(አዲስ አበባ፣ ኅዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
በ2017 በጀት ዓመት አራት ወራት ከጥራጥሬና ቅባት እህሎች ከ156 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
13ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባኤ ከህዳር 10 ቀን እስከ ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተመላክቷል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከጥራጥሬና ቅባት እህሎች ካላት የምርት አቅም አንጻር ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እያገኘች ባይሆንም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው አራት ወራት የተገኘው የገቢ አፈጻጸም ካለፉት ጊዜያት መሻሻል አሳይቷል።
በ2017 በጀት ዓመት አራት ወራት ከቅባት እህል 66 ሚሊዮን ከጥራጥሬ ደግሞ 90 ሚሊዮን በድምሩ ከ156 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን አስታውቀዋል።
ሙሉ ዜናውን ለማንበብ ሊንኩን ይክፈቱ!
https://www.facebook.com/share/12Ahgz8x2bD/
----------------
ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦
ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/@AgricultureEthiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia