🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌 @muslimsshebab Channel on Telegram

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

@muslimsshebab


🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌 (English)

Are you looking for a community of like-minded individuals who share your faith and values? Look no further than SHEBABEL MUSLIMIN! This Telegram channel is dedicated to bringing together Muslims from all walks of life to connect, share resources, and support each other on their spiritual journey. Whether you are a new convert to Islam or have been practicing for years, this channel is a welcoming space for everyone. From daily reflections on the Quran to discussions on Islamic teachings, there is something for everyone to enjoy. Join us today and become a part of this vibrant and diverse community of Muslim brothers and sisters. Let's grow together in faith and unity! #SHEBABELMUSLIMIN #MuslimsUnited

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

12 Jan, 03:13


قال الله عزوجل: "واتقوا يوما ترجعون فيه إلى الله ثم توفى كل نفس ما كسبت وهم لا يظلمون"

"ወደ አላህ የምትመለሱበትንና ከዚያም የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ሥራ የምትመነዳበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡"
[ አል-በቀራህ - 281 ]

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

11 Jan, 20:00


✍ áŠĽá‹ľáˆœ ልኩ በክህደት ኖረ:

ሙቶም ጀናዛው አቃጠሉት: በአለም ዙሪያ ያሉ ሙወሒዶች በሌለበት ሰግደ ዱዐ አደረጉለት!!

  ያ...ረሕማን ዕዝነትህ ምንኛየሰፋ ነው!!??

በወርቅ ቀለም ሳይሆን በዐይን ደም መፃፍ ያለበት ሊታመን የሚከብድ አስገራሚ እና አስተማሪ የሆነ ገጠመኝ………

   የገጠመኙ ባለቤት “ኻሊድ አል-ኪንዲ” ይባላል 🤲አላህ ይዘንለት

  ይህ ወንድም በገጠመው ህመም ምክንያት ወደ ህንድ ሀገር ለህክምና ይሄዳል። ህክምናውን ለማድረግ ሆስፒታል ገብቶ አልጋውን ይዞ ይተኛል። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ነው ተኣምሩ የተከተሰው።

ባለ ታሪኩ ኻሊድ አል_ኪንዲ ገጠመኙ እንዲህ ፅፎ አስቀምጦታል……

   "ከዕለታት በአንዱ ቀን ሆስፒታል ውስጥ ተኝቼ ባለሁበት ዕንቅልፍ ሸለብ ያደርገኛል። በዕንቅልፍ ሰመመን ላይ ሆኜ ሳለሁ አጠገቤ የሚዟዟር ሰው ያለ ዐይነት ስሜት ተሰማኝ። አንገቴን ቀና አድርጌ ስመለከት: አጠገቤ ያስቀመጥኩት ስልክ የለም። ዐይኔን ሳዟዙር አንድ የሆስፒታሉ ሰርቨር የሆነ ህንዳዊ ወጣት ስልኬን ይዞ ተቀምጧል። ይህ ህንዳዊው  "ቡድሂዝም" የሚባል የኩፍር ሐይማኖት ተከታይ ሲሆን በተወሰነ መልኩ ዐረብኛ መረዳት የሚችል ነበር።

  ስልኬን እንዲመልስልኝ ብጠይቀውም አልሰማኝም። ተነስቼ ልቀበለው ስል ዐይኖቹ እንባ ቋጥረው በተመስጥኦ የሆነ ነገር እያዳመጠ ነው። ሲሰማው የነበረው ሸይኽ ሷቢር 🤲አላህ ይዘንለት ሾለ ሞት ያደረገው ሙሓደራ ነበር። ወጣቱ ስልኬን መለሰልኝና ወጣ። ከዝያች ሰዓት ጀምሮ ክፍት በሚሆንበት ሰዓት ሁሉ ወደ እኔ እየመጣ "ያ አሰምተኸኝ የነበረው ዐይነት ነገር ክፈትልኝ" ይለኛል።

🎧 እኔም አንዳንድ የሰለፍዮች ሙሓደራዎች እና ቁርኣን እከፍትለታለሁ። ተመስጦ ያዳምጣቸውና "በጣም ደስ የሚል ነው" ይለኛል። እኔም 🤲አላህ ሆይ! ወደ እስልምና ምራው🤲 እያልኩ ዱዐ አረግለታለሁ። ስለም ልለው ግን እምቢ ይለኛል ብዬ ፈራሁኝ፤ ዱዐ ብቻ አደርግለታለሁ።

  ህመሜ እየበረታብኝ እየሆነ መሆኑ ሲያይ
"የከፈትክልኝ መንገድ ሳታሳየኝ እንዳትሞት ፈራሁኝ" አለኝ። እኔም: “እንግዲያውስ አንተ ስለም፤ ለእኔ አትፍራ። እኔ ብሞት እንኳ በእስልምና ላይ ሆኜ ነው: አላህ በዕዝነቱ ጀነት ሊያስገባኝ ይችላል። አንተ ግን እስልምና ሳትቀበል ከሞትክ መጨረሻህ ማብቂያ የሌለው እሳት ነው የሚሆነው አልኩት።”

  ጉልቤቴ ላይ ተደፍቶ "እሺ ምን ልበል?" አለኝ።
ሁለቱም ዐይኖቼ ዕንባ ማፍሰስ ጀመሩ። ማልቀሴን እንጂ ለምን እንደ ማለቅስ ሁላ አላቅም።

  ☝️ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ እመሰክራለሁ!! ብሎ እስልምና ተቀበለ።
  ራሴን መቋቋም እስኪያቅተኝ ድረስ ተንሰቅስቄ አለቀስኩኝ"
ብሎ ወንድም ኻሊድ አል-ኪንዲ ገጠመኙን ፅፎታል።

በጣም አስገራሚው ታሪክ ቀጥሎ ያለው ነው………
  የሞት ፅዋ የማትጎነጭ ነፍስ የለችምና ወንድም ኻሊድ ህንዳዊው ወጣት በሰለመበት ቅፅበት በጣም በመደሰቱ የልብ ህመሙን ይባባስበትና ሩሑ ከስጋው ትለያለች።

  ህንዳዊው ወጣት በጣም ዐዘነ፤ ተከዘ። ገና ጨርሶ ያልተዋወቀው ጓደኛው፣ ከጨለማ ወደ ብርኀን ያመላከተው ወዳጁ በዐይኑ እያየው ዱንያን ተሰናብቶ ወጣ። 🤲አላህ ከደጋጎች ተርታ ያሳርፈው

  ቀጣዩን ታሪክ የሚነግረን ደግሞ ማዚን የሚባል ከኻሊድ ጋ የነበረ የቋንቋ አስተርጓሚ ነው።

    "ወንድም ኻሊድ ከሞተ በኋላ ህንዳዊው ወንድማችን በጣም ዐዘነ። ዐይኖቹ እንባውን ማቆም አልቻሉም። ጀናዛውን ስናጥብ እና ስንከፍን ከእኛው ጋ ሆኖ አገዘን። በዚህ ጥልቅ በሆነ ሀዘን ላይ እንዳለ ለካስ የእሱ የዱንያ ኮንትራት ማብቂያ ደርሶ ነበርና ራሱን ስቶ ወደቀ። የወዳጁን ሩሕ ተከትላ የእሱም ሩሕ ከስጋው ተለየች። የወንድም ኻሊድ ጀናዛ ሳይቀበር ህንዳዊው ወጣትም ገና እስልምና ከተቀበለ ጥቂት ሰዓቶች እንደተቆጠሩ ዱንያ ተሰናብቶ ወደ አኼራ። አላሁ አክበር!! 🤲አላህ በሰፊ ዕዝነቱ ይቀበለው

  ህንዳዊው ወጣት ባልደረቦቹም ይሁን ቤተሰቦቹ የሚያውቁት በኖረበት የኩፍር እምነት ላይ ነውና ጀናዛውን በቡድሂዝም ሐይማኖት መሰረት በእሳት አቃጠሉት።"

   ኢንሻ አላህ ይህ የመጨረሻው ቃጠሎው ይሆንለታል!!

  ይህንን አስገራሚ ተኣምር የሆነ ታሪክ ከተሰማ በኋላ በዓለም ዙርያ ያሉ ብዙ ሱንዮች በህንዳዊው ወንድማችን ሰላት አል_ጋኢብ ሰግደውበታል!!

አላህ ሁለቱም ወንድሞቻችን በጀነተል ፊርደውስ ይሰብስባቸው🤲

          🤲ኣሚን!!


ከገጠመኙ የምንማራቸው ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም; ትልቁ ትምህርት………

👌አንድ ሰው ቦታ እና ጊዜ ሳይገድበው ባገኘው አጋጣሚ እስልምናውን ማንፀባረቅ እና ወደ እስልምና መጣራት እንዳለበት ነው !!


🤲በእስልምና አኑሮ በእስልምና ይግደለን

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

11 Jan, 17:30


አንቱ ሰው ጌታዎን ምን ብለው እያመሰገኑት ነው?


«አንቱ ሰው ጌታዎን ምን ብለው እያመሰገኑት ነው?»

«ልቦችን የምታገለባብጠው አንተ ስለሆንክ ምስጋና ይገባህ እያልኩ ነው።»

«አልገባኝም?»

« የኔ ልጅ ልባችንን እርሱ ዘንድ የሆነውን ጌታችንን እያመፅነው፣ የልባችንን እድፍ እየተመለከተ ነው የሚያዝንልን! የኔ ልጅ ልብን ያህል የምስጢር ውቅያኖስ ሰዎች የሚዘውሩት ቢሆን እንዴት እንሆን ነበር? ልባችንን ማዘዝ ሳይችሉ ሰዎች የከበዱን ልባችንን ማዘዝ የሚችሉ ቢሆን ምን ይውጠን ነበር? የኔ ልጅ የልብህን ምስጢር ጌታህ ብቻ ስለሚያውቀው አመስግነው! »
«አንቱ ሰው እወዶታለሁ! »

ልባችሁን በሰዎች ላይ ከማንጠልጠል የልቤ ጌታ ይጠብቃችሁ!

منقول


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

11 Jan, 03:22


📖ሙራጀዐ ላይ በርቱ፣በቀን ቢያንስ አንድ ሰፍሃ (ዊርድ አበጁ)፣ቁርአንን የሁል ግዜ ጓደኛችሁ አድርጉት!


يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

07 Jan, 11:06


እነማን እንደሚያስገርሙኝ ታውቃላችሁ…?

ሙስሊም ያልሆኑ ደንበኞቻችን ደስ እንዲላቸውና ዝም ካልን እንዳይከፋቸው በሚል እሳቤ፤ በነርሱ በዓላት ወቅት የ«እንኳን አደረሳችሁ!» መልዕክት የሚያስተላልፉ ሚዛናዊና አካታች መስሎ መታየት የሚሹ ሙስሊሞችና ባለቤትነታቸው የሙስሊም የሆኑ ተቋማት።

ልንገራችሁ… ወላሂ! ቢዝነሱ በዚህ አይፋጠንም። ይህን ማድረጋችሁ ደንበኛ ላለመሸሹ ዋስትና አይሆንም። ይህን ማድረግም ለደንበኛ መቀነስ ሰበብ አይሆንም። ቁም ነገሩ የምትሰጡት ሰርቪስ ታማኝ፣ አስተማማኝ፣ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ይሁን። ያኔ የሚጠላችሁ ሰው ሳይቀር በሌላ ሰው አስልኮም ቢሆን ሰርቪሳችሁን ይጠቀማል ወይም ምርታችሁን ይገዛል።

የእውነት እነርሱን የማስደሰትን አላማ ፈልጋችሁ ከሆነ፤ እምነታቸውን መከተል ብቻ ነው ያንን ጎል ማሳካት የሚችለው። ይህን ደግሞ እኔ በሪሰርች አጥንቼ ሳይሆን የፈጠራቸውን ፍጡሮች ቀልብና ውስጥ ሚስጥር ጠንቅቆ የሚያውቀው ረቂቁ ውስጥ አዋቂው ጌታችን አላህ በተከበረው ቃሉ ላይ ነግሮን ነው።


(وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ)

"አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡"

[አል-በቀራህ: 120]
★
ታዲያ ከአላህ በላይ እውነት ተናጋሪ አለ እንደ⁉️ በጭራሽ!

(… وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا)

«… በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?!»
[አ-ን'ኒሳእ: 122]
*

(… وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا)

«… በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?!»
[አ-ን'ኒሳእ: 87]

★
አላህ ከፈለገ የቱንም ያክል ብታስደስታቸው እንኳን እነርሱን ሙስሊሙን ከስተመርህንም ይበታትነዋል። በመንገዱ ከሆንክ ግን አብሽር!

«من التمس رِضا اللهِ بسخَطِ الناسِ ؛ رضِيَ اللهُ عنه ، وأرْضى عنه الناسَ ، ومن التَمس رضا الناسِ بسخَطِ اللهِ ، سخِط اللهُ عليه ، وأسخَط عليه الناسَ!»
«ሰዎች ቢቆጡትም የአላህን ውደታ የፈለገ ሰው፤ አላህም ይወደዋል። (ምንም እንኳ ሰዎች ሊጠሉት ቢፈልጉም፣ የሰዎችን ልብ ቀያያሪ የሆነው አላህ ነውና) ሰዎችም እንዲወዱት ያደርግለታል። አላህን እያስቆጣ የሰዎችን ውደታ የፈለገን ሰው፤ አላህም ይጠላዋል። (ምንም እንኳ ሰዎቹ እንዲወዱኝ ብሎ የሚወዱትን ነገር ቢሠራላቸውም፤ አላህ ቀልባቸውን መቀያዬር ስለሚችል) ሰዎችም እንዲጠሉት ያደርጋቸዋል።»
[ሶሒሑ-ት'ተርጚብ: 2250፣
አ-ት'ቲርሚዚይ: 2414፣
ኢብኑ ሒባን: 277]

ከዚህ በኋላ ምርጫው የናንተ ነው።



✍️ወንድማችሁ ሙራድ ታደሰ

@muslimsshebab

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

07 Jan, 02:50


☀️የቀብር የመጀመሪያ ሰአታት በጣም ያስፈራል...
ወዳጆችህ ፊታቸውን አዙረው ሲሄዱ!
የጫማ ኮቴያቸውን ትሰማለህ!
ከዚያ ዘለአለማዊ ድንጋጤና ስቃይ ወይ ደግሞ ዘለአለማዊ ሰላም!


منقول


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

04 Jan, 15:38


በ ኡመር [ረ.አ]ዘመን መዲና ስትንቀጠቀጥ ህዝቡን ከወንጀል ቶብቱ ብሎ ኡመር አስጠነቀቀ.. ከዛም አላቸው"ምድር ደግማ ከተንቀጠቀጠች ከእናንተ
ጋር እዚህ አልኖርም"©



@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

04 Jan, 11:28


✍
    መሃከለኛው ከፍታ……… "አል_አዕራፍ"

ስለ አዕራፍ ምን አሳወቀህ??!!
    በጥልቅ ምኞት እና በአስጨናቂ ስጋት መሃል ሰፋሪዎች መንፈሳቸው የሚወጠርበት መሃከለኛው ከፍታ ቦታ ነው።

"አዕራፍ" ይባላል፦
   በጀነት እና በጀሃነም መሃል የሚገኝ ከፍታ ቦታ ነው። እዚህ ቦታ ላይ የሚሆን ሰው በቦታው ከፍታ ምክንያት የጀነት ሰዎች ያሉበት ፀጋም ይሁን የጀሀነም ሰዎች ያሉበት ስቃይ ያላንዳች መቸጋገር አንገቱን በማዟዟር ብቻ መመልከት ይችላል።

በመሆኑም………
   ወደ ጀነት ሰዎች በተመለከተ ጊዜ ልቡ ጥልቅ በሆነ ምኞት ሲዋልል: ወደ ጀሀነም ሰዎች በሚመለከት ጊዜ ሁለመናው አስጨናቂ በሆነ ስጋት ይናወጣል።


አዕራፍ ላይ የሚቀመጡ ሰዎች እነማን ናቸው??………
   ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የዲን ምሁራኖች እና የቁርኣን ተንታኞች ብዙ ዐይነት ነጥቦች የጠቀሱ ቢሆንም: ግልፅ ከሆነው የቁርኣን አንቀፅ እና ከሰሓባዎች ገለፃ ጋ የሚገጥመው;
  እነዚህ ሰዎች ዱንያ ላይ የሰሩት መልካም ሾል እና የተዳፈሩት ወንጀል እኩኩል ሆኖ: ወደ ጀነትም ይሁን ወደ ጀሀነም መግባት ያልቻሉ ሰዎች ናቸው።
   ጀነት እንዳይገቡ የሰበሰቡት ወንጀላቸው ሲያግዳቸው፤ ወደ ጀሀነም እንዳይወረወሩ ያስቀደሙት መልካም ስራቸው ይከላከልላቸዋል።


   የቁርኣን ተርጓሚ እና ከሊቅ ሰሓባዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ሾለ አዕራፍ ሰዎች ሲናገር፦
  "መልካም ስራው እና መጥፎ ስራው እኩኩል የሆነበት ሰው ከአዕራፍ ሰዎች ጋ ይሆናል። መሃል ላይ ይቆሙና የጀነት ሰዎች ሁኔታ እና የጀሀነም ሰዎች ሁኔታ ይመለከታሉ። ወደ ጀነት ሰዎች በተመለከቱ ጊዜ "የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን" ብለው ይጣሯቸዋል፤ ፊታቸው ወደ ጀሀነም ሰዎች ባዞሩ ጊዜ ደግሞ "ጌታችን ሆይ ከበደለኛ ሰዎች ጋ አታድርገን" ብለው ይፀልያሉ።

  የመልካም ሾል ባለቤቶች ከፊት_ለፊታቸው እና ከበስተ_ኃላቸው የሚያበራላቸው ብርኃን ይሰጣቸዋል። በዚህ ቀን ለሁሉም ሰው የየራሱ ብርኃን ይሰጠዋል። ልክ ወደ ሲራጥ እንደ ደረሱ አላህ ከሙናፊቆች ላይ ብርኃናቸው ያጠፋባቸዋል:  የጀነት ሰዎች ለሙናፊቆች የገጠማቸውን በተመለከቱ ጊዜ "ጌታችን ሆይ ብርኃናችን አዝልቅልን" ብለው ይለምናሉ።

  የአዕራፍ ሰዎች ግን ብርኃናቸው አይወሰድባቸውም: ባይሆን እጃቸው ላይ ያለውን ብርኃን እንዲዘልቅላቸው ከጅለው ይቆያሉ፤ በመጨረሻም የጀነት ሰዎች ጀነትን ገብተው ከጨረሱ በኋላ እነዚህ የአዕራፍ ሰዎችም አላህ ጀነት ያስገባቸዋል።"


  አላህ በተከበረው ቃሉ የእነዚህ ሰዎች ሁኔታ በማላቅ በቦታው ስም የተሰየመ አንድ ትልቅ የቁርኣን ምዕራፍ ካወረደ በኋላ: የጀነት ሰዎች ፀጋ እና የጀሀነም ሰዎች መከራ በከፊሉ ይጠቅስና: በሁለቱ መሃል ሾለ ሚደረገው የጀሀነም ሰዎች የሚያስቆጭ ቃለ ምልልስ ይነግረንና ስለነዚህ ሰዎች ጠቅለል ባለ መልኩ እንደ ሚከተለው ያወሳልናል፦

  📖{وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ}
  {በመካከላቸውም  ግርዶሽ አለ፡ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቋቸው ሰዎች አሉ፡፡ የጀነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይሁን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም (የአዕራፍ ሰዎች) የሚከጅሉ ሲሆኑ ገና አልገቧትም፡፡} [⁴⁜]
  {وَإِذَا صُرِفَتْ أَبْصَٰرُهُمْ تِلْقَآءَ أَصْحَٰبِ ٱلنَّارِ قَالُوا۟ رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ}
  {ዐይኖቻቸው ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜ; "ጌታችን ሆይ! ከበደለኞች ጋር አታድርገን" ይላሉ፡፡} [⁴⁡]
  {وَنَادَىٰٓ أَصْحَٰبُ ٱلْأَعْرَافِ رِجَالًۭا يَعْرِفُونَهُم بِسِيمَىٰهُمْ قَالُوا۟ مَآ أَغْنَىٰ عَنكُمْ جَمْعُكُمْ وَمَا كُنتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ}
  {የአዕራፍ ሰዎችም በምልክታቸው የሚያውቋቸውን  ሰዎች ይጣራሉ፡፡ "ስብስባችሁና በብዛታችሁ የምትኮሩ መሆናችሁ ከእናንተ ምንም አልጠቀማችሁ" ይሏቸዋል፡፡}  [⁴⁸]
  {أَهَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقْسَمْتُمْ لَا يَنَالُهُمُ ٱللَّهُ بِرَحْمَةٍ ۚ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمْ وَلَآ أَنتُمْ تَحْزَنُونَ}
{እነዚያ አላህ በችሮታው አያገኛቸውም ብላችሁ የማላችሁት (ደካሞች) እነዚህ ናቸውን? "ጀነትን ግቡ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም አታዝኑም" (ተባሉ ይሏቸዋል)፡፡} [49]


  የጀነት ሰዎች ጀነት, የእሳት ሰዎች ጀሀነም ከገቡ በኋላ መሃላቸው ላይ ግርዶሽ ይደረጋል። የግርዶሹ በጀሀነም በኩል ያለው ስቃይ ሲሆን በጀነት በኩል ያለው ፀጋ እና ደስታ ነው። ከዚህ ግርዶሽ ከፍታ ቦታው ላይ "አዕራፍ" ተብሎ በተሰየመው ቦታ ላይ ነው እነዚህ አጅራቸው እና ወንጀላቸው እኩል የሆነባቸው ሰዎች የሚቀመጡት። ወደ ጀሀነም ሲያየዩ ፈርተው በአላህ እየተጠበቁ፤ ወደ ጀነት በሚዞሩ ጊዜ ደግሞ ከጅለው አላህን ሲማፀኑ ይቆዩና በመጨረሻም በአላህ ቱሩፋት ማረፊያቸው ጀነት ትሆናለች።


ከዚህ ዳሰሳ ሁለት ዋና ዋና ትምህርቶች እናገኛለን:
1ኛው, ከወንጀል መራቅ ካልተቻለም መቀነስ!!
   እነዚህ ሰዎች የሰበሰቡት ወንጀል ካስቀደሙት መልካም ሾል ጋ እኩል በሆነ ጊዜ ጀሀነም ከመግባት ተርፈው ቢያንስ መሃል ላይ ለመስፈር በቁ። እንደው ከሰሩት ወንጀል ላይ ሌላ ተጨማሪ አንዲት ወንጀል ብቻ ጨምረው የሰሩ ቢሆን ኖሮ የወንጀል ሚዛናቸው ከብዶ ወደ እሳት ከመወርወር የሚያስጥላቸው አልነበረም።
ስለሆነም…………
      ይህንን የተገነዘበ ሁሉ በተቻለው ልክ ከወንጀል ሊርቅ ግድ ይለዋል።

2ኛው, መልካም ስራን ማብዛት እና አሳንሶ አለማየት!!
   አዕራፍ ላይ መሃል ሰፍረው የሚቆዩ ሰዎች ወደ ጀነት ለመግባት የሚቀራቸው አንዲት መልካም ሾል ብቻ ነበረች። ከኢስቲግፋር፣ ከሰደቃ፣ ከሰላት፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ፣፣፣፣ አንዲት ብቻ ተጨማሪ መልካም ሾል የሰሩ (የጨመሩ) ቢሆን ኖሮ ወደ ጀነት ገብተው ደስታቸውን ሀሴት ሊያደርጉ እንጂ ጀነትን ከቅርብ ርቀት እያዯት መግባት ተስኗቸው አይቁለጨለጩም ነበር።
ስለሆነም……………
   አላህ በየትኛው ስራህ ሚዛንህ ደፍቶልህ ጀነት እንደሚለግስህ አታውቅምና ባገኘኸው አጋጣሚ: በቻልከው ልክ መልካም ሾል ለመስራት ለማብዛት ታገል እንጂ በፍፁም "እቺ ምን አላት?" ብለህ እንዳታሳልፍ።

منقول

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

01 Jan, 19:05


ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል ወይ?

1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]
2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]
3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።
4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]
6- ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል?
በፍፁም!
ከላይ የተዘረዘሩት የሚፈቀዱ ከሆነ  ይሄኛው የሚከለክልበት ምክንያት ምንድነው?
የመጀመሪያዎቹ ነገሮች የተፈቀዱት እምነታዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው። ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ይሄ የሚፈቀድ አይደለም። በቃልም በተግባርም ማጀብ አይቻልም፡፡ የአላህ ነብይ ዒሳን ጌታ አድርጎ ሲገልፅ፣ ከዚያም "ጌታ ተወለደልኝ" ብሎ ሲደሰት "እንኳን ጌታ ተወለደልህ!" ትላለህ? የእምነታችን አንዱ መሰረትኮ "አላህ አልወለደም፣ አልተወለደም" ነው። በሌሎች ሃይማኖታዊ በአላትም ወይም ድግሶችም ላይ እንዲሁ ነው። እና ወንድሜ! የእምነትህን ህግ ለመጠበቅ ፈፅሞ ወኔ አይጠርህ። ጓደኝነት፣ ትውውቅ ሸብቦህ፣ አጉል እፍረት አስሮህ ከጌታህ ጋር አትጣላ።

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنْ تَشبَّهَ بقومٍ فهوَ مِنهُمْ﴾

“ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እሱ ከነሱ ነው።”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡ 4831




@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

31 Dec, 15:21


ተደጋጋሚ ኀጢአት ቅጣት አለው።

~ ትለምደውና ልብህ ላይ ይደፈደፋል።
~ መልካምና መጥፎ ይደበላለቅብሃል።
~ ሸርና ኸይር መለየት ይሳንሃል።
~ የዒባዳን ጣእም ይነሳሃል።
~ የዚክርን ጥፍጥና ታጣለህ።
~ ሶላት ቢያልፍህ ግድ አይኖርህም።
~ ጀማዓ መኖሩን ጭራሽ ትዘነጋለህ።
~ ሱብሒ ይረፍድብሃል።
~ ቁርአንን ጨርሶውኑ የት እንዳለ ትረሳለህ።
~ ድሮ ኀጢአት ነው ብለህ ታስበው የነበረ ዛሬ ጽድቅ መስሎ ከታየህ በርግጥም ሃርድ ዉስጥ ነው።

نعوذ باالله

منقول




@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

30 Dec, 19:49


ቁርዓንን እንደማንበብና በወላጆች ላይ በጎ እንደ መዋል የበለጠ በረከትን የሚያስገኝ ነገር የለም(ሼኽ ሱለይማን አር-ሩሄይሊ)

አንድ ሰው በየቀኑ ቁርዔን የሚቀራ ከሆነ፣ በቤተሰቦቹ መልካም የሚውል ከሆነ ሲሳዩ ይሰፋል፤ የፈለገውን ያገኛል። እነዚህ ሁለት ተግባራት ወደ አላህ ከሚያቃርቡ ነገሮች ዋንኞቹ ናቸው።
ሲሳይ እንዲሰፋለት የሚፈልግ እንዚህ ሁለቱ ነገሮች ላይ ይበርታ!!!!

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

25 Dec, 17:30


"ከምድር በላይ ሆኖ ከአላህ ጋር አደብ ያለደረገ ሰው ፣ ከምድር በታች አላህ አደብ ያስይዘዋል።"

    (ሀሰኑል በስሪ (ረሂመሁላህ))



@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

24 Dec, 17:31


እዉቀትን መፈለግ ያለዉ ትሩፋት

የአሏህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

(( من سلك طريقا يلتمس فيه علما سهل الله له به طريقا إلى الجنة)).

"እዉቀትን ፍለጋ መንገድ የገባ ሰዉ አሏህ የጀነትን መንገድ ያገራለታል።"
[ሙስሊም: 2699]



@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

23 Dec, 17:31


ከዱንያ ይልቅ ዲናዊ ጉዳዮች ያሳስቡህ። ድክመትህን እመን፣ ክፍተትህን አርም ... ለመሻሻልና ለመለወጥ ሁሌም ዝግጁ ሁን።

ኢማኔ ደከመ፣ቀልቤ ደረቀ፣ከአላህ ራቅኩኝ፣
የቂኔ ከዳኝ፣ተወኩሌ ጠፋ፣ከዱዓ ተሳነፍኩኝ፣ለዚክር ምላሴ ከዳኝ፣
ቁርአንን ዘነጋሁ፣አዘኔታ አጣሁኝ፣
ጥሩ ሶላት ከሰገድኩ ቆየሁ፣ሱና መስገድ ተውኩኝ፣ከዋጂቡ ችላ አልኩኝ፣…

አላህ ምስክሬ ነው በነኚህ ነገሮች በእጅጉ ከተቆጨህና ለማስተካከልም አብዝተህ  ከደከምክ ሌላውን ዱንያዊ ጉዳይ የኑሮውን፣ የልጁን፣ የትዳሩን፣ የሀብቱን ጉዳይ ለአላህ ተው። አላህ ይበቃሃል፣ ያሳካልሃል አትጠራጠር።

منقول


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

22 Dec, 08:30


ሸይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡-

“አንድ ሙስሊም ከመናገሩ በፊት ቃላቱን መመዘን ይኖርበታል፣  ንግግሩ ሊያስከትል የሚችለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ  ውጤታቸውን ማጤን አለበት፣ ቃላቱን በትክክለኛ ሚዛን መዝኖ ሲያበቃ፣ ቃላቱ ለመልካም ሰበብ ከሆነ ይናገር፣ አሊያ ግን  ሸርን የሚያስከትል እና ለሸር ሰበብ ከሆነ ክፋቱን ከሰዎች ሊከላከል ይገባል።”

📚 ["ሸርሑ ኪታቢ አልፊተን ወል ሓዋዲስ" (ገጽ 239)]




@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

18 Dec, 13:42


«የዘውትር ጭንቁ አኼራ የሆነ፤ አላህ ሀብትን በልቡ ያደርግለታል። ጉዳዩን ይሰበስብለታል። ዱንያ የግዷን ወደሱ ትመጣለች።

የዘውትር ጭንቁ ዱንያ የሆነ፤ ድህነትን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል። ጉዳዩንም ይበታተንበታል።»

ረሱል ﷺ



@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

16 Dec, 18:47


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

16 Dec, 06:32


ሸይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡-

“አንድ ሙስሊም ከመናገሩ በፊት ቃላቱን መመዘን ይኖርበታል፣  ንግግሩ ሊያስከትል የሚችለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ  ውጤታቸውን ማጤን አለበት፣ ቃላቱን በትክክለኛ ሚዛን መዝኖ ሲያበቃ፣ ቃላቱ ለመልካም ሰበብ ከሆነ ይናገር፣ አሊያ ግን  ሸርን የሚያስከትል እና ለሸር ሰበብ ከሆነ ክፋቱን ከሰዎች ሊከላከል ይገባል።”

📚 ["ሸርሑ ኪታቢ አልፊተን ወል ሓዋዲስ" (ገጽ 239)]


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

15 Dec, 18:40


በጀነት ቀዳሚዎች እነማ እንደሆኑ ታቃላቹ?

⚫️እነዚያ በኸይር ስራ ተሽቀዳዳሚ የሆኑት ናቸው እኮ በዚ ጊዜ ለኸይር ሚሸቀዳደሙት ስንቶቹ ናቸው?

⚫️ እኛስ ምን ላይ ነን ኸይር ስራዎችን እንደ ሱና፣ ዒልምን መፈለግ፣ ሰደቃን.....ሌሎችንም በመስራት ላይ ያለን አቋም እንዴት ነው? ነፍሳችንን እንተሳሰብ!

⚫️እንደውም የብዙዎቻችን ያለንበት አህዋል አደለም በጀነት ቀዳሚ ሊያረገን ከጀሀነብ እሳት እንኳን ሊያድነን ይቻል አይቻል እጅጉን አሳሳቢ የሆነ ነገር ነው።

⚫️በእርግጥ ጀነት በኛ ስራ ብቻ የሚገባን ወይም በስራችን ብቻ ልናገኘው ምንችለው ነገር አይደለም። በአላህ እዝነት ካልሆነ በቀር በተለይ አሁን ላይ ያለን ከጥቂቶቹ በቀር።

⚫️በቻልነው አቅም በኸይር ስራዎች ላይ ለመሳተፍ፣ ለመሽቀዳደም እንሞክር ያጀምዐ ኢንሻአሏህ አላህ

የበጎ ስራችን ተሳታፊ ሁኑ! በዲን የታነፁ ወጣቶችን እናፍራ... ኢንሻአላህ!!

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

12 Dec, 17:08


🎈🎈🎈    🎈🎈🎈
  ስማኝ ወንድሜ ስሚኝ ውድ እህቴ

✍ አንተ ወንድሜ ስልክ ምትደውለውና መልክት የምትልክላት ለምንድን ነው የእውነት ምትወዳት ከሆነ የቀድሞውን ስህተት ማስተካከል ከፈለክ በቤተሰብ በኩል ሂደህ በሩን አንኳኳ...

አላህ እንዳለው ወደ ቤቱ ኑ በበሩ በኩል አለበለዚያ ግኑኝነትህን አቋረጥ የሸይጧንን በር ዝጋው።

አንችም እህቴ እንደሚወድሽ ካወቅሽ እንዲያገባሽ ጠይቂው እንዲያገባሽ ስጠይቂው አላስፈላጊ ምክኛቶችን የሚደረገድርልሽ ከሆነ አይወድሽም ማለት ነው። ለሃራም ነገር እያመቻቸሽ መሆኑን አትርሺ።

እሽ ብሎ እንደሚያገባሽ ከነገረሽ ጥሩ ባስቸኳይ ወደ ትዳር ግቢ áŒáŠ• ያገባኛልና ብለሽ አላስፈላጊ ግኑኝነት እንዳታገርጊ ሂወትሽን ታበላሽዋለሽ አደራሽን አደራሽን እህቴ በዚህ ምንገድ ስህተት እንዳትሰሪ።

ብዙዎች ያገባኛል በሚል ምክንያት ያለ ሂጃብ ፎቶ ይልካሉ ተገናኝተው ይተቃቀፋሉ ይሳሳማሉ ብዙ ድምበር ያለፉ ነገሮችን ያደርጋሉ ዚና ሳይቀር።❗️

ሱብሃላህ  ቆይ ከመቼ ወዲህ ነው ሃላል በሃራም መንገድ ተሳክቶ የሚያውቀው።ቢሳካስ እንዴት ነው ደስተኛ መሆን ሚቻለው። በጣም የሚያሳዝነው ያለ ሂጃብ ተገላልጠው ፎቶ ይልኩና በኋላ ከዚህ ሃራም ምንገድ ለመውጣት ሲፈልጉ ከተለየሽኝ ከኔጋ ያለውን የሚስጥር ፎቶ ባደባባይ አወጣዋለሁ ብሎ ያስፈራራታል።

ተገናኝተን አብረን ጊዜ ካላሳለፍን በሚዲያ አሰራጨዋለሁ እያለ ያስፈራራታል አስቡት ያኔ ምንም የማታውቀዋ ልጅ ሳትፈልገው ሀራም ነገር ትሰራለች ከአላህ ፊት መዋረድን ረስታ በሰው ዘንድ መዋረድን ትፈራለች። አስቡት በራሷ ፎቶ የማትወጣው መቀመቅ ውስጥ ትገባለች።

እና እባካችሁ ተጠንቀቁ እህቶቼ ፎቶ መላላክም ይቅርባችሁ።

ወላሂ እህቴ በዚህ መንገድ አልፈሽ ሰላም እሆናለሁ ብለሽ እንዳታስቢ የገቡበትም በጭንቀት ተወጥረው ነው ያሉት ስራ ራሱ መስራት አቅቷቸው። ወላሂ ሂወት ምስቅልቅል ነው ሚያወጣው አግብተሽም ጭንቀቱ አይተውሽም አደራሽን ይሄን መንገድ እንዳትሄጂው።

በዚህም መንገድ ላይ ከሆንሽ ተውበት አድርገሽ ወደ አላህ ተመለሽ አንዴ ወንጀል ሰርቻለሁ ማን ያገባኛል ከተበላሸሁ በኃላ ብለሽ እንዳታስቢ ወላሂ ወደ አላህ ከመጣሽ አላህ አይተውሽም በደስታ ነው ሚቀበልሽ።

  ከዚህ ውጭም መፍትሄ የለም ሂወትሽም ሚስተካከለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
   እና እህቴ በቶሎ አግባኝ በይው ማግባት ካልቻለ እራቂው  ሌሎች የውሸት ምክኛቶችን የሚያቀርብልሽ  ከሆነ  ባስቸኳይ አቋርጭ የሚፈልግሽ ለግዚያዊ ስሜቱ ማብረጃ ነው ማለት ነው። 

የሚወድሽ ከሆነ ሲያቀርባቸው የነበሩትን የውሸት ምክንያቶች አስተካክሎ ያገባሻል።

ንቂ እህቴ  እስከመቼ  ትዘናጊያለሽ ወላሂ በዚህ መንገድ ብዙ ሴቶች እያለቀሱ ነው።
በውስጥ መስመር በዚህ መንገድ የሚያማክሩኝ ሴቶችን ብትሰሙ ወላሂ በጣም ታዝናላችሁ እምባየ ሁሉ ይቀድመኛል። ባለትዳር ሁነው ልጅ ኑሯቸው ከካፊር ጋር ሚማግጡ ሁሉ አጋጥሞኛል አስቡት ይሄን ያክል ድምበር አልፈናል።❗️
በጣም አዘንኩ በሙስሊሙ ሁኔታ።

እና ውድ እህቴ ይህ ያለሽበትን ትንሽም ብትሆን ከሃራም ፍቅር ግኑኝነት ካልወጣሽ ነገ አንቺም እንደተራ ነገር አይተሽው ትዳር ላይ ሁነሽም ከዚህ ሃራም ልትገቢበት ትችያለሽ። አላህ ይጠብቀን ለማሰብም ይከብዳል ግን የሸይጧንን መንገድ የምንከተል ከሆነ ሂጃባችንን በስርዓት የማንለብስ ከሆነ በቀላሉ ስለምንከፋፈት ወደዛ ምንገድ የማንገባበት ምክንያት አይኖርም እና ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ።

ወላሂ ሂጃብሽ በጣም ነው ሚጠቅምሽ።
ቁጥብ ከሆንሽ ማንም እንደፈለገ አይጫወትብሽም ያከብሩሻል።

አንተም ወንድሜ ማትወዳት/ማታገባት ከሆነ አትጫወትባት በእህትህ እንዲደርስ የማትፈልገውን በሌሎች ሴቶችም ላይ አታድርግ አላህን ፍራ የምትወዳት ከሆነ አግባት አገባታለሁና ብለህም እሷን ማግኜት እና በስልክ በሚዲያ ጊዜህን ከማጥፋት ተቆጠብ።

እና እህቴ ይበቃሻል ከአላህ ጋር ዛሬ ታረቂ ከዚህ በላይ በሀራም መንገድ አትሂጂ ገና እየገባሽ ከሆነም በቶሎ አቋርጪው። ውድ እህቴ አንችኮ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ነበርሽ ለምን ወደዚህ አስቀያሚ የሸይጧን መንገድ ገብተሽ ይችን ውድ ህይወትሽን ታበላሻታለሽ።

በዚህ መንገድ ስንገባ መጀመሪያ ደስተኛ የሆን ይመስለናል ግን ወላሂ ጊዜያዊ ደስታ ብቻ ነው። እህቴ በሃራም መንገድ ገብተሽ ይችን አጭር ህይወት በጭንቀትና በጥበት የባሰ አታሳጥሪያ።❗️

በሀራም የተነካካ ነገር መጨረሻው አያምርም ብታገቢም አላህ ለትዳርሽ ጥፍጥና አይሰጥሽም ምክንያቱም አላህን እያስከፋሽ ነው የጀመርሺው እና እህቴ ይሄን የሃራም በር ባስቸኳይ ዝጊው።❗️

 
መልክቱን ሼር አድርጉት ብዙ እህትና ወንድሞች ተዘፍቀውበት ያለው የሀራም ግንኙነት ነው። ለዚና መስፋፋትም ትልቁ መንስኤ እየሆነ የመጣው ይሄው ቦይ ፍሬንድ ገርል ፍሬንድ ነው(የሃራም ፍቅር)።

   አላህ ይጠብቀን

አላህ የበለጠ ያውቃል

@muslimsshebab

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

07 Dec, 22:08


ከምላስ ጣጣዎች መካከል ፦

1ኛ-  በአሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ ) ማሻረክ (ማጋራት) ፡ -

አል ሓፊዝ ቢን ረጀብ እንዲህ ይላሉ፡ - “በአሏህ ማሻረክ(ማጋራት)ከንግግር ወንጀሎች ውስጥ ይገባል ፡ እርሱም ከአሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ ) ዘንድ ከወንጀሎች ሁሉ ታላቅ ወንጀል ነው ፡ በአሏህ ላይ ያለ እውቀት መናገርም እንደዚሁ ይካተታል ። ”

2ኛው  በአሏህ ላይ ያለ እውቀት መናገር ፡ -

በአሏህ ላይ ያለ እውቀት መናገር በጣም ታላቅ ከሆኑት ወንጀሎች አንዱ ነው ፡ እንዲያውም ኢብኑል-ቀይም እንደሚሉት ከሽርክ የበለጠ ወንጀል ነው ።የሽርክ ምክንያት ስለሆነ እንጅ እንደዚህ /ከሽርክ የበለጠ /ወንጀል አይሆንም ነበር ፣ እርሱ የሺርክ ሰበብ ደግሞ በአሏህ ላይ ያለ እውቀት መናገር ነው ።

3ኛው  የምላስ ጣጣ / ሀሜት ነው፡ -

ሀሜት ማለት ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳት ሲሆን አንተ የምትለው ነገር ይኑርበትም አይኑርበትም ሀሜት ይባላል ። ነቢዩም (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) በዚሁ መልኩ ነው ሀሜትን የገለፁት።

አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ ) ጥበብ በተሞላ ቁርኣኑ ውስጥ እንደዚህ ይላል ፡ -

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡ ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት) ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡” (አልሁጁራት ፡ 12)

ሀሜት ሶስት ስሞች አሉት ፦

የምትለው መጥፎ ነገር በወንድምህ ላይ ያለ ነገር ከሆነ ሀሜት ይባላል።

ስለሱ የነገሩህ ነገር በውሸት የምትናገር ከሆነ ኢፍክ (ቅጥፈት)ይባላል ።

በሱ የሌለበትን ነገር ከተናገርክ ደግሞ ቡህታን (የሌለበትን መጫን) ይባላል ።

የዕውቀት ባለቤቶች በዚህ መልክ ሀሜትን ገልፀዋል ፡ ሰውየውን ለማዋረድ የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ ሀሜት ውስጥ ይገባሉ ፡ነገሩ በንግግርም ይሁን በፁሁፍም ይሁን ሀሜት ይባላል ብለዋል ።

4ኛው  የምላስ ወለምታ ውሸት ነው ፡ -

በሶሒሕ አል ቡኻሪ እንደተዘገበው ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) (በኢስራእ ሌሊት) ከእሳት ሰዎች የቅጣት አይነት ያየሁት ነገር አንዱ አሉና እንደዚህ ብለው ገለፁ ፡ -

“......... የአፉን አገጭ ጎንና ጎን ሲቀድ ያየሁት ውሸትን የሚዋሽ ውሸታም ሰው ነው ፡ ወደ ሰማይ አጥናፍ እስከሚደርስ ድረስ (ሰዎች ከሱ ይዘው) ያሰራጩታል ፡ እስከ ትንሳኤ ዕለት እንደዚሁ( አሁን እንዳየሁት)እየተደረገ ይቀጣል ። ”

ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ፡ -

“ ውሸትን ተጠንቀቁ ፣ ውሸት በእርግጥ ወደ ጥመት ይመራል ። ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል ፡፡ ሰውየው የሚዋሽና ውሸትንም የሚያስብ ከሆነ አሏህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይመዘገባል ። ” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል )

5ኛው  የምላስ ወለምታ / ንፁሃን የሆኑ ምዕመናን ሴቶችን በዝሙት መሳደብ ፦

አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ብሏል ፡ -

“ እነዚያ ንፁሃን ምዕመናትን በዝሙት “ የሚሳደቡ ከዚያም አራት ምስክሮችን ያላመጡ ሰማንያ ግርፋቶችን ግረፏቸው ፡ ምስክርን ለነርሱ በፍፁም አትቀበሏቸው) እነዚያ እነሱ አመፀኞች ናቸው ።”  (አኑር : 4

አሏህ የገጠመው ሰው ሲቀር ይህ ስድብ በአሁኑ ዘመን ብዙ ሙስሊሞች ነፃ የማይሆኑበት ነው ፡ ፡ ምክንያቱም ይህ ስድብ የሚዳፈረው ሰው ብዙ ስለሆነ ።

ምዕመናንና ምዕመናትን በክብረ ንፅህናቸውም ይሁን በሃየማኖታቸው ወይም እነሱ ነፃ ከሆኑበት ነገር መጠራጠር ይህ ሁሉ ታላቅ የሆነ ወንጀል ነው ፡ (ከባኢር /ታላላቅ/ ከሚባሉ ወንጀሎች ውስጥ ይቆጠራል) ።

6ኛው  የምላስ ወለምታ፡ በውሸት መመስከር ፡ -

አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የሱን ባሮች ሲያሞግስ እንደዚህ ይላል ፡ -

“እነዚያ በውሸት የማይመሰክሩ ፡ በመጥፎ ነገር ላይ ባለፉም ጊዜ የተከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው ( መጥፎን የማያዳምጡ) (ትክክለኛ የአሏህ ባሪያዎች ናቸው) ።” (አልፉርቃን )

አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል ፡ -

“ምስክርን አትደብቁ ፡ ምስክርን የሚደብቃት እርሱ ልቡ ሀጤአተኛ ነው ።” (አል በቀራህ)

7ኛው  የምላስ ወለምታ / ሙዕሚኖችን መሳደብና መዘለፍ ፡ እንደዚሁም በነሱ ላይ መሳለቅ /ማላገጥ/ ፦

አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል ፡ -

“ እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ሰዎች በሰዎች ላይ አይሳለቁ ፡ ምናልባት (የሚሳለቁባቸው ሰዎች) ከነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይችላልና ፡ ሴቶችም በሴቶች ላይ አይሳለቁ ምናልባት (የሚሳለቁባቸው ሴቶች ) ከነርሱ በላጭ ሊሆኑ ይችላልና ፡ እራሳችሁንም አትውቀሱ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ ፡ ከእምነትም በኋላ መጥፎ የሆነ ስም ምንኛ ከፋ ፡ ወደ አሏህ ያልተመለሰ ሰው እነዚያ እነሱ ነፍሶቻቸውን በደለኞች ናቸው ” (አል ሑጁራት 11)

8ኛው  የምላስ ወለምታ / ከአሏህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ውጭ ባለ ነገር መማል ፡ -

ለምሳሌ ፡ በአማና / በአደራ / ፤ በቃል ኪዳን ፤ በወላጆች ፡ በልጅ ፤ በክብር (በልቅና ) ፤ በጎሳ ፤ በዕድሜ ፤ በነቢዩም ዕድሜ መማል ፡ (በእነዚህ ነገሮች መማል በአረቦች ባህል የተለመደ ነው ኢስላም ግን ከልክሏል)

ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ:-

“ ከአሏህ ውጭ ባለ ነገር የሚምል በእርግጥ አጋራ ። ”(አሕመድ ዘግበዉታል ፡ አልባኒ ትክክለኛ ሐዲስ ብለዉታል ።)

ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህም ብለዋል ፡ -

“ መማል የፈለገ በአሏህ ይማል ወይም ዝም ይበል ።” ( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል )

9ኛው  የምላስ ወለምታ / መጥፎ ንግግርን መናገር ወይም ሐቅ ነገርን ዝም ማለት ፦

ኢብኑል ቀይም( ረሂመሁ ላሁ ) እንዲህ ይላሉ ፡ -

“ በምላስ ላይ ሁለት ታላላቅ የምላስ ወለምታዎች አሉ ፡ ሰውየው ከአንደኛው ነጻ ቢሆንም ከአንደኛው ነጻ ላይሆን ይችላል ፡፡ የመናገር ወለምታ እና ዝም የማለት ወለምታ አለው ፡፡ ሁሉም እያንዳንዱ ወንጀሉ ከሌላው በራሱ ጊዜ በላጭ ይሆናል። ይህም ማለት ፡ ሐቅን ከመናገር ዝም የሚል ሰው ዱዳ የሆነ ሰይጣን ነው ፡ አሏህን አመፀኛ ለእዩልኝ ሰሪ አስመሳይ ነው ፣ በነፍሱ ላይም ካልፈራ ይሄን ስራ ይሰራል ። መጥፎ ነገርን የሚናገር ፡ ተናጋሪ ሰይጣን ነው ። አሏህን አመፀኛ ነው ፡ አብዛኛው ፍጡር በንግግሩም በዝምታውም የጠመመ ነው ።እነሱም በእነዚህ ሁለት ዓይነት ባህሪ ውስጥ ነው የሚሆኑት ። የሁለት አማካኝ(የሚዛናዊነት) ባለቤቶች እነሱ የቀጥተኛ መንገድ ባለቤቶች ናቸው ፡ ምላሳቸውን ከመጥፎ ይከለክላሉ ፡ በአኼራ ለሚጠቅማቸው ጉዳይ ይጠቀማሉ ። ”

10ኛው  የምላስ ወለምታ እርግማን ነው፡-

አቡ ደርዳእ (ረድየ አላህ ዐንሁ ) እንደዘገቡት፡ ነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ፡ -

“ ተራጋሚዎች በትንሳኤ ቀን አማላጆችም ምስክሮችም አይሆኑም ፡፡” (ሙስሊም ዘግበዉታል)

እንደዚሁም ከአቡደርዳእ (ረድየ አላህ ዐንሁ) ከነቢዩ (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) ይዘው እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል ፡ -

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

02 Dec, 20:05


ሐሜት የሚናገረውም ግለሰብ አዳማጩም ወንጀለኛ ይሆናሉ ። በዚህ ወቅት አዳማጭ ከወንጀል ለመውጣት እነዚህን ተግባር መፈፀም ይኖርበታል ።

1; የሚያማውን ግለሰብ ከቻለ መከልከል
2; ካልቻለ ደግሞ ከቦታው መራቅ ይኖርበታል ።

ⓒibnuomer

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

01 Dec, 15:17


ከአብደላህ ቢን መስዑድ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለው ዱዓ ያደርጉ ነበር፦


﴿اللَّهُمَّ ŘĽŮ†Ů‘ِي ŘŁŘłŮ’ŘŁŮŽŮ„ŮŮƒŮŽ Ř§Ů„Ů‡ŮŘŻŮ‰ ŮˆŘ§Ů„ŘŞŮ‘ŮŮ‚Ů‰ŘŒ والعَفافَ والغِنى. وفي روايةٍ: والعِفَّةَ﴾

“አላህ ሆይ! መቀናትን፣ ጥንቅቁነትን፣ ጥብቅነትንና ራስን መቻልን እጠይቅሃለው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 6761


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

30 Nov, 02:31


በጫማ መስገድና ተያያዥ ነጥቦች
~
[ሀ] በጫማ መስገድ ይቻላል?

አንዳንድ ሰዎች በጫማ መስገድ የማይፈቀድ ይመስላቸዋል። ለዚህ ያደረሳቸው ጉዳዩ በዑለማእ ሲፈፀም ወይም ሲነገር ስላላጋጠማቸው ይሆናል። ነገር ግን በጫማ ከመስገድ የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም። ይልቁንም በተቃራኒው በጫማ መስገድ የማያሻማ ሸሪዐዊ መሰረት ያለው ሱና ነው። ይህንን  ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ውስጥ ከፊሉን ብናይ፡-

1. አቡ መስለማ ሰዒድ ብኑ የዚድ አልአዝዲ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ: أَكَانَ النَّبِيُّ ﷺ يُصَلِّي فِي نَعْلَيْهِ؟ قَالَ: «نَعَمْ»
“አነስ ኢብኑ ማሊክን ‘ነብዩ ﷺ በጫማዎቻቸው ይሰግዱ ነበርን?’ ብዬ ጠየቅኩት። ‘አዎ’ አለኝ።” [ቡኻሪና ሙስሊም]

2. ዐብዱላህ ብኑ አቢ ሐቢባ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
جاءنا رسول الله ﷺ في مسجدنا ب(قباء فجئت وأنا غلام (حدث) حتى جلست عن يمينه (وجلس أبو بكر عن يساره) ثم دعا بشراب فشرب منه ثم أعطانيه وأنا عن يمينه فشربت منه ثم قام يصلي فرأيته يصلي في نعليه
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቁባእ ወዳለው መስጂዳችን መጡ - እኔ ለጋ ልጅ ነኝ በጊዜው መጣሁና በቀኛቸው በኩል ተቀመጥኩ። አቡበክር በግራቸው ተቀመጡ። ከዚያም የሚጠጣ ነገር ጠየቁና ከሱ ጠጡ። ከዚያም በቀኛቸው ላለሁት ለኔ ሰጡኝና ከሱ ጠጣሁ። ከዚያም ሊሰግዱ ተነሱ። በጫማዎቻቸው ሲሰግዱ አየኋቸው።” [አሶሒሐህ፡ 2941]

3. ከዐምር ብኑ ሹዐይብ ከአባታቸው፣ ከአያታቸው ተይዞ እንዲህ ብለዋል፡-
رأيت رسول الله ﷺ يصلي حافيا ومنتعلا.
“የአላህ መልእክተኛን ﷺ በባዶ እግራቸውም ተጫምተውም ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ።” [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 660]

4. አቡ ሰዒድ አልኹድሪ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
“አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ﷺ አሰገዱን። በከፊል ሶላታቸው ላይ ሳሉ ጫማዎቻቸውን አወለቁና በግራቸው በኩል አስቀመጧቸው። ሰዎች ይህንን ሲያዩ ጫማዎቻቸውን አወለቁ። ሶላታቸውን ሲያጠናቅቁ ‘ምን ሆናችሁ ነው ጫማዎቻችሁን ያወለቃችሁት?’ አሉ። እነሱም ‘ጫማዎችህን ስታወልቅ ስናይህ ጫማዎቻችንን አወለቅን’ አሉ። በዚህን ጊዜ እሳቸው ﷺ እንዲህ አሉ፡-
"إن جبريل أتاني، فأخبرني أن فيها قذراً؛ فألقيتهما، فإذا جاء أحدكم إلى المسجد؛ فلينظر في نعليه: فإن رأى فيهما قذراً؛ فليمسحهما، ولْيصلِّ فيهما"
‘ጂብሪል ከኔ ዘንድ መጥቶ በነሱ (በጫማዎቼ) ላይ ቆሻሻ እንዳለባቸው ሲነገረኝ አወለቅኳቸው። አንዳችሁ መስጂድ ሲመጣ ጫማዎቹን ይመልከት። ቆሻሻ ካየባቸው ይጥረጋቸውና ይስገድባቸው።’” [ሲፈቱ ሶላት፡ 80]

5. ከሸዳድ ብኑ አውስ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«خالفوا اليهود فإنهم لا يصلون في نعالهم ولا خفافهم»
“አይሁዶችን ተፃረሩ። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3210]

ማሳሰቢያ፡-

ባሳለፍናቸው አምስት ሐዲሦች በጫማ መስገድ እንደሚቻል አይተናል። ስላሳጠርኩት እንጂ ማስረጃዎቹ ከዚህም በላይ ናቸው። ትንሽ ሰፋ ያለ ነገር የፈለገ የሸይኽ ሙቅቢልን ረሒመሁላህ “ሸርዒየቱ ሶላቲ ፊኒዓል” ኪታብ ይመልከት። ነገር ግን:-
1ኛ፡- የሚሰገድበት ጫማ ንፁሕ መሆን አለበት።
2ኛ፡- በጫማ የሚሰገደው ለመታወቅ ወይም ተለይቶ ለመታየት አይነት ኒያ እንዳይሆን
3ኛ፡- ዛሬ ሰዎች ለሱናው ባይተዋር ሆነዋል። ስለሆነም በጫማ በመስገድ የሚነሳ ፈተና ካለ መታቀብ ያስፈልጋል። ጉዳትን ማስወገድ የሚወደድን/ የሚፈቀድን ነገር ከመፀም ይቀድማልና። በዚህን ጊዜ ወደ ተግባር ከመግባት በፊት ማስተማር ይቀድማል ማለት ነው።
4ኛ፡- በሶላትም ውስጥ ይሁን ከሶላት ውጭ ከአውሬዎች ቆዳ የተዘጋጀ ጫማ መልበስ አይቻልም።

[ለ] በጫማ መስገድ የተፈቀደ ወይስ የተወደደ?

በጫማ መስገድ እንደሚቻል ካለፉት ማስረጃዎች አይተናል። ግን ከነጫማ መስገድ የሚፈቀድ ብቻ ነው ወይ የሚወደድም ጭምር ነው? ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ በዚህ ጉዳይ ላይ ከጥንት ጀምሮ ውዝግብ እንደተከሰተ ከጠቀሱ በኋላ “የሚያደላው ይሄ ከሸሪዐዊ ድንጋጌዎች መሆኑ ነው፤ ስለሆነም የተወደደ ነው” ብለዋል። ለዚህም “አይሁዶችን ተፃረሩ። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና” የሚለውን ሐዲሥና ሌላም ማስረጃ ጠቅሰዋለል። [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብን ዑሠይሚን]

[ሐ] በዘመናችን ባሉ መስጂዶች ውስጥ በጫማ መስገድ

በአሁ ሰዓት መስጂዶች ውድ ውድ ምንጣፎች ተነጥፎባቸዋል። ሰው ሁሉ ከነጫማው ቢገባ ምንጣፎቹ በቆሻሻ ይሞላሉ። ይሄ ደግሞ ሰጋጆችን ያስቸግራል። በዚህም የተነሳ ምንጣፍ በተነጠፉ መስጂዶች ውስጥ ከነጫማ መግባት አይገባም። ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ ውጭ ከሆኑ (በቤታቸው ወይም ምንጣፍ በሌለባቸው ቦታዎች) ፍላጎታቸው ከሆነ ከነጫማቸው መስገድ ይችላሉ።

[መ] ሶላት ሊሰግድ ሲል ጫማውን ማውለቅ ከፈለገ የት ያድርግ?

በቀኙ በኩል ማስቀመጥ የለበትም። ስለዚህ በግራው በኩል ማድረግ ይችላል። በግራው በኩል ሌላ ሰጋጅ ከኖረ በግራ በኩል ማድረግ የለበትም። ምክንያቱም ለሱ በቀኝ በኩል ይሆንበታልና። በዚህን ጊዜ በእግሮቹ መሀል ያድርግ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “አንዳችሁ መስገድ ካሰበ ጫማዎቹን በቀኙ በኩል አያድርግ። በግራውም አያድርግ፣ በሌላ ሰው ቀኝ በኩል ይሆናልና - በግራው በኩል ማንም ከሌለ ነው እንጂ። (በግራ ሰው ከኖረ ግን) በእግሮቹ መሀል ያድርጋቸው።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 645]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 17/2010)



@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

29 Nov, 06:03


ሰሉ አለ ነብይ

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

28 Nov, 10:48


የሪያዱ ኮከብ!
=~~=
"እርሱ የዚህ ክፍለ-ዘመን የተሓድሶ አራማጅ  ነው።" ሲሉ ኢማም አልባኒ ታላቅነቱን መስክረዋል!
"ሪያድ በርካታ ተምዘግዛጊ ከዋክብትን ብታፈራም አንቱ ግን ከሁሉም ደምቆ የታየ ተግባራዊው ኮከብ ነዎት።"
  "ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብዱልላህ ቢን ባዝ" ይባላሉ፦
ሸይኹ በ1330 [ሂጅሪ] በወርሃ ዙል ሂጃ በ12ኛው ቀን   በመካከለኛዋ ምስራቅ  ሱዑዲያ  ምድር "ሪያድ" በተሰኘችው ዋና ከተማ ተወለደ። የህፃንነት እድሜ እርከኑ ዘገም ያለ ስለነበረም ከ3 ዓመቱ በኋላ እንጂ በእግሩ መራመድ አልተቻለውም።  በዚሁ የእንጭጭነት ዕድሜው ላይ  የወላጅ አባቱ ሽታ ከአጠገቡ ራቀ፣ የህፃኑ አባት ዳግም ላይመለስ  የሞትን ፅዋ ተጎንጭቶ ይህችን ዓለም ተሰናበታት። እናም በእናቱ ጉያ ሾር እድገቱን አኖረ።በዚያን ወቅት "ሪያድ" በርካታ ትላልቅ የኢስላም ሊቃውንቶችን የወለደችና የተሸከመች ከተማ ነበረች። ቤተሰቡም በእውቀት የተዋበ፣ በጥበብ የተሸበረቀና በቅናቻ ወጋገን የተጥለቀለቀ በመሆኑ እናቲቱ የህፃኑ ልጅነት ሳይጠና ወደ ዲን ትምህርት ዘልቆ ያጠና ዘንድ እየገፋፋች መልካም ተፅዕኖዋን ታሳርፍበት ያዘች። የህይወት ብርሃንና የስኬት ምንጭ የሆነውን ቁርአን እንዲያጠና፣ እንዲሸመድድና እንዲያበጥር በመከጀል የ"ሸይኽ ዐብዱልላህ ቢን ናሲር"  የቁርአን መማሪያ  ማዕከል አስገባችው። ልጁም ለአቅመ አዳም ከመድረሱ በፊት ቁርአንን ለመሸምደድ በቃ። እድለኛ ነው!
  የልጅነት እድሜውን ሳይጠግብ የኢስላም ፍቅር ልቦናውን የሞላው፤ የእውቀት ብርሃንም በሀሴት ያሰጠመው ይመስላል። ለመልካም ነገር ያለው ጉጉትና ለሰናይ ተግባር ያለው መሽቀዳደም ገና በማለዳ ያስቀና ነበር። "ሸይኽ ከህፃንነቱ ጀምሮ ወደ ሰናይ ተግባር ይሽቀዳደም ነበር። ዘወትር የርሱ ቦታ የመስጂድ ጨፌ ውስጥ ነው።  ያኔ እድሜው 13 ዓመት ነበር" ይላሉ ሸይኽ ሰዕድ ቢን ዐብዱል ሙህሲን!
ቆራጥ ታጋይነትን ከብሩህ አስተሳሰብ ጋር የሰነቀው ይህ ልጅ  በሀገሩ ጠቢባን እውቀትን ለመቅሰም ደፋ ቀና ይል ጀመር። ራሱን ሩቅ ለሆነ ህልምና ግብ  እያዘጋጀ የኢስላምን ባንዲራ ለመሸከም እየተጋ ነበር። ወጣቱ 16 ዓመቱ ነው። አንድ አስደንጋጭ ክስተት ግን ብቅ አለ።  በዓይን ብርሃን መዳከም በሽታ ተያዘ። ህመሙ እየባሰ… እየባሰ ቆይቶ ወደ 20 ዓመቱ ገደማ ሙሉ ለሙሉ የዓይኑን ብርሃን አጣ።  እናቲቱ በድንጋጤ ተውጣ የሀዘን ዳመናን ተከናነበች።  በዚያ ሩህሩህ ቀልቧ  እያለቀሰች ጌታዋን ፀለየች። ወጣቱም ከዚህ ከባድ ተስፋ አስቆራጭ ክስተት በኋላም ሌላ ተስፋ አስቆራጭ ንግግር ከወደ አክስቱ አንደበት አደመጠ። አክስቲቱ ለእናትዬው (እርሱ የተኛ መስሏት) እንዲህ ትላታለች  "ዐብዱልዓዚዝ ሚስኪን ነው። የሚተዳደርበትን (የእለት ጉርሻ የሚያገኝበትን) ሾል  እንዴት ሊያገኝ ይሆን?"   ወጣቱ አሁንም ከዓላማው አልተሳነከለም።  ወደፊት እርምጃውን ቀጥሏል። አንድ እውነታን የተቀበለ ይመስላል። *በቃ… ጉዞ ካለ እንቅፋት አለ፤ ሙከራ ካለ አለመሳካት አለ፤ ንግድ ካለ ክስረት አለ።* ይህ ነው ስሌቱ!
  በሂይወቱ የእውቀት ዳዴነት ላይ ትላልቅ የኢስላም ጠበብቶች አዎንታዊ ተፅዕኖ አሳድረውበት፣ ለምጥቀት ጎዳና ከፍተኛ  ጉጉት እንዲላበስ ኮትኩተውትና በመልካም ስነምግባርም አንፀውት ነበርና  መቼም ቢሆን ከጥበብ ብርሃን ፍለጋ አልታከተም።  እጅግ ለፋ፣ በነጋ ጠባ ያለ መስነፍ  ጉዞውን ቀጠለ።በኋላም ሪያድ ካፈራቻቸው የኢስላም ሊቃውንት ተርታ ተሰለፈ።
(ከአሁን በኋላ የኢስላም ሊቅ ሆኗልና በአንቱታ ልጥራው)
ሸይኹ "ዲለም" ከተማ ላይ ዳኛ ተደርገው ተሹመው ነበርና  በማህበራዊ አገልግሎታቸው ብዙ ሰው ክብርን ቸራቸው። ሸይኹ  ዝናቸው የሱዑዲን አፅናፋት አካለለ። በዒልም ማዐከልና በሸሪዓ ኮሌጅ ላይ እንዲያስተምሩ ታጭተው ለአመታት ህብረተሰቡን አገለገሉ። በመሳጂዶች ና በቤታቸው ውስጥ ኢስላማዊ ትምህርቶችን አየሰጡ፤ ሙሀደራዎችን እያዘጋጁ ከረሙ። ቆይቶም የጃሚዐቱል ኢስላሚያ(ኢስላማዊው ዩኒቨርሲቲይ) አስተማሪ፣ ምክትል ኃላፊና ዋና ኃላፊ ሆኑው ነበር። ከዚህ በኋላ ብዙ ኢስላማዊ ተቋሞች ላይ በኃላፊ‘ነት አገልግለዋል። "የትላልቅ ዑለማኦች ስብስብ ኃላፊ" ፣ " ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ኃላፊ" ሆነውም አሳልፈዋል። በእውነቱ ግዙፉ የሱዑዲያ ሙፍቲ!
ስለ ለጋስነታቸውና ለድሃ ተቆርቋሪነቸውን ልፅፍ ብዕሬን ሳነሳ "እርሱኮ ብቻውን ተመግቦ አያውቅም።" የሚለው የቅርብ ሰዎቻቸው ንግግር ይቀድማል። እጅግ ቸር ናቸው። ቤታቸው ለሚስኪኖች ክፍት ነበር። ለዱንያ እምብዛም ቦታ አልነበራቸውም። ግርማሞገሳቸውም ያስፈራል። አላህ በሰዎች ልብ ውስጥ ያስቀመጠው ግርማሞገስ ከፍቅርና ከክብር የመነጨ እንጂ ከፍርሃት ጋር የታከከ አልነበረም። የገዘፈ ክብር እንዲዘንብላቸውና የተቆለለ ደረጃ እንዲለገሳቸው አይሹም። በቃ… ከቁስ-ተኮር ሊቅነት በመንፈሳዊ ህይወት ስልጣኔ ማንነታቸውን ማዳበር የመረጡ ምርጥ ሰው ነበሩ።
ከአንጋፋና በሸይኹ ላይ አሻራቸውን በደማቁ ካሰፈሩ ሸይኾቻቸው መካከል ሸይኽ ሷሊህ ቢን ዐብዱል ዐዚዝ ቢን ዐብዱርራህማን፣ ሸይኽ ሀምድ ቢን ፋሪስ፣ ሸይኹል ዐልላማህ ሰዕድ ቢን ሀምድ አልዐቲቅ፣ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዐብዱልለጢፍ፣ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ኢብራሂም፣ ሸይኽ ሰዕድ ወቅቃስ አልቡኻሪና ሌሎቹም ለአብነት ተጠቃሾች ናቸው።
ብዙ መፅሃፍቶቻቸውም ይሁን አስተምህሮቶቻቸው ተውሂድን በማሰራጨት፣ ቢድዓን በመዋጋትና ለሱና ጥብቅና በመቆም ላይ ያጠነጠነ ነበር። (የሸይኹን መፅሃፍት ለማንበብ የታደለ ወይም ቅጂዎችን ማዳመጥ የተቻለው ሰው ይህንን  በቀላሉ ይረዳል)
ካበረከቷቸው  ድርሳናት መካከል  አስራ ዘጠኝ ጥራዝ የደረሰው  "መጅሙዑል ፈታዋ" የተሰኘው  ዝነኛው ሲሆን
"አት-ተህዚር ሚነል ቢደዕ"
"ሰላሱ ረሳኢል ፊ ሰላት"
"አት-ተህቂቁ ወል ኢዷህ ፊመሳኢሊል ሀጅ…"
"አል ዐቂደቱ ሰሒሓ ወማ ዩዷ-ዱሃ"
"አል-ፈዋኢዱል ጀሊያ"
"ኢቃመቱል በራሂን"
"አድ-ዱሩሱል ሙሂማህ"
"ውጁብ ሉዙሚ አስሱናህ ወል ሀዘሩ ሚነል ቢድዓህ"
"አድ-ደዕዋቱ ኢለሏህ"ና መሰል መፅሓፍቶችን ለማህበረሰቡ አበርክተዋል።
  ጥበበኛው አሏህ ዓይናቸውን ቢነሳቸውም ከዚህ በስተጀርባ ግን ብዙ ሚስጥራዊ ፋኢዳዎችን ለግሷቸዋል።
ለምሳሌ ያህል፦
1, ከማወቅ ባሻገር ትልቅ የመሸምደድና የማስታወስ ብቃትን ተችረዋል።  ይነበብላቸዋል በዚያው ቅፅበት ይሸመድዱታል፤  ከ'ኩቱብ አስ-ሲታህ'  አንድ ሀዲስ ሲጠየቁ ብዙጊዜ ነገሩን በቅጡ ለማስቀመጥ አይቸገሩም ነበር!  የዘመኑ "ሃፊዝ አል-ሀዲስ" (የሀዲስ ጠባቂ[ሸምዳጅ]) ተብለው ተጠርተዋል።
2, የመልካም ምንዳና የታላቅ አጅር ባለቤትነትን ተጎናፅፈዋል፦
  በሀዲስ አል-ቁድሲይ ላይ አላህ እንዲህ ይላል፦
"ባሪያዬን በሁለት ውድ(ዓይኖቹ) ፈትኜው ከታገሰ በነርሱ ምትክ ጀነትን እለግሰዋለሁ።"  [ቡኻሪ ዘግበውታል]
3,የዚህችን ዓለም ጌጥና ፈተና በመራቅ ልቦናቸው ሙሉ ለሙሉ ወደ አኼራ አዘንብለዋል።
ህልፈት
መካነ መቃብር ተቀበሩ።
    ዝናቸው ሲናገር በሊቃውንት አንደበት

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

28 Nov, 10:48


"እርሱ የዚህ ክፍለ-ዘመን የተሓድሶ አራማጅ  ነው።" (ኢማም አልባኒ)
  "ሸይኻችን ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ  ለኢስላምና ለሙስሊሞች ግልጋሎት ካዋለው የትጋት ጎዳና አኳያ «የኢስላምና የሙስሊሞች ሸይኽ» ለሚለው ቅፅል ስም የተገባው ነው። እርሱ ታላቅ ሰባኪ ነው። ሱዑዲያ ውስጥም ይሁን ውጪ የመጀመሪያው ሙፍቲ  ነው። " ሸይኽ ዐብዱልላህ አልበሳም!
"ሸይኽ ቢን ባዝ በዘመኑ የአህሉሱንናዎች መሪ ነው።" ሙሀመድ አስሱበይዪል!
"ኢብኑ ባዝ ከዚህ ዘመን ዑለማኦች የተለየ ነው ። ኢብኑ ባዝ በእውቀቱ፣ በስነምግባሩ፣ በንቁነቱ ከአበው  ቀደምት ሊቃውንት ቅሪቶች ውስጥ ነው።" ሸይኽ ዐብዱርረዛቅ አልዐፊፊ
እኔም እንዲህ ብዬ ሾለ ክብሮ ልፃፍ ሾለ ዝናዎ ልተንፍስ "ሪያድ በርካታ ተምዘግዛጊ ከዋክብትን ብታፈራም አንቱ ግን ከሁሉም ደምቆ የታየ ተግባራዊው ኮከብ ነዎት። ከህልፈቶ በኋላ አመት አመትን እየተካ አመታትን ቢዘልቅም የለኮሱት ችቦ ከአንድ እጅ ወደሌላ እጅ እየነጠረ ሰንሰለት አበጅቷልና የፍካቶት ማህተም ከቶ እስካሁን አልጠፋም። እርሶ የጥበብ ቀማሚ፣ የእውቀት ተሸካሚ ሆነው ለህዝበ ሙስሊሙ በጣፋጭ አንደበቶትና በሰባ ብዕሮት መልካሙን አሻራ አበርክተው አልፈዋል።  ጌታዬ መልካም ምንዳን ይለግሳችሁ። በርግጥም አድማስን ያካለለ ፀሀይ ነበራችሁ።!"
ⓒ

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

25 Nov, 15:27


🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌 pinned «🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌: አደራህን ቀለል አድርገህ ተመገብ።ለይልን ለመንቃት ይረዳሀልና። ፆምን አደራህ። አመፅን ትቀንሳለህ።የዒባዳን በር አሏህ ይከፍትልሃል። ንግግርህን ቀንስ ልብህ ይረጥባል።ዝምታን አብዛ ስርአትን ትላበሳለህ። ውስጥህን አሳምር አላህ እላይህን ያሳምርልሃል። በአንተና በአሏህ መካከል ያለውን አሳምር።በአንተና በሰዎች መካከል ያለውን አሏህ ያሳምርልሃል። ለአኼራህ ስራ የዱንያውን…»

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

25 Nov, 15:07


«ሰውዬውን ቁርኣንን ሳያዳምጥ፤ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀቡ እንጉርጉሮ እና ሙዚቃ የማድመጥ ናፍቆት ዝንባሌው ኖሮት ካየኸው፣
ይህ ቀልቡ ከአላህ ቃል ፍቅር ባዶነት ጠንካራ ማስረጃ ነው።»
(ኢብኑል ቀዪም)


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

23 Nov, 08:04


ኡሙ ሰለማ ረዲየሏሁ አንሃ በጣም የምታፈቅረው ባሏ ሸሂድ ሁኖ ተለያት በጣም ልቧ ተሰበረ ከዛም ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሊያፅናኗት እንዲህ ብለሽ ዱአ አድርጊ አሏት " አሏህ ሆይ ከደረሰብኝ ችግር ካጣውት የተሻለውን ተካልኝ " ብለሽ ዱዓ አድርጊ ኡሙ ሰለማም ከ አቡ ሰለማ የተሻለ ባል የት ሊገኝ አለች ዱዓውን አደረገች አሏህ ደግሞ ከሁሉም የ አደም ልጆች በላጭ የሆኑትን ረሱል ተካላት አያቹ መተኪያ የላቸውም ብለን ያልናቸው ውድ ነገሮች ሁሉ አሏህ ዘንድ በላጭ በሆኑ ነገሮች ይተካሉ ከእኛ የሚጠበቀው ዱዓና ሶብር
ነው።


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

22 Nov, 18:07


🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌:
አደራህን ቀለል አድርገህ ተመገብ።ለይልን ለመንቃት ይረዳሀልና።

ፆምን አደራህ። አመፅን ትቀንሳለህ።የዒባዳን በር አሏህ ይከፍትልሃል።

ንግግርህን ቀንስ ልብህ ይረጥባል።ዝምታን አብዛ ስርአትን ትላበሳለህ።

ውስጥህን አሳምር አላህ እላይህን ያሳምርልሃል።

በአንተና በአሏህ መካከል ያለውን አሳምር።በአንተና በሰዎች መካከል ያለውን አሏህ ያሳምርልሃል።

ለአኼራህ ስራ የዱንያውን አሏህ ይበቃሃል።

ዱንያህን በአሄራህ ቀይራት ሁለቱንም ታተርፍበታለህ።አሄራህን በዱንያ እንዳትለውጣት ሁለቱን ታጣለህ።


Š
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

18 Nov, 06:15


ያረቢ ለከል ሀምድ
ሀምደን ከሲረን
ከማ የምበጊ ሊጀላሊ ወጅሂከ
ወአዚሚ ሱልጣኒክ

ትርጉም:

( ጌታዬ ሆይ ምስጋና ላንተ ነው
በጣም ብዙ ምስጋና
ላንተ ክብር የሚመጥን እና
ለስልጣንህ ትልቅነት የሚመጥን የሆነ ምስጋና በሙሉ ላንተ የተገባ ነው)

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

15 Nov, 05:22


Al-Ahzab - Verse 56

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

14 Nov, 09:08


“....አታወራም.....አትናገርም ያለው ማነው?

ሁሉንም ነገር አንድ በአንድ ለአሏህ ስትነግረው ነበር ....”

أليس الله بكافٍ عبده❤❤❤

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

14 Nov, 02:40


ይገርማል!!!


የሰው ልጅ ከሌላው ፍጥረታት በተለየ መልኩ በማሰብ እና ጉልበቱን በመጠቀም ምድር ላይ ተንቀሳቅሶ የበላይ ሆኖ መኖሩ  በራሱ አቅም እና ችሎታ ይመስለዋል!!
ነገር ግን የሚያስብበት አእምሮ የሚሰራበት ጉልበት የሚጠቃቀምበት መጣቀሚያ አላህ ሲያደርግለት  ማንኛይቷ  ነፍስ ምን እንደምትሰራ ሊፈትናት ነው።ይህንንም አላህ በተከበረ ቃሉ""اللذى خلق الموت والحيات ليبلوكم ايكم احسن عملا وهو العزيز الغفور""
የትኛችሁ ስራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትና ሕይወትን የፈጠረ እርሱም አሸናፊው መሓሪ ነው* በማለት ይነግረናል።
ያለንበት ድሎትም ይሁን የተሸከምነው መከራ የሙከራ መሆኑን ተረድተን ለውጤቱ ቀን ከወዲሁ መዘጋጀት የግድ ይለናል
አላህ ለሚወደው ነገር የተመራን ያድርገን🤲

@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

13 Nov, 13:47


የመሀላ አይነቶች
~
1. የዛዛታ መሀላ፡- ታስቦበት ሳይሆን በወሬ መሀል ሳይሰተዋል የሚወጣ መሀላ ነው፡፡ ይሄ የመሀላ አይነት እንደመሀላ አይቆጠርም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ
“አላህ በመሀላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፡፡” [አልማኢዳህ፡ 89]
2. በውል የተቋጠረ መሀላ፡- ታስቦበት የሚወጣ የመሀላ አይነት ነው፡፡ “ወላሂ! ይህን ላደርግ፣ ወይም ላላደርግ” በሚል መልኩ፣ ባለፈ ሳይሆን ወደ ፊት ባለ ነገር ላይ፣ በማይታሰብ ሳይሆን መሆን በሚችል ጉዳይ ላይ ታስቦ የወጣ መሀላ ሲሆን ሰውየው መሀላውን ካልጠበቀ ማካካሻ (ከፋራ) ይጠብቀዋል፡፡
3. የሀሰት መሀላ፡- የሰዎችን ሐቅ ለመብላት ወይም ለማታለልና ለማጭበርበር ወይም ለሌላም አላማ ቢሆን ሆን ተብሎ በውሸት ላይ የሚፈፀም መሀላ ነው፡፡ ይሄ ዛሬ በንግዱ እና በሌሎችም ማህበራዊ ህይወቶች ውስጥ የተንሰራፋ ጥፋት ነው፡፡ ሆን ብሎ በሀሰት እየማለ የሚሸጥ የሚለውጠው ዛሬ ቀላል አይደለም፡፡ ጌታችን አላህ በዚህ ላይ ምን አይነት ከባድ መልእክት እንዳስተላለፈ እንመልከት፡-
إِنَّ الَّذِينَ يَشْتَرُونَ بِعَهْدِ اللَّهِ وَأَيْمَانِهِمْ ثَمَنًا قَلِيلًا أُولَئِكَ لَا خَلَاقَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ وَلَا يَنْظُرُ إِلَيْهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
“እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን እና በመሀላዎቻቸው ጥቂትን ጥቅምን የሚለውጡ በመጨረሻይቱ አለም ምንም እጣ የላቸውም፡፡ በቂያማ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም፤ ወደነሱም አይመለከትም፤ አያጠራቸውም፡፡ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡” [አሊ ዒምራን፡ 77]
ጥፋቱ ከከባኢር ማለትም ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ የሚመደብ እንደሆነ ሲገልፁ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “በአላህ ማጋራት፣ ወላጆችን ሐቃቸውን መጣስ፣ ነፍስን ማጥፋት እና የቅጥፈት መሀላ ታላላቅ ወንጀሎች ናቸው፡፡” [ቡኻሪ]

የሀሰት መሀላ ከባድ ወንጀል ከመሆኑ የተነሳ ማካካሻ አልተደረገለትም፡፡ ይሄ የብዙሃን ዑለማእ እይታ ነው፡፡ ይህን የፈፀመ ሰው ያለው ምርጫ የወሰደው ሐቅ ካለ መልሶ፣ የፈፀመው በደል ካለ አስተካክሎ ትክክለኛ ተውበት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አምስት ጥፋቶች ማካካሻ የላቸውም፡፡ በአላህ ማጋራት፤ ያለ አግባብ ነፍስን ማጥፋት ሙእሚንን መዝረፍ፣ በጂሃድ ላይ በፍጥጫ ሰዓት መሸሽ እና ያለ አግባብ ገንዘብ የሚበላበት ሀሰተኛ መሀላ!!” [አልኢርዋእ፡ 2564] ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ “ሆን ተብሎ የሚፈፀም የሀሰት መሀላ ማካካሻ ቅጣቶች ከሚያብሱት በላይ ነው” ብለዋል፡፡ [አልሙደወናህ፡ 1/577]

የመሀላ ማካካሻ /ከፋራህ/
-
አንድ ሰው የሆነን ጉዳይ ሊፈፅም ከማለ በኋላ ቃሉን ቢያፈርስ ወንጀለኛ እንዳይሆን የሚያመልጥበትን ቀዳዳ አላህ አመቻችቶለታል፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “በአንድ ጉዳይ ላይ የማለ ሰው ከማለበት ጉዳይ የተሻለ ነገር ከታየው ይፈፅመው፡፡ ከዚያም መሀላውን ያካክስ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] ማካካሻውን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፡-
فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ فَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ ذَلِكَ كَفَّارَةُ أَيْمَانِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ
“ማበሻውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው (ምግብ) አስር ምስኪኖችን ማብላት ወይም እነሱነ ማልበስ ወይም ጫንቃን (ባሪያን) ነፃ ማውጣት ነው፡፡ (እነዚህን) ያላገኘም ሰው ሶስት ቀናትን መፆም ነው፡፡ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሀላችሁ ማካካሻ ነው፡፡” [አልማኢዳህ፡ 89]

ስለዚህ ማካካሻዎቹ፡-

1ኛ፡- አስር ምስኪኖችን ቤተሰቡን ከሚመግበው መካከለኛ የምግብ አይነት የአንድ ወቅት ምግብ ማብላት፣
2ኛ፡- አስር ምስኪኖችን ሶላት የሚያሰግድ ልብስ ማልበስ፣
3ኛ፡- ሙእሚን ባሪያ ነፃ ማውጣት
ከነዚህ ማካካሻዎች ውስጥ ቅደም ተከተል ሳይጠብቅ የቀለለውን መርጦ መፈፀም ይችላል፡፡ እነዚህን ካልቻለ ግን፡-
4ኛ፡- ሶስት ቀን መፆም አለበት፡፡ ከ 1 – 3 ካሉት ውስጥ መፈፀም የሚችል ሰው ዘሎ ወደ ፆም መግባት አይችልም፡፡

ማሳሰቢያ 1፡- የመጀመሪያዎቹን ምርጫዎች ባለመቻሉ ፆም የመረጠ ሰው አከታትሎ የመፆም ግዴታ የለበትም፡፡

ማሳሰቢያ 2፡- ከፋራ ወይም ማካካሻ የሚመለከተው መሀላ፡-
1. ወደ ፊት ባለና ሊሆን በሚችል ጉዳይ ላይ ከተማለ ነው፡፡ ባለፈ ወይም ፈፅሞ ሊሆን በማይታሰብ ጉዳይ ላይ የማለ ሰው ከፋራ አይመለከተውም፡፡
2. መሀላው በአላህ ወይም በስሞቹ ወይም በሲፋዎቹ ከሆነ ነው፡፡ በፍጡር የተማለ መሀላ ወንጀል ስለሆነ ማካካሻ ሳይሆን ተውበት ነው የሚያስፈልገው፡፡
3. ተገዶ ሳይሆን በምርጫው የማለው መሀላ ከሆነ ነው፡፡
4. በቃሉ ሳይገኝ መሀላውን ካፈረሰ ነው፡፡

ማሳሰቢያ 3፡- አንድ ሰው በሚምል ሰዓት “ኢንሻአላህ” የሚል ቃል አብሮ ካወጣ መሀላውን ቢያፈርስም ማካካሻ መፈፀም አይጠበቅበትም፡፡ [ሶሒሑ ቲርሚዚ፡ 1237]

ማሳሰቢያ 4፡- አንድ ሰው ሌላውን “ወላሂ እንዲህ ልታደርግ” ብሎ ቢምልና ያኛው ሰውየ ሳያደርግ ከቀረ የማለውን ሰው ከፋራ ይመለከተዋል፡፡ ነገር ግን ሰውየውን ለማስገደድ ሳይሆን ለማክበር ብሎ ከሆነ ያደረገው ከፋራ ግዴታ አይሆንበትም፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን አቡበክር ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ እንግዶች መጥተው ምግብ ሲያቀርቡላቸው “አንተም ብላ” አሉ ለአቡበክር፡፡ “ወላሂ እኔ አልበላም” አሉ እሳቸው፡፡ እንግዶቹም “ወላሂ እኛም አንበላም” አሉ፡፡ ሁሉም ሲምሉ ጊዜ አቡበክር “ይሄ ከሸይጧን ነው” በማለት በሉ፡፡ እንግዶቹም በሉ፡፡ ነብዩ ﷺ ሲነገራቸው አቡበክርን “አንተ ከሁሉም መልካም የሰራና በላጭ ነህ” በማለት ከማሞገስ ውጭ ከፋራ እንደሚመለከታቸው አልነገሯቸውም፡፡ [ሙስሊም፡ 2057]

ማሳሰቢያ 5፡- አንድ ሰው ሌላውን “ወላሂ እንዲህ ልታደርግ ወይም ላታደርግ” ብሎ ቢምል ከሰውየው ጋር እልህ ከመጋባት ይልቅ በመሀላው እንዳይጠየቅ ብንተባበር መልካም ነው፡፡

ማሳሰቢያ 6፡- መሀላን ማፍረስ የተለያየ ብይን አለው፡፡
1. ዋጂብ የሆነ ማፍረስ፡- ወንጀል ሊፈፅም የማለ ሰው መሀላውን ማፍረሱ ግዴታው ነው፡፡
2. ሐራም የሆነ ማፍረስ፡- የማለው ያለበትን ግዴታ ለመፈፀም ወይም ከሐራም ለመራቅ ከሆነ ቃሉን ማፍረሱ ሐራም ነው፡፡
3. ምርጫ ያለው ማፍረስ፡- በሸሪዐው የተፈቀደን ወይም ግዴታ ያልሆነን ነገር ለመስራት ወይም ለመተው ቢምል ፍላጎቱ ከሆነ መሀላውን የማፍረስ ምርጫ አለው፡፡

በሶስቱም ሁኔታዎች መሀላውን ያፈረሰ ሰው ማካካሻ ወይም ከፋራ መፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ ይህ የሚሆነው ግን እያወቀ፣ በምርጫው እና እያስታወሰ መሀላውን ካፈረሰ ነው፡፡ እንጂ ባለማወቅ ወይም ተገዶ ወይም ረስቶ መሀላውን የሚፃረር ነገር ቢፈፅም ማካካሻ የመፈፀም ግዴታ የለበትም፡፡

ማሳሰቢያ 7፡- አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ለምሳሌ “ወላሂ ይህን ላልሰራ” እያለ ደጋግሞ ቢምል የሚመለከተው ከፋራ አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
Š

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

08 Nov, 08:48


❤️ Quran ❤️
✨Qari- idress abkar
🌙 Suretul Kahf

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

08 Nov, 08:48


FRIDAY

May allah fulfil our derams and remove our sadness AMEN
ﷺﷺﷺ🤍

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

04 Nov, 14:12


ፍቅር❤️


የምስል እርሣቸዉን የምትመስል ቆንጆ ናት፣ ዉብ …..
ዕድሜዋ ለጋብቻ ሲደርስ ብዙ ሰዎች ሊጠይቋት እርሣቸው ግስ መጡ፤ ብዙ የተከበሩና ትላልቅ ሰዎች …

አንዲት ዐሊን የምትወድ የአንሷር ሴት ዐሊ ዘንድ ሄዳ
“ፋጢማን ብዙ ሰው እንደጠየቃት ታውቃለህ ግን?” አለችው፡፡
“አዎን” አላት፡፡
“አንተሰ ለምን ሄደህ አትጠይቅም፤ ለምን ዳሩልኝ አትላቸዉም፣ ትወዳት የለ?” አለችው፡፡
አንገቱን አቀረቀረ
“ድሃ ነኝ ምን አለኝና? በምንድነው የማገባት?” አላት፣
“ዝምብለህ ሂድና ጠይቅ፤ መልካም ነገር ልትሰማ ትችላለህ አብሽር፡፡” ብላ አሳመነችው፡፡

ሄደ፡፡ ፈራቸው፤ እርሣቸው ፊት ተቀምጦ መናገር ከበደው፡፡ እናም ዝም አለ፡፡
“ምነው ዐሊ ምን ሆነህ ነው? ምንድነው ያመጣህ ጉዳይ?” አሉት፤ አከታትለው ጠየቁት፡፡
ዐሊ አሁንም ዝም አለ፡፡
“ምናልባት ፋጢማን እንድሰጥህ ለመጠየቅ መጥተህ እንዳይሆን፡፡” አሉት፡፡
አዎን በሚል ሀሳብ ራሱን ነቀነቀ፤
“ታዲያ ጥሎሽ ይኖርሃልን?” አሉት፡፡
“ምንም የለኝም” አላቸው፡፡
“የሆነ ጋሻ እንዳለህ አስታውሳለሁ፡፡” አሉት፡፡
“አዎን አለኝ፣ ግን እሱ ምን ያደርጋል፣ ምን ዋጋ ያወጣል?” አላቸው፡፡
“ይጠቅማል ሽጠዉና ...፡፡” አሉት፡፡

ቤት ገዙላቸው፤ ጋብቻው ተፈፀመ፡፡

ዐሊ እንዲህ ይላል 
'ከዚያ በኋላ ፋጢማን እጅግ ወደድኳት፡፡ አንድም ቀን በስሟ ጠርቻት አላውቅም፤ “ የአላህ መልዕክተኛ ልጅ ሆይ” ነበር የምላት፡፡
ልክ እሷን ሳይ ሀሳብና ጭንቀቴ ሁሉ ይወገዳል፣ ልቤ እረፍት ይሰማዋል፣ አንድም ቀን አስቆጥቻት አላውቅም፣ አንድም ቀን አላስለቀስኳትም፣ አንድም ቀን አስቆጥታኝ፣ አንድም ቀን አስቸግራኝ አታውቅም፡፡ በአላህ አምላለለሁ አንድም ቀን ጀርባዬን ሰጥታችት አላውቅም፤ ሁሌም እጆቿን እንደሳምኳት …   

ፋጢማ ከአባቷ ከአላህ መልዕክተኛ (ሜ.ዐ.ወ.) ህልፈት ከስድስት ወር በኋላ ተከተለቻቸው፡፡ በሞተችም ጊዜ ባለቤቷ ዐሊ አጠባት፣ ከፈናትም፣  ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎም
      
“ፋጢማዬ እኔ ዐሊ ነኝ፡፡” አላት፡፡  




@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

02 Nov, 18:35


ያ አሏህ ምን ዓይነት ተደቡር ነው !!!!



በዚህ እድሜያቸው ቁርአንን እያስተነተኑ ያነባሉ ።
ቪዲዮውን ተመልከቱት ያለንበትን ያስታውሰናል  ።


ⓒibnuomer




Join👉@muslimsshebab
@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

01 Nov, 05:15


ጁሙዐ ይለያል!
~
ጁሙዐ ከሳምንቱ ቀናት የተለየ እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ ነጥቦች አሉ። ለምሳሌ ያህል:-

1- ጁሙዐ የሳምንቱ ቀናት አይነታ ነው። ከሁሉም በላጭ የሆነ ቀን ነው፣ ሳምንታዊ ዒድ።
2- ጁሙዐ አደም የተፈጠሩበት እና የሞቱበት የዓለም ፍፃሜ የሚሆንበትም ቀን ነው።
3- አላህ ዘንድ ከሶላት ሁሉ በላጩ የጁሙዐ እለት በጀማዐ የተሰገደ የሱብሕ ሶላት ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 1119]
4- ጁሙዐ የጠነከረ ትእዛዝና ማሳሰቢያ የመጣበት ልዩ የሆነችዋ የጁሙዐ ሶላት የሚሰገድበት ቀን ነው።
5- ሳምንታዊ ኹጥባ የሚገኝበት ቀን ነው። ኹጥባውን በፀጥታ ማዳመጥም ግዴታ ነው።
6- ገላን በመታጠብ ትእዛዝ የመጣበት ቀን ነው።
7- ሽቶ መቀባት፣  መፋቂያ መጠቀም ይወደዳል።
8- ያማረ ልብስ መልበሱ ይወደዳል።
9- ጁሙዐ ግዴታ ለሆነበት ሰው የሶላት ወቅት ከገባ በኋላ ጁሙዐን ሳይሰግዱ መንገድ መውጣት አይፈቀድም።
10- ጀሀነም በየ እለቱ ትቀጣጠላለች፣ ጁሙዐ ቀን ሲቀር።
11- ጁሙዐ ቀን አላህ ዱዓእን ከሌሎች ጊዜያት በተለየ የሚቀበልባትን ሰዓት የያዘ ቀን ነው።
12- ጁሙዐ ቀን ሱረቱል ከህፍ መቅራት የሚወደድበት ቀን ነው።
13- ጁሙዐ ቀን በነብዩ ﷺ ላይ ሶላት ማብዛት የሚወደድበት ቀን ነው።
14- ጁሙዐ ቀን ሱብሕ ሶላት ላይ ነብያችን ﷺ ሱረቱ ሰጅደህ እና ሱረቱል ኢንሳንን ይቀሩ ነበር።
15- የጁሙዐ ቀን ወይም ሌሊት የሞተ ሰው አላህ ከቀብር ፈተና ይጠብቀዋል። [ቲርሚዚይ፡ 1074]
16- ጁሙዐ ለወንጀሎች ምህረት የሚገኝበት ቀን ነው።
17- የጁሙዐ ቀን በፆም፣ ሌሊቱን በሶላት መለየት የተከለከለ ነው።

Šibnu munewor

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

30 Oct, 20:41


የ ወንድ ልጅ ሂጃቡ መልካም ስነምግባሩ ነው።

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

30 Oct, 17:47


ጥርት ያለ ተዉባ ማለት የሰራኸዉን ወንጀል
የወደድከዉን ያክል ስትጠላዉ እና ገና ስታስታዉሰዉ አስተغፊሩላህ የምትልበት ነዉ።
    
       ሀሰነል በስሪ رحمه الله


Join👉@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

28 Oct, 20:00


መራቆት መብት ተብሎ መሸፈን ሲከለከል አይገርምም።



@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

28 Oct, 17:07


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች "ኒቃባችሁን ካላወለቃችሁ አትማሩም" በሚል ሙስሊም ተማሪዎችን ከት/ት ገበታ ማገዳቸው ተገለፀማ


- ሀሩን ሚዲያ፣ ጥቅምት 18/2017፣ አዲስአበባ

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች "ኒቃባችሁን ካላወለቃችሁ መማር አትችሉም" በማለት በርካታ ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማገዳቸው ተማሪዎች ለሀሩን ሚዲያ በላኩት መረጃ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ ከዚህ በፊት ያለምንም ችግር ኒቃብ ለብሰው እየተማሩ የነበረ ቢሆንም በጥቅምት ወር ጀምሮ ኒቃብ እንዲያወልቁ መታዘዛቸውን ተናግረዋል። አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በኒቃብ ምትክ ማስክ ፈቅደው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ማስክ ለብሰው መማር እንደማይችሉ መደረጉን ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ ከኒቃብ መከልከላቸው ባሻገር በርዕሰ መምህራኖቹ "ኒቃብ ለብሶ የሚመጣ ተማሪ አሸባሪ እንጂ የእኛ ተማሪ አይደለም" በማለት የተማሪዎችን ስነ-ልቦና በሚነካ መልኩ መናገራቸው ተሰምቷል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ይህ ችግር ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ከተማሪዎች እና ከወላጆች ጋር በመሆን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱን ገልፆ ነገር ግን ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ለአዲስ አበባ መጅሊስ እንዲሁም ለሌሎች ለሚመለከታቸው ተቋማት ደብዳቤ መፃፉን ለሀሩን ሚዲያ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ በኒቃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ከታገዱ ከ15 ቀን በላይ እንደሆናቸው የገለፁ ሲሆን የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

- ሀሩን ሚዲያ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።



©: ሀሩን ሚዲያ



Join👉@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

28 Oct, 09:06


እንድ አንድ የቁርአዐን ዐያዎች ግን እጅግ በጣም ከማስደንገጣቸው የተነሳ እኮ ፣ ወላሂ የሰው ልጅ አላህን ለመፍራት ይህ ዐያ ብቻ ይበቃው ነበር ያስብላሉ ፣ ነገር ግን እኛ ሰዎች ምን ያህል ቀልባችን እንደሚደርቅ ፣ ይህን እየሰማን እያወቅንም ምን ያክል ከአላህ እንደምንሸሽ ፣ ምን ያህል አላህን እንደምናምፀው ራሳችንን እንይ እስቲ... አጃዒብ ነው

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

27 Oct, 13:58


ችግራችን

ወደዚህች ዓለም የመጣንበት ዓላማ ጠንቅቀን አለማወቃችን፡፡ ብናውቅማ ኖሮ ከዓላማችን ዝንፍ ባላልን ነበር፡፡ ያስቀደምነው አኺራን ሣይሆን ዱኒያን ነው:: የምንኖረው ለመኖር ሣይሆን ለመብላት ነው፡፡ የምንበላው ለመሥራት ሣይሆን ለማውራት ነው፡፡ የምናነበው ለማወቅ ሣይሆን ለመከራከር ነው፡፡ የምንማረው ለመለወጥ ሳይሆን ለጉራ ነው፡፡ የምንሰግደው ለአምልኮ ሣይሆን ግዴታን ለመገላገል ነው፡፡ ሀጅ የምንሄደው ለዚያራ ሣይሆን ለሃጃ ነው፡፡ የምንለግሰው ለአጅር ሣይሆን ለውለታ ነው፡፡ የምንዋደደው ለአላህ ብለን ሣይሆን ለጥቅም ነው፡፡ የምንፈራው አላህን ሣይሆን ሞትን ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ الذاريات : ٥٦ “ጋኔንንና ሰውንም፥ ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡”

(አዝ-ዛሪያት፡ 56)

Š MuradTadesse

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

26 Oct, 06:07


አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላለፍት ሶስት አመታት ኒቃብ ለብሰው ሲማሩ የነበሩ ተማሪወች ወይ አውልቁ ወይ ትምህርት ቤት አትምጡ ተብለዋል ።

ከትምህርት ከታገዱም ሳምንት አለፍቸው መጅሊሱም መረጃ ቢደርሰውም  ዝምታን መርጠዋል።

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

26 Oct, 02:01


“The strong man is not the one who wrestles well, but the one who controls himself when angry.”

Prophet Muhammad 

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

25 Oct, 05:17


ሰሉ አለነቢይ
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

25 Oct, 02:00


❣ Honestly
መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ቁርአንን ከፍታችሁ ያነበባችሁት?

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

24 Oct, 02:01


ከዚህ ሀገር ሌላ መልካም ስራ የምንሰራበት ሀገር አለ ?

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

23 Oct, 02:00


ؾابع

Wallahi everything happens for a reason, keep your sabr and trust in Allahs plan.
توكل

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

22 Oct, 04:27


ትላንት ያለን ኢማን ዛሬ አለን ወይ ????


join👉👉👉@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

22 Oct, 02:00


Anything that cost you your akhirah is not worth it.💔

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

21 Oct, 02:01


See everything from an islamic prespective.🖤

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

20 Oct, 02:01


መቼ ነው የ ለሊት ሰላት መስገድ የምንለማመድው?

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

19 Oct, 02:01


Remember

You can only win when your mind is stronger than your emotions

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

18 Oct, 05:52


Al-Ahzab - Verse 56

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

17 Oct, 22:21


لقد كان قلقًا بشأن الغد,مات الليلة.


ስለ ነገ ተጨንቆ ነበር, ዛሬ ማታ ሞተ.

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

17 Oct, 02:00


When your iman is low the dunya heart you easily.

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

16 Oct, 16:18


- መስጂድ ፍፁም ለሆኑ ሰጋጆች አይደለም
- ቁርኣን ፍፁም ለሆኑ አላህን ተገዥዎች አይደለም
- ዱአ ወንጀል ለሌለባቸው አይደለም
🕋 ዲኑ የሁሉም ነው

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

15 Oct, 17:28


እኔ በነዛ በዲናቸው ብቻ በደል ለሚደርስባቸው የአላህ ባሮች ከ ዱዐ ውጪ ምንም አለማድረጌ ያስፈራኛል አላህ ሆይ ይቅር በለኝ ቢያንስ ለ እናንተን ዱዐ እንድታደርጉላቸው ማስታወሴ የአላህን ጥያቄ ካቀለለልኝ አላህ ያውቃል

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

15 Oct, 14:02


وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَنُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَحْسَنَ الَّذِي كَانُوا يَعْمَلُونَ

[ ሱረቱ አል-ዐንከቡት - 7 ]
እነዚያም ያመኑ፤ መልካሞችንም የሠሩ መጥፎዎቹን ሥራዎቻቸውን ከእነሱ ላይ እናብስላቸዋለን፡፡ በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን፡፡


@muslimsshebab
@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

15 Oct, 02:00


Sabr is when your heart burns,but you keep silent.
ؾابع

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

14 Oct, 02:00


አላህ ሆይ ኢማንን በኛ ልብ ውስጥ የተወደደ አድርገው

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

13 Oct, 20:30


اصبر لِكُلِّ مُصِيبَةٍ وَتَجَلد

وَاعْلَم بِأَنَّ المَرءَ غَيْرُ مُخَلَّدِ

أَوَما تَرَى أَنَّ المَصابِبَ جَمَّةً

وترى المنية للعباد بمرصد

من لم يُصب من ترى بمصيبة

هَذَا سَبِيلُ لَستَ فِيهِ بِأَوحَدِ

وَإِذا ذَكَرتَ مُحَمَّداً وَمَصَابَهُ

فَإِذْكُرْ مُصابَكَ بِالنَبِي مُحَمَّ

Endure every difficulty with patience

and be strong

Like the shortness of life, your

suffering will end before long

Mishaps are so many, don't you see?

Death's in ambush, can anybody

flee?

Is there anyone you know who suffered no pain ?

No doubt you aren't alone in this plain

When the affliction of Nabi

Muhammed you remember

Ask yourself, in your heart wasn't his

passing the hottest ember?

@muslimsshebab

🕋SHEBABEL MUSLIMIN 🕌

13 Oct, 02:00


Choosing the right mother is more important than choosing the beautiful wife for your self.

@muslimsshebab

5,386

subscribers

841

photos

163

videos