በወሊድ ወቅት ለእናት ሞት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች ውስጥ በወሊድ ወቅት የደም መፍሰስ ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳል።
በተለይም ባላደጉ አገራት እናቶች በብዛት በጤና ተቋም ውስጥ ስለማይወልዱ በደም መፍሰስ ምክንያት የብዙ እናቶች ህይወት ይቀጠፋል።
በ ወሊድ ወቅት መጠነኛ የደም መፍሰስ የሚጠበቅ ሲሆን ከፍተኛ ደም መፍሰስ ስንል በማህፀን ወይም በኦፐሬሽን ለወለደች እናት ህይወቷን አደጋ ላይ የሚጥል አይነት (hemodynamically unstable) የሚያደርግ አይነት የደም መፍሰስ ነዉ።
📌 አጋላጭ ሁኔታዎች
• ካለ ጤና ባለሙያ እርዳታ ቤት ውስጥ መውለድ
• የምጥ መርዘም
• የእንግዴ ልጅ ሙሉ በሙሉ አለመውጣት፣ ተቆርጦ ማህፀን ውስጥ መቅረት
• የመንታ እርግዝና
• በእርግዝና ወቅት መድማት (APH)
• የፅንሱ ክብደት ከመጠን በላይ መጨመር
• የእንሽርት ውሃ መብዛት
• በምጥ መርፌ መውለድ
• በመሳሪያ ታግዞ መውለድ
📌ህክምናው
• ደም መውሰድ ፦ ከሰውነትሽ የወጣው ደም ለመተካት ደም አስፈላጊ ስለሆነ ከለጋሾች የተገኘ ደም እንዲሰጥሽ ይደረጋል።
• የተለያዪ ደም ማቆሚያ መድሃኒቶችን በየደረጃው እንዳስፈላጊነቱ ይሰጡሻል።
• የኦፕራሲዮን አገልግሎት ፦ በህክምና እርዳታ ደሙ ካልቆመ ህይወትሽ ለማትረፍ ኦፕራሲዮን ሊደረግልሽ ይችላል። ይህም ከቀላል የደም ማቆሚያ መቋጠር (B-lynch suture) እስከ ማህፀን ማውጣት (hysterectomy) የሚደርስ ሊሆን ይችላል።
📌እንዴት መከላከል ይቻላል?
• ጤና ተቋም መውለድ
• የተነገሩሽ ከፍተኛ ችግሮች ካሉ ከፍተኛ ጤና ተቋማት በመሄድ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ማማከር
ደም በመለገስ የብዙ እናቶችን ህይወት መታደግ እንችላለን!!!
***
ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE