የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) @house_of_immanuel Channel on Telegram

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

@house_of_immanuel


ይህ ቴሌግራም ቻናል ቃለ እግዚአብሔር ብቻ ይነገርበታል:: አንድም እግዚአብሔር አምላክ በቃሉ እየረዳን መንፈሳዊ ህይወታችንን ራስ ወደሆነ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እናሳድግበታለን::

በዚህ ቻናል የሚተላለፉ መልእክቶች

- መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች
- ዕቅበተ እምነትና ምክረ አበው
- የበረከት ሥራዎችና የምክር አገልግሎት

"ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን" ሮሜ 16

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) (Amharic)

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) በዚህ ቴሌግራም ቻናል ቃለ እግዚአብሔር ብቻ እንኳን ይነገርበታል። ይህ እግዚአብሔር አምላክ እየረዳን መንፈሳዊ ህይወታችንን ራስ ወደሆነ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እናሳድግበታለን። በዚህ ቻናል የሚተላለፉ መልእክቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች, ዕቅበተ እምነትና ምክረ አበው, የበረከት ሥራዎችና የምክር አገልግሎት ይሆናል። "ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን" ሮሜ 16 ። እንዲሁም, ቴሌግራም ቻናል "የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)" እንደሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በመላው ሕግ ትክክለኛ እንዲሆን በማሰብና በማረጋገጥ እንዲሁም አቶ ዲያቆን ዘአማኑኤል በትክክለኛ አገልግሎት ይሁኑ።

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

26 Jan, 22:06


የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) pinned «እግዚአብሔር ይመስገን በደማቅ ሁኔታ የክርስቶስ እስረኛ ተማሪዎች ተመርቀዋል::...........ፎቶ ነገ ይጠብቁ😀»

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

26 Jan, 22:06


እግዚአብሔር ይመስገን በደማቅ ሁኔታ የክርስቶስ እስረኛ ተማሪዎች ተመርቀዋል::...........ፎቶ ነገ ይጠብቁ😀

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

24 Jan, 17:25


የእናታችን የቅድስት ኪዳነምሕረት ምልጃ አይለየን እግዚአብሔር አምላክ ፍቅሯን ያብዛልን::


ላእከ ወንጌል ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

22 Jan, 22:20


የክርስቶስ እስረኛ ተማሪዎች ለማስመረቅ ዝግጅታችንን ጨርሰናል እሁድ በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን እንገናኝ::

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

22 Jan, 11:53


"ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ" መዝሙረ ዳዊት 118:26

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

19 Jan, 15:05


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ አደረሰን::

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

18 Jan, 16:17


ዲያቆን ያሬድ

https://youtu.be/AJhsM83T_zM?si=0cB7jlt0kDHzqWYu



ዲያቆን ዘአማኑኤል

https://youtube.com/@dn_zeamanuel?si=gLgRChA1W7T74YZl



ሰብስክሪያብ እያደረጋችሁ ቤተሰብ ይሁኑ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

17 Jan, 15:36


የአሜሪካ ታላቁ ፍርድ ቤት (Supreme Court) ቲክቶክ (TikTok) ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ዛሬ ውድቅ አደረገ ይህ ማለት ቲክቶክ ለአሜሪካን ካንፓኒ ካልተሸጠ በአሜሪካ ሀገር ይታገዳል::

~supremecourt.gov~

በጣም ያሳዝናል ጉዞ ወደ (YouTube)

Link:- https://youtube.com/@dn_zeamanuel?si=RUBXTHNzbfSZWD8p

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

06 Jan, 13:06


"እግዚአብሔር ሰውን ወደ እንስሳ ደረጃ ዝቅ ብሎና ተዋርዶ አገኘው:: ስለዚህም ሰውን ዝቅ ካለበት እንስሳዊ ጠባይ ወደ ማወቅና ማስተዋል ደረጃ ከፍ እንዲልና ወደ ጥንት ተፈጥሮ እንዲመለስ በከብቶች ግርግም (በረት) ውስጥ ራሱን ምግብ አድርጎ አቀረበለት:: እኛም ልዩ ወደ ሆነው ግርግምና ምሥዋዕ ስንቀርብ ከሥጋዊ ኅብስት የሚልቀውን ሕያው የሆነውን ሰማያዊውን ኅብስት እናገኛለን::"

ቅዱስ ጎርጎዮስ ዘእንዚናዙ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ አደረሰን::

ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

30 Dec, 20:33


ሚስጥረኛዬ ♥️♥️♥️

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

30 Dec, 12:13


https://youtu.be/Wdx3l0WUcVk?si=U8RVLK0Vkk7M94dP

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

29 Dec, 20:32


Spiritual Tiktokers Creative Award
የመንፈሳዊ ቲክቶከርስ የሽልማት መርሐ ግብር

የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ -
የተለያዩ ገዳማትን አድባራትን በቪዲዮዎቻቸው እንዲሁም ላይቭ በመግባት ገቢ ለሚያሰባስቡ ፣ የወጣቶችን ህይወት ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመልሱ የህይወት ተሞክሮዎቻቸውን ለሚያካፍሉ እንዲሁም ኢአማንያንን ወደ ቤተ ክርስቲያን ለሚመልሱ ቲክቶከሮች ማበረታቻ የሚሆን ሽልማትን መስጠት ነው ።

የፕሮግራሙ ይዘት -
ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በፀሎት የሚጀመር ይሆናል ፤ ትምህርትና የዝማሬ ጊዜ በመሐል በመሐል የሚኖር ይሆናል ፤ በተለያዩ ተጋባዥ አርቲስቶችና የቢዝነስ ሠዎች ከእጩ ተወዳዳሪዎች መሐል የብዙ ሠው ድምፅ ያገኙ ቲክቶከሮች የሚሸለሙ ይሆናል በመጨረሻም ሁሉም እጩ ተወዳዳሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሠጣቸው ይሆናል ።

ይህ መርሐ ግብር እንዲዘጋጅ ያሠብኩት ከሰዓሊ ቅዱስ ኤፍሬም ጋር 2024 Tiktok Creative Award ላይ በመገኘት የተለያዩ ዓለማዊ ይዘት ያላቸውን ስራዎች የሚሠሩ ቲክቶከሮች ሲሸለሙና ሲበረታቱ በማየቴ ነው ፤ ዓለማዊ ነገርን የሚያስተምሩ እየተበረታቱ ለምን ነፍስን ሊያድኑ የሚችሉ ቲክቶከሮችን ቤተ ክርስቲያን አታበረታታም ብዬ በማሠብ ነው ።

ማሳሰቢያ - የግል ሀሳቤ ነው ፤ ሀሳብ ሠጥታችሁበት ሀሳቡን ሊያስፈፅም የሚችል ሠው ጋር እንድታደርሱልኝ ነው ።
ቤተ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

28 Dec, 15:15


የቅዱስ ገብርኤል ምልጃ ጥበቃው አይለየን

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

24 Dec, 14:16


ሁሉንም በሰላም በእግዚአብሔር እርዳታ ጨርሰን ተመልሰናል:: ረቡዕ ታኅሣሥ 16 በኢትዮጵያ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ መዝሙረ ያሬድ ቤት በመጽሐፍ ዳሰሳ እንገናኝ::

በክርስቶስ ፍቅር እወዳችዋለሁ::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ታኅሣሦ 15,2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

23 Dec, 12:54


እንኳን ደስ አላችሁ:: ከክርስቶስ መጽሐፍ ተጠናቋል:: በቅርቡ አንባብያን እጅ ይደርሳል::

የመጽሐፉ ሙሉ ገቢ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት መንዝ ጌራ ምድር መሃል ሜዳ ወረዳ የውጥን ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መርጃ ይውላል::


የመጽሐፍ ሽፋን በዲያቆን ዮርዳኖስ ዘሪሁን



ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ታኅሣሦ 14,2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

21 Dec, 13:04


የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃና ጸሎቱ አይለየን::

"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዋል::" መዝ 34:7

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

20 Dec, 13:33


“ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።”

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:16

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

18 Dec, 17:42


የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ "ከክርስቶስ" መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ይጠናቀቃል እኛም ወደ ሚዲያ እንመለሳለን:: ከወንድሞች መምህራን ጋር መጽሐፍ ዳሰሳ መርሃግብር መዝሙረ ያሬድ ቤት ረቡዕ ይኖረናል::

(ቀኑ ሲቀርብ ሰዓቱን አሳውቃለሁኝ::)


"ወልደ ሰማዕት" እያላችሁ በጸሎት አስቡኝ::



ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ታኅሣሦ 9, 2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

17 Dec, 12:33


እንኳን ደስ አላችሁ:: ሃይማኖታዊ ገድል መጽሐፍ ተጠናቋል:: በቅርቡ ለአንባብያን ይቀርባል::

የመጽሐፉ ሙሉ ገቢ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ አንድነት ገዳም

የመጽሐፍ ሽፋን በማራኪ ግርማ



ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ታኅሣሦ 8,2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

16 Dec, 15:56


እንኳን ደስ አላችሁ:: የክርስቶስ እስረኛ 3ኛ ዕትም በአዲስ መልኩ ተዘጋጅቶ ተጠናቋል:: በቅርቡ ለአንባብያን ይቀርባል::

የመጽሐፉ ሙሉ ገቢ ለሴት ደብር ቅድስት ኪዳነምህረት ገዳም የሚውል::

የመጽሐፍ ሽፋን በማራኪ ግርማ



ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ታኅሣሦ 7,2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

15 Dec, 13:53


እናቴ 💕

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

12 Dec, 19:41


የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) pinned «♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ♥️ "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።" ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21»

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

12 Dec, 19:41


♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ♥️


"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

11 Dec, 16:36


“ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ተፈቀደለት።”

ሐዋ 28:16


ሮም, ኢጣልያ 🇮🇹

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

10 Dec, 17:29


የክርስቶስ ኢየሱስ ቤተሰቦች "ወልደ ሰማዕት" እያላችሁ በጸሎት አስቡኝ በቅርቡ 3 እጅጉን ለመንፈሳዊ ህይወታችን ጠቃሚ የሆኑ መጽሐፎችን ይዤ ወደ እናንተ እቀርባለሁ:: አንድም እነዚህን መጽሐፎች በማንበብ እራስ ወደ ሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንድናድግ በትህትና እጠይቃለሁ::



ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ኅዳር 30,2016
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

10 Dec, 12:53


“ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ”

2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:17

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

10 Dec, 12:23


የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) pinned «"ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።" ፊል 4:13 የክርስቶስ ቤተሰቦች "ወልደ ሰማዕት" እያላችሁ በጸሎት አስቡኝ እግዚአብሔር እረድቶኝ እያዘጋጀሁኝ ያለሁትን መጽሐፎች በቶሎ ጨርሼ አስመርቄ ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ አስረክቤ በቶሎ ወደ እናንተ እንድመለስ:: በክርስቶስ ፍቅር ሁላችሁን እወዳችዋለሁ:: ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ ኅዳር 27,2016 ሰሜን አሜሪካ»

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

09 Dec, 13:11


"እግዚአብሔር ፈጽሞ ያረጋጋቸው ዘንድ ስለ አዘኑና ስለ ተከዙ ሰዎች እንማልዳለን::"

መጽሐፈ ቅዳሴ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

07 Dec, 16:36


“ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና”


ማቴ 19:14


መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከክርስቶስ እስረኞች ህጻናት ጋር በደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን (Alexandria VA)

ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ኅዳር 28,2016
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

06 Dec, 15:40


"ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"

ፊል 4:13



የክርስቶስ ቤተሰቦች "ወልደ ሰማዕት" እያላችሁ በጸሎት አስቡኝ እግዚአብሔር እረድቶኝ እያዘጋጀሁኝ ያለሁትን መጽሐፎች በቶሎ ጨርሼ አስመርቄ ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ አስረክቤ በቶሎ ወደ እናንተ እንድመለስ::


በክርስቶስ ፍቅር ሁላችሁን እወዳችዋለሁ::



ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ኅዳር 27,2016
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

04 Dec, 12:34


"ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።"
ራእይ 2:10

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

02 Dec, 20:22


“ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና” ማቴ 19:14


Video from TikTok:- mareyu143

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

26 Nov, 12:09


Mamertine Prison (Carcer Tullianum)

በጥንታዊቷ ሮም መሀል ከተማ የተተከለው ይህ እስር ቤት (7 century BC, by Ancus Marcius) እንደተመሰረተ ሲነገርለት የሮም ጠላቶች (Enemies of Rome) በማለት የሮም መንግሥት የፈረጃቸው ሰዎች ከሰው ተገልለው በጨለማ ውስጥ የሚታሰሩበት ታሪካዊ እስር ቤት ነው::

በዚህ ጥንታዊ ወይኒ (እስር ቤት) በዚህ መንገድ እየተባሉ በሚጠሩት ምዕመናን (ክርስቲያኖች) ዘንድ እጅጉን የሚፈቀሩት ቅድስት ቤተክርስቲያን አዕማድ (ምሰሶ) እያለች የምትጠራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በታማኝነት አገልግለው ወንጌልን ሰብከው ለብዙዎች የመዳን ምክንያት የሆኑት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ በአስከፊው ሮማዊ ገዢ ኔሮ ቄሳር ዘመን (54-68 ዓ.ም) ሰማዕትነት ከመቀበላቸው በፊት ታስረውበታል ተብሎ የሚታመነው ይህ እስር ቤት እንደሆነ በብዙ የታሪክ ምሁራንና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዘንድ ይታመናል::

የቅዱሳን ሐዋርያት ጳውሎስ ወጴጥሮስ በረከታቸው ይደርብን:: እነርሱ የተላበሱትን የእምነት ጽናት እግዚአብሔር አምላክ ያላብሰን::

ምንጭ (Reference):-

📍መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት

📍The Victims of the Mamertine. Scenes from the early church. Second series. Rev. A. J. O’Reilly, D.D.,

📍 omniavaticanrome. org. The Mamertine Prison

Photo & Video by:- M_V

ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ኅዳር 17,2016
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

24 Nov, 15:04


እንኳን ለጾመ ነቢያት አደረሳችሁ አደረሰን::

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

22 Nov, 12:57


Colosseum በጊዜው 50,000 - 80,000 ሰዎች የማስተናገድ አቅም እንዳለው ይገመታል:: በዚህ ስቴድየም ብዙ ታዳሚዎች ተገኝተው ግላዲያተሮች እርስ በርስ እስከሞት ድረስ የሚያደርጉትን ፍልሚያ : የዱር አራዊት ትግል: የተለያዩ አስገራሚ የሆኑ ድርጊቶችን በመመልከት በጥንታዊቷ ሮም ይዝናኑ እንደነበር ይነገራል::

በተጨማሪም ክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት ምክንያት በዘመኑ እጅጉን ይጠሉ ስለነበር በዚህ ግዙፍ ስቴድየም ውስጥ በተለያየ አሰቃቂ ሁኔታ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል:: “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ” ይሁዳ 1:3 እንዲል ታላቅ ገድል ተጋድለዋል::

ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር እንደሆነ የሚነገርለት ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ በዚህ ስቴድየም ለአናብስት ተሰጥቶት ሰማዕት መሆኑንም የቤተክርስቲያን የታሪክ መዛግብት ያሰፍራሉ::

የቅዱሳን ሰማዕታት በረከታቸው ይደርብን እኛንም በእምነት ያጽናን::

ምንጭ (Reference):-

📍ስንክሳር

📍The Roman Colosseum (The history of the world’s most famous arena) by Charles River editors

📍The Martyrs of the coliseum Or, Historical Records of the Great Amphitheatre of Ancient Rome an early Christian History- A.J. O’Reilly

📍 The Colosseum by Keith Hopkins, Mary Beard

📍The Colosseum A History, Robert B. Abrams

Photo & Video by:- M_V


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ኅዳር 13,2016
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

18 Nov, 12:15


ሰማይና ምድርን የፈጠረ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ የተመሰገነ ይሁን የተወደደ ጸጋው በሁላችን ላይ ይደር::

ብዙዎቻችሁ በውስጥ መስመር ለምን ጠፋህ ? የሚል መልእክት
አስቀምጣችሁልኛል:: አስቀድሜ ደህንነቴ አሳስቧችሁ ስለጠየቃችሁኝ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ::

ለምን ጠፋህ የሚለውን ስመልስ ሁላችሁም እንደምታውቁት በቅርቡ 3 መጽሐፍ አዘጋጅቼ ለቤተክርስቲያን ስጦታ አበረክታለሁ:: ከዚህ ጋር ተያይዞ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ደግሞ ከነገሮች በመራቅ ለእራስ ጊዜ መስጠት ማንበብ ግድ ስለሚል ይህን በማድረግ ላይ እገኛለሁ::


"ወልደ ሰማዕት" በማለት ታናሽ ወንድማችሁን በጸሎት አስቡኝ ከመጽሐፍ ምርቃት በኃላ በአዲስ መልኩ ወደቀደመው አገልግሎት እንመለሳለን::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

10 Nov, 18:02


እግዚአብሔር አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያምን ፍቅሯን ያብዛልን::

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

10 Nov, 04:45


የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ ጸሎት አይለየን:: እግዚአብሔር አምላክ የጠየቅነውን ሳይሆን የሚያስፈልገንን ይስጠን::





ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ኀዳር 1/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

06 Nov, 13:32


…….ኢየሱስ ክርስቶስ…….

♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ ♥️
♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብስተ ሕይወት ለዘይበልዖ ♥️
♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋዐ መድኀኒት ለዘይሰትዮ ♥️
♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ በግዐ መድኀኒት ለዘይሠውዖ ♥️

ከመ ይባርኩነ ይፈኑ አርዳኦ ለጸባኢነ ይጽብኦ ወልታሁ ነሢኦ

♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ ጣፋጭ ነው ♥️
♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚበላው የሕይወት እንጀራ ነው ♥️
♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠጣው የመድኃኒት ጽዋ ነው ♥️
♥️ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚሠዋው የድኅነት በግ ነው ♥️

ይባርኩን ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን ይላክ፤ ጋሻውን አንሥቶ የሚጣላንን ይጣላው

""

ተአምረ ኢየሱስ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

01 Nov, 12:39


"ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን" 2 ቆሮ 9:15


በእግዚአብሔር እርዳታ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ተፈጸመ::


የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን::



ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ጥቅምት 22/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

31 Oct, 11:24


የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) pinned «የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች የመጨረሻ ክፍል ምዕራፍ 4 ሐሙስ ጥቅምት 21 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን:: የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን:: ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ ጥቅምት 21/2017 ሰሜን አሜሪካ»

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

31 Oct, 11:24


የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች የመጨረሻ ክፍል ምዕራፍ 4 ሐሙስ ጥቅምት 21 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን::


የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ጥቅምት 21/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

29 Oct, 12:02


የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች የመጨረሻ ክፍል ምዕራፍ 4 ማክሰኞ ጥቅምት 19 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን::


የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ጥቅምት 19/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

27 Oct, 19:24


“ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።”

መጽሐፈ ምሳሌ 22:6

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

23 Oct, 14:17


የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) pinned «የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 3 የመጨረሻ ክፍል ሐሙስ ጥቅምት 14 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን:: የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን:: ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ ጥቅምት 13/2017 ሰሜን አሜሪካ»

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

23 Oct, 14:17


የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 3 የመጨረሻ ክፍል ሐሙስ ጥቅምት 14 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን::


የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ጥቅምት 13/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

23 Oct, 12:35


“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።”

መዝሙረ ዳዊት 34:7



የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃና ምልጃ አይለየን::

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

22 Oct, 13:36


የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 3 ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 12 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን::


የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ጥቅምት 12/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

18 Oct, 13:11


“ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም፡ አላት።” ሉቃስ 10:42

Follow me on TikTok (dn_zeamanuel)

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

18 Oct, 11:25


"እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ እናካፍላችሁ ዘንድ በጎ ፈቃዳችን ነበረ፥ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና።"

1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2:8

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

17 Oct, 13:45


የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 2 የመጨረሻ ክፍል ዛሬ ጥቅምት 7 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን::


የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ጥቅምት 7/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

17 Oct, 03:14


ወንድማችን ዲ/ን ዘአማኑኤል ገና በወጣትነት ዕድሜው ሀሁ ብሎ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ራሱን ያዘጋጀ፣ ለብዙ ወጣቶች አርኣያና ሞዴል መኾን የሚችል፣ ብስለትን ከትሕትና አንድ አድርጎ የያዘ፣ ትጉህና ቅን፣ አርቆ አሳቢ የኾነ ድንቅ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው።

በዚህ የወጣትነት ዕድሜው የሐዋርያው የቅዱስ ይሁዳን መልእክት መሠረት አድርጎ ስለሃይማኖታዊ ገድል በሁሉም የዕድሜ ደረጃ ላለነው በሚመጥን መልኩ አዘጋጅቶ አቅርቦልናል። የይሁዳ መልእክት አንድ ምዕራፍ ብቻ ያለው ሲሆን ዶግማና ቀኖናን በጠበቀ መልኩ በብዙ መንገድ ተንትኖ እና አብራርቶ ትልቅ መጽሐፍ አድርጎ ጽፎ እነሆ ይለናል። በአንድ ምዕራፍ ተነሥቶ ትልቅ መጽሐፍ መጻፍ እንደሚቻልም ሞዴል ኹኖ አሳይቶናል።

በዚያ ላይ ወጣት እንደመሆኑ ብዙ ፍላጎቶች ያሉት ሲሆን ነገር ግን ራሱን ገዝቶ ከራሱ ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን አስቀድሞ ይህን የመሰለ መንፈሳዊ ሥራ ሠርቶ ትውልድ ለሚታነጽበት ለቤተ ጉባኤ መስጠቱ ለቤተ ክርስቲያን ይበልጥ ያለውን አርቆ አሳቢነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።
ስለዚኽ ምእመናን ሆይ ይኽን መጽሐፍ ገዝተን በማንበብ ራሳችንን እንድናንጽበት ወዲኽም ት/ቤቱን እንድናግዝበት ለማለት እወዳለኹ።

ሊቀ ሊቃውንት ትሕትና ተስፋዬ በሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ አንድነት ገዳም የኆኅተ ብርሃን ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍተ ትርጓሜ አዳሪ ት/ቤት የቅኔ፣ የአቡሻኽርና የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍተ ትርጓሜ ምስክር መምህር።

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

16 Oct, 03:44


“አንድ ድንጋይ ወደ መስታወት ቢወረወር መስታወቱን ይሰብረዋል; ወደ አንድ ተራራ ቢወረወር ግን ተራራውን ያሳድገዋል; አንተም እንደ ተራራው ሁን እንጂ እንደ መስታወቱ አትሁን!”

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

15 Oct, 12:36


የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 2 ዛሬ ጥቅምት 5 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንማራለን::


የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን::


ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ጥቅምት 5/2017
ሰሜን አሜሪካ

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

13 Oct, 22:42


የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል) pinned «https://youtu.be/eEHjzzGtjyk?si=eJGOAnwSP4jMCSAY ሁሉም ሊያደምጠውና ሊማርበት ይገባል::»

የክርስቶስ እስረኛ (ዲያቆን ዘአማኑኤል)

13 Oct, 22:42


https://youtu.be/eEHjzzGtjyk?si=eJGOAnwSP4jMCSAY


ሁሉም ሊያደምጠውና ሊማርበት ይገባል::

3,723

subscribers

272

photos

17

videos