• ሰዎች በእኔ ላይ ምን እንደሚያስቡ ለማወቅ የታገልኩትን ያህል ራሴን ለማወቅ ብሰራ ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• በፍጹም የማይፈልጉኝን ሰዎች ስለማመጥና ስከታተል ያሳለፍኩትን ጊዜ ለእኔ ዋጋ ላላቸው ሰዎች ሰጥቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• በማያገባኝ የሰዎች ስራና ሃሳብ ላይ በማውራትና በመቃወም ያባከንኩትን ጊዜ የሚደገፍ ሰው ፍልጌ ደግፌ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• በየጊዜው ካለእቅድ የማወጣቸውን የገንዘብ መጠኖች በጥንቃቄ ብቆጥባቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• ምንም ያህል ብጨነቅ መለወጥ በማልችላቸው ነገሮች ላይ መጨነቄን ትቼ ለመለወጥ አቅም ያለኝ ነገሮች ላይ አተኩሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• የሚወዱኝ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ሲመክሩኝ የመስማትና ጥሩውን ምክር የመቀበል ልማድ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• ለመጀመር ያሰብኳቸውን እነዛን ወሳኝ ነገሮች ጀምሬያቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• የማይሆኑ የማሕበራዊ ጎጾች ሳስስ ያመሸሁባቸውን ምሽቶች የቀኑን ውሎየን ለመገምገምና ለነገ በማቀድ ባሳልፋቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
• ለየእለት ገጠመኞች ምላሽ እየሰጡ ከመሯሯጥ ይልቅ በራእይና በዓላማ ኖሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!
ያም ሆነ ይህ ያለፈው አልፏል! ከጥቂት አመታት በኋላ እንደገና “ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!” የሚል የግምገማ ስሜት እንደሚመለስብኝ ስለማውቅ አሁኑኑ ለውጥን አመጣለሁ።
@lifeandwisdom