የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት @gcyu9 Channel on Telegram

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

@gcyu9


በዚህ ህብረት ውስጥ
#1 መንፈሳዊ የሆኑ መጣጥፎችን በመለጠፍ እንማማር እንጂ ለሌላ መጥፎ ዓላማ ማዋል የተከለከለ ነው።
#2 መንፈሳዊ መዝሙሮችን ፣ ስብከቶችን ፣ እይታዎችን በመለጠፍ...አብረን ወደ ክርስቶስ ሙላት እንደግ ዘንድ ግብዣችን ነው።

ሳምንታዊ ፕሮግራም ስለጀመርን በየሳምንቱ ዓርብ ምሽት ከ3:30 - 5:00 የሚቆይ መንፈሳዊ ተከታታይ ትምህርት ይኖረናል።

ወጣትነታችንን ለክርስቶስ!!

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት (Amharic)

እንኳን ወደ የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት የቴሌግራም አባል 'gcyu9' በልዩ ቦርዱ እና ለዚህ ቦርዱ እርዳታ መሳሪያ አማካኝ የነበረው ተግባር መሆኑን በግልፅ ማገዝ እየተከተሉ ባለፈው መልኩ እንደገናና ዜና አካባቢ ላይ ተከትሏል. የክርስቲያን ነገሮችን ውጤቶችንን ወደ ጉም እንቀናለን ለሚለወጣው ህብረት በከባድ ተግባራት እንጠንክርላቸዋለን. ይህ ቦርዱ ከዚህ ቦርዱ ላይ በአሳች ለማንበብ የሚዘው ያለ ህብረት የጠበቁ ቢሆንም የተለያዩ የወጣት ክሊኒንዴር በመንካታቸው ይውረዳሰናል. የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት በአጠቃላይ መጽሀፍ አቀማመ፡ አጠቃላይ ሽልማቶችን መረጃዋን ማስረጃዋን የሚጠቀሙ ሰዶምን ለማገዝ ፣ የወጣትን ግንኙነት አማካኝ እና ሌሎች አጠቃላይ ክንውንዝንና የሕብረቁጥር ተግባራት እንጠቀማቸዋለን።

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

24 Jan, 08:23


🚨ምን ይፈልጋሉ?
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

20 Jan, 17:06


✍️ ውብ ቀኔ አንተ ነህ
*
ሚያስፈራው ሌሊት ምሽቱ ውድቅቱ
አይሎ ሳለ ፅልመቱ
የፅድቅ ፀሐይ ሆነኸኝ ቀኔ
አፌን ሞላኸው በቅኔ

አለልኝ እላለሁ የአብ ቃል
ካንተ ጋ ያለ ሰው ደስታው መቼ ያልቃል
የነገስክ ጨለማዬን ሽረህ
አለልኝ የምልህ ውብ ቀኔ አንተ ነህ

ውብ ቀኔ አንተ ነህ
ብርሃኔ አንተ ነህ
ንጋቴ አንተ ነህ
ቅኔዬ ቃል ያለህ

ንጉሥ ነኝ ያለው ጨለማ ገስግሶ
ለሙሾ አጭቶኝ ለለቅሶ
መች ያውቅ ኖሯል ፣ እንዳለኝ ደራሽ
ደሙን የሰጠኝ ፣ ደም መላሽ

አለልኝ እላለሁ የአብ ቃል
ካንተ ጋ ያለ ሰው ደስታው መቼ ያልቃል
የነገስክ ጨለማዬን ሽረህ
አለልኝ የምልህ ውብ ቀኔ አንተ ነህ

ውብ ቀኔ አንተ ነህ
ብርሃኔ አንተ ነህ
ንጋቴ አንተ ነህ
ቅኔዬ ቃል ያለህ

ዳግም ላይጨልም በኔ ላይ ጨለማ
ሀዘን በቤቴ ላይገባ
ሳቅክልኝና ባንተ ፈገግታ
ድንኳኔን ሞላው እልልታ

ገጣሚ; ሔኖክ አሸብር

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

19 Jan, 18:42


የማንን መዝሙር ይፈልጋሉ?

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

17 Jan, 15:24


ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ።

ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ገላ. 4፥4-5

አዳምና ሔዋን ታላቁን ውድቀት ሳይወድቁ ወይም በጥንተ አብሶ ሳይበከሉ ምን ያህል እንደቆዩ አናውቅም። ቀናት? ሳምንታት? ወራት? ዓመት? ዓመታት? አናውቅም። ምን ያህል ሳይወድቁ እንደቆዩ ወይም እንደኖሩ ባይጻፍም፥ ግን ወደቁ፤ ሞትንም ሞቱ። በወደቁ ቀን ምሽት ላይ ለአዳም ካቀረበለት ጥያቄዎች 3ኛው፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? ነበር፤ ዘፍ. 3፥11። አስቀድሞ ግልጽ ትእዛዝ ተሰጥቶት ነበር። ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍ. 2፥17። አዳምና ሔዋን ወደቁ፤ ሞትንም ሞቱ። በሥጋ ወዲያው ሳይሆን ቆይተው ነው የሞቱት፤ በበሉ ቀን የሞት ኑሮን ጀመሩ። ሟቺዎች በምድር መኖር ጀመሩ። ከእግዚአብሔርም ኅብረት ተለዩ፤ ይህ መንፈሳዊው ሞት ነው።

በአዳምም፥ በሔዋንም፥ በእባብ (በሰይጣንም)፥ በምድርም እርግማን ተበየነ። እነ አዳም ምን ዓይነት ድርግም ያለ ጨለማ ውስጥ እንደገቡ እኛ ልንገምተው ብቻ ነው የምንችለው እንጂ አናውቀውም። በእግዚአብሔር እጅ ተሠርተው፥ ከሠሪያቸው ጋር በሰመረ ኅብረት የኖሩት ሲለያዩ የተፈጠረውን ታላቅ ውድቀት፥ እኛ ራሳችን በውድቀት ስለተወለድን ልንገምተው እንጂ ልንገልጠው አንችልም።

በዚያው ቀን ግን በስነ መለኮት፥ ‘መቅድመ ወንጌል’ የተባለው ተስፋ ተሰጠ፤ በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ። ዘፍ. 3፥15። አንድ ቀን የሚፈጸም ተስፋ ተሰጠ። ያ ተስፋ እየተጠበቀ ሺህዎች ዓመታት አልፈው የዘመኑ ፍጻሜ ደረሰ። ሐዋርያው ጳውሎስ በገላ. 4፥4-5 ያንን ገለጠ፤ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።

ዘመኑ ተፈጸመ። ያ ጊዜ እጅግ ትክክለኛው ጊዜ ነበረ። ተስፋ የሰጠው እግዚአብሔር ተስፋውን ፈጸመ፤ ልጁን ላከ። ይህ ልጁ ከዘላለም ጀምሮ የኖረ ሳለ፥ ዘላለማዊ ቃል ሥጋ ሆነ፤ በሥጋ መጣ፤ መለኮት ሳትቀነስበት በሰውነት ተገለጠ። ይህም ይሆን ዘንድ ከሴት ተወለደ። ተስፋው የተሰጠው፥ ‘በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል’ ተብሎ ነው። መንፈስ ቅዱስ በሴቲቱ (በኢየሱስ እናት በማርያም) ላይ መጣ፤ የልዑል ኃይልም በእርስዋ ጸለለ፤ ከእርስዋ የተወለደውም ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ ሉቃ. 1፥35። የሴቱቱ ዘር፥ የእግዚአብሔር ልጅ ተወለደ። እንደተሰጠው ተስፋም የእባቡን፥ የሰይጣንን ራስ ቀጠቀጠ፤ መታ፤ በቀራንዮ፥ በጎልጎታ።

ይህን ለምን አደረገ? እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ለምን ላከ? እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ገላ. 4፥5። ይዋጅ ዘንድ እና እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ። እዚህ ሁለት ትልልቅ ቃላት አሉ፤

አንደኛው፥ መዋጀት ነው። ἐξαγοράσῃ የሚለው ቃል ἐξαγοράζω (ኤክሳጎራዞ) ከሚል ቃል የመነጨ ነው። በቀጥታ ሲተረጎም ከገበያ ገዝቶ ማውጣት ማለት ነው። በዋጋ፥ በዎጆ ሙሉ በሙሉ መታደግ ነው። ከሕግ በታች፥ ከፍርድ በታች፥ ከኵነኔ በታች ያሉትን፥ የቀደመው ሞት የታወጀባቸውን ሊታደግ፤ ሊዋጅ።

ሁለተኛው υἱοθεσίαν ወይም υἱοθεσία (ሁዮቴሲያ) ልጅ ተደርጎ መወሰድ ነው። አንዳንድ የስሕተት አስተማሪዎች ይህንን ጥቅስ ያወላግዱትና ስሕተት ያስተምራሉ። ‘እኛ ልጆች ነን እንጂ ማደጎ አይደለንም!’ ይላሉ። እኛ ልጆች ነን? አዎን ነን። እንዴት ልጆች ሆንን? እንደ ልጆች በመደረግ፤ እንደ ልጆች ተደርገን በመወሰድ። እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ገላ. 4፥5።

ልደቱ ለእግዚእነን ስናስብ፥ ከሴት የተወለደውን የላከውን እና ለምን እንደላከውም እናስብ።

ከ ዘላለም መንግስቱ

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

13 Jan, 20:00


ርዕስ :- በማዕበላችን ላይ የሚረግጥ

◉ በህይወታችን ማዕበል ያጋጥመናል ይህም በትዳር፣ በግል ህይወት፣ በስራ፣ በመንፈሳዊ ህይወት እና በሌሎችም ምዕራፎች ሊሆን ይችላል።

◉ አንዳንድ ጊዜ መጓዝ ጣር ሲሆን መሄድ ሲያቅት ብርቱ መፍጨርጨር እናደርጋለን ግን ያ አልሰራ ይላል።

◉ አብሮኝ የሚቆም የለም ያልንበት ቀን በዛ ጊዜ ብቸኛ ተስፋ እርሱ ነው።

◉ የጌታን እርዳታ በፈለግንበት ጊዜ ያ እያየን ነው ከመጣስ ይረዳል ብለን እንጠይቃል።

📖 ማር 6:45-52

- ቀደም ብሎ የእንጀራውና አሳ የበዛበት ታሪክ ነበር።
- ደቀ መዛሙርቱ ያንን ያዩበት ይጠቅማቸው ነበር በማዕበሉ ለገጠማቸው ነገር።

◉ ተአምር አይታን ስናበቃ ምንድን ነው ማስተዋል ያለብን :-

1- በመንገድ ላይ ምን እንደሚያጋጥመን ዝርዝሩን ሳይነግረን ይልከናል።

- ጌታ ደቀ መዛሙርቶቹን ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲሄዱ የላካቸው ምን እንደሚገጥማቸው ሳይነግራቸው ነበር።

- ኢየሱስ በጊዜው በምድር ላይ ለብቻው ነበር ለጸሎትም ወደ ተራራው ወጥቶ ነበር ይህም የእርሱንና የአባቱን ግንኙነት የሚያሳይ ነው።

- ዮሴፍ በህይወቱ ህልሙን ሲያይ ከዛ በኋላ በወንድሞቹ የሚገጥመውን መከራ፣ ጥላቻ እንዲሁም ሌሎች ፈተናዎች ዝርዝሩ አልተነገረውም።

- በእኛ ህይወት በመንገዳችን ዝርዝሩ አይነገረንም ነገር ግን እርሱ በምንም ሁኔታ አብሮን ይሆናል።

2- በችግር ውስጥ ስንገባ የሚያየን ጌታ በክብር ይመጣልናል።

- ደቀ መዛሙርቱ በባህር ላይ ሆነው ከልካይ ማዕከል ከፊታቸው መጥቶ ነበር።

- ኢየሱስ ግን በምድር ሆን ወደፊት ያለ ንፋስም ቢኖርም ያያቸው ነበር ።

- ኢየሱስ ካያቸው በኋላ ዝም አላለም አዘነላቸው፣ ራራላቸው፣ አዳናቸው።

-መጸልይ ሲያቅተን ያየናል፣ሲያይ ከመከራ ለመታደግ ነው።

-እግዚአብሔር ብቻ ነው በማዕበል ላይ የሚራመደው ኢዮ 9:8 ይህንን ያሳያል።

-ኢየሱስ ሲያልፍ ክብሩን ሲገልጥ ነው።

3- በመከራችን ላይ ክብሩን መግለጥ ስለሚፈልግ ነው።

- ወደ እኛ ያናወጠንን መጥቶ ጸጥ ያደርገዋል።

- ደቀ መዛሙርት ይህ ሁሉ ሲሆን ታውከው ደንግጠው፣ ደንዝዘው ነበር ግን ኢየሱስ እኔ እኔ ነኝ አላቸው ፣ አይዟችሁም ብሎ ተናገራቸው።

- ኢየሱስ በየትኛውም ማዕበል ላይ የሚራመድ አምላክ ነው።

4/05/17
በሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተ- ክርስቲያን

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

09 Jan, 08:41


በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረገዉን ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕርሜር ሊግ  ጨዋታዎችን በቀጥታ ለማግኘት JOIN ያድርጉ ።
WAVER👉 @ETCWAVER

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

07 Jan, 13:00


✍️ይገርማል!!!


ኢየሱስ :- ለዘመኑ ጥንት ለመንግሥቱም ሹምሽረት እና ለታላቅነቱም ጥግ የሌለው አምላክ በቅድስት ድንግል ማርያም ውስጥ አድሮ ህጻን ሆኖ ተወለደ።

የዘላለም ንጉሥ ልብሳ መንግሥቱን አውልቆ ፣የባርያን መልክ ይዞ በጨርቅ ተጠቅልሎ ፣የክብሩን ዙፋን የመላእክቶቹንም አጀብ ትቶ በከብቶች በረት በግርግም ተገኘ ።

ሰማይንና ምድርን ፣ይብስንና ባህርን ፣አራዊትንና እጹዋዕትን ፣በሰማይ የሚበሩ አእዋፍቶችንና የማይንቀሳቀሱ ግዑዝና ግዙፍ ተራሮችን በዘላለም ቃሉ ያለ አጋዥ ደግፎ የያዘው ኃያል አምላክ ኃይል የከዳው ድኩም እና የወላጆቹን ትኩረት የሚሻ ጥገኛ ህጻን ሆነ ።

ነፋሳትን በመዛግብት ፣ውኆችን በእልፍኙ የሰፈረው ፣ለዝናብም ሥርዓትን የሚያስተምርና ደማናዎችንም የሚቆጣጠር አምላክ በእናቱ ብርሃነ ልደት በሠላም አደረሳችሁ!!
🙏🙏🙏🙏
ኢየሱስ ያድናል

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

02 Jan, 16:07


🎅🎄እንኳን አደረሳችሁ 🎄🎅
የገናን በዓል ምስንያት በማድረግ በዓሉን የሚያደምቁላችሁን የክርስቲያን ቻናሎች ልጠቁማችሁ🎅
Wave መግባት ምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ @free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

02 Jan, 08:35


🎄ይኤንን የመሰሉ እና ልዩ የገና ጥቅሶች እና ለፕሮፋይል የሚሆኑ picture ለማግኘት ከታች መልካም በዓል የሚለውን ይጫኑ🎄

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

31 Dec, 10:30


ይሄንን አስተውለው ያውቃሉ??

በጥንት ዘመን ለዛውም እጅግ ሃይማኖተኛ በሆነ፣ ስምና ክብር ከሕይወት በላይ በሚከበርበት ማኅበረሰብ ውስጥ አንድ ወንድ ያጫት ልጃገረድ ከእርሱ እውቅና ውጪ አርግዛ ብትገኝ እና ይህንንም ጉድ ገና ሰው ሳይሰማ እሱ ብቻ ቢያውቅ ምን የሚል ይመስልዎታል? እሺ፥ እርግዝናው የአንድ ጊዜ ክስተት ነውና በምህረትና በይቅርታ ይታለፍ እንበል፣ የራስ ያልሆንን፣ ከእጮኛ የተወለደን ልጅ ማሳደግ ግን የዕለት ተለትና የዕድሜ ልክ ኃላፊነት ነውና ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ሰው ቸርና ሩህሩህ ከሆነ የሰውን ችግረኛ ልጅ ልጁ አድርጎ በመውሰድ ሊያሳድግ ይችላል። ነገር ግን እጮኛው ከእርሱ ጋር እያለች ያረገዘችውንና የወለደችውን ልጅ የራሱ ልጅ አድርጎ ማሳደግ ግን ከቸርነትና ከርህራሄ ያለፈ መልካምነትን ይጠይቃል።
የዚህ ጽሑፍ ዳርዳርታ ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት በዓለም ላይ በደማቁ ሲከበር የኖረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት ታሪክ እንደ ሰው ጠጋ ብለን እንድናየውና ከታሪኩ ተዋንያን መሃል ብዙ ጊዜ ትኩረት የማይሰጠውን የዮሴፍን ተግባር አጉልተን እንድናይና ከአብራካችን ያልወጣውን የሌላ ሰው ልጅ በፍቅር እና በሙሉ መብት ማሳደግን በአዲስ ብርሃን እንድንመለከት ለመጋበዝ ነው።
የክርስቲያኑ ዓለም ከበዓላት ሁሉ በልዩ ድምቀት የሚያከብረው የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የማደጎ ወይም የጉዲፈቻ መልዕክት ያዘለ መሆኑን ምን ያህል አስበውት ያውቃሉ?
አዎን! የጌታ ልደት የራስ ያልሆነን ልጅ በአደራ ተቀብሎ፣ ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ፣ ሙሉ መብት ሰጥቶ በፍቅርና በምሳሌነት የማሳደግ ታሪክ ነው። ፍጹም አምላክ የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ በሥጋ የማሳደግ ታላቅ ኃላፊነትን ለመሸከም በእግዚአብሔር የተመረጠው ዮሴፍ መለኮታዊውን ህጻን የተቀበለው በማደጎ ወይም በጉዲፈቻ ነው። ዮሴፍ ህጻኑን ኢየሱስን በዚህ መልኩ ባይቀበልና ኃላፊነቱን ባይወጣ ኖሮ የዓለም ገጽታ፣ የሰው ልጅ ታሪክ ምን ሊመስል ይችል እንደ ነበር ለመገመት አዳጋች ነው።
የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ምድር መጥቶ በጉዲፈቻ በሰው ቤት ያደገው እኛን የአዳም ልጆች፣ የቁጣ ልጆች የነበርነውን በሞቱና በትንሳኤው ከአብ ጋር በማስታረቅ የእግዚአብሔር ልጆች ሊያደርገን ነው። ዮሴፍ እሱን በሥጋ ልጁ አድርጎ እንደ ተቀበለው እንዲሁ እግዚአብሔር እኛን ልጆቹ አድርጎ ተቀበለን።
“በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።” ኤፌ. 1፡5
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን “ልጆቹ ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን” የሚለውን ኦርጅናሉ የግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ υἱοθεσίαν (ሁዮቴሲያን) በማለት ይጠራዋል። ይህ ቃል የሁለት ቃላት ውህድ ሲሆን ሁዮስ (ልጅ)፣ ቴሲያን (ማኖር) ማለት ነው። ይህንኑ ቃል እንግሊዘኛውና ሌሎች ቋንቋዎች adoption (አዶፕሽን) በማለት ተርጉመውታል።
ምናልባትም ላለፉት ረዥም ዘመናት መጽሐፍ ቅዱሳቸውን እግዚአብሔር አዶፕት አደረገን ብለው ያነበቡት ነጮች ከዓለም ዙሪያ ልጆችን የራሳቸው አድርገው ሲወስዱ እኛ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች አጠገባችን የተጣሉትንና የረዳት ያለ እያሉ የሚጮሁትን ህጻናት እንኳ ልጅ አድርጎ መውሰድ የተሳነን የመጽሐፍ ቅዱሱን ሃሳብ “እግዚአብሔር ወለደን” ብቻ ብለን ስላነበብን ይሆን! በእርግጥ አሁን በአገራችን በተለይ በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ዘንድ ህጻናትን ልጅ አድርጎ የመውሰድ ልምዱ ይበል በሚያሰኝ መልኩ እየጨመረ መጥቷል። ነገር ግን ሊሆን ከሚገባው ጋር ሲነጻጸር ገና ኢምንት ነውና የበለጠ መበረታታት አለበት።
ሰው ሁለት ዓይነት ልጆች ሊኖሩት ይችላሉ። አንድ ከሆድ፣ ሌላው ከልብ። ጉዲፈቻ ወይም ማደጎ፥ ልጅን ከልብ መውለድ ማለት ነው። ዮሴፍ ጌታን ከልቡ ወልዶታል፦ “… እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ …” ሉቃስ 3፥23።
እኛስ ዛሬ የልደትን በዓል ስናከብር ስለ አዶፕሽን ምን እናስባለን? ያለ ፈቃዳቸው ተወልደው፣ በወላጆቻቸው ተጥለው ወይም ወላጆቻቸውን በሞት ተነጥቀው የወላጅ ያለህ በማለት የሚጣሩ አዕላፋት ሕጻናት በዙሪያችን አሉ። እኛም እንደ ዮሴፍ በቤታችንና በሕይወታችን ብንቀበላቸው በምድር ከምናገኘው ደስታና በረከት ባሻገር ለዘላለም መዝገብ ላይ የማይጠፋ ታሪክ እንጽፋለን።
ላቭ ዩር ኔበር አዶፕሽንን ያበረታታል። በተለይ ደግሞ ሎካል ወይም አካባቢያዊ አዶፕሽንን እጅጉን ያበረታታል። ልጆች ካካባቢያቸው፣ ከባህላቸው፣ ከቋንቋቸው ሳይርቁ በቆዳ ቀለም በሚመስላቸው ቤተሰብ ውስጥ ማደጋቸው ጠቀሜታው ጉልህ ነው።
ስለዚህ የመዳናችን መሠረት የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስን ልደት ስናከብር በአካባቢያችን ያሉ ሕጻናት ማሳደጊያዎችን እንጎብኝ። እንደ ባልና ሚስት እንደ ቤተሰብም ተማክረን ልጆችን ከልባችን እንውለድ።

ያሬድ ጥላሁን (ወንጌላዊ)
ላቭ ዩር ኔበር

ለሌሎች ይሄንን ግንዛቤ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ LIKE AND SHARE እናድርግ

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

30 Dec, 20:53


Prayerlessness the worst sin, because:-Prayerlessness is ignoring the Great God. So, Ignoring the Great God is the worst Sin!(Jeremiah 2:13)

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

29 Dec, 12:01


የትኛውች የ tv ቻናል ይመለከታሉ🤔
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

28 Dec, 13:43


የማንን ሙሉ አልበም ወይም ነጠላ ይፈልጋሉ
የፈለጉትን የዘማሪ ስም ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

27 Dec, 14:48


~የተማረ የት ደረሰ~
~ ~ አይባልም ~ ~

ከዱባ ወጥ ቀጥሎ ኢቶጲስ ውስጥ የማይወደድ ነገር ቢኖር ትምህርት ነው ። አለመማር አንድ ነገር ሁኖ ሳለ የተማሩት ላይ መሳለቅ ደግሞ የሚገርም ነው።

ትምህርት አያስፈልግም ብለው የሚናገሩ ሰዎች በኩራት የሚያነሷት ነጥብ "የተማሩ ሰዎች የት ደረሱ" የምትለዋ ቀሽም የማሸማቀቂያ ምክንያት ስትሆን፤ የተማሩት የት እንደደረሱ አብረን እንመልከት።

ከመሰረታዊ ጥናቶች እንጀምር።

1. ወንጀል

በ2021 Institute for Securities Studies (ISS) ባሳተመው ጥናት መሰረት 92.7% ገደማ ከባድ ወንጀሎች የሚፈፀሙት ዩንቨርስቲ ባልቀመሱ ግለሰቦች ሲሆን፤ 6.5% ወንጀሎች ዲግሪ ባላቸው እና ቀሪው 0.8% ብቻ ደግሞ ማስተርስ እና ከዛ በላይ ባላቸው ግለሰቦች የሚፈፀሙ ናቸው ይላል።

ይሄ ጥናት ኢቶጲስ ውስጥም የሚሰራ መሆኑን ለማወቅ፤ ስልክ ለመስረቅ ብሎ አንገት በጩቤ የሚወጉትን እና ወጡ ላይ ጨው አበዛሽ ብለው ሚስታቸውን በዘነዘና ከሚገሉት ሰዎች ጀምሮ መመልከት በቂ ነው።

እዚህ ጋር የተማረ ሰው ምን አተረፈ ካልክ? "ህሊና" የሚባል ነገር እልሀለሁ።

2. ገንዘብ

ሌላኛው የተማሩ ልጆች ላይ የመዘባበቻ ነጥብ፤ ስራ እና ገንዘብ የማጣታቸው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሄ የነሱ ድክመት ሳይሆን የሀገሪቱ ድክመት ነው፤ እሱን ትተን ወደ ንግድ እንኳ ብንመለስ፤ ንግድ ላይም የተማረ እና ያልተማረ ሰው ቢሳተፍ የተማረው ሰው የተሻለ successful የመሆን እድል እንዳለው የሚያሳዩ ብዙ ዳታዎች አሉ።

ለምሳሌ አለማችን ላይ ካሉ ቢሊየነሮች መሀል 71 ፐርሰንቱ ከዩንቨርስቲ ዲግሪ እስከ PhD የጨረሱ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው። Bill Gates ወይም ማርቆስ Zuckerበርግ አይነት በጣም ጥቂት ባለሀብቶች በእርግጥ ከኮሌጅ ት/ት አቁመዋል፤ ነገርግን እነዚህ ግለሰቦች ት/ት ያቆሙት ከ Harvard እና Yale እንጂ ማትሪክ ወድቀው አይደለም።

ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን ሀብታሞቹ ደንቆሮ ሆኑ ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፤ አግባብም ነው። ለዚህ ቀላሉ መልስ "ቁጥር 1ን" ተመልከት ነው፤ የኛ ሀገር ሀብታም በአመዛኙ ደፋር፣ ወንበዴ፣ አጭቤ፣ አምታች ነው። ይሄንን ውንብድና ደፍሮ እንዲሰራ የሚያደርገው ደግሞ አለመማሩ ነው።

ኢትዮጲስ ውስጥ ለምን generational wealth እንደሌለ ታውቃለህ? አባት ሀብታም ሲሆን ልጆቹን ጥሩ ቦታ ያስተምራል፤ ከዛ ልጆች ህሊና ይኖራቸዋል፤ ከዛ የአባታቸውን የወንበዴ ቢዝነስ ማስቀጠል ይከብዳቸዋል፤ አለቀ።

የተማረ ሰው ቁጥር ማነስ ከPolitical Stability፣ ከPoverty Alleviation፣ ከInnovation & ከEntrepreneurship እና አጅግ ብዙ አሁን ላለንበት አዘቅት ምክንያቶች ጋር በብዙ ጥናቶች አስደግፎ ማስረዳት ይቻላል።

በአጭሩ ት/ት ምን ያደርጋል የሚልህ ነጋዴ ሂሳቡን የሚያሰራው በተማረ Accountant ነው፣ ሲከሰስ ተከራክሮ ንብረቱን የሚያስመልስለት የተማረ ጠበቃ ነው፣ ህንፆውን የሚያስገነባው በተማረ ኢንጂነር ነው፣ ሲያመው የሚሄደው የተማረው ዶክተር ጋር ነው፤ ከዛ አልፎ ልጁን አጥና እያለ የሚጨቀጭቀው እና ፅድት ያለ international school ልኮ የሚያስተምረው ይሄው ራሱ ሰውዬ ነው።

እና ምን ልልህ ነው፤
አለመማር አያኮራም።
እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ አይባልም፤ ነውር ነው።

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

26 Dec, 16:50


Do you love Jesus?
Free wave folder የምትፈልጉ በውስጥ👇 አውሩኝ. @free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

25 Dec, 11:11


ዛሬ የሚደረጉትን ተጠባቂ ጨዋታዎች በ ነፃ በስልኮዎ ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ(JOIN) የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉ አሁኑኑ እንዳያመልጥዎ 👇 🏆

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

25 Dec, 11:06


በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረገዉን ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕርሜር ሊግ  ጨዋታዎችን በቀጥታ ለማግኘት JOIN ያድርጉ ።
WAVER👉 @ETCWAVER

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

25 Dec, 11:04


የማንን መዝሙር ይፈልጋሉ?

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

24 Dec, 09:30


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

24 Dec, 03:50


አየር ልቀቅ!

በአንድ ትልቅ የመኪና ማምረቻ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሠራ መሐንዲስ፤ በዐይነቱ ልዩ የሆነ፣ በተወዳዳሪነቱም የላቀ- አዲስ የመኪና ሞዴል ይነድፋል። የድርጅቱ ባለቤትም በውጤቱ እጅጉን በመደነቅ ምስጋናን ይቸረዋል። ይሁንና መኪናውን ከማምረቻ ሥፍራ ወደ ማሳያ ክፍል ለመውሰድ በሚሞክሩበት ጊዜ፤ አዲሱ መኪና ከመግቢያው በር በ10 ሳ.ሜ እንደሚረዝም ይረዳሉ።

መሐንዲሱም፤ ቀድሞውኑ የመኪናውን ንድፍ ሲሠራ ይህንን ግንዛቤ ውስጥ ባለማስገባቱ ይተክዝና ያዝን ጀመር። የድርጅቱ ባለቤትም መኪናውን ከማምረቻ ሥፍራ እንዴት እንደሚያወጣው ግራ ይገባዋል። ይህን ጊዜ ቀለም ቀቢው ተነሥቶ፤ "መኪናውን ሊያወጡት እንደሚችሉና በመኪናው ላይኛው ክፍል ብቻ ትንሽ ጭረት እንደሚኖር እሱም ቢሆን ከወጣ በኋላ በቀለም ሊስተካከል እንደሚችል" በመናገር ተስፋን ይሰጣል።

ለጥቆ መሐንዲሱ፤ "የመግቢያውን በር ሰብረው መኪናውን ማውጣት እንደሚችሉና መልሰውም በሩን እንደሚጠግኑት" ይናገራል። ይሁንና የኩባንያው ባለቤት የተነሱት የመፍትሄ ሐሳቦች በመላ አልተዋጡለትም፤ መኪናው ላይ የሚደርሰው ጭረትም ሆነ የመግቢያውን በር መስበሩ መልካም መስሎ አልታየውም። ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን ዳር ቆሞ ሲታዘብ የነበረው የኩባንያው ጥበቃ ሠራተኛ በዝግታ ወደ ባለቤቱ ይጠጋና የሚቻል ከሆነ በነገሩ ላይ ሐሳብ ለመስጠት እንደሚፈልግ ይናገራል።

ኃላፊውም የጥበቃ ሠራተኛው የነገራቸው ኤክስፐርቶች ሊሰጡ ያልቻሉትን በመሆኑ እጅጉን ተደነቁ። ጥበቃው የተናገረው፤ "መኪናው ከመግቢያው በር በትንሽ ሳ.ሜ ከፍታ ብቻ ነው የሚረዝመው፤ ስለዚህ በቀላሉ በጎማው ያለውን አየር ስትለቁ የመኪናው ቁመት ይወርዳል፤ በቀላሉም መውጣት ይችላል" የሚል ነበር። ሁሉም በአንድ እጅ አጨበጨቡ!

አየህ ውስጥህን የሞላው 'አየር' ያንተን እጣ ፈንታ ይወስናል። ምናልባት ይህ አየር ንዴት፣ ጸጸት፣ ምቀኝነት . . . ጉዞህን ገቶት፣ ነገህን አጨልሞት፣ እርምጃህን ገድቦት፣ ተስፋን አሳጥቶ ሩቅ አልመህ ሩቅ እንዳታድር አድርጎህ ይሆናል። የተሞላኸውን አየር ልቀቅ። ያን ጊዜ አላልፍም ካልክበት ሁኔታ ልታልፍ፣ አልወጣም ካልክበት ማጥ ልትወጣ ትችላለህ።
👉 ሳሙኤል ገዳሙ እንደጻፈው🙏🙏

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

18 Dec, 19:46


✍️ ይሄ ነው ገድል
***
ነፍስ በግዞት ፣ በጽልመት መዓት
ሸብቧት ሳለ ፣ የሞት ፍርሃት
የፊጥኝ ታስራ ፣ የግርንግሪት
ራሷን ስታ ፣ በሞት አዙሪት
ተይዘን ሳለ ፣ በእዳ ተዘፍቀን
በነውር አድፈን ፣ በክስ ደቀን
በደል ያጠፋን ፣ አገኘን ደሙ
መኖር አቃተን ፣ እንደቅድሙ

እርሱ ወድቆልን ፣ ቆመናል በድል
ይሄ ነው ድርሳን ፣ ይሄ ነው ገድል
ይሄ ነው ጽህፈት ፣ ይሄ ነው ፊርማ
በደም ተጽፎ ፣ ፍትህ ያሰማ

በቀጠረው ቀን ፣ ባቀዳት ሰዓት
የተሸከመ ፣ የዓለምን ኃጢአት
እንደሚታረድ ፣ እንደ በግ ሆኖ
በሸላቾቹ ፣ ፊት ዝም ብሎ
ቃል ሳያወጣ ፣ ዘግቶ አንደበቱን
የአብን ፈቃድ ፣ ጠጣት ጽዋይቱን
ነደደ ቁጣው ፣ አገዘው ክንዱ
ኃጢአት ጥላቻው ፣ ሰውን መውደዱ
ተገልጦ ታየ ፣ ተንበለበለ
ያለም መድኃኒት ፣ ተንጠለጠለ
ገትሮ ስቦ ፣ የፍቅር ቀስቱን
በስቶ ሲጥለው ፣ የሞት ጅማቱን
ከመውጊያው ለየው ፣ ከኃይሉ አፋታው
እኛን አስተፋው ፣ ተቀ'ቶ ቀጣው

እርሱ ወድቆልን ፣ ቆመናል በድል
ይሄ ነው ድርሳን ፣ ይሄ ነው ገድል
ይሄ ነው ጽህፈት ፣ ይሄ ነው ፊርማ
በደም ተጽፎ ፣ ፍትህ ያሰማ

ስለሁላቸው ፣ እኔን ግደለኝ
ከ'ቅፍህ ልውጣ ፣ መስቀል አውለኝ
እነሱን "ይቅር" ፣ "ሙት" በለኝ እኔን
ይቸንከር እጄ ፣ ልወጋ ጎኔን
ልሙትላቸው ፣ ሞታቸው ይሙት
ሙታን ይነሱ ፣ ድምጽህን ይስሙት
ያለ ሰው የለም ፣ ከኢየሱስ በቀር
የተሸከመ ፣ የሁሉን መስቀል
ያላንዳች አጋዥ ፣ ብቻውን ብቻ
ራሱ ዘምቶ ፣ የኛን ዘመቻ

እርሱ ወድቆልን ፣ ቆመናል በድል
ይሄ ነው ድርሳን ፣ ይሄ ነው ገድል
ይሄ ነው ጽህፈት ፣ ይሄ ነው ፊርማ
በደም ተጽፎ ፣ ፍትህ ያሰማ
ሰውን ከአብ ጋር ፣ በ'ርቅ ገበታ
በፍቅር ማዕድ ፣ በስሙ ፌሽታ
ደሙን አፍስሶ ፣ ያሳረፋቸው
የኔ የሚሉት ፣ አንድ የጋራቸው
መሀል ላይ ያለ ፣ መካከለኛ
ለኛ እግዚአብሔር ፣ ለእግዚአብሔር እኛ
አምላክና ሰው ፣ በአንድ ገላ
ያውም ያለ እንከን ፣ በፍጽምና
ሊነገርለት ፣ ይህ የተገባው
የታረደ ነው ፣ ሞት ሳይገባው
መስክር አጣጥም ፣ ዘክር ይሄን ድል
እዛ መስቀል ላይ ፣ ተሰርቷል ገድል
ሕይወት ተጽፏል
ሕይወት ተደርሷል
ሕይወት ታትሟል
ሞት ለዘላለም ፣ ላይበላህ ጹሟል!!

ገጣሚ; ሔኖክ አሸብር

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

14 Dec, 11:47


🙏🙏🙏

God will protect you from situations you won't even know about.

Say 🗣️ Amen🙏

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

13 Dec, 05:22


ሁሌም ተጠንቅቀን እንድንኖር የሚያደርገን እውነታ . . .

ቅንነት
; ሞኝነት አይደለም በጊዜው፣ በረከት የምንቀበልበት መልካም አዝመራ ነው እንጂ።
ክፋትና ተንኮልም በህይወት የሚታጨዱ ለነገ የተቀመጡ የመከራ ዘሮች ናቸው።

()

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

12 Dec, 03:51


✍️ አብ በላከው
****
እንከን አልባ ፣ ንጹህ ጠቦት
ሀረግ ይዞት ፣ አራጅ ከቦት
የታረደ ፣ በአብ ቢላ
ያረፈበት ፣ የሞት ዱላ
ያልቻልኩትን ፣ ለኔ ችሎ
የሞተልኝ ፣ ምትክ ሆኖ
መጋረጃውን ፣ ከላይ ቀዶ
ለሞት ነግሮት ፣ የሞት መርዶ
በትንሳኤው ፣ እኔም ወጣሁ
አብ በላከው ፣ ወደ አብ መጣሁ!!

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

08 Dec, 03:38


የማንን ሙሉ አልበም ወይም ነጠላ ይፈልጋሉ
የፈለጉትን የዘማሪ ስም ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

07 Dec, 14:53


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

06 Dec, 17:54


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

05 Dec, 19:14


የትኛውች የ tv ቻናል ይመለከታሉ🤔
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

05 Dec, 04:57


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

04 Dec, 19:04


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

04 Dec, 18:46


Whose fault is this accident?
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

04 Dec, 17:03


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

03 Dec, 19:41


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

03 Dec, 17:11


በአዲስ ኪዳን አጢያት የሚሰረየው እንዴት ነው? መልሱን ይሆናል የምትሉትን ይንኩት
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

02 Dec, 20:07


🌟ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ አመራጮችን ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

02 Dec, 19:49


የትኛውች የ tv ቻናል ይመለከታሉ🤔
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

30 Nov, 18:47


የ ፊልሞና መልዕክት ስጥም
አንብባችሁ ተባረኩበት


ከቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን አስገራሚ ባሕርያት አንዱ በአማኞች መካከል የነበረው ፍቅርና መተሳሰብ ነበር። በተራራቁ ስፍራዎች የነበሩት ብዙም የማይታወቁ አማኞች ሳይቀር ከልባቸው ይዋደዱ ነበር። ጳውሎስ የሚኖረው ሮም ውስጥ ሲሆን ፊልሞና ደግሞ በቆላስይስ ውስጥ ይኖር ነበር። ይህም በመካከላቸው ከ1200 ኪሎ ሜትሮች በላይ ርቀት መኖሩን ያመለክታል። ጳውሎስ ቀደም ብሎም ከፊልሞና ጋር አብሮ ያሳለፈ አይመስልም። ይሁንና ለፊልሞና የጻፈው መልእክት ጥልቅ የወዳጅነት መንፈስ የሚታይበት ነበር። በተጨማሪም ጳውሎስ በቀላሉ የሰውን ስሜት ሊነኩ ስለሚችሉ አንዳንድ ጉዳዮች የፊልሞናን እርዳታ ለመጠየቅ ሲደፍር እንመለከታለን። ጳውሎስ አማኞች ሁሉ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካላት ናቸው የሚለውን እውነት ተግባራዊ እያደረገ ነበር። በመሆኑም፥ ጣልቃ እንደገባን ወይም ሌላውን ሰው ለራሳችን ዓላማ እንደተጠቀምንበት ሳናስብ ከክርስቲያን ወገኖች እርዳታ ልንጠይቅና አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይ እንደምንችል ከዚህ መልእክት ውስጥ መረዳት ይቻላል።

የፊልምና'ን መልዕክት አንብቡ🙏
በጣም ትወዱታላችሁ

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

20 Nov, 19:35


በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረገዉን ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕርሜር ሊግ  ጨዋታዎችን በቀጥታ ለማግኘት JOIN ያድርጉ ።
WAVER👉 @ETCWAVER

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

20 Nov, 14:46


በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረገዉን ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕርሜር ሊግ  ጨዋታዎችን በቀጥታ ለማግኘት JOIN ያድርጉ ።
WAVER👉 @ETCWAVER

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

20 Nov, 10:51


ምን ይፈልጋሉ
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

20 Nov, 09:24


በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረገዉን ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕርሜር ሊግ  ጨዋታዎችን በቀጥታ ለማግኘት JOIN ያድርጉ ።
WAVER👉 @ETCWAVER

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

20 Nov, 08:38


🛑🛑ሰበር መረጃ

ፔፕ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያቆየውን ውል ለመፈራረም ከክለቡ ጋር ተስማምቷል ክለቡም ነገ አልያም ከነገ ወዲያ ይፋ ያደርገል።
@ethio_manchester_city9
@ethio_manchester_city9

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

19 Nov, 12:56


✍️ ሰዓሊ ~ ስዕል ~ አንተ ~ እኔ
**

እንደገባቸው ልክ
እንዳረዳዳቸው ፣ ሸራ ላይ ስለውህ
ሚስማር የጠረቀህ
ጦር የወጋህ አንተን ፣ በብሩሽ ወግተውህ
የበጠበጡትን
ቀለም ደም ነው ብለው ፣ ካላመንክ ይሉኛል
እኚህ ሰዓሊዎች
ኢየሱስን ሳልነው ፣ ሲሉ ይገርሙኛል

እንደችሎታቸው
የየራሳቸውን ፣ መስቀል አበጅተው
ስቃይ ያላገኘው
ከውስጥ ያልወጣ ደም ፣ ከውጭ ቀብተው
በየብሩሻቸው
የየግላቸውን ፣ ክርስቶስ በመስቀል
በውጥር ሸራቸው
አንተን እንደሳሉህ ፣ አምኜ እንድቀበል
ይሄውና ጌታህ
ኢየሱስ ነው ሲሉኝ ፣ እንዴት ልመናቸው
አልገጥምልህ ቢለኝ
ክቡር ደምህና ፣ ብጥብጥ ቀለማቸው

ደሞ ሌላ ነገር......

ሚስማር ያረፈበት
የተተለተለ ፣ እግሩ የተጣበቀ
ያንድኛው ሰዓሊ
ብዙ ደም 'ሚፈሰው ፣ ያንዱ የደረቀ
ክርስቶስ ነው ብለው
በቀለም በብሩሽ ፣ ከመስቀል በስተቀር
እንሳለው አይሉም
ትንሳዔህንና ፣ ያንተን በአብ ቀኝ መክበር

እንደው ይሁን ቢባል
እንደው ሳሉ ቢባል
እሾህ ለመጎንጎን
ጎንህን ለመውጋት ፣ ቀለም ለመቀባት
ይቸኩላሉ እንጂ
እጅህን ለመብሳት ፣ ገላህን ለማድማት
ሊስሉ አይነሱም
እኔ ካንተ ጋራ ፣ በክብር መክበሬን
ስዕል ትርጉም ቢስ ነው
አንተን ብቻ ስለው ፣ ካላስገቡኝ እኔን

ለኔ ነው መውረድህ
ለኔ ነው መልፋትህ ፣ መሞትህ ለኔ ነው
ካንተ ጋር ስከብር
እስካልሳሉ ድረስ ፣ ስዕሉ ከንቱ ነው
ትርጉም አይሰጠኝም
የደምህን ሥራ ፣ አይነግረኝም ቀለም
በልቤ ሸራ ላይ
እንደ መንፈስ ቅዱስ ፣ የሚስልህ የለም
ያውም ሳያዛንፍ
መልዕክት ሳይቀንስ ፣ ሳይቀይጥ ሳይሸርፈው
የራስህ መንፈስ ነው ፣ ካንተ ጋራ ስሎኝ
የት እንዳለሁ ነግሮ ፣ ልቤን ያሳረፈው!!


✍️ ገጣሚ ሔኖክ አሸብር🙏

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

17 Nov, 13:02


𝗣-rayer is a
𝗥-ight decision todo
𝗔-nd the best way
𝗬-ou can talk to GOD.

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

15 Nov, 18:26


የተሳካልህ ሰው ለመሆን . . .



የአለማችን የናጠጡ ባለሃብቶች 75% ኢንተርፕርነር 15% ኢንቨስተር
7% በውርስ ያገኙ 3% አክተሮች ስፖርተኞችና የመዝናኛ ኢንደስትሪ ተዋናዮች ናቸው

እዚህ ጋር ባለሃብት ነው ያልኩህ
ባለፀጋ
ደግሞ ከፍ ይላል
እነዚህ ፍሬዎች አሉት / Treasures
1 Grace of God/ በፈጣሪ ፀጋና በረከት ያምናል
2 Beloved family/ ተወዳጅ ቤተሰብ አፍርቷል
3 Vibrant health / በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል
4 Meaningful life/ ትርጉም ያለው ህይወት ይመራል
5 Relevant network/ አግባብ ያለው ምርጥ ትስስር ፈጥሯል

እንዴት ትቀዳጀዋለህ

1በአላማ ኑር

አላማና ኢላማ ከሌለህ ትስታለህ
በቃ አለ አይደል ?
የተኩስ ድምፅ እየሰማህ ትኖራለህ ::
ያለምከው ነገር ስለሌለ አንዱንም አግኝተህ አትመታም።

የሎተሪ ህይወት ትኖራለህ ህይወትን ትፍቃለህ 'እንደገና ሞክር' ትባላለህ

አንተ እድለኛ እንድትባል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቆራጮች እድለቢስ እንዲባሉ ትመኛለህ

ስለዚህ ግብህ ጨው ነው የኑሮን ቃና የምታጣጥመው በዓላማ ስትኖር ነው

ለምሳሌ ''ጎል ማስቆጠር ቢቀር እግር ኳስን ቅርጫት ኳስን ... ማን ያየዋል''?

ግብ ከሌለህ ልክ እንደ ካንጋሮ እግርህ ረዝሞ እጅህ ያጥርብሃል

ወዳጄ ግብ ከሌለህ ይህ አለም የሰሃራ በረሃ ይሆንብሃል
ያለ አቅጣጫ ከተንቀሳቀስክ ትጠፋለህ።
ጂፒኤስ ያስፈልግሃል (ግብ)!

2 ሰውን አክብር

ሥነሥርዓት ይኑርህ , ሰው ካላከበርክ ሰው አያከብርህም
ስለዚህ በሰው ላይ የምታደርገውን በራስህ ላይ እንዳደረከው ተረዳ
አትሳደብ አታመናጭቅ
ረጅም ነኝ ብለህ አጫጭሮች ላይ አትመፃደቅ
ከባድ ኪሎ አለኝ ብለህ ቀጠን ያለውን አታስቦካ😅
ሀብት ከብት አለኝ ብለህ ምስኪን ላይ አታቅራ፤

ብቻ ሰውን በትህትና ቅረብ
ቀለል በል።

3 ፈጣሪን ፍራ
እርሱ የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ስለሆነ!!!
ፈጣሪን መፍራት በጎ ስነምግባር ማጎልበት ነው።

ሳጠቃልለው . . .
ወዳጄ ፅና
ስር ስደድ

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

14 Nov, 20:25


እግዚአብሔር የሚሰጠውን መልስ እንጠብቅ


ምናልባት ሁላችንም በአንድ ወይም በሌላ ወቅት በጣም ብዙ ክፋት ተመልክተን በመደነቅ እግዚአብሔር ይህንን ነገር ለምን እንደማይቀጣው ጠይቀን ይሆናል።
ዙሪያችንን ስንቃኝና ሰዎች ኃጢአት ሲሠሩ፥ ድሆችን መጠቀሚያ ሲደረጉ፤ ትክክለኛ ፍርድን በጉቦ የሚያጣምሙ ሰዎች ያለምንም ቅጣት ተዝናንተው ሲኖሩ በመመልከት፥ ልባችን በኃዘን ይሞላል።
ዓለም በቅን ፍርድና በጽድቅ የምትሞላበትን ጊዜ በልባችን እንናፍቃለን። ክፋት እስካልተቀጣ ድረስ ይህ ቀን ሊመጣ እንደማይችልም እንገነዘባለን።

በዚህ አንጻር እግዚአብሔር ክፋትን ለምን እንደማይቀጣና ለእግዚአብሔር ለመኖር አጥብቀው የሚፈልጉትን ሰዎች ለምን እንደማይባርክ በማሰብ እንደነቃለን።
ነቢዩ ዕንባቆምም ከዚህ ጉዳይ ጋር ግብግብ ገጥሟል።
የደም መፍሰስና ክፋት ያለ ቅጣት በዙሪያው ተንሰራፍቶ መመልከት ሰልችቶት ነበር። በመሆኑም ክፋትን በመቅጣት ጽድቁን እንዲገልጥ ወደ እግዚአብሔር ይጮህ ነበር፤ እግዚአብሔር የሚሰጠውን መልስ ግን አልጠበቀም ነበር።


ዛሬም በአገራችንና በዓለማችን እየተከሰቱ ስላሉት አሰቃቂና አነጋጋሪ ድርጊቶች እግዚአብሔር የሚሰጠውን ምላሽ እንጠብቅ🙏
አንቻኮል!!
ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣል!!
ይፈርዳልም

🙏

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

13 Nov, 16:54


ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
³⁶ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።

🔥 ዛሬ በዚህ ማለዳ ሁለት ሃሳቦችን ልነግራችሁ እወዳለው የመጀመሪያው ከክርስቶስ ፍቅር የትኛውም ሃይል ሊለያችሁ አይችልም

🔥 ሁለተኛው የትኛውም ህይወታችን ላይ የሚመጣ መከራ ከአሸናፊዎች በላይ እንጂ ተሸናፊ አያደርገንም ከወደደን ከእርሱ ከክርስቶስ የተነሳ ከአሸናፊዎች ሁሉ በላይ እንሆናለን

🔥 ስለዚህ በህይወታችሁ የሚመጣ የትኛዎቹም መከራዎች ወደ ክርስቶስ እንድትቀርቡ እና እግዚአብሔርን እንድትፈልጉ ያደርጋችዋል እንጂ አያጠፋችሁም ደግሞ የምታልፉበት የትኛውም ነገር ካለፈ በዋላ ከአሸናፊዎች በላይ እንድትሆኑ ያደርጋችዋል ኢየሱስ ጌታ ነው

🔥🔥 አዎ አንተን ወንድሜን አዎን አንቺን እህቴን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያችሁ የሚችል ምንም ነገር የለም ደግሞ ከወደዳችሁ ከእርሱ የተነሳ ከአሸናፊዎች በላይ ናችሁ ሃሌሉያ አሜን እናንተ ብሩኳኖች ናችሁ🙏🙏🔥🔥

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

08 Nov, 16:09


የሰሞኑን መነጋገሪያ የሆኑትን የኢኳቶሪያል ጊኒ የፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ዋና ጄኔራል ዳይሬክተር ሰሞኑን በሙስና ተጠርጥረው ቤታቸው ሲፈተሽ ከተያዙ የብልግና ቪድዮዎች ጋር በተያያዘ በርካታ ሚድያዎች ዘገባዎችን እያወጡ ይገኛሉ።

መነሻዬ ግለሰቦቹ ላይ መፍረድ ሳይሆን የዚህ የጨለማው ዓለም ገዥ መንፈስ ከዚህ ዜና ምን ሊያተርፍ አሰበ የሚለው ነውና ቆም ብለን እንድናስብ የሚከተለውን ፃፍኩኝ።

የጨለማው መንፈስ በዚህ ሰው ምክንያት ምን አደረገ?

👉 ሰይጣን ባለስልጣኑን በመጠቀም ከአራት መቶ በላይ ሴቶች ጋር እንዲባልግ እና እራሱ ረክሶ ሌሎች ብዙ ሴቶችንም እንዲረክስ አድርጎታል።

👉ይህን የእርኩሰት ቪድዮ እንዲቀርፅ አድርጎት ምናልባት ቢሞት አልያም በሆነ አጋጣሚ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከቤቱ ቢወጣ ዘመን ተሻጋሪ የእርኩሰት ዶክመንተሪ አድርጎ እንዲያስቀምጥ አድርጎታል።

👉ሰይጣን ያሰበውን ይህንን ዕቅዱን ከባለስልጣኑ አልፎ ብዙ ሚልዮን ህዝቦች ጊዜያቸውን ሰጥተው እንዲያዩት እና በሀሳባቸው እንዲረክሱ በማድረጉ በእጥፍ ተሳክቶለታል።

👉ፌስቡክ፣ቲክታክ፣ዩቲዩብ፣ኢንስታግራም እና ሌሎችም ሚድያዎች ስለእነዚህ ሰዎች በመዘገብ፣በመቀለድ እና በማስተዋወቅ አየሩን ተቆጣጥረውታል።

👉ቢያንስ የአራት መቶ ባለትዳሮችን ትዳር፣ቤት እና መተማመን አፍርሷል።

👉የባለትዳሮቹን የባሎቻቸውን፣የልጆችን የዘመድ አዝማድን ልብ እንዲሰበር አድርጓል

👉መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለውም በዝሙት ምክንያት እነዚህ ትዳሮች የሚፈርሱ ከሆነ የተፋቱ በርካታ ሴት እና ወንዶችን እንዲፈጠሩ አድርጓል ያደርጋል።

👉በዚህ ስነልቦና ጉዳት ምክንያት እራሷን ያጠፋች ሴት እንዳለችም ተደምጧል ይሄም ስኬቱ ነው።

ስለዚህ በጌታ የሆንን ሁላችን በዓይናችን ስለምናየው፣በጆሮዋችን ስለምንሰማው መቆጠብ ስላለብን ከእንዲህ ዓይነት እርኩሰት ሀሳብ በመራቅ፣ባለማጋራት አዕምሮዋችንን እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይርዳን።

መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚነግረን
“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።”
— 2ኛ ቆሮ 2፥11

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

05 Nov, 19:31


ማለት አላቆምም ✍️

👇👇👇👇👇

በጥላቻ ጅራፍ ፣ ፍቅር ተገረፈ
ለእድፋም ገራፊ ፣ ንጹሕ ሰው አደፈ
የገዘፈ ሸክም ፣ ያ ቁልል መከራ
እጅግ የጠለቀ ፣ የውርደት ተራራ
ላዩ ላይ ተደፋ ፣ መሢሕ ተሰቃየ
ውቡ ሰው ተጠላ ፣ ክብር ውርደት አየ
ተናቀ ተገፋ ፣ እውነት ተሰደበ
ቃል የሆነ እ'ሱ ፣ ቃሎቹን ገደበ
ዝም አለ አንደበቱ ፣ ግፍን ተቀበለ
በደል ተሸከመ ፣ ወረደ ቀለለ
የፍቅር ዓይኖቹን ፣ ዓይኖች አይተው ጠሉት
በማይስበው መልኩ ፣ ናቁት አቃለሉት

እንዲህና እንዲያ.....

ብየ ብቻ አልቆምም ፣ አውቃለሁኝ ሚስጥር
ምትክ እስከመሆን ፣ እኛን ባያፈቅር
ያን እድፋችንን ፣ ወስዶ ባያድፈው
ይሄን ያህል ነበር ፣ የምናጸይፈው
የ'ሱ ነበር የኛ ፣ የኛ የ'ሱ ነበር
የ'ሱን ለኛ ሰ'ቶ ፣ የእኛን ባይቀበል

ብየም ደሞ አልቆምም.......

እዩ ጎልጎታ ላይ
ለገዳይ 'ሚነገር
የፍቅር ቃል ሆኖ ፣ ዝምታ ጮክ አለ
የገራፊዎቹን
ጆሮ ሰንጥቆ አልፎ ፣ ልብን ተናገረ
ፍቅር በጥላቻ ፣ ተወግቶ ቆሰለ
ሞት በሞት ተረታ ፣ ገዳይ በሟች ዳነ

ብየም አላቆምም......

አወራለሁ ገድል ፣ ጀብድ እናገራለሁ
ዝም ላለኝ ቃል ፣ ቃል እሰድራለሁ
ኃጢአት ያህል እንከን ፣ ሞት ያለው ስህተት
በደል ያህል ጉድፍ ፤ ጥፋት ያለው ቅጥፈት
ነውሬን ነው እንጂ ፣ የዕዳዬን ጽሕፈት
የፊደል አይደለም ፣ ያቃናልኝ ግድፈት

ብየም አላቆምም
.
.
.
ዝምም ልል አልችልም ፣ ባለታሪኩ ነኝ
ከሲዖል ወጥቼ ፣ ያለሁኝ በአብ ቀኝ
አብን አባ የምል ፣ ልጅ ሆኜ እንደ ልጁ
አልፌ ገብቼ ፣ በተወጋው እጁ

ብየም አላቆምም.....
.
.
.

ገጣሚ ሔኖክ አሸብር

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

04 Nov, 10:18


✍️ በግ - አንበሳ - ልጅ
**
አብ ገበያ ወጣ ፣ ዓለም እየጠላው
አንድ በጉን ሽጦ ፣ በረቱን በግ ሞላው

በግ ከሞላው በረት ፣ መሰማሪያ አግኝቼ
እኔም በግ ሆኛለሁ ፣ ይሄን በግ በልቼ

እኔንም ገርሞኛል ፣ እንዴት እንደሆነ
በጉን ስለበላሁ ፣ አንበሳው ውስጤ አለ

ይሄው አንበሳ ነው ፣ ከሞት የተነሣው
በዚህች ዓለም ጫካ ፣ ወንጌል የሚያገሳው

ያውም በእኔ ሆኖ ፣ አፍ አ'ርጎኝ አንደበት
እግዚአብሔር በልጁ ፣ ለእርቅ የሚጠራበት

እናልህ ወንድሜ ፣ አብ በልጁ ሆኖ
ታረቀኝ ይለሃል ፣ እ'ሱው ተበድሎ

ተበዳይ ደግሶ ፣ በዳይ ተጋብዘሃል
ውዱ ምግብ ቀርቦ ፣ በአንተና በአብ መሃል

ገጣሚ ሔኖክ አሸብር
🏹

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

02 Nov, 08:36


Channel photo updated

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

01 Nov, 15:55


prayer is the best and only solution to your próblems, so pray and don‘t give up.

ምን ማለት ነው ‽
ጸሎት ለችግሮችህ ሁሉ ምርጥ እና ብቸኛው መፍትሔ ነው፤
ስለዚህ ጸልይ እንጂ ተስፋ አትቁረጥ


@ያዕቆብ

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

30 Oct, 19:44


I had a plan,
but God had a better plan for me.
ምን ማለት ነው . . .?
እኔ እቅድ ነበረኝ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የተሻለ ዕቅድ አቅዶልኛል።


አሜን🙏

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

29 Oct, 19:14


በዚህ አመት ላንተ/ቺ በጣም ምርጡ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የምገባ ድንቅ ቻናል👏👏👏👏👏👏👏
Add channel የምለውን ይጫኑ 👇👇👇Wave👉 @EtCwaver

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

29 Oct, 17:25


▣ Click on This 👇
         Join Us
             ⇣
           🌺🌺
         🌺🌺🌺
       🌺🌺🌺🌺
     🌺🌺🌺🌺🌺
   🌺🌺🌺🌺🌺🌺
   🌺🌺🌺🌺🌺🌺
      🌺🌺🌺🌺🌺 
         🌺🌺 
              
                 🎋                   🍃
                 🎋              🍃🍃
                 🎋          🍃🍃🍃
                 🎋      🍃🍃🍃🍃
                 🎋    🍃🍃🍃🍃
                 🎋🍃🍃🍃🍃🍃
                 🎋🍃🍃🍃🍃
                 🎋
                 🎋
                 🎋
      ⿻ Join Us ⿻
      ⿻ Join Us ⿻
      ⿻ Join Us ⿻
      ⿻ Join Us ⿻

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

27 Oct, 19:35


ወንጌልን_ስበኩ!

በየዕለቱ ብዙ ነፍሳት (ሰዎች) ወደ ሲዖል እየተጓዙና እየጠፉ ነው። በየደቂቃው በሺዎች የሚቆጠሩ ነፍሳት ወደ ሲዖል ይወርዳሉ።
ወደ ሲዖል የሚገቡት ኢየሱስ ስለእነርሱም መስቀል ስላልተሸከመና ስላልሞተ ሳይሆን አሁን በዚህ ዘመን ያለን ክርስቲያኖች መስቀላችንን ተሸክመን ወንጌል ስላልሰበክን ነው።
ክርስቶስ የራሱን ድርሻ በሚገባ ተወጥቷል።
1ጴጥሮስ 3 : 18 ...
“ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥”
— -~~~
አንድ ነገር ለማድረግ ተራው የእኛ ነው።

መስቀላችንን ስንሸከምና ወንጌልን ስንሰብክ ብዙዎች ይድናሉ፤ ብዙዎች ይፈወሳሉ!

ደህንነትንና ዕርቅን ወደ ዓለም ለማምጣት የክርስቶስ መስቀል ከእኛ መስቀሎች ጋር አብሮ ይሰራል።

መስቀላችንን እንሸከም!
ወንጌልን እንስበክ!
ነፍሳት ይዳኑ!

በ ያዕቆብ ተጻፈ

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

26 Oct, 10:20


ይቅርታ የጎጂዎችህን ሕይወት ከመቀየር ይልቅ የተጎጂዎችን ሁለንተና ይቀይራል


Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በ18 አመቱ በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶበት 39 አመት ከታሰረ በኋላ (አብዛኛውን ግዜ የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል)፣ ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት በነፃ የተለቀቀ ሰው ነው።

እናም ልክ ከእስር ቤት ተለቆ ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና ... «ይቅር ብዬሃለው» .... ብሎ አቀፈው።

ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ :-

....«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»....

ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አይምሯቹ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!!
ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ ፣ ጉዳታችሁ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ፣ ብዙ ደርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!!

ይቅርታ ለራስ የሚሰጥ ድንቅ ስጦታ ነው ሰው ይቅር ማለት ሲጀምር ህይወት ይጀምራል።

የበደለንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሣይሆን ፍቅርን ማስተማር ፣ ቀንነትን መዝራት ፣ ህይወትን ማደስ ነው።

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

25 Oct, 15:55


መርሕ አራት፡-

🙏 ዘውትር ለመጸለይ ትጋ

እግዚአብሔር የትጋት ጸሎትን ያከብራል (ማቴ. 7፡7-10)

ኢየሱስ ቀደም ሲል ስለ ጸሎት አስተምሯል (ማቴ. 6፡9-15)።
ክርስቶስ የጸሎት ኣመለካከታችን ከእግዚአብሔር በምንቀበላቸው ነገሮች ላይ ሳይሆን፥ «እግዚኣብሔር ከሁሉም በላቀ ሁኔታ እንዴት ሊከብር ይችላል?» በሚለው ጉዳይ ላይ ማተኮር እንዳለበት አሳይቷል።
በተጨማሪም ክርስቶስ ስለ ደቀ መዛሙርቱ ሕይወት ዐበይት የለውጥ አሳቦችን እያስተማረ ነበር። ብዙዎቻችን ፈጥነን የምንሰጠው ምላሽ፥ «ይሄ የማይቻል ነው።» «እኔ ጠላቶቼን ልወድ፥ ባሕሪዩን ልቀይር አልችልም» የሚል ነው። ክርስቶስም ይህ በተፈጥሯዊ ብርታታችን ሊሳካ እንደማይችል ተናግሯል።

ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች እንደ መሆናችን መጠን፥ ሁሉንም ነገር የሚያስችል የኃይል ምንጭ አለን።
''ያ የኃይል ምንጭ የሚገኘው በጸሎት ነው።''

ኢየሱስ ወደ ጸሎት ርእሰ ጉዳይ ተመልሶ ደቀ መዛሙርቱ እንዲጠይቁ፥ በር እንዲያንኳኩና እንዲሹ አበረታትቷቸዋል።

በተለይ ክርስቶስ ' እንደሚሆኑና እንደሚቻሉ' ስለገለጸላቸው ጉዳዮች ባለማቋረጥ ከጸለይን፥ እግዚአብሔር ጸሎታችንን በመመለስ ኃይልን ይሰጠናል።
በዚህ ጊዜ ባሕርያችን ይለወጥና ለዓለም በማይቻል መንገድ እንመላለሳለን።

(ማስታወሻ፡- ምንም እንኳ ይህ የጸሎት መርሕ ከእግዚአብሔር ለምንፈልጋቸው ነገሮች ሊሠራ ቢችልም፤ ዓውደ ምንባቡ የሚያሳየው እግዚኣብሔር የክርስቶስን ትእዛዛት የምንፈጽምበትን መንፈሳዊ እይታና ባሕርይ እንዲሰጠን መጠየቅን ነው።)

እግዚአብሔር ጸሎትን የዕድገታችን ሂደት አካል አድርጎ ይጠቀማል። በጸሎት ሳይተጋ መንፈሳዊ ብስለትን ሊያገኝ የሚችል ሰው የለም።
በጸለይን ጊዜ እግዚአብሔር ፈጥኖ የሚመልስ ቢሆን ኖሮ፥ ማናችንም ለጸሎት ልንተጋ አንችልም ነበር። እርግጥ እግዚአብሔር ፈጣን ምላሽ የሚሰጥባቸው ጊዜያት አሉ። እንደዚሁም ደግሞ ትዕግሥትንና ለፈቃዱ መገዛትን እንማር ዘንድ ምላሹን የሚያዘገይባቸው ጊዜያትም አሉ።

በጸሎት ላይ ልበ ሙሉነትንና ባለማቋረጥ መትጋትን የሚሰጠን ስለ እግዚአብሔር ማንነት ያለን ግንዛቤ ነው። እርሱ ከምድራዊ አባቶቻችን በላይ ለእኛ ከሁሉም የሚሻለውን ነገር ለመስጠት ይቸኩላል። ነገር ግን ለእኛ የሚሻለንን የሚያውቀው እርሱ ነው። የትኛው ዳቦ፥ የትኛው እባብ እንደሆነ ያውቃል። ለዚህ ነው እግዚአብሔርን በመተማመን፥ ለእርሱ በመገዛትና ለፈቃዱ መፈጸም ሳናቋርጥ መጸለይ የሚገባን።
በማንኛውም ሰዓት ቢሆን ያለማቋረጥ በትጋት መፀለይህን አታቁም!


@ww_yaiki9

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

25 Oct, 10:40


⚡️ WAVE FOLDERS ⚡️

channel ያላቹ በቀን 400 🔰Subscribe በላይ በማስገባት የሚያሳደግ
Wave folder መግባት የምትፈልጉ

••••••••••••••••••••||||••••••••••••••••••••

5000+Subscribe እስከ
50,000+Subscribe

መግባት የሚፈልግ በውስጥ ያናግረኝ።
መንፈሳዊ ቻናል ብቻ

INBOX 📥👇
@free_wave1

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

24 Oct, 20:39


እግዚአብሔር በህይወትህ የሚያደርገውን ያውቃል። የሚሰጠውና የሚወስደው ሁሉ ለራስህ ጥቅም ነው።
ከአመድ ውስጥ ውበትን እንዴት እንደሚሰራ ሙሉ ግንዛቤ ላይኖርህ ይችላል፣ ግን ለማንኛውም እሱን እመን። ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን አይቶታል። እግዚአብሔር ላንተ ሊያደርግልህ ካሰበው ነገር የሚያስቀረው ትግል ወይም ሀይል የለም።
አምንሃለው በለው!

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

21 Oct, 19:23


ግንባታው እንዴት እየሄደላችሁ ነው



ሁሉም ሰው ህይወት የሚባል ቤት እየገነባ ነው። ግን ጥያቄው የት ነው?
አንዳንዶቹ በዓለት ላይ ይሠራሉ፤ አንዳንዶቹ ግን በአሸዋ ላይ፤
ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ያለ ሲመስል በሁለቱ መካከል ብዙ ልዩነት አታይም።
ነገር ግን የቤቱ ጥንካሬ የሚገለጠው ዝናቡ ሲወርድ፣ ጅረቶች ሲነሱ፣ ነፋሱ ሲነፍስ እና ቤቱን ሲመታ ነው።
ሕይወታቸውን በዓለም መሠረት ላይ የሚገነቡ ችግሮች፣ ቀውሶች እና አደጋዎች ሲጋፈጡ መቆም አይችሉም።
ከኢየሱስ ስም በቀር ከዲያብሎስ ኃይል የሚጠብቀን ምንም ነገር የለም።
✍️ ከኢየሱስ ስም በቀር ከኃጢአት ኃይል ነፃ የሚያወጣን ምንም ነገር የለም።
✍️ ከኢየሱስ ስም በቀር በገሃነም ኃይል ላይ ድል ሊሰጠን የሚችል ምንም ነገር የለም።
@ ልንመካበት የምንችለው እውነተኛ እና ብቸኛው መሰረት ኢየሱስ ነው።
👉 የኢየሱስ ስም መጠጊያ የምንገኝበት ጠንካራ ግንባችን ነው (ምሳ 18:10)

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

19 Oct, 13:16


የኢየሱስ ተከታዮች ሊከተሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መርሖዎች
(ማቴ. 6፡19-7፡29)

ክፍል 3

መርሕ ሦስት፡-
ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት የፈራጅነትን አመለካከት አታንጸባርቅ!
(ማቴ. 7፡1-6)።

«የሆነ ምሥጢራዊ ነገር ስላለ ተጠንቀቅ።
ልታታልልህ እየሞከረች ነው።
አፉዋ የሚናገረው ቃል ከልቧ የፈለቀ አይደለም።
«ይህንን ለምን እንዳደረገች አውቃለሁ።
ስለማትወደኝ ልትጎዳኝ ትፈልጋለች።»
«ከእኔ ለመቅደም ስለሚፈልግ፥ ከእኔ ጋር አይስማማም።
ይህን ያደረገው እርሱ የሌላ ጎሳ አባል ስለሆነና የእኛን ጎሳ ስለማይወድ ነው።»
«ሊፕስቲክ መቀባቷ መንፈሳዊት ሴት አለመሆኗን ያሳየናል።»
. . . ወዘተ . . .

ክርስቶስ ተከታዮችን ከሚያጋጥማቸው ታላላቅ ችግሮች አንዱ፥ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር መልካም ግንኙነት አለማድረግ ነው። የችግሩም መንሥዔ በጎሳዎች፣ በመሪዎችና በግለሰቦች መካከል ጥርጣሬ የሚከሰትባቸውን ዐበይት ምክንያቶች አለመገንዘባችን ነው።
ከግለሰቡ ተግባር ባሻገር ዘልቀን፥ ልቡን የምንመረምርበት የተለየ ዓይን ያለን ይመስለናል። ይህ ግን ስሕተት ነው።
✍️ የሰውን ልብ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ይለናል።

ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ከዚህ የሰዎች ዝንባሌ እንዲታቀቡ «አትፍረዱ» ሲል አጥብቆ አስጠንቅቋቸዋል።
«
#መፍረድ» የሚለው ቃል ሁለት ፍካሬያዊ ትርጉሞች ኣሉት።
`Ä' ክርስቲያኖች ሊያደርጉ የሚገቧቸውን ነገሮች መገምገምን ሊያመለክት ይችላል።
¤ - ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ የሰዎችን፥ በተለይም የሐሰተኛ አስተማሪዎችን ሕይወት በመገምገም እውነተኛ ደቀ መዛሙርት መሆን አለመሆናቸውን እንዲለዩ ነግሯቸዋል (ማቴ. 7፡15-20)።
ግምገማው የሚካሄደው ግን በግልጽ መረጃዎች እንጂ በስውር አነሣሽ ምክንያቶች አይደለም።

'B' - መፍረድ የሌሎችን ኣነሣሽ ምክንያቶች በንቀት መመልከትን ሊያመለክት ይችላል።

✍️ ይህንን በምናደርግበት ጊዜ ኣመለካከታችን፥ «እኛ ከእነርሱ እንሻላለን» የሚል ነው።
ከተግባራቸው አልፈን ልባቸውን ለማየት የምንችል ይመስለናል። ክርስቶስ በዚህ መንገድ መፍረድ እንደሌለብን ተናግሯል።

ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ስንተች የራሳችንን ልብ በኃጢአት መቆሸሽ ከምንም አንቆጥርም። ኢየሱስ በዓይኑ የእንጨት ግንድ (ምሰሶ) ስላለበት ሰው በሚናገር ኣስገራሚ ምሳሌ ተጠቅሟል።
ይህ ሰው በዓይኑ ጉድፍ ያለበት ሰው ሲያጋጥመው ለመርዳት ይሽቀዳደማል።
በራሱ ዓይን ውስጥ ያለው ግንድ ግን ይህን ከማድረግ ይከለክለዋል።
በተመሳሳይ መንገድ፥ የሌላውን ሰው የባሕርይ ችግር ወይም ድብቅ ኃጢኣት ማየቱ ቀላል ነው። ነገር ግን ብዙዎቻችን ራሳችንን አጥርተን አንመለከትም።
ለዚህ መፍትሔው የሌላውን ሰው ችግር ለማቃለል አለመሞከር አይደለም። ችግር ያለበትን ሰው መርዳቱ ተገቢ ነው።
በመጀመሪያ ግን የራሳችንን ሕይወት አይተን ሌሎች ሕይወታችንን ለመመርመር እንዲረዱን ልንጠይቃቸው ይገባል።
መጀመሪያ ሕይወታችን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲስተካከል ካደረግን በኋላ፥ ሌላው ሰው በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ሕይወቱን እንዲመረምር በትሕትና ልንረዳው እንችላለን (ያዕ. 5፡19-20፤ ገላ. 6፡0።

የሌሎች ሰዎችን ችግሮች እየተመለከትን አነሣሽ ምክንያቶቻቸውን መፍረድ በምንጀምርበት ጊዜ፥ ምን ይከሰታል?

በመጀመሪያ፥ ሰዎች በእኛ ላይ ይፈርዳሉ።
በሁለተኛ ደረጃ ፥ ለአመለካከታችን በእግዚአብሔር ፊት እንጠየቃለን።

ይህን ኣሳብ ወደ ተቃራኒ ኣቅጣጫ እንዳንወስድ መጠንቀቅ አለብን።
አንዳንድ ሰዎች ግምገማ መፍረድ እንደሆነ በመግለጽ የዚህ ዓይነት ተግባር እንዳንፈጽም ያስጠነቅቁናል።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን በእግዚአብሔር ቃልና በግልጽ ተግባራቸው ላይ ተመሥርተን ሰዎችን መገምገም እንዳለብን ያስተምራል። ለዚህ ነው ክርስቶስ የተቀደሰን ነገር ለውሾችና ለእሪያዎች መስጠት እንደሌለብን የሚያስረዳውን ምሳሌ የተናገረው።
በዚህ ክፍል ውሾችና እሪያዎች ወንጌሉን ለመቀበል የማይፈልጉትን ሰዎች ያመለክታል። ስለሆነም ክርስቶስ፥ ደቀ መዛሙርቱ እግዚአብሔርን የሚቃወም አመለካከት ይዘው መስማት ለማይፈልጉ ሰዎች በመመስከር ጊዜያቸውን ማጥፋት እንደሌለባቸው ገልጾአል።
ስለዚህ ከማንኛውም ሰው ጋር ባለህ ግኑኝነት ውስጥ የፈራጅነት ባህርይ በፍጹም አታንፀባርቅ!!


@ww_yaiki9

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

17 Oct, 10:01


የ''ዕብድ ጴንጤዎች ጉዳይ . . . !

አንዲት ነቢይ፥ «ክርስቶስ የዛሬ ዓመት ይመጣል። ስለሆነም ሁላችሁም በፍጥነት መጋባት ይኖርባችኋል። ሥራ ያላችሁ ደግሞ ሥራችሁን ለቅቃችሁ ባላችሁ ገንዘብ ራሳችሁን ማስደሰት አለባችሁ። እህል መዝራቱ አስፈላጊ አይሆንም። ባጨዳው ጊዜ እዚህ አትኖሩምና» ስትል ተነበየች። ብዙ ሰዎች አስተዋይ ሽማግሌዎች የሰነዘሩትን ማስጠንቀቂያ ችላ ብለው ምክሯን ተቀበሉ።

ወጣቶቹ ስለ ነገ ሳያስቡ የትዳር ጓደኞችን መረጡ። ወዲያውም እነዚህ ልጃገረዶች አረገዙ። ሰዎች ሥራቸውን ለቅቀው ያጠራቀሙትን ገንዘብ ሁሉ መጠቀም ጀመሩ። ንብረቶቻቸውን ሁሉ ሸጡ። በዓመቱ መጨረሻ ላይ ሁሉም ነቢይቱ ክርስቶስ ይገለጣል ባለችው ስፍራ ላይ ተሰበሰቡ።
የክርስቶስን መገለጥ እየተጠባበቁና እየዘመሩ ለረጅም ጊዜ ጠበቁት። እርሱ ግን ብቅ አላለም። በሁኔታው ተበሳጭተው ነብይቱን ከቤተ ክርስቲያን አባረሯት። ይሁንና ጥፋቱ ቀድሞውንም ተፈጽሞ ነበር።
በውጤቱም . . .
አንዳንዶች ክርስቶስ ቃሉን አላከበረም በሚል እምነታቸውን ተዉ።

ሥራቸውን የለቀቁት ወጣቶች ሕፃናት ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ባለመቻላቸው ትዳራቸውን ጥለው ወደ ከተማ ኮበለሉ።
ባሎቻቸው የተለዩአቸው ወጣት ሴቶችም የገቢ ምንጭ ለማግኘት ሲሉ ወደ ሴተኛ አዳሪነት ተሠማሩ።
ብዙዎቹ ኑሮ ስለተናጋባቸው በድህነት ይማቅቁ ጀመር።
🏹 በማኅበረሰቡ ውስጥ ይኸው የእብድ «ጴንጤዎች» ጉዳይ መሳለቂያ ሆነ።

መልዕክታችን እንዲህ ነው . . .

¤ የእግዚአብሔርን ቃል እንወቅ

¤ ሁሉንም ነገር እንመርምር

¤ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንኑር

🏹 ያዕቆብ እንደከተበው🤗

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

12 Oct, 19:43


የኢየሱስ ተከታዮች ሊከተሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መርሖዎች
(ማቴ. 6፡19-7፡29)


መርሕ ሁለት፡-

ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቅ፥ ለሁሉም በእግዚአብሔር ተማመን (ማቴ. 6፡25-34)

በዕብ. 11፡6 ላይ፥ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንደማይቻል ይናገራል።

በአንድ ደቀ መዝሙር ሕይወት ውስጥ እጅግ መሠረታዊ የሆነው መርሕ በነገር ሁሉ በእግዚአብሔር የመታመን መርሕ ነው። በምንጨነቅበት ጊዜ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ፍላጎታችንን ስለ ማሟላቱ መጠራጠራችን ነው።
✍️ ሰዎች የሚጨነቁባቸው መሠረታዊ ነገሮች ምንድን ናቸው?
፩- ምግብና
፪- ልብስ ናቸው።
ክርስቶስ ግን ለእነዚህም መጨነቅ እንደማያስፈልግ አስተምሯል። ገንዘብ የሚያስቀምጡባቸው ባንኮች ወይም ምግብ የሚገዙባቸው የገበያ አዳራሾች ባይኖሯቸውም፥ እግዚአብሔር የምድር ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባል።
እነዚህ ፍጥረታት ምግብ አጥተው አይራቡም።
እግዚኣብሔር ሰዎች ከአዕዋፋትና ከእንስሳት እንደሚበልጡ ገልጾአል። ስለሆነም እግዚአብሔር አነስተኛ አስፈላጊነት ያላቸውን እንስሳት ከመገበ፥ የሰዎችን ብቻ ሳይሆን የመንፈሳዊ ልጆቹን ፍላጎቶች እንደሚያሟላ እንገነዘባለን።

ክርስቶስ የንጉሥ ሰሎሞንን ውብ (ማለፊያ) ልብሶች ከአትክልቶች ጋር አነጻጽሯል። እግዚአብሔር ትናንሽ ተክሎችን እንደ ሰሎሞን ካሉት እጅግ ሀብታሞች የበለጠ አድምቆ ያላብሳቸዋል። እነዚህ አበቦች ከጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት የበለጠ ዕድሜ የላቸውም። ወዲያው ጠውልገው በእሳት ይቃጠላሉ።

ሰዎች፥ በተለይም የእግዚአብሔር ልጆች፥ ለእግዚአብሔር ከአበቦችና ከተክሎች በላይ አስፈላጊዎች ናቸው። ስለሆነም ያለጥርጥር የምንፈልገውን ልብስ ያለብሰናል።

ቆይ እኔ የሚልህ የምትጨነቀው ምን ለማግኘት ነው?

የጭንቀት ተቃራኒ ምንድን ነው?
ከጭንቀት ለመገላገል የሚረዳን ምንድን ነው?
በሕይወት የተሳሳቱ እሴቶችን ከመያዝ የሚጠብቀን ምንድን ነው?
ክርስቶስ ተከታዮቹ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ከፍተኛ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስቧቸዋል። ዓይኖቻችንን በእግዚኣብሔር ዘላለማዊ ነገሮች ላይ ልንጥል ይገባል።
ክርስቶስ . . .
- በእርሱ አገዛዝና ለእርሱ አስፈላጊ በሆኑት ነገሮችና
- ከእርሱ ጋር ካለን ግንኙነት በሚመጣው ጽድቅ ላይ ብናተኩር፥ ጭንቀታችን እንደሚወገድ ገልጾአል።
ይህም ጽድቅ በታዛዥነትና በትክክለኛ መንገድ በመመላለስ ራሱን ይገልጻል።

ይጠቅሙናል የምንላቸው ነገሮች ከእግዚአብሔር መንገዶች ጋር የሚስማሙ ሲሆኑ፥ እንደ ገንዘብና ትምህርት ያሉ ሌሎች ጌቶች እንዲቆጣጠሩን አንፈቅድም። ይህም ሲሆን እግዚኣብሔር ብዙውን ጊዜ የሚያስጨንቁንን መሠረታዊ ፍላጎቶቻችንን ያሟላል።

በመጨረሻም ክርስቶስ ስለ ወደፊቱ ዘመን መጨነቁ ሞኝነት እንደሆነ አብራርቷል። ምንም ያህል ብንጨነቅ የነገን ክስተቶች መለወጥ አንችልም።
ጭንቀት የሚያስከትለው ነገር ቢኖር
ኀዘን፥
ሽበትና
የጨጓራ ሕመም ብቻ ነው።
አባታችን የወደፊቱን ዘመን እንደሚቆጣጠርና እርሱ ያልወሰነው ነገር እንደማይደርስብን እርግጠኞች ልንሆን ይገባል። በእርሱ ላይ ዓይኖቻችንን ተክለን በታዛዥነት የምንመላለስ ከሆን፥ እግዚአብሔር ወደፊት የሚመጣውን የትኛውንም ችግር ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት ይሰጠናል።
" ችግሩ የሚመጣው መፍትሔውን ከራሳችን ለማመንጨት በምንታገልበት ጊዜ ነው።"
ስለዚህ ስለማንኛውም ነገር አትጨነቅ!!

መርህ_2
በ ያዕቆብ ✍️

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

10 Oct, 19:43


በ 1 አልቤም 26 መዝሙር ይቻላል


በመዝሙር ሥራ ውስጥ (በፕሮዲውሰርነት) ለበርካታ ዓመታት ቆይቻለሁ፤ ለዚህ ዐይነቱ መረጃም ቅርብ ነኝ። 26 መዝሙሮችን ሰብስቦ አዲስ ሰንዱቅ ያወጣ ዘማሪ ኖሮ አያውቅም። እኔ እስከማውቀው ድረስ እንዲህ ዐይነት መልካም ዝማሬዎችን እንዲህ አትረፍርፎ በመስጠት ጉዳይ አስቴር አበበ የመጀመሪያ ናት። እናመሰግናለን።

የመዝሙር ቁጥር መብዛቱ የመልእክት ልዩልዩነትን (variety) ስለሚፈጥር ባለፍንባቸውና በምናልፍባቸው ሁኔታዎች ላይ የእግዚአብሔርን ምክር የምናገኝበት መልካም ዕድል ይጨምራል። እናም ባልተኬደበት መንገድ ላይ እንደ አስቴር የእግዚአብሔርን ጸጋ ታምኖ መራመድ መታደል ነው። እናመሰግናለን።

የቁጥር ብዛት በራሱ መልካም ነገር ቢሆንም፣ በራሱ በቂ አይደለም። የአስቴር መዝሙሮች ግን ጥሩ መልእክቶችን የያዙ፣ ከሕይወት የተጨለፉ፣ በጥሩ ሁኔታ የተሠሩ መልካካም ዝማሬዎች ናቸው። እንዲህ ዐይነት በረከት በዚህ ልክ ማግኘት እንቁጣጣሽና ፋሲካ በአንድነት ሲመጡ እንደ ማለት ነው። እናመሰግናለን።

እኅቴ አስቴር አበበ፤ በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ስላስቀመጠው ጸጋ ስሙን እባርካለሁ። ይህ ገና ጅማሬሽ እንደሆነም አምናለሁ።

ለዚህ ሥራ የደገፉሽንም ሁሉ እግዚአብሔር ይደግፋቸው።


ጳውሎስ ፈቃዱ እንደከተበው🏹

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

09 Oct, 09:58


የውሸት እየኖርን፤
የእውነት አንሙት


ከተገለጠው ድርጊታችን በላይ የልብ አካሄዳችን የነገ ፍሬያችንን ይወስናል!

የተገለጠው ድርጊታችን ለሰው ይታያል!

ልባችን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ታይቶ ይመዘናል!

ምንም ነገር ስናደርግ የምናደርግበት መንፈስ ከድርጊታችን በላይ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ አለው!

ያልተኖረ የታይታ ገፅታ ብቻ ምን በሰው ዘንድ ጎሽ ቢያሰኝና ቢገነባ ጊዜ ቆጥሮ ባዶነቱ ይገለጣል፤ ከትወና ሕይወት አያልፍም!
እግዚአብሔር እያዘነ የምንገነባው ገፅታ የትም አያደርሰንም!

በልባችን እንለወጥ!
ብልህ እንጂ ብልጣብልጥ አንሁን!

ሳይረፍድ ብዙ ሳንከስር . . .
የእውነት እንሁን!
የእውነት እንኑር!
አንሸነጋገል!
የእውነት ልብና ቅንነት ገፅታችን ይሁን!
እርሱ ጎሽ ይበለን፤ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው!

በእውነት መንፈስ ተባረኩ!

ሃና ተክሌ🥰

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

09 Oct, 06:20


ራእይ ሲጠፋብን

1.  የመኖር ግለትና ጉጉትና መነሳሳት እያጣን እንሄዳለን፣

2.  ስሜታችን አንድ ወጥ ያለመሆንና መዋዠቅ ያታይበታል፣

3.  አንድን ነገር ለመጀመር የመወላወልና ከጀመሩ በኋላ ሃሳብን መቀየር ይታይብናል፣

4.  የሰዎችና የሁኔታዎች መለዋወጥ በቀላሉ የሚጎዳንና ከሁኔታውም ማገገም አለመቻል ያጠቃናል፣

5.  ራሳችንን ካወጣነው ግብ አንጻር ሳይሆነ ሰዎች ካሉበት ደረጃ አንጻር በማነጻጸር የዝቅተኛነት ስሜት ይጫነናል፣

6.  ከሰዎች ጋር በቀላሉ የመጣበቅ (attached የመሆን) እና ከአንዳንድ ሰዎች ውጪ በፍጹም ለመኖር ያለመቻል ተስፋ ቢስ ስሜት ውስጥ እንገባለን፣

7.  መማር፣ መስራትና መሰማራት የምንፈልገውን መስክ ባለማወቅ ግራ ስንጋባ ራሳችንን እናገኘዋለን፣

8.  ምንም ነገር ላይ ማተኮር እስከማይቻል ድሰረስ ከማሕበራዊ ሚዲያ እና ከመሳሰሉት አሁል ልማዶች ለመላቀቅ አለመቻል፣

9.  ካለፈው ስህተት ከመማር ይልቅ በጸጸጽ ውስጥ የመኖር ዝንባሌ፣

10.  በአመለካከትና በክህሎተት ራስን የማሻሻል ፍላጎት ማጣት፡፡

ከላይ የተጠቀሱት መሰል ችግር እንዳለባችሁ ካሰባችሁ ምንጩ ራእያችሁን ያለማወቅ ሊሆን ይችላልና አስቡበት፡፡

ዶ.ር ኢዮብ ማሞ🙏

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

08 Oct, 08:50


#አስተካክለናል

ከዚህ በፊት አላስፈላጊ ማስታወቂያዎች በዚህ ቻናል ላይ ስሰሩ ቆይተዋል።
በእናንተ ጥያቄ መሠረት ከዛሬ ጀምሮ መንፈሳዊ ያልሆኑ ማስታወቂያዎች አይቀርቡም

ስለሰጣችሁን አስተያየት እናመሰግናለን🙏

መልዕክቶቻችን ለሌሎችም እንዲደርሱ ሼር እናድርግ🙏

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

07 Oct, 12:23


የኢየሱስ ተከታዮች ሊከተሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መርሖዎች
(ማቴ. 6፡19-7፡29)

አንዳንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት እናወሳስበዋለን። የተለያዩ ክርስቲያን መሪዎች አገልጋዮች እንደ ክርስቲያን ፍሬያማ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ብዙ አሳቦችንና ደንቦችን ያስተምራሉ።
ይህ ደግሞ ክርስቲያኖች ተስፋ እንዲቆርጡና የበደለኛነት ስሜት እንዲሰማቸው ከማድረጉም በላይ በኋላ ሰዎችን ለማስደሰት ከመጣር በቀር ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖረን አያደርግም።

ኢየሱስ በቀጣዩ የተራራው ላይ ስብከቱ የመንፈሳዊ ሕይወትን መሠረታዊ መርሖዎች ቀለል አድርጎ አቅርቧል።
እነዚህን መርሖዎች ከግል ሕይወታችን ጋር ብናዛምድ፥ በመንፈሳዊ ሕይወታችን አድገን የክርስቶስ በሳል ደቀ መዛሙርት ለመሆን እንችላለን።


#መርሕ_አንድ፡-

🏹 በግል ሕይወትህ ላይ ሳይሆን፥ በዘላለሙ መንግሥት ላይ ትኩረት አድርግ!!

ክርስቲያኖችን ከሚያጋጥሙ ዐበይት ፈተናዎች ኣንዱ፥ የገንዘብ ጉዳይ ነው። ሁላችንም ለመተዳደሪያ የምንፈልገው ነገር በመሆኑ ገንዘብ በራሱ መጥፎ አይደለም።

በዛሬው ዓለም ውስጥ ገንዘብ ከሌለን፥ ምግብ ለመመገብ ልብስ ለመግዛት፥ የመኖሪያ ቤት ለመከራየት አንችልም። ነገር ግን ከዚህ አልፈን ገንዘብን በልባችን ውስጥ ከዐበይት ፍላጎቶቻችን ኣንዱ እንዲሆን በቀላሉ እናደርጋለን። ብዙ ገንዘብ ካገኘን ደስታችን የሚጨምር ይመስለናል። ኣዳዲስ ልብሶችን ልንገዛ፥ የተሻለ ምግብ ልንመገብ፥ በምርጥ ቤት ውስጥ ልንኖር እንችላለን። ይህም ብዙዎቻችን ተጨማሪ ገንዘብን እንድናገኝና ገንዘቡ የሚያስገኘውን ተጽዕኖና ደኅንነት እንድናሳድድ ያደርገናል።

ገንዘብ ሕይወታችንን እንዲቆጣጠር የምንፈቅድበት ዋንኛው ምክንያት፥ የተሳሳቱ ነገሮችን መመልከታችን እንደሆነ ኢየሱስ ራሱ ገልጾአል። ሥጋዊና መንፈሳዊ ዓይኖቻችን ለራሳችን የተመቻቸ ሕይወትን በማዘጋጀት ላይ ካተኮሩ፥ ልባችን በመንፈሳዊ ጽልመት ይሞላል። ነገር ግን መንፈሳዊ ዓይኖቻችን በመንፈሳዊ ነገሮችና በዘላለማዊ ጉዳዮች ላይ ካተኮሩ፥ ከሁሉም የሚልቀው ምን እንደሆነ በመገንዘብ ለዘላለም ሕይወታችን የሚጠቅም አኗኗርን እንከተላለን።
ሥጋዊ ዓይኖቻችን መንገድ አይተን እንድንሄድ እንደሚረዱን ሁሉ፥ መንፈሳዊ ዓይኖቻችንም መንፈሳዊ እውነቶችን ተረድተን በመንፈሳዊ አኳኋን እንድንመላለስ ይረዱናል።
የዓለም ነገሮች መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን እንዲያሳውሩ ከፈቀድንላቸው መንገዳችን በጨለማ ተደናቅፎ ከእግዚአብሔር እውነት እንርቃለን። ከዚያ በኋላ ክርስቶስን ልንከተል አንችልም።
(ይህ የምንመለከታቸውን ቪዲዮዎችና የምናነባቸውን መጻሕፍት በጥንቃቄ መምረጥ እንዳለብን ያስጠነቅቀናል። የምንመለከታቸው ቪዲዮዎች፥ የምናነባቸው መጻሕፍትና መጽሔቶች በአስተሳሰባችንና በተግባራችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖን ያስከትላሉ።)

ኢየሱስ አንድ ልብ ከአንድ ጌታ የበለጠ ሊያስተናግድ እንደማይገባው ገልጾአል። ይህም ክርስቶስ ወይም እንደ ገንዘብ ያለ ሌላ ነገር ሊሆን ይችላል።
አንድ ሰው ገንዘብን ወይም ሌላ ማንኛውንም ሥጋዊ ነገር የሕይወቱ ቀዳሚ ትኩረት እያደረገ የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ሊል አይችልም። ብዙም ሳይቆይ የገንዘብ ፍቅሩ ከምድርና ከሰማይ መርሖዎች አንዱን እንዲመርጥ ስለሚያስገድደው፥ ምድርንና ጊዜያዊ በረከቶቿን መምረጡ አይቀርም።
ስለዚህ የመጀመሪያ መርህ ሊሆን የሚገባው፥
"በግል ህይወትህ ላይ ሳይሆን በዘላለማዊው መንግስት ላይ ትኩረት አድርግ" የሚለው ነው።

ይቀጥላል . . .
#መርህ_አንድ
በ ያዕቆብ ✍️

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

03 Oct, 16:11


DHL እዚህ ደረጃ እንዴት ደረሰ ።

#Ethiopia | እ.ኤ.አ. በ 1969 ፣ 3 ወጣት ወንዶች በእጃቸው ላይ ጥቂት ሀብቶችን ይዘው የመላኪያ ንግዳቸውን ለመጀመር ወሰኑ ።

1. ADRIAN DALSEY
2. LARRY HILLBLOM
3. ROBERT LYNN

የየስማቸውን የመጀመሪያ ፊደሎች ወስደው *DHL* የሚል ስያሜን ፈጠሩ ፤ ሃሳባቸው በዚህ ኢንዱስትሪ ላይ ለውጥ ማምጣት ነው ።

ከ55 ዓመታት በኋላ ዛሬ DHL የአለማችን ግዙፉ የመላኪያ ካንፓኒ ሆነ ።

♤250 አውሮፕላኖች ።
♤ 32,000 ተሸከርካሪዎች ።
♤ 550,000 ሰራተኞች ይዞ ዛሬ DHL በሁሉም የአለማችን ክፍሎች ላይ ፓስታ እና መሰል ቁሳቁሶችን በመላክ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል ።

የዓመታዊ ገቢው በመቶ ቢሊዮን ዶላር ይገመታል።

*በህይወት ውስጥ፣ ስለ ፕሮጀክቶች፣ ንግድ፣ ስኬት፣ ህልም፣ ግቦች... አሉታዊ ሀሳብ ከሚያመነጩ፣ ፈሪ ከሆኑ እና ሰነፍ ሰዎች ከሚናገሩ ንግግር እራስህን ማራቅኸን አረጋግጥ።

``ጓደኛህ ንግድ ለመጀመር ከአንተ ጋር ለመቀላቀል ፈቃደኛ ካልሆነ እሱን ችላ በል እና ቀጥል።``

``ወንድምህ በንግድህ ስራህ ላይ ለውጥ እንድታመጣ ሊረዳህ ካልቻለ... ችላ በል እና ቀጥል።``

ወደ ንግድ ሥራ ከገባህ... በጠንካራ ሁኔታ ያዝ... DHL DHL ለመሆን 55 ዓመታት ፈጅቷል።

ስኬት ጊዜን፣ ጥረትን፣ ቁርጠኝነትን፣ ድፍረትን፣ ብልህነትን እና ትኩረትን ይጠይቃል።

ታሪኩ ዘዉዱ
ከካናዳ 🇨🇦

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

02 Oct, 19:02


' ጥቂት እንታገስ '


የእግዚአብሔር ጊዜ
¥ በጣም ዘገምተኛ ነው ግን ነፋስን ይቀድማል!!
¥ በጣም ፈጣን ነው ግን በእኛ ግምታዊ ልኬት አይጣጣምም!!

ኣይ የእግዚአብሔር ነገር🤗

የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት

02 Oct, 03:52


“አይቻለሁ፣
እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ
እመሰክራለሁ።”

— ዮሐንስ 1፥34 (አዲሱ መ.ት)

Please join & Sher 🙏
@GCYU9
@GCYU9
@GCYU9