ማር ይስሐቅ @mar_yisihak Channel on Telegram

ማር ይስሐቅ

@mar_yisihak


" መንፈስ ግን በግልጥ.....አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል'' 1ኛ ጢሞ 4÷1 ስለዚህ እንንቃ!!!

ማር ይስሐቅ (Amharic)

ማር ይስሐቅ (Mar Yisihak) ከሆነ የለምንም የአምባሽ ተናጋሪዎች በትክክል የምሳሌ ተመሳሳይ ሥራዎችን እንንቃት። በዚህ እውነት አጋንንትን ትምህርት ለመመልከት ባለስልጣን ጉዳዮች ዋጋ እና ገና እንዲላሊቱ ለመሮጥ ተስታል። ማር ይስሐቅ በከፍተኛ ስራው ላይ በየዕለቱ ለመረጃ ዳይስን መስጠታችንን በማስገባት የምሳሌ ትእዛዙን እንግዳ በመደበኛ ውሽጣዊ ሥራዎች ምክንያት እንዲያገኙበት ይችላል። እናወዝን በድርጅት መደብሽያችን ከማየቅ በፊት እናስተፋለሁ።

ማር ይስሐቅ

04 Jan, 11:48


🎁 🎁 🎁  የገና አባት 🎁 🎁 🎁

ለኦርቶዶክሳዊ ሰው ቅዱሳንን መምሰል ክርስቶስ ጋር ለመድረስ መንገዱ ነው።

እንግዲያውስ በዚህ የልደት በዓል የመስጠት አባት የሆነ የገና አባትን (ቅዱስ ኒቆላዎስን) በተግባር እንምሰለው፡፡

ቅዱሱ በድሆች መንደር ምጽዋትን እንደሰጠ እኛም ለበዓለ ልደት የተቸገሩትን በመርዳት፣ ለወዳድ ዘመዶቻችን የምሥራችን በማሰማት..... እናክብር።

በቃል የገና አባት ከማለት ባለፈ እንደ የገና አባት (ቅዱስ ኒቆላዎስ) በስጦታ የገና አባትን እንምሰል፡፡

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

28 Dec, 07:20


እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሰን!

አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን እንዲሁም ዳንኤልን የረዳ መልአክ እኛንም ይርዳን፣ ይባርከን፣ ከኃጢአት በቀር የልቦናችንን ፍላጎት ይፈጽምልን!

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።”

መዝሙር 34፥7

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

25 Nov, 03:13


ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው። በግብጻውያን ልዩ ቦታ አለው ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም። ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው። በተለይ ለታመመ ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ ባለ በጎ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው።

ቅዱስ ሚናስ ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው። በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ፣ በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ፣ በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ፣ ሃብትን ክብርን ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ፣ በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ በአላውያን ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ኅዳር 15 በሰማዕትነት ያረፈበት ሲሆን ሰኔ 15 ደግሞ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው።

#በአንድ_ወቅት፦
ዐሥራ ስምንት ቀሳውስት በሥራ ጉዳይ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛን ለማነጋገር መርዩጥ ወደ ሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ጉዞ ጀመሩ። ቀሳውስቱ በጉዞአቸው መንገድ ስተው ሲባዝኑ ከአንድ የበረሓ ሰው ጋር ተገናኙ።

የበረሓው ሰው መርዩጥ የሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ለመሄድ መንገድ እንደሳቱ ቀድሞ ተረድቶ ነበርና "የማር ሚናስን ገዳም ነው የምትፈልጉት? በማለት ይጠይቃቸዋል። እነርሱም ችግራቸውን እንዴት እንዳወቀ በልባቸው እያደነቁ "አዎን" አሉት። የበረሓው ሰውም እየመራ ከገዳሙ አደረሳቸው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛም ወደ በር ወጥተው ተቀበሏቸው።

ከዚያም "ምነው ዘገያችሁ? መንገድ ሳታችሁ እንዴ?" ብለው እንደ ቀልድ ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን! በጣም ተቸግረን ሳለን ይህ የበረሓ ሰው ደርሶልን መንገዱን አሳየን" ብለው ወደ ሰውየው ለማመልከት ዘወር ሲሉ እርሱ በአካባቢው የለም። አቡነ ቄርሎስም "መንገድ እንደጠፋችሁ ስለተረዳሁ ሚናስን ልኬላችሁ ይዟችሁ የመጣው እርሱ ነው" አሏቸው።

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን!!

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

23 Nov, 14:43


"ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፤ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።

የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል።

ከዓይናችን ፊት ምግብ፥ ከአምላካችንም ቤት ደስታና እልልታ የጠፋ አይደለምን? ዘሩ በምድር ውስጥ በሰበሰ፤ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎተራዎቹም ፈርሰዋል።"
ኢዮኤል 1፥14-17

ማር ይስሐቅ

23 Nov, 14:00


ከህዳር 15 (እሑድ) ጀምሮ የገና ጾም (የነቢያት ጾም) ይጾማል።

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

11 Nov, 09:06


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የቤተክርስቲያን ምርቃት እና የጉባኤ ጥሪ
ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
ኅዳር 6-8 (ከአርብ እስከ እሑድ)
ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ስለሚመረቅ
በጠዋቱም በማታውም መርሐ ግብር ተገኝተው ወንጌል እየተማሩ እግዚአብሔርን ያመስግኑ፡፡
አድራሻ፦ ከጦር ኃይሎች ዝቅ ብሎ የቀድሞው 3 ቁጥር ማዞሪያ ቶታል

ለወዳጅዎ ያጋሩ

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

09 Nov, 10:47


ማኅሌተ ጽጌ

ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማይ ወምድር፤
ከመ በሕፅንኪ ያስምክ ፍቁር ።

ትርጉም

የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዥንጉርጉር የሆነ ንጹሕ ተዓምርሽ በወርቅ አምሳል የተሰራ ነው፤

እነሆ የተወደደ መልካም ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ፤

የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በእቅፍሽ እንዲጠጋ (እንዲንተራስ) በእርሱ አማጽኝ ።

ምስጢር

ቀይና ነጭ ቀለም ያለ'ው ማለቱ
ቀይ በትስብእቱ (በሥጋው)
ነጭ በመለኮቱ
ማለትም ፍጹም ሰው፤ ፍጹም አምላክ
ዥንጉርጉርም ያለው ሰው እና አምላክነቱን ነው።

ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሰራ ነው ሲል ወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ነውና እመቤታችንም ንጽሕተ ንጹሐን ናትና። | ኵለንታሃ ወርቅ |

ወርኀ ጽጌ አልቋል ሲል ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ስሙር አለ የሰማይና የምድር ንግሥት
(መዝ 44 )

የመጨረሻ ሳምንት ነውና እንበርታ!

አሜን !


@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

09 Nov, 09:41


ማኅሌተ ጽጌ 6ኛ ሳምንት.pdf

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኅ ታኅሣሥ
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ጥር
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ የካቲት
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

07 Nov, 06:50


ስንክሳር ዘወርኀ ጳጉሜን
ግዕዝ እና አማርኛ

ማር ይስሐቅ

06 Nov, 13:01


#መድኃኔዓለም

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

1. የእርጋታ መምህር ነው።

ከእርጋታው የተነሣ "የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤስን የጧፍ ክርም አያጠፋም" ተብሏል (ማቴ.12፥20)።

2. የትሕትና መምህር ነው

"ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።" (ማቴ.11፥29)

3. የይቅርታ መምህር ነው።

በመስቀል ተሰቅሎ ይቅርታን ለሰው ልጅ ያደለ እርሱ ነው።
"ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።" እንዲል (ሉቃ.23፥34)።

4. የሰላም፣ የፍቅር፣ የትዕግሥት፣ የሰማዕትነት በጠቅላላው የመልካም ሥራዎች ሁሉ መምህር እርሱ ነው።

እርሱን ሁልጊዜ ማሰብ ለነፍስ ዕረፍት ነው። እኛም ዋና አብነታችን እርሱ ስለሆነ መልካም ሥራዎችን ሁሉ አባታችንን እርሱን መስለን እንሥራ።

እንኳን አደረሳችሁ
@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

04 Nov, 14:48


ይህን ያወቁ ኖሯል?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስፍረ ሰዓት(ሰዓት አጣቆጠር)

👉 የመስከረም ወር
ቀኑ 12 ሰዓት ሌሊቱ 12 ሰዓት ነው፡፡

👉 የጥቅምት ወር
ቀኑ 11 ሰዓት ሌሊቱ 13 ሰዓት ነው፡፡

👉 የህዳር ወር
ቀኑ 10 ሰዓት ሌሊቱ 14 ሰዓት ነው፡፡

👉 የታህሳስ ወር
ቀኑ 9 ሰዓት ሌሊቱ 15 ሰዓት ነው፡፡

👉 የጥር ወር
ቀኑ10 ሰዓት ሌሊቱ 14 ሰዓት ነው፡፡

👉 የየካቲት ወር
ቀኑ 11 ሰዓት ሌሊቱ 13 ሰዓት ነው፡፡

👉 የመጋቢት ወር
ቀኑ 12 ሰዓት ሌሊቱ 12 ሰዓት ነው፡፡

👉 የሚያዝያ ወር
ቀኑ 13 ሰዓት ሌሊቱ 11 ሰዓት ነው፡፡

👉 የግንቦት ወር
ቀኑ 14 ሰዓት ሌሊቱ 10 ሰዓት ነው፡፡

👉 የሰኔ ወር
ቀኑ 15 ሰዓት ሌሊቱ 9 ሰዓት ነው፡፡

👉 የሐምሌ ወር
ቀኑ 14 ሰዓት ሌሊቱ 10 ሰዓት ነው፡፡

👉 የነሐሴ እና ጳጉሜን ወር
ቀኑ 13 ሰዓት ሌሊቱ 11 ሰዓት ነው፡፡

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

04 Nov, 03:18


“ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤”

1ኛ ቆሮንቶስ 8፥2

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

01 Nov, 19:42


“በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።”

ምሳሌ 10፥19

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

01 Nov, 12:47


ልትመጸውት ብትወድ ጥረህ ግረህ ካገኘኸው መጽውት፡፡

ማር ይስሐቅ

@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

31 Oct, 05:02


https://t.me/Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

14 Sep, 18:21


https://t.me/Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

26 Jul, 09:59


“ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?”
ዕብራውያን 1፥14

እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስን እና ቅድስት ኢየሉጣን ላዳነበት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደርሳችሁ!

https://t.me/Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

17 Jun, 04:49


📖ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትራችሁ የምትመጡ ይህን ልመናዬን ስሙ፤ ሰነፍ የኾኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድን አስፈላጊነት አስተምሯቸው፡፡ የትምህርቷን ውበት ቀምሳችኋልና እናንተ ያወቃችሁትን ሳያውቁ እንዳይቀሩ፡፡

     ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ የነፍስ ፍርድ ቤት አይደለችም። የኃጢአትን ስርየት ትሰጣለች እንጂ ኃጢአትን አትፈርድም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደምናገኘው ምስጋና በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ደስተኞች ደስታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ የሚጨነቁት፤ ያዘኑት፣ ሰላምን ያገኛሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፤ የተቸገሩ ሰዎች እፎይታ ያገኛሉ፤ ኹሉም ከተሸከሙት ያርፋሉ፡፡

    ቤተክርስቲያን ኹሉን ታቅፋለች፡፡ ውስጥ ከሆንክ ተኩላው አይገባም፣ ብትሄድ ግን አራዊቶች ይይዙሃል፡፡ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፣ ከቤተክርስቲያን የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን መዳንህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከድንጋይ ትከብዳለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከዓለም ትስፋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አታረጅም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እራሷን ታድሳለች፡፡

"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ በመከራና በኃጢአታችሁ የከበደ ኹሉ' ወደ እኔ ኑ" ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡" (ማቴ ፲፩፥፳፰)
ይህንን ድምጽ ከመስማት የበለጠ ምን ደስታን ሊሰጠን ይችላል? ከዚህ ግብዣ የበለጠ ጣፋጭ ምንድነው? ጌታ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጠራችሁ ለታላቅ ግብዣ ነው፡፡ ከትግል ወደ እረፍት፣ ከስቃይ ወደ እፎይታ ያሸጋግራችኋል፡፡ ከኃጢአታችሁ ሸክም ያገላግላችኋል፡፡ ጭንቀትን በምስጋና፣ ሐዘንንም በደስታ ይፈውሳል፡፡ለክርስቶስ ከሚኖረው በቀር በእውነት ነጻ፣ በእውነት ደስተኛ የሆነ ማን ነው? እንዲህ ያለው ሰው ክፋትን ኹሉ ያሸንፋል ምንም አይፈራም!ቤተ ክርስቲያን ለኹሉም መጠጊያ ሆና ቆማለች፡፡

   የአምላክን ትዕዛዝ የምትፈጽም መልካም ሰው ከሆንክ ቅድስናህን ለመጠበቅ ግባ፤ ኃጢአተኛ ከሆንህ መዳንን ለማግኘት እርምጃህን ፈጠን አድርገው:: የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይሰሙስ እንዴት ነፍስን ወደ መልካም መንገድ መምራት ይቻላል?የእግዚአብሔር ቃል 'ብርሃን' በመባል ይጠራል፤ ፀሐይ ከምታፈልቀውና እኛም ከምናየው ብርሃን፣ እጅግ በጣም የከበረ ብርሃን፣ የነፍሳችንን ጥልቀት የሚያበራ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ እውነት እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው::"

    ከእናንተ መካከል በታማኝነት ቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉ፤ 'ስራ በዛብኝ፣ ልመጣ አልችልም' እንዳይሉ ሌሎቹን ምከሩ፡፡ ወደ ንጉሡ ግብዣ የተጋበዙ ግን መምጣት ያልቻሉትን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ አንደኛው አምስት ጥማድ በሬዎችን ሊገዛ እንደሄደ ተናገረ፣ ሌላው አዲስ መሬትን ሊገዛ እንደሄደ ሲናገር ሌላው ደግሞ ሚስት ማግባቱን ተናገረ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ንጉሡ ግብዣውን ንቀው ስለቀሩ የሚታገሳቸው ይመስልሃል? እናም ንጉሡን በሰበብ አስባቡ አታናዱት፡፡

  ከጊዜህ ላይ አንድ ሰዓት ያህል እንኳን መቆጠብ ያቅትሃል? ቤተክርስቲያንን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሥራ መሄድ በእውነት ይህን ያህል ከባድ ነውን? አንድ ሰው ወርቅ፣ ብር፣ ማር ወይም ወይን በነጻ እየሰጠ ነው ቢባል፤ ማንም ሳይቀድማችሁ ለመድረስ አትቸኩልም? ነገር ግን፣ ከወርቅ የሚበልጥ፣ ከማርም ከወተትም የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማድመጥ ወደ ቤተክርስቲያን የምትመጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡

   ስለዚህም፣ ይህን ችላ ማለታችሁን አውግዣለሁ፤ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ያላችሁን ግድየለሽነት እቃወማለሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቶቿ በመራቃችሁ፣ በውስጣችሁ የእግዚአብሔር ፍራቻ የለም፤ እግዚአብሔርን የማትፈራ ነፍስም ለኃጢአት የተገዛች ትሆናለችና ነፍሳችንን እንጠብቃት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው

https://t.me/Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

07 May, 16:53


1000608839295

Asefa Abera & Tezerach Fikre

ማር ይስሐቅ

28 Apr, 16:45


ወደ ፈጣሪያችን በቃል ሳይሆን በተግባር የምንመለስበት ሳምንት ይሁንልን!
@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

12 Apr, 20:31


https://www.tiktok.com/@dn_yishak_kelemework/photo/7356715062100233478?_r=1&u_code=e5550g2911k2jl&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e55503klgbl4cc&share_item_id=7356715062100233478&source=h5_m&timestamp=1712932199&user_id=7171054631740982278&sec_user_id=MS4wLjABAAAA4GlMFMdzyEXbekarR6OKQYnozmr5pdfk8Fo_q8A8wETkQ2x6b-ZbsKQVuA_5cskO&aweme_type=150&pic_cnt=1&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7323179210347579141&share_link_id=4ab1efc5-1d6b-4611-9ca2-2712a0c10e39&share_app_id=1233&ugbiz_name=UNKNOWN&ug_btm=b8727%2Cb2878&enable_checksum=1

ማር ይስሐቅ

09 Apr, 06:04


እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ ፣ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ 29:27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከነዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር

በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም
ዓይን ያላየችውን
ጆሮ ያልሰማውን
በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

መንፈሳዊው መንገድ
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንደ ጻፉት
አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።
@Mar_Yisihak

ማር ይስሐቅ

08 Apr, 17:06


እንዴት አረፈዳችሁ ?
    2 ቀን ብቻ ነው የቀረው !!!
cbe 1000214420477

(በመርዳት እና ሼር በማድረግ ተባበሩኝ) ወንድማችን  ቢኒያም ሐለፎም
የ 23 ዓመት ወጣት ሲሆን
ተወልዶ ያደገውም በአዲስ አበባ(አየር  ጤና )
ሲሆን በአሁን ሰዓት ላይ በሊቢያ ስለተያዘብን እሱን በህይወት ለማስለቀቅ 1,200,000(አንድ ሚልየን ሁለት መቶ ሺ ብር  ) ስለተጠየቅንና የሰጡን ጊዜ የ 1 ሳምንት ጊዜ ብቻ ስለሆነ፤ ቤተሰቦቹ ደግሞ የመክፈል አቅም ስለሌለን
እንድታተርፉልን በፈጣሪ ስም እንማጸናለን።
ሁላችሁም ከጎናችን ሁኑ 🙏🙏
50 ሎሚ ለ 50 ሰው ጌጥ ነው ።

ማር ይስሐቅ

08 Apr, 05:45


ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫው🙏🏽
***

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ አሐዱ አምላክ አሜን
++++++++++++
የጋራ የስምምነት ነጥቦች
ፍኖተ ጽድቅ በአንድ በኩል የአቶ ጸጋዬ ደበበ ሱፐር ደብል ቲ ሮዳስ የሮቶና ቀለም ፋብሪካ ሠራተኞች የመንፈሳዊ ትምህርት መማሪያ ማኅበር ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የማኅበሩ የዩቱብ ሚዲያ ስያሜ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በማኅበሩ አገልግሎትና የማኀበሩ ሚዲያ በአሠራጫቸው ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ላይ የትምህርተ ሃይማኖት፣ የሥርዐተ አምልኮና የትውፊት ጥያቄዎች ሲቀርቡበትም ነበር፡፡
በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ጉባኤና በጉባኤው በሚመደቡ መምህራንና መዘምራን፣ በጉባኤው በሚሰጡ ትምህርቶችና በሚዘመሩ መዝሙራት፣ በመዝሙር መሣሪያዎች አጠቃቀምና የአዘማመር ስልቶች ላይ ጥያቄዎች ሲነሡና አንዳንድ ጊዜም በአንዲት የቤተ ክርስቲያን ልጆች መካከል የልዩነትና የውዝግብ ምክንያት ሲሆንም ታይቷል።
ይህን ተከትሎም የፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነትን፣ ሥርዐተ አምልኮንና ትውፊትን ብቻ ማዕከል አድርጎ ማገልገል በሚያሰችሉት ጉዳዮች ላይ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምህራነ ወንጌልና በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን የሚሠሩ ወንድሞች፤ የፍኖተ ጽድቅ መሥራች ከሆኑት ከአቶ ጸጋዬ ደበበና ከማኅበሩ አመራሮች ጋር ለበርካታ ጊዜያት ውይይትና ምክክርም ሲያደርጉም ቆይተዋል፡፡ የተለያዩ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱም ሲያሳስቡም ሰንብተዋል።
ይልቁንም በማኅበራዊ ሚዲያ የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን በፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የሚሠሩ ወንድሞች ፍኖተ ጽድቅን በተመለከተ ሰነድ አዘጋጅተውና ፍኖተ ጽድቅም በሰነዱ ለተነሡ ጥያቄዎች ማብራሪያ እንዲሰጥም ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ መልኩ ለረጅምና ለተደጋጋሚ ጊዜያት በተደረጉት ውይይቶችና ምክክሮች የፍኖተ ጽድቅ መሠረታዊ ችግሮች ተብለው የተለዩት አምሰት ነበሩ፡፡ መተማመን እና ስምምነት ላይ የተደርስባቸውም ችግሮች ፦
**
1)
ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርትን አዛብቶ   ማስተማር፤
2) ከኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና የአዘማምር ይትባሃል ያፈነገጡ መዝሙራትን መዘመር፤
3) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቀኖኗ ከፈቀደቻቸው የዜማ መሣሪያዎች ውጭ የሙዚቃ መሣሪያዎችን መጠቀም፤
4) በማኅበሩ ጉባኤ ላይ የሃይማኖት ነቀፋ ያለባቸው አንዳንድ መምህራን እንዲያስተምሩ መመደብ፤
5) በፕሮቴሰታንት መድረኮች ላይ ሲዘምሩ የነበሩ ዘማርያን በማኀበሩ የኅብረት መዘምራን ውስጥ አባል ሆነው መገኘታቸው ናቸው፡፡
*****
ፍኖተ ጽድቅ እነዚህን መሠረታዊና ጉልህ ችግሮች አርሞና አስተካክለሎ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት የራሱን በጎ አሰተዋጽኦ እንዲያበረክት፤ ኦርቶዶክሳውያን ታዛቢዎችና አወያይ ኮሚቴዎች በተገኙበት የፍኖተ ጽድቅ መሥራች ከሆኑት ከአቶ ጸጋዬ ደበበና ከሥራ ሓላፊዎቻቸው እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የዕቅበት እምነት ሥራዎችን ከሚሠሩ ወንድሞች ጋር  ሰፋፊ ውይይቶች ተደርገዋል። በውይይቱም መሠረት ፍኖተ ጽድቅን በተመለከተ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ እነዚህም፦
1. በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር በመደበኛ መምህርነት ተቀጥረው የሚያስተምሩ መምህራን ማስተማር አቁመው በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ገዳም ሔደው ጥሞና እንዲወስዱና በሚመደቡላቸው ኦርቶዶክሳውያን መምህራን ሥልጠና እንዲወስዱ፤

2. ከኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮና ትውፊት ያፈነገጡ መዝሙራትም ሆኑ ያልሆኑ ከፍኖተ ጽድቅ የዩቱብ ቻናል ሙሉ በሙሉ እንዲወርዱ፤

3. ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለመዝሙር አገልግሎት ከምትጠቀማቸው የዜማ መሣሪያዎች ወጭ ያሉት የሙዚቃ መሣሪያዎችና ማቀናበሪያዎች በሙሉ እንዲወገዱ፤

4. በኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና የዜማ መሣሪያዎች አጠቃቀም ላይ የፍኖተ ጽድቅ የኅብረት ዘማርያንና የዜማ መሣሪያ ተጫዋቾች ሥልጠና እንዲወስዱ፤

5. ፍኖተ ጽድቅ ወደፊት በሚሰጣቸው የትምህርትና የመዝሙር አገልግሎቶች ኦርቶዶክሳውያን መምህራንና ዘማረያን ብቻ እንዲያገለግሉ፤

6. የፍኖተ ጽድቅ መሥራችና የሥራ ሐላፊዎች ኦርቶዶክሳውያንን ይቅርታ እንዲጠይቁ፤
7. በፍኖተ ጽድቅና በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን ላይ አተኮረው የሠሩ ቲክቶከሮች የሠሯቸውን ቪዲዮዎች እንደያወርዱ፤ መምህራኑም እንዲሁ እንዲያደርጉ።

እነዚህ ስምምነቶች ላይ ለመድረስ የአቶ ጸጋዬ ደበበ ቅንነት የተሞላበት ውሳኔ ታሪክ የሚዘነጋው አይደለም። በእነዚህ የጋራ ስምምነት መሠረትና የወደፊቱን አገልግሎት በማሰብ ፍኖተ ጽድቅ የሚከተሉትን የእርምት እርምጃዎችን ወስዷል፡፡                                             
1. የፍኖት ጽድቅ መደበኛ መምህራን ማስተማር አቁመው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና እና ጥሞና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው፤
2. ኦርቶዶክሳዊ መሠረት እምነት ፣ ሥርዓት አምልኮ ፣ ትውፊት የተላለፋም ሆኑ ያልተላለፋ መዝመሮች በሙሉ ከዩቱብ ቻናል እንዲውርድ ተደርጓል፤
3. ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የዜማ መሣሪያ ውጭ የሆኑ የሙዚቃ መሣሪያዎች በማኀበራዊ ሚዲያ የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን የሚሠሩ ወነወድሞቻችን በቪዲዮ እየቀረጹና ታዛቢዎች በተገኙበት ሙሉ በሙሉ ተወግደዋል፤
4. ፍኖተ ጽድቅ ለተፈጠረው ትምህርት ሃይማኖት እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መተላለፍና ውዝግብ ምክንያት በመሆኑ ይቅርታ ጠይቋል።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የዚህ መርሐ ግብር ተሳታፊዎች!
ዛሬ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ዋጋ ተከፍሏል። በርካታ ሌሊቶችን ያለን እንቅልፍ አንግተናል። በእነዚህ ሌሊቶች ተሰባስበናል፤ ተውያይተናል፤ ይበጃል ያልናቸውን መፍትሔዎች ጠቁምናል፤ ክፋና ደግ ተነጋግረናል፤ ተጨቃጭቀናል፤ ተከራክረናል፤ ተለቃቅሰናል፤ ይቅርታ ተጠያይቀናል፤ በአጭሩ የብዙ ብዙ ሆነናል። ሂደቱ መራራና አድካሚ ቢሆንም፤ በአደባባይ ከመነቃቀፍና ከመዘላለፍ ወጥቶ፥  በርን ዘግቶ ችግሮችን በውይይትና በምክክር የመፍታትን ዋጋ በሚገባ  እንድንረዳ አግዞናል።
ይሁንና ድል አድራጊዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ድል አድርጋለች። አሸናፊዋ ቤተ ክርስቲያን በማሸነፏ፥ ሁላችንም አሸንፈናል፡፡ አንዱ አሸናፊ፤ ሌላው ተሸናፊ አልሆነም፡፡
የእኛ ድርሻ ፍኖተ ጽድቅን እስከዚህ ማምጣት ነው። ፍኖተ ጽድቅን ማጽናትና መዋቅራዊ መልክ ማሲያዝና መቆጣጠር የቤተ ክርስቲያን ድርሻ ነው። ይህ ማለት ግን ፍኖተ ጽድቅ እንደከዚህ ቀደም መሠረት እምነትን፣ ሥርዓት አምልኮንና ትውፊትን ሲተላለፍና ሲጥስ አፋችንን ዘግተን፤ እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት ግን አይደለም። እነርሱ በተለወጡ ማግስት እኛም በእነርሱ ላይ ያለን አቋም እንደሚለወጥ ከወዲሁ ለማሰሰብ እንወዳለን። ከዚህ በተረፈ እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ፍኖተ ጽድቅን በሁሉም ነገር ለመተባበርና ለማገዝ ዝግጁ መሆናችንን በታላቅ አክብሮት ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ማር ይስሐቅ

05 Apr, 19:00


በአንዳንድ መምህራን ዘንድ የጌታ ምጽዓት
1. እለቱ: - እሑድ
2. ወሩ: - መጋቢት
3. ቀኑ: - 29
4. ዘመኑ: - ዮሐንስ
5. ??? ተብሎ ይነገራል

እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዘንድሮ ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ተገጣጥመዋል እና ዘንድሮ የዓለም ፍጻሜ ይሆን? 😥😥😥

እስቲ ይህንን እናስተውል

ዘንድሮ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2016 ዓ.ም ነው።

በጌታ ዘንድስ?

“እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመትሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።”
2ኛ ጴጥሮስ 3፥8

እናም በጌታ ዘንድ ዘንድሮ መጋቢት 29 ነው?

አናውቅም።

ሲጀመር ጌታ ከቀን አቆጣጠር ውጪ ነው።

የቀን አቆጣጠር ከመፈጠሩም በፊት ነበርና።

ለምሳሌ አዳምን ለማዳን 5,500 ዘመን ሲፈጸም ተወለደ እንላለን
ነገር ግን በጌታ አቆጣጠር 1 ሺህ ዓመት እንደ 1 ቀንም ስለሆነ 5 ቀን ከግማሽ ብለንም እንናገራለን።

ሌላውና 5ኛው ነጥብ

“እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።”

ተብሎ በዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 13 ከቁጥር 13 ላይ የተነገረለት  ሐሰተኛው ክርስቶስስ መች መጣ?

በዮሐንስ ራእይ የተቀመጠው ቃል ገና መቼ ተፈጸመ?

ስለዚህ የጌታን አቆጣጠር አናውቅምና ተዘጋጅተን እንጠብቅ
እስከዚያ ድረስ ይህችን ዓመት ተወን? እንበል።

@Gamel_Media