ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ ) @kesemay2mezigeb Channel on Telegram

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

@kesemay2mezigeb


ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ ) (Amharic)

እናንተ የከተማ ልጅ ህመም ወንዝ እና ከሰማይ መዝገብ የምንባርክ እንቅስቃሴ አሉ። በዚህ እድገት ከአፍሪካ፣ ሂንጆልና እስዩም ሌሎቹን መንገዶች ተወዳጁ። ከተነሳሁባቸው ፈላጊዎች አሉ። ከሰማይ መዝገብ ዝርዝር ውስጥ ከፋጁን ሺህ ብር ተመከራል። የከሰማይ መዝገብ ጥያቄዎች በተመለከተ ሰኞ እና አርብ በሐሙስ በትክክል ይገኛሉ። የእርሻው ከፋጁን ሺህ ብር ነው ። እነሆ ካብድ ልባራትን እና ደምሽን ልጅ ምጭ ለሚካፈበው ህመምን ስኬት እንዳበረኩት አገልግሎታችሁን እንዲሻር ወደ ከሰማይ መዝገብ አሳይሏችኋል።

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

08 Jan, 12:29


✴️ ከቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል የተላከ የግሸን ጉዞ ፦
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ጥር 21 ቀን የሚከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ እረፍት ( አስተርእዮ ) ምክንያት በማድረግ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም የንግሥ ክብረ በዓል ጉዞ አዘጋጅተናል ምዝገባም ጀምረናል የመሄድ አሳብ ካሎ በጊዜ ይመዝገቡ ፦
የጉዞ መነሻ ቀን ቅዳሜ ጥር 17 ቀን
የጉዞ መመለሻ ቀን አርብ ጥር 23 ቀን
የጉዞ ዋጋ 5,500 ብር መሆኑን እያሳወቅን የጉዞ ዋጋችን ግሸን ከገባንበት ቀን አንስቶ እስከምንወጣ ድረስ ሙሉ ማረፊያ እና መስተንግዶ አካቶ ነው ።
👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች ፦
▶️ ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202
ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415
ለበለጠ መረጃ ፦ 0963676767/0964020202
*https://t.me/kesemay2mezigeb

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

07 Jan, 11:03


"ከሦስትነቱ ሳይለይ መጣ፣ ከአንድነቱም ሳይለይ ወረደ። በላይ ሳይጎድል በማኅፀን ተወሰነ፤ በታችም ሳይጨመርበት ተወለደ። ከኀጢአት በቀር ፈጽሞ ሰው ሆነ። እንደ እግዚአብሔር እየሠራ እንደ ባርያ ታየ። ወንጌሉን ያስተማሩ እንደመሰከሩ እኛም በልቡናችን የጌትነቱን ምስጋና እንናገራለን።"
/ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ቁጥር 25 /
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! ( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

01 Jan, 05:34


👉 ከቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል የተላከ ፦
የዘንድሮ የጥምቀትን በዓል በጎንደር ማክበር የምትፈልጉ የፕሌን የደርሶ መልስ ዋጋ 11,000 ብር ገብቷል የመሄድ አሳብ ካሎ ከዚህ በላይ ዋጋው ሳይወደድቦ በጊዜ ይመዝገቡ እና ይቁረጡ ።
የመነሻ ቀን እንደ ፍላጎቶ አርብ ጥር 9 እና ቅዳሜ ጥር 10 ቀን
የመመለሻ ቀን እንደ ፍላጎቶ ሰኞ ጥር 12 ቀን እና ማክሰኞ ጥር 13 ቀን ።
👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች፦
▶️ ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202።
ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415።
👉 #ለበለጠ_መረጃ_ጉዞ_ለመመዝገቡ በእነዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ፦ 0964020202 /0963676767/ 0912699825
▶️ አዘጋጅ ፦ ቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

30 Dec, 13:22


እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ከታኅሣሥ 17 ቀን አንስቶ እስከ ታኅሣሥ 20 ቀን አዘጋጅተን የነበረው የቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓል አጠናቀን ትናንት ታኅሣሥ 20 ቀን ከምሽቱ 1:30 ላይ በሰላም ወደ አዲስ አበባ ገብተናል የመልዕኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከቱ ለሁላችንም በያለንበት ይድረሰን አሜን!!!
( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

16 Dec, 15:59


👉 ከቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል የተላከ ፦
የዘንድሮ የጥምቀትን በዓል በጎንደር ማክበር የምትፈልጉ በቅናሽ ዋጋ በ9,850 ብር የደርሶ መልስ የፕሌን ትኬት መቁረጥ ጀምረናል የመሄድ አሳብ ካሎ ዋጋው ሳይወደድቦ በጊዜ ይመዝገቡ እና ይቁረጡ ይህ ዋጋ እስከ የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን ድረስ የሚቆይ ነው ይፍጠኑ ።
የመነሻ ቀን ቅዳሜ ጥር 10 ቀን
የመመለሻ ቀን እንደ ፍላጎቶ ሰኞ ጥር 12 ቀን እና ማክሰኞ ጥር 13 ቀን ።
👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች፦
▶️ ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202።
ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415።
👉 #ለበለጠ_መረጃ_ጉዞ_ለመመዝገቡ በእነዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ፦ 0964020202 /0963676767/ 0912699825
▶️ አዘጋጅ ፦ ቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

09 Dec, 09:35


👉 ከቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል የተላከ የጉዞዎች መልዕክት ፦
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እሑድ ታህሳስ 6 ቀን የሚከበረው የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ ባሻኔ ቅድስት አርሴማ ገዳም የደርሶ መልስ ጉዞ አዘጋጅተናል የጉዞ ዋጋ 850 ብር ከእነ ሙሉ መስተንግዶ ።
👉 በቀጣይ ታኅሣሥ_19_ቀን_2017 ዓ.ም የሚከበረው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ ቁልቢ ጉዞ አዘጋጅተናል ።
✴️ #የጉዞ_መነሻ፦ # ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
✴️ #የጉዞ_መመለሻ፦ # ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
✴️ #የጉዞ_ዋጋ፦ ቁልቢ ላይ ማረፊያና መስተንግዶ ጨምሮ #3,500_ብር ።
እንዲሁም # ታኅሣሥ_29_ቀን_2017 ዓ.ም የሚከበረው ዓመታዊ የልደት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ ቅዱስ ላል ይበላ ገዳም ጉዞ አዘጋጅተናል ።
👉 #የጉዞ_መነሻ፦ # ታኅሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
👉 #የጉዞ_መመለሻ፦ # ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም
👉 #የጉዞ_ዋጋ፦ ላል ይበላ ላይ ማረፊያና መስተንግዶ ጨምሮ #7,000_ብር
በመጨረሻም ወደ በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር እና ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በምዝገባ ላይ ነን ማንኛውም ጉዞ የመሄድ አሳብ ካሎት በጊዜ ይመዝገቡ ።
👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች፦
▶️ ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202።
ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415።
👉 #ለበለጠ_መረጃ_ጉዞ_ለመመዝገቡ በእነዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ፦ 0964020202 /0963676767/ 0912699825
▶️ አዘጋጅ ፦ ቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

07 Dec, 10:34


እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በአክሱም ቆይታችን ላይ ከዘጠኙ ቅዱሳን መካከል ሰባቱን የተሳለምን ሲሆን በተጨማሪም በትግራይ የሚገኙ ሌሎች አድባራትና ገዳማትን ተሳልመናል እነርሱም፦
አክሱም መካነ ፆማዕት አቡነ ጴንጤሌዎን ገዳም
አክሱም ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ ገዳም
አድዋ መደራ አቡነ ገሪማ ገዳም
ይሐ አቡነ አፍፄ ገዳም
ዕደጋ ዓርቢ ደብረ ሀተታ ዘፀድያ አቡነ ጽሕማ ገዳም
ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም
ገርዓልታ ደብረ ጎህ አቡነ ይምዓታ ገዳም
ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ፅዮን ገዳም
አርባዕቱ እንስሳ ገዳም
አቡነ ሊባኖስ እና አቡነ አረጋዊ አንድነት ገዳም
በስዕለ ቅዱሳን የታጀበው ኢየሱስ ገዳም
ማይ ኪራሕ ቅዱስ ያሬድ ገዳም (የቅዱስ ያሬድ ዛፍ ያለበት)
ውቅሮ ማራይ ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም
ሽሬ ደብረ አባይ አቡነ ሳሙኤል ገዳም
ማኅበረ ዶጌ አቡነ አቤል ዘግብፅ ገዳም
ማኅበረ ዶጌ ዘፃድቃን ገዳም
ተንቤን ደብረ ዓሳ አቡነ ዮሐኒ ገዳም
መቀሌ ቅዱስ ሚካኤል ደብር
አላማጣ ቅድስት ሥላሴ እና ኢየሱስ ገዳም
ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ሞዓ ኢየሱስ ገዳም
ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ደብር
ደብረ ብርሃን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር
የተሳለምን ሲሆን በቪዲዮ የላክነው በአሁኑ ጉዞ ያልተሳለምነው በቀጣይ ዓመት ብንደርስ የምንሳለመው ከአክሱም በ12 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የሚገኘው እጅግ አስደናቂው ደብረ ቃል (ደረቃ) አቡነ ሊባኖስ ገዳም ሲሆን ፃድቁ ዋሻውን የፈለፈሉት ያለ ምንም የብረት መሳሪያ ሳይጠቀሙ አለትን በአለት በመጠቀም የሰሩ ሲሆን ይህ የሰሩበት የድንጋይ መሳሪያ ከዋሻ ውስጥ ሲወጣ ማንኛውም ሰው ካለበት ከማንኛውም ደዌ ወዲያውኑ ይፈወሳል። ( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

05 Dec, 10:14


ከህዳር 16 ቀን ጀምሮ በጋራ የማኅበራት ጥምረት የተዘጋጀው የአክሱም ፅዮን ገዳም የንግሥ ጉዞ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በሰላም አጠናቀን ወደ አዲስ አበባ ዛሬ ገብተናል ። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን አሜን !!! ። ( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

22 Nov, 10:29


እንኳን ለፆመ ነቢያት መቃረቢያ በሰላም አደረሰን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የዘንድሮ ፆመ ነቢያት የፊታችን እሑድ ኅዳር 15 ቀን ስለሚጀመር እና እሑድም ፆም ስለሆነ እራሳችንን አስቀድመን እናዘጋጅ አምላካ ነቢያት በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈፅመን መልካም የፆም ጊዜ ይሁንልን ። እርሶ በሚጠቀሙበት በማንኛውም ድህረ ገጽ ላይም ሼር በማድረግ ያሳውቁ ። ( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

19 Nov, 06:47


ቤተ-ጳውሊ አስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ አሰናድቷል !!!                 
መዳረሻ ቦታዎች :-- እርሰ_ገዳማት_ወአድባራት_አክሱም_ጽዮን።  ህዳር /21/ቀን 2017 ዓ.ም የሚከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ ጥንታዊቷ አክሱም ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም ለንግሥ የምናቀና ይሆናል።                                               
        👉 የጉዞ_መነሻ ቀን፦ ኅዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም።
👉 የጉዞ_መመለሻ ቀን፦ ኅዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም።
         👉 የጉዞ_ዋጋ፦ # 9,000 # ብር ሲሆን የተጠቀሰው ዋጋ አክሱም ላይ ማረፊያና መስተንግዶን ያካትታል::
         👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች፦
         👉 ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202።
   👉 ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415።
👉 ለምዘገባ እና ለተጨማሪ መረጃ ቀጥሎ በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች  ይደውሉ፦ 0964 020202 /0963 676767/ 0912 699825

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

14 Nov, 09:13


ታላቅ_መንፈሳዊ_ጉዞ_ወደ_እርሰ_ገዳማት_ወአድባራት_አክሱም_ጽዮን። #ሼር_ሼር_ሼር እናድርግ።
▶️ #ኅዳር_21_ቀን_2017 ዓ.ም የሚከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ ጥንታዊቷ አክሱም ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም የንግሥ ጉዞ አዘጋጅተናል ።
👉 #የጉዞ_መነሻ፦ #ኅዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም።
👉 #የጉዞ_መመለሻ፦ #ኅዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም።
👉 #የጉዞ_ዋጋ፦ አክሱም ላይ ማረፊያና መስተንግዶ ጨምሮ #9,000_ብር።
👉 የጉዞ አዘጋጅ፦ ቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል።
👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች፦
▶️ ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202።
ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415።
👉 #ለበለጠ_መረጃ_ጉዞ_ለመመዝገቡ በእነዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ፦ 0964020202 /0963676767/ 0912699825

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

07 Nov, 11:38


ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የ2017 ዓ.ም የመስከረም 21 ቀን የግሸን ጉዞ ላይ ለአድባራት እና ለገዳማት፤ለመነኮሳት አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ለአብነት እና ለአስኳላ ተማሪዎች እንዲሆን በማቴሪያል እርዳታ የለገሱ ሰዎች በተመለከተ ክፍል ሁለት የቀረበ ፦
ወ/ሮ ዙሪያሽ አርጋው እና ወ/ት ምሥራቅ አለሙ ለ23 ለመነኮሳት አባቶችና እናቶች የሚሆን የገዳማት ወይባ ፎጣ ለግሰዋል ።
የሻሸመኔ ተጓዦች በአቶ ወንድዬ አምሳለ አስተባባሪነት ለ200 ህፃናት የሚሆን አዲስ ሙሉ ልብሶችን ለግሰዋል ።
ወልደ ገብርኤል ለሴት እናቶች የሚሆን 20 ፍሬ አዲስ የተሰፋ ሺቲ ጨርቅ ለግሰዋል ።
በኃይለ ጊዮርጊስ በኩል የ20 ሺ ብር የሰም ጧፍ ለግሰዋል ።
አቶ ቢኒያም ጌታቸው ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የመጣ ለእያንዳንዳቸው አድባራትና ገዳማት የሚሆን በገንዘብ ሲተመን 40 ሺ ብር ያክል ያወጣ ቅብዓ ቅዱስ ለግሰዋል ።
ክንፈ ገብርኤል ካህናት በቅዳሴ ሰዓት የሚባርኩበት ትልቁ የመባረኪያ የእጅ የእንጨት መስቀል ብዛት አንድ ፍሬ ለግሰዋል ።
▶️ በቀጣይ የገንዘብ እርዳታ በመለገስ አስተዋፅኦ ያደረጉት ሰዎች ሪፖርተር እናቀርባለን ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል ይቀጥላል ፦

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

30 Oct, 16:14


በምዕራብ ሐረርጌ በዳሮለቡ ወረዳ ለሚገኘው የመቻራ መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያንን የመግቢያ በር እያሰራን እንገኛለን የቀረን የፊኒሺንግ ስራ ብቻ ነው ይህንን ስራ ለማጠናቀቅ የሚቀረን 7 ቀን ብቻ ነው እንደሚታወቀው አመታዊው የመድሃኔአለም ክብረ በዓል የሚከበረው የዛሬ ሳምንት ነው እና ለመጨረስ የእናንተ እርዳታ በእጅጉ ያስፈልገናል እና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ የአቅማችሁን እንሆ በረከት በማለት የበረከቱ ተሳተፊ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን
✴️ 1️⃣0️⃣0️⃣0️⃣4️⃣5️⃣3️⃣0️⃣9️⃣5️⃣5️⃣2️⃣9️⃣
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
▶️ ለበለጠ መረጃ ፦ 0948222323

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

29 Oct, 13:49


ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የ2017 ዓ.ም የመስከረም 21 ቀን የግሸን ጉዞ ላይ ለአድባራት እና ለገዳማት፤ለመነኮሳት አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ለአብነት እና ለአስኳላ ተማሪዎች እንዲሆን በማቴሪያል እርዳታ የለገሱ ሰዎች በተመለከተ፦
አባታችን ቀሲስ ኃይሉ ለአድባራት እና ለገዳማት የሚሆን 10 ሺ ጧፍ በማስተባበር ለግሰዋል
አቶ ቴዎድሮስ በቀለ 5 ካርቶን ( 500 ፍሬ ) ደብተር እና የተሟላ እስክሪብቶ
ወ/ት ፍሬ ገነት ተገኑ 2 ደርዘን ደብተር እና 5 እስክሪብቶ
ወ/ሮ ብርቄ ( ከደብረ ብርሃን ) 100 ኪሎ ዕጣን
አቶ ግርማቸው ተክሌ 3 ጣቃ ( 180 ፍሬ ) ፎጣ
ወ/ሮ ማርታ ሀብታሙ 2 ጣቃ ( 120 ፍሬ ) ፎጣ እና 3 መቶ ፍሬ የሰም ጧፍ እንዲሁም 5 ኪሎ ዕጣን እና 5 ኪሎ ዘቢብ
ወ/ሮ አዳስ ገብሩ 2 መቶ ፍሬ የሰም ጧፍ
አቶ ሚክያስ ( ገብረ ሥላሴ ) 5 ኪሎ ዘቢብ
አቶ ጌታቸው ወልዴ 4 መቶ ፍሬ የሰም ጧፍ እና 8 ኪሎ ዘቢብ
ወ/ሮ ጃፋ ታደለ 100 ፍሬ የሰም ጧፍ
አቶ ተሾመ ፀጋዬ ለ300 መቶ አድባራት እና ገዳማት ለእያንዳንዳቸው የሚሆን አንዳንድ ባኮ ሻማ
ወ/ት ፅጌረዳ ገብረ ሚካኤል ለዕጣን እና ለዘቢብ ማሸጊያ የሚሆን ባለ ሁለት ኪሎ ላስቲክ 5 ኪሎ እና 500 ፍሬ ትልቁ ጥቁር ፌስታል
አቶ ሙላት ተሾመ 125 ኪሎ ዘቢብ እና ለአብነት ተማሪዎች የሚሆን 6 ፍሬ የተደጎሰ መዝሙረ ዳዊት
መርጌታ እንግዳ ለአብነት ተማሪዎች የሚሆን አንድ ፍሬ ፆመ ድጎ መፅሐፍ
አቶ አስቻለው ካሳዬ ለአብነት ተማሪዎች የሚሆን አንድ መፅሐፍ ቅዱስ ፤ አንድ አርባዕቱ ወንጌል እና አንድ ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል
ወለተ ዩሐንስ 200 ፍሬ የሰም ጧፍ እና 2 ጥላ ለግሰዋል ።
▶️ ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል ይቀጥላል

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

16 Oct, 14:27


በግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ገዳም እና በተለያዩ አድባራት እና ገዳማት ለረጅም ዓመታት በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት እንዲሁም ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምን ለመሳለም የበቁት በ1921 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ተጉለት ወርቅ ጉር አካባቢ የተወለዱት ሊቀ ትጉሃን ባህታዊ አባ መፍቀሬ ሰብዕ በተወለዱ በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም አርፈዋል አምላከ ቅዱሳን ነፍሳቸውን በቅዱሳን እቅፍ ያኑርልን የቀብር ስነ ስርዓት በታላቁ በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም እሑድ ጥቅምት 10 ይፈፀማል ተብሏል በረከታቸው በሁላችንም ላይ ይደርብን ። ( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

12 Oct, 11:05


✴️ ከቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል የተላከ ጉዞ ወደ በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ጥቅምት 16 ቀን ተነስተን ጥቅምት 24 ቀን የምንመለስበት እስከ ባህር ዳር ድረስ በፕሌን በመጓዝ ከባህር ዳር በኋላ ደግሞ የመኪና ትራንስፖርት በመጠቀም ጉዞ ወደ በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር መንፈሳዊ ጉዞ ያዘጋጀን ሲሆን አጠቃላይ ዋጋ 15,000 ብር ።
▶️ ቀኑ ሲቃረብ የፕሌን ዋጋ ስለሚጨምር እኛም ዋጋ ቢጨምር አላፊነት ስለማንወስድ የመሄድ አሳብ ካሎት እና ከወሰኑ በቶሎ ይመዝገቡ እንላለ ።
👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች ፦
▶️ ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202
ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415
ለበለጠ መረጃ ፦ 0963676767/0964020202/0918222560
*https://t.me/kesemay2mezigeb

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

05 Oct, 14:24


እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ያዘጋጀነው የቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ በሰላም አጠናቀን ትናንት ከምሽቱ 11:40 ላይ ወደ አዲስ አበባ ገብተናል የግሸኗ ቅድስት ማርያም በረከት በሁላችንም ላይ ይደር ። ( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

21 Sep, 15:22


✴️ ከቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል የተላከ
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ መስከረም 15 ቀን ያዘጋጀነው የግሸን ገዳም ጉዞ የሞላን ሲሆን በቀጣይ መስከረም 17 ቀን የሚነሳው ቁጥር ሁለት መኪና ምዝገባ ጀምረናል በጊዜ ይመዝገቡ ፦
የጉዞ መነሻ ቀን መስከረም 17
የጉዞ መመለሻ ቀን መስከረም 24
የጉዞ ዋጋ 6,500 ብር መሆኑን እያሳወቅን የጉዞ ዋጋችን ግሸን ከገባንበት ቀን አንስቶ እስከምንወጣ ድረስ ሙሉ ማረፊያ እና መስተንግዶ አካቶ ነው ።
በተጨማሪም በግሸን ጉዞ ላይ በየዓመቱ ለአድባራት እና ለገዳማት ጧፍ ፤ ዕጣን ፤ ዘቢብ ሻማ እና ነዋየ ቅድሳት ፦
ለመነኮሳት አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ለነዳያን ፎጣ ማልበስ ፤ ምግብን መመገብ
ለአብነት ተማሪዎች መንፈሳዊ ቅዱሳት መፅሐፍ መለገስ
ለአስኳላ ተማሪዎች ደብተር ፤ እስክሪብቶ ፤ እስራስ እና ቦርሳ መስጠት መርዳት ስለሆነ እርሶም ልቦናዎ በፈቀደው ላይ ዕርዳታዎን ይለግሱ ።
👉 የመመዝገቢያ ቦታዎች ፦
▶️ ቁጥር 1 የመመዝገቢያ ቦታ፦ ፒያሳ የሚገኘው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ባስገነባው ሕንፃ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት 2ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202
ቁጥር 2 የመመዝገቢያ ቦታ ፦ መገናኛ መተባበር ሕንፃ ላይ 4ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415
ለበለጠ መረጃ ፦ 0963676767/0964020202
*https://t.me/kesemay2mezigeb

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

19 Sep, 05:34


👉 በግሸን አካባቢ ለሚገኙ ለአብነት ተማሪዎች እስከ መስከረም_13_ቀን_2016 ዓ.ም ሁላችንም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የበኩላችንን አስተዋጾ እናድርግ አደራ ።
1,መዳልዎ አልባብ የሚያስፈልገወሸ ብዛት 60 የአንዱ ዋጋ 1500 ጠቅላላ ዋጋ 1500*60= 90,000 ብር።
2,መጽሐፈ ቅዳሴ ዘደብረ ዓባይ የሚያስፈልገው ብዛት 90 የአንዱ ዋጋ 2,300 ጠቅላላ ዋጋ 2300*90=  207,000 ብር።
3,ጾመ ድጓ የሚያስፈልገው ብዛት 20 የአንዱ ዋጋ  650*20= ጠቅላላ ዋጋ 13,000 ብር።
4,ዝክረ ቃል የሚያስፈልገው ብዛት 30 የአንዱ ዋጋ 1500 ጠቅላላ ዋጋ 30*1500= 45,000 ብር።
5,መዝሙረ ዳዊት የሚያስፈልገው ብዛት 20 የአንዱ ዋጋ 700 ብር ጠቅላላ ዋጋ  20*700= 14,000 ብር።
6,ሰዓታት የሚያስፈልገው ብዛት 15 የአንዱ ዋጋ 300 ጠቅላላ ዋጋ 15*300= 4,500 ብር።
7,አንቀጸ ቅዳሴ የሚያስፈልገው ብዛት 5 የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ 5*750= 3,750 ብር።
8,ወርኀ በዓል የሚያስፈልግ ብዛት 5 የአንዱ ዋጋ 950 ጠቅላላ ዋጋ 5*950= 4,750 ብር።
9,ያሬድ ግስ የሚያስፈልግ ብዛት 10 የአንዱ ዋጋ 700 ጠቅላላ ዋጋ 10*700= 7000 ብር።
10,መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስፈልገው ብዛት 5 የአንዱ ዋጋ 900 ብር ጠቅላላ ዋጋ  5*900= 4,500 ብር።
👉 #አስተባባሪ፦ ቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል ።
👉 በአገር ውስጥ በባሕር ማዶ ያላችን መጽሐፍቶችን ገዝታችሁ ለመርዳት የምትፈልጉ ምዕመናን በእነዚህ ቁጥር #0911414852፣ #0912699825። #በኢሞ_በዋትሳፕ_በቴሌግራም(#@Teamhokidusan) ማውራት ትችላላችሁ ከበረከቱም የምትሳተፉ ስመ ክርስትናችሁ አባቶች በጸሎት እዲያስባችሁ ላኩልን።

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

18 Sep, 08:01


ይህን የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም የገዳሙ ማስታወቂያ ሁላችንም ሼር እናድርግ ። ( ከቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል )

ከሰማይ መዝገብ Kesemay Mezigeb ( ቤተ ጳውሊ )

13 Sep, 15:40


ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል የተላከ ባሳለፍነው ዓመት መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተከበረው የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ገዳም ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ለአድባራትና ለገዳማት ፤ ለመነኮሳት እናቶችና አባቶች እንዲሁም ለነዳያን በተጨማሪም ለአስኳላ ተማሪዎች አጠቃላይ የተለገሱ የ2016 ዓ.ም የገንዘብ ገቢ እና ወጪ ሪፖርት ለማስታወስ ያክል በድጋሚ እናቀርባለን ።
አጠቃላይ የተሰበሰበ ገቢ 169,218 ብር
አጠቃላይ የወጣ ውጪ 146,200 ብር
ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ሳይከፈል የዞረ ዕዳ እና በ2016 ዓ.ም ተከፍሎ የተጠናቀቀ 16,656 ብር
▶️ 169,218 - 146,200 - 16,656 = 6,362 ብር
✴️ በቀጥታ ከወጪ ቀሪ ለ2017 ዓ.ም የተገኘ ትርፍ 6,362 ብር መሆኑን እያሳወቅን ሙሉ የወጪ ገቢ መረጃ ማወቅ ካስፈለገን በዚሁ ከሰማይ መዝገብ የቴሌግራም ቻይናል ላይ ወደ ኋላ እየተመለስን ማየት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን እናሳውቃለ ።
በቀጣይ ለመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለግሸን ጉዞ እርሶ አሁን በምስሉ ላይ ላዩት አድባራት እና ገዳማት ዕጣን ፤ ጧፍ ፤ ዘቢብ ፤ ሻማ እንዲሁም ቅዱሳት መፅሐፍ ፤ ለመነኮሳት እና ለነዳያን ፎጣ ፤ ለአብነት ተማሪዎች እና ለአስኳላ ተማሪዎች ደብተር ፤ እስክሪብቶ ፤ እስራስ ፤ ቦርሳ ምን ለመለገስ አስበዋል በረከቱን ይሳተፉ አደራ አደራ አደራ ።
( ከቤተ ጳዉሊ የጉዞ ወኪል )

1,634

subscribers

1,100

photos

679

videos