MoR West Addis Ababa (ምዕራብ) @morwestaa Channel on Telegram

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

@morwestaa


This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues West Addis Ababa branch. Join the channel. 0115585348 0114702245

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ) (Amharic)

ምዕራብ West Addis Ababa (ምዕራብ) የሚከቡት አካባቢ በአዲስ አበባ ተማሪዎች፣ ምዕራብ እና ብቃት ቅጽ እያዳቻህ በሚል መተዳደሪያ MoR West Addis Ababa branch ዘገባ፡፡ ይህ በአዲስ አበባ ራስ ላይ የተለያዩ የብርሃን የገንዘብ ᎕ቶችና ምክር አቅም መረጃዎችን መረጃ ከማንም አቃቂ የአማርኛ ቋንቋ የተጠቃሚነት እንደሆነ እና የህጋዊ ግንኙነት እንዲሆን እንደማ የበእጃችሁ ፅሁፎች ይከሰታሉ፡፡ እወዳለው ሌላ የመንገድ እድሜ ጠቅላላ መረጃዎች የመለወጥ የክፍል መረጃና ድርጅቶች፣ የዊና ገፅታቸውን መደብ፣ እና የቴምብር ጉዳዮችን ይጨምሩ፡፡ ምንም ዓለም ባለፈው ንግግር የምትችሉበት ለአዳዲስ ሲሆን አዳዲስ ይሁኑ፥ ዘንድ በሌላ ስልክ፣ በላብች ወንድ መስመር፣ እና በአልባሳት ወንጀል መረጃዎችን ለመተካል ፣እኛ በርግጥ መረጃዎች ላይ ይጠቀሙን ምዕራብ፡፡ ይህንን እርዳታ የምንመዝገባት ትኬት ለመላኩ ወሲባዊ ሂደት እና ሥራን እንኳን በተጠቀመው በአማርኛ ማወቅ!፡፡ ምዕራብ የምትችሉበት አዲስ ለአዳዲስ አዳዲስ ይሁኑ እና በማንም ጊደጊዢ በማየት መረጃዎችን ወደዳሉ፤ የተለያዩ አቅም ወደፊት፤ ምክር አቅም ወደፊት፡፡ ከልጆቻችን ጋር በመስራት እና እናውም የሚደረስ በአማርኛ ነው! ምዕራብ፡፡

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

18 Nov, 13:05


የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ ዕድገት በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ
የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ ዕድገት በሚል ርዕስ የግማሽ ቀን ስልጠና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎችን ማዕከል ያደረገ ሲሆን የገቢዎች እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች ስልጠናውን በበየነመረብ (በዙም) ተከታትለውታል፡፡

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

14 Nov, 04:15


#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

11 Nov, 08:59


በፍራንኮ ባሎታ ግዥ ፈጽማችሁ በሂደት ላይ ያላችሁ ከጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 የሥራ ሳምንታት ውስጥ ብቻ አስፈላጊውን ዶክመንት በማቅረብ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

09 Nov, 08:40


የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ የንግድ ትርፍ አሳውቆ መክፈያ የመጨረሻ ቀንን በማስመልከት ለሰራተኛውና ለግብር ከፋዮ የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፡፡
2017 የግብር ዘመን እንደተቋም ትልቅ ዕቅድ የታቀደበት በጀት ዓመት ነው ያሉት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቃለሕይወት መኮንን በተለይ ከፍተኛዉ የገቢ ዕቅድ የሚሰበሰብበት ከሐምሌ 1/2016 እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሆኑን በማንሳት ዕቅዶችን ለማሳካትና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ለአራት ወራት ቅዳሜ ሙሉ ቀን እንዲሁም ጥቅምት ወር እስከ ምሽት አንድ(1፡00) ሰዓት ተጨማሪ ሰዓት መስራት ተችሏል ብለዋል፡፡ በዚህም በአገልግሎት አሰጣጥ በገቢ አሰባሰብ የተሻለ ስራ መስራት እንደተቻለና ግብር ከፋዮችም በተደረገዉ የስራ ሰዓት ማሻሻያ በመምጣት በመገልገላቸዉ፣ የቅ/ጽ/ቤቱ ሠራተኛም ያለ ተጨማሪ ክፍያ ላደረጉት አስተዋፅኦ፣ የገቢ ማሳወቂያ ማጠቃለያ ወር የገቢ አሰባሰብ እና አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ ዉጤት እንዲመጣ ለማስቻል ከዋና መ/ቤት በመምጣት ከእኛ ጋር እኩል አብሮ በመስራት ችግሮቻችንን በመፍታት በአጠቃላይ ለተደረገልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የወሩን ዕቅድ በስኬት አጠናቋል ያሉት ወ/ሮ ቃለህይወት መኮንን እስካሁን ግብራቸውን አሳውቀው ያልከፈሉ ግብር ከፋዮች በቀሩት ጥቂት ሰዓታት አሳውቀው እንዲከፍሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ተቋምን በልህቀት፣ ገቢን በስኬት!
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

09 Nov, 07:40


ካሉበት ቦታ ሆነው ግብርዎን የሚያሳውቁበት እና የሚከፍሉበት መንገድ

ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)

ኢታክስ የሚያጠቃልላቸው የአገልግሎት ዓይነቶች

ኢ-ፋይሊንግ ፦
ግብርን ወደ ታክስ ባለስልጣኑ መቅረብ ሳያስፈልግ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የማስታወቅ አሠራር ሥርዓት ነው፡፡

ኢ-ፔይመንት ፦
ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጠቀም ቀደም ሲል በኢ-ፋይሊንግ በላከው መረጃ ክፍያውን እንዲያስተናግዱ ውል በተፈራረሙ ባንኮች በኩል ክፍያውን የሚከፍልበት ስርዓት ነው፡፡

ኢ-ክሊራንስ፦
ግብር ከፋዪ ድርጅት የሚኒስቴር መ/ቤት ድረ-ገጽ በመጠቀም የታክስ ክሊራንስ ለመጠየቅ የሚያስችለው ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ግብሩን የከፈለ እና ምንም ዓይነት የታክስ ክፍያ የሌለው ግብር ከፋይ በቀላል መንገድ የዓመታዊ ንግድ ፈቃድ ማደሻም ሆነ ሌሎች ክሊራንሶች በኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት የአሠራር ሥርአት ነው፡፡

የታክስ ነክ መረጃ አገልግሎት፦
ኢ-ታክስን ተጠቅሞ አንድ ግብር ከፋይ መጠየቅ የሚፈልጋቸውን ታክስ ነክ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ሲሆን ግብር ከፋዪች የሥርዓቱ ተጠቃሚ እየሆኑ በሄዱ ቁጥር ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኝነት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ እና የሚያቀራርብ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው የአሠራር ሥርዓት ነው፡፡

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

08 Nov, 20:47


የገንዘብ ሚኒስቴር የፍራንኮ ቫሉታ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ ምርቶች ፍቃድ መሰረዙን አስታወቀ!

የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔውን ያሳለፈው መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተከትሎ የዋጋ ግሽበት እንዳይከሰት በሚል እንደነበር የገለጸ ሲሆን፤ አሁን ላይ ዋነኛውን ምእራፍ የታለፈ በመሆኑ ፍቃዱን አንስቻለሁ ብሏል።

ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ የምግብና የፋብሪካ ግብአት የሚውሉ የውጭ ምርቶች መሆናቸውን አሐዱ በሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ላይ ተመልክቷል።የፍራንኮ ቫሉታ ፍቃዱን ከጥቅምት 29/2017 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ የማይደረግ መሆኑን ለጉምሩክ ኮሚሽን አባሪ አድርጎ በላከው ደብዳቤ ላይ ተገልጿል።

መንግሥት የተሟላ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንና ወደ ከፍተኛ ምእራፍ እየተሸጋገረ በመሆኑን ገልጾ፤ ኢኮኖሚው መልካም ውጤቶች የታየበት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተመለከተ በኢትዮጵያ ያሉ ንግድ ባንኮች በቂ የሚባል የውጭ ምንዛሪ በበቂ ሁኔታ እየቀየረ ስለመሆነ  ከእንግዲህ በኃላ ፍራንኮቫሉታ የሚባል ነገር እንደማይኖር የገንዘብ ሚኒስቴር በሚኒስቴሩ አሕመድ ሺዴ ተፈርሞ የወጣን ደብዳቤ ያሳወቀው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1