HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ @hailegebriel2021 Channel on Telegram

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

@hailegebriel2021


❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ (Amharic)

ሃይሌ ገብርኤል - በማለዳ ንቁnnየአስተባብዖት ትኩሳት አባቶች እንዲህ በዚህ አገልግሎት ይታወሳሉ፡ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም የሆነ**፡ እግዚአብሔር በመስጠት አንዳንድን የተለያዩ አባቶችን በመስጠት ስለሆነልን 👏 እና ከእኛ በሚለው ማንጫወት ለሹመቼ የተለያዩ አባቶችን እንቀበላለንnnበቴሌግራም እናት ስም "hailegebriel2021" የይነጋገረ ገጽ ለአጠቃላይ ገጽ ማንነት እና የዝናሽ ተዋብያ የኤርትራን ለውጥ እንቀረዋለንnnበገፅ ከፍተኛ እና ምስጋና ተዋብያን ጥረት ማድረግ እና ሰላምን እርዳን እንለዋለንnnበመካከል የእርምጃ ማህበረሰብዎን እና የመንፈሳዊ ድርጅቶችዎን ፀረ-ልዩወት የተወያዩ መረጃዎች በማሸነፍ ካልቻለው የቁሳቁሶ ጸጋ እና መሀከል መለዋወጫዎች ለምሳለችnnይህ ገጽ በቴሌግራም የሚኖረውን የተለያዩ አባቶች ብዛት እና በእንስትና ምን ያለውን መረጃን እና ከክፋት ለመብላት ከፍተኛ ጥቅም ማንነት እና ማስሻሻላት ይችላሉnnበማህበራት እና የፅዮን ብሔር መተግበሪያ ቋንቋ በአማርኛ ከፍተኛ ዘመን እየተወያዩ ነውnnእናት ምስጋና ተለዋወጣል ስለሆነል ❤️

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

20 Nov, 18:08


በዓለ ሢመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ህዳር 12 "ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል› ሲል ቅዱስ ኤጲፋንዮስ እንዳመሰገነው፤

ቅዱስ ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመ ሊቀ መላእክት እንደመሆኑ በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ)

ኃይላት የተባሉት መላእክትም ሰዎች በዓለም ፈተና ውስጥ ሆነው ሰይጣን ሊያደክማቸው ሲፈልግ ኃይልን ብርታትን የሚሰጡ፣ ይህን ዓለም ንቀው በበርሃ ወድቀው ከሥጋ ምኞት ጋር የሚጋደሉትን፣ በከተማም እየኖሩ መንፈሳዊ ትሩፋት የሚያደርጉትን ደግሞ የሚያበረቱ ናቸው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ‹እርሱም ወደ ሰማይ ያረገ እግዚአብሔርም ተቀምጦ ያለ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም የተገዙለት ነው…› ሲል ‹ኃይላት› በማለት ያነሣቸው በኢዮር አራተኛይቷ ከተማ የሚኖሩትን ነው፡፡ በእነዚህ ላይ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን አለቃቸው አድርጎ ሾሞታል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፳፪)

የቅዱስ ሚካኤል ሢመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻም ግን አይደለም፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ ‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!›› ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ የስሙን ፊደላት በመተንተን እንዲህ ተርጉመውታል፤ ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ ‹‹መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ ማን ነው!›› (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)

የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ይህ ኃያል መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባሉትን እስራኤል ዘሥጋን ሲረዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡

ለምሳሌ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት ‹‹… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ፤ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?” አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫)

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ‹‹ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ ፥እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ›› እንዲል፤ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ይለምንላቸው ነበር፡፡ (ዘፀአት.፳፫፥፳)

ነገር ግን ኃጢአት ሲሠሩ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ይቀጣልና ሕዝቡን ‹‹ራስህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እንቢም አትበለው፤ ስሜ በእርሱ ስለሆነ ይቅር አይልምና›› ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፤ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ (ዘፀ.፳፫፥፳፩)

ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር ‹‹በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም›› ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ (ዳን.፲፥፳፩)

የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በሐዲስ ኪዳንም እንደነበር ይህ ነቢይ በትንቢቱ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ተናግሮለታል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ (ዳን.፲፪፥፩)

በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪)

ስለሆነም በኃጢአት ባርነት ተይዘን በችግር እና በመከራ ውስጥ ተዘፍቀን ለምንኖር ሰዎች ስለ ሕዝበ እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት የቆመው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ለእኛም ያማልደንና ተራዳኢ ይሆነን ዘንድ በጸሎት እንማጸነው።

አምላካችን እግዚአብሔርም የምሕረት ፊቱን ወደ እኛ በመመለስ በጸብና በጦርነት ምትክ ፍቅርን፣ ሰላምንና መግባባትን፤ በመለያየት ምትክ አንድነትን እንዲሰጠን በቅዱስ ሚካኤል ስም እንለምን።

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡፡

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

20 Nov, 18:03


መጽሐፍ ቅዱስን ያወቁ የአጋንንት ውጊያ ያልተረዱ መምህራን! | አባቶችን መረዳት ያቃተን ለምንድነው? | 3ቱ የእኛ ጠላቶቻችን ቀሲስ ሄኖክ ተስፋዬ አበራ 😱💥🔥

https://youtu.be/i2xyaNXF1t8

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

19 Nov, 19:19


እውነት ለአባ ዮሐንስ ፎቶ ይሰግዳሉ? || መናፍስት በስልክ ብሸኙ ምን ችግር አለው? | ከባዕድ አምልኮ የወጡ ቤተሰቦች ምስክርነት | ወንቅ እሸት ገዳም 😭😱🔥

https://youtu.be/T1ISMoRAAgM

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

19 Nov, 13:21


የሚያዞሩ የሚያንከራትቱ ክፉ መናፍስቶች!! || የመናፍስት ማታለያ መንገዶችና ሴራ! || አጋንንት ለምን ቶሎ አይወጡም?? | አባ ዮሐንስ | መምህር ግርማ 😱😭 https://youtu.be/9Zk2oZYXyoU

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

18 Nov, 08:50


«ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ ሁሉ መልካም ነው። ሰሞኑን ከአባታችን ከአባ ዮሐንስ ተስፋማሪያም ጋር በተገናኘ የተለያዩ ምስሎችና ድምጾች ሸር ሲደረጉ አያለሁና ይሄ ጉዳይ ተደጋጋሚ እየሆነ ነው። በተለይም ደግሞ አገልጋዮች ነን የሚሉ እንኳን ሳይቀር የማይሆኑ ቃላትን ሲናገሩ አዳመጥኩ በጣምም አዘንኩ። ሌላው ደግሞ አባታችን በማያውቁት መንገድ በወንቅሸት ገዳም ስም ማህበራት ተደራጅተው የማይሆኑና የማይረቡ ሥራዎችን እየሰሩ ሆነ ብለው የቦታውን መልክና በረከት ለማስነወር የሚያራግቡት ድምጾች በጣም ያሳፍራል። የሚገርመው ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ በወንቅሸት ገዳም ስም ተደራጅተው ብዙ የበረከት ሥራዎችን የሚሰሩ ድንቅ ቤተሰቦች እንዳሉ እኛው ምስክሮች ነን። ነገር ግን ብዙ ሰው መረጃ ሳይኖረው በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ በሚሰራጭ ድምጽና ምስል ወደ ማያስፈልግ ነገር ይገባሉና ብንጠነቀቅ እላለሁ። የፈለገ ጥፋት እንኳን ቢኖራቸው በዚህ ደረጃ አባቶችን መናገርና መተቸት በጣም ያሳዝናል። እኔ በግሌ አባታችንን በአካል አግኝቼ አላውቅም ነገር ግን ትምህርታቸውን ሳዳምጥ አንድም ስህተት አግኝቼ አላውቅም። ብዙ ሰው ባልገባው ነገር ያወራል። አሁን ዋናው አላማዬ ወደዛ ቦታ ሄዳችሁ የበረከቱ ተካፋይ የሆናችሁ ቤተሰቦች እስቲ የግል ተሞክሯችሁንና ገጠመኞቻችሁን በድምጽ ወይም በቪዲዮ በውስጥ በኩል እባካችሁ ላኩልኝ። በዚሁ አጋጣሚ ማንኛውም አይነት ተሞክሮ ካላችሁ በድምጽ ወይም በቪዲዮ በዚህ በኩል ላኩልኝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ።» => https://t.me/haile_gebriel_tube_bot

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

17 Nov, 15:04


በድብቁ የአስማት ግብዣ ላይ መገኘት በፓንት የተደገመ የመስፋቅር መንፈስ የመናፍስቱ መንደር ድብቅ ሴራዎች || ደብተራና መንቋዮች #ethiopia 😱🔥

https://youtu.be/5u3pgtKHEsM

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

16 Nov, 13:17


የመምህር ግርማ ገጠመኝና ፈተና ክፍል 2 || መምህር ግርማ ጋር የሄዳችሁ ንስሐ ግቡ! | የቆንጅዬዋ ልጅ የሕይወት ፈተና | ከእናትየዋ ይልቅ የልጅቷ ባሰ 😭😱

https://youtu.be/tRo9oi4GaeA

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

15 Nov, 18:31


እግዚኦ! ይኼንን ጉድ በእውነት ተመልከቱ!! | መምህር ግርማ በግዕዝ ሰብከው አያውቁም!! | ሩካቤና የጸሎት ሕይወት | መዓት የወረደብን ለዚህ ይሆን!! 😱💥😭

https://youtu.be/B0f2OCvR70o

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

14 Nov, 13:33


The Nature of Diabolic Wars: Spiritual Battles Explained #EstifanosTube #devils #saint #ethiopia https://youtu.be/8htAgVxuQjY

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

14 Nov, 11:08


ባሏን በመተት ከቤቷ ያባረረች ምስት ጉድ!! || የእህቷን ቤት በመንፈስ አደንዝዛ የዘረፈች እህት! || የብዙ ትዳሮች መፍረስ ምክንያት #ethiopia 😱😭😱 https://youtu.be/4_swP6GXyN8

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

13 Nov, 13:04


«የቤተ-እግዚአብሔር አንዳንድ አገልጋዮች ወጣ ያሉ ጠባዮች»

=> ቅድስናን የሚፈልጉ ቢሆንም፤ ውጊያው ግን ያስፈራቸዋል፤

=> ቅድስና እንቢ ብሎት ተስፋ የቆረጠና፤ ሌላውን ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ፤ የእግዚአብሔር መንግስት ከባድ ነው! እያሉ ሰውን የሚያስጨንቅና የወግ መዓት የሚያመጡና የሚያስፈራሩ ፤

=> በቤተ እግዚአብሔር ሆኖ ዲያብሎስን የሚያገለግል፣ ምዕመናንን በመተት የሚያስር፣ የሐሜትና የተንኮል መንገድን የሚያስተምር፣ የአፍዝ አደንግዝ መኖሪያና የምትሐት አስተማሪ፣ የሐሰት መንፈስ መግለጫው ሆኖ የሚኖር፤

=> በትርፍ አምልኮትና በጥቅም ላይ ብቻ አተኩሮ የሚኖር፣ የምዕመናን ለቅሶአቸው፣ ሐዘናቸውና ችግራቸው የማይሰማው፤ ለደሞዙና ለትርፍ ብቻ የሚኖር፤ በነጣቂ ተኩላ ተበሉ አልተበሉ፣ በአጋንንት መንፈስ ተያዙ፤ አልተያዙ ደንታ የሌለው፣ ዓላማና ግቡን የማያውቅ፣ የጥቅም ባለቤት፣ አምልኮት በሌለው አገልግሎቱ የሚመፃደቅ፣ የሚኮራና የሚታበይ፣ ለፍቅረ-ንዋይና ለሥልጣን ብቻ የሚያገለግል፤

=> ጠላት ይቀድማል ብሎ የማያስብ ቸልተኛ አገልጋይ፣ የዲያብሎስን ሩጫ ያልተረዳ፣ የዛሬው የጥጋብ ጊዜ ለነገም ይሆናል! ብሎ የሚያምን፣ ለዕለት ደስታ ብቻ የሚኖር፣ ስለዲያብሎስ አሠራር ለማወቅም ሆነ ለመስማት የማይፈልግ፣ ዘመናዊነት ተጠናውቶት እያገለገለ፤ የሚያገለግለውን አምላክ የሚጠራጠር፣ መንፈሳዊነቱ የቀዘቀዘና በይበልጥ በዓለማዊነት ላይ የሚያተኩር፤

=> መኖሪያው ቤተ እግዚአብሔር ሆኖ ሥራው መቶ በመቶ ዓለማዊ የሆነ፤ እሁድ ጧት ቤተ-እግዚአብሔር፣ ከሰዓት በኋላ ጠንቋይ ቤት፣ እሁድ ማታ ደግሞ፤ የምሽት ክበብ ውስጥ የሚገኝ፤ የዓለም ፍቅር የተጫነው፣ ከመንፈሳዊው መንገድ የራቀ ፍልስፍናን የሚሰብክ፣ የሥጋን ደስታ ሕይወቱ ያደረገ፣ የመቀደስን ቅድስና የማይወድ፣ የቤተ-እግዚአብሔር ጉብል ጥቂት አለመሆን፤

=> ለሥልጣንና ለማዕረግ ዕድገት የሚሯሯጥ፣ የአቋራጭ የሥልጣን ከፍታን የሚያሳድድ፣ በሐሰት ወሬ በማቀበል ቅራኔ የሚዘራና ዕድገት እንደሚገኝ የሚያምን፣ በወንጀል ክስ የሚተዳደር፣ የወሬ ታማኝ ለመሆንና ጉቦ ለማቀበል እራሱን ለዚህ እርግማን ያዘጋጀ፣ ለቤተ እግዚአብሔርና ለምዕመናን የጽድቅ ቡራኬ መሆን ያቃተው፤

=> ጽድቅንና የኢኮኖሚ ድጎማን ከመናፍቃን እየቀላወጡ፤ በቤተ እግዚአብሔር ሰዎች ሁለት ልብና ሁለት ኑሮ፣ ሁለት እምነት ያላቸው ለእምነት መጠናከር አርዓያ የሚያደርጉና ሃይማኖቱ የተሞታታባቸው፣ መነሻና መድረሻቸውን ያልለዩ፤ ድክመትን የሚፈላልጉና መናፍቅነትን የሚያራግቡ፤ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

=> ለአምልኮት ጸሎት ለሥራና ዕለት ለሚጠይቀው ፈጣን ክንውን ደንታ የሌለው፣ የጊዜው ፍጥነት የማይሰማው፣ በቢሮ አሠራር ቀጠሮን በማስረዘም ውሳኔን የሚጎትት፣ መማለጃ የለመደ ዓይኖቹና እጆቹ ያሉት፣ መንፈሳዊ ጥሪውንና የያዘውን እምነት፣ ኃላፊነት፣ ቦታና የእግዚአብሔርን ክብር የሚያሰድብ፣ ለቤተ እግዚአብሔር ታሪክና ለመንፈሳዊ አርዓያነት ቦታ የሌለው አገልጋይ ሁሉ፤ በተደጋጋሚ እንደተገለጸው፤ ራእይ አልባ የሆነው የልማዳዊው አገልግሎት ውጤት ነው፡፡ በመሆኑም ደንታቢስ አገልጋዮች በሚበዙበትና በበዙበት ዘመን፤ መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያቀጭጨው፤ የክፋት አባት ዲያብሎስ ይደሰታል፡፡

=> በአጠቃላይ፤ እነዚህ ድክመቶች ባሉበት ወደ ሕዝብ ልንሄድ ቀርቶ፤ ራሳችንም ከዚህ ልማዳዊ አገልግሎት ወጥተን፤ ወደ ቅድስናው አምልኮት የምንደርስበት ኃይልና ጉልበት አጥተናል፡፡ ቤተክርስቲያን ከአምላካችን የተቀበለችው አደራ ግን ‹‹ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፡- ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኃቸው፣ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡›› ማቴ 28÷18-20 የሚል ነው፡፡

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

13 Nov, 11:21


4ቱ የአምልኮት ስግደት ምስጥራዊ በረከቶች! | ሰይጣን ከበረከትና ከአምልኮት አዘገየን | ሰይጣን በአሳባችንና በግብራችን ይናገራል! መምህር ግርማ ወንድሙ 🔥😱 https://youtu.be/WcZIcDHl4H4

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

13 Nov, 10:02


በተለያዩ አገራት ወደ ገጠሩ መላክ ጀምረናል
ገጠመኝ በፍላሽ እና ሚሞሪ
መንፈሳዊ ትምህርት
ማዳመጫ ጂፓስ
መቁጠሪያ
የፀሎት መፅሐፍ
መቁረቢያ
የፀሎት ቤት ስዕል
https://t.me/+Epopm7Wd60QzYjA0

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

13 Nov, 09:29


«የመምህራችን መልዕክት ነው ሁላችሁም በዚህ የበረከት ሥራ ተሳተፉ! ደግሞም ለሁሉም እንዲዳረስ ሸር አድርጉ!»

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

12 Nov, 13:52


"የመሆን እንቢታን ማን ይመራዋል? የስግደት በረከቶች ምንድናቸው? ድንቅ ትምህርት #subescribe_now ትውልድ ይዳን! https://youtu.be/i_O1aqAGVEA

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

12 Nov, 13:13


«እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበለው ይባላልን?»

=> መናፍቃን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበል ማለታቸው ትክክል ነውን? በፍጹም ትክክል አይደለም፡፡ ሲጀመር ይህ ዓይነቱ እምነት የሚመነጨው ትምህርቶችን በሙሉ “ብቻ” በምትል ቃል ውስጥ ከመክተት ነው። እምነት ብቻ፣ ጸጋ ብቻ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ፣ ኢየሱስ ብቻ የመሳሰሉትን ትምህርት በልቡ የጸነሰና በአፉ የወለደ ኹሉ ዞሮ ክርስቶስን በብቻ መርሕ ውስጥ ከትቶ እንደ ግል አዳኝ አድርገህ ተቀበለው ቢል ብርቅና ድንቅ አይደለም። ደግሞ አለማስተዋል ካልኾነና ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመረዳት አለመፈለግ ካልታከለበት በቀር ማዳንን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መስጠት ትክክል አይደለም፡፡ ማዳን የአብ የወለድና የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት ውጤት ነውና፡፡ ቤዛነት ወይም መሥዋዕትነት ወይም የሰው ልጆችን ተክቶ (በተገብቶ) የተፈጸመው ሥራ ወልድ በሥጋዌው በተለየ አካሉ ያደረገው ነው፡፡ ይህንን ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ሰጥተን አንናገርም፡፡ ምክንያቱም በተለየ አካሉ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በአዳም ቦታ ተገብቶ ራሱን ቤዛ አድርጎ ያቀረበው አማናዊው መሥዋዕት እርሱ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና። ይህን በተመለከተ ሩሲያዊው ቭላድሚር ሎስኪ የተናገረውን መ/ር ፀሐዬ ደዲማስ እንዲህ ተርጒሞልናል፡- "በእርግጠኝነት (የድኅነት) ሥራ የሚከናወነው ልዩ በኾነው ማንም በማይጋራው በሥላሴ ፈቃድ ነው፤ በእርግጠኝነትም የዓለም (የሰው ልጆች) ድኅነት የዚህ አንድና የጋራ የኾነው የሦስቱ አካላት ፈቃድ ውጤት ነው፡፡ … ነገር ግን ይህ አንድ ፈቃድ በድኅነት ሥራ ላይ የተፈጸመው በእያንዳንዱ አካል በተለያየ ኹኔታና አፈጻጸም ነው፤ አብ ላከ ወልድ ታዘዘ (ተላከ) መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ያከናውንና ይረዳ ነበር፤ በዚህም ወልድ ወደ ዓለም ገባ፡፡ የወልድ ፈቃድ ያው ራሱ የሥላሴ ፈቃድ ነው፤ ነገር ግን የተገለጠው በመታዘዝ ወይም በመላክ ነው፡፡ እኛን ያዳነን ሥላሴ ነው፤ ነገር ግን የድኅነትን ሥራ እውን ለማድረግ ሰው ኾኖ (በተለየ አካሉ) የተገተጠው ወልድ ነው፡፡" ይላል፡፡ ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን መናፍቃንን ይህን ጉዳይ ልብ እንዲሉ ትመክራለች፡፡

=> በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው እያንዳንዱን ግለ ሰብእ እየዞረ በማዳን አይደለም፡፡ ማለትም 1000 ሰዎች ቢኖሩ ለሁሉም በየግል እየሄደ እየተሰቀለ ድኅነትን አልሰጠም፡፡ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ለዓለም ሁሉ ተሰቅሎ፡ ራሱን ቤዛ አድርጎ ዓለምን አዳነ እንጂ፡፡ የተጸነሰውም፣ የተወለደውም፣ የተገረፈውም፣ የተሰቀለውም፣ ወደ መቃብር የገባውም፣ ሞትን ድል አድርጎ የተነሣውም፣ ያረገውም ለግለ ሰብእ ሳይኾን አንድ ጊዜ ለዓለም ሁሉ ነው፡፡ ዓለምን ሁሉ አንድ ጊዜ ስላዳነ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ አዳኝ መኾኑን ስንናገር ዓለም በተባለው ውስጥ የሰው ልጆች ሁሉ መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ የሰውን ልጆች በሙሉ ሲያድን እንዳንዱን ግለ ሰብእ ማዳኑን ልብ ይሏል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን የዓለም አዳን ስንል የሰውን ልጅ በሙል ከጽንስ እስከ ዕርገት በፈጸመው ቤዛነት በአንዴ ማዳኑን ለመግለጽ ነውና፡፡ ሁሉን በማዳን ውስጥ እያንዳንዱን አድኗል እንጂ እያንዳንዱን እያዳነ በመጨረሻም ሁሉን ወደ ማዳን የደረሰ አይደለም፡፡ እንግዲህ ሁላችንንም በየግላችን ሳይኾን በአንድነት ያዳነንን እንዴት በየግል ብቻ እንዳዳነን አደርገን የግል አዳኝ እንለዋለን?

=> በእኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት እያንዳንዱ አማኝ ክርስቶስን መድኃኒቴ ማለት ቢችልም የግሌ መድኃኒት ግን አይልም፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ስትጸልይ "… ነፍሴ በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴትን ታደርጋለች …" በማለት አርአያ ኾናናለችና፡፡ ስለዚህ መድኃኒቴ፣ አምላኬ እንለዋለን ነገር ግን የግሌ መድኃኒት፣ የግሌ አምላክ አንለውም፡፡ ምክንያቱም የግሌ የሚለው አገላለጽ የሌሎችስ አይደለም እንዴ የሚል ጥያቄን ይፈጥራልና፡፡

=> በሌላ በኩል ካየነው ድኅነት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሚቻል እንደ ኾነ ያስመስላል፡፡ ምክንያቱም ከቅድስት ቤተ ክርስቲን ውጭ ኾኜ በግሌ ክርስቶስ ያድነኛል ማለት ፈጽሞ ስሕተት ነውና፡፡ ድኅነት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ፈጽሞ የማይኾን ነውና፡፡ የመዳን መንገዶች በሙሉ ተዘርግተው የተቀመጡት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነውና፡፡ አንድ ሰው ሌላው ቀርቶ ቤተ ክርስቲያን አታስፈልገኝም ብሎ በግሉ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ምጽዋዕት እና የመሳሱት አድርጎ እዳናለሁ ካለ እንኳን በፍጹም ተሳስቷል፡፡ ምክንያቱም በግል ብቻ ኾኖ መዳን አይቻልምና፡፡ ለመዳን የግድ ማመን፣ መጠመቅ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል፣ ኃጢአት ሲሠራ ንስሐ እየገባ እንደ ገና ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል፣ መልካም ሥራዎችንም መሥራት አለበት፡፡ በዚህ መሠረት ለመጠመቅ፣ ለመቁረብ እና ንስሐ ለመግባት የግድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መኖር አለበት፡፡ እነዚህን ነገሮች በግሉ ብቻ ሊያደርጋቸው አይችልምና፡፡ ሌላው ቀርቶ በምንሠራው መልካም ሥራ እንኳን ብዙ ጉድለቶች ስለሚኖሩብን በቅዱሳን ቅድስና አምነን በስማቸው ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ የተጠሙትን ማጠጣት አለብን፡፡ ይህን ሁሉ መስመር የዘረጋው አምላካችን ክርስቶስ ነውና፡፡ እምነታችንም ቢኾን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሠረት ላይ ካለው ውጭ ከኾነ መዳን አይቻልም፡፡ ስለዚህ በምንም መንገድ ብናስብ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውጭ ኾነን በግል መዳን አንችልም፡፡ እንግዲህ "እንደ ግል አዳኝ አድርገህ ተቀበል" ማለት ከላይ ከተዘረዘሩት መሠረታዊ የመዳን መንገዶች ውጭ እድናለሁ ብሎ ማሰብ ነውና ፍጹም ስሕተት ነው፡፡ ያለ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ያለ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት፣ ያለ ቤተ ክርስቲያን ቁርባን እና ምሥጢረ ንስሐ መዳን ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነውና፡፡

=> ከላይ የገለጽነውን ጉዳይ አጽንዖት ሰጥቶ ታላቁ ሊቅ ቆጵርያኖስ "ማንም ቢኾን ራሱን ከቤተክርስቲያን ለይቶ ከአመንዝራዎች ጋር ቢቀላቀል፤ ከቤተክርስቲያን ቃል ኪዳን ይለያል፤ ቤተክርስቲያንን ትቷት የሄደ የክርስቶስን የክብር አክሊል አያገኝም። እርሱ እንግዳ ነው፤ እርሱ የተቀደሱ ነገሮችን የሚያቃልል ነው፤ እርሱ ጠላት ነው። ቤተክርስቲያን እናቱ ያልኾነችለት እግዚአብሔር አባቱ አይኾንለትም። ማንም ከኖኅ መርከብ አምልጦ ውጭ ከኾነ ከቤተክርስቲያንም ውጭ ይኾናል በማለት የኖኅ መርከብ የተባለችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ትቶ መሄድ ተገቢ አለመኾኑን ያስረዳል። በመኾኑም ድኅነት የሚገኘው የጸጋው ግምጃ ቤት በኾነች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል መኾኑን ልብ እንበል፡፡ ስለዚህ እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበል የሚለውን ከላይ ያብራራነውን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሚንድ ክሕደታዊ ሐሳብ መኾን እንስተውል፡፡ ... !

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

11 Nov, 13:34


የቆሞስ አባ ሳሙኤልና የመምህር ግርማ ነገር! || የአመቺሳና የራሔሎ መንፈስ ከባዱ ፈተና! || የቆሞስ አባ ሳሙኤል አገልግሎት #ethiopia #ebstv 😱😭 https://youtu.be/oXmK_1kZr_k

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

11 Nov, 11:05


የጠንቋዩ የመምህር ግርማ ልጅ ይሉኛል! || ጹሙ ጸልዩ የምል ጠንቋይ || የመምህር ግርማ የፀጋ ምንጭ አስማት ነው ወይ? || ልጃቸው ይናገራል! #ebstv 😱 https://youtu.be/YFx-FWa6Qyk

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

11 Nov, 05:49


የመምህር ግርማ ገጠመኝና ፈተናዎቸ || ክፍል 1 መናፍስት ተንኮለን ከሰው ልጅ ሲማሩ || ዕድልና ራዕን የሚወጉ አጋንንቶች #ethiopia #ebstv 😱😭💥🔥🚩 https://youtu.be/TAxpwR6c--c

2,116

subscribers

1,553

photos

77

videos