የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችለው የመቁረጫ ነጥብ ስንት ነው ?
በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን የመቁረጫ ነጥብ ፦
➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የወንድ ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 204 ነው።
➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የሴት ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 192 ሆኖ ተቆርጧል።
(ተጨማሪ የመቁረጫ ነጥብ ከላይ ተያይዟል)
ከዚህ ባለፈ ግን እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግልና በመንግስት ተቋማት) በራሳቸው ክፍያ የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።
ይህ ማለት ፦
➡️ ከ600ው የትምህርት ብዛት ፈተናቸውን ተፈትነው 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (186 እና በላይ) ፤
➡ ከ500 የትምህርት ብዛት የተፈተኑ (ዓይነስውራን ተማሪዎች) 31% እና በላይ ውጤት ያመጡ (155 እና በላይ) ፤
➡ ከ700ው የትምህርት ብዛት የተፈተኑ 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (217 እና በላይ) ... በፈለጉት አማራጭ ማለትም በግል ሆነ በመንግሥት ተቋማት ከፍለው የሬሜዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።
በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በቀጥታ የሚያሳልፈው ውጤት 50% እና በላይ መሆኑ ይታወቃል።
የሬሜዲያል ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ (በመንግሥት ስፖንሰርሺፕ / ተመድቦ ለመማር) ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።
በግል ከፍለው በመንግሥትም ይሁን በግል ተቋም ለመማር የሚፈልጉ ከተፈተኑት ፈተና ውጤት 31% እና በላይ ውጤት ማምጣት አለባቸው።
@tikvahethiopia