Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️ @alexcasting1 Channel on Telegram

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

@alexcasting1


ÆX ©asting
🎙️🗣️🎙️Vocal and acting training 🎭
🗣️ Casting
🎬 film
🎥 Advertising
📽 🎶music clip
Please send your...
photo:
Name:
Age:
Number:
Address:
@Al_as13_7

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️ (Amharic)

አሌክስ ካስቲንግ & ፊልም ንግስት ዘጋሁን ተጠቃሚያቸው ከዚህ እስከ እለፉ ለምትለዋወቱ የተከሰታቸው መዝናኛ እና ፊልሞች እንደሚመልሱ እንጠቀሙለን n እኛ በቀበሮው አባላት ሰላምና መጪውን እናወዳለን፡፡ በቀላሉ ወደኛም ሆኖ አስተመልክ በሌሉኮች አካባቢ አመት ጊዜ ድጋፍን የማስወደድ እና በዚህ ስለሚያስቡ አልበሩህም፡፡n በአሌክስ ካስቲንግ & ፊልም ንግስት መነቀፅ የዚሁ ቦታ ያላትን አገልዎቶች በሐዘን በቀቢታ እያለፈ መከላከያ ማጠናቀቅ ምንም ነገር ያልተቻለ የሚያጠናክረውን አድርገን በማሻሻል የምስኪኑን ማነጋገር ስለሚችል እኛን መረጠ ብለን ግንብገን ይህን እናዣለን፡፡n እንዲሁም በመሆኑ አሌክስ ካስቲንግ & ፊልም ንግስት ፈቃዳቸውን ለማስተዋወቅ በጥንቃቄና በፍላጎታ መከታተል ዝርዝሩን ለአስተምረናል፡፡

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

13 Jan, 18:07


ይህ ማስታወቂያ ተጠናቋል የሚበቃን ባለሞያዎች አግኝተናል መልእክቱን በማጋራት ለተባበራችሁን ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

10 Jan, 08:06


የምግብ ባለሞያ ይፈለጋል

ለ ወንድ የምግብ ባለሞያ ብቻ የወጣ ማስታወቂያ

በምግብ ሞያ ምሩቅ የሆናችሁ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ
እንዲሁም ልምድ ያላችሁ የሀበሻ ምግብ በደምብ የመስራት ችሎታ ያላችሁ 3ወንዶች ትፈለጋላችሁ

ስራው ከሀገር ወጪ ነው ፓስፖርት ሊኖራችሁ ይገባል ለበለጠ መረጃ

@Gman073 @Gman073

በዚህ ያነጋግሩን ይህ ማስታወቂያ ያለው የጊዜ ቆይታ 7ቀናት ብቻ ይሆናል 🙏

ሻሎም ኢትዮጵያ 🙏

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

06 Jan, 21:04


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Alex film production and casting

መልካም በዓል🙏

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

02 Jan, 16:39


#ታሪኮን_ያጋሩ ቻሌንጅ
የመጨረሻ ዙር ውድድር - አጠቃላይ መግለጫ

ሰላም የAlex casting and film production ቤተሰብ እንደምን ናችሁ እነሆ የ #ታሪኮን_ያጋሩ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል⚡️

የዳኝነት ሂደቱ

1⃣ 30% ፦ ከተመልካች ድምጽ
ከእናንት ውድ የAlex film production and casting ቤተሰቦቻችን የሚገኘው ድምፅ ይሆናል።

✔️ Vote ፦ ታሪኮቹ ከአንባቢያን ተመልካቾች በሚያገኙት (👍 🙏 🔥 🥰 👏)

💬 Comment ፦ ከአንባቢ ተመልካች በሚያገኙት አስተያየት እንዲሁም ምን ያህል የውይይት ምህዳርን መፍጠር ቻሉ

👀 View ፦ ምን ያህል ሰው ታሪኮቹን አነበባቸው። ስለዚህ ባለታሪኮች እና ታሪኮቹን የወዳዳችሁ ቤተሰቦቻችን የወደዱትን ታሪክ ማጋራቶን አይርሱ።

📌  የተመልካች ዳኝነት ሂደት የአንድ ሳምንት ያህል ጊዜ ብቻ ነው የቀረው❗️ስለዚህ ይፍጠኑ 🏃‍♂️🏃

2⃣ 70% ፦ ከዳኞች

Alex film production and casting ባዘጋጃቸው የ #ታሪኮን_ያጋሩ ዳኞች የሚያዝ ነጥብ ነው። ይህም ነጥብ የሚያዘው በተዘጋጀ መስፈርት በተጨማሪም ከባለ ታሪኮቹ ጋር በሚኖረው ቃለ መጠይቅ ላይ የተሞረከዘ ነው።

🏆 ሽልማቶች🎉

1⃣ በአንደኝነት ለሚያሸንፈው ባለታሪክ
     ▫️10,000 💸 ብር የገንዘብ ሽልማት
     ▫️ታሪካቸው ወደ ፊልም 🎬 ይቀርላቸዋል
     ▫️የህይወት ታሪካቸውን እንደ ድርሰት ይዞ በሚሰራው ፊልም ላይ መሳተፍ በሚችሉባቸው ዘርፎች ( acting 🎭, script writing , directing, cinematographer or any production crew) የመሳተፍ ዕድል

2⃣ በሁለተኝነት ለሚያጠናቅቀው ባለታሪክ
     ▫️5000 ብር 💸 የገንዘብ ሽልማት
     ▫️ሰርተክፌት እና የፕሮዳክሽኑ ቋሚ አባል
     ▫️በሚሰራው ፊልም ላይ መሳተፍ በሚችሉባቸው ዘርፎች ( acting 🎭, script writing , directing, cinematographer or any production crew) የመሳተፍ ዕድል

3⃣ በሦስተኝነት ለሚያጠናቅቀው ባለታሪክ
    ▫️2500 ብር 💸 የገንዘብ ሽልማት
    ▫️ሰርተክፌት እና የፕሮዳክሽኑ ቋሚ አባል
    ▫️በማሰራው ፊልም ላይ መሳተፍ በሚችሉባቸው ዘርፎች ( acting 🎭, script writing , directing, cinematographer or any production crew) የመሳተፍ ዕድል

🔑 በ #ታሪኮን_ያጋሩ ቻሌንጅ ላይ ተሳትፎ ስታደርጉ የነበራችሁ ቤተሰቦቻችን በሚሰራው ፊልም ላይ በየዘርፋችሁ የመሳተፍ ዕድልን ታገኛላችሁ። ስለዚህ ተሳትፏችሁ አይለየን🙏

📩 ለበለጠ መረጃ @writeramanu ላይ መጠየቅ ትችላላችሁ።

🌟ለተወዳዳሪ ባለታሪኮች ሁሉ መልካሙን ሁሉ ተመኘን🌟

Alex film production and casting

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

28 Dec, 17:28


ሰላም ቤተሰብ🙏 እንዴት ናችሁ

#ታሪኮን_ያጋሩ ቻሌንጅ ሁለተኛ ዙር አምስት ተወዳዳሪ ታሪኮችን(የሕይወት ገጠመኞችን) ለእናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን አጋርተናል።

📌 የትኛው የህይወት አጋጣሚ ይልበልጡኑ ወደ ፊልም ይቀየር ዘንድ ወደዳችሁት ለምን

🔑 ይህ ቻሌንጅ ከባለታሪኮቹ ባለፈ ለእናንተ የፊልሙ ዓለም ቤተሰቦቻችን መልካም አጋጣሚ ይዞ የመጣ ሲሆን በታሪኮቹ ዙሪያ ሀሳብ ለሚሰጡ አካላት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ልናበስራችሁ እንወዳለን🙏

ድምጻችሁን በመስጠት እንደቀደመው ዙር በዳኝነት ትሳተፉ ዘንድ Alex film production and casting ጥሪውን ያቀርባል።

ለተወዳዳሪ ባለታሪኮች መልካሙን ሁሉ ተመኘን!💖

ሠናይ ሰንበት!

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

28 Dec, 10:01


"ሰው ይወድቃል ይነሳል!"
ገና በልጅነቴ አየሁት ለሰው ቅን ሁኑ ሰው ሲጠላቹ ውደዱት በምላሹ ታተርፋላቹ ህይወት እንዲ ናት እኔጋ ።

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

28 Dec, 10:01


መለያ ኮድ 007

ሰላም እንዴት ናቹ

ተወልጄ ያደኩት በውቢቱዋ ናዝሬት ከተማ ላይ ነው። እናቴን ያጣሁት ገና ጨቅላ እያለው ነው ፤ የእናቴን ቤተሰቦች ሁሉ አላቃቸው አባቴን ሁሌ ስለእናቴ  ቤተሰባች  ሳነሳበት 'እንደሆነ ነገር' ያደርገዋል "ለምን?" ካላቹሁኝ እናትሽ ባረፈችበት ቀን አንቺን "ውሰድልን ልጅክን እኛ አናሳድግም" እኔ እዛ ነበርኩ ክፉላገር ምክንያቱም አባቴ ደሀ ስለነበር  አባቴም እናቱጋር ጠንከር እስክል አስቀመጠኝ እሱም ወደናዝሬት ተመለሰ የጉልበት ስራ  የተለያዩ ስራዎች ይሰራል ኑሮን ለማሸነፋ እንደዛም ሆኖ ልክ እንደሀብታም ልጅ ነበር   የሚያቀብጠኝ አንድቀን አክስቴ ወደ እናቱዋጋር መታ አብሬያት ካሌድኩ አልኩኝ እሱዋም በጣም ትወደኝ ነበር አላስችል ብሉዋት በጀርበዋ ተሸክማኝ መጣች አባቴ  ሚስት አግብትዎ ነበር እንጀራ እናቴ አትዎደኝም ነበር አባቴም ታዋቂ የከብት ነጋዴ ሆነ ድህነትን አሸነፈ ሁለት ወንድም አለኝ አጠቃላይ ሶስት ነን ሁላችንም የግል ትምህርት ቤት ነው የተማርነው እንጀራ እናቴ ሁሌም ታስለቅሰኝ ነበር ከልጆችዋ እኩል አታየኝም ሁሌም ወደፈጣሪ ነው ማለቅሰው ምክንያቱም እኔ በቁጣ የማለቅስ ልጅ ነኝ ድንገት አባቴ  ምንሆነሽ ነው እሞ ሲለኝ አይ አባቴ ስቄ ነው እላለው እኔ ስስቅ ስለማለቅስ ብዙ ነገሮችን በዚ አልፋለው ምክንያቱም ቤተሰብ እንዳይበተን ብዬ እኔ ያየሁትን እንዲያዩ ስለማልፈልግ አስራሁለት ውጤት አልመጣልኝም በሰአቱ ግራ ገባኝ በዚ እድሜ ቤት ልቀመጥ ነው ብዬ የልጅነት ህልሜ ደራሲ ተዋናይ ፕሮዲውሰር መሆን ነበር አንድቀን አባቴ ያልጠበኩትን ነገር አደረገልኝ ምግቤት ከፈተልኝ በጣም ደስ አለኝ ስለቴን አስገባው እውነት ነጋልኝ ከሱዋ ተገላገልኩ በቃ አልኩ ብቻ ደስ አለኝ ያኔ 21 አመቴ ነበር።
ምግብ ቤቴን መስራት ጀመርኩ እስኪለምድልኝ ድረስ ለሁለት ወር እንጀራ እየጋገርኩ ነበር ምግቤቴን የምዘጋው 6,7 ሰአት ነበር ከዛ 10 ሰአት እንጀራ ጋግራለው ኮሌጅ ትምህርት ጀምሬ ነበር ሲለምድልኝ  ግን አቃተኝ ሁለት ቀን ብቻ ነው ክላስ የሄድኩት  አቃተኝ መማር ማንቀላፋት ጀመርኩ አስተማሪው የሚለኝ ነገር አልገባ አለኝ እኔም አቆምኩ ስራዬላይ አተኮርኩ እቁብ ገብቼ እቃዎችን መግዛት ጀመርኩ ሰራተኛ አበዛው ለቤተሰቦቼም ሙሉ ልብስ አለበስኩ ያቺ እንጀራናቴም ተቀየረች ለኔ መልካም ሆነችልኝ ሁሌም መልካምነት እንደሚያሸንፋ አየው  አልፎልኝ በአል ሲሆን ቅርጫ ገብቼ ዶሮ አርጄ ጠላ ጠምቄ ቤተሰቦቼን ቤቴ መጥራት ጀመርኩ ብዙ በአላት ቤቴ አከበርኩ ሁሌም በወር አስራት ሰጣለው አባቴ እኔጋ ነው የሚያድረው ምክነያቱም ሴቶች ነን ሁላችንም ዘበኛ ተቀጥሮልኝ ነበር ትልቅ ሰው ናቸው በቀን ይሰክራሉ አይደለም በማታ እኔም አረቄ በጣም ስለሚወዱ  እንዳሰጡ አልኩ እኔ  ስከለክል ሌላጋ ጠጥተው ይመጡ ጀመር እኔም ወደሀገራቸው ሸኘዋቸው ከአቅሜ በላይ ሆኖ አባቴም ማደር ጀመረ ከለታት አንድ ቀን ቤቴ በጣም ይጨፈር ነበር አየር ያለኝ በአካባቢያችን ላይ እኔ ነበርኩ ሰራተኛዬ ውጪ ቆሻሻ እያቃጠለች ነበር በድንገት የለቅሶ ድምፅ  ሰማን እሮጨ ወጣሁን  የሰፈር ታጣቂ በድንጋይ እግሯን መትዋት በጣም እየጮኸች ነበር ቤቴ ተረበሸ አባቴ እንዴት ሰራተኛዬን ይመታል በማለት ሌላ ፀብ ተፈጠረ አባቴን ማረጋጋት ጀመሩ ከስተመሮቼም አባቴ በጣም አይለኛ ሰው ነው ከነኩት ማንንም አይለቅም ድጋሜ ያሰውዬ ቤቴ መጣ የአስር ደቂቃ ልዩነት  እንዴት ብትንቀኝ ነው ድጋሜ የመጣከው በማለት ሌላ ፀብ ተፈጠረ ፈጣሪ አትርፎካል በሰአቱ ልጄ ብትሆን ኖሮ በመሳሪያ ነበር የምደፋክ አይኔን ሲነኩኝ  ያመኛል አለው አባቴ በኔ ቀልድ አያቅም በጣም ይወደኛል ሁሉ ነገሩነኝ ጓደኛው አማካሪው ሀብቱ ነኝ ብቻ በሽማግሌ ታረቁ እኔንም ይቅርታ ጠየቀኝ አባቴ አንድ ቀን እንዲ አለኝ ልጄ እኔ ሁሌ ላልኖር እችላለው እዛጋም ቤተሰብ አለ እዛም አስፈልጋለው ስለዚክ መሳሪያ እንዴት እንደሚቀባበል አሳይሻለው አለኝ በጣም ነበር የደነገጥኩት ሲያሳየኝ በጣም ይከብድ ነበር መተኮሱ ብቻ ነበር የሚቀለው ሌላው በጣም ይከብዳል እኔም ለመድኩ መሳሪያ መፋታት ማፅዳት ቻልኩ አባቴ ማደር አቆመ ያኔ አንድቀን ቤቴ ኮቴ ተሰማኝ የበሬ በር ሲታገሉ ሰማው መጀመሪያ ባትሪ አበራው መሳሪያዬን አቀባበልኩ አባቴ ጋር ደወልኩ በፋጥነት መጣ እሱ ከውጭ እኔ ከውስጥ ወጣው ስንወጣ ምንም ነገር የለም ነበር ለካ ባትሪ ሳበራ መስታወት ስለነበር እንደሚያሳይ እረሳውት ያኔ አባቴ ኮራብኝ ድፋረቴን አያይዜን አይቶ ልጄ ጠንክራለች ማለት ጀመረ ድምፅ ከሰማሽ ሳትቀደሚ ሁሌ ቅደሚ ግንባሩን በይው አለኝ ስራው ለሴት ልጅ በጣም ከባድ ነው ከሰው ጋር መጣላት ክፈሉ አትክፈሉ ማለት እራሱ ስልችት ይላል ሰራተኛዬ አንድ ቀን አንዱ መቀመጫዋን ሲመታት አየው በጣም ተናደድኩ።

እሱዋ ትስቃለች "ለምንድነው ቤቴን ምታስንቂው ሲመታሽ ለምንድነው ዝም ያልሽው!" ብዬ ጨውኩባት ግን ምን አለቺኝ ስራሽ እንዳይቀዘቅዝ ነው ከስተመር እንዳታጪ ተናግሬ ማስቀየም አቅቶኝ አይደለም ቤቲ አለቺኝ በጣም ነበር የደነገጥኩት እንደዛ ስትለኝ ከፈለገ አይጠቀም መሄድ ይችላል ለኔ ብለሽ ክብርሽን አታዋርጂ አልኩዋት ቁጥር ሁለት ለመክፈት ቤት መፈለግ ጀመርኩ ከለታት አንድ ቀን ማብራት ጠፋትዎ ነበር ያን ቀን አባቴ እንደሚመጣ ነገረኝ መምጣቱም አይቀርም መጣ እኔ በቆልት እያዘጋጀው ነበር ለከስተመር ከየት መጡ የማልላቸው ሰዎች ቤቴን ወረሩት አባቴን ያዙት ፖሊሱ ኪችን ድረስ ሲመጣ የሰፈር ታጣቂ መስሎኝ በሰላም ነው አልኩት በቆልቱን እየቀመስኩ በሰላም ነው አለኝ ጥዬው ወጣው አባቴን ከበውት በጥፊ አሉት ያኔ እራሴንአላቅም ወደመኝታ ቤቴ እሮጥኩኝ መሳሪያዬን ላመጣ ስሄድ ከየት መጣ ያላልኩት ሰው ተይ ላባትሽ ብለሽ እንዳታደርጊው አለኝ ወደራሴ ተመልሼ መሳሪያዬን ካለበት አውጥቼ ጡቴ ውስጥ ከተትኩኝ ትዝ ሲለኝ እንደ ተቀባበለ ነበር ካርታውን አላወጣሁም ነበር አይምሮዬ ቢባርቅስ ወይዬ እያልኩ  ፓሊሱ ቁሚ አንቺ ምንድነው እንዲ ምቶኚው የደበቅሽው አለ እንዴ አለ አባቴን በዛ ጭለማ ወሰዱት በነጋታው ወደ አባቴ ጋር ለመሄድ በዛ ሰአት እንጀራ እናቴ ነብሰጡር ነበረች በጣም ከባድ ነበር በሰአቱ ቤተክርስቲያን በር እላይ እያለፋኩ ተሳልኩ ስለት አባቴን በብር ወደቤት አመጣሁኝ ለካ የባለፈው ታጣቂ ነበር የጠቆመው አባቴ ሀብታም ነው እዛ አካባቢ ላይ ብዙ ቤት አለው ሰው ሰርቶ ባመጣው ነገር ሌላው አይኑ ደም ይለብሳል ፈጣሪም መቼም ቢሆን አያልቅበትም ሰውዬው ገበያ መሀል በሬ ወጋው።

ቤተሰቦቼ ስራውን አቁሚ ዘመድ አዝማድ ለመኑኝ እኔም እሺ ከማለት በስተቀር ምንም አላልኩም አቆምኩ በዛላይ ብሄር የሚሉት ጉዳይ ነበር ብቻ  ሰማይ የተደፋብኝ ያክል ተሰማኝ አግኝቶ ማጣት በጣም ያስጠላል እኔም ወደ አዲሳባ መጣሁ ሌላ ስራ ቀየርኩ ጋራጅ ገባው ደሞዜ 3000 ነበር ለመዋያ ነበር የገባሁት ባለቤቱ ሲያዘን በጣም  እናደዳለው ሲፈልገው ኮቱን አልብሽኝ ይላል ለኔ ከባድ ነበር ሳዝ የኖርኩ ልጅ እታዘዝ ጀመር ትዛዝ አሎድም አቆምኩት ስራውን የልጅነት ህልሜን ለምን አልኖርም አልኩ ድራማ ሰራው ታወኩኝ ደስ አለኝ መስመሬን ወደዚክ ቀየርኩኝ አንድ ሰው ተዋወኩ መልካም ሰው ነው ችግሬን ነገርኩት ወጣት ስለነበር ተረዳኝ ስራ እንድጀምር የንግድ ስራ አሳየኝ ከልጁጋር ጎደኛሞች ሆንን  የልጅነት ህልሜ ተሳካልኝ ለኔ ውድቀቴን ሲመኙ ጥንካሬዬን አሳየዋቸው አሁን ተዋናይት ተባልኩ።

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

27 Dec, 10:00


መለያ ኮድ 008

በመጀመሪያ ዳኞች እና የዚህ ግሩፕ ቤተሰቦችን ከልብ አመሰግናለሁ ክብር ይስጥልኝ🙏
ምርጫውስጥ እገባለሁ ብዬ አላሰብኩም ምናልባት በእኔ ታሪክ 1 ሰው ቢማርበት ብዬ  ነበር የፃፍኩት።

ቢሆን እና ቢሳካልኝ ሙሉ  ወደፊልም ቢቀየር ደስ ይለኛል ግን ደግሞ መለየት ግዴታ ከሆነ።

እኔ የመጨረሻ ልጅ እንደመሆኔ አቅብጠው ነው ያሳደጉኝ አባት ስሌለኝ ወንድሜ እኔን ለማስተማር ከሰው እንዳላንስ የሚከፍለው መሰዋትነት እና ከእናቴ አፍ ሁሌም የማይጠፋው የሴት ልጅ እንዳታስብሉኝ የሚለው ምክሯ በአንድ የተረገመች ቀን sport ቤት ብለው ባስገቡኝ ስአት የእናቴን ምክር የወንድሜን ልፋት ዋጋ ቢስ አደረኩኝ።

ያኔ sport ቤት ከገባሁ ቦሗላ  ዳውድ ከሚባላል ሙስሊም ልጅ ጋር ፍቅር ጀመርኩ እኔ ክርስቲያን ነኝ  ነገር ግን ዳውድ ሀይማኖቱን እንደሚቀይርልኝ ቃል ገብቶልኝ ነበር የጀመርን ወንድሜ ገና በልጅነቴ ፍቅር ከመጀመሬም በላየ  ልጁ ሙስሊም በመሆኑ በጣም የተናደደ። ከዳውድ እና ከሱ ምረጪ ነበር ያለኝ እኔ ለዳውድ ላልከዳው ቃል እና ፍቅር ስላለኝ ምንም ሳላቅማማ ዳውድን ምርጫዬ አደረኩ ከዛ ቀን በኋላ  ቤተሰብ በጣም ገልተኛ አድረጉኝ።

ዳውድ ስራ የለውም  በsport ቢጨርስም በራሱ ስም ከፍቶ ለመስራት ግዴታፈርስት ዳን ያስፈልጋል። ፈርስት ዳን ለመፈተን 2000 ብር ግዴታ ያስፈልገዋል ያነን ብር ለማገኘት የተጨነቅነው ጪንቀት አይረሳኝም ዳውድ በጣም ከፈቶት እያለቀሰ ነበር ብር የምናገኝበት መንገድ ምንም አልነበረም እንዴትም ብለን ብሩን ለማግኜት እንሞክራለን ብዬው ተለያየን በጣም ተጨነኩ ገራ ገባኝ በመጨረሻም አንድ ነገር ወሰንኩ። ፊልም ላይ ያየሁትን የእውነት ልተገብር እራሴን ለመሸጥ ውስጤን አሳምኜ አባንዳ የሚባል ሆቴል ሄድኩ።

ከዛ በፊት ስለሴተኛ አዳሪ የነበረኝ አመለካከት በጣም ያስጠላ ነበር። ሴተኛ አዳሪዎች ወላጅ የሌላቸው እንደፈለጉ ሁነው ያደጉ በቃ ባለጌ መስለው ነበር የሚታዩኝ። ለካ ሰው ወዶ አይደለም እንደዚህ አይነት ሂዎት ውስጥ የሚገባው በኔ ሲደርስ ተረዳኋቸው።

እኔ አልኮል ነክ ጠጥቼ እንኳን አላቅም።ገብቼም ያዘዝኩት ስፕራይት  ነው ገና ስገባ ዳውድ በጣም የሚወደው ጓደኛው ቴዲ ባጃጅ ሲያልፍ አይቶኝ ነበር ተከትሎኝ የገባ።ሁኔታዬን ሲያይ የተጣላን መስሎት ነበር ሁሉንም ነገር ነግሬው እንሂድ ቢለኝም አልወጣም ብዬው እሱ ግን ሄደ ቴዲ ሲመለስ ብቻውን አልነበረም።  ብሩንም ዳውድንመ ይዞልኝ ነበር የመጣ ።ቴዲ የመኪና እረዳት ነው በቂ ስራ የለውም ግን ከሌሎች ጓደኞቹ ተቀብሎ ነበር ብሩን ያመጣልን። ደውድ እዛ ውስጥ በመግባቴ በጣም አዘነ አስጨነኩሽ አይደል ብሎ በጣም አለቀሰ እኔ ጠንካራ ሁኜ አይዞህ እያልኩ ብሩን በማግኘታችንም ተደስተን ያ ቀን አለፈ። እሱም ሂዶ ፈተናውን አልፎ መጣ። ከባዱ ጊዜ ስራ የሚጀምረው ከከተማ ውጪ በመሁኑ የትራንስፖርት ብር የለውም ያን ግዜ እናቴ በኔ አትጨክንም እና ለብስኩት እያለች 10ም 5ም ተሰጠኛለች የኮፒም እያልኩ እቀበላታለሁ አንዳዴ ሱቅ ስትልከኝ ቀናንሺ ሰባስቢ ለዳውድ ለትራንስፖርቱ ነበር የምሰጠው እሱ 20ብር ይዞ እኔ 50 ብር ከያዝኩ እቀይረዋለሁ።ያነን ሁሉ ፈተና ካለፍን በደንብ ስራ ከጀመረ በኋላ በጣም ነበር የሚንከባከበኝ ደስ የሚል ጊዜ ነበር። የማያልፍ የለም ያ አልፎ ሳይነስ በጣም ያመኝ ጀመር በፊቴ ላይም እንደቡጉር እየወጣ ፊቴ ሙሉ በሙሉ ቆሰለ ከቤት መውጣት እንኳን ፈራሁ ሙሉ ሰውነቴ ቆሳሰለ  በጣም ሲብስብኝ ፀበል ገባሁ።

ከፀበል ስወጣ በፊቴ እና በሰውነቴ ላይ የነበረው ቁስል ሁሉ ድኖልኝ ሲያዬኝ በጣም ደስ ብሎት የሚቀበለኝ አድርጌ ነበር የጠበኩት። የኔን መዳን አይቶ ቶሎ ክርስቲያን ይሆናል ብዬ ነበር ያሰብኩት። ነገር ግን ስመለስ ያልጠበኩት ነገር ነበር የገጠመኝ። ፀባዩ ተቀይሯል በቃ ሌላ ሰው ሁኖ  አዲስ ሂዎት ጀመሮ ጠበቀኝ ልጅቷ ጎረቤታችን ነች የሀብታም ልጅ ነች ደውዬ እያለቀስኩ ማንም የለኝም እባክሽ ተይልኝ  ብዬ ለመንኳት በጣም ደንግጣለች  እሽ ብላ ዘጋችብኝ። 5 ደቂቃ ሳይቆይ ደውድ ደውሎ ሂዎቴን በጠበጥሽዋ? አለኝ  እኔ ያልጠበኩት ንግግር ስለሆነ እሽ ይቅርታ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት።በገንዘብ እኔን ቀየረኝ።
ያኔ ለኔ ከባድ ነበር አለም ሁሉ ነበር የጨለመብኝ።ከቤተሰቤ ያስበለጥኩት ሌላ የሃብታምልጅ ከኔ አስበልጦ ሄደ።

ሁሉም ነገር ከበደኝ ግን ቢከብደኝም መጠንከር ነበረብኝ ትምህርቴን ላለማቆም የቀን እየሰራሁ የማታ እየተማኩ ከዛም አልፎ ክረምት እረፍት በሆንኩበት ሰዓት የትወና ስልጠና ለመማር አ.አ ሂጄ ተማርኩ አሁን በጣም ደስተኛ ነኝ በዛላይ ዘንድሮ እመረቃለሁ። ጥንካሬዬን በመከራዎቼ በፈተናዎቼ ውስጥ አግቼዋለሁ ።እድሜ ለዳውድ  ምንም ሰው እንዳልቀርብ አድርጎ አስተምሮኝ አልፏል  ሰለሁሉም
ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ🙏

የቃላት ስህተት ካለው ይቅርታ ይደረግልኝ🙏

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

26 Dec, 16:00


መለያ ኮድ 006

የተወለድኩት አ.አ ውስጥ ነው።አሁን ላይ በጣም አሪፍ ሂወት ነው ያለኝ ግን አባቴ እና እናቴ ግን ተቸግረው እና ተሰቃይተው ነው እኔን የወለዱኝም እዚም ያደረሱኝ ። ማለትም አባቴ እናቴን ሳያገኝ በፊት የሚኖረው ገጠር ውስጥ ነው።ገበሬ ወይም አራሽ ነበር።እናም ከወንድምና እህቶቹ ጋር አይስማም ነበር፤ግን በጣም ሚገርመው ያለምንም ምክንያት ነበር ሚጠሉት ባጭሩ ክፋዎች ነበሩ ፤ከመጥላታቸውም ብዛት ብዙ ጊዜ ሊጎዱት ሞክረዋል ።ግን አባቴ ይህን ሁሉ ታግሶ ብዙ ቆየ ነገርግን ነገሮች በጣም እየከበዱበት መጡ ራሱን እስከማጥፋት ድረስ፤ከጊዜያት በዋላም ከፈጣሪ ጋር እና አንድ በጣም ሚወደው ጓደኛም ነበረው።ከሱ ጋር በመካከር ከቤት ለመጥፋት ወሰነ፤እና ቤተሰቡን እንኳን ሳይሰናበት እንዳለው ትንሽ ብር ተበድሮ ከጓደኛው የራሱንም ጨምሮ ወደ አ.አ መጣ ጠፋ። ማንንም እና ምኑንም ሳያቅ ማለት ነው።እንደመጣም ከትንሽ ቀናት በዋላ ቀን ስራ  እና የመሳሰሉትን ስራዎች መስራት ጀመረ፣ቤትም ተከራየ ኑሮውንም እንደዛ መኖር ጀመረ እና ፤እንደዛ እንኳን እየሰራ በሚችለው ቤተሰቡን ይረዳ ነበር የሚጠሉትንም ወንድምና እህት ጨምሮ፤.....እና ወደእናቴ ደሞ ስንመጣ የሀብታም ቤተሰብ ልጅ ናት፤እና ገና በተወለደች በ 3ወሯ ነበር ሙሉ ቤተሰቦቿ የሞቱባት፤እናም ያደገችው በሞግዚቷ ነበር ከ3ወሯ ጀምሮ።እናም ሞግዚቷም ከልጆቿ በላይ አርጋ አሳደጓት በጣምም ይወዷት ነበር።አድጋም ትምህርትም ጀመረች፤ከጊዚያት በዋላም እናቴ 11 ክፍል ደርሳ መማር ጀመረች።እናም የእናትና አባቴ ህይወት እዚጋ ነው የጀመረው። ከለታት አንድ ቀን አባቴ ኑሮውን ለማሸነፍ ተፍ ተፍ እያለ እናቴም ወደ ት/ቤት እየሄደች እያለ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዩት ግን አባቴ እንዳያት ነበር የወደዳት እሷ ግን ብዙም አላስተዋለችውም ነበር፤ግን በተደጋጋሚ መተያየቱን ቀጠሉ፤አንድ ቀንም ደፈር ብሎ አናገራት እሷም ትንሽ ተግደርድራ ሀሳቡን ተቀበለችው።መዋደድም ጀመሩ፤ግን አባቴ ስላላስቻለው እሷ ምትኖርበት ቤት ውስጥ ተከራየ ይበልጥም መቀራረብም ጀመሩ ። ግን አባቴ ስራውን ትቶ እሷን ማሰብ መሸኘት ሆነ ስራው እሷም ትምህርት እያለች ጊዜዋን ማሳለፍ ጀመረች።እናም ኑሮ እየከበደው መጣ በዛ ላይም የሷ ቤተሰቦች ያላቸውን ግንኙነት አወቁ፤ሲሰሙም ከቤት አባረሩት።ጎዳናም ወጣ፤ነገሮችም ተደራረቡበት፣እናቴንም ማግኘት አቆመ። ግን እናቴ እየሸወደችና ትምህርት እየቀረች እሱን ማግኘት ጀመረች።ፍቅራቸውም በጎዳና ላይ ይበልጡኑ ተባባሰ፤እናም ተነጋገሩና እሷም እሱም ተያይዘው ጠፉ ያለምንም ብር፣ቤት እና ወዘተ በፍቅር ብቻ።ከዛም አባቴ ያገኘውን መስራት ጀመረ እሷም ትምህርቷን አቁማ ተከራይተው መኖር ጀመሩ። በመሀልም እኔ ተረገዝኩ እና እሱ ጊዜም በጣም ከባድ ነበር ማለትም መራቡ መጨነቁ እኔን ማሳደጉ በዛ ላይም ስራ ማጣቱ መኖርያም ያስፈልጋል ደሞ ማንምም አይረዳቸውም እና በቃ በጣም ተሰቃይተው ነበር በዛ ላይ።እሷን መንከባከብና የቤተሰብ ሁኔታ አባቴን አስጨንቆት ነበር ፤ግን ሁሌ በፈጣሪ ያምኑ ነበር ከፈጣሪ ጋርም ስራም አገኘ እና በሌሎች ነገሮች ችግሩን አለፈው። እኔም ተወለድኩ ትንሽም አደኩኝ።፤እሷም ቤተሰቦቿን እንደምንም አሳምናቸው ተስማማች እኔንም ለነሱ ሰጠችኝ ለትንሽ ጊዜ ቢሆንም ያው የተሻለ ህይወትን ወደፊት ለመኖር ብለው ሁለቱም መስራት ጀመሩ ።የተሻለ ነገርም ማግኘት ቻሉ ፤እና እኔንም መልሰው ወሰዱኝ ሰፈርም ቀይረን መኖር ጀመርን፤ተጨማሪ  2 ወንድ እና 2ሴትም ወለዱ። እኔም አድጌላቸው በአቅሜ አግዛቸዋለሀ ያው 12 ስለጨረስኩኝ እና በቃ በጣምም ደስተኛ ነን፤ያን ሁሉ ስቃይ አይተው አልፈውት እዚ አድርሰውናል፤በጣምም እወዳቸዋለሁም.....

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

26 Dec, 04:31


Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️ pinned «#ታሪኮን_ያጋሩ በAlex film production በተዘጋጀው #ታሪኮን_ያጋሩ ቻሌንጅ ስር በዳኞች እና በተመልካች ድምር ነጥብ ተመርጠው ባለታሪኮቹን የገንዘብ 💸💸  ተሸላሚ ለማድረግ እንዲሁም ወደ ፊልም 🎥 ለመቀየር በጉዞ ላይ የሚገኙ ምርጥ አምስት ታሪኮች እነሆ 👇👇 መለዶ ኮድ 003 መለዶ ኮድ 004 መለዶ ኮድ 006 መለዶ ኮድ 007 መለዶ ኮድ 008 🎉 ባለታሪኮች እንኳን ደስ አላችሁ!⚡️»

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

26 Dec, 03:01


መለያ ኮድ 004

የምኖረው ከ አያቴ ጋር ነበር በ አጋጣሚ ዳንኤል የሚባል የሰፈሬ ልጅ ጋር ተዋወኩ በመግባባትም ብዙ የፍቅር ጊዜያትን አሳለፍን በሆነ አጋጣሚ እሱ ወደ ውትድርና ሄደ እኔም እወደው ስለነበር ከሱጋር ሄድኩኝ እዛም ወጥ ቤት መስራት ጀመርኩ እዛም 1 የሴት ጓደኛ አገኘው እሱም ስልጠናውን ጨርሶ አንድ ቀን ወደ ውጊያ ሄደ እንድ እግሩን ተመታ በዛውም ጡረታ ወጣ አብረንም ተጋብተን በፍቅር መኖር ጀመርን አንድ ሴት ወለድን እሷም ፈጣሪ ስላልፈቀደ በ 3 ወራ አረፈች  እግዚአብሔር ፍቃድ 2ተኛ ሴት ልጅ ወለድን ስሞንም ቅድስት አላት የተወለደችው ድሬደዋ ነበር ከዛም ወደ በዴሳ የምትባል ከተማ ገባን ብዙ አመታትን በሰላም እየኖርን እያለ አንዳንድ ጊዜ ያልሆነ ባህሪ ማምጣት ጀመረ ልጄም 5 አመት ሆናት ከለታት አንድ ቀን ታዲያ እኔ በከሰል ሽሮ እየሰራው ሳለ አሱ በመሀል መቶ  ነገ የጓደኞዬ ሚስት ስለወለደች ሄደን እንጠይቃታለን ሲለኝ እኔ ደግሞ አይመቸኝም ብዬ መለስኩለት በመሀልም ጭቅጭቅ ተፈጠረ እሱም ተናዶ ሲወጣ ሽሮውን በርግጫ ብሎ ደፋብኝ እኔም ኡኡ ብዬ ስጮህ ጎረቤት መተው ሆስፒታል ወሰዱኝ እንደ አጋጣሚ ሲለጋው አንኔን ጨፍኜ ስለነበር አይኔ ውስጥ አልገባም ግን ፊቴ ,ደረቴ,እግሬ ላይ ነበር የተደፋው ህክምና ከተደረገልኝ በኋላ ወደ ዘመዶቼ ጋር ገባው ዘመዶቼም ተሰብስበው ካልገደልው አሉ ከዛም ፖሊሶች ወስደውት ሲጠይቁት ካደ ይህ ሁሉ ነገር ሲፈጠር ልጄ ትመለከት ነበር ፖሊሶቹም ልጅቶን ጠየቆት ልጅቶም ያየችውን ተናገረች እሱም 2 አመት ተፈረደበት እኔም ልጄን ይዤ ደወ ድሬ ደዋ መጣው በመሀልም ሁርሶ እያለን ያወኮትን ጓደኞዬን አገኘዋት እሷም ደንግጣ ስጠይቀኝ ሁሉንም ነገር ነገርኮት ልጄን እሷ ጋር እያስቀመጥኩ ሰው ቤት ስራ መስራት ጀመርኩ በዛ መሀል ብዙ ችግሮች እና መከራዎች መምጣት ጀመሩ ከምንም በላይ ልጄ የሰው አባት ስታይ ትቀና ነበር ወንድም እኸት የላት ብዬ በማሰብ መልኬን ህይወቴን ቢያመላሸውን የልጄ ስል በስልክ መነጋገር ጀመርን በ አመትም 1 እየሄጀች ታየዋለች እሱም ይመጣል የ አንድ ቀን ስህተት የዘላለም ፀፀት ሆነበት ከዛ ሁሉ በኋላ ይቅርታ አድርጌለት አብርን ባንኖርም ልጃችንን አብረን እያሳደግን ነው ለሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን ሁሉም መከራ ችግርም አልፌ ከልጄ ጋር እዚህ ደርሼአለው ።

"  እናት ለልጆ የማትከፍለው
       መሰዋትነት የለም"

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

25 Dec, 16:01


መለያ ኮድ 003

እኔ እንዲሰራልኝ የምፈልገው ከአባቴ ጋር እና ከአሳዳጊየ ጋር ያለውን ታሪኬን ነው።

እናም ወደ ታሪኬ ሰገባ።

እናቴ ከሞተች በሃላ አባቴ ምንም ስራ የሌለው ሆነ ለእኔ ጫማ መግዛት አልቻለም። (ባራባሶ) ወይም የጎማ ጫማ ነበር የሚገዛልኝ ጫማው ቶሎ ሰለማያልቅ እሱን ነበር የሚደረገው እኔም አባቴም ።
ምግብ በአግባቡ አልበላም እሱ ስራ
ፈለጋ ከሄድ ቶሎ ሰለማይመለስ  ቤት
ምንም ነገር ሰለሌለ በየ ሆቴሉ እየዞርኩኝ
ብሌ እየበላው ነው እቤት የምመጣው።

የጎረቤት ቤት ምግብ ይሸጣል ቤታችን የመንግሰት ቤት ሰለሆነ ተያይዞ ነው ያለው ጊቢያችን አንድ ነው።

እናም ምግብ ስለምሽጡ አባቴን ሁሉም አሰቸግርዋለው ምግብ ካልገዛህልኝ ብየው  የጎረቤት ልጆች የሚደረግላቸውን ባየው ቁጥር ለእኔም እንደነሱ ግዛልኝ እያልኩ አስቸግርዋለው።

የእኔ ፈላጎት ከአቅሙ በላይ ሰሆንበት ዱቤ ምግብ መውሰድ ጀመረ።

ሁልጊዜ ሰለምንወሰድ  አባቴ ላይ ገንዘብ ተወዘፈበት።
ያለውን ሸጦ የድቤውን ከፈለ ከዛ ግዜ ጀምሮ የምግቤቱ ቤት ጓሮ ድስት አሰቀምጠን ከሰወች የተርፈ ቡሌ መብላት ጀመር። ጥዋት ተነስተን ድስቱን ከጓሮ ካሰቀመጥን በሀላ ምሳ ሰዓት ድርስ ድስቱ ይሞላል ያን ምሳ ከበላን ለእራት እናስቀምጣለን የእለት ኑሮዋችን እንደዛ ሆነ።

አባቴ ደሞ መጠጥ እና ስጋራ ያጨሳል መጠጥ ለመጠጣት ከወጣ እቤት ቶሎ አይመጣም በጨለማ እሱን ሆቴል ለሆቴል እየገባው ፈልገዋለው ሳጣው ከአጥር ግቤ ውጭ በረንዳ ላይ ቁጭ ብየ  እስኪመጣ  ድርሱ ብርድ ላይ ሆኝ እጠብቀዋለውኝ።

  እየተንገዳገደ ነው የሚመጣው እቤት ገብቶ ከተኛ አንሶላ አልብሸው
እኔ መደብ ላይ እተናለው።

ሰያመኝ ህክምና አላውቅም እፅዋት ነው የኔ መደሀኒት ምክንያቱም ገንዘብ ቶሎ ቶሎ አያገኝም ካገኝም የእኔን ፈላጎት ለሟሟላት ነው የሚፈልገው ።

ስራ የሚሰራው ያገኝውን ነው ግንበኝነት ይሰራል፣ ሺንት ቤት ይቆፈራል፣
ጥበቃ ይሰራል።

አባቴ  ምንም በላወኩበት በፀና ታመመ  ሆስፒታ ለብዙ ግዜ ታሞ ታክሞ ሰውጣ የማሳደግ አቅም ሰላጣ ለአሳዳጊ  ስጠኝ።

አሳዳጊየ ቤት የበጎች እረኛ ሆንኩኝ ትምህርት ቤታችን እሩቅ ነው  የጥዋት ተማር  ከክላሰ ሰንለቀቅ  ለምሳ በቶሎ ቤት መድርስ አለብኝ ካለዝያ ዛፍ ላይ በፈሰታል ተንጠልጥሎ ነው ምግቡ የምቀመጥልኝ እሱዋ ስራ ትሄዳለች እሱዋ ከሎለች በር ክፈት አይደርግልኝም።

ውሎየ ሁሉም ከበጎች ጋር እና በአግባብ መሰማት የተሳናት ልጅ ጋር ነው ጓድኝነቴ
  የምልክት ቋንቋ የምናገሩ ትምህርት ቤት ነው የምትማርው ።

ዘውትር ውሎየ ከበጎች ጋር ስለሆነ
ትምህርት ቤት ለሶስት እንድ ወንበር ላይ ስንቀመጥ ልጆች ለማሰቀመጥ አይፈልጉኝም።
ምክንያቱም በግ በግ ትሽቻለሺ፣ ሺንት ሺንት ትሼቻለሺ፣  እያሉኝ ያሳቅቁኝ ነበር።

አሳዳጊየ የትምህርት ቤትም ሆነ የሰፈር ጓደኛ መያዝ አትፈቅድልኝም ለምን እንድሆነ ባላውቅም ።
የስፈር ልጆች እንዳንዶች ቦታም  አይሰጡኝም እረኛ  ሰለሆንኩ።

አንድ ላይ ሰንጫወት ተጠራርተው አንድ ሰው ቤት ለመጫወት የምንገባ ከሆነ ሎሌሎችን አሰገብተው እኔን ከልክላኝ በር የዘጉብኝ ልጆች ነበሩ ሰፈር ላይ።

ስፈር  መጠርያ አንዳንድ ልጅች ያወጡልኝ አንቺ በግ፣ አንቺ እርኛዋ፣ ዳዊት እንድዛ የሚጠሩኝ አሉ   ከዛ ግዜ ልጆች ላይ  ቂም እየያዝኩ አደኩኝ።
ከግዜ በሀላ ዝምተኛ የምትባል ልጅ መሆን ጀመርኩኝ ከሰው ጋር አላወራም።

ከዛ ከፍ እያልኩኝ መጣው  የሆነ ግዜ ከእኔ በእድሜ ከፍ የሚል ልጅ  ሰፈራችን አይቸው የማላውቀው ልጅ የጎርቤታችን ልጅ የትምህርት ቤት ጓደኛው እኛ ሰፈር  ጋር መቶ  በጎችን ስጠብ  በፍቅር አይን ያየኝ እሱ ነው።
ልጅ በጣም አፈቀርኝ እና ቤታችን ይመላለስ ነበር በሰው ያሰጠይቀኝ ነበር።

ወንዶችን የማስበው ወድ ፍቅር ህይውት ውሰጥ ብገባ ከአላማየ ያሰናክለኛል ብየ ሰለማሰብ ለወንዶች ቦታ አልሰጠም ።

ሰለምያፍቅርኝ ብዙ ልያሳምነኝ ሞከር
በጎችን የምጠብቅበት ደርስ መቶ ሰያወራኝ እኔ እጆቼ እና እግሬ በላብ ስምጥ ይለኝ ነበር ከፍርሀት የተነሳ ።

አንድ ግዜ አምስቼ ወደ ቤት ሰመጣ መንገድ ላይ ተገናኘኝ እጀን ይዞ ካላወራሺኝ አለቅሺም እያለ ሰንታገል  በኛ ለይ የመኪና ባዉዛ ስያበራብን  በእጆቹ እና በትከሻው ልከልለኝ የሞከረው ግዜ ሁሉ ነበር እንደዛም ሆኖ እኔ ዝምተኛ ነኝ ምንም ነገር አላዋራውም።

የፍቅር ጥያቀ ከሰፈሩ ወደ ትምህርት ቤት አጀግ።
ከዛ ግዜ ጀመሮ ለካ ሰው ይወደኛል የሚለውን ማሰብ ጀመርኩኝ።

ያልጅ ብዙ ልያሳምነኝ ሞከር እኔ ግን አላማየ ሰው ሆኝ ሰው እንድገርምብኝ ስለነበረ የፍቅር ጥያቄውን አልተቀበልኩኝም  የዛኔ የ6ኛ ክፍል ተማር ነበርኩኝ።
ልጅም ሰፈራችን መምጣት ተወ ሳንገናኝ ተለያይተን ቀርን።

የ8ኛ ከፍል ተማሪ ስሆን ደሞ ሁሉም ደብዳቤ ደብተር ውሰጥ አግኝ ጀመረ ለካ የሚፀፈልኝ ልጅ አብሮኝ የሚቀመጥ ልጀ ነበር።
በሁሉም ነገር ይንከባከበኛል ለራሱ ለመብላት የገዛውን ነገር ሁሉ ለእኔ ነበር የምሰጠኝ ይሄን ሁሉ ሰያደርግ አይገባኝም ነበር።

አንድ ቀን የሎላ ክፈል ተማሪ ደብዳቤ ፅፎ ለእኔ እንድሰጠኝ ተሰጠው ደብዳቤውን አብረን አነበብን እሱም ያን ልጅ ሰድበው ጥሩ ልጅ አይደለም ሰለኝ ባለኝ መሰርት መልስ የስድብ መልስ ለልጅ ሰጠውኝ ያቀበለው እሱ ነበር ከዛ ግዜ ጀምሮ ደብዳቤውን የላከልኝ ልጅ ጠፍ።

ከ3ቁን በሃላ አብሮኝ የሚቀመጠው ልጅ በጓደኛው አሰጠልኝ ለካስ ደብተር ውስጥ ስያሰቀምጥ የነበረው እሱ ነበር እሱ እንደሆነ አላውቅም ነበር በጓደኛ
ው ስልክልኝ ነው ያወኩት ።

የፍቅር ጥያቄውን እንደማይሆን ነገርኩኝ ከዛን በ8 ክፍል ምንሰትሩ ምክንያት እሱ አለፈ እኔ ወደኩኝ በዛ ተለያየን ሳንገናኝ ብዙ ግዝያቶችን ካሳለፈን እኔ ጭራሺ እርሰቸው ነበር እሱ ግን አርሳኝም።

ከሰባት እሰከ ሰምንት አመታት በሀላ ሆነ ግዜ ስልኬን አፈላልጎ ደወለልኝ እና አሁንም ደርስ እንደምያፈቅርኝ እና የመጀመሪያ ፍቅር የያዘበት ግዜ ላይ ፎቶ  ተነስ ከጀርባው ላይ ፍቅር የተያዝኩበት ግዜ ብሎ የፃፈውን በ imo video chat ፎቶውን አሳየኝ።

እንደዛም ሆኖ እኔ ምንም ቦታ ለሱ የለኝም አላማየ ሀኪም ሆኝ የተሻለ ሰው ሆኝ በሰፈሩ መታየት ስለምፈልግ የፍቅር ህይወት ያንን አላማየን ያበላሸዋል ብየ ስለማምን ከማንም ጋር የፍቅር ህይወት ለመጀመር አልወሰንኩም።

ከዛ በሀላ አሁን ላይ እሱም አገባ ግን ምንም ያገባት ሴት እንድኔ ልያፈቅራት እንዳልቻለ ይነግረኛል።

እኔም ብዙ የፍቅር ህይወት ሳላሳልፍ የህክምና ትምህርቴን ልጨርስ ነው እሱ ግን አሁን ድርስ ይደውልልኛል ድር በጣም ሰለምያፍቅርኝ ክላስ ተምሮ እስከሚወጣ ድር ቀና ብሎ አያየኝም አሁን ድርስ አግብቶም እኔን በሙሉ አይኑ ለማየት አይደፈርም።

ከህይወት የተማርኩት ከጠነከረን እና አላማችንን ካሰብን ወደምንፈልገው ነገር ለመድረስ ምንም ልያስቆመን እንደማይችል ተምሬበታለው።

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

25 Dec, 13:14


#ታሪኮን_ያጋሩ
ሰላም ውድ የAlex casting and film production ቤተሰብ እንደምን ቆያችሁ

⚡️ በታሪኮን ያጋሩ ቻሌንጅ ምርጥ ሶስት ወደ ፊልም 🎥 ለመቀየርና የገንዘብ💸💸 ተሸላሚ ለመሆን የሚወዳደሩ ታሪኮችን የምንለይበት ሁለተኛው ዙር ውድድር ተጀምሯል።🎉

ስለሆነም ታሪኮችን በማንበብና ድምጽ በመስጠት እንደ የመጀመሪያው ዙር አብራችሁን ሁኑ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን🙏

📌 የመጀመሪያው ታሪክ ዛሬ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ በዚሁ ቻናል ላይ የምናጋራችሁ ይሆናል።

ለተወዳዳሪ ባለታሪኮች መልካሙን ሁሉ ተመኘን🙏

Alex casting & film production

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

24 Dec, 21:48


https://t.me/Starsop_bot?start=_tgr_R2oQoS1lMzZk

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

18 Dec, 17:03


#ታሪኮን_ያጋሩ

በAlex film production በተዘጋጀው #ታሪኮን_ያጋሩ ቻሌንጅ ስር በዳኞች እና በተመልካች ድምር ነጥብ ተመርጠው ባለታሪኮቹን የገንዘብ 💸💸  ተሸላሚ ለማድረግ እንዲሁም ወደ ፊልም 🎥 ለመቀየር በጉዞ ላይ የሚገኙ ምርጥ አምስት ታሪኮች እነሆ 👇👇

መለዶ ኮድ 003
መለዶ ኮድ 004
መለዶ ኮድ 006
መለዶ ኮድ 007
መለዶ ኮድ 008

🎉 ባለታሪኮች እንኳን ደስ አላችሁ!⚡️

🔑 አምስታችሁ ባለታሪኮች ለቀጣይ ዙር ምርጥ ሦስት ታሪኮች ለሚመረጡበት ውድድር አልፋችኋል።

ማሳሰቢያ📌
ባለታሪኮች ከላካችሁት አጠቃላይ የሕይወት ጉዞ ታሪካችሁ ውስጥ ወደ ፊልም 🎬 እንዲቀየር የምትፈልጉትን ቦታ ለይታችሁ ዳግም ጻፉት።
የጻፋችሁትን ታሪክ በ (@al_as13_7) ላይ በሁለት ቀናት ጊዜ ውስጥ ታጋሩናላችሁ🙏

📩 ለተጨማሪ መረጃ @writeramanu ላይ መጠየቅ ትችላላችሁ።

🌟መልካም ዕድል!🌟

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

17 Dec, 20:40


Live stream finished (1 hour)

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

17 Dec, 18:54


ምርጥ አምስት ሊለዩ ነው ባለ ታሪኮች የት ናችሁ ።

ደጋፊዎችስ የናንተ ምርጡ ታሪክ የቱ ነው ምርጫችሁ በኮሜንት ስር አሳውቁን።

በፊልም ልትመለከቱት ያሰባችሁት ታሪክ የቱ ነው?

አሸናፊዎች ይሸለማሉ ታሪካቸው ህይወት ተዘርቶበት በምስል ትመለከቱታላችሁ።

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

17 Dec, 18:41


Live stream started

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

17 Dec, 18:35


Live stream scheduled for

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

17 Dec, 06:42


ክቡራን የተመረጣችሁ ዳኞቻችን የተጋሩት ታሪኮች በተሰጠው የማወዳደርያ መስፈርት መርጣችሁ እሰከ ዛሬ ምሽት አራት ሰአት ታሪኮቹ ከነ ውጥታቸው እድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን 🙏

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

12 Dec, 18:26


Live stream finished (12 minutes)

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

12 Dec, 18:14


Live stream started

Alex casting & film production ♈️ (አሌክስ )ካስቲንግ ️️

10 Dec, 20:54


Live stream finished (2 hours)