የአዲስ አበባ መሬት መረጃ አገልግሎት(Addis Ababa land information service) @landmang Channel on Telegram

የአዲስ አበባ መሬት መረጃ አገልግሎት(Addis Ababa land information service)

@landmang


የአዲስ አበባ መሬት መረጃ አገልግሎት(Addis Ababa land information service) (Amharic)

ይህ ገንዘብ በትርጉም መሰረታዊ መረጃዎችን አውሬዎችን እና አገልግሎቶችን እንዲለዋወጥ በተለያዩ አዝናኝ መረጃዎች በመሄድ የተሻለ ማድረግ እንዳለመኖሩ። በአለም የደረሰባቸው እቅዶችና መመሪያዎች ከእናንተ ጋር ባገኙ እና እንደማየት አብሮ ማንኛውም መረጃ እየተሳሳተ የሚገኙን መለያዎች በተቀጠረ ግልጽ ዓረቦች ለመማር የተወሰደ እና ስንት ያክለለው ለመክፈት እና ለመለዋወጥ መረጃ ላይ ማየት እንደሚችሉ መሆን አለብዎት። የስንት ያክለለው ማን ነው? ከዚህ በኋላ አለም ሌሎች ትምህርቶችን የመለያዎቹንና እርሶቹን ከጽኑ በመጠበቅ እንዲለቁ አገልግሎትን የሚጠንቀቁ በእንግዲሞስ አማርኛ መረጃዎች እንዲታዘዙ ለማየት ንገረን። የአለም ትምህርት ከተሰማበት የህብረት ዋና ዓረብ ሰላምታ ማየት እና ስንት እና ያበምሉት መረጃዎች ለመጠቀም የተወሰደ ሃላፊዎች እንዲጠቀሙ በማስተናገድ።

የአዲስ አበባ መሬት መረጃ አገልግሎት(Addis Ababa land information service)

12 Jul, 16:02


የቢሮው  የሪፎርም ስራዎች  ለሌሎች  ተቋማት  ሞዴል እንደሚሆን  ተገለፀ፡፡
***
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ  ለቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና ለቤቶች ልማት ኮርፖሬሽ  የሚሰጡ አገልግሎቶች  ከማዘመን ብሎም የተገልጋዩን እንግልት በመቀነስ እረገድ  ያከናወናቸውን  ስራዎች  ተግባራት እና አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ምቹ የስራ ከባቢን ለመፍጠር  የተሰሩ ስራዎችን  ከፍተኛ  አመራሮች እና  የስራ ክፍል ሀላፊዎች እና ለባለሙያዎች በተገኙበት በሰነድ  እና በአካል ምልከታ  ልምድ አከፍሎል ፡፡
ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ ተሞክሮ ለመቅሰም ወደ ተቋማችን  በመምጣታቸው አመሰግነው አገልግሎቱ በመዘመኑ ለሰራተኛው ምቹ  ሁኔታን በመፍጠር የስራ ተነሳሽነትን  እና የስራ ባህሉን የቀየረና ለውጥ  ያመጣ  እንደሆነ እንዲሁም  ለተገልጋይ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት  አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን  የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አቶ ሲሳይ ጌታቸው  ገልፀዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ  ቢሮው የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ከማዘመን አንፃር የተተገበረው የሪፎርም ስራ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ  በተቋሙ ራዕይና አላማ መሳካትና ተፈላጊውን አገልግሎት በተፈላጊው ጊዜ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ለማድረስ የተደረጉ
እንቅስቃሴዎች የሚታይ ለውጥ ማምጣታቸውን ገልፀዋል  አክለውም ከተማዋ ለጀመረችው የስማርት ሲቲ ግንባታ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን  ገልጸው ቀጣይም  ከተቋማቱ  ጋር  ለለውጥ እንደሚሰሩ  ተነግረዋል ፡፡ 
ቢሮ እና ኮርፖሬሽንም የጀመሩትን  በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ከእጅ ንክኪ የፀዳ ስራ ወደ ተግባር ለመቀየር የልምድ ልውውጡ ጠቀሜታው የጎላ ነው ያሉት የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ሲሆኑ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ  ሪፎርሙ  ባመጣው ለውጥ ከዚህ ቀደም የነበረውን የተዛባ አመለካከት  በተግባር ቀይሮ ያሳየ በመሆኑ  ለሌሎች ተቋማት አርአያ እና ሞዴል  የሚሆን ነውም ብለዋል።
ተቋሙ ከዚህ በፊት  ምልልስ የበዛበት እንዲሁም  ትልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር  የነበረበት  ነገር ግን ለዚህ ለውጥ  መድረስና  ለትልቅ  ስኬት መብቃት በጣም አስደሳች መሆኑን  ገልጸው አገልግሎትን ማዘመን  ለከተማዋም ብሎም ለአገር  ትልቅ  ለውጥ ያመጣል  ያሉት አቶ ሽመልስ ታምራት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ  ከሌብነት እና ከብልሹ አሰራር  ተቋማትን  የሚያድን ሲሆን   የተገኘነውን ተሞክሮውን ወስደን ተግባራዊ  እናደርጋለን ብለዋል፡፡ 
መጨረሻም  የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተዘዋውረው በመጎብኘት ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ያደረገውን ጥረት  አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፃቻችን ያግኙ
Website:- https://https://www.aalb.gov.et
Face book :-Addis Ababa City Land  Develoment  Administration and Bureau
Email:[email protected]
youtube :-https://www.youtube.com/@AddisAbabaCityLandDevelopment
tiktok :- https://www.tiktok.com/@aa.land.administr?_t=8nxZie4Czi9...

የአዲስ አበባ መሬት መረጃ አገልግሎት(Addis Ababa land information service)

11 Jul, 21:43


የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በየካ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤በኮልፌ ቀራንዮ ፤በአቃቂ ቃሊቲ፤በአዲስ ከተማ፣ልደታ እና በጉለሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን በ(2merkato.com link:- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) በመግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነድ ግዢውን ከሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት መፈፀም ይችላሉ፤ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 7 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ በስልክ ቁጥር +251111570595 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
በድህረ ገፅ https//www.aalb.gov.et/መመልከት ይችላሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ መሬት መረጃ አገልግሎት(Addis Ababa land information service)

08 Jul, 15:01


ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በየካ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤በኮልፌ ቀራንዮ ፣በአቃቂ ቃሊቲ፤በአዲስ ከተማ ፣ልደታ እና በጉለሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በ(2merkato.com link :- https://addisland.2merkato.com afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ማንኛዉም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል፡፡
3. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
4. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
5. ተጫራቾች ሞልተዉ የሚያቀርቡት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘዉን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሰሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወረክ የተያያዘ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር ቢሮው አይጠየቅም፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣
7.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)
7.2 የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ
7.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ
7.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፒ (ደረሰኝ)
7.5 ኦርጅናል የአቅም ማሳያ ማስረጃ
7.6 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ
7.7 የውጭ አገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ /ቆንስላ ጽ/ቤት/ የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ በውልና ማስረጃ የፀደቀ መታወቂያ የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት፡፡
7.8 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ
7.9 ጨረታው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
7.10 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች
ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ኮፒ
ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7.11 በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ የቸረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በፖስታው ላይ በመጻፍ ሐምሌ 12/2016ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ስዓት ድረስ ብቻ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ በ05/11/16ዓ.ም፣08/11/16 ዓ.ም እና በ10/11/16 ዓ.ም ጠዋት በ3፡00 እና ከሰዓት በ8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል፡፡
9. ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለፀበት ከ15 የስራ ቀናት በኀላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ መ/ቤት ለባንክ በመላክ ወዳሰሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ በካሽ ያሰሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም፡፡
10. መስሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-

በስልክ ቁጥር +251111570595 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
https://www.aalb.gov.et/
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

2,654

subscribers

476

photos

10

videos