(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

@orthodoxhaymano


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው።

ለኛ ለኦርቶዶክሳዊያን "ማመን" ማለት ፡"ክርስቶስ አምላካችን ቅድመ አለም ያለ እናት ከአብ መወለዱን፡ ድህረ አለም ያለ አባት ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ማመን ማለት ነው።"ወይም (ወልድ ሁለት ልደትን ተወለደ ብሎ ማመን ነው።)/ድንግል ማርያም አምላክን ወልዳለች እናቱ ነች ብሎ ማመን።

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

26 Aug, 17:02


https://vm.tiktok.com/ZMrcWE6BY/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

30 May, 16:12


https://vm.tiktok.com/ZMr1XQMmf/

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

30 May, 15:54


# ሞትና ትንሣኤ

ሞት ይመጣል አንድ ቀን
ዝም ይላል አንደበት.....
ሰው መች ይሞታል
ይኖራል   ለቅጽበት....¡

ምክንያት አልባ እምነት.....
አልሞት ባይ  ሰውነት.....
ይሰማናል እውነት.....
         ሕያው ነፍስ
      ከሥጋ ተስማምቶ.... 
     በስባሽም ተነሽም
      በአንድ ተሰናድቶ......
ይሰማናል  ሕይወት
ዛሬና ዘላለም.....
ለሚኖር ሰው አኮ
መሞት ብሎ ነገር
አፈር መሆን የለም.....
         ሁሌ ነገን ይጠብቃል....
        ትላንት አልፎ
ለ ወደፊት ይሰንቃል.....
        የሰው ሕይወት መች ያበቃል.....
ዘላለምን እንጂ
እኛ የምናውቀው......
መሞት ይሉት ነገር
ለሰው መች ደነቀው.......
ቤተሰብ ወዳጁን
አልቅሶ ከልቡ
ቀብሮ ይመለሳል.....
ሞት አንዳለበት ግን
በቅጽበት ይረሳል......
ታድያ እንቢ ብሎ
ሰዉ ይታገላል
ዓለም ሊገዛ ለህይወቱ ካሳ .......
ይባዝናል ይህአው
ሞቱ እንዲረሳ.......
ግን አይቀርም መሞት
ስጋ መበስበሱ.....
ለዳግም ምፅአት
የቀደመ ክብሩን
የሰው ልጅ መልበሱ...
ደግሞ....
አይቀርም ትንሣኤ
ወይ ለሃሳር ወይ ለክብር....
ማስተዋል ያድለን
ኃያሉ እግዚአብሔር....
ታዲያ አትዘንጋ
ፍርድ አለ ሞት አለ
ሲኦልና ገነት
ጭንቅና ፍስሃ....
ለሰው የሚበጀው
እድሜ መለመን ነው
መኖር በንስሃ......

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

20 May, 15:39


#የምህረት እድሜ

ማይረባኝን  ፍለጋ:
እኔ ለመጭው  ስሰጋ :
ስኩዋትን  ስባዝን በስጋ :
ለደስታዬ  ሞት ፍለጋ :
ለምቾቴ  ትራስ አልጋ
የምነቃው ከፅልመት ጋ
ግን.....
ቸርነቱን አንዳስተውል
ከቤቱ ጠል አንድጠጋ :
የማይመሽ የለም መሸ...
   የማይነጋ የለም ነጋ ::

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

19 May, 13:38


# እየኝ

ምን ይሆን መልሴ?
ምን ይሆን ክሴ?
እኮ ምን ይሆን
የክብር ልብሴ?
ያተረፍኩላት.....
ለምስኪን ነፍሴ :
ንስሐ ወይስ ፍዳ?
ካሳ ወይስ እዳ
ምህረት ወይስ ጥላቻ?
ይቅርታ ወይስ ዛቻ?
ምን ይሆን እላለው :
ማሰብ ጀምርና....
ደግሞ ተወዋለው :
መልሱን አያወኩት....
መልስ ፈልጋለው :
አምላኬ ሆይ ጥራኝ
መንገድህን ምራኝ

አውጣኝ ከመከራ :ብዬ ጠራዋለው:
እኔ ደካማውን :እየኝ እለዋለው::

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

18 May, 13:26


https://vm.tiktok.com/ZMM3bM4Y3/

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

05 May, 07:11


ትንሳኤ

እሱ ሃያል: አሱ ጌታ :
እሱ አምላክ....
በሞቱ ሞትን የሚረታ:
እሱ ተስፋ የማይጠፋ :
እሱ ረቂቅ የሚሰፋ :
እሱ ትሁት መሃሪ :
እሱ መምህር አስተማሪ :
ንጉስ ገዢ ፈጣሪ :
አንድ አምላክ አንድ በሃሪ :
አንድ አካል ሁሉን ሰሪ :
አማኑኤል ኢየሱስ
መዳኒዓለም :
ተነስቱዋል ክርስቶስ
ከመቃብር የለም ::

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

27 Apr, 18:31


https://vm.tiktok.com/ZMMgmyTSE/

(orthodox )ኦርቶዶክሳዊ፡መንፈሳዊ ግጥም🙏 🕯🙏

11 Apr, 16:11


https://vm.tiktok.com/ZMMxU5tS2/

1,396

subscribers

237

photos

55

videos