Mohammedamin Kassaw @mohammadamminkassaw Channel on Telegram

Mohammedamin Kassaw

@mohammadamminkassaw


📌 ከእስልምናና ሙስሊሞች ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አጋራለሁ::

📌 ለማህበረሰባችን ለውጥ የሚውሉ እይታዎችን አንፀባርቃለሁ::

አስተያየታችሁን @MOHAMMADAMMINM ያድርሱ:: ቻናሉን ለሌሎች በማጋራት ተደራሽ ያድርጉ:: ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!

Mohammedamin Kassaw (Amharic)

ሞሃሜዳምን ካሳው ቡኮ አዲሱ ቦታ ነው ከእስልምናና ሙስሊሞች ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎችን እና ለማህበረሰባችን ለውጥ የሚውሉ እይታዎችን በቀላሉ አድርገናል። የዚህ ቦታ በሞሃሜዳምን ካሳው ላይ ከከፈለው ጥሩ በሽታ የሚገኝ ቢሆን ይመረጣል። እሱም በ@MOHAMMADAMMINM በመካከል ይዘቱን ለሌላው ቡክ በመተግበር የተገኘውን የእውነት ይመሰለናል። እሱ በግንቡ ይህንን በሆነ እና በሆነ ቻናሉ ተመዝግበዋል። ነገር ግን የሚፈልጉ ሰዎች የጀዛኩሙላህ እራሱን ለማዳን እና እንደገና እንዲገደብ ይጋራሉ።

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 21:05


እዚሁ ኢትዮጵያ ወንዶ የሚባል ወረዳ ሰደድ እሳት አመሻሹን እንደተከሰተ ተገልፇል::

ያስፈራል ••• በእዝነቱ ይታረቀን!

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 20:32


ይህ ሰው ካህሳይ ይባላል:: የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎችን እያወናበደ ያለ መምህር የሚልን ስም የያዘ የክፋት መምህር:: ሙስሊም ተማሪዎችን የሚከለክል መመሪያ ት/ቤታችሁ ከጥቅምት ጀምሮ ለምን አወጣ ተብሎ ሲጠየቅ "ፀጉራቸውን የሚገላለጡት ተማሪዎች ፀጉራቸውን ከሚሸፍኑት ጋር አንማርም!" ስላሉ ነው አለ::

ማለቱን አይሉም ••• ግን ቢሉስ ••• ሀገር አንድን አካል ብቻ መምሰል አለባት ማለት ነው? ወይ ደግሞ በዚህች ሀገር ውስጥ እምነቴ ብሎ ክብርን መጠበቅ አይፈቀድም ነው?

ግን ምንድን ነው የተማረው በአላህ?

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 20:04


ኒቃብ ህልውና ነው!

ኒቃብ ሲነሳ አጀንዳዎችን መዝዞ ኒቃብን ትንሽ አጀንዳ ለማስመሰል የሚሞክር አካል ካለ እርሱ ምስጥ ነው:: የኒቃብ ጥያቄ ሲነሳ የኡማው ክብር እና የሴት ልጁ ህልውና የማይታየው ሰው Short-sighted ከመባል አያልፍም::

እስልምና ለሚስቱ ሲል የተጋደለ ብሎ ከሸሂድነት ጎራ ይመድባል:: ለክብሩ ሲል ነፍሱን የሰጠንም ሸሒድ ያደርጋል::

እዚህጋ በምንም መልኩ በምንም ምክንያት ከትግል መስመር የሚሸሽ ሰው ክብር የሚባለውን ቀይ መስመር እየተላለፈ መሆኑን ይወቀው:: ከዚያ ደግሞ ኒቃብን አልፈው --- ሴት ልጁንም አልፈው --- በራሱ ክብር እና ህይዎት ሲመጡበት ራሱን መች እንዳዋረድ በግልፅ ይገባዋል::

ኒቃብ ሕልውና ነው ••• ከደማችሁ ጋር አዋህዱት!

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 18:54


ዲላ ዩኒቨርሲቲ ••• ተጨማሪ!

ኦዳያ ካምፓስ ያሉትን ተማሪዎች ቢያስገቧቸውም በዋናው ግቢ (agri campus) ያሉትን ግን ሒጃብ ካልወለቀ አትገቡም ብለዋቸው ሁሉም ተማሪዎች ተመልሰው ከመስጂድ አድረዋል:: የሚገርመው በዋናው ግቢ ያሉት አውልቁ ያሉት even ማስክን ነው::

ያሳዝናል ••• ክብርህን ካላወለቅክ ብሎ ተማሪውን ከግቢ ውጭ የሚያሳደር የልሕቀት ማዕከል ተፈጥሯል:: ግን እንደው ምንድን ነው የሚያስምሩት? የተማሩትስ ምን ይሆን?

ብቻ ••• ነፃነት በነፃ አይገኝም!

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 18:16


ዲላ ኒቃቢስቶቹ ለዛሬ ገብተዋል!

ዩኒቨርሲቲው አይገቡም ብሎ ቢከለክልም የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች "ኒቃቢስቶች ካልገቡ አንገባም!" በማለት አብረዋቸው እስከ ምሽት 3:00 ቆይተው ገብተዋል::

መሠል ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ ችግር ፈጣሪዎችም ለፍትሕ እንዲቀርቡ ሁሉም አካል ተረባርቦ መስራት ይጠበቅበታል::

ነፃነት በትግል እንጅ በነፃ አይገኝም!

©️ EHEMSU

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 17:51


ነገረ ኒቃብ ••• በዲላ ዩኒቨርሲቲ!

ከአንድ ወር በፊት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አገልግሎት እና የደህንነት ክፍል ሀላፊ የሙስሊም ተማሪዎችን ተወካዮች ጠርተው "ከአሁን ቡሃላ ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብን ለብሰው መግባትም ሆነ መንቀሳቀስ አይችሉም!" ብለው ነበር:: ተወካዮቹም አይሆንም መብታችን ነው በማለታቸው ሳቢያ በታህሳስ 9 ለሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አካላት ሁሉ ደብዳቤ አስገቡ:: የደብዳቤውን መግባት ተከትሎም ዩኒቨርሲቲው "ጉዳዩን ወደ ሕግ ክፍል መርቸዋለሁ:: ውሳኔ ጠብቁ:: እስከዚያ ግን ይልበሱ::" የሚልን መልስ ሰጠ::

ሆኖም አልፎ አልፎ ክልከላ እና ትንኮሳ ማካሄዳቸውን ተከትሎ የጌዴኦ ዞን መጅሊስ ጉዳዩን በመቃወም ለዩኒቨርሲቲው በጥር 5 ከአምስት ቀናት በፊት ደብዳቤ አስገባ:: ይህንንም ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተማሪዎች እንወያይ የሚል ጥያቄን ሲያቀርቡለት "እሺ! እደውላለሁ!" የሚል መልስን በመስጠት ዛሬ ደረሰ::

ሆኖም በዛሬው እለት ተማሪዎችን ሳያማክሩ "ኒቃብ ተለብሶ መግባት አይቻልም!" ብለው ከልክለዋል:: ተማሪዎች እስካሁንም ከመስጂድ ናቸው:: በሕገ- ወጥነታቸው ይቀጥሉበት እንደሆነ የሚታይ ይሆናል::

ፍትሕ ለኒቃቢስቶች!
ፍትሕ ለሙስሊም ተማሪዎች!!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!!


©️ EHEMSU

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 17:36


ዲላ ዩኒቨርሲቲ ኒቃብ ለባሽ ተማሪዎች እንዳይገቡ ከልክሏል!

  ከዚህ በፊት ዩኒቨርሲቲው በትዕዛዝ ደረጃ እንዳትለብሱ ብሎ ተማሪዎች ከሕግ ውጭ ነው በማለታቸው ሳቢያ ለውይይት ቀጠሮ ቢሰጣቸውም ተማሪዎችን ሳያወያይ በዛሬው እለት መግባት አትችሉም ብሎ ከልክሏቸዋል:: ተማሪዎቹም በአሁን ሰዓት ከግቢ ውጭ ናቸው::

©️ EHEMSU

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 16:16


መቱ በደሌ ••• ተደገመ!

ዛሬ የWelcome ፕሮግራም አዘጋጅተው ደስታቸውን ገልፀዋል:: ኒቃቢስቶችም በዝተዋል ብለዋል:: ከዚያ ባሻገር የኦርቶዶክስ ወገኖቻችንም ከዚህ በፊት ይከለከሉት የነበረውን ነጠላ በእነርሱ ሳቢያ ለብሰው በነፃነት መንቀሳቀስ እንደጀመሩ ነግረውናል::

አልሐምዱሊላህ ••• ፍትሕ የሁላችንም ነች!

NB:- በደሌ ላይ በቅርብ ለአመታት ሲከለከል የነበረውን ኒቃብ ታግለው አስከብረዋል::

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 16:06


በሮች ሁሉ የተዘጉ ቢመስል እንኳ መውጫ በርን ፈልግ ••• አንድ ይኖራል:: መንገዶች ሁሉ የጠፉ ቢመስልም መጓዣ መንገድን ፈልግ ••• በእርግጥ አንድ ይኖራል:: ከፍ ለማለት የምትጨብጠው ገመድ የጠፋ ቢመስል እንኳ ፈልግ ••• የእውነት አንድ አይጠፋም:: there is always a way habibi.

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 15:26


ለእኔም ሆነ ለሌሎች ወዳጆቻችሁ ቁርዓንም ሆነ ሌላ ስጦታ መስጠት ከፈለጋችሁ በተመጣጣኝ ዋጋ አለን ብለዋል::

ቻናላቸውን https://t.me/collection34 ተቀላቀሉ:: ስጦታም ተሰጣጡ::

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 14:11


ለፈጣን መልሳችሁ አመሠገንኩ ••• የነበሩት አለቁ:: በአላህ ፈቃድ በሌላ ዙር እንገናኝ ይሆናል::

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 12:18


አልገደሉትም አልሰቀሉትም - ዘመቻ 2!

እስልምናን ማጥናት ለሚፈልጉ የሌላ እምነት ተከታይ ተማሪዎች ቅን ልቦች በሰጡት ልገሳ እስካሁን የኡስታዝ ወሒድን "አልሰቀሉትም አልገደሉትም!" መፅሐፍ በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ ተማሪዎች ይደርስ ዘንድ 13 መፅሐፍትን ሰጥተናል:: አሁንም ጥቂት መፅሐፎች አሉና የሚያነቡ እስልምናን ማወቅ የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉ inbox ላይ @MOHAMMADAMMINM አሳውቁኝ::

ጭማሬ:- በመሠል ኸይር ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ኸይር ፈላጊ ወዳጆቼ ካላችሁም inbox ላይ አሳውቁኝ::

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 10:51


ጥምቀት ነው ••• ተማሪዎች ስትንቀሳቀሱ መታዎቂያ መያዝ አትርሱ ••• ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው Videoዎች በቅርብ ካሉ ወደ ሚስጢር ቦታ አዛውሯቸው ••• በዓሉ እስኪያልፍ ጥንቃቄ አይለያችሁ::

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 09:47


ሰለመች!

በአዲስ አበባ ት/ቤቶች በነበረው የኒቃብ ክልከላ "ኒቃብ ለምን ተከለከለ? ኒቃብ ምንድን ነው? እስልምናስ ምንድን ነው?" በሚል ተገፋፍታ እስልምናን ማጥናት የጀመረች ተማሪ የሆነች እህት ትላንት እስልምናን ተቀበለች::

እስልምናን ለማጥፋት ሲሞክሩ ለሌሎች የእስልምናን በር ይከፍታሉ ••• አልሐምዱሊላህ ••• አላህ ፅናቱን ይስጣት!

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 07:57


"ተንኮል እና ሸር ለጤናም ለሪዝቅም ጠንቅ ነው!"

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 07:41


"ዙልም የመከራ እናቱም አባቱም ነው።" - KH Abate

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 07:37


እናት አባቱን ጠርቶ "ልጃችሁን ልገድል ነውና ኑ እዩ!" በማለት ገደለው:: ይህ ተቀርፆ ያየነው ነው:: ያልተቀረፀስ ምን ያክል ይሆን? ይህ በአንድ ቦታ የተከሰተ የሚከሰት ሳይሆን በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ያለ ነው:: መተዛዘን ጠፍቷል:: ጭካኔ ነግሷል:: ጭካኔም እንደ ፅድቅ ተቆጥሮ በጀብደኝነት ይሰራጫል::

እና በዚህ ልክ ሆነን መሬት ብትውጠንስ ምን ይደንቃል? አላህስ እሳት ቢያዘንብበን ምን ይገርማል? አላህ መልካም ሰሪዎችን ያብዛ:: መጥፎዎቹን ይቅጣ::

ያሰላሙ:- ሰላምን ስጠን!

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 07:05


በሰቆጣ ከአንድ ግለሰብ የተገኙ የውሐ ቆጣሪ እና መክፈቻዎች ናቸው:: አሳዶ ይሰርቃል ይላል ዜናው::

••• ኑሮ ከፍቷል:: እና ደግሞ ካምፓስም ሻወሩ ሁላ መክፈቻ የሌለው መሰል መቅሰፍት አጋጥሞት ይሆን? በተለይ FBEዎች ....?

@MohammadamminKassaw

Mohammedamin Kassaw

18 Jan, 04:13


እለታዊ ማስታዎሻ - 336

"وَقَالُوا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَذْهَبَ عَنَّا الْحَزَنَ ۖ إِنَّ رَبَّنَا لَغَفُورٌ شَكُورٌ

ይላሉም «ምስጋና ለእዚያ ከእኛ ላይ ሐዘንን ላስወገደልን አላህ ይገባው፡፡ ጌታችን በጣም መሓሪ አመስጋኝ ነውና፡፡" [35:34]

@MohammadamminKassaw

1,189

subscribers

2,152

photos

197

videos