንያቱም የሚያምኑት አምላክ ከእኔ የላቀና እጅግም ከፍ ያለ ሃይል ያለው ነውና፡፡ ነገር ግን ብዙዎች በየጥቃቅኑ ምክንያት እምነታቸውን በየመንገዱ እየጣሉ ሲሄዱ አግኝቼ በመሠብሠብ ከእኔ ዘንድ ያስቀመጥኩትን እንደሠረቅሁ አድርገው እየዋሹ ነው፡፡›› በማለት መለሠ፡፡

አቡል ቢስታሚም ደቀመዛሙርቱን ከሠይጣን ጋር ላኳቸውና እንዲህ አሉ፡-

‹‹እምነቱን የጣለ ታግሎ ያስመልስ፡፡ ሠይጣን ያለጥፋቱ ምን ባደረገ ይቀጣ?›› በማለት ወሠኑ፡፡ እስከዛሬ ደቀመዛሙርቱ ወደቢስታሚ አልተመለሱም ይባላል፡፡

ወዳጆች ምንድነው በዓለም ያለን ትርፍ?? ካነሳነው ይልቅ የጣልነው አይበልጥም?? ምንድነው የዕድሜአችን ዓላማ?? በዕድሜአችን ውስጣችንን ካስደሰትንበት ይልቅ የተከፋንበት አይበልጥም?? የምንኖረው ለመብላት ብቻ ነውን?? የሐገርን ሃብት ለብቻ በጉልበትና በተንኮል እየመዘበሩ መኖር ጥቅሙስ፣ ሠበቡስ፣ ትርፉስ፣ ውጤቱስ ምንድነው?? የተለየ ግቡ ምንድነው?? ሕሊናን፣ ልቦናን፣ ነፍስያን፣ መንፈስን የሚያረካውና የሚያጠግበውን ፍላጎታችንን እንዴትስ ነው ልናረካው የምንችለው??

ለማንኛውም ለሆዳችን ብቻ ሳይሆን ለውስጣችንም፣ ለነፍሳችንም፣ ለህሊናችንም፣ ለልባችንም እኩል በእኩል እንኑር የዛሬው መልዕክት ነው!

ቸር ጊዜ!

__________________
(እ.ብ.ይ.)

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

06 Oct, 14:34


ፈጣሪ እኛ እንጎበኛዋለን እንጂ እሱ አይጎበኘንም

እንድ የበቁ የዜን አባት አንድ ወጣት መጥቶ " ወደ ዜን መግቢያው በር በየት ነው ? " ብሎ ጠየቃቸው ። እሳቸው ግን መልስ ከመሰጠት በአርምሞ አለፉት። ልጁ በድጋሚ ጠየቃቸው ። አባ በዛን ሰአት እንዲህ ብለው ለወጣቱ ጥያቄን በጥያቄ መለሱለት ...
" ምንጩ ይሰማኸል ? "
ወጣቱ " የምን ምንጭ ? " ...ለደቂቃዎች የምንጩን ድምፅ ለማወቅ ትኩረት ሁሉ ወደእዚያው አደረገ ። የምንጩን ድምፅ ሲፈለግ በአእምሮ ሲንጡት የነበሩ ሀሳቦች ሁሉ እንደ ጠጅ አንቡላ ቀስበቀስ ወደ ታች መዝቀጥ ጀመሩ። ከዛም ከወዲያ ማዶ ካለ ተራራ ስር ያለቸው ምንጭ ስትፈስ አዳመጣት ።
"አባ...ምንጩን ሰማሁት " አለ ወጣቱ
"የዜን መግቢያው እሱ ነው አሉት"
በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በዙሪያው ያለውን ህይወት ተረዳ ። አበቦች ፣ መስኩ ፣ ተራራዎች ፣ ወንዙ ፣ የአእዋፍ ዝማሬ ሁሉ ነገር እንደ አዲስ ነገር ተገነዘባቸው ። በህይወቱ ተሰምቶት የማያውቅ ሰሜት ተሰማው። ነፈሱ ረጋች። ብዙም ሳይቆይ ሀሳቦቹ አንሰራርተው አእምሮ በሀሳብ ተሞላ ። ነገሮች ወደ ነበሩት ተመለሱ ።
ፈጣሪ በፈጠረው ነገር ሁሉ ወስጥ ይኖራል ። የምንተነፍሰው አየር ፣ የምንጠጣው ውሀ ፣ የምንበላው ምግብ የምንኖርበት አከባቢ...በኛም ውስጥ ይኖራል ....ልብ ምታችን...ደም ዝውውር ...የተመጠኑ ሆሮሞኖች ወዘተ። ፍጥረት አንድ ትልቅ ኦኬስትራ ባንድ ትመስላለች ሳሩ ደኑ ቅጠሉ አእዋፋት አራዋት ጨረቃና ፀሀይ በአንድ ስልተ- ምት ይፈሳሉ ። የሰው ልጅ የገዛ አእምሮ ሳንካ ሆኖበት ሌላ ስልተ - ምት ይፈልጋል ። ዝና ፣ ገንዘብ ፣ ስልጣን ውስጥ እራሱን ለማግኘት ይሞክራል ። ለምሳሌ ሱናሚ በተከሰተ ጊዜ ገና ከመምጣቱ በፊት እንስሳት ሁሉ የመጣውን አደጋ ተረድተው ወደ ከፍታ ቦታ አሰቀድመው ሸሽተው ነበር። የሰው ልጅ ግን ከተፈጥሮ ስልተ-ምት ወጪ በመሆኑ 150000 የሚሆኑት ዝርያዎቹ ጠፍተዋል ። የፈጠሪና የተፈጥሮ አንድ አካል ነን...ፈጣሪ ሁሉ ነገር ውስጥ ካለ ...ሁሉም ቦታ ካለ....ልክ እንደ ወጣቱ ብርሀነ ህሊናችንን ሳንጠቀምበት ቀርተን ፤ ከስልተ - ምት ወጥተን ሳናስተውለው ቀረን እንጂ እሱ እኮ ሁሌም አለ።

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

06 Oct, 14:34


የስሜት ጭቆና ምንድ ነው ?
🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡
"የስሜት ጭቆና መኖር የሌለባችሁን ህይወት መኖር ማለት ነው። የስሜት ጭቆና ማለት ፈጸሞ የማትፈልጓቸውን ነገሮች ማድረግ ማለት ነው። የስሜት ጭቆና ራስን የማወደሚያ መንገድ ነው። የስሜት ጭቆና ራስን ማጥፋት ነው። በርግጥ ራስ መሠጥፉቱ በጣም የዘገየ ነው። ግንበጣም እርግጠኛ የሆነ ምረዛ ነው።
....ስሜትን መግለጽ ህይወት ሲሆን ስሜትን መጨቆን ደግሞ ራስን የማጥፋ!ት ያህል ነው።"
🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡
#ነፃ ስሜቶች# ገጽ 58
#ኦሾ/Osho
#ትርጉም በዮሐንስ አዳም

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

06 Oct, 14:34


ሕፃናት ዘንድ የፈጣሪ ቁጣ ; ፍርሃት ; ቅጣት ... የሚባል ነገር የለም። ለእነሱ ህይወት በራሷ ምሉዕ እና ትርጓሜም ሆነ መሻት የተሸከመች ባለመሆኗ ፈጣሪን ያለምንም ፍርሃትም ሆነ ጥያቄ ይቀርቡታል።
ታዋቂው የአሜሪካ የመፅሐፍ ቅዱስ ሰባኪ ቢሊ ግርሃም አንድ ቀን ወደ አንዲት ትንሽ የገጠር ከተማ ለስብከት አገልግሎት ይሄዳሉ ። በከተማዋ ደርሰው የአገልግሎት ሰዓታቸው እስኪደርስ ደብዳቤ ለመላክ ፖስታ ቤት ፍለጋ በጎዳና ላይ መዘዋወር ይጀምራሉ። ይሁንና የፖስታ ቤቱ አድራሻ በቀላሉ የሚገኝ አልሆነም።ዶ/ር ቢሊ ግርሃም በዚህ መካከል አንድ የስምንት ዓመት ህፃን በመንገድ ዳር ለብቻው ሲጫወት ይመለከቱትና ወደ እሱ በመሄድ "የኔ ልጅ ስምህ ማነው?" ይሉታል።

ልጁም " ጆን እባላለሁ " ይላል።

" ጆን እባክህ የፖስታ ቤቱ አድራሽ ጠፍቶኝ ተቸግሬያለው። የከተማዋ ፖስታ ቤት የት እንደሆነ ታውቃለህ?" በማለት ይጠይቁታል። ጆንም ቀኝ እጁን ከፊት ለፊቱ በተዘረጋው መንገድ ላይ እየጠቆመ ለዶ/ር ቢሊ ግርሃም የፖስታ ቤቱን አዳራሽ አሳያቸው።

ዶ/ር ቢሊ ግርሃም በዚህ ግዜ ልጁን አመስግነው "ማታ ጎስፔል ባኘቲስት ቤተክርስቲያን በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ሰዎች እንዴት መንግስት ሰማያት መግባት እንደሚችሉ መንገዱን አስተመራለሁና ከቻልክ ከወላጆችህ ጋር እንድትመጣ።" በማለት ይጋብዙታል።

ሕፃኑ ልጅ ግን በማቅማማት ፍላጎትም እንደሌለው አንገቱን በመነቅነቅ እየገለፀ "የምመጣ እንኳን አይመስለኝም " አላቸው።

በጆን ምላሽ የተገረሙት ዶ/ር ቢልግርሃም ለምን መምጣት እንዳልፈለገ ሲጠይቁት ጆን:- " የፖስታ ቤቱን መንገድ የማታውቅ ሰው እንዴት ብለህ ነው የመንግስተ ሰማይን መንገድ የምታሳየኝ ?" በማለት ማጫወቻዎቹን ይዞ ሮጠ።

#ጥበብ ከጺላጦስ
(ኅይለጊዮርጊስ ማሞ) ቅፅ 2

ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች

06 Oct, 14:34


ፖለቲከኛ የስነልቦናና የመንፈስ ታማሚ ነው። በአብዛኛው ፖለቲከኞች ጤናማ ተክለ ቁመና ይኖራቸዋል። አካላቸው እንከን አልባ ሲሆን ዋናው ሸክም የሚያርፍበት አእምሮአቸው ግን ህመምተኛ ነው። አእምሮአዊ ህመማቸው ሲበዛ ደሞ የመንፈስ ታማሚ ይሆናሉ። የህመሙ አይነት የዝቅተኝነት ( የበታችነት) ስሜት ወይም Inferiority complex የሚባለው አይነት ነው።

የስልጣን ጥማት ያለበት ማንም ሰው የበታችበት ስሜት ተጠቂ ነው። በውስጡ የሚሰማው ዋጋ ቢስነትና ከሌሎች ማነስ ብቻ ይሆናል። በተለያዩ መንገዶች ከሌሎች እናንሳለን። ይህ ማለት ግን የበታችነት ስሜት ሊሰማን የግድ ነው ማለት አይደለም። ፖለቲካኛ ግን የበታችነት ደዌ ተጠቂ ነው። ራሱን ምጡቅ ከሆኑ የሰው ልጆች ጋር ሊያነጻጽር መሞከሩ የበታችነት እንዲሰማው ያደርገዋል። ራሳችሁን ከአንስታይንና ሲግመንድ ፍሩድ ጋር የምታፎካክሩ ከሆነ ዋጋ ቢስነትና ትንሽነት ሊሰማችሁ ይችላል።
ይህ የዋጋቢስነት ስሜት በሁለት መንገዶች ይወገዳል። አንዱ ሀይማኖት ሲሆን ሌላው ደግሞ ፖለቲካ ነው።
ፖለቲካ ይህን ደዌ ይደብቀዋል እንጂ አያጠፋውም። የህመሙ ተጠቂ በዚህ የበታችነት ስሜት የሚሰቃየው ሰው ፕሬዚዳንት ሊሆን ይችላል። የመሪነትን ወንበር መያዝ በውስጣዊ ማንነታችሁ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?
ኦሾ/osho