ከፍልስፍናው ጎራ <<❓>> @phylosophy_gora Channel on Telegram

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

@phylosophy_gora


<<ደስታን ምን እንደሚያካትት መፈለግህን ከቀጠልክ ፈጽሞ ደስተኛ አትሆንም..! የሕይወትን ትርጉም እየፈለግህ ከሆነ ፈጽሞ ሕይወትህን አትኖርም..! >>

አልበርት ካሙ

ለማስታወቂያ ሥራ➝ @Naolviva

ከፍልስፍናው ጎራ <<❓>> (Amharic)

ከፍልስፍናው ጎራ የሰላምን አገልግሎት ለማስታወቂያ ሥራ፣ በቀጠልክ የጎራው ዜናዎችን ለመነሻ እና ለመቀጠለያ ወደ ታላቁ የጎራ ቴሌግራም እሱህ ከናውላቅ መሲብ ጋር እንዲያነካን እና ፍቱዎቹን ፈቀቅ ለማስረዳት ነው። እንዴት ለማስታወቂያ ሥራ እንደሚዘወት ከፍልስፍናው ጎራ ምናልባት ማን ነው? ከፍልስፍናው ጎራ እንዴት ማለፍን እንደሚመለከተው መፈለግ እና መመለስ ለመቀጠል በፈጠሙ ምኞታዎች ላይ ፈጽሞ ደስተኛ አብረው አግኝቷል። እናልተኛውም ሕይወትህን ከሚክተለው ፈጽሞ ሕይወትህን አትኖርም እንደሚላትን ለምንድን ነውድ በመሆን ነው። እስከ መቼም ይህን አስተዋውቂ ባህል ላይ ሦስተኛኑን ጀንቲክ እና ቡድኑን ለመመለስ እሱህ ለማከማቻ የጎራው ቴሌግራሙን በእንግሊዝኛ ወደ ታላቁ ግምት ነው። እንደምትሉኝ፡ ከፍልስፍናው ጎራ ልዩነትን ለማንበብ ከፍልስፍናው ጎራ ጋር እንደሚገኙ ለምን እነሱን የሚመጣ ተፈጥሮ ለብቃት ሊኖራቸው ነው።

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

07 Jan, 04:31


በከብቶች በረት ውስጥ በዚያ በተናቀው
ተወልዶ ብናየው ልባችን🫀 ደነቀው 😇

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

01 Jan, 20:53


የስልክ ቁጥሮን የመጨረሻ ቁጥር በመምረጥ እድሎን ይሞክሩ 🤩

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

01 Jan, 20:41


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

20 Dec, 19:01


"ፈጣሪ የት ነው..?"
       (ሩሚ)


የክርስቲያን መስቀል ላይ ልፈልገው ሞከርኩኝ ነገር ግን ከዛ የለም! የሒንዱስ ጥንታዊ ቤተ-መቅደስ ፓጎዳ ጎራ አልኩኝ ቢሆንም ዱካውን የትም ላገኘው አልቻልኩኝም!

ከተራራው እና ከሸለቆው አሰስኩት ግን በከፍታም፣ በዝቅታም ለማግኘት አልተቻለኝም! መካ ውስጥ ካዕባም ተጓዝኩኝ በተመሳሳይ እዛም ቢሆን የለም!

ጠበብቶች እና ፈላስፎችን ጠየኩኝ ዳሩ ግን እሱ (ፈጣሪ) ከመረዳታቸው በላይ ነው!

በመጨረሻ ከልቤ ስፍራ ማተርኩኝ፣ ማረፊያውን ያፀናው እዛ ነው፤ አየሁትም! እናም ሊገኝ ሚችልበት ሌላ ቦታ የለም!



@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

20 Dec, 18:51


ወጣቱ ልጅ ታክሲ ውስጥ ቸኮሌት እየላጠ ይበላል። የመጀመርያውን ጨርሶ ሁለተኛውን ቸኮሌት ሊጀምር ሲል ከጎኑ የተቀመጠው ሰውዬ " ይህ ነገር ለጥርስህ ጥሩ አይደለም እንደሚጎዳው አታውቅም " በማለት ይጠይቀዋል ልጁም መለስ አርጎ "የአባቴ አባት ለ132 ዓመት ኖሯል " ይለዋል ሰውዬውም " ይህን ያህል የኖረው ቸኮሌት ስለበላ ነው " በማለት እያሾፈ ጠየቀው ወጣቱም ልጅም " አይደለም አያቴ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በማያገባው አይገባም ነበር " በማለት መለሰለት። 😊


             
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

20 Dec, 18:25


ይህን በደንብ እወቁ !!

"ስራ ከፈታ አይምሮ፤ ከማያነብ አይምሮ በምንም ነገር ምንም እንዳጠብቁ ምክንያቱም ከነገር ውጪ ምንም አያቅምና መልካም ነገር እንኳን ብታሰያው የሚታየው ክፉ ነገር ለምን ብትሉ!? አያነብም ሲቀጥል አይሰራም። ሁሌም አንድ ነገር ማወቅ ያለባችሁ የማይሰራ አይምሮ አይሳሳትም፤ የሚሰራ አይምሮ ደሞ ቢሳሳትም ማስተካከል ይችላል"።

"ያላነበበ ጭንቅላትና ጨጓራ አንድ ናቸው። ሁለቱም ባዶ ሲሆኑ አሲድ ያመነጫሉ።"

🗣 መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

06 Dec, 10:13


የቴሌግራም ቻናል እንዲሁም ግሩፖችን መግዛት የምትፈልጉ በዚህ User አዋሩኝ @MIKEY12M

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

05 Dec, 21:11


ጎልልልልልልልልል ክርስትያኖኖኖኖኖ

ሮናልዶ በሳውዲ ሊግ ላይ ተገልብጦ ያስቆጠራትን ድንቅ ጎል ይመልከቱ 👇👇

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

28 Nov, 18:05


ጥያቄ፦ ውልብታ ላይ ያሉት አጭር ታሪኮች አላጠሩም?
መልስ፦ አጭር ሰው አላለቀም ይባላል ወይ?! ልክ እንደ እንጎቻና እንጀራ አስቡት። እንጎቻውም እንጎቻ ነው። እንጀራውም እንጀራ ነው። እንጎቻው አነሰ አይባልም። ወይም እንጎቻውን እንጀራ ለማድረግ አንሞክርም


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

21 Nov, 17:36


ገጣጣ ነች። ስትስቅ አፏን ከፍታ ነው ። አሳሳቋን ከማንም ጋ ብትሆን አትቀይረውም ።
ስንት ቀን እኔ ባለሁበት የሚያምር ጥርስ አይታ ስታደንቅ አይቻታለሁ ።

የሌለውን ያላጣጣለ እሱ ትልቅ ሰው ነው።

ፎቶ ላይ ገጣጣነቷን ለመደበቅ ጥረት ስታደርግ አይቻት አላቅም ። እራስን የመሆን እና ራስን የማወቅ ጥግ እራስን መቀበል ነው።

አንድ እለት ሆን ብዬ ግንባሯ ላይ ፍንክት ስላለባት እና በሻሽ በሻርፕ ስለምትደብቀው ልጅ ነገርኳት

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እንዲቀበሉን እኛ ቀድመን እራሳችን መቀበል አለብን አለች።

ደካማ ሰው ነው ድክመት ላይ የሚመሰጠው። በራሱ የማይተማመን እንከኑ የሚያሳቅቀው ነው ጉድለት የሚያስሰው ።

የማይለወጥ ነገርን መቀበል ከራስ ጋ ያዋህዳል። ያየነውን መልካም ጥሩ ነገር በትክክለኛው ሰዓት ማንፀባረቅ በራስ መተማመን ይባላል። በራሳቸው የማይተማመኑ ሰው ማሳነስ ላይ ሲረማመዱ የሚውሉ ናቸው አለቺኝ ።

በራሳቸው የማይተማመኑ ድኩማኖች አላግጠው አሸማቀዋት ነው እራሷን ያልተቀበለችው። አስተዳደጓ ላይ ራስን ስለመሆን ራስን ስለማወቅ እና ራስን
ስለማሸነፍ ማንም ስላላሰረፀባት ነው ።

ማንም በጀርባዬ ስለገጣጣነቴ ሲንሾካሾክ ባይ ውስጤ አይታወክም ድብርት አያንጠኝም ምክንያቱም ራሴን ተቀብዬዋለሁ ። ድሃን ድሃ ስትለው ከተንጨረጨረ ድህነቱን እንዳይቀበል ትምህክተኝነቱ ጋርዶታል ማለት ነው

መስተወት ላይ ስቆም ጥርሴን ስድብቅ ምን እንደምመስል በከንፈሬ እየደበቅኩ ለማየት አልጥርም።

በአደጋ፤ በበሽታ፤ በእድሜ መግፋት አካል እንደሚዛነፍ እንደሚጎድል እንደሚበላሽ አውቀዋለሁ ።

እንደዚህ እያልኩ ግን ተፅናንቼ አላውቅም መፅናናት አማራጭ የማጣት መንገድ ነው።

ተፅናንተ አለባብሰህ ራስህን አሞኝተክ የተውከው ነገር ባስታወሱክ ባስታወስከው ቁጥር ምቾት አይሰጥህም ።

ዘለቄታዊ መፍትሄ ራስን መቀበል ነው። አስተዋፆ ባላበረከትኩበት ነገር ስለምን እመሰጣለሁ አለቺኝ ስታወራኝ ስሜታዊነት መውረግረግ ምናምን የለባትም ።

እውቀት ነፃ እንደሚያወጣ አየሁኝ !


Adhanom Mitiku

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

16 Nov, 10:18


ማይክ ታይሰን ለእኔ ቦክሰኛ አይደለም!
(አሌክስ አብርሃም)

ከህይወት ቡጢ ለማምለጥ ሲሮጥ ያቀረቡለት የቦክስ ጓንት ውስጥ የወደቀ ሚስኪን ወፍ ነው። እንደብዙ ጥቁር አሜሪካዊያን ገና በልጅነቱ ብዙ መከራ ተቀብሏል። አባቱን በእርግኝነት አያውቅም ነበር። አንድ ጀማይካዊ የታክሲ ሹፌር ነው ይባላል።ይሁንና እሱ አባቴ ብሎ የሚያስበው /የተነገረው/ ሴቶችን ለሴተኛ አዳሪነት የሚያቀርብ ሰካራምና ዱርየ ሰው ነበር። ያም ሆነ ይህ ከንቱ ነበሩ። የሆነ ሁኖ የአባት ፍቅርም ይሁን ከለላ ሳይኖረው እናቱ ጋር መጠጥ አደንዛዥ እፅ ፣ወሲብና ወንጀል በተሞላ በዘግናኝ ሰፈር ውስጥ ለመኖር የተገደደ ሚስኪን ህፃን ነበር። የባሰው አሳዛኝ ነገር እናቱ በሴተኛ አዳሪነት ስራ የተሰማራች ሴት መሆኗሲሆን የምታሳድጋቸው በዚሁ ስራ ነበር። ማይክ እናቱ በመጠጥና ድራግ በናወዙ ሰካራሞች እናቱ ላይ ብዙ ግፍ ሲፈፀም አይቷል።

በቤተሰቤ እንደተሳቀኩ ነው የኖርኩት ይላል በሀዘን።ብዙዎቹ የተገፉ ህፃናት ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፣ ከሰው ያጡትን ፍቅር ከአሻንጉሊት፣ ከቤት እንስሳት ወይም በሃሳባቸው ከሚፈጥሩት ታሪክ ለማግኘት ይጥራሉ. . .ማይክ ታይሰን ርግብ ነበረችው የሚወዳት ! አንድ የሰፈር ጉልበተኛ እርግቡን ገደለበት . . .የማይክ ታይሰን የታፈነ ብሶት ለመጀመሪያ ጊዜ ቡጢ ሁኖ የተገለጠው እዚህ እድለቢስ ወጣት ላይ ነበር ይላሉ ታሪኩን የፃፉ! ከዛማ ምኑ ቅጡ ማይክ ከአንደበቱ ቡጢው የሚፈጥን የለየለት ተደባዳቢ የጎዳና ልጅ ሆነ። እስርቤትና ፖሊስ፣ ክስና መታሰር. . .!

በመሰረቱ ይሄ ባህሪው በዛ መንደር መሞቻው ነበር! ግን አንድ ጣሊያናዊ የቡጢ አሰልጣኝ ዓይን አረፈበት! የማይክን የጎዳና ቡጢ ከሞት ወደህይዎት፣ ከእስር ቤት ወደቦክስ ሪንግ አመጣው! እነዛን ቁጡና በብሶት የተሞረዱ የማይክን ሰንጢ ጥፍሮች በጓንት ሸፍኖ ስፖርት አደረጋቸው። ደም ሳይሆን ዝናና ገንዘብ አፈሰሱ። የምታዩት ማይክ ታይሰን ተፈጠረ። ስሙ በዓለም ናኘ። ግን ምን ዋጋ አለው ገና በ20 ዓመቱ የአለምን የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻንፒየን የተቆጣጠረው ማይክ የገንዘብ ጎርፍ አጥለቀለቀው፣ የልጅነቱን ስነልቦናዊ ህመም ፣ብቸኝነትና የውስጡን ረብሻ የማያክም ገንዘብ። በ16 አመቱ በካንሰር ለሞተች እናቱ ያልደረሰ ገንዘብ ። እንደጉድ ብሩን ረጨው፣ ባለፈ ባገደመበት ሴት ነው፣ መጠጥ ነው፣ ድራግ ነው። ውድ መኪና ቅንጡ ቤት ... ከተራ ሰው እስከፖሊስ በውሃ ቀጠነ እየደበደበ ቅጣት ነው። ባዶውን ቀረ።

ይታያችሁ ፎርብስ አንድ ጊዜ የማይክን ሃብት 685 ሚሊየን ዶላር ገምቶት ነበር። ዛሬስ? ከየኪሱ የቀሩትን ሳንቲሞች ጭምር ቆጣጥሮ የቀረው ሀብት 10 ሚሊየን ብር ቢሆን ነው። ተራ በሚባሉ ፊልሞች ሳይቀር ተራ ገፀ ባህሪ ወክሎ አሰሩኝ እያለ እስከመለመን ደርሶ ነበር። ማይክ ታይሰን ብዙዎች እንደሚያስቡት የሚንጎማለል አንበሳ ፣ ከአለት የጠነከረ የቡጢ ንጉስ አይደለም። ቤተሰብ እና ማህበረሰብ እንዲሁም ዘረኝነት የፈጠረው ጠባሳ ለዚህ ያበቃው የቦክስ ጓንት ውስጥ ጎጆውን የሰራ ሚስኪን ወፍ ነው። የልጅነት አዕምሮ ላይ የቆመ ጠባሳ በተጠቂው ቡጢ አይጣልም። ልጆች ላይ የሚሰነዘርን የህይወትን ቡጢ፣ የስነልቦና ፍላፃ ይከላከል ዘንድ የተፈጠረ ጋሻ ወላጅ ይባላል። ወላጅ ናችሁ? እንግዲያውስ ለልጆቻችሁ ህያው አጥር ሁኑ
!


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

15 Nov, 18:50


"እግርህ ሥር የሚያደናቅፍህ ድንጋይ ተቀምጦ ዓይንህን ከድንጋዩ ለማሸሽ ብትሞክር እራስህን ማታለልህ በቅፅበት ይገባሃል። ድንጋዩ የሚመታው ዓይንህን ሳይሆን እግርህን ነዋ! ብዙዎች እራሳቸውን በማታለልና በመሸንገል መንገድ ሲሄዱ እውነት እያሠናከለች ስትጥላቸው የምንመለከተው ለዚህ ነው"

#ሩሚ


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

14 Nov, 18:56


"ሁሉም እንስሳት እኩል ናቸው፤ ነገር ግን አንዳንድ እንስሳት ከሌሎቹ የበለጠ እኩል ናቸው።

“በውጭ ያሉት ፍጥረታት ከአሳማ ወደ ሰው፣ ከሰውም ወደ አሳማ፣ ከአሳማም ወደ ሰው ዳግመኛ ይመለከቱ ነበር። ግን የትኛው እንደሆነ አስቀድሞ መናገር አልተቻለም።

“ሰው ሳይለፋና ሥራ ሳይሠራ የሚበላው ብቸኛው ፍጡር ነው። ወተት አይሰጥም ፥ ዕንቍላል አይጥልም ፥ ማረሻውን ብቻውን በማቀናጀት ለማረስ  በጣም ደካማ የሆነ ፍጡር ነው። ጥንቸሎችንለመያዝ በፍጥነት መሮጥ አይችልም። ነገር  ግን እርሱ  የእንስሳት ሁሉ ጌታ ነው።

   -  ጆርጅ ኦርዌል "ANIMAL FARM"


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

10 Nov, 20:58


ሁለት ዘመን ፍቅር!

ድሮ በእኛ ዘመን ፍቅሮ በዐይን ተጸንሶ፤ እንባንና ወኔን አፍስሶ፣ ሰውነትን ጨርሶ፣ የሚጥል አደገኛ መተት ነበረ የአሁን ዘመን ፍቅር ግን በሞባይል ተጸንሶ፤ ካርድና ጊዜን ጨርሶ፣ ከአንድ ቀን ግንኙነት በኋላ በብሎክ የሚጠናቀቅ ተራ ክስተት ሊሆን ዜ

በእኛ የወጣትነት ዘመን ከፍቅረኞቻችን ጋር የምንገናኝበት ምንም አይነት ቴክኖሎጂ እልነበረም:: ኮንዶምም ጭምር!

ስለዚህ ያፈቀርናትን ሴት ለማግኘት ወደ ወንዝ ወርዳ ልብስ የምታጥብበትን፣ ውሃ የምትቀዳበትን፣ ገበያና ትምህርት ቤት የምትሄድበትን ሰዓት መጠበቅ ነበረብን:: በዚህ ጊዜ ግን እድሜ ለቴከኖሎጂ ከባዱ ነገር መገናኘት ሳይሆን መለያየት ነው:: ያፈቀርካትን ሴት ለማግኘት 'አፕሊኬሽን' ማውረድ እንጂ ወደ ወንዝ መዉረድ አይጠበቅብህም :: ለትዳርም ይሁን ለአዳር፣ ለፍቅርም ይሁን ለወሲብ፣ ያሰብካትን ኮረዳ ፌስቡከ ላይ ብታጣት “ዋትስ አፕና ቫይበር” ላይ አታጣትም::

ስለዚህም ሰው እየኝ አላየኝ ብለህ ሳትሳቀቅ፣ ፍርሃቴን አወቀችብኝ ብለህ ሳትጨነቅ፣ ከተለያዩ ድረ-ገፆች ያሰባሰብካቸው የፍቅር ኑዛዜዎች ስትፈልግ በጽሑፍ አስፍረህ፣ ስትፈልግ በድምጽህ ቀድተህ ትልከላታለህ:: መስመር ላይ ስትጠፋብህ ደግሞ ወደ ፎቶ መደርደሪያዋ በመሄድ ባቷን ገልጣ፣ ጡቷን አሳብጣ የተነሳቻቸውን ፎቶዎች እየጎበኘህ Hot እና Cool የሚል ኮሜንት እየሰጠህ፣ እስክትመጣ ድረስ ትጠብቃታለህ::

የእኛ ዘመን ሴቶች ግን፣ ለፍቅረኞቻቸው ቀርቶ ለመታወቂያቸውም የሚሆን ፎቶ አልነበራቸውም ነበር:: በዚህ ላይ ደግሞ ለምንወዳት ልጅ ያለንን ስሜት የመግለጫ መንገዱ በሰፈራችን ጸሐፊ ትዕዛዝ ተደርሶ ለድፍን የአውራጃው አፍቃሪዎች በካርቦን እየተገለበጠ የሚሰጥ ደብዳቤ ብቻ ሲሆን፣ ይሄውም ኑዛዜ የጸሐፊውን እንጂ የአፍቃሪውን ስሜት የሚገልጽ አልነበረም::

ከሞላ ጎደል የደብዳቤውን ይዘት በጨረፍታ ስንመለከተው_ ከፍቅር ይልቅ ተፈጥሮን ማድነቅ ላይ ያነጣጥራል:: የጸሐይ ርቀቱን፣ የሰማይ ስፋቱን፣ የውቅያኖስ ጥልቀቱን፣ የኮከብ ብዛቱን፣ የደመና ንጣቱን፣ የልምላሜ ውበቱን... ያህል ለምወድሽ ፍቅሬ_" እያለ የሚተረተር ነው..

አሳዬ ደርቤ
ጎዳናው እስኪቋጭ


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

02 Nov, 19:36


የሰው ልጅ የሚሰቃየው ራሱ ባጠረው አጥር ራሱ በገነባው ቅጥር ራሱ በሸበበው ውትርትር ነው። የዘር ፣ የሃይማኖት ፣ የርዕዮተ አለም ፣..... የፍልስፍና አጥር ። የብቸኝነት ፣ የአውሬነት ፣ የወፈፌነት ፣ ......አስማት የሚመስል አጥር።...

"ክቡር ድንጋይ"


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

28 Oct, 19:12


በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ  አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ  ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።

  "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ...ለምሳሌ ሰው ፣ አህያ ወይም  የተናኘ  ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው"  አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ  ፍቅረኛው ናት፤ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው?) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ  ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ  እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ  ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች።  መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ  መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ  የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ  ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣  የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው  የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

22 Oct, 08:56


``እግዚአብሔር በመጀመርያ ዓለምን ፈጠረ፤ በቀጣዩ ቀን ሰውን ፈጠረና ከስራውም ሁሉ አረፈ..። በማግስቱ ሴትን ፈጠረ፤ እነሆ ከዚያን ቀን ጀምሮ እግዚአብሔርም ሆነ ሰው አንዳች እረፍትን አላገኙም!።``

፦Western_philosophers

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

18 Oct, 19:27


አንዲት ሴት፦``አንተ ባሌ ብትሆን ኖሮ ቡናህ ውስጥ መርዝ እጨምር ነበር`` አለችኝ። እኔም መለስኩላት፦ አንቺም ሚስቴ ብትሆኚ ቡናውን እጠጣሁ ነበር. .🙂


፦George Bernard shaw

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

17 Oct, 18:18


('አጥቢያ' በአለማየሁ ገላጋይ)
ሙሉጌታ ‹ጎሽ ና አለው፡፡ ኮምሬድ ቆሎ በጥብቆው እንዳሳተፉት ልጅ ሱሪውን ጨምድዶ አንድ እግሩን እየጎተተ መጣ፡፡ የግራ እጁ ትንሿና ተከታይ ጣቶቹ ታጥፈው ሳንቲም ይዘዋል፡፡ በሦስቱ ጣቶቹ ጨበጠን፡፡
‹‹ዕውቀቴን ወደ ገንዘብ ለመለወጥ ነው የመጣሁት››
«ጥሩ፣ ምን አዲስ ዕውቀት አለህ?›› እያለ ወደ መንገድ ዳር ይዞት ወጣ፡፡ ከስሜቱ መገላገያ ሰበብ አድርጎ ተቀብሎታል ስል አሰብኩ፡፡
‹‹ስለ ሰው›› አለ ኮምሬድ
‹‹ጥሩ፣ ሰው ምንድነው?››
‹ሰውማ ሸቀጥ ነው፡፡ ተነፃፃሪ ልውውጥ ይኖረዋል፡፡ ከዱር ያለከልካይ ሄደህ ከምትለቅመው አቃቅማ ይልቅ የጓሮ ጎመን ዋጋ አለው፡፡» ቢድባባማ ብርሃን ውስጥ እድፍ የተሰደፈበትን ፊቱን አየሁት፡፡ ንግግሩ በስሜት የታጀበ አይደለም ‹‹የጓሮ ጎመን ከዱር ፍሬ በላይ ዋጋ የሚኖረው ጊዜና ጉልበትህን ስላፈሰስክበት ነው፡፡ ሰውም እንደዚያ ነው፡፡ እንደ ዱር ፍሬ፣ ወፍ እንደዘራው የሚበቅል፣ ምንም ዕውቀት ያልፈሰሰበት የሰው አቃቅማ አለ፡፡ ከዚህ ሰው ይልቅ የኔታ ጋር የተማረው እንደ ጓሮ ጎመን በጥቂት ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ጉልበትና ጊዜ የፈሰሰበት ሰው የተሻለ ዋጋ አለው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች በንጽጽሮሽ ልውውጥ ገበያ ቢወጡ የአምስት ቁና አቃቅማ ዋጋ አንድ ነጠላ ጎመን ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲያ ነው፣ ሰው ሸቀጣዊ ባህርይ አለው፡፡› ያብሰለሰለ መስሎ ቀጠለ...
‹‹እኔ በራሴ ላይ ካፈሰስኩት ዕውቀት ውጭ ነጥለህ ከተመለከትከኝ አርባ አምስት ኪሎ ሥጋና አጥንት ብቻ ነኝ፡፡ በቃ ሊያወም ስለማይበላ ጠያቂ የሌለው፣ ለመግማትና ለመበስበስ የተዘጋጀ 45 ኪሎ ሥጋና አጥንት››
ኮምሬድ እራሱን የሚያስበው ከሃያ አመት በፊት ባለው ኪሎ ነው ስል አሰብኩ፡፡
ሙሉጌታ አዳምጪው እንደማለት ጎሸም አድርጎ አነቃኝ፡፡እሱ ላይ ያደረውን መጥፎ ስሜት እኔ ላይ አጋብቶ እንዳይለየኝ የኮምሬድን ዲስኩር የዘየደበት ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ኮምሬድ ቀጥሏል...
‹‹ማርክስ እራሱ ምንድነው? ለሰላሳና ለአርባ አመት አድፍጦ መንፈሱን ባያበረታ፣ በራሱ ላይ ዕውቀት ባያከማች ኖሮስ? ጢም ያለው በግ ነበር የሚሆነው፡፡ በቃ! እንደወረደ የተፈጥሮ ሰው በሁለት እግሩ የሚሄድ ያልታረደ በሬ ነው...
‹‹እዚህ ሰፈር የተከማቹ፣ ምንም አይነት ዕውቀት ያልታከለባቸው አስር ሰዎች የአንድ ደብተራ ዋጋ የላቸውም፡፡የዚህ ሠፈር ሰዎች መሪ ከመሆን የሰለጠነ አህያ መንዳት ያዋጣል፡፡ ሰውነታችሁ ለምን ክብር አጣ? ጉልበታችሁ ስለምን ዋጋ ተነፈገው? እንደምንስ እንደአይጥ ጎሬ ውስጥ ለመኖር ተገደዳችሁ? የረጋ ዕውቀት ስላልተከማቸባችሁ አይደለም? ታዲያ እንዴት ልጆቻችሁን ዕውቀት ትነፍጋላችሁ? ልጆቻችሁ የረጋ ዕውቀት ካልተከማቸባቸው በግ ለመሆን በሂደት ላይ ያሉ ግልገሎች አይደሉም


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

14 Oct, 17:44


"ዝግመተ-ለውጥ"

«እንጋባ» ሲል ጠየቃት አሳምነው፤ አልተቀበለችውም አስማሩ። «ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል» አለችው፤
ተስማሙ።
ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል፤ ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፤ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ፤
አውግተው ይለያያሉ።
የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም።
አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሐይ መጣ።
እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ፤ ስለሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ።
አስማሩ አሳምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት።
ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና፣ የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ
አላስፈለገውም፤ ጃኬቱን አውልቆ ሄደ።
አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው።
ሱሪውን ደርቦ መጣ «ወበቀኝ» ብሎ አወለቀው፤ አስማሩ አጥባ አኖረችው። ካፖርቱን ጥሎ ሄደ፤ አጥባ አኖረችው።
አንድ ቀን በጠራራ ፀሐይ፣ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ፤ አስማሩ «ምነው?» አለቸው።
«በጠራራ ፀሐይ፣ ብርድ ሆዴ ገባ» አላት።
"ምች ይሆናል።" አለችው፤ የምች መድኃኒት ብታሽለት ተሻለው።
ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ።
አስማሩ አጥባ አኖረችው።
ትንሽ ቆይቶ፣ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ።
«ምነው?» አለችው።
«ላሳድሰው መሄዴ ነው። አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው።» አላት፤ አመነችው።
ጨዋታው ደራ፤ ፍራሹን እረስቶት ሄዶ ኖሮ፣ እኩለ ሌሊት ቢመጣ፣ አስማሩ ቦታ ስላጣች፣ ፍራሹን ፍራሿ ላይ ደርባው ደረሰ። ያኔ «ተነሽ» ከማለት «ጠጋ በይ» ማለት ቀልሎ ተገኘ።

ኩርቢት


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

10 Oct, 17:24


ሰዎች ለውጥ ማድረግ የሚፈልጉት መጥፎ ነገር ሲከሰት ብቻ ነው።

ይሄ በጣም የሚገርመኝ ነገር ነው፤ ሁሉም ነገር የተረጋጋ ሲሆን ለውጥ ማምጣት አይፈልግም አብዛኛው ሰው።
ያሉበትን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይፈልጉም፣ ህይወታቸውን ማሻሻል አይፈልጉም፣የበለጠ አሪፍ ማድረግ፣አዳዲስ ነገሮችን መጀመር፣ መሞከር የሚባሉ ነገሮችን አያስቦቸውም ባሉበት መቅረትን እንጂ...

እራሳችንን መለወጥ አለብን ሁሌም የተሻለ ማድረግ።

ግዴታ breakup አስክናደርግ መጠበቅ የለብንም
እራሳችንን ለመለወጥ ፣ለማሳመር፣ለመንከባከብና ለራሳችን የበለጠ ጊዜ ለመስጠት።
ግዴታ አስኪያመን መጠበቅ የለብንም፤ ሱሳችን ለማቆም አመጋገባችንን ለማስተካከል፣ የበለጠ በቂ እንቅልፍ ለማግኘት።

ግዴታ አዲስ አመት አስኪመጣ መጠበቅ የለብንም ፤ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር፣ለማወቅ፣ለመሞከርት፣አዳዲስ ነገሮችን ለመጀመር፣ጥሩ ነገር ለማድረግ።

ግዴታ እስክንባረርና ትክክል አይደለም አይበቃም አይመጠንም እስክንባል
መጠበቅ የለብንም፤ አሻሽሎ ለመስራት ።

ግዴታ እስክንወፍር መጠበቅ የለብንም፤ sport ለመስራት ወይ ለመጀመር።
Sport ሁሌም መስራት ያለብን ነገር ነው ጤናችን ለመጠበቅና ለረጅም ጊዜ ሰውነታችን እየታዘዝልን እንዲቆይ ለማድረግ።

ግዴታ ሀጢያት አስክንሰራ መጠበቅ የለብንም ወይ ግዴታ አስኪቸግረን ህይወታችን ላይ የሆነ ነገር እስኪከሰት መጠበቅ የለብንም፤
ለመፀለይም ወደ ቤተ እምነቶች አዘውትረን ለመሄድ ወይ መሄድ ለመጀመርም።

አስኪደብረን መጠበቅ የለብንም፤ መፅሃፍት ለማንበብ፣ትምህርቶችን መዝሙሮችን ለመስማት... ለመውጣት ለመዝናናት አዲስ ቦታዎችን ለማየት ሰዎችን ለማግኘት

እነዚህ ሁሌ ማድረግ ያለንባቸው ነገሮች ናቸው ማድረግ ብቻ ሳይሆን ግን ከትናንቱ በበለጠ ዛሬ እያሻሻልናቸው እየጎበዝንባቸው ከፍ እያልን ልንሄድባቸው የሚገቡ ነገሮች

ዛሬን ከትናንቱ በተሻለ ሁሉንም ነገር እናድርግ ለአይምሮችንም ለሰውነታችንም ጥሩ ነው በእራሳችን ላይና በምናደርጋቸው ነገሮች ላይ ለውጥ ስናይ ደስታንም ይሰጠናል።

ቦን ጆርኔ ኣ ቩ ቱስ 🖤



@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

22 Sep, 11:18


"እዉቀት ብለህ የምትጠራዉና ፈጣሪ ብለህ የምትገልፀው የተለያዩ አይደሉም. ፈጣሪ ፍፁም የሆነ እዉቀት ነው. ከ አመክንዮ (logic) ባሻገር ያለ እዉቀት ፈጣሪ ነው. በ አንተ እዉቀት መሰረት እና ዉስንነቶች ዉስጥ ብቻ ከሆነ ፈጣሪ ብለን የገለፅነዉን ፍፁም አታዉቀዉም ማለት ነው" ይላል ሳዱጉሩ ጃጋዲሽ

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

11 Sep, 21:43


አዝመራው
(በእውቀቱ ስዩም)

አንድ ዲያስፖራ ጓደኛ ነበረኝ፤ ስለኢትዮጵያ ባወጋ ቁጥር “ያገሬ ሴቶች እሸት እኮ ናቸው ‘ ይላል፤ “ ፈጣሪየ! ከአገሬ እሸቶች አንዷን መርቀህ ስጠኝ” እያለ እንደሚጸልይ ሁሉ አጫውቶኛል፤ አንድ ቀን ከአሜሪካ ወደ አገሩ ገብቶ ፥ከአየር ማረፍያ ወደ እናቱ ቤት በታክሲ እየሄደ ነው፤ ባጋጣሚ በወቅቱ፥የሴቶች ታላቅ ሩጫ ቀን ነበር፤ የመዲናይቱ ቆነጃጅት በሙሉ አረንጓዴ ማልያና ቁምጣ ለብሰው አስፓልቱን ሞልተው ይሮጣሉ፤ አጅሬ ታክሲው ውስጥ ሆኖ እያየ አሁንም አሁንም ምራቁን ሲውጥ ከቆየ በሁዋላ እንዲህ አለ፤

“ ጌታየ ሆየ ቸርነት አያልቅብህ! አንዲት እሸት ስለምንህ አዝመራው መሀል ጣልኸኝ”

ትናንትና ወደ ወደ ፒያሳ ወክ ሳደርግ አራትኪሎ አስፓልት ላይ ከመቶ እማያንሱ ቆነጃጅት ባለ አበባ ቀሚስ ለብሰው አሸንዳ ይጨፍራሉ፤ ልቀላቀላቸው ፈለግሁ፤ ግን “እኔጋ ና እኔ ጋ ና” እያሉ እንዳይጣሉብኝና ፤ መንግስት ባህል አሸበርህ ብሎ እንዳይከሰኝ ሰጋሁ፤ ያም ሆኖ በስሜት ተነድቼ በመካከላቸው ራሴን አገኘሁት፤

ሴቶቹ ድንገት ተጠቃቀሱና ጭፈራቸውን አቆሙ፤

ዋናዋ አቀንቃኝ “ይቅርታ! ወንድ መጨፈር አይችልም” አለቺኝ፤

“ ከበሮ በመምታት እህቶቼን እንዳገለግል ይፈቀድልኝ “ አልኳት፤

“ ከበሮ የሚመቱ በቂ እህቶች አሉን” አለች ክርር ባለ ድምጽ፤

“እሺ ለለውጥ ያክል ክራር እየመታሁ ወይም እምቢልታ እየነፋሁ ላጅባችሁ”

ሴቶቹ በህብረት ገላመጡኝና እየጨፈሩኝ ትተውኝ አለፉ፤

የእርመን ቤተክሲያን አካባቢ ሲደርሱ በእግረኛ መንገድ ሳይክሌን እየጋለብኩ ደረስኩባቸው ፤

“ችግርህ ምንድነው?’ አለችኝ አቀንቃኚዋ፤

”ምን አጠፋሁ?”

ልጇን እንደምትመክር እናት ጎንበስ ብላ፤ እንሶስላ የሞቀ መዳፏን ተከሻየ ላይ ጭና ፥
“ አሸንዳ የሴቶች በአል ነው፤ ወንድ አይደባለቅበትም ፤ አይገባህም?” ብላ ጮኸችብኝ፤

“ ሽልማት መስጠትስ አልችልም? ”አልኳት፤

“ ወደ ቤትህ ሂድና ሽልማቱን በእህትህ ላከው “

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

11 Sep, 13:47


እየተዛዘን ጎበዝ

(በእውቀቱ ስዩም)

ትላንትና ከቀበና ወደ መገናኛ ፈጠን ብየ ስራመድ ነበር ፤

እየተራመድሁ ፥ የሾላ መታጠፍያ ጋ ስደርስ የመናፈሻው አግዳሚ ወንበር ላይ ሁለት ቆነጃጅት ቁጭ ብለዋል፤ ወደ እኔ አቅጣጫ የሚያዩ መሰለኝ፤ እስቲ ለማንኛውም ብየ አለባበሴን በወግ በወጉ አደረግሁት ፤ የሱርየን ዚፕ ዘግቼ ፥ የሸሚዜን የደረት ቁልፎች ከፈትኩ፤ ሁለት ለምለም የደረት ጸጉሮች እንደ ንብ አንቴና ብቅ ብለው ግርማ ሞገስ ጨመሩልኝ ፤

ከሽኮቹ ፊትለፊት ደርሼ ወደ ተቀመጡበት ዞር እንደማለት ቃጣኝ፤ ከታች ሲያዳልጠኝ እግሬ ብድግ ሲል ይሰማኛል፤ መሬት አንሸራተተችኝ ከማለት በጠረባ መታችኝ ማለት ይቀለኛል፤ አየር ላይ ብዙ ደቂቃ ስለቆየሁ፥ በጀርባየ ልውደቅ ወይስ በጎኔ ልውደቅ ? ብሎ ለመወሰን ሁሉ በቂ ጊዜ ነበረኝ፤

ከወደቅሁበት ለመነሳት ስቅመደመድ ፥ ቆነጃጅቱ ሆዳቸውን ይዘው ይስቃሉ፤ ሳቃቸው እንደ ሳውንድ ትራክ አጅቦኝ ተነሳሁ፤

የምር በጣም አዘንሁባቸው ፤ ተሯሩጦ ማንሳት እሺ ይቅር ! “ እኔ ይድፋኝ “ እሚለው ባህላችን የት ደረሰ? አዳራሽ ውስጥ ወግ ሳነብ ራሱ እንደዚህ አይነት ደማቅ እና ዘለግ ያለ ሳቅ አጋጥሞኝ አያውቀም፤ በእልህ ተነሳሁ፤ የጉልበቴ ሎሚ ወደ ቁርጭምጪሚቴ የተንሸራተተ ይመስለኛል፤ ማነከሴን ላለማስባንን ትንሽ ስታይል ጨምሬበት ጉዞየን ቀጸልሁ ፤

ለተጎዳ የምናዝን እና አጥቂን የምንቃወም ህዝብ ነበረንኮ! ያ ባህላችን የት ደረሰ ከቶ?

ድሮ ትያትር ስናይ የነበረው ሁኔታ ትዝ ይላችሁዋል? መድረኩ ላይ ኦቴሎና ዴዝዲሞና ይፋቀራሉ፤ ኢያጎ ፍቅረኛሞችን በቅናት ያበጣብጣቸዋል፤ በመጨረሻ ኦቴሎ ዴዝዲሞናን ሲጥ አድርጎ ይገላትና እሱም ሽጉጡን ይጠጣል፤

ትያትሩ ሲያልቅ ተመልካቹ ኢያጎን መስሎ የተጫወተውን ተዋናይ ለመደብደብ ዱላ ገጀራና ዲሽቃ በመያዝ የትያትር ቤቱ በር ፊት ይሰበሰባል 🙂 ተዋናዩ ስጋት ተሰምቶት የትያትር ቤቱ ዘበኞች አጅበው በሁዋላ በር እንዲያስወጡት ይማጸናል ፤ ግን ዘበኞቹ ራሳቸው ስለተናደዱበት ከትያትር ቤቱ ጀርባ ወስደው በቆመጥ እና በከስክስ አሩን ያስበሉታል! በመጨረሻ ብሄራዊ ትያትር አመራሮች፥ ከሩስያ ኢምባሲ ጋር በመተባበር ለጥቂት ቀን ካገር ዞር ብሎ እንዲቆይ ያደርጉታል፤

አሁን ያ የለም! እንኳንስ በትያትር በእውኑ አለም ለተጎጂ መቆርቆር እየቀረ ነው!

በቀደም አንዱ በማጅራት መች ተደብድቦ ያበጠ ፊቱን ይዞ ቲክታክ ላይ ቀረበ፤ ሲሆን ሲሆን፥ የመታከሚያ ያዋጡልኛል ፤ ያም ባይሆን እንኳ “ የውሻ ቁስል ያርግልህ፤እግዜር ይማርህ” ብለው ያጽናኑኛል ብሎ አስቦ መሆን አለበት፤አስተያያት መስጫውን ሳየው በማጽናኛ ሳይሆን ሙድ በሚይዙ አስተያየቶች ተሞልቷል፤

አንዱ እንዲህ ብሏል፤

“ አባ ! ፊህትኮ የቨላንታይን ፊኛ መስሏል! ከውስጥ ወደ ውጭ ነው እንዴ የደበደቡህ? “

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

10 Sep, 22:15


🌼 እነሆ አዲስ ዓመት መጣ። 🌼

🌻 እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሰን
!

🌼አዲሱ ዓመት በማኅበረሰባችን ውስጥ እውቀት ዘልቆ ጥበብ ሰርጾ ፍቅርና ሰላም ናኝቶ፣ ኑሯችንን ክፉና ደግን በማገናዘብና መልካሙን በመምረጥ የምንመራበት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን። 🌼🌻

   ፈጣሪ አገራችንን ከክፉ ይጠብቃት!
    ₂₀₁₇ መልካም አዲስ ዓመት!❤️

@phylosophy_gora🌼
@phylosophy_gora🌼
@phylosophy_gora🌼

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!🌻

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

20 Aug, 20:04


ስብዕና በልጅነት እንደተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደደረቀ አርማታ ነወ።

የብዙ ሰው ስብዕና እንደተቦካ ሲሚንቶ በልጅነቱ በትክክል የሚቀርፀው ካላገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። እድሜው ከገፋ በሁዋላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶ አገር ያጠፋል።

ዶክተር ምህረት ደበበ


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

16 Aug, 19:35


የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ህይወት መውጫ የሌላት መስላ ስታስጨንቀን በምንወስነው ውሳኔ ውስጥ ነው፡ የማንነታችን ትርጉም የሚለካው ነን ብለን የምናስበው ማንነታችን ፈተና ሲገጥመው በምንወስደው እርምጃ ነው፡ እራሳችንን የፍቅር ጥግ አርገን የምናይ ከሆነ የፍቅር ጥግ መሆናችንን የሚረጋገጠው ጥላቻ ግድ የሚሆንበት ቦታ ላይ የፍቅርን ፀዳል መልቀቅ ስንችል ነው፡ የይቅርታ ሰው መሆናችን የሚታወቀው ይቅርታ ለማረግ በሚያስቸግርበት ሁኔታ ላይ ይቅር ማለት ስንችል ነው፡

ኦሾ


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

15 Aug, 19:40


❝... መማር አለማውቅን ማወቂያ ነው ‒ ብስለትን ፣መረዳትን የሚጨምር። አለማወቅ ደግሞ የማወቅ ፍላጎት መሰላል ነው፤ ሰውን ከግብዝነቱና ከትምክህቱ የሚያወጣ።...
ከወንዝ በታች ሐይቅ አለ ፤ከሐይቅ በታች ውቅያኖስ አለ፤ ከውቅያኖስ በታች አለማወቅ አለ - ዲካ የሌለው!ዝቅ ስንል አዳዲስ ከፍታ ይታየናል።
ልጅ ሆኜ 'ፒ ኤች ዲ ' የነበረው አጎቴ «ልትኮሩብኝ ይገባል» ይለን ነበር‒ ራስን አምልኮ እኛን በማስመለክ። የዕውቀት ቁንጮ ማወቅ ሳይሆን አለማወቅ መሆኑን ያወኩት ግን አሁን ነው ‒ ማወቄን ባለማወቅ ስለካው! ❞

ፍቅረ ማርቆስ ደስታ ‒ የሚሳም
ተራራ!

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

11 Aug, 13:54


ተንታኝ

(በእውቀቱ ስዩም)

ቅድም የሆነ ምግብ ቤት ቁጭ ብየ ፤ ከፊቴ በተንጣለለው ቲቪ ማራቶን ስመለከት ከጎኔ የተቀመጠ ተመጋቢ ያጉተመትማል፤

“ይረባሉ ብለህ ነው?” አለኝ፤

“ያቅማቸውን እየሞከሩ ነው “ አልኩት፤

“ ለሜሳ የተባለው ባለፈው መሰናክል ላይ ወድቆ ሆስፒታል መግባቱን ሰምተሀል መቼም”

“ የወደቀውኮ ወድዶ አይደለም፤ አደናቅፎት ነው፤ በነገራችን ላይ ስሙ ለሜሳ ሳይሆን ለሜቻ ነው”አልሁት ፤

“ ከተሸነፈ በሁዋላ እንኩዋን ስሙን ዜግነቱንና ጾታውን አሳስቼ ብጠራው መብቴ ነው’ አለ ሰውየው

አስከትሎ እንዲህ አለ፤ ” እንደ ነገርኩህ መውደቁ አይደለም ችግሩ፤ እንዴት በወሳንሳ ሆስፒታል ይገባል? መሰናክሉ ቢያደናቅፈው መሰናክሉን እንክትክት አርጎ እንክትካቹን ከእግሩ ላይ እንደ አቧራ አራግፎ መሮጥ ነበረበት ፤ የኛ አትሌቶች ፍጥነት እንጂ ጉልበት የላቸውም፤ ጡንቻማ ላመል አታገኝባቸውም ፤ የጀመይካ ያጭር ርቀት ሯጮችን ተመልከት ፤ እግራቸው ያንጋፋ ዝግባ ግንድ ነው የሚያክለው፤ ደረታቸው ከደራርቱ ቱሉ አደባባይ ይሰፋል፤ የክንዳቸውን ፈርጣማነት ስትመለከት በትርፍ ጊዜያቸው ቦክስና ነጻ ትግል እንደሚወዳደሩ ትገምታለህ፤ በሲኖትራክ ብትገጫቸው ራሱ አይወድቁም፤ ቢወድቁ እንኳ የወደቁበት መሬት ይጠረመሳል፤”

“ህም “ አልሁና ወደ ማራቶኑ ማፍጠጤን ቀጠልሁ፤

ሰውየው ቀጥሏል፤

“ የኛ አትሌቶች ገንቢ ምግብ መመገብ አለባቸው፤ ሩጫ በድርቆሽ ፍርፍርና በበሶ የሚዘለቅ አይደለም፤ ፍሪምባና ሻኛ እየበሉ ክብደት ማንሳት አለባቸው፤ ይልቁንም ውድድሩ ቢያንስ ሀለት ወር ሲቀረው ከወሲብ መታቀብ አለባቸው፤ ከሚስታቸው ጋራ ከተኙ እንኩዋ ካንድ ዙር በላይ እንዳይሄዱ ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል፤”

ታምራት ቶላ አንደኛ ሲወጣ የምግብ ቤቱ ተስተናጋጆችና አስተናጋጆች ቆመን ማጨብጨብ ጀመርን፤ ሰውየው ከተቀመጠበት ሆኖ መዳፎቹን በዝግታ ማማታት ጀመረ፤

“ተነስተህ አታጨበጭብም?” ስለው፤

“ ይቅርታ፥ ዲስክ ላይ ችግር ስላለ፤ መቀመጡን እመርጣለሁ”

bewketu syoum

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

11 Aug, 13:49


በነገራችን ላይ በባህላችን ከወርቅ በላይ የተከበረው ማእድን ብር ነው፤ ገንዘባችንን ብር ብለን የጠራነው ለዚህ ነው፤ በሰርግ ወቅት “ ወርቅ አምባር ሰበረልዎ “ ተብሎ ሳይሆን “ ብር አምባር ሰበረልዎ” ተብሎ እንደሚዘፈን አንርሳ፤ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ውስጥ “ብር “ እሚል ቃል አይጠፋም፤

ለምሳሌ-

ክብር
ደብር
ነብር

ወዘተረፈ
እንዲህ ብየ በመጽናናት እሁዴን ቅደሜ ላድርገው ፤😑

Bewketu syoum

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

08 Aug, 17:52


ሰፈራችን ቢራ ቤት አለ ሸምገል ያሉ ጃኬት ሹራብ ያደረጉ ጠና ያሉ ሰዎች በረንዳ ላይ እየጠጡ ቁጭ ብለው ያወጋሉ ...

እኛ ከትምህርት መልስ ኳስ እንጫወታለን !

ሰፈራችን ቤርጎ አለ ጥንዶች ተቃቅፈው ተረጋግተው እያወጉ እየተሳሳሙ እየተሽኮራመሙ ፣ አልጋቤት ገብተው ይወጣሉ እኛ እርግጫ ላይ ስለምንሆን ወይ ሲገቡ ወይ ሲወጡ እናያቸዋለን ፦

እቤት ስንገባ ታላላቆቻችን ዜና ጓጉተው ያያሉ ይወያያሉ ዜናውን እያዩ ትክዝ ግርም ይላቸዋል ፦

"ዜና አሁን ምኑ ይታያል ?"
ይላል ልጅነታችን

እኛ ድራማ ፣ፊልም፣ Wrestling ፣ታላቅ ፊልም፣ኳስ፣ ህብረት ትርኢት ለማየት እንጠብቃለን ።

እንቅልፍ አሸንፎ ካልጣለን ፦

ማታ ያየነውን ከጓደኞቻችን ጋ እንቀዳለን ።

"እከሌ እከሌን ወደደ ፣ እከሌ እከሌን ካደችው፣ ካዳት ፣አስረገዛት ፣እከሌና እከሌ ተጋቡ፣ ወለዱ" ብለው ያወራሉ እንሰማለን ብዙ ትርጉም አይሰጠንም ።

እኛ ትርጉም የሚሰጠን ኳስ ፣ እርግጫ ፣ብይ፣ቆርኪ ፣ ሌባ እና ፖሊስ ፣ቃጤ ቃጤ ፣ በረዶ ፣ጠጠር ፣ ሱዚ.... ነበር

ስጋታችን እዛ ሰፈር የተጣላነው ትንሽ ልጅ ፣ በቴስታ የሚማታው ጓደኛችን ፣እምትቧጨረው ጓደኛችን ፣ እዚ ጋ አትጫወቱ የሚሉት ሴትዮ ፣ "ሲጫወቱ አጥሬን መቱብኝ "ብሎ ለቤተሰብ የሚከሰን ሰውዬ ... ጨዋታ አትጫወቱም አጥኑ የሚል የቤተሰብ ክልከላእና ጡጫ ፣ ለበዓል የሚገዛልን ልብስ ....

እምንፈራው በተረት የሰማነው አያ ጅቦ ..ስጋታችን በጨለማ ለሽንት ስንወጣ የምንሰማው ኮቴ ነበር
ማደግ ያጓጓንም ነበር ።

አደግን ፦

መጠጥን ቀመስነው ...
ቤርጎውን አየነው ...
ዜናውን ተራኳትንበት ...
ተካካድን ....

የማናቀው ነገ አስፋራን ፣ ማደጋችን አስደነገጠን ፣ ትልቅ ሰውዬ ነው ያልነው ሰው እድሜ የኛ ሆነ።

ልጅ ሆነን የምናዉቀው አለም ተቀየረ !!
Adhanom Mitiku


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

04 Aug, 19:26


..ሰ ባ ኪ ው..

የደንና የዱር አራዊት ተወካዩ የአካባቢውን ሽማግሌ እንዲያስተምሩለት ጋበዘ ተስማሙ። በቀጠሮ ቀን የነብር ቆዳ ለጌጥ ትከሻቸው ላይ አድርገው መጡ። ''የዱር አራዊትን አትግደሉ የዱር አራዊት መግደል በእግዚአብሔር ዘንድ በነፍስ ያስጠይቃል ሀገር ይጎዳል''ጥያቄ ያለው እጁን አወጣ..

"እኔ እምለው እሱን ቆዳ ነብሩ አውልቆ ሰጥቶት ነው?"



ውልብታ 📖
፦አለማየሁ ገላጋይ


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

02 Aug, 18:44


“ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወድህ ስትሞት ነው፤ እኔ ደሞ እንዲወደኝ ብዬ አልሞትም!። ”

፦ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

01 Aug, 18:15


ካርል ማርከስ ከመሞቱ ትንሽ ቀናት በፊት ታሞ የአልጋ ቁራኛ በነበረበት ጊዜ አንዷ የቤት ሰራተኛው ወደአልጋው ጠጋ በማለት "ለትውልድ የመጨረሻ ቃል ማስቀመጥ ትፈልጋለህ?" ብላ ጠየቀችው። ማርክስ እንዲህ ሲል መለሰ `` ከዚህ ለቀሽ ውጪ! በህይወታቸው ፈሪነታቸው ያደደባቸው ብቻ ናቸው የመጨረሻ ቃል የሚናገሩት ``

ካርል ማርከስ ፈላስፋ፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ተቺ፣ የታሪክ ተመራማሪ፣ Social researcher፣ Political activist፣ ጋዜጠኛ እና የጀርመን ሶሻሊስት አብዮተኛ ሰው ነበር..።

`` የሰው ልጅ ታሪክ የምግብ ፍለጋ ታሪክ ነው..`` -Karl marx


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

30 Jul, 19:27


እዚህች ከተማ ውስጥ ለረጅም አመታት መጽሀፍ የሚሸጥ ሰው አለ

👇🏾

ይህ መጽሀፍ ሻጭ ከሱቅ ኪራይ ውድነት ጋር በተያያዘ ከዋናው መንገድ ላይ ተነስቶ ውደ ሁለተኛው መንገድ ረከስ ያለ ሱቅ ያገኛል

ሆኖም ግን ለረጅም አመታት የሰበሰባቸውን እና በሺህ የሚቆጠሩ መጽሀፍቶቹን ወደ አዲሱ ሱቅ ለማዘዋወር ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ ራስ ምታት ሆነበት:: ይህንን የሰሙ የአካባቢው የረጅም ጊዜ ደንበኞቹ አንድ መላ ዘየዱ

👇🏾

ከመጽሀፍት ቤቱ ጀምሮ እስከ አዲሱ ሱቅ ድረስ ሰልፍ ሰርተው መጽሀፎቹን እየተቀባበሉ ቤቱን ቀየሩለት: በአካባቢው የሚያልፍ ሰው ሁሉ ሰልፉን እየተቀላቀለ በጥቂት ሰአታት ውስጥ የቤት ቅየራው አለቀ



@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

27 Jul, 19:00


ከሃሳብ የተጣላች ሃገር

ኢትዮጵያውያን ለሃሳብ ሩቅ ነን። ጥናት የሰራ የለም። ሳይንሳዊ በሆነ መንገድም አልተረጋገጠም። ግን ብዙ ነገሮችን በቀላሉ በማስተዋል መደምደሚያው ለትክክልነት የተጠጋ መሆኑን እንገነዘባለን።

በቅርቡ ደጃፍ ቲቪ ፖድካስት ላይ አዘጋጁ ዳዊት ተስፋዬ ከአርቲስት ኪሮስ ኃይለሥላሴ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር። ኪሮስ በ55 አመቱ ከብሔራዊ ቲያትር በግዜ ጡረታ ከወጣ በኋላ ሸገር ኤፍ ኤም ላይ ከአንድ ወዳጁ ጋር የሬዲዮ ፕሮግራም ጀምረው ነበር። የስፖንሰር ማስታወቂያ ሲያፈላልጉ ብዙ ድርጅቶች ኮሌጅ ነው የከፈታችሁት ወይ እያሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ይቀሩ ነበር። ይህን ሽሙጥ አዘል አስተያየት የጋበዘው፣ ማስታወቂያም ያሳጣቸው የፕሮግራማቸው ቁምነገር የበዛው ይዘት ነው። ቁምነገር አይፈለግም። የሚሰማ የለም። ድርጅቶችም ምርትና አገልግሎታቸውን በእንደዚህ አይነት ማንም በማይሰማው ፕሮግራም ማስተዋወቅ አይፈልጉም። አንድ!

ቴዎድሮስ ጸጋዬ ኢቢኤስ ቲቪ ላይ ከጥቂት አመታት በፊት ርእዮት በሚል ስም የሃርድ ቶክ ወይም ብርቱ ወግ የሚል ፕሮግራም ጀምሮ ነበር። ከጥቂት ሳምንት በላይ አልዘለቀም። ምክንያት? አያስቅም። ሃሳብ እንጂ ቧልት የለውም። የሚያሳስብ እንጂ የሚያዝናና አልነበረም። ፕሮግራሙ ተመልካች አጣ። ልክ ሲጀምር አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ሪሞታቸውን አንስተው ጣቢያውን ይቀይራሉ። ሁለት።

ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ አርትስ ቲቪ ላይ በነገራችን ላይ የሚል ፕሮግራም ነበረው። ደረጀ የተዋጣለት ቃለመጠይቅ አድራጊ ነው። አብዛኛዎቹ እንግዶቹ የፖለቲካ ሰዎች ነበሩ። ይሄም በይዘቱ ቁምነገር አዘል የሆነ ሃርድ ቶክ ነበር። ፕሮግራሙ ግን አልቀጠለም። የተመልካች ማጣት ሊሆን ይችላል።

እስቲ ለረዥም ግዜ ሳይቋረጡ የቆዩ ፕሮግራሞችን ተመልከቱ። ምንም የቁምነገር ጠብታ የሌላቸው በዋነኝነት በማዝናናት ወይም በማሳቅ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ከሾው አቅም እንኳን ከአስር አመታት በላይ የዘለቀው ሰይፉ ሾው የተወዳጅነት ሚስጥሩ ምንም አይነት እንግዳ ቢጋበዝ ቁምነገር ከማውራት ይልቅ ሳቅ መፍጠር ላይ ያተኮረ ስለሆነ ነው።

መዝናናት ምንም ነውር የለውም። ግን ሰው እንዴት 24 ሰአት ሙሉ ያገጣል? ቀልድ እኮ ቅመም ነው። ወጡ ውስጥም ትንሽ ነው ጣል የሚደረገው። ቅመም ሙሉ ወጥ ይሰራል እንዴ?! እስቲ ሲትኮሞችን ተመልከቷቸው። ከ20 እና 30 ደቂቃ በላይ አይዘልቁም። ሳቅ ጥፍጥ የሚለው እጥር ምጥን ሲል ነው።

ፌስቡክ ላይም እንምጣ። ብዙ ሰው የሚያነባቸው ሳቅ የሚፈጥሩ አጭር ፖስቶችን ነው። ረዘም ያለ ወይም ቁምነገረኛ ፖስት ማንም ዞር ብሎ አያየውም። ግዜ ማጣት አይደለም። ስር የሰደደ የሃሳብ ጥላቻ ነው። እንደ ህዝብ አፍቃሪ ቧልት ነን።

ባለፈው አንዱን በእውቀቱ ስዩምን ታውቀዋለህ ስለው እ! ኮሜዲያኑ አለኝ። በእውቀቱ ኮሜዲያን አይደለም። ገጣሚና የወግ ጸሐፊ ነው። ይሄን የሚያክል ትልቅ የስነጽሁፍ ሰው በኮሜዲያንነት ያስፈረጀው የማህበረሰቡ ሃሳብ ጠል አስተሳሰብ ነው። በእውቀቱን በጥልቅ ሃሳቦቹ የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው። አብዛኛው የሚያውቀው ሳቅ በሚያጭሩት ወጎቹ ነው። በእውቀቱ ጥልቅ ቁምነገር በቧልት እያዋዛ አሳምሮ መጻፍ ይችላል። ብዙዎች ግን በቧልቱ ስቀው ማለፍ እንጂ ከስር ያለውን ቁምነገር ነገሬም አይሉትም።

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚዲያ ደረጃ ትልቅ ቁምነገር ይዞ ብዙ አድማጭ ማግኘት የተሳካለት ሸገር ኤፍኤም ብቻ ነው። ሸገርም ቢሆን አብዛኛው አድማጮቹ ጎልማሳዎች ናቸው። የወጣቶች ተመራጭ ሚዲያ አይደለም። ለሸገር ስኬት የመአዛ ብሩ አስተዋጽኦ ጉልህ ነው። ሸገር ጨዋታና ሸገር ካፌን በመሳሰሉ ፕሮግራሞቿ ጥልቅ ቁምነገር በማይቸክ አቀራረብ ለአድማጭ ጆሮ በማድረስ የብዙዎችን ቀልብ መያዝ ችላለች።

ሌላው የሃሳብ ድሃ መሆናችንን የሚያሳየው ያሉት አዝናኝ የቲቪ ፕሮግራሞች እንኳን ፎርማታቸው እንዳለ ከውጪ የተኮረጀ መሆኑ ነው፦

ሰይፉ ሾው — Late Show with David Letterman
የቤተሰብ ጨዋታ — Family Feud
እስማማለሁ አልስማማም — Deal or No Deal
ድንቅ ልጆች — Little Big Shots
Jeopardy — ጥያቄና መልስ

የቲቪ ፕሮግራሞች ብቻ አይደሉም የሚኮረጁት። መጻህፍት፣ ሙዚቃ፣ የቢዝነስ ሃሳብ ወይም ምርት ሁሉንም ከውጪ በመኮረጅ ቀዳሚ ነን። ሃሳብ ከሸቀጥ እኩል import እናደርጋለን። የቁስ ብቻ ሳይሆን የሃሳብ ድሃ ነን። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው አመንጭተው ለአለም ያበረከቱት አንድም አዲስ ሃሳብ የለም። ስልጡን የምንላቸው ሃገሮች አሳቢዎቻቸው፣ ፈላስፋዎቻቸው፣ ደራሲዎቻቸው፣ አርቲስቶቻቸው፣ ሳይንቲስቶቻቸው በየመስኩ አዳዲስ ሃሳብ በየግዜው በየመስኩ እያፈለቁ ነው አስደናቂ ስልጣኔ የገነቡት። ሃሳብ ከሌለ ስልጣኔ የለም። እያንዳንዱ ስልጣኔ የሚጀምረው በአዲስ ሃሳብ ነው። እስቲ ኢትዮጵያ ያልነበረ ምን ወጥ ሃሳብ አፍልቃለች? ለ3000 ዘመን በበሬ የሚያርስበትን መንገድ ያልቀየርን ማህበረሰብ ነን። ይሄን ያህል ነው የሃሳብ ድህነታችን። ሌሎች የሰሩትን ትራክተር እንኳን ኮርጀን መስራት አንችልም። የዚህ ሁሉ ምንጭ የትምርት ስርአቱ ነው። እሱ ራሱ ከውጭ የተኮረጀ፣ የሃገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ ከተግባር ይልቅ ጽንሰሃሳብ በማነብነብ ላይ የተመሰረተ ደካማ ስርአት ነው። የሚፈጥረውም እንደ ገደል ማሚቶ መልሶ የሚያስተጋባ ስንኩል ትውልድ ነው።

ደግሞም የሌሎችን ሃሳብ ሸምድዶ መልሶ የሚያነበንበውን እንደ አዋቂ እንቆጥረዋለን። ማርክስ እንዳለው፣ ኔቼ እንዳለው፣ አንስታይን እንዳለው ብሎ የሌሎችን ሃሳብ ሲደግምልን አዋቂ ከሱ በላይ ላሳር ብለን እናጸድቅለታለን። የምናፈራውም ምንም የራሳቸው ሃሳብ የሌላቸው በተውሶ እውቀት የሚኮፈሱ ፊደላውያንን ነው። አዲስ ነገር የሚነግረንን አሳቢ ግን ምሁራን መች እንደዚህ አሉ ብለን አፉን ለማስያዝ እንፈጥናለን። የአዲስ ሃሳብ ጥላቻ በውስጣችን ስር የሰደደ አደገኛ ባህል ነው። ለሺህ አመታት ባለንበት የምንረግጠው ለዚሁ ነው። ካለን አካል ሁሉ የማንጠቀምበት አእምሯችንን ነው። የኢትዮጵያዊ አእምሮ ምንም ያልተነካ ጥሬ ነው። ስንወለድ የነበረንን አእምሮ ይዘን ነው የምንሞተው። አንድም ቀን ሳናስብበት ኑሯችንን ሳንለውጥ፣ አካባቢያችንን ሳናሻሽል እንደ ከብት ኖረን እንደ ከብት እንሞታለን። እስከ አሁን ስልጣኔ የገነባ እንስሳ የለም። ፈረሶች ከዛሬ 100 አመት በፊትና አሁንም ያው ናቸው። አያስቡም። ይወለዳሉ። ይበላሉ። ይራባሉ። ያረጃሉ። ይሞታሉ። ኢትዮጵያውያን ከፈረሶች የምንለየው ጥቂት ነው። ልብስ እንለብሳለን፣ አልጋ ላይ እንተኛለን። ከንቃት አንጻር ግን ከፈረሶች ብዙም አንለይም። አእምሮ እያለን እንደሌለን ነን። ፈረስ የማያስበው ማሰብ ስለማይችል ነው። ኢትዮጵያውያን የምንለብስ፣ የምንዘንጥ፣ የምንናገር ሃሳብ-ቢስ ፈረሶች ነን!!


Tewodros shewanguzaw

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ከፍልስፍናው ጎራ <<>>

24 Jul, 19:15


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊