TenAdam online clinic

@tenadamm


የምክር አገልግሎት/ask anything on @tenadamm_bot or @Tenadamm1 /Dr.Tariku & Dr.Abenezer
Welcome to TenAdam online clinic 🏥🚑💉💊Doctor tips on Depression Contraception ,Sexual dysfunction ,Abortion ,Menstrual period related, anxiety,social phobia and more

TenAdam online clinic

23 Sep, 16:53


✳️🥼📢 #ስቲች | Episotomy ⁉️⁉️

✅️በተለምዶ ስቲች የምንለው ፣ የብልትን የውጨኛውን ክፍል በመቀስ በመቁረጥ ማስፋት ነው።

✅️ከውጨኛው የብልት ከንፈር ላይ ፣ቀላል ማደንዘዣ በመርፌ በመውጋት ፣ ከፍ ያለ ቁርጠት፣እና መግፋት ሲኖር መቁረጥ ነው።

⁉️❓️አስፈላጊነቱ
👉በምጥ ሰዐት ለማዋለድ መሳሪያ መጠቀም ሲኖርብን

👉 ፅንስ ኪሎው ከፍ ያለ ሆኖ የበለጠ ጉዳት (tear) ያመጣል ተብሎ ከተገመተ።

👉የፅንስ ልብ ምት ጥሩ ሳይሆን ቀርቶ ቶሎ ለማዋለድ ሲያስፈልግ፣

👉በመቀመጫው ያለ ፅንስ ፣

🚫⛔️🔴ለሁሉም ሴት አይደረግም ፣

⁉️⁉️ከ ስቲች ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ምንድናቸው?
👉ህመም (pain) ቁጭ ብሎ ማጥባት እስኪያቅትሽ ድረስ ህመም ሊኖርሽ ይችላል።

👉የቁስሉ መብገን (ኢንፌክሽን : infection)

👉በግብረስጋ ግኑኝነት ጊዜ ህመም ፣ (Dyspareunia)

👉ሽንትን መቆጣጠር አለመቻል ፣
👉ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል ፣
👉ቶሎ ላይድን ይችላል።

👉ከታቀደው ከፍ ያለ መጠን ያለው ስቲች (ይህ ሲሆን የፊንጢጣ ጡንቻ ጉዳት በተለያየ ደረጃ ይከሰታል)

⁉️❓️ስቲች እንዴት ይድናል?

👉ስቲች ለመዳን ከስድስት እስከ ስምንት ሳምንት ይፈልጋል (6-8 ሳምንት )

✳️አሁን በብዛት ለመስፋት የምንጠቀመው ክር በራሱ ከሰውነት ጋር ይዋኻዳል ፣✳️

👉ማስታገሻ መድኃኒት መውሰድ
👉በመጀምሪያዎቹ ቀናት እብጠቱን ለመቀነስ በረዶ ማድረግ (perineal cold pack ):

👉የሰገራ ድርቀት እንዳይኖር መጠንቀቅ (ይህ አንድ በእርግዝና ጊዜ ይባባሳል ፣ ከወሊድ በኻላም ይቀጥላል) እንዳይኖር

👉አመጋገብን ማስተካከል ፣
👉ውሃ መጠጣት፣
👉አንዳንድ የሰገራ ማለስለሻ መድኃኒቶችን መጠቀም

👉ቁስሉን በ ቀን አራት ጊዜ በ ንፁህ ውሃ መዘፍዘፍ (መታጠብ አደለም)

⁉️❓️ግኑኝነት መች ነው ማድረግ የሚቻለው?
❤️ቁስሉ ከዳነ ከወር ካስራ አምስት ቀን ጀምሮ ይቻላል

🥼📢❤️ማስተዋል ያለብሽ ለጥቂት ወራት ህመም ይኖርሻል ፣ በተጨማሪም ስለምታጠቢ የብልት መድረቅ ሊኖርሽ ይችላል : ይሄንን ከግምት በማስገባት በግኑኝነት ጊዜ ማለስለሻ መጠቀም ጥሩ ነው።

❓️⁉️ከስቲች ጋር በተያያዘ ህክምና መቼ መሄድ አለብኝ?
👉ህመሙ እይባሰ ሲሄድ ፣
👉መጥፎ ጠረን ያለው ፈሳሽ ከ ቁስሉ ሲወጣ
👉መግል ከቁስሉ ሲወጣ፣
👉ቁስሉ ከደማ፣
👉ቁስሉ እያበጠ ሲመጣ ፣
👉ትኩሳት ፣ብርድ ብርድ ማለት ሲኖርሽ፣
👉ሰገራ መቆጣጠር ካቃተሽ

በስቲች ከወለድሽ ከወራት በኃላም ህመም( በግኑኝነት ጊዜ) ይኖራል ፣ ይህ ከሆነ ሀኪምሽ ጋር መሄድ ፣ እናም በማማከር የተለያዩ መፍትሔዎችን መፈለግ አለብሽ።

ሀኪም ጋር እስከምትሔጂ ድረስ ፣ የውጨኛውን የብልት ክፍል ማሳጅ ማድረግ

Source : ዶ/ር ቅድስት

TenAdam online clinic

11 Nov, 16:53


#ክብደት_ለመጨመር_የሚመከሩ_ምግቦች 

ጣፋጮች፦
እንደ ኬክ፣ ቸኮሌት፣ አይስክሬም ያሉ በስኳር እና በወተት የተሰሩ ምግቦችን መብላት ከመጠን ያለፈ ቅጥነትን ላላቸው ሰዎች የሚመከር ነው፡፡

ኦቾሎኒ፦
ኦቾሎኒ ጤናማ እና በቫይታሚን፣ ቅባት እና ፋይበር ሚኒራሎች የበለፀገ ነው፡፡ ለልብ ጤንነትም ከመጥቀሙ ባሻገር ተፈጥሮአዊ ዘይት ስላለው በፍጥነት ሰውነታችን ክብደት እንዲጨምሮ ያደረጋል፡፡

ጥራጥሬ፦
ቡናማ ሩዝ፣ ገብስ፣ አጃ እና ስንዴ ካርቦሀይድሬታቸው ከፍተኛው ስለሆነ ጡንቻዎቻችንን ይገነቡልናል፡፡

የእንስሳት ተዋጽኦ፦
ወተት፣ አይብ እና ቅቤ የካልሺየም ፕሮቲን እና ቅባት ስብስብ አላቻ፡፡ እነዚህም ተፈጥሮአዊ የክብደት መጨመሪያ መንገዶች ናቸው፡፡

የእንስሳት ቅባት፦
የእንስሳት ቅባት እንደ ጮማ እና ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ በፕሮቲን እና ካርቦሀይድሬት የበለጸጉ ናቸው፡፡ እነዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክብደት እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡

ሙዝ፦
ሙዝ ክብደት ለሚፈልጉ ሰዎች ሁነኛ መፍትሄ ነው። አንድ ትልቅ ሙዝ 120 ካሎሪ ሀይል ይይዛል። በተጨማሪም ፓታሺየም እና ሚኒራል ያካተተ ነው፡፡ የሙዝ እና ወተት ውህድ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

የፍራፍሬዎች ጭማቂ፦
ፍራፍሬ ጤናማ ቫይታሚን ከመስጠቱን ባሻገር በአንድ ብርጭቆ 57 ካሎሪ እናገኝበታለን።

ስኳር ድንች፦
ድንች ጣፋጭም ሆነ የተለመደው በካርቦ ሀይድሬት የበለፀገ በመሆኑ የተስተካከለ ቅርፅ ለሚፈልጉ ሰዎች መፍትሄ ነው፡፡

እንቁላል፦
እንቁላል በካሎሪ፣ ሚኒራል፣ ፕሮቲን እና ቅባት የበለፀገ በመሆኑ፡፡ ክብደት ከመጨመር ባለፈ ለአዕምሮ እና አጠቃላይ ጤንነት ጠቃሚ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የምግብ ዝርዝሮች ሲጠቅሙ ከስፖርት ጋር ቢሆን ተመራጭ ይሆናል።

መልካም ምሽት💚💛

TenAdam online clinic

10 Nov, 18:07


ወድ ቤተሰቦች ዛሬ ይዘንላቹ የቀረብነው በሆዳችን ክፍል ህመማችንን ለመለየት የሚረዳን ፅሁፍ ነው ተከታተሉን።

በሆድ ክፍል ህመምን የመለየት ዘዴ

👉 ዘጠኝ አይነት የሆድ ክፍሎች በእነሱ እንዴት ህመማችንን መለየት እንችላለን?
1. የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል
• የጉበት ህመም
• የሆድ ቁስለት
• የሃሞት ጠጠር
• የቀኝ ኩላሊት ህመም

2. የላይኛው የመሃል የሆድ ክፍል
• የጨጓራ ህመም
• የምግብ አለመፈጨት
• የሆድ ቁስለት
• የጣፊያ ኢንፌክሽን
• የጉበት ህመም

3. የግራ የላይኛው የሆድ ክፍል
• የሆድ ቁስለት
• የአንጀት ቁስለት
• የግራ ኩላሊት ህመም
• የሃሞት በሽታ
• የጣፊያ ህመም

4. የቀኝ የጎን መሁለኛው የሆድ ክፍል 
• የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
• የሆድ ድርቀት
• የኩላሊት ጠጠር

5. የእንብርት አካባቢ የሆድ ክፍል(center)
• ትርፍ አንጀት
• የአንጀት መታወክ
• የእንብርት መቁሰል
• የጣፊያ ህመም

6. የግራ ጎን መሃለኛው የሆድ ክፍል 
• የኩላሊት ጠጠር
• የአንጀት መታወክ
• የአንጀት ኢንፌክሽን

7. የቀኝ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
• ትርፍ አንጀት
• የሆድ ድርቀት
• የማህጸን አካባቢ ህመም
• ትንሹን እና ትልቁን አንጀት የሚያገናኘው ህዋስ ህመም

8. የሆድ ታችኛው መሃለኛው ክፍል
• የፊኛ ኢንፌክሽን
• የማህጸን አካባቢ ህመም
• የትልቁ አንጀት ህመም

9. የግራ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
• የትልቁ አንጀት ህመም

TenAdam online clinic

20 Oct, 09:12


#ስትሮክ

#ስትሮክ ምንድን ነው?

🖋 የራስ ቅል (ጭንቅላት)ውስጥ ደም ሲፈስ
🖋 ወደ ጭንቅላት ውስጥ የጓጎለ ደም ሲገባ
🖋 ወደ ጭቅላት የሚገባው ደም ሲቋረጥ ነው።
እንደ አጠቃላይ ስትሮክ ማለት ከላይ በተጠቀሱት ምክናየት አንጎል ሲጠቃ ነው።

🖋 ሁለት አይነት ስትሮክ አለ

📌 1ኛው ኢስኬሚክ(Ischemic) ስትሮክ የሚባል ነው።

ይህ አይነቱ ስትሮክ በሰውነት ውስጥ ባሉና በተለያዩ የደም ቱቦዎች ውስጥ ደም ይጒጉልና ከዚያም ወደ አንጎል በመሄድ የአንጒል ህዊሳትን ሲያውክና ሲያውክ የሚፈጠር ነው። ይህም የአንጎል ህዋሳት ግልኮስና ኦክስጅን እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። 80% የሚሆነው ስትሮክ በዚህ ምክናየት ይከሰታል።

📌 2ኛው ሄሞረጅክ(Hemorragic) ስትሮክ የሚባል ነው።

ይህ ደግሞ ቀጥታ አንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ የሚከሰት ነው።ምክናየቱ ደግሞ ከፍተኛ የደም ግፊት፡ የደም ቱቦዎች መሳሳትና መቅጠን ነው።

#ዋና ዋና የስትሮክ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

1. የእጅ፡ የእግርና የፊት መደንዘዝና መስነፍ
2. እይታን ማጣት
3. መናገር አለመቻል
4. ሌሎች የተናገሩንንም መረዳት አለመቻል
5. ድንገተኛና ከባድ የራስ ምታት
6. የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል

#ስትሮክን መከላከል ይቻላል?

አዎ 50% መከላከል ይቻላል።

#ለስትሮክ የሚያጋልጡ ነገሮች

1. ከፍተኛ የደም ግፊት
2. የልብ ችግር(ሁሉም አይደለም)
3. ከቁጥጥር ያለፈ የስኳር በሽታ
4. የኰሌስትሮል መጠን መጨመር
5. ማጤስ
6. መጡኑ የጨመረ የአልኮል መጠጥ
7. ውፍረት
8. ጭንቅላትንና ልብን የሚመግቡ የደም ቱቦዎች ላይ ችግር ካለ።
9. ወንድ መሆን፡ እድሜ ከ65በላይ ከሆነ፡ በቤተሰብ ካለና ጥቁር መሆን የመጠቃት እድል ከሌሎች አኳያ ይጨምራል።

❗️ ስትሮክ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት።

1. Major Stroke የሚባል፡ ለማከብ አስቸጋሪ የሆነና ወድያው ገዳይ የሆነ ነው።
2. Minor Stroke የሚባል፡ የሚታከምና በህክምና ለውጥ ማምጣት የሚቻልበት አይነት ነው።

🔺አስታውሱ

በህይዎተዎ ሳያውቁት አንድ ጊዜም ይሁን ከዚያ በላይ እራሰዎን ስተው የመውደቅ አጋጣሚ ከገጠመዎት በስትሮክ የመመታት እድሉ ሊኖረዎት ስለሚችል እራሰዎን ለሀኪም ያሳዩ።

መልካም ቀን💚💛
Ask anything @tenadamm_bot

TenAdam online clinic

18 Oct, 16:09


#ልጆች_የላም_ወተት_መች_ነዉ_መጀመር_ያለባቸው?"

ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው? ጤናማ የሆነ የልጅ አመጋገብ ምንድነው?

ጤናማ  የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉ ምንድናቸው?

- የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ዕድሜ
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ  በተወለዱ በ30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡

- ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ወራት ዕድሜ

በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከየእናት ጡት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡

እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ (እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ (እንደ ገንፎ) በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡

በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ (እንደ እንጀራ፣ ዳቦ፤ እንቁላል፣ ሥጋ፣ ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር  ይቻላል፡፡


ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?

- ህጻናትን ቶሎ የላም ወተት ማስጀመር ያለው የጤና ጉዳት
የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት   የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከአንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ ከአንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ (Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡

- የላም ወተት ለልጆች በቶሎ ማስጀመር የጤና ጉዳቶች
o ዝቅተኛ የአይረን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል
o ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለአንደኛው የስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል
o የህጻናት ሆድ ድርቀት
o የወተት አለርጂ
o ላክቶዝ ንጥረነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል፡፡
o ተቅማጥ የመሳሰሉትን የጤና እክሎች ያመጡባቸዋል

TenAdam online clinic

29 Sep, 12:03


የሌዊ ቦዲ ዲመንሻ ምንድን እንደሆነ ያውቃሉ ?

ስለህመሙ በቀላሉ ለመረዳት እንድትችሉ የአንድን ታዋቂ ግለሰብን ታሪክ እናካፍላችሁ።

📍 በአስቂኝ ገፀባህሪው የምናውቀው ዝነኛው የሆሊውድ ተዋናይ ሮቢን ዊልያምስ እኤአ በ2014 አ.ም. በ63 አመቱ በአሳዛኝ ሁኔታ የራሱን ህይወት ያጠፋል፤ ለዚህም መንስኤ የሆነው ለአመታት ሳይታወቅለትና ሲያሰቃየው የነበረው ሌዊ ቦዲ ዲመንሻ (DLB) የተባለው የነርቭ ህመም ነበር።

📍 ዊልያምስ ከሞተ በሗላ ሚስቱ Susan Schneider Williams ከህመሙ ጋር ስለነበረው ትግል ስታስረዳ ከአንድ አመት በፊት መንስኤው ያልታወቀ የአንጀት ድርቀት፣ ለመሽናት መቸገር፣ የእንቅልፍ እጦት፣ የማሽተት ችግር፣ የእጅ መንቀጥቀጥና አብዝቶ መጨነቅ ነበረበት። እነዚህ ምልክቶች በተለያየ ወቅት ይመጡና ይሄዳሉ ነበር፤ ለዚህም በተደጋጋሚ ሀኪም ጋር ቢቀርብም ይሄነው የተባለ በሽታ አልተነገረውም።

📍 በሚያዝያ ወር Night at the Museum 3 ፊልምን እየቀረፁ ሳለ ዊልያም የተሰጠውን ገፀባህሪ ደጋግሞ ሲረሳና ከባድ የፍረሀት ስሜት ሲረብሸው እንደነበረ ታስታውሳለች። ከዚህ በሗላ በነበሩት ወራት የህመሙ ምልክቶች በፍጥነት በመባባስ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ጭንቀት፣ ፍርሀት፣ ግራ መጋባት፣ የቁምና የእንቅልፍ ቅዠት፣ መዘንጋትና ለመንቀሳቀስ መቸገር ይታዩበት ነበር። በዚህ ጊዜ ያየው የነርቭ ሀኪም ዊልያምስ የፓርኪንሰን ህመም እንዳለበት ይነግረውና መድሀኒት ያስጀምረዋል። ብዙም ሳይቆይ ስሜቶቹ ተባብሰው አካባቢውን ለመቃኘት፣ ለመንቀሳቀስና በንግግር ለመግባባት ተቸገረ። በስተመጨረሻ በነሀሴ ወር አንድ ምሽት ባለቤቱ ሱዛንን ተሰናብቶ ወደአልጋው ከሄደ በሗላ አልተመለሰም ።

📍 ከህልፈቱ በሗላ በአንጎሉ ላይ በተደረገው የስነደዌ ምርመራ ከሌሎች ታማሚዎች በተለየ በሁሉም የአንጎል ሴሎች ውስጥ DLBን የሚያመጣው ሌዊ ቦዲ የተባለው በአድ ፕሮቲን በብዛት ተከማችቶ ተገኝቷል። ለዊልያምና ለሚስቱ ትልቅ ፈተና የነበረው የህመሙ ምልክቶችና ጫናው ብቻ ሳይሆን ምን እንደታመመ በትክክል አለማወቁ ነበር።

📍 ሌዊ ቦዲ ዲመንሻ ከፓርኪንሰን ህመም ጋር የሚቀራረብ በነርቭ ህዋሳት መሞት የሚመጣ በሽታ ሲሆን እስካሁን ፈውስ ያልተገኘለትና በሚሊዮኖችን እያጠቃ ያለ ህመም ነው። ከ40 የሚበልጡት የህመሙ ምልክቶች በተለያየ ቅደም ተከተል ስለሚመጡ ለረጅም አመታት ታማሚዎች ህመማቸውን ሳያውቁ የተለያዩ ሀኪሞችን በመጎብኘት ገንዘብና ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይቆያሉ። የሌዊ ቦዲ ዲመንሻ ምልክቶችን በህክምና መርዳት ሲቻል ታማሚዎችም በአማካኝ ከ6-12 አመት በህይወት መቆየት እንደሚችሉ በጥናቶች ተረጋግጧል።

አልዛይመርስ ኢትዮጵያ

Ask anything @tenadam_bot

TenAdam online clinic

24 Sep, 08:08


#የእግር #ፈንገስ #ምንድን #ነው?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#የእግር ፈንገስ በእግሮቹ ላይ ቆዳን የሚጎዳ ተላላፊ የፈንገስ በሽታ ነው። እንዲሁም ወደ ጥፍር እና እጆች ሊሰራጭ ይችላል፡፡ የእግር ፈንገስ በቀላሉ ማከም ይቻላል አንዳንድ ጊዜ ከባድ የሚሆንበት ጊዚያት ይኖራል ። የስኳር በሽታ ካለብዎ ወይም
በሽታ የመከላከል አቅሙ ደካማ ከሆነ እና እግር ፈንገስ እንዳለዎት ከተጠራጠሩ ወዲያውኑ ለሐኪምዎ በመሄድ መታከም ይኖርብዎታል ፡፡

👉👉 #እግርን #ፈንገስ #መንስኤ #ምንድ #ነው?

📌 የእግር ፈንገስ ቲኒያ በተባለ ፈንገስ በእግር ላይ ሲያድግ የሚከሰት ሲሆን ፡፡ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በቀጥታ
በመገናኘት ወይም በፈንገስ የተበከሉ ቦታዎችን በመንካት ፈንገሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ ፡፡ ፈንገሱ በሞቃት እና እርጥበት አካባቢዎች ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

👉👉 #እግርን #ፈንገስ #ምልክቶች

📌 የጥፍር መበስበስ 
📌በጣቶችዎ መካከል ወይም በእግርዎ ላይ ማሳከክ ፣ ማበጥ  እና ማቃጠል
📌 በእግር ጣቶችዎ መካከል እና በእግርዎ መካከል አብዛኛውን ጊዜ በእግርዎ ላይ ቆዳ መሰንጠቅ እና መፋቅ
📌 ደረቅ ቆዳ መኖር
📌 ቀለም መቀየር ፣ ወፍራም ቆዳ መኖር

👉👉# እግር #ፈንገስ #አጋላጭ #ሁኔታዎች

📌 ባዶ እግሮችን መጓዝ
📌 መታጠቢያ ቤቶችን እና የመዋኛ ገንዳዎችን በጋራ የሚጠቀሙ
📌 ካልሲዎችን ፣ ጫማዎችን ወይም ፎጣዎችን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር መጋራት
📌 ጠባብ ፣ ሽፍን ጫማዎችን መልበስ
📌 እግርዎን ለረጅም ጊዜ እርጥብ በማድረግ እና ንፁህና በአግባቡ አለመጠበቅ
📌እግሮች ላብ
📌 በእግርዎ ላይ ትንሽ የቆዳ ወይም የጥፍር ቁስለት መኖር

👉👉 #እግርን #ፈንገስ #ለመከላከል

📌 በየቀኑ እግርዎን በሳሙና እና በውሃ መታጠብ እና ማደራረቅ በተለይ በእግር ጣቶች መካከል
📌 ካልሲዎችን ፣ አንሶላ እና ፎጣዎችን በፍላ  ውሃ  ማጠብ 
📌 ካልሲዎችን ፣ ጫማዎችን ወይም ፎጣዎችን ከሌሎች ጋር አይጋሩ ፡፡
📌 በሕዝብ መታጠቢያዎች ፣ በሕዝብ መዋኛ ገንዳዎች እና በሌሎች ሕዝባዊ ቦታዎች ላይ ጫማዎችን ያድርጉ ፡፡
📌 እንደ ጥጥ ወይም ሱፍ  ቃጫዎች የተሠሩ ካልሲዎችን ወይም ከቆዳዎ ርቀትን ከሚወስዱ ሰው ሠራሽ ክሮች የተሠሩ     ካልሲዎችን ያድርጉ ፡፡
📌 እግርዎ በሚያልቦ ሰአት ካልሲ መቀየር (ድጋግሞ ካልሲ አለማድረግ )
📌 እግርን አለማፈን (አየር እነዲነካው ማድረግ)
📌 ክፍት ጫማዎችን መዘውተር

TenAdam online clinic

19 Sep, 12:02


ጥርስ መታጠብ በተለምዶ የጥርስ መስታወት ተብሎ የሚጠራ (Enamel) ይጎዳል አይጎዳም?

ጥርስ ማጠብ (scaling) ማለት ቤት ውስጥ በምንጠቀመው መደበኛ ብሩሽ የማይለቀውን የጥርስ ቆሻሻ በScalar machine ማስለቀቅ ማለት ነው።

ይሄ የጥርስ ቆሻሻ dental calculus የሚባል ሲሆን እንደ ኮንክሪት ጥርስ ላይ ተጣብቆ የሚቀመጥ ነው።  በቆየ ቁጥር ጥርስን አቅፎና ደግፎ የሚይዘውን ድድና አጥንትን ይጎዳል።

አንደኛ ጥርስ በሚታጠብበት ግዜ ይህ calculus የተባለ ኮንክሪት የሚመስል ነገር እየተሰባበረ ሲነሳ ብዙ ሰው የሚሰባበረው ቆሻሻው ሳይሆን የጥርስ መስታወት ይመስላዋል።

ሁለተኛ Calculus'u ጥርስ ላይ ተጣብቆ በነበረበት ወቅት ለጥርሱ የተወሰነ thickness ስለሚጨምር ከምንጠቀመው ትኩስ ወይም ቀዝቃዛ ነገር  ጥርሱን coat ያደርጋል ማለት ጥርስ ውስጥ ያለው ነርቭ የአፋችን temperature ለውጥ በደንብ sense አያደርግም። Dental Calculus'u ተነስቶ ጥርስ ወደ normal thickness'u ሲመለስ ታካሚው ለተወሰነ ግዜ sensitivity develop ሊያደርግ ይችላል። በዚህ ምክንያት የጥርስ መስታወት ተሰብሮ ጥርሱ የሳሳ ይመስለዋል።

ከዚህ ውጪ within normal situation ጥርስ በማጠብ ጥቅም እንጂ የሚደርስ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም።

Source: Dr Fikadu

TenAdam online clinic

09 Sep, 05:00


የመንታ እርግዝና ምልክቶች

መንታ እርግዝና እንቁላል በሚለቀቅበት ወቅት ሁለት እንቁላሎች በአንድ ጊዜ ከእንቁላል ማምረቻ ክፍል ተለቀው ከሁለት የወንድ የዘር ህዋሶች ጋር ሲገናኙ ወይንም አንድ እንቁላል ከአንድ የዘር ህዋስ ጋር ተገናኝተዉ እንቁላል ለሁለት ሲከፈል ሁለት ጽንስ ይፈጠራል፡፡

የመንታ እርግዝና በሚፈጠርበት ጊዜ የሆርሞን መጨመር ስለሚኖር ከአንድ ጽንስ እርግዝና ላይ የሚታዩ ምልክቶች ተባብሰው ይከሰታሉ።

💎ከእነዚህም መካከል:-
🍀የተባባሰ የማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
🍀ጠንከር ያለ የድካም ስሜት
🍀በታችኛው የሆድ አከባቢ ቁርጠት/ ምቾት አለመሰማት
🍀የሆድ ድርቀት
🍀የእንሽርት ውሃ መቀነስ
🍀የፊንጢጣ ኪንታሮት
🍀የትንፋሽ ማጠር
🍀የጀርባ እና የወገብ ህመም
🍀የፊት፣ የእግር እና የእጅ እብጠት
🍀የቆዳ ላይ የደመቀ ማድያት እና የሆድ ሸንተረር

💎የመንታ እርግዝና ሲኖር ሊያጋጥሙ የሚችሉት ችግሮች
በእርግዝና ወቅት ከሚከሰቱ ችግሮች በመንታ እርግዝና ጋር ተያይዞ ላይከሰቱ ሚችሉት የፅንስ ክብደት መብዛት እና ከግዜው ያለፈ እርግዝና ብቻ ናቸዉ

💎እናቱየው ላይ
❖የደም ማነስ
❖የደም ግፊት
❖የስኳር ህመም
❖ከወሊድ በኋላ ከፍተኛ የደም መፍሰስ
❖ከማህጸን ደም መፍሰስ

💎ፅንሱ ላይ
❖የእንሽርት ውሃ ከምጥ በፊት መፍሰስ
❖ያልተስተካከለ የጽንስ አቀማመጥ
❖ምጥ ያለግዜው መምጣት
❖የጽንስ መታፈን
❖የእትብት መጠምጠም/መቋጠር
❖የጽንስ አፈጣጠር ችግሮች

TenAdam online clinic

29 Aug, 04:01


✍️#የትኛው #የደባቴ (#depression) #አይነት #ያጠቃዎታል?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🔹ሜጀር ዲፕሬሲቭ ዲስኦርደር (ኤምዲዲ)/Major depressive disorder(MDD) ፡- ከፍተኛ የመንፈስ ጭንቀት ሲሆን (ክሊኒካዊ ዲፕሬሽን) ይባላል፡፡ ከሁለት ሳምንት በላይ የሚቆዩ ኃይለኛ ወይም አስጨናቂ ምልክቶች አሉት። እነዚህ ምልክቶች በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ይገባሉ፡፡

🔹ባይፖላር ዲፕሬሽን/ Bipolar depression፡- ባይፖላር ዲስኦርደር ያለባቸው ሰዎች ተለዋዋጭ የዝቅተኛ ስሜት እና እጅግ በጣም ከፍተኛ ሃይል (ማኒክ) ወቅቶች አላቸው። በዝቅተኛ ጊዜ ውስጥ፣ እንደ ሀዘን ወይም ተስፋ መቁረጥ ወይም ጉልበት ማጣት ያሉ የመንፈስ ጭንቀት/ዲፕሬሽን ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል።

🔸 የፐርናታል እና የድህረ ወሊድ ጭንቀት/ Perinatal and postpartum depression ፡- “Perinatal” ማለት በወሊድ አካባቢ ማለት ነው። ብዙ ሰዎች ይህንን አይነት ዲፕሬሽን  ከወሊድ በኋላ የመንፈስ ጭንቀት ብለው ይጠሩታል። የወሊድ ጭንቀት በእርግዝና ወቅት እና ልጅ ከተወለዱ በኋላ እስከ አንድ አመት ድረስ ሊከሰት ይችላል፡፡ ምልክቶቹ ሀዘን፣ ጭንቀት ወይም መረበሽን ያካትታሉ።

🔸 የማያቋርጥ ዲፕሬሲቭ ዲስኦርደር/ Persistent depressive disorder (PDD)፡- ፒዲዲ ዲስቲሚያ / dysthymia ተብሎም ይታወቃል። የ PDD ምልክቶች ከከባድ የመንፈስ ጭንቀት ያነሱ ናቸው፤ ነገር ግን  PDD ያለባቸው ሰዎች ከሁለት አመታት ወይም ከዚያ በላይ የፒዲዲ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡

🔹 ከወር አበባ በፊት የሚመጣ  ዲስፎሪክ ዲስኦርደር/ Premenstrual dysphoric disorder (PMDD)፡ ከወር አበባ በፊት የሚመጣ ዲስፎሪክ ዲስኦርደር በጣም ከባድ የሆነ የቅድመ የወር አበባ መታወክ (PMS) ነው። ከወር አበባቸው በፊት ባሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ሴቶችን ያውካል፡፡

🔹 ሳይኮቲክ ዲፕሬሽን /Psychotic depression ፡- ሳይኮቲክ የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች ከባድ የጭንቀት ምልክቶች እና ውዥንብር ወይም ቅዠቶች አሉባቸው። ቅዠቶች በእውነታ ላይ ያልተመሠረቱ ነገሮች ማመንን ጨምሮ  ማየትን፣ መስማትን ወይም በእውነታው የሌሉ ነገሮች መነካትን ያካትታሉ::

🔸 ወቅታዊ አፌክቲቭ ዲስኦርደር/ Seasonal affective disorder (SAD)፡ ወቅታዊ የመንፈስ ጭንቀት፣ ወይም  ሴሶናል አፌክቲቭ ዲስኦርደር፣ ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በ ክረምት መጨረሻ እና በክረምት መጀመሪያ ወቅታ ላይ ነው። ብዙውን ጊዜ በፀደይ እና በበጋ ወቅት ይጠፋል::

TenAdam online clinic

28 Aug, 12:07


#ነስር (Nose bleeds)

ነስር የምንለው አስደንጋጭ የሆነ፤ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የአፍንጫ መድማት ነው፡፡

ነስር በሁለት ዓይነት ይከፈላል፡፡

1) ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds)

• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይነት ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት
ነው፡፡ ከፍተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣን ነስር በቀላሉ መቆጣጠር ወይንም ማቆም ይቻላል፡፡

2) ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds)

• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይንት በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን
ከሌላኛው የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡
ነስር በአብዛኛው በቅዝቃዜ ወቅት የሚከሰት ሲሆን ከ2 - 10 ዓመትና ከ50 - 80
ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትንም ያጠቃል፡፡

#ነስርን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

• በአፍንጫ ላይ ከውጭ የሚከሰት አደጋ ወይንም አፍንጫ በመጎርጎር ምክንያት
• በzvsvተለያዩ የሕመም ወይንም መድኃኒቶች ምክንያት ደም መርጋት አለመቻል
• የደም ግፊት መጨመር ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነስር ነው፡፡

#የነስር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

• በአብዛኛው ደም የሚፈሰው በአንደኛው የአፍንጫ ቀዳዳ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ
የሆነ የደም መፍሰስ ካለ በሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች ደም ሊፈስ ይችላል፡፡ እጅግ
ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ደግሞ በጉሮሮ አድርጎ በአፍ በኩል ሊመጣ ይችላል፡፡
• ከፍተኛ የሆነ ድም መፍሰስ ሲኖር ራስ ማዞር፣ግራ የመጋባት እና ራስ መሳት
ሊያስከትል ይችላል፡፡

#ነስርን እንዴት ማቆም ይቻላል?

• በመጀመሪያ ራስዎን ማረጋጋት
• ቀጥ ብለው መቀመጥ
• ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ ከማምጣት ባለፈ ጥቅም የለውም)
• ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣትዎ እና በጠቋሚ ታትም ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት
• በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት
• ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት ናቸው፡፡

#ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው?

• አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ የሚያቆም ካልሆነ
• በአጭር ጊዜ ልዩነት በተደጋጋሚ የሚነስርዎ ከሆነ
• ራስ ማዞር ወይንም ራስዎን የሚስቱ ከመሰለዎት
• የልብ ምትዎ የሚጨምር ከሆነ እና ለተንፈስ ከተቸገሩ
• ደም የሚያስመልስዎ ከሆነ
• በሰውነትዎ ላይ ሽፍታ ከኖረ
• ትኩሳት ካለዎት ናቸው፡፡

መልካም ቀን💚💛
Ask anything @tenadamm_bot
Join us @tenadamm

TenAdam online clinic

23 Aug, 06:57


#የዲስክ #መንሸራተት

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

👉👉 የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት  መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ። ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚቋቋሙ ክፍሎች ናቸው።ዲስክ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ አለው ።

👉የዲስክ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውስጥ ፈሳሽ መውጣት ነው። ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው።ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል።

👉አንዳንድ ግዜ በእጅ ላይ የመደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም ስሜት አይኖረውም። የተንሸራተተው ዲስክ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማንም።

👉#መንስኤዎች

🔺 የዲስክ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከጊዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ዲስክ ከእድሜ ጋር ውሃማ ይዘቱን ያጣል። ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል::
የዲስክ መንሸራተት መቼ እንደተፈጠረ ማወቅ ያስቸግራል ነገር ግን የሚከተሉት እንደ መንስኤ ይገለጻሉ፡፡
ቁርጭምጭሚታችንን ሳናጥፍ ከባድ እቃ ለማንሳት ስንሞክር
ከባድ እቃ ይዘን ከጀርባችን ስንታጠፍ ነው።

👉#ተጋላጭነት #የሚጨምሩ #ነገሮች

🔺 ከመጠንያለፈ የሰውነት ክብደት
🔺 እድሜ
🔺 ከባድ ስራ መስራት
🔺 በዘር ተመሳሳይ ችግር ካለ

👉#ምልክቶች

🔺 የታችኛው ጀርባ ህመም
🔺 በትከሻዎ ፤ በጀርባዎ ፣ በእጆችዎ ወይም  በእግሮችዎ ላይ የመደንዘዝ ስሜት።
🔺 የአንገት ህመም
🔺 ጀርባዎን ማጠፍ ወይም ለማስተካከል ሲጥሩ ህመም
🔺 የጡንቻ ድክመት
🔺 ከወገብ በታች የዳሌ ህመም

👉#ውስብስብ #ችግሮች


🔺 ህመም  መደንዘዝ ወይም ድክመት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎን እስከሚያደናቅፉ ድረስ ሊጨምር ይችላል
🔺 የፊኛ ወይም የአንጀት ችግር

👉#መከላከያ #መንገዶች

🔺 ትክክለኛ የሰዉነት አቋም እንዲኖር ማድረግ
🔺 ከባድ እቃ በሚያነሱበት ወቅት ጫናዉን/ክብደትዎን ከጀርባዎ ይልቅ በእግሮችዎ ላይ ማድረግ
🔺 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
🔺 ለረጅም ጊዜ የሚቀመጡ ከሆነ ቀጥ ብለዉ ለመቀመጥ መሞከር
🔺 የሚተኙበትን ሁኔታ ምቹ ማድረግ
🔺 ክብደትዎን በትክከል መጠበቅ

👉#ህክምና

🔺 ሙቅ ነገር መያዝ ህመምን ለማስታገስ ይረዳል
🔺 ከመጠን ያለፈ እረፍት ማስወገድ/ መጠነኛ እንቃስቃሴ ማድረግ
🔺 የህመም ማስታገሻ መድሐኒቶች
🔺 ጡንቻን የሚያፍታቱ መድሐኒቶች መጠቀም
🔺 በባለሙያ የታገዘ የፊዚዮቴራፒ ህክምና
🔺 በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል

👉👉 #የዲስክ መንሸራተት ችግር ሲከሰት ሕመሙ በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበት ወቅት፣ሰገራ ሲጠቀሙ በሚያምጡበት ወቅት ወይም ወደ ተወሰነ አቅጣጫ የጀርባ አጥንቶችን በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡

TenAdam online clinic

22 Aug, 04:01


ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው!

ሲወለድ ክብደቱም ሆነ ጤንነቱ ኖርማል ነው። ድንቡሽቡሽ ያለ ነው። በሁለተኛው ቀን "እሪ" ብሎ ማልቀስ ጀመረ። እናቱ ብታባብለው ብታባብለው ለቅሶው አልቆም አለ። በተደጋጋሚ አስመለሰው። ላብበላብ ሆነ። ሰውነቱ መንቀጥቀጥ ጀመረ። ሀኪሞቹ ያሉትን ምርመራዎች ሁሉ ቢሰሩለትም ምንም ሊገኝ አልቻለም። እናቱንም መመርመር ጀመሩ። ከዛ እሷ ሄሮይን የተባለው ዕፅ ሱሰኛ እንደሆነች ደረሱበት።

ለካ ህፃኑ ማህፀን ውስጥ እያለ እናቱ ሄሮይን ስትጠቀም እሱም በደሟ አማካኝነት ይደርሰው ነበር። ከተወለደ በኋላ ግን ወተት ውስጥ መጠኑ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ የለመደውን አላገኘም። ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው።

እናቶች የሚወስዷቸው ሱስ አስያዥ ነገሮች (ከቡና ጀምሮ) ከእነሱ አልፎ ልጆች ላይም ተፅእኖ እንደሚያደርስ አስታውሶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው የምንለው በምክኒያት ነው።

ምንጭ: ዶ/ር ዮናስ ላቀው

TenAdam online clinic

21 Aug, 10:13


#ክብደት_ለመጨመር_የሚመከሩ_ምግቦች_ዝርዝር

ጣፋጮች፦
እንደ ኬክ፣ ቸኮሌት፣ አይስክሬም ያሉ በስኳር እና በወተት የተሰሩ ምግቦችን መብላት ከመጠን ያለፈ ቅጥነትን ላላቸው ሰዎች የሚመከር ነው፡፡

ኦቾሎኒ፦
ኦቾሎኒ ጤናማ እና በቫይታሚን፣ ቅባት እና ፋይበር ሚኒራሎች የበለፀገ ነው፡፡ ለልብ ጤንነትም ከመጥቀሙ ባሻገር ተፈጥሮአዊ ዘይት ስላለው በፍጥነት ሰውነታችን ክብደት እንዲጨምሮ ያደረጋል፡፡

ጥራጥሬ፦
ቡናማ ሩዝ፣ ገብስ፣ አጃ እና ስንዴ ካርቦሀይድሬታቸው ከፍተኛው ስለሆነ ጡንቻዎቻችንን ይገነቡልናል፡፡

የእንስሳት ተዋጽኦ፦
ወተት፣ አይብ እና ቅቤ የካልሺየም ፕሮቲን እና ቅባት ስብስብ አላቻ፡፡ እነዚህም ተፈጥሮአዊ የክብደት መጨመሪያ መንገዶች ናቸው፡፡

የእንስሳት ቅባት፦
የእንስሳት ቅባት እንደ ጮማ እና ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ በፕሮቲን እና ካርቦሀይድሬት የበለጸጉ ናቸው፡፡ እነዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክብደት እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡

ሙዝ፦
ሙዝ ክብደት ለሚፈልጉ ሰዎች ሁነኛ መፍትሄ ነው። አንድ ትልቅ ሙዝ 120 ካሎሪ ሀይል ይይዛል። በተጨማሪም ፓታሺየም እና ሚኒራል ያካተተ ነው፡፡ የሙዝ እና ወተት ውህድ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

የፍራፍሬዎች ጭማቂ፦
ፍራፍሬ ጤናማ ቫይታሚን ከመስጠቱን ባሻገር በአንድ ብርጭቆ 57 ካሎሪ እናገኝበታለን።

ስኳር ድንች፦
ድንች ጣፋጭም ሆነ የተለመደው በካርቦ ሀይድሬት የበለፀገ በመሆኑ የተስተካከለ ቅርፅ ለሚፈልጉ ሰዎች መፍትሄ ነው፡፡

እንቁላል፦
እንቁላል በካሎሪ፣ ሚኒራል፣ ፕሮቲን እና ቅባት የበለፀገ በመሆኑ፡፡ ክብደት ከመጨመር ባለፈ ለአዕምሮ እና አጠቃላይ ጤንነት ጠቃሚ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የምግብ ዝርዝሮች ሲጠቅሙ ከስፖርት ጋር ቢሆን ተመራጭ ይሆናል።

መልካም ቀን💚💛

TenAdam online clinic

16 Aug, 07:24


ነጻ  ሕክምና
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ትምሕርት ክፍል ዳይሬክት ኤይድ ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባባር ከነሐሴ 28 እስከ  ጳጉሜ 2/2015 ዓ.ም ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ይሰጣል፡፡ለዚህም ይረዳ ዘንድ የዓይን  ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ታካሚዎች የመለየት መርሀግብር ነሐሴ13፣14፣20 አና 21 /2015 ዓም ስለሚካሄድ  አገልግሎቱን ለመግኘት  በ976 በመደወል  ተራ ማስያዝ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡