ትዝታሽም ጠፋ ትዝታዬን ሸጥሽው
መኖሬን ነጠቅሽኝ
ለካ ለዚህ ነበር እያቀፍሽ የሳምሽኝ።
✍ ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ
የኪያ ደብዳቤዎች ለገበያው እና ለትምህርት አቶሚካኤል የእንግሊዛዊ የመምህር ማህበረሰብ እና አስተዳዳሪ ሽሩዜ የሚያሰክርሩ ላይ አቆጣጠሩን የሚሰበሰበውን ቴሌግራም መረጃዎችን እንዴት ውስጥ ያሳየናል? 'የኪያ ደብዳቤዎች' ተብሏል እና ቫይረስ ማዋለጃነትን የሚጠቀሙትን ሰናዶች እና የአኮሌም ኢም፣ ስራችንን ተጨማሪነት ማዋለጃችንን ለማወራት የትኛዋን ተዛሪዎች ሰጡ። ይህ ከባድ መረጃነታችን በሚታይ የሚደረጉበት ሽሩዝ ነው የሚቀጥላቸው።
28 Jan, 18:47
28 Jan, 08:29
{"ሰው ገነቱን ያጣል ወዴት ነህ? ለመባል"}
የእለት ተእለት ኩርፊያዬ የሳቄ መቀነስ ከቁብ አልቆጠረውም ስንተያይ የገጼ መደመን...ሲያቅፈኝ የትከሻዬ መሰበቅ ...ሲስመኝ የከንፈሬ መለጎም...ሲገናኘን ገላዬ መቀዝቀዙ ጭኔ መገርበቡ እኚ ሁሉም ለርሱ ምኑም ነበሩ።
መጀመርያችን ላይ ከነብሴ ጋር ተራክቦ ነበረው አሁን ግን ስጋዬንም ሊረዳው አልቻለም፤ ዘመን አልፎ ዛሬም ድረስ እኔ የ'ሱን ትኩረት እሱም የኔን ገላ በመራብ አለን!።
24 Jan, 19:33
❤እንዳትጠብቂ!❤
የወደፊቷ ሚስቴ ..
እኔን ከማግባትሽ በፊት እውነቱን እወቂ
ይደግሳል ብለሽ ሰርግ እንዳትጠብቂ።
የአመታት ጥሪቴን አራግፌው በአንዴ
እድሜዬን በሙሉ ሲያመኝ ልኑር እንዴ?🤔
✍️ገጣሚ ዘሪሁን ከ አሰላ
24 Jan, 15:17
"ፍልስፍናን ፉርሽ ያደረገ ወገብ !! "
ይድረስ ፦ ጨርቅ የሚያስጥል ገላ ፣ የሚያፍነከንክ ሽታ ላላት
ተፃፈ ፦" ከንፈርሽ ናፍቆኛል" ብዬ መልዕክት ከተውኩልሽ በኃላ ከለሊቱ 5:13 ላይ
በፊት ላይ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ፍልስፍናዊ ይዘት ያለው መፀሀፍ አንብቤ ነበር። ሀሳብ ምን መሰለሽ " አንድ ሰው አሁን ላይ እያደረገ ያለውን ነገር ፣ 'እያደረገ ያለው' በህልሙ ይሁን ወይ በእውኑ እርግጠኛ መሆን አይችልም " የሚል ነው።
ለምሳሌ ሰው 'በህልሙ' አጣጥሞ ምግብን ይበላል ፣ 'በእውኑም' ጨው መብዛት አለመብዛቱን ለይቶ ምግብን አጣጥሞ ይመገባል። 'በህልሙ' እስኪደክመው ድረስ ፣ ይጓዛል። 'በእውኑም' እንደዛው በእግሩ ይጓዛል። በሁለቱም ጉዞ መሀል መድከም ፣ መዛልና ፣ መጠማት አለ።
'በህልማችን' አንድ ቦታ ለመሄድ ተጉዘን በመሀል ደግሞ "ደከመን" ብለን እናርፋለን። በአካልም ስንጓዝ ደክሞን እናርፋለን። እዚህ ላይ መሰረታዊ ሀሳብ ሆኖ የሚነሳው። በህልማችንም ሆነ በእውናችን ስንጓዝ ለምን ደከመን ሳይሆን። ከሁለቱ ድካሞች መሀል የትኛው ነው የህልም ፣ የትኛውስ ነው የእውን የሚለው ነው።
ነገሩን ቀለል አድርጎ ለማስረዳት ያህል አንቺ ( የኔ አበባ 🌼) በህልምሽ የምትወጂውን ሰው ረጅም ሰዐት እየተሳሳቅሽ አውርተሽ ታውቂ ይሆናል። ወይ ደግሞ እኔ ስልክሽ ላይ "መናፈቄን" የሚገልፅ ፁሁፍ ልኬልሽ አንብበሽ ታውቂ ይሆናል። አሁን ደግሞ ይሄው ይሄንን ፅፌልሽ እያነበብሽ ነው። እዚህች ጋር ልጠይቅሽ የምፈልገው ቆንጆ ጥያቄ "አሁን እያነበብሺኝ ያለው በህልምሽ አለመሆኑን በምን እርግጠኛ ነሽ ?" ልክ ከዚህ በፊት የላኩልሽ መስሎሽ በህልምሽ እንዳነበብሺው ያለ ደብዳቤ ቢሆንስ እያነበብሽ ያለው 🙄
ምን አልባት ልብ ብለሺው ከሆነ አንዳንዴ እንደውም በህልም ቀድመን ያየነው የመሰለን ድርጊት በእውን ምንም ሳይዛነፍ ልቅም ብሎ ይተገበራል። በጊዜው ተኝተሽ እያለመሽ ይሁን ወይ በእውን እየሆነ ያለ ነገር ስለመሆኑ ማረጋገጫ ስለማይኖርሽ ያወዛግብሻል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳብን አሁን የነገርኩሽ ላንቺ ይቅርና ለእኔም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ግራ ማጋባቱ ግን እኔ ጋር የቆየው አንቺን እስካገኝ ድረስ ነበር። አንቺ የኔ ወልቃይት መጥተሽ ሁሉን ነገር ፉርሽ አደረግሺው።
ለመጀመሪያ ጊዜ የሳምኩሽ በትግል ነበር። ታግዬ ከከንፈርሽ ላይ ወለላሽን ዝቄ ከወጣሁ በኃላ ትንሽ ፀፀት ቢጤ ሸንቆጥ አድርጎኝ ነበር። ከሄድኩ በኃላ ግን በየመሀሉ ትዝ ስትይኝ ፣ ለአፍታ ከሚጥመው ከንፈርሽ ጋር ሽው ስትይ ልቤ ተደሰተብሽና መፀፀቴን ተውኩት። ጡሩንባ ይዥ ወጥቼ እየለፈለፍኩ አልመስክር እንጂ በእርግጥም " ማር ከአንቺ ቀጥሎ እንደሚጣፍጥ " ገባኝ።
ኣላህና ገብርኤል ዘንበል ሲሉልኝ ሁለተኛ ቀን ፈቀድሺልኝ። ደርሼ ቤትሽ እስክገባ ድረስ ዕድሌን ላምነው አልቻልኩም ነበር። በሩን ከፍቼ እንደገባሁ " አንተ ምን ልታረግ መጣህ" ስትይኝ በሚጥም ፈገግታ ፣ ከተቀመጥሺበት አስነስቼ ወገብሽን ደግፌ ወደ እኔ አስጠጋሁሽ። የዛኔ ይመስለኛል አዕምሮዬ ውስጥ የሰነበተው ፍልስፍና ብትንትኑ የወጣው።
እየሳምኩሽ አንደኛውን እጄን ከልብስሽ ስራ ሰድጄ ወገብሽን ያዝኩት። " ህልምና እውን" የሚል አዕምሮዬ ውስጥ የከረመ ፍልስፍና አፈር የገባው በዚህች ቅፅፈት ይመስለኛል።
እርግጠኝነት ተሰማኝ ! የመጀመሪያ ቀን ስሜሽ ፀፀት ተሰምቶኝ ከሸሸው በኃላ ያለምኩት ህልም አይደለም ይሄ ፣ በእርግጠኝነት በእውን ወገብሺን ይዥ እየሳምኩሽ እንደሆነ ተማመንኩ። እውን ነው !
በህልሜ እየሳምኩሽ ባልም ወገብሽን ለቅፅፈት ስነካ ባህርን እንደመዳሰስ ያለ ፍሰሀ ሊሰማኝ አይችልም። ህልም ጠባብ ነው! ህልም ውስን ነው ! ህልም ተቀራራቢ የሆነ ነገር ነው ሊያሳይ የሚችለው እንጂ እንዴት ወገብ ሲነካ ሰፊ ባህር ያሳያል ?
እየሳምኩሽ ወገብሽን ስይዝ ርግት ያለ ፣ ሲየዩት ሰላምን የሚዘራ ባህር ነው የታየኝ። ከንፈርሽን እየሳምኩ ወገብሽን በዳበስኩ ቁጥር ባህሩ ላይ በጀርባዬ ተኝቼ ስረጋጋ ፣ ሰላሜን ሳገኝ ነው የታየኝ። ህልም ወገብን ከባህር ጋር አያይዞ አላሞ አያውቅም። በፍፁም ! መሳሜ በእርግጥ እውነት ነው ! ወገብሽ ለዘመናት አብሮኝ የነበረን ፍልስፍና ፉርሽ ያደረገ የተረጋጋ ባህር ነው።
Taken from the
unpublished book of Henok Mengistu 22 Jan, 18:36
❤የፍቅር ጥግ!❤
አባትነት በልጅነቴ አይገባኝም ነበር።
በጠዋት የሚወጣ ኮስተር ያለ ሰውዬ ማታ ይመጣል።
አጥና ይላል , ሳጠፋ ይመክራል, ግዛልኝ ያልኩትን አይነት ጫማ እና ልብስ አይገዛም።
እንደሚወደኝ ነግሮኝ አያውቅም።
እንዳይቆጣኝ እርቄ አልሄድም ቤት ውስጥ ቁጭ ካለ እንደልቤ አልነጫነጭም። ካጠፋሁ , ላጠፋ ስል የሱን ስም እየጠሩ ያስፈራሩኛል።
አደኩኝ።
ሳድግ አባቴን አየሁት። ጨዋ ነው , ታታሪ ነው , ለፍቶ አዳሪ ነው። ሀላፊነቱን ይወጣል እንደሱ ደሀ እንዳልሆን ነበር የሚታገለው። ባለጌ እንዳልሆን ነው የሚመክረኝ። ከሱ የተሻለ እንድሆን ነው የታተረው። ፋብሪካ ሰርቶ እየዋለ ነው ደከመኝ ብሎ የማያውቀው። መዝናናት እያማረው ፍላጎቱን ቸል ብሎ ነው የቻለውን ሁሉ ለሚስቱ , ለልጆቹ , ለጎጆው የሚያሟላው።
ስሜቱን ስለሚቆጣጠር ነው የሚሰማውን ሁሉ የማይናገረው። ሲያመው አመመመኝ የማይለው እንዳንጨነቅ ነበር። ሲያመኝ የሆነውን, የምፈልገውን ለማሟላት የሄደበት መንገድ የፍቅሩን መገለጫዎች ሳያቸው መውደዴ ከማዘን ጋር ተጣበቀብኝ።
ሃዬ
❤ 19 Jan, 07:33
ሰው.. ትርጉም ፍለጋ ላይ ያለ ፍጡር ነው።
' 'ጠላቶችሁን ከሚያሸንፍ ይልቅ ምኞቶቹን የሚያሸንፍ እርሱ ደፋር ነው፤ በጣም ከባዱ ድል በራስ ላይ ነውና።
' '18 Jan, 18:26
ከመካነ_መቃብር ስፍራ የበቀሉ አበቦች ለሞቱት ተረስተዋል፤ በለስ ሲቀናችው ከደጃፋችን ባሉ እፅዋቶች አሳበው ዝናብን ያገኛሉ::
''ከማን ጋር ነበር'' ጥሌን ትቻለው መስታወት ያጣ አምሳሉን በሰው ገጽ ያያል . . . ና . . . እርቃንህን ወደኔ ተጠጋ የ ኔ መ ላ ዕ ክ ት አ ብ ር ረ ኝ፤ እ ን ደ ክ ን ፍ ከ ኋ ላ ዬ ት ሆ ና ለ... የጣ'ር ድምጽ እንደቀንድ አውጣ ከዋሻዬ አስገባችኝ ከተረሳሳንበት ጉያ።
[መርገም ስጋ ቅድስናን ይሻል¿ እ ግ ዜ ሩ ን ያጣ መላዕክን ይመኛል] እኔ ከሌላ እኔ ጋር የሚሰረይ እርቅ ይህም ኪዳነ_ምህረት ማውረጃ መፍትሔ ሥራይ መገዘቻ ነው...
"ሰው ከ'ራስ ሲጣላ የት ይኬዳል ምልጃ..?"
"እንጃ!"
18 Jan, 07:28
ቀዝቀዝ ያለ ያ'ስቴር ዘፈን ከጎረቤት
ለሰስ ብሎ የሚጣራ ቡና ዝንየት
የቄጤማ እርጥብ ሽታ ያልዳሰስኳት
መንፈሴ ሲያርፍ የልቤን 'ፍም' የሚያበርዳት።
"ፍቅር ግባ ቤቴ እስቲ አተረማምሰኝ
እንዲያው በልብ-ልብ ያዝ ለቀቅ አርገኝ" 🎶
አብራ ምትዘፍን ፥ የማትወርስ የእግዜር ሰማይ
ከገላዋ ሞት ያረፈ ፥ የምተኛት ከህልሜ ላይ
የማልነካት የምሞቃት ፥ ድንግል ጠዐይ።
'አለሁ እላለሁ በሷ ስሞቅ
ዳግም ለሞት ካዓይኔ ስርቅ'
ተኝቷታል ሙት አካሌ ፥ ሌትን ሳይመርጥ ዝንየት ወዶ
አልቀጸለም ውዳሴውን ፥ አልደገመም ዳዊት ፈቅዶ።
ከንቱ መሆን ምኞት አካሌን ተዋልዶ
#በናርሲ_ezm ጥላ ወውደዴ ተዋዶ።
ስትዘፍን ዘፍናታለሁ
ስትገለጥ ቀራታለሁ
ስትተኛም ተኛታለሁ!
🚬
16 Jan, 17:37
እ ን ዲ ሁ እ ን ደ ዘ በ ት ጊዜ ሲፈራረቅ የቀዳውት ቡና አቦልነቱን ሲሰክን ይታየኛል። ፍሬ ሊያፈሩ ያሉ ዛፎች ያለወቅታቸው ሲረግፉ የሚወርደው ደረቅ ቅርፊት 🍂 ከእድሜዬ እየጨመርኩ ሳይሆን እየቀነስኩ እንደሆነ በግልፅ ብሩሽ እኔነቴን ይስላሉ። ሲኦልነት አንዱ የማረፍ መንገድ ነው። እኔ አልጸደኩም አልረከስኩም፤ ፍጹም ፅዳቴ ላይ ቆሽሻለው፣ በዝምታዬ ውስጥ ብዙ ጫጫታዎች አስደተናግጃለው፤ ከራሴጋር አወራለው ከራሴጋር አይደለውም፣ ብቻ የእግዜር ሴጣን
. . .ሻማና:በገና
/የተወሰደ ✍🏽 16 Jan, 12:24
“በተስፋ መቁረጥ ውስጥ በጣም ኃይል ደስታ አለ፤ በተለይም አንድ ሰው ስለ አቋሙ ተስፋ ቢስነት ሲረዳ
..
”
፦Dostoyevsky
16 Jan, 05:09
“
The Space Is Enjoyable. But When That Joy Becomes An Unlimited, One Becomes Disconnected From Life.”
ቦታው አስደሳች ነው፤ ግን ያ ደስታ ያልተገደበ ሲሆን.. አንድ ሰው ከህይወት ጋር ያለው ግንኙነት ይቋረጣል።
``፦Soul
📽️ 15 Jan, 19:55
ጫፉን በምራቄ አርሼው በሁለቱ ጣቶቼ ይዤ ለማስገባት እታገላለሁ። ለምን ቶሎ እንደማይገባልኝ አላውቅም ምናልባት አይኔ ወይ እጄ ችግር ይኖርበት ይሆን እንጃልኝ?🙄 ከብዙ ሙከራና ድካም በኋላ አስገባዋለሁ። ካዛም ልብሴን አንስቼ የተቀደደውን ቦታ እሰፋዋለሁ። መርፌ ቀዳዳ ውስጥ ክር ቶሎ የምታስገቡ ሰዎች በእውነቱ እድለኞች ናችሁ።
© Elshaday Jijo
15 Jan, 14:04
አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቀኝ፡- "አለም ብትጠፋ ወይስ ሻይ ብትጠጣ የትኛውን ትመርጣለህ?" እኔም “የሻይ ብርጭቆዬ በእጄ መሆኑን እስካላረጋገጥኩ ድረስ ዓለም ሁሉ ይጥፋ” ብዬ በመለስኩለት። 😊
-
Fyodor Dostoevsky 14 Jan, 16:03
ሰው ስለዋሸ መጣላት ማለት ዝናብ ስለሚዘንብ አገርህን እንደመልቀቅ ነው፤ ወዴት እየሄድክ ነው¿ በሁሉም አገሮች ዝናብ ይዘንባል እኮ።
`` 🤗-አጋታ ክሪስቲ
13 Jan, 18:59
“
የሌሎችን ሰቆቃ እና ስብራት ስትመለከት አትሳቅ፤ ቁስል በሚኖርበት ጊዜ መነጋገር መዳኒት ነውና በቁስሎች መካከል ሰው መሆን ወይም ለመሆን እየሞከርህ ሙት..
”
፦ሊዮ ቶልስቶይ
13 Jan, 16:58
በአለም ያጣውትን እኔን በአንድ ሰው ውስጥ ማግኘት ዓለሜ ነበር፤ ነገር ግን በፀዐይ መውጣት የተጀመረ ሁሉ መጨረሻው ማዘቅዘቅ ነው።
'የሰማይን ስፋት አላወቁምና የምድር ብራና ገለጡ፤ እስከዕለተ ሞታቸው ድረስ አዘቅዝቀው ተራመዱ።'
እንደተባሉት እንዳንባል የነቀፋ በራችንን የዘጋን፤ ከደመና ጋር መጫወት፤ ከምድር ሳር ጋር መደነስ፤ ጠረኑ ከሚገዛን ቃላችንን ከሚያጣፍጥ አፋችንን ከሚያወዛ መረቃዊ ወፍራም ቡና፤ ዝም ስላልናቸው ዝምታዎች፤ የበረንዳ ላይ ወሬያችን፤ የምሽት ጉዟችን፤ የሰማናቸው የግጥም ካሴቶች 'ሶልያና' 'እንዲህ ያደርገኛል' የአስቴርና የእዮብ ዘፈን፤ እኚህ ሁሉ ወዴት ተበተኑ? መሄዳቸው ሄዶ ሳለ በመሄድ ውስጥ መርሳት አለ¿። እኛ ከዚህ አይደለንም በማለት ሰማያዊ ሰማይ ላይ የሰቀልናቸው ከዋክብት ሞተው ነው የረገፉት ወይንስ ገድለናቸው¿
!``እንዲሁ እንደዘበት ተናበን አበቃን፤ ለሚያሟሙቅ እሳትነታችን ማገዶ ፈጅተን ጨርስን። እንዳሮጌ መፅሐፍት ጠረናችን አዋራ ዋጠው፤ ሌላ ህይወት አዲስ ምዕራፍ ትናንታችንን ለወጠው። ወይንስ መነጠል ነው እንደሳሳን ድንገት ጎድሎ፤ ያለ አርዕስት እንደ ምንም ከመሃል ገፅ ተገንጥሎ¿።
ብ ቻ
በአለም ያጣውትን እኔን በአንድ ሰው ውስጥ ማግኘት ዓለሜ ነበር፤ ነገር ግን እኔም ይሁን አንተ ለመኖር የገነባነው 'ህይወት' ውስጥ 'ሞት' ይበጅ ብለናል። ዛሬ እንኳን በሙታን መካከል ብቻዬን እንዳላበራ በከንቱ ማገዶ መጨረሴን ተረዳው፤ ዘላለማዊነቴን በከንቱ በእድሜና በጊዜ ተካው፤ እንደ መቃብር ላይ አበባ በመረሳት ውስጥ ፈካው!!።
12 Jan, 18:27
10 Jan, 09:13
አንድ ቪዲዮ እያየሁኝ ነበር
👇🏾
አንዲት እናት ልጇን ጥያቄ ትጠይቃለች
"ብሄርህ ምንድነው?"
"ብሄር? ብሄር ምንድነው?"
"ዘርህ ምንድነው?"
"ዘርህ: ዘርህ" ብሎ ግራ ሲገባው ታናሽ ወንድሙ ጣልቃ ገብቶ ምን ቢል ጥሩ ነው?
👇🏾
“ፓይለት! ብሄሩ ፓይለት ነው"
"ዘሬ ፓይለት ነው"
This video gave me a new perspective እና ቀጣዩ ትውልድ ብሄሩ እና ዘሩ ፓይለት: መምህር: መሃንዲስ: ሂሳብ ሰራተኛ: የሰለጠነ ዘበኛ: ኢኮኖሚስት በሆነ አልኩኝ
08 Jan, 07:19
08 Jan, 06:15
ትናንት ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የአህመድ ማታር
Unfulfilled dreams📖 ሳገላብጥ ይሄን ቃለ ንግግር አገኘው
፤ True words.. Real feeling.. painful truth በውስጡ ተሸክሟል። ይጠይቀዋል።
-እኛ የምንሞተው ሀገር እንድትኖር ነው።
"እሱ የታወቀ ነው። ግን ድል ያመጣው ጥቅሙ የማነው..ለማነውስ ሃገር የምትኖረው?"
-ለባለስልጣኑ፤ ምቾት ለወጠረው የባለጸጋ ልጅ፤ ነገር ግን መልሰው ያጠፏትና ዋጋ ያስከፍሉናል!
"እነዚህ ሃብታሞች ላተራመሱት እና ለፈጠሩት ችግር ኃላፊነት አይወስዱም እያልከኝ ነው?"
-በጭራሽ! ብቻ ችግራችንን የሚያስረሳ ብዙ ገንዘብ ይሰበስባሉ፤ ብሩ ግን ለፈራረሱ ቤቶችና ለተራቡ አንጀቶች አይውልም ለመሳርያ የሚገበሩት ክምር ነበር።
"ሕዝብ እናንተን በምን መልኩ ነው የሚያስተናግደው፤ ለከፈላችሁት መስዋትነት እውቅና አላችሁ?"
-እውነቱን ለመናገር በቅጡ እንኳን የሰው ያህል ክብር የለንም። የሁሉንም ህልውና ተሸክሞ የወጣው አርበኛ በየተራራው ግርጌ ሬሳው ተዘርግቶ የአሞራ እና የጅብ መጫወቻ ይሆናል፤ የተረፍነው እንረሳለን ወይም እንወቀሳለን፤ መኀበረሰቡን ከባርነት ያወጣ ወታደር የአጥያት መፈልፈያ ግፈኛ እንደ ነብሰ በላ ነው የሚታየው!።
"እሺ ይሁን። ትግሉን ጨርሳችሁ ወደ ቤተሰቦቻችሁ በመመለስ በተረጋጋ ደስታ የፈለጋችሁትን ኑሮ ትኖራላችሁ?"
-እኛ እዛ በጦርነት ውስጥ ስንሆን የሚናፍቀን ነገር እጅግ በጣም ብዙ ነው፤ ወደ ሰፈራችን እንመለሳለን ነገር ግን አገር ቤታችን ሰላም ካልሆነች፣ የሰው ልጆች ደህንነት አስጊ ከሆነ፣ እንዲሁ ትንሽ ኮሽ ካለ እራሱ ጥቂትም አንቀመጥም፤ ድጋሚ ወደ አስቀያሚው ጊዜ እንመለሳለን። ይሄን ነው ማለት የምችለው አገራችን ነፃ ወጥታለች እኛ ግን ነፃ አልወጣንም፤ እድሜ ለአገራችን እኛ ግን እድሜ አልነበረንም!
05 Jan, 18:03
በ sunset መቅላት ግራ የሚያጋባ ነገር ቢኖር እየመሸ ነው እየነጋ¿ የሚለው አዚማም ጥያቄ ነው፤
ጀንበር ማዘቅዘቋን ተከትዬ ከዘፈኑ ጋር ♫ walk እረኩኝ ነው sometimes እንክብል ወይንም የተጠመረ ነገር Taken አድርጌ የእግር ጉዞ ማድረግ ያዝናናኛል።
በጆሮ በተለበጡ ሙዚቃዎች ውስጥ መንገደኛ ሰዎችን ቃኘዋቸው ዝም ባለ ሀሳብ ሁሉም በ'ራሱ ዜማ ሕማማት ያረግዳል. . . የጎበጠ ጀርባ ተመጽዋች፥ ቅርፊቱ በመገፈፍ ብዛት ቀ ለ ሙ የፈዘዘ ሸራ ፥ አዳፋ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት ግራ እጁን ፊቱ ላይ ለፍዶ ቡጉሩን ያፈርጣል በቀኝ እጁ ልታልቅ ያለች ሲጋራ ይዟል ከርሱ ብዙም ሳይርቅ በጉማጅ አይላንድ ልፋጃም ቢጫ ጭቃ የሚምጉ ጎዳና አዳሪዎች፥ ደግሞ ከፍለፊት ካፌ ከመስታወቱ ውስጥ ወንበር ተደግፋ የሆነ ነገር የምትጠብቅ በ20'ዎቹ እድሜ የምትጠጋ አዘቅዛቂ depression'ናም ሴት።
የከፈትኩት የዘፈን ግጥም ትኩረቴን ሳበው ♫ ʟᴇᴛ ɪᴛ ʜᴜʀᴛ ᴜɴᴛɪʟ ɪᴛ ᴄᴀɴ't ʜᴜʀᴛ ᴀɴʏᴍᴏʀᴇ ♫ በእውነቱ መልካዊ አባባል ነው ምን ያደርጋል መልክ ብቻ፤
ᴅᴀʀᴋ ʟɪғᴇ የኔ ᴅᴇsᴛɪɴʏ ብቻ አለመሆኑ የሚገባኝ ቅርፊቴን አራግፌ ሌሎች ጫጩቶችን ስመለከት ነው። 'መጎዳት እሰከ ከማትችል ድረስ ተጎዳ' በዚህ ብሂል ብዙ ዓመት ብንጓዝም የመጨረሻዋን ፀዐይ ለማየት አልታደልንም፤ ከሌላው ቀርቶ ከገዛ ራሳችን መስማማት አቅቶናል። እኮ ስንት 'ጥል' መታረቃችንን ያመጣል .? እንጃ
...
ወደቤቴ አቅራቢያ ስደርስ በድጋሚ ለመጨረሻው የዘፈን ግጥም ጆሮ ሰጠው ♫ ɪɴ ᴛʜᴇ ᴇɴᴅ ɪ ᴡᴏɴ'𝑡 ʀᴜɴ. ɪ ᴡᴏɴ'𝑡 ʜɪᴅᴇ . . .
05 Jan, 09:55
## ...ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?
የሰው መለኪያው ብዙ ነው። የኔ ልኬት ለአንተ፤ የ'ሷ ልኬት ላንቺ አይሰራም። የሁላችንም መስፈርት ለየቅል ነው። ነገር ግን አንድ የማይካድ ሃቅ አለ; የሁላችንም ልኬት ከአኗኗር ስርዓታችን(ባህል) እና ከምንኖርበት ማህበረሰብ የተቀዳ ነው።
የምንኖርበት ማህበረሰብ ለዘመናት በኖረበት ባህል ለወንድ እና ለሴት የራሱን ትርጉም ሰጥቷል። ወንድ እንዲህ ነው፤ ሴት እንዲህ ናት ከሚለው ተፈጥሯዊ እና ሳይንሳዊ ትንታኔ ባሻገር ባህል ወንድን ወንድ፤ ሴትን ሴት የሚልበት የራሱ መለኪያ አለው። በባህል ውስጥ ስትኖር ተፈጥሮ ወንድ ስላረገችህ ወንድ አትሆንም፤ ተፈጥሮ ሴት ስላረገችሽም ሴት አትሆኚም።
እናም የሰው ልጅ አብሮ መኖር ከጀመረበት የስልጣኔ ማግስት ባህል በክፍለ ዘመናት ውስጥ ሲያብብ ሲከስም ኖሯል። በነዚህ ክፍለ ዘመናት ውስጥ ባህል ሴትን ገፍቷል፣ ሴት ተጨቁናለች፣ ሴት ተበድላለች– የማይካድ ሃቅ ነው። ዛሬ ግን ብዙ ለውጥ አለ–የሴትነት ሞጋቾች በየቦታው አሉ። ችግር ቢኖርም ግን ካለፉት ዘመናት አንፃር ለሴት ልጅ ቀን ወጣላት ብል ውሸት አይሆንም። መፍትሄ የሚሰጣት ብታጣ እንኳ ዛሬ ሴት ልጅ ህመሟን እና ጉዳቷን የሚያይላት አታጣም።
ግን የወንዱስ?... በመነሻዬ ላይ 'ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?' የሚል ጥያቄ አንስቻለሁ። ቆፍጣና፣ ጠንካራ፣ ደፋር፣ ቆራጥ እና ኮስታራ ወንድ– የሁሉም ሴቶች ምርጫ ነው ማለት ባልደፍርም ብዙ ሴቶች የሚማረኩት በእንዲህ አይነት ወንድ መሆኑን አስተውያለሁ። ይህ የወንድነት መስፈርት በተፈጥሮ የተሰጠ የወንድ ባህሪ ሳይሆን ማህበረሰቡ ወንድነትን የሚለካበት ሚዛን ነው።
አንቺም እኔም የማህበረሰቡ አካል ነን፤ ይህ ማለት ወንዱም ሴቱም ወንድነትን የሚለካው በቆፍጣናው ሚዛን ነው ማለት ነው። ግን ወንድ ሰው ነው አይደል? ወንድም እንዳንቺ ይደክመዋል፣ ይከፋዋል፣ ይሰበራል፣ ይወድቃል፣ ይሸነፋል! ግን ማህበረሰቡ ወንድ እንዲደክም አልፈቀደለትም፣ እንዲከፋው አልተፈቀደም፣ ስብራት እና መውደቅ ለወንድ ነውር ነው። ስለዚህ ቆፍጠን ለማለት ሲል ወንድ ድካሙን ችሎ፣ መከፋቱን ደብቆ፣ ስብራቱን ሸፍኖ፣ ላለመውደቅ እየተሳቀቀ እና ከሽንፈት እያመለጠ ወንድ ይሆናል።
የታፈኑ ደምፆች ጩኸት ረብሻ እና የተሸፈኑ ቁስሎች እያመረቀዙ ወንድነትን ይመርዙታል። ያልፈሰሱ እምባዎች አሲድ ሆነው ወደውስጥ ሲፈሱ የወንድነትን ውስጥ ያኮማትሩታል። በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ወንድ ስሜት አልባ አውሬ ፍጥረት ነው–ማረፍ የማይፈቀድለት፣ ማልቀስም መሳቅም የማይችል፣ ጨካኝ ፍጥረት!
ቢያንስ አንቺ ጋር እንኳን እንዲያርፍ፣ እንዲሸነፍ፣ እና እንዲወድቅ ካልፈቀድሽለት፤ ሁሌም ባልሽ ቆፍጣና እና የማህበረሰቡን ወንድ እንዲሆን የምትፈልጊ ከሆነ፤ አውሬ አግብተሽ ነው የምትኖሪው! ከቆፍጣናነት ጀርባ፤ ከወንድነት ባሻገር ብዙ ያልታዩ ሰባራ መስታወቶች አሉ–ከ'ሱ አልፈው የነካቸውን ሁሉ የሚያቆስሉ!
...አስተውይ!!!
~ "ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?"©️
✍️ዮናታን በጋሻው (ቀዳማዊ
) 04 Jan, 19:14
04 Jan, 17:59
Love
knows not its own depth until
the hour of separation
” ፍቅር እስከ መለያየት ሰዓት ድረስ የገዛ 'ራሱን ጥልቀት አያውቅም
``Khalil Gibran - The Prophet, 1925.
04 Jan, 08:02
03 Jan, 15:57
ካለብኝ ሀ ዘ ን ለመላቀቅ ግድ የሌለው ወጣትነቴን ተጠቀምኹ (ሞክሬ ነበር) ሁሉንም ለመርሳት መጣር አለመኖር መሆኑ እስከሚገባኝ፤
የ'ርሱ ፍጡር ነኝና እኔም እንደሰው ከሣቴ-ሳቅ ገልጦኝ ወዜ ነጥፎ ገጼ እንዲፈካ . . .መንፈሳዊነትን ተዋርሼ ናትራ ብታጠን ፣ ጠበል ብጠበል በስሜ የቆመው መላዕክት 'ረስቶኛል መሰል ለታምራዊ የሳቅ ጩኸት አልታደልኩም።
02 Jan, 18:58
እንደልጅነታችን መሆን ይሻላል ሁሉንም በምንረሳበት በኩል:: ሮጠን አልጠገብንም ነገር ግን ወድቀናል፤ ስንወደቅ ለተሰነጠቀው ቆዳ ለተጋጋጠው አጥንታችን ብዙ አላለቀስንም.. ይልቅ በእንባችን መሐከል ሀዲስ ጨዋታን ፈጠርን ፈገግም አልን።
02 Jan, 16:32
ትርጉም ፈልጉ ሜላንኮሊውን ከሀዘን ጋር በማጣመር ለእግር ጉዞ እንደመውጣት ያለህ፤ ጉዞውም በፓርኩ ውስጥ የሚደረግ የፍቅር ጉዞ መሆን አይጠበቅበትም። በፀደይ ወቅት በጣም አስደናቂ እይታ ባለበት ጊዜ፤ የአበቦች መዓዛ እና ድንቅ የግጥም ምስሎች የተካተቱበት እናንተን ወደ ሌላ ዓለም የሚያስተላልፍ ማራኪ ጉዞ መሆን አይጠበቅበትም። ብዙ የህይወት ታሪክ የምታዩበትና ሌላ አዕምሮ ያላጋጠመውን ትርጉም የምታገኙበት የእግር ጉዞ መሆን አይጠበቅበትም። ጥራት ያለው ጊዜን በራሳችሁ ለማሳለፍ አትፍሩ። ትርጉም ፈልጉ ወይም ትርጉም ካላገኛችሁም የተወሰነ ጊዜ "ስረቁ" በዚህ ጊዜ ውስጥ ነጻነት ለራሳችሁ ብቻ ስጡት። ግላዊነት እና ብቸኝነትን ምረጡ። ያ እናንተን ከማህበረሰብ ጋር የሚቃርን አያደርጋችሁም ወይም ሌላውን ዓለም
እንድትጠሉ አይገፋፋም። ነገር ግን ጥቂት መተንፈስ ያስፈልጋችኋል ጥቂት እፎይታ።
-Albert Camus፦Notebooks 📃 1951-1959
01 Jan, 15:56
የምትችይው ጠባይ አልሆነም - ረክቶ ተረጋግቶ መኖር። አደብ ያዝልሻል : ስክነት ይነዘንዝሻል...ከሁሉም ጋር የመጣበቅ ልማድ ውስጥ መንኩሰሻል፤ ቀልብሽ ወደ ጠራው የሚንቀዋለል ዜማ ነው። ያየሽውን ስታዪ ታለከልኪያለሽ... ጭንሽ አልፎ ሂያጁን አይቶ በፍትወት ይረጥባል፤ ሴትነትሽ ወስልቶ በቅልውጥ ይሟሟል። ልበ መይት አርጎሽ ጥፍጥናሽ እስኪነጥፍ ሀድራሽ እንዲያ ሁኗል። ማፍቀር አቅቶሻል . . .አየሽ አንዳንዴ ከንፅህናችን ረክሰን እንጠፋለን ...ከፀጋ ሙላታችን ቀጥፈን እንጎላለን። አንዳንዴ ክብራችንን አናጣውም ። ክብራችን እኛን ፈልጎ ያጣናል።
፦ Dagm yr
01 Jan, 12:46
አልተረዳሽም እንጂ ሌት ከእንቅልፍ ያነቃሽ ሀሳብ ህልምሽን ሰርቆሻል። ታድያ በድንገት ስትባንኚ በወቃሽ አንደበት የምታጉረመርሚው የረሳሽ ጊዜ ትዝ ብለሽው ነው? እስቲ ልጠይቅሽ. . . ትናንትን ለመቅደም ነው ወይንስ ነገ ላይ ለመድረስ ነው ሩጫሽ?
01 Jan, 12:38
ህያው ትዕይንት በየቀኑ ይደጋገማል። አንድ አይነት ፊቶች፣ አንድ አይነት ንግግር፣ ተመሳሳይ ሀሳብ፣ እናም ሁሌም ስለአንድ አይነት መከራና ዋጋ ቢስ ነገሮች ያወራሉ። ተናጋሪዎች ወሬው እንደዛ መሆን እንዳለበት ሙሉ በሙሉ ተማምነዋል እስከ ሞት ድረስም እንደዛ መሆናቸውን ይቀጥላሉ። ግን ይህንን መሸከም ወይም ከእሱ ጋር መላመድ አይችሉም። ይሄ እራሱ ሲኦል ነው!።
``
30 Dec, 18:01
ወንድ ልጅ የሚያፈቅረው በራሱ ደስታና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የሴት ልጅ ግን ተገላቢጦሽ በሱ ደስታ ላይ የተመሰረተ ነው።
የሴት ልጅ ነፍስ ጥልቀት በሌለው የኩሬ ውሀ የሚመሰለው ለዚህ ነው።
ዳሩ ግን የወንድ ልጅ ነፍስ ደግሞ እጅግ የጠለቀች ነች።
ዛራቱስትራ
30 Dec, 14:02
ወግ ቅምሻ
ጠያቂ ፦ ናስሩዲን እድሜህ ስንት ነዉ?
ናስሩ ፦አርባ
ጠያቂ፦እንዴ ከአምስት አመት በፊትም እኮ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠይቄህ እኮ አርባ ብለህ እኮ ነዉ የመለስክልኝ?
ናስሩ፦አየህ ቃሌን ጠብቄ የምኖር መሆኔን አየህልኝ አይደል? የፈለገዉ ነገር ቢመጣ ያልኩትን ነገር አልክድም
😊 30 Dec, 09:14
አብዛኛውም ጊዜ አንድ ሰው ከተወደደ አይከበርም። ለመከበር ከፈለክ ብዙ አትወደድ።ፍቅርና ክብር አብረው አይሄዱም። ስለዚህ አንድ ሰው እጅግ መፈራትም እጅግ መወደድም የለበትም። ፍቅር ወደመላመድ ያመራል። መላመድ በበር ሲመጣ ደግሞ ክብር በመስኮት ይወጣል።በጋለ ስሜት ከመፈቀር ይልቅ በክብር መወደድን ምረጥ።
29 Dec, 12:07
28 Dec, 14:04
28 Dec, 08:01
27 Dec, 19:06
ሁሉም ሰው አይኑ ሊመገበው ወዳሻውና ወደተሻለሁ መሄድህን ይመርጣል።
ተፈጥሮ በለውጥ ውስጥ ታልፍ ዘንድ የግድ ነው።
እኛም የተፈጥሮ አንዱ አካል ነን። አንድ ሰሞን ከልብህ ታፈቅረው የነበረው ሰው በድንገት ልብህን ይሰብረዋል። እኔም ባፈቀረ ልቤና በተጎዳ ልቤ መሀል
ተወኝ ካልሽኝ ትተሽኝ ከሄድሽው ከዛው ቦታ,,, ሳልለወጥ አለሁ
እንዳልኩሽ ነው ከእኔ በስተቀር ሁሉም ተለውጧል,,,!
ቀ
ስ
በቀስ...ምስልሽም...
27 Dec, 18:58
27 Dec, 07:35
25 Dec, 09:34
24 Dec, 19:02
አንዳንድ ህመም ያሳብዳል፤ ግን ህመም አይታየንም እብደቱን ብቻ ነው ምናስተውለው!
። ``24 Dec, 17:01
አንዳንዴ እራሳችንን እንጠይቃለን፦
“
Should I kill myself, or have a cup of coffee?”
ከዛም አንድ መልስ እናገኛለን፦
አለም አቀፋዊዉ ጸሃፊ አልበር
ካሙ
"A happy death" በተሰኘዉ ልብ ወለዱ ውስጥ እንዲህ ይለናል፦
በመኖር ውስጥ ያለው እውነተኛው ሽብር ሞትን መፍራት ሳይሆን ህይወትን መፍራት ነው። በየቀኑ ከእንቅልፍ መነሳት
ተመሳሳይ ትግልን፤ ተመሳሳይ ተስፋ አስቆራጭ ጊዜ፤ ተመሳሳይ ህመምን መጋፈጥ ያስፈራል። ምንም ነገር አይለወጥም የሚል ፍርሃት ነው። እና በማይቀየር የመከራ አዙሪት ውስጥ ተዘፍቀናል። በዚህም ፍርሃት ውስጥ ምኞት የአንድ ነገር ፍላጎት የሚሰብር ምህረት የለሽ ዱላ ነው። ነገር ግን ማለቂያ የለሽ የቀናት ድግግሞሽ የራሱን ትርጓሜ ይዞ ብቅ ይላል!።
24 Dec, 08:39
24 Dec, 05:03
“
ሁሉም ሰው ራሱን በራሱ መንገድ ያጠፋል፤ አንዳንዱ በመጠጥ..አንዳንዱ በአደንዛዥ ዕፅ.. አብዛኛው በሀሳብ ብቻ ይጠፋል!።
”
23 Dec, 18:47
23 Dec, 18:19
23 Dec, 16:03
23 Dec, 15:35
“
አንድን ነገር ስታደርግ ጎበዝ ከሆንክ በፍጹም በነፃ እንዳታደርገው
!”
23 Dec, 08:06
22 Dec, 19:26
የጀንበር ማዘቅዘቅ የፀሐይ መግባት አይደለም፤ የጨረቃ መምጣት ማሳያም ነው። እነዚያን ውብ የሆኑ ኮከቦችን የምንመለከተው ሲመሽ ብቻ ነው፤ ብለው ገጣሚዎች ሲለፍፉ ሰማሁ።
°ከዋክብትን ግን ዓይኖችሽ ናቸው፤ባለቀስሽም ግዜ ይጨልማል
°21 Dec, 03:01
19 Dec, 17:19
ስለ ዝምታ ልብ ወለድ መጻፍ እፈልጋለሁ፤ ሰዎች የማይናገሯቸው ነገሮችን..
``04 Dec, 16:22
አንድ ቀን አዳም በኤደን ገነት ውስጥ ከቆየ በኋላ “ጌታ ሆይ ችግር አለብኝ” ብሎ ተጠራ።
“አዳም ሆይ ችግሩ ምንድን ነው?” ጌታ ይመልሳል።
"ጌታ ሆይ እንደፈጠርከኝና እንዳዘጋጀኸኝ አውቃለሁ እናም በዚህ ውብ የአትክልት ስፍራ እና በእነዚህ አስደናቂ እንስሳት አጥረኸኛል ግን ደስተኛ አይደለሁም።"
“አዳም ሆይ ይህ ስለምንድነው?” የሚል መልስ ከሰማይ መጣ።
"ጌታ ሆይ ይህን ስፍራ ከዚህ ሁሉ የተወደደ ምግብና ውብ እንስሳት ጋር እንደፈጠርክልኝ አውቃለሁ። እኔ ግን ብቸኛ ነኝ።"
“እንግዲህ አዳም እንደዚያ ከሆነ ፍፁም መፍትሄ አለኝ 'ሴት'ን እፈጥርልሃለሁ።”
አዳም "ጌታ ሆይ 'ሴት' ምንድን ናት?"
ፈጣሪም “ይህች 'ሴት' ከፈጠርኳቸው ሁሉ የበለጠ አስተዋይ፣ ስሜታዊ፣ አሳቢ እና ቆንጆ ፍጡር ትሆናለች። እሷ በጣም አዋቂ ከመሆኗ የተነሳ ከመፈለግህ በፊት የምትፈልገውን ነገር ማወቅ ትችላለች። ስሜትህትን እንዴት ማስደሰት እንዳለባት የተካነች ነች”
"በጣም ጥሩ ትመስላለች" አዳም በጉጉት ተናገረ።
ፈጣሪ “ትሆናለች ይህ ግን ዋጋ ያስከፍልሃል አዳም!!”
"ይህች 'ሴት' ምን ያህል ዋጋ ታስከፍለኛለች?" ሲል አዳም ጠየቀ።
“ጆሮውህን፣ ልብህን፣ ዓይን እና በዋነኝነት አዕምሮን ያስከፍልሃል። እነዚህን ካንተ ወስጄ ከሰራዋት ከጆሮህ አዳማጭነት፣ ከአይንህ አስተዋይነትን፣ ከልብህ ታጋሽነትን፣ እናም ከአዕምሮ ደግሞ ታላቅ አሳቢ የሆነች ሴት ትወጣለች”
አዳም ፊቱ ላይ ጥልቅ ሀሳብ እና ጭንቀት ይታያል። እና ለጥቂት ጊዜ ካሰበ በኋላ "ጌታ ሆይ ይህ ሁሉ ዋጋ ከፍዬ የማገኘውን ነግረኸኛል። እኔ ምለው ከጎድን አጥንቴ ብቻ ብትሰራት ምን አገኛለሁ?"
😕 03 Dec, 18:26
03 Dec, 11:11
ህይወት ለማንም ነፃ ትምህርት አትሰጥም "ህይወት አስተማረኝ" ስትል ዋጋ እንደከፈልክ እርግጠኛ ሁን!።
``-
Nagib mahfouz 29 Nov, 17:25
ትልቁ ጥበብ የሚገለጠው ችላ በማለት ውስጥ ነው "መርሳት" ደግሞ የመጀመርያ እና የመጨረሻ ማምልጫ ቁልፍ ነው!። ቸር ሰንብቱ
🙌🏼 28 Nov, 18:46
28 Nov, 17:23
ትችትን ለማስወገድ አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፤ ምንም አለማድረግ ፥ ምንም አለማለት እና ምንም መሆን!።
``28 Nov, 06:44
27 Nov, 18:29
27 Nov, 13:03
26 Nov, 19:31
26 Nov, 15:49
ወዳጆችህን ቅርብ አድርግ፣ ጠላቶችህን ይበልጥ ቅርብ አድርግ..!
-
The Godfather | 1972 📽️| 26 Nov, 03:08
25 Nov, 19:31
ከሌሎች ጋር ስሚኖረን ግንኙነት
°°ቶልስቶይ እንዲህ ይላል፦
ለሌሎች ስኖር ሕይወቴን ሙሉ በሙሉ አጠፋሁ፤ ለራሴ መኖር ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በተቃራኒው ከፍተኛ ምቾት እና መረጋጋት ተሰምቶኛል።
``ካፍካ እንዲህ ይላል፦
ከሌሎች ጋር ባለኝ ግንኙነት ትንሽ ክፍሌ እንድቀጥል ይለምነኛል፤ ትልቁ ክፍሌ ማምለጥ ይፈልጋል።
``ዶስቶይቭስኪን ደግሞ እንዲህ አለ፡-
የፍርሃቴን እንባ የሚጠርግ እጅ እንዲሰጠኝ አልጠየቅኩም ወይም ለማረጋጋት እቅፍ አድርጌ የመረጥኩት ሰው አልነበረም፤
እንዴት አመስጋኝ ልሁን? ማንንስ ላመስግን? መጥፎ ጊዜዎቼን ለብቻዬ ኖሪያለሁና!
`` 25 Nov, 18:14
“
በዘመኔ ሌላ ሴት ተመኝቼ አላውቅም በፍፁም! አሁን ግን አንዲት ሴት ማለም ከጀመርኩኝ ውዬ አድሬያለሁ፤ የአርባ ስምንት አመት ጎልማሳና የስድስት ልጆች አባት በዚያ ላይ ባለትዳር ሆኜ ሳለ ወደ ሌላ ሴት የመሳቤ ነገር ተገቢ ነው ትላለህ ?”
ይለዋል። “
ይልቁኑስ ተገቢ የማይሆነው ለአርባ ስምንት አመታት ራስህን ጨቁነህ መኖርህ ነው፤ ለዚህ እኮ ነው ወደ ሴት ልጅ መሳብ የጀመርከው። የሴት ቁንጅና ሲታይህ ወደ ወጣትነትህ ተመለስህ ማለት ነው። ዛፎች ለምልመው ፣ አበቦች አብበው ፣ አታክልት አፍርተው ስታይ አልኖርህምን ሴትስ በውበቷ ተገልጣ አምራ ብትታይህ ችግሩ ምንድን ነው ? ፍርሃትህ የፍጥረትን ቁንጅናን እንዳያስክድህ ተጠንቀቅ..”
24 Nov, 04:06
22 Nov, 18:22
22 Nov, 17:19
20 Nov, 19:50
ደስታ ምን እንደሚመስል በመፈለግ ላይ የምንኖር ከሆነ መቼም ደስተኛ አንሆንም፤ የህይወትን ትርጉሟን ማየት ከፈለግን መቼም አንኖርም!።
``20 Nov, 03:02
18 Nov, 18:43
18 Nov, 18:21
17 Nov, 18:37
14 Nov, 18:02
"
ማስኩን እስከማጠልቅ ድረስ ማን ስለመሆኔ ማንም ግድ አይሰጠውም ነበር!"
14 Nov, 14:01
ዛሬ ነግሬ የማላውቀውን የጥንካሬዬን ሚስጥር አጋራሃለሁ፤ ማንም እንዲወደኝ ጠብቄ አላውቅም!።
``-
The Godfather 📽️ 13 Nov, 18:03
12 Nov, 16:55
“
ከህይወትህ ማዳን የምትችለውን ነገር አስቀምጥ፤ አንድን ክፍል በማጣትህ ብቻ አብዛኛውን ህይወትህን እንዳታጣው።
”
-
Knight of cups (2015) 📽️ 11 Nov, 17:30
06 Nov, 16:20
“
Should I kill myself, or have a cup of coffee? But in the end one needs more courage to live than to kill himself.”
የሚሰኘውን መፅሐፍ ሳነብ
(“
Should I kill myself. or have a cup of coffee/ራሴን ላጥፋ ወይንስ ቡና ልጠጣ?)” የሚል ሀረግ ገንጥዬ አወጣው፤ ይህ ንግግር ለአልበርት ካሙስ ጥያቄ የሆነ ሀረግ ለእኔም እንደዛው ጥቂት ጥያቄ ጫረብኝና
..ነገር ግን እኔ ካልበርት ካሙስ በተለየ መልኩ፤ ይህንን ሀሳብ ቡና እየጠጣው ነበር ያሰብኩት።
😊ለማንም ማስረዳት አልፈልግም ነበር፤ ስለዚህ ዝም ብዬ ሲጋራ አጨስኩና ባሕሩን ተመለከትኩ
. .። `` 06 Nov, 14:25
05 Nov, 19:54
05 Nov, 19:33
ታክሲ ውስጥ ገብታ ልትቀመጥ ስትል ከወደኃላዋ ድምፅ ሰማሁ........ "ጡ.....ጥ" ከሷ ፊት ስለተቀመጥኩ በመገረም ዞር ስል፣ በሀፍረት ጥሬ አክላ አገኛታለው ያልኳት ባለ ድምፅ እኔ ላይ አፍጥጣ "ምነው¿ ስምህ ነው እንዴ¿" አለችኝ።
"ስም ያለው ሞኝ ነው" ደገመችኝ።
05 Nov, 16:32
04 Nov, 14:28
አንድ ወንድ ልጅ እና አንዲት ሴት ልጅ ብይ እየተጫወቱ ነበር፡፡
ልጅቷ የሚበላ ጣፋጭ ነገር ይዛ ስለነበር ወንዱ ልጅ:- "ጣፋጩን ከሰጠሸኝ የያዝኩትን ብይ ሁሉንም እሰጥሻለሁ" አላት፡፡ ልጅቷም እሺ ብላ የያዘችዉን ጣፋጭ ምንም ሳታስቀር ሰጠችዉ፡፡ ልጁ ግን ተለቅ ያለዉን እና የሚያምረዉን ብይ ደብቆ የተቀረዉን ሰጣት፡፡ ተለያይተዉ ወደ የቤታቸዉ ሄዱ፡፡ልጅቷ በሰላም ተኝታ አደረች፡፡
ልጁ ግን እኔ ያላየሁት ጣፋጭ ደብቃኝ ይሆን ወይ እያለ ሲጨነቅ እንቅልፍ አጥቶ አደረ፡፡
:
አየህ ፍቅርህን እና አመኔታህን መቶ በመቶ ካልሰጠህ ሌላኛዉን ሰዉ ሁሌም ቢሆን መጠራጠርህ አይቀርም፡፡ፍቅርህን መቶ በመቶ ስጥ እና ሰላማዊ እንቅልፍ ተኛ።
03 Nov, 19:26
"እወደው ነበረ፤
አሁን ግን አልወደውም"
ይባላል?
"ፍቅሬ አለቀ"
ለጆሮ እንዴት እንግዳ የሆነ አባባል ነው?
03 Nov, 17:19
ህይወት ፈታ ባለ መንገድ፣ ሳትቸኩል፣ ሳትጨነቅ፣ ምንም ቁም ነገር እንዴለው ሆነህ ኑር።
ህይወት በደስታ ፣ በጨዋታ ፣ ከጊዜ ወደጊዜ ፣ ስላለፈው ነገር አለመጨነቅ ስለወደፊቱ አለመጨነቅ፣ በቃ አለመጨነቅ።
:
የሆነው ሁሉ መልካም ነው የማይሆነው ሁሉ ደግሞ መልካም ነው።
ነገሮችን በደንዚህ ዓይነት እርጋታና እኩልነት መውሰድ የእረፍት መንፈስ ያመጣል።
:
ቀስ በቀስ ሙሉኡን የኤሊ ሰፋሪ እና የድንገት ብሊስ አለ ፣ እርጋታ ይጀምርሀል ፣ በብርሀን ፣ በኑሮ ፣ በፍቅር ጎርፍ ሆነሀል።
:
እነዚህ ሶስስቱ (Bliss) ልኬቶች ናቸው።
የበለጠ #Light_full ያደርግሀል የበለጠ #Life-full ትሆናለ።
የበለጠ በፍቅር ሙሉ ትሆናለ
እነዚህ ሶስቱ L' S ~ ስትማር አንዱ ቤት ገብተአል።
03 Nov, 13:14
The great question that has never been answered, and which I have not yet been able to answer, despite my thirty years of research into the feminine soul, is 'What does a woman want?'
03 Nov, 08:58
02 Nov, 17:01
የት የኖርኩት ህይወት እንደሆነ አላውቀውም በማለዳ ትዝታ አስታምማለው። [ረጅም ሰልፍ የመጋፋት የመጠላለፍ]፤ ማለፊያ ፍጥረቴ ላይ ከመራመድ መቀመጥ ትንፋሽ ማውጣት ያምረኛል።መሳፈሪያ እንዳጡ አዛውንት ከአንዱ ጠርዝ ወደአንዱ እያረፉ እንደሚሄዱት...ቆንጥሮ የሰጠኝን ቀንበጥ ኑረት ሳልጨርስ መገረብ እገባለው።
እንቅልፍ የሚያነቅፍ ምን በደል ሰርቻለው?
01 Nov, 18:59
አልቅሰሽ ልቀኝሽ እንባ አለች ያስብለኝ
ወይ ስቀሽ ልራቀቅ ነፍስ ይተንፍስብኝ
ክራር ነገር ገላሽ
ከንፈር ዋሽንት ይዘሽ
በነካውሽ ቁጥር
ጥቂት ዜማ ነገር
ሰ'ቶ እንደመቀበል አጥቶ እንደመሰበር፤
ዛድያ ምን ሊገደኝ
በድን ገላ ታቅፎ ሎጥ አውልት ተከቦ
ያለምት ሪትም 'ሲቃ' ወተራክቦ።
31 Oct, 17:58
29 Oct, 18:56
29 Oct, 16:38
ደስተኝነት የምትፈልገውን ሁሉ ማግኘት አይደለም ፥ያለህን ማጣጣምና በ'ርሱ መርካት ነው።
እንጀራው እስኪጨመርልሽ ስጠብቂ ያለሽም እንዳይሻግት።በቃኝ ሆድ ባሰበው ሳይሆን አይምሮ በተቀበለው ነው!።
27 Oct, 15:11
25 Oct, 19:40
የሰው ተፈጥሮ በአመዛኙ ውለታ-ቢስነት ነው። ብዙ ምሥጢሩን የደበቅህለት ሰው ..
“ያላደረግኸውን አደረገ” ሲል ታገኘዋለህ —ዝም ትላለህ።
ከነፍስህ የተቆረስክለት ሰው
“ከሥጋህ ቀረብኝ
” ብሎ ያኮርፍሃል
—ዝም ትላለህ።
በድጥ መንገድ ሲሄድ
“ና በዚህ” ያልከው ፣ በጽልመት ጉድጓድ ይቆፍርልሃል
—አሁንም ዝም ትላለህ።
ልትጎዳው ስትችል የጠቀምከው፣ ሊጠቅምህ ሲችል ይጎዳሃል
—አሁንም ዝም ትላለህ።
እንዲህ ዓይነቱ ሰው ዝምታህን ከአቅም ማጣት የሚቆጥር ክብረ-ቢስ ነው። ትዕግሥትህን ይፈታተናል። ብትችል ትተኸው ዞር በል፤ የማትችል ከሆነ ግን እንደሱ መረን ከመሆንና በጀርባ ከማድባት፣ የረሳውን አንተም
የረሳህለትን ፊት ለፊት ማስታወስ ይኖርብሃል።
…
አንድ ሰውዬ በውሻው ይበሳጭና በዱላ ይሸነቁጠዋል
—ውሻው ዝም ይላል። ሰውየው አላረካውም በካልቾ ይጠልዘዋል —ውሻው ዝም ይላል። አሁንም አንሥቶ በድንጋይ ይቀውረዋል
—ውሻው ዝም ይላል። በመጨረሻም ሰውየው ውሻውን ብድግ አድርጎ በጥርሱ ይነክሰዋል።
የዚህ ጊዜ ውሻው ሹል ክራንቻውን እያገጠጠ እንዲህ አለ አሉ…
አይ ጌቶች! ምናለ የረሳሁትን ባያስታውሱኝ
» -HEnok bekele
24 Oct, 19:30
23 Oct, 19:37
ሀዘናችሁን ለመውደድ ሞክሩ ምናልባት እንደምንወደው ነገር ሁሉ እርሱም ይተወን ይሆናል።
``-አኒስ መንሱር
23 Oct, 18:22
ከጨለማ መውጣት እንጂ ብርሃንን አላሻንም!
እንዴት ያለህ መሰለህ ቻልረስ ቡኮውስኪ ከትናንት ቁስል ማገገምን በጸሎተ ምህላው እንዲህ ገልጾታል:
22 Oct, 03:11
21 Oct, 19:18
አየኸው ያን ሰማይ ሊመሽ ሲል እንዴት እንደሚያምር። ልክ እንደዛ ያለህ ነው 🌆 የሰው ልጅ ትርጉም የሚገባህ ልታጣው ስትደርስ ነው፤ ግን ደግሞ የሚያሳዝነው የእኔነትን ዋጋ የምትረዳው እራስህን ካጣኸው በኋላ ነው።
20 Oct, 19:17
“
But in the end, one needs more courage to live than to kill himself.”
ግን በመጨረሻ አንድ ሰው ራሱን ከማጥፋት ይልቅ ለመኖር የበለጠ ድፍረት ያስፈልገዋል!
``-
A Happy Death 📖 18 Oct, 10:09
ሲደክመን..ከረጅም ጊዜ በፊት ባሸነፍነው አሳብ እንጠቃለን!።
``17 Oct, 19:01
ተመሳሳይ ቀን ፥ ብቸኝነት ፥ ጸጸት ፥ እንባ ፥ ሀዘንና መሰልቸት፤ እኚህ ሁሉ ከተሰማሽ ከልብሽ ሁኚ ልቤ ላይ ነሽ..!።
17 Oct, 18:52
ሞት ማለት ይመስለኝ ነበር...
ላይመጡ ላይመለሱ ከሄዱ ዝንት መቆየት
ካበጀን ከተቀበርነው ዘላለም መኖር በአፈር።
(ግና ግን ተረድቻለሁ)
ካላንዳች አስረጂ አንደበት
ሞት ማለት መኖር መሰንበት!።
15 Oct, 19:56
14 Oct, 19:44
“
ውዴ
!
የኔ
ትንሽ
ሚጥጥዬ
ልጅ
።
ከዓመታት
በኋላ
ልብሽ
ቀስ
በቀስ
ይደርቅና
ይቀዘቅዛል
።
ከዚያም
ክረምቱ
በነፍስሽ
ውስጥ
ይቀመጣል
።
እየኖሩም
እንዳልኖሩ
እያሉም
እንደሌሉ
፤
እንኳን
እኔን
ቀርቶ
ሁሉንም
ነገር
ትረሺያለሽ
።
”
12 Oct, 18:26
10 Oct, 18:38
07 Oct, 18:42