((ምክረ ቅዱሳን)) @mikrekidusan Channel on Telegram

((ምክረ ቅዱሳን))

@mikrekidusan


ምክረ ቅዱሳን (Amharic)

ምክረ ቅዱሳን በአማርኛ እና በትክክለኛ ባህሊ ከታች መሳሪያ ሰዎችን ይሸምታል። የዚህ ቦታ ኃላፊነትን እና የምስጋናን የሚሻል ነው። ለምን አንድነት ኃላፊነት በጣም ተገምታለች? ምክረ ቅዱሳን ለአምልኮ አዋጅ እና ስለ ማስጠንቀቂያ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው፣ ስለ በሽታዎ ጥንቃቄ ብቻ አድርጎ በማወቅ ይመለሳል። በአስተማሪ ስራ ለሚሰማባቸው በጣም ፊልሞንል ማስጠንቀቂዎችን ለመጠበቅ እና ለመስተጠጋ የሚለዋወጥ ክፍል ነው። ለዚህም ግምት በታላቅ መልእክት ውስጥ ስለ መጀመር የሚለዋወጥ ነው።

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Nov, 09:35


818👉የፃድቅ ሰው ዕድሜ መርዘም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለሀጢአተኛው አለም ምሳሌ የሚሆን ትውልድ ማቆየት ሲሆን የክፉ ሰው ዕድሜ ማጠር ግን ከመዳን ይልቅ ለመጥፋት ምክንያት የሚፈልገውን አለም በክፉዎች ተበርዞ እንዳይጠፋ ለመታደግ ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Nov, 09:22


817👉የክፉ ሰው ዕድሜ መርዘም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የንስሐ ግዜ መስጠት ሲሆን እንደ ዲያብሎስ ዕቅድ ግን ለበለጠ ክፉ ስራ ማዘጋጀት ነው የመልካም ሰውም በጊዜ መወሰድ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከጥፋት አለም ማዳን እና ማሳረፍ ሲሆን እንደ ዲያብሎስ ዕቅድ ግን ለሀጢያተኛው አለም ምሳሌ የሚሆነውን ትውልድ ከምድረ ገፅ ማጥፋት ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

14 Nov, 12:02


816👉ያለ ንስሐ እና ያለመንፈሳዊ ሕይወት እየኖርን ትዳር ሲኦል ስራ ባርነት እና ሕይወት የቀን ጨለማ ሲሆንብን ለንረዳው የሚገባን ነገር ይሄ ሁሉ የተፈጠረው ጥሩ የትዳር አጋር ስላላገኘን ወይም ጥሩ ስራ ስላላገኘን እና ዕድል ፊቷን ስላዞረችብን ሳይሆን ለስኬታችን እና ለደስታችን ምክንያት የሆነውን እግዘብሔርን ወደ ሕይወታችን ስላላስገባነው እና በእሱም ምትክ በሀጢአታችን የሕይወት ፀር የሆነውን ዲያብሎስን ስላነገስን ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

14 Nov, 11:34


815👉እሳቱ እንዳይጠፋ ከፈለግን እሳቱን ሊያጠፉ ከሚችሉ ነገሮች እሳቱን እንደምንከላከል እና ለእሳቱ መንደድ ምክንያት የሆነውን የእንጨት መጠን እንደምንቆጣጠር ሁሉ ንስሐ ገብተን መንፈሳዊ ሕይወት ከጀመርን በኋላም ድጋሚ በሃጢአት ላለመውደቅ ወደ ሀጢያት ከሚገፋፉንና መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሊያጠፉ ከሚችሉ አለማዊ ነገሮች ራሳችንን ማራቅ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ዕድገት ምክንያት የሆኑትን ቅዱስ ቁርባን ፆም ፀሎት ስግደት እና ምፅዋት አጥብቀን ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም ቅዱሳት መፃሕፍትን እና የቅዱሳንን ሕይወት አዘውትረን ማንበብ መከታተል አለብን!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

14 Nov, 11:21


814👉ብዙውን ጊዜ ሀጢያት መስራት እንደሌለብን እያወቅን ሀጢያት የምንሰራው መጀመሪያ ንስሐ ስንገባ ጥልቅ በሆነ ስሜት የጀመርነው መንፈሳዊ ሕይወት በአለማዊ ነገሮች ተውጦ ሲቀዛቀዝ÷አያስኮኑንንም ብለን የምናስባቸውን ትንንሽ ሀጢአቶች መቃረም ስንጀምር በእነዚህም ምክንያት የፀፀት አጥር ከልባችን ተወግዶ ልባችን በሀጢአት የማዕበል ሀሳብ እና ምኞት ሲናወጥ እና እግዘብሔርን መፍራት ስናቆም ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

14 Nov, 11:07


813👉ምንም ነገር አንፍራ አዎ ደግሜ እናገራለሁ ምንም ነገር አንፍራ ግን አንድ ነገር ብቻ አጥብቀን እንፍራ ከሰውነት ዝቅ አድርጎ የሚያዋርደንን ከዚያም ባለፈ የዲያብሎስ መጫወቻ እና ባሪያ የሚያደርገንን የመጨረሻ ደግሞ እስትንፋሳችን ከሆነው አምላካችን እግዘአብሔር የሚለየንን ሀጢያት አጥብቀን እንፍራ!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

14 Nov, 10:53


812👉ሀጢአት ከመስራታችን በፊት ምን ጊዜም ቀድመን ማሰብ ያለብን በሀጢአቱ የሚገኘውን ደስት እና እርካታ ሳይሆን ሀጢአቱን ከፈፀምን በሗላ የሚጠብቀንን ውድቀት እና ከዱላ ያልተናነሰ የማያባራውን ፀፀት ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

14 Nov, 10:48


811👉ሀጢአት ከሰራን በኋላ ሊሰማን የሚገባው ስሜት ልክ አዳም ዕፀ በለስ ከበላ በሗላ ዕፀ በለሱን በመብላቱ ምክንያት እግዘብሔርን የሚያህል ጌታ እና ገነትን የሚያህል ቦታ በማጣቱ የተሰማው የብቸኝነት እና የባርነት እንዲሁም የመረረ ፀፀት አይነት ስሜት ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

24 Oct, 11:05


810👉በተደጋጋሚ በሀጢአት ለመውደቃችን ዋና ዋና ምክንያቶች በመጀመሪያው እና በእያንዳንዱ የሀጢአት ግብራችን ወደ ሕይወታችን የሚገቡ የዲያብሎስ እና የእርኩሳን መናፍስት ግፊት እና ጫና÷ለአመታት ያጣጣምናቸው የሀጢአቶቻችን ትዝታዎች እና ዳግም ወደ ሀጢአት ላለመመለስ የማያዳግም የልብ ቆራጥነት እና የስነ ልቦና ዝግጅት ዕጥረቶች ናቸው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

24 Oct, 10:28


809👉ከሰውም ሆነ ከሰይጣን ቢገጥመን ፈተና የምንፈተነው ሁሉ ለበጎ ነውና አንድም መልካም ነገር ቢጠብቀን ነውና መፈተኑን አንጥላው በትዕግስት እንፅና በለሷን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላልና!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

24 Oct, 07:41


808👉አለማዊ ቅናት ከራስ ወዳድነት÷ራስን ዝቅ ካለማድረግ እና ለራስ ከፍተኛ ግምት እና ቦታ ከመስጠት የሚመጣ የሕይወት እና የፍቅር ተቃራኒ በሽታ ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

24 Oct, 07:19


807👉በአለማዊ ነገሮች ላይ እልከኛ መሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያልተረዳ እና የአጋንንትን ውጊያ ያላወቀ ቢያውቅም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር እና አጋንንትን ለመቃወም ራሱን ያላዘጋጀ ሰው ምልክት ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

24 Oct, 07:02


806👉አለም ላይ ያለው ውጊያ ከምናስበው በላይ እልህ አስጨራሽ ፊልሚያ ነው ውጊያውም በዓይን ከማይታዩ እና በጦርነት ውጊያም የረጅም ጊዜ ልምድ ካካበቱት ጦረኞች ጋር ነው ይሄን ውጊያ ያሸነፈ ብርቱ ተዋጊ መጨረሻ በሌለው የዘላለም ሕይወት ደስታውን ሲያጣጥም ውጊያውን የተሸነፈ ምስኪኑ ጦረኛ ግን ፍፃሜ የሌለው እና መፈጠሩን የሚያስመርር ስቃይ ይጠብቀዋል!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

24 Oct, 05:15


805👉የትናንት ያለፈ የደስታ እና የሀዘን ሕይወት የዛሬን የደስታ እና የሀዘን ሕይወት ለማለፉ ሕያው ምስክር ነው የማይነጋ ሌሊት እና የማያልፍ ቀን የለም ከታገሱት ሁሉም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋል!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

24 Oct, 05:06


804👉ሰዎች ስህተታችንን አውቀው በእኛ ላይ ከመፍረዳቸው እና እኛን ለማስተካከል ጥረት ከማድረጋቸው በፊት አስቀድመን ራሳችንን ፈትሽን በራሳችን ላይ እንፍረድ ያኔ የራሳችን አራሚዎች እና መሪዎች እኛው እራሳችን ከመሆን ባለፈ በራስ የመተማመን መንፈሳችንም ይጨምራል!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 19:29


803👉ትልቁ ችግራችን ስህተታችንን አለማወቃችን እና ከስህተታችን አለመማራችን ነው ከዚህም የሚከፋው እና እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ እየተጎዳን እና የማንወጣበት አዘቅት ውስጥ እየገባን እንደሆነ እያወቅን በስህተታችን መቀጠላችን ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 17:14


802👉አብዛኛውን ጊዜ ከውሳኔ በሗላ ፀፀት የሚመጣው ውሳኔያችን እውነታው ላይ ሳይሆን ፍላጎታችን እና ስሜታችን ላይ ብቻ  ስለተመሠረተ ነው ምክንያቱም ፍላጎት እና ስሜት ሁሌም ትክክል ስለማይሆኑ እና አንዳንድ ጊዜም የዲያብሎስ ዕቅዶች መሸሸጊያ ስለሚሆኑ ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 16:37


801👉አለም ላይ ስንኖር አንድን ነገር አጥብቀን ስንፈልግ አናገኘውም በፈለግነው ልክ እንደሰማይ ይርቀናል ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገን ትተን በእግዚአብሔር ፈቃድ መኖር ስንጀምር ግን ያ የተውነው ነገር በሕይወት ዘመናችን ሲፈልገን እና ሲያሳድደን መኖር ይጀምራል ምክንያቱም የአለም ትልቁ አላማዋ ሁሉን የያዘውን ክርስቶስን ማስጣል ነውና!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 12:41


800👉በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ ሆነን ድንገት በሀጢአት መውደቅ ያለ እና የተለመደ ነው÷በተደጋጋሚ በሀጢአት እየወደቁ መነሳት ፈተና ነው÷ ከሀጢአት መውጣት አለመቻል ግን ውድቀት ሲሆን ጭራሽ ተስፋ መቁረጥ እና ከመንፈሳዊ ሕይወት መውጣት ደግሞ ፈፅሞ መጥፋት እና ገሀነም መግባት ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 12:29


799👉ሰይጣን እኛ ውስጥ መኖሩን እና አለመኖሩን ማወቅ ከፈለግን ሀጢአትን ለመተው መቸገራችንን እና ከሀጢአት በቀር በእያንዳንዷ የሕይወት እንቅስቃሴያችን የምንፈልገውን እና የምንመኘውን መልካም ነገር ሁሉ ማድረግ እና ማግኘት አለመቻላችንን ማየት ብቻ በቂ ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 12:07


798👉የውድቀታችን ትልቁ መጀመሪያ እና መሠረት ስንፍና እና ቸልተኝነት ነው የስኬታችንም ትልቁ ምክንያት ፀሎት እና ትጋት ነው ፀሐይ ካለ ብርሃን እሳትም ካለ ሙቀት እንደሚከተል ሁሉ ስንፍና ካለ ውድቀት ፀሎት እና ትጋት ካለ ደግሞ ስኬት እና ድል መከተላቸው የማይቀር ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 11:10


797👉ዲያብሎስ ምን ጊዜም ትህትናችንን ለማጥፋት ትዕቢተኛ÷ትዕግስታችንን ለመፈታተን ደግሞ ተናዳጅ እና ግልፍተኛ ሰው ሲልክብን መልካምነታችንን ለማበላሸት ደግሞ ክፉ እና ምቀኛ ሰው ይልክብናል!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Oct, 10:52


796👉ብዙዎቻችን የማናስተውላቸው ነገር ግን ዲያብሎስ ከፆም ከፀሎት እና ከስግደት በላይ አጥብቆ የሚፈራቸው ሶስቱ የጦር መሳሪያዎች ትህትና÷ትዕግስት÷መልካምነት ናቸው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

22 Sep, 16:41


795👉መልካም ሥራን አድርጎ ከሰው ክብርን የሚጠብቅ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ያለደመወዝ እንደሚያገለግል ሰራተኛ ነው!!!

አባ ሚካኤል ኤል ባሕሬ

((ምክረ ቅዱሳን))

31 Aug, 17:17


794👉የሥጋ ቤቱ በር እስካልተዘጋ ድረስ ውሾች ከሥጋ ቤቱ በር ዞር እንደማይሉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆን የራሳችንን ምኞት እና ፍላጎት መከተል እስካላቆምን ድረስ አጋንንትም እኛን ከመፈተን ወደ ሗላ አይሉም!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

31 Aug, 15:11


793👉በምድር ላይ ሳለን እያንዳንዷ የሕይወት እንቅስቃሴያችን በዲያብሎስ እና በሰራዊቱ ከበባ እና ክትትል ውስጥ ናት ስለዚህ የሚታየውን አለም ከማየት አቁመን የማይታዩትን ጠላቶቻችንን እንመልከት ያን ጊዜ ለማይታዩ ጠላቶቻችን እጅግ አስፈሪ ተዋጊዎች መሆን እንጀምራለን!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

31 Aug, 15:04


792👉ሰው ነቃ አወቀ እና ተመራመረ የሚባለው በአለም ላይ የሚታዩ ችግሮችን ተመራምሮ ሲደርስባቸው እና መፍትሔ ሲያገኝላቸው ብቻ ሳይሆን ለችግሮች ሁሉ መፈጠር ምክንያት የሆኑትን የአጋንንትን ሰራዊት ከእነሴራቸው እና ተንኮላቸው ተመራምሮ ሲደርስባቸው እና ጠንክሮ እጅ ሳይሰጥ እስከመጨረሻው ብርቱ በሆነ ፆም ፀሎት እና ስግደት ሲፋለማቸው እና ድል ሲነሳቸው ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

31 Aug, 14:44


791👉ለፆም ለፀሎት እና ለስግደት ድንገት ሰንፈን እና በሀጢአት አለም ውስጥ ተዘፍቀን እራሳችንን ብናገኝ ሊሰማን የሚገባን ስሜት እረፍት እያደረግን እና እየተደሰትን ሳይሆን በባዶ እግራችን ሚስማር እና ፍም ላይ እየተራመድን እና ቁልቁል ገሀነም እየወረድን ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

31 Aug, 14:24


790👉 አንዳንድ ጊዜ እርኩሳን መናፍስት ሰውን ወክለው በሰው አንደበት ሰውን የሚያነጋግሩበት ጊዜ አለና ከሰው ድንገት የማንጠብቀው ቃል ወይም ተግባር ስንሰማ እና ስንመለከት በሰው ላይ ከመፍረድ ይልቅ ሰው ላይ ሆነው የሚዋጉንን አጋንንት በትዕግሥት ሲብስም በፀሎት ልንዋጋቸው ይገባል!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

29 Aug, 13:17


789👉እየኖርንበት ያለው አለም የውሸት እና  የህልም አለም መሆኑን ለማረጋገጥ ትናንት አብሮን ሲስቅ እና ሲጫወት የነበረን ዛሬ ግን በሞት የተለየንን ሰው ማሰብ በቂ ነው!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

30 May, 11:30


788👉<<በራሱ ቤት ሰው የሞተበት የጎረቤቱን ልቅሶ እንደማያስብ እና እንደማይመለከት ሁሉ እያንዳንዱም ሰው የየራሱን በደል እና ሀጢአት ቢያስብ ኖሮ የሌላውን በደል ባላሰበ እና ባልተመለከተ ነበር!!!

ቅዱስ ሙሴ ፀሊም


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Mar, 08:36


787👉<<ሰዎች ውስጣቸው የዲያብሎስ መንፈስ ካደፈጠ የገዛ ሕይወታቸው ስልችት ይላቸዋል÷አጋንንቱ ውስጣቸው ሆኖ ትዳራቸውን ሲዖል÷የሚሰሩት መደበኛ ሥራቸውን ደግሞ ባርነት መስሎ እንዲታያቸው ያደርጋቸዋል÷እያንዳንዷንም ቀን የውዴታ ሳይሆን የግዴታ ሕይወት አድርጎ እያሳያቸው የሚይዙት እና የሚጨብጡት÷የሚናገሩት እና የሚያቅዱት ሁሉ አልታይ እንዲላቸው ያደርጋል ÷እያንዳንዷንም ቀን እላያቸው ላይ አዚም ሆኖ ያለ ሥራ እና ተግባር እጃቸውን እና እግራቸውን አሳስሮ ያስቀምጣቸዋል÷ መኖሪያ ቤታቸው መቃብር ቤት መስሪያ ቦታቸው ደግሞ እስር ቤት መስሎ ይታያቸዋል÷ሌላው ቢቀር ከሰው ሁሉ ጋር መገናኘት አስጠልቶአቸው በራቸውን ዘግተው ለብቻቸው እያለቀሱ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል!!!>>

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Mar, 08:19


786👉<<ሰዎች ውስጣቸው የዲያብሎስ መንፈስ ካደፈጠ አጋንንቱ ሁል ጊዜ ሰዎቹን በሚገጥማቸው ነገር ሁሉ እያነጫነጨ እና እያጨቃጨቀ ከማንም ሰው ጋር ተስማምተው መኖር እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል÷ሁሌም እነሱ ትክክል እና እውነተኞች እንደሆኑ አድርጎ ያሳያቸዋል÷ሁሌም እራሳቸው ላይ ሳይሆን ሰዎች ላይ ብቻ እንዲያነጣጥሩ÷የራሳቸውን ሳይሆን የሰውን ስህተት ብቻ እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል÷ ዓይተው እንዳላዩ ሰምተውም እንዳልሰሙ ማለፍ የሚገባቸውን ትንሿን ስህተትም አግዝፈው እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል÷በዚህም መውጫው እስኪጠፋባቸው እና ምን እንደሚያደርጉ ግራ እስኪገባቸው ድረስ ወደ ለየለት ፀብ እና ክርክር ይመራቸዋል÷በዚህም አጋንንቱ ከሚያገኙት ሰው ሁሉ ጋር እያባላ እና እያጨቃጨቀ ሰው በሚኖርበት አለም ውስጥ እየኖሩ ሰው አልባ አድርጎ ያስቀራቸዋል!!!>>

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Mar, 07:41


785👉<<ሰዎች ውስጣቸው የዲያብሎስ መንፈስ ካደፈጠ ሰዎቹ ራሳቸውን እንዲያጠፉ ለማድረግ መንፈሱ ምንጊዜም በህሊናቸው እያንሾካሾከ ሀሳቡን ከሀሳባቸው ጋር አዋህዶ የራሳቸው በሚመስል ሀሳብ ራሳቸውን ቢያጠፉ ለጭንቀታቸው ሁሉ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚችሉ እየወተወተ እረፍት በመንሳት ያስጨንቃቸዋል÷ሰዎቹ በሕይወት መኖራቸው ሙሉ ለሙሉ ጥቅም እንደሌለው እና ከጭንቀታቸው ሊያወጣቸው የሚችል ብቸኛው አማራጭ ራስን ማጥፋት እንደሆነ ደጋግሞ ይነግራቸዋል÷በሕይወት ዘመናቸው የገጠማቸውን እና የሚገጥማቸውን ችግር ሁሉ ከፊታቸው እየደቀነ ይሄን ራስን የማጥፋት ሀሳብ ከመቀበል ውጪ ሌላ ምንም አይነት አማራጭ እንደሌላቸው አድርጎ ያሳያቸዋል÷አንዳንዴም እራስን ማጥፋት የጀግኖች እና የቆራጥ ሰዎች ውሳኔ እንደሆነ እና እራሳቸውን በማጥፋታቸው የጎዱአቸውን ሰዎች እንደሚበቀሏቸው አድርጎም ያወጋቸዋል÷ከሞት በሗላ ግን አይደለም ሊናገሩት ሊያስቡት የማይቻለውን እና መፈጠርን የሚያስመርር ስቃይ እንዳለ ትዝ እንዳይላቸው ቢላቸው እንኳን ትኩረት እንዳይሰጡት ያደርጋቸዋል!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

((ምክረ ቅዱሳን))

23 Mar, 07:09


784👉<<ሰዎች ውስጣቸው የዲያብሎስ መንፈስ ካደፈጠ አጋንንቱ ሰዎቹ በመንፈሳዊ ተጋድሎአቸው ይበልጥ እየበረቱበት እና እየጠነከሩበት ካስቸገሩት ተስፋ ለማስቆረጥ እና ወደ እግዚአብሔር እየገሰገሱ ያለውን ጉዞ ለመግታት ከፊት ለፊታቸው የፈተና መዓት ይደረድርባቸዋል÷የሀሳብ ውጊያውን ሲያሸንፉ÷በማጣት እና በመቸገር÷ማጣት እና መቸገራቸውን ሲቋቋሙ÷በህመም የህመሙን ውጊያ ሲያልፉ ደግሞ ከሰው ጋር በማጣላት እያለ ሰዎቹ ምርር ብሏቸው ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው እስኪወጡ ድረስ ይፈታተናቸዋል÷አንዳንዴም እየሄዱበት ያለው መንገድ እና እየኖሩት ያለው ሕይወት ልክ እንዳልሆነ እያሳሰበ ያጠራጥራቸዋል÷ ከሰይጣን ጋርም የማያዋጣቸውን ትግል እና ውጊያ እንደጀመሩም ያሳስባቸዋል÷ በእግዚአብሔር መንገድ መጓዝም በጣም አስቸጋሪ እና ሊዘልቁት የማይቻል አድርገው እንዲያስቡ ለማድረግም ይሞክራል!!!>>

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mikrekidusan

1,958

subscribers

360

photos

0

videos