¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
🔎 ክፍል አንድ
👉 ሐቅ የተዳፈነ እሳት ነው ንፋስ አግኝቶ የተቀጣጠለ ቀን ባጠለልን ወሬ ነጋሪ እንዳይኖር አድሮጎ ይፈጀዋል። ባጢል የፈለገ ቢገን ገናናነቱ ሐቅ እስኪደርስበት ነው። ሲደርስበት የገባበት ይጠፋል አንገቱን ይደፋል የውርደት ካባ ይከናነባል።
➪ የሱፍይ የኢኽዋንና ሙመዪዓ ጥምር የባጢል ሀይል እያቅራራና እየፎከረ በኢኽዋን መሪነት ሐቅን ለመቅበርና የሐቅ ባልተቤቶችን ለማንበርከክ መንግስት ነን እኛ ያልፈቀድንለት መኖር አይችልም እስከማለት ደርሶ በቀረርቶና ሽለላ እንደ እንቦሳ በማናለብኝነት ሲፈነጥዝ ብዙዎችን አስፈርቶ ነበር።
➩ በተቃራኒው የሐቅ ሰዎች እንደ ብረት ሙሶሶ ረግጠው ቆሞው ከቁርኣንና ሐዲስ መርህ ያፈነገጡ ሸሪዓ ደንጋጊዎች ነን የሚሉ የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንም ያሉት ሰለፍዮች ዛሬ ተአምር እያዩ ነው። እናንተ የተቋም መሪ እንጂ የሀገር መሪ አይደላችሁም። መመሪያችሁም የተቋም መመሪያ እንጂ የሀገሪቱ ዜጎች የሚተዳደሩበት መመሪያ አይደለም። እንደ ሀገር ሁሉንም የሚመለከት የዜጎችን የእምነት ነፃነት ያወጀ ህገመንግስት አለ በመሆኑም መብታችን ሊከበር ይገባል። በናንተ የጭቆናና የአምባገነን መመሪያ አንተዳደርም ብለው በመፅናት ከዳር እስከዳር ሲታገሉ የሐቅ ብርሃን አድማሱን እያሰፋ ደቡብ፣ ምእራብ፣ ሰሜን ላይ ጮራውን እየፈነጠቀ የነበረው ሰለፍያ ምስራቁን ክፍል በማይታመን ሁኔታ ባጢልን እያናወጠውና እያሳደደው ነው።
➜ የፌዴራሉ መጅሊስ መሪ ፕሬዝዳንት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከወራት በፊት ምስራቅ ሐረርጌ አመራሮቹን አስከትሎ በመሄድ ሁሉም ዑለሞችና ኢማሞች እንዲሁም ኡስታዞች በግድ እንዲገኙ በማድረግ እኛ ያልፈቀድንለት አይኖርም። ዝም ስንል የተኛን መሰላችሁ እንደ ውሀ ነን ውሀ ዝም ብሎ የተነሳ ቀን ይበላል። እኛም ዝም ስንል ያላወቅን እንዳይመስላችሁ እናጠፋችኋለን። ኬት የመጣ ሰለፍይ ነው? ሰለፍይ አይደለም ሰለኽይ ነው። እያለ እያላገጠና እያሸማቀቀ ፎክሮ ከተመለሰ ከጥቂት ወራት በኋላ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ የማይታመን ክስተት ተከሰተ። ዝም ብለው የነበሩት ዑለሞች በቃ አሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሐቅ መሰከሩ። ኢኽዋኖቹ የዘመናችን ቡኻሪይ ሲሉዋቸው የነበሩት የእድሜ ባለፀጋው አንጋፋው ሸይኽ አሕመድ ወተሬ ሰለፍያ ሐቅ ነው አሉ።
አላሁ አክበር !!!
አላሁ አክበር !!!
አላሁ አክበር !!!
♻️ ሸይኽ አሕመድን የማያውቅ ምስራቅ ሐረርጌያዊ የለም። በዙህዳቸውና በዒልማቸው የሚታወቁት የእድሜ ባለፀጋው ሸይኽ አሕመድ ኢኽዋኖች ጃኬታቸውን የሚሰቅሉባቸው የኛ የሚሏቸው ነበሩ።
🔎 እኚሁ ታላቅ ዓሊም ከሳቸው ስር የወጡ በርካታ ዑለሞችንና መሻኢኾን ይዘው ኢኽዋንን በቃ አሉት። እኛ ሰለፍዮች ነን የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንም ዑለሞች አሉን መመሪያችን ቁርኣንና ሐዲስ በሶሓቦች ግንዛቤ ነው። የናንተን የሰው ሰራሽ መመሪያ አንፈልግም በቃን አሉ። ኢኽዋንና ግብረ አበሮቹ ምድር ዞረባቸው። ስልጣንም ገንዘብም ምንም ማድረግ እንደማይችል አምነው ለመቀበል ተገደዱ። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መንገድ በሚያጨናንቁ የሰለፍዮች ፕሮግራሞች ናላቸው የዞረው የመጅሊስ አመራዞች ምስራቅ ሐረርጌ ላይ በተፈጠረው ነገር እግራቸው ራሳቸውን መሸከም ያቃተው ይመስላል። በአላህ ፈቃድ የመሻኢኾቹን የአቋም መግለጫ በሚቀጥለው ክፍል የማቀርብላችሁ ይሆናል። ሁላችሁም ለእነዚህ መሻኢኾች ረዥም እድሜ ከመልካም ፍፃሜ ጋር ለምኑላቸው እላለሁ።
https://t.me/bahruteka