የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል @halaba_ahles_suna Channel on Telegram

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

@halaba_ahles_suna


قال بعض السلف "عليك بطريق الحق ، ولا تستوحش لقلة السالكين ، وإياك وطريق الباطل ، ولا تغتر بكثرة الهالكين "

እዚህ ቻናል ላይ የሚተላለፉ ማንኛውም ት/ቶች ምንጫቸው አስተማማኝ እንዲሆን እንጥራለን።

ቁርኣንሀዲስየሰለፎቻችንናየተከታዮቻቸው ንግግሮች ይተላለፋሉ፥

👇የቻናሉ አባል ለመሆን||
@Halaba_Ahles_suna

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል (Amharic)

እንኳን ለዚህ ታሪክ መረጃዎች፦ የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻናል 'እዚህ ቻናል ላይ የሚተላለፉ ማንኛውም ት/ቶች ምንጫቸው አስተማማኝ እንዲሆን እንጥራለን።' የስራውን በቁርኣን ሀዲስ የሰለፊችንና የተከታዮቻችን ንግግሮች ለመሆን የቻናልን አባል በ @Halaba_Ahles_suna ላይ ይታይታል። በዓለም ላይ ያለው የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊን ቻናልን የቀረበ በሰላም ተጠናቀቀ እና ብዙ ሰሞን ለዘላለም የሚያልቅ ይሆናል።

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

03 Feb, 14:26


Share شروط التراجع.pdf

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

23 Jan, 22:48


🚫 ከሀዲያንን በባአላቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት

በመለኮታዊ የሕይወት መመሪያ በሆነው የአላህ ቃል የሚመራው እንከን የለሹ ኢስላም ካስቀመጣቸው ግልፅና የማያሻሙ ህግጋቶች ውስጥ ከሃዲያንን በባአላቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት ክልክል መሆኑ ነው ።
ተህኒኣ ( እንኳን አደረሳችሁ ) ለከሀዲያን ማለት ሐራም መሆኑ አጠቃላይ የኢስላም ሊቃውንቶች በአንድ ድምፅ ያፀደቁት መሆኑ ኢብኑል ቀዪም አሕካሙ አህሊ ዚማህ በሚለው ኪታቡ የጠቀሰው ሲሆን በኩፍር መደሰትን ስለሚያሲዝ ወደ ኩፍር ሊያደርስ እንደሚችል በዚሁ ኪታቡ ላይ ያብራራል ። ቀድሞ እንኳን አደረሳችሁ ማለት ብቻ ሳይሆን እነርሱም ሲሉ እንኳን አብሮ አደረሰን ማለትም ተመሳሳይ ብይን እንዳለው የኢስላም ሊቃውንቶች ያስቀምጣሉ ።
በዚህ ጉዳይ ላይ አራቱም አኢማዎች ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ሲሆን ከዘመናችን ዑለሞች እንደነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ, ሸይኽ ዑሰይሚንና ሸይኽ ፈውዛን የመሳሰሉት ሐራም መሆኑን አስቀምጠዋል ።
በመሆኑም ይህ ጉዳይ የቀደምቶች ስምምነት ያለበት ስለሆነ መወዛገብ አይፈቀድም ። የኻለፈ አካል ትንሹ ብይኑ የስሜት ተከታይ ( ሙብተዲዕ) ይሆናል ። ከፍ ሲል በኩፍር ላይ የደስታ መልእክት ማስተላለፍ ስለሆነ ያከፍራል ።
በጣም የሚገርመው እንዲህ አይነት ግልፅ የሆነ ሸሪዓዊ ብይን የተሰጠበትን ከባድ የመሰረታዊ የእምነት ነጥብ በሚቃረን መልኩ ለዛው በአላህ ቤት መስጂድ ላይ ይህን ወደ ኩፍር ሊያደርስ የሚችል መልእክት በአደባባይ የቅርብም የሩቅም በሚያየው መልኩ ተሰቅሎ መታየቱ ነው ። ይህ የሆነው ቄራ ሰላም መስጂድ ላይ ነው ። ይህን መልእክት በገፃችን ላይ መለጠፉ ስለሚቀፍ በሚቀጥለው ሊንቅ ገብታችሁ ተመልከቱት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://drive.google.com/file/d/11ISLKe4SHvZ_5tf3MRxdCKK2sdcqi0yf/view?usp=drivesdk

የሚያሳምመውና የሚያሳዝነው በአላህ ቤት ላይ መሆኑ እንጂ የተጠቀሰው መስጂድ የሚያስተዳድረው ዲኑን ለስልጣንና ለግል ጥቅም የሚሸጠው የኢኽዋን አንጃ አካል ስለሆነ አይገርምም ። ምክንያቱም ፈለጋቸውን የሚከተሉት የግብፅ, የቱርክና ሱዳን ኢኽዋኖች ወደ ሀይማኖት አንድነት ነውና የሚጣሩት ። በመሆኑም ከሀገራችንም ኢኽዋኖች አላህ ይምራቸው እንጂ እንኳን አደረሳችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ሀይማኖት አንድነት ይጣራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።
መሪዮቻቸው ከእንጀራ አባቶቻቸው ጋር የተለጠፉት የነሲሓ ቲፎዞዎች ምን ይሰማቸው ይሆን ? ነው ወይስ 30 ክኒኖቹ ይህም እንኳን እንዳይሰማቸው አደንዝዟቸው ይሆን ? ወይስ በሱፍይ ሙሪዶች ቀመር ስለሚጓዙ ሸይኾቻቸው የሰሩት ነገር ለምን አይባልም ? አላህ ሆይ ልባችንን ሐቅ ካሳወቅከው በኋላ አትቀይረው ።

https://t.me/bahruteka

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

17 Jan, 10:17


🔜 ልዩ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም

🔛 ከዛሬ ጥር 9/5/2017 የጁመዓ ኹጥባና ሰላት ጀምሮ  ለተከታታይ 3 ቀናቶች ተዘጋጅቷል።

↪️ በዝግጅቱ ላይ ከሚገኙ ውድና ብርቅዬ መሻይኾች መካከል

🪑🎙 አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ቢን ያሲን አለተሚይ (ከለተሞ)
🏝 بعنوان : وقفات مع سورة نوح
🏝 ልዩ ቆይታ ከሱረቱ ኑህ ጋር

🪑🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ሀያት (ከወሎ ሐራ)
📚 بعنوان : دورة مكثفة في المنهج
📚 ልዩ ኮርስ በሚንሃጅ ዙሪያ

🪑🎙 አሸይኽ ሁሰይን ከረም (ከወሎ ሐራ)
📝 بعنوان : الإعتصام بحبل الله
📝 በአላህ ገመድ መተሳሰር

🪑🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (ከኮምቦልቻ)
🚥 بعنوان : خطر البدع وأهلها في الإسلام
🚥 የቢድዐ እና የቢድዐ ባለቤቶች አደጋ በእስልምና ላይ

🪑🎙 አሸይክ ሙባረክ አልወልቂጢይ (ከወልቂጤ)
🏖 بعنوان :- مجمع الشرك 
የሺርክ መናሀሪያዎች 

🪑🎙 አሸይኽ ሁሰይን  ሙሐመድ አስልጢይ  (ከአዲስ አበባ)
🔍 بعنوان : الصبر في الدعوة إلى الله
🔎 ሰብር ወደ አላህ በመጣራት ላይ

🪑🎙 አሸይኽ መህቡብ (ከሳንኩራ)     
💡 بعنوان : كن على بصيرة في ديك
💡 የቻሌ የንበሪ (በስልጢኛ ቋንቋ)

🪑🎙 አሸይኽ አወል (ከዳሎቻ)
💻 بعنوان : إن هذا الدين أمانة عظيمة
💻 ዲኒ እኮ የሮሬን አማነ (በስልጥኛ ቋንቋ)

🪑🎙 አሸይኽ አቡ ዘር (ከሱኡዲ አረቢያ) 🛜  በቀጥታ ስርጭት

ለዝርዝሩ ➴➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/9635

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

13 Jan, 00:35


🚫 የአላህ ታአምር በአሜሪካ ምድር

አሜሪካ ትላንት በሰው ሰራሽ እሳት የፍልስጢንን ምድር ስታቃጥል አዛውንትና ህፃናትን መኖሪያቸው ቀብራቸው እንዲሆን አድርጋ ከፍርስራሽ ስር ጀናዛ ስትቀብር የምእራቡ ዐለም በድል አድራጊነት ቁጭ ብሎ እያየ ነበር ከተሞች ወደ ምድረበዳነት ሲቀየሩ እርጥብና ደረቅ ሲቃጠል ማን አለብኝ ባይዋ አሜሪካ ገና ነው ጠብቁ ትል ነበርፍልስጢናዊያን አቅመ ደካሞች ነፍሳቸውን ማዳን የቻሉት ሲሰደዱ ደካሞቹ የሰው ሰራሹ እሳት በላያቸው ላይ ሲለኮስ የዛሬዎቹ ደም እንባ አልቃሽ የሆሊዩድ አክተሮች በሉዋቸው ሲሉ ነበር። የእናታቸው ጡት እንደጎረሱ ከፍርስራሽ ስር የቀሩ ህፃናትን ጀናዛ ማውጥት እንዳይቻል የአሜሪካ የጦር ጀቶች የቦንብ ናዳ ሲያወርዱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ውስኪ ያገሱ ነበር። የፍልስጢን ሰማይ በሰው ሰራሽ እሳትና በአቅመደካሞች ደም ከለሩ ሲቀየር የዛሬዎቹ የሆሊዩድ አክተሮች ፊልም ይሰሩበት ነበር።
ምንዳ በሰሩት ስራ ልክ ነውና ዛሬ እብሪተኛዋ፣ ትምክህተኛዋ፣ ማን አለብኝ ባይዋ፣ አንባ ገነኗ አሜሪካ የስራዋን ውጤት ለማየት ተገዳለች። ፍልስጢንን ለማውደም በቢሊየን ዶላይ የመደበው ባይደን ዛሬ የደረሰበትን ውድመት ለማስቆም የሚችል ዶላርም፣ መሳሪያም፣ የምርምር ተቋምም፣ የጦርም ይሁን የተማረ ሀይል አጥቶ የሚሆነውን በቁጭት ለማየት ተገደደ።
ከአላህ የተላከው እሳት ሎስ አንጀለስ ላይ ከፊቱ የሚቆም ሀይል የለም በቃህ ባይ የለውም ሁሉንም ነገር ያቃጥላል ያወድማል ያከስማል፣ ከተማን ወደ አመድነት ይቀይራል ። ዝነኞቹ የሆሊዩድ አክተሮች ማን ይወዳደረዋል ከሚባልለት መኖሪያቸው ባዶ እጃቸውን ወጥተው የሲቃ እንባ እያነቡ አለኝ የሚሉት ነገር እሳት ሲበላው እያዩ ነው። የአሜሪካ ባለ ስልጣናት የስብእና ዝቅጠትና የማንነት ማዝቀጫ ፋብሪካ የሆነውን ሆሊዩድን እሳቱ ሲበላው ለማየት እየተገደዱ ነው። ያ የዝቅጠት ፋብሪካ ሆሊዩድ ያ ፈጣሪ የሚባል ነገር የለም የሚሉ አክተሮች የሞሉበት የኩፍር መናሃሪያ የሆነው ሆሊዩድ እሳቱ ደረስኩ እያለው የይድረሱልኝ ጣር እያሰማ ሲሆን ጣኦቱ ባይደን የለምና ድንጋይ ቆሞ ከመቅረት ውጪ አማራጭ አጥቷል።
የትኛውን የጦር ጀት ወዴት ያሰማራ? ወደ ማን ይተኮስ ይበል? በማን ላይ ያቧርቅ? በድን ሆኖ መቅረትና የሚሆነውን ከማየት ውጪ መላ የለውም። ለመሆኑ ባይደን የትላንቱን የፍልስጢንንና የኑፁሃን ህዝቦቿ ዋይታና ሲቃ በአይነ ህሊናው ይቃኝ ይሆን? ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ህሊናው እብሪት ጋርዶታልና ዛሬ በንፁሀን ደም የጨቀየው እጁ የዘራውን እያጨደ ነውና ልቦናው ታውሯል። በድን ሆኖ የሚሆነውን ከማየት ውጪ አማራጭ የለውም እሱም አጋሮቹም ሺ ጊዜ አምሳያቸው ቢጨመርም ምንም ማድረግ አይችሉም ምክንያቱም የአላህን ሰራዊት የሚገጥም የለምና
የፊራኦንን ሰራዊት በውሃ ያሰመጠ፣ የኑሕ ዘመን እብሪተኞችን ከሰማይና ምድ በታዘዘ ፍል ውሃ ያጠፋ የመድየንን የሉጥንና የሰሙድን ህዝቦች በመላኢካ ጩኸት ያጠፋ አምላክ በዛሬዎቹ እብሪተኞች ላይ ከሰራዊቱ መካከል የሆነውን እሳትና አውሎ ነፋስ ልኮ አሜሪካን እያመሰ ይገኛል። የጌታህ ሰራዊት እሱ እንጂ ማንም አያውቀውም

«وَمَا جَعَلْنَا أَصْحَابَ النَّارِ إِلَّا مَلَائِكَةً ۙ وَمَا جَعَلْنَا عِدَّتَهُمْ إِلَّا فِتْنَةً لِّلَّذِينَ كَفَرُوا لِيَسْتَيْقِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَيَزْدَادَ الَّذِينَ آمَنُوا إِيمَانًا ۙ وَلَا يَرْتَابَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَالْمُؤْمِنُونَ ۙ وَلِيَقُولَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَالْكَافِرُونَ مَاذَا أَرَادَ اللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًا ۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ اللَّهُ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ ۚ وَمَا يَعْلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَ ۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكْرَىٰ لِلْبَشَرِ »
المدثر ٣١
"የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም። እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል የሚሻውንም ያቀናል የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም። እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም።"

ይህ ዛሬ በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ምፅዓት የሚመስለው እሳት አኼራ ላይ ከሚጠብቃቸው አንፃር ኢምንት ነው። ሩቅ ይመስላቸዋል ግን ቅርብ ነው። ወደ አላህ ተመልሰው ለአላህ ትእዛዝ እስካላደሩ ድረስ። እስኪ የዛን ቀን ሁኔታ በቁርኣን ገለፃ እናስተውለው፦

إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا
እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል።
وَنَرَاهُ قَرِيبًا
እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡
يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِ
ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን
وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ
ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን
وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا
ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)
يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ
(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡
وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ
በሚስቱም በወንድሙም፡፡
وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْوِيهِ
በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡
وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِ
በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡
كَلَّا ۖ إِنَّهَا لَظَىٰ
ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡
نَزَّاعَةً لِّلشَّوَىٰ
የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡

تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ
(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች።

ሱረቱል መዓሪጅ ከአንቀፅ 6 –17

እነዚያ የአላህን ባሮች የሚፈትኑ አካላት ተውበት አድርገው ካልተመለሱ ምን እንደሚጠብቃቸው በሚከተለው የአላህ ቃል እናያለን፦
«إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ»
    البروج ١٠
"እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው። ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡"
     
ለማንኛውም እኛ ለእነዚህ አካላት የምንለው ሂዳያ የሚገባቸውን አላህ ሂዳያ ይስጣቸው። ሂዳያ የማይገባቸውን ደግሞ በጥበቡና ፍትሀዊነቱ የሚገባቸውን ይስጣቸው ነው

https://t.me/bahruteka

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

12 Jan, 11:41


ሞኝና ወረቀት የያዘውን አይለቅም ይሉሃል ይሄ ነው።
———
ከኢልያስ አህመድና የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሙሪዶች ብዙዎች እየገፋ በመጣውና ግልፅ በወጣው ከአል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን ጋር አንድ በመሆናቸው የሚደረድሩላቸው የነበረውን ዑዝር በመተው ቆም ብለዋል። አንዳንዶች ደግሞ ድሮ ሲያስተኟቸው "ለመስለሃ ነው እንጂ መች አንድ ሆን?" ብለው ሲያምታቷቸው ያስጨበጧቸውን እንደ ወረቀትና ሞኝ አሁንም እሷን ይዘው ሙጥኝ እንዳሉ ናቸው።

"ለመስለሃ እንጂ ኢኽዋንና ሰለፊይ በአንድ ጥላ ስር አይሆንም" ይላል።

እውነታውማ:- በማያልቅ መስለሃ ስም ጭልጥ ያለ ኢኽዋንነት ውስጥ ካልተገባ መቼም ሠለፊይነትን እየሞገቱ ከኢኽዋን ጋር በአንድ ጥላ ስር መሆን የለም!!

🔸 የሚደንቀው ኢኽዋኖች ሰዎችን ሙሃዶራ ብለው ጠርተው እንደሚያደርጉት በዚህ ፍጥነት ወርዶ ኢልያስ አህመድም የኢኽዋኖችን አይነት ሰዎችን በቂሷ እና በግጥማግጥሞች ቢዚ አድርገው የሚረባ መልእከት ስለ ሺርክና ተውሒድ ሳይናገሩ እንደሚበቱኑት ወጣቶችን ሰብስቦ ይህን አድርጎ መበተኑ ነው። እንደተለመደው እንኳን በሱንና አንደበት ተናግሮ ሙሪዶቹን ለማጭበርበር አልሞከረም። ያው ሁኔታው ግልፅና ግልፅ ነው፣ አልተቀየረም እያሉ ለሚሞግቱ ጭፍን ሙሪዶቹም "መንገዴን በአደባባይ ከጀመርኩ ቆየሁ እርማችሁን አውጡ" የሚል መልእክት እያስተላለፈ ይመስላልና ጭፍን ሙሪድነት ትታችሁ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ርቃችሁ ቀጥ ያለችውን መንሀጀ-ሰለፍን አጥብቃችሁ ያዙ!!

✍🏻ኢብን ሽፋ
#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

31 Dec, 05:11


👉 ሀገሪቷን ማን በየትኛ ህግ ነው የሚያስተዳድራት ?

ሀገራችን ኢትዮዽያ የምትመራበት ህገመንግስት አንቀፅ 27 የዜጎች የእምነት ነፃነትን ያውጃል ። የዜጎች ሲባል እየአንዳንዱ ዜጋ ማለት ነው ። ይህ ማለት አንድ ሰው የፈለገውን እምነት የመቀበል ፣ እምነቱ የሚያዘውን ነገር የመተገብር መብቱ ማንም ሊነጥቀው የማይችል ወይም በማንም መልካም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑና ይልቁንም የዜግነት መብቱ መሆኑን ነው የሚያሳየው ።
በሀገራችን በየትኛውም ደረጃ ያሉ ክልሎችም ይሁን ዞንና ወረዳዎች በዚህ ህገመንግስት ስር ሆነው ነው ክልላቸውን ወይም ዞንና ወረዳቸውን ማስተዳደር ያለባቸው ። ከላይ ያየነው አንቀፅ የአንድን ግለሰብ መብት የሚያስጠብቅ ከሆነ በሺዮች ወይም በመቶ ሺዮች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲሆኑ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው ። ማንም ተነስቶ የግለሰብን እንኳን ህገመንግስታው መብት የሚጥስ መመሪያ ማውጥት የማይችል ከሆነ የህዝቦችን መብት የሚጥስ መመሪያ ማውጣት አለመቻሉ ከበጋ ፀሀይ የበለጠ ግልፅ ነው ማለት ነው ።
የህገ መንግስቱ መመሪያ ይህ ከሆነና መንግስት የሚሰራው በዚህ ከሆነ በምን ሒሳብ ነው ይህን የህዝቦች መብት ያረጋግጣል የተባለውን መመሪያ አሻፈኝ ብሎ ይህን የሚፃረር መመሪያ ስራ ላይ በማዋል የዜጎች መብት የሚረገጠው ?
በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ላይ በተለያዩ ክልሎች በግልፅ ይህን ህገመንግስታዊ የዜጎች መብት በጣሰ መልኩ የራሳቸው ህግ በማርቀቅ መብት የሚረግጡ መኖራቸው የአደባባይ ሚስጢር እየሆነ ነው ። ለመሆኑ እነዚህ አካላት ህገ መንግስቱ እኛን አይወክልም የራሳችን ህገመንግስት አለን ባዮች ናቸው ወይስ ከህገ መንግስቱ ውስጥ ለኛ የሚስማማውን ወስደን የማይስማማውን እንተወዋለን ማን ምን አገባው ባዮች ናቸው ? ወይስ ጠያቂ የለም ነው ነገሩ ። ለማንኛውም እንዲህ አይነት ፅንፈኝነት ለማንም አይጠቅምም ።
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማንኛውም ተማሪ ሀይማኖትን የሚያንፀባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም በሚል ሙስሊም ሴት ተማሪዮችን ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እዳይገቡ መከልከሉ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንደሚሉት ነው ። ለመሆኑ እነዚህ አካላት አንገታቸው ላይ ክር አስረው ክርስቲያን መሆናቸውን የሚገልፅ ነገር ያደረጉትንም ጭምር ነው ያባረሩት ወይስ የሙስሊሞችን እስልምና የሚገልፅ ነገር ነው ወንጀል የሆነው ? ለመሆኑ በትግራይ ክልል እንደ አፄዎቹ ዘመን የሙስሊም ኮፍያ መልበስም ወንጀል ነው ? በአክሱም ከተማ እስልምናን የሚገልፅ ነገር እንደ ኮፍያ ፣ ሒጃብ ፣ ጅልባብና የመሳሰሉ መገለጫዎችን የሚያደርጉ ሙስሊሞች አይደለም በሴክተር መስሪያ ቤት ሊሰሩ ለጉዳይም መግባት አይችሉም ሊሉ የሚፈልጉ ይመስላል ።
የሚገርመው በሒጃብ ዙሪያ እንደሀገር ሙስሊም ሴት ተማሪዮች ከዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ሒጃብ ለብሰው መማር የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ መመሪያ እንደ ኢትዮዽያ አቆጣጠር በ2000 ወጥቶ በስራ ላይ የዋለ መመሪያ አለ ። ይህ ከህገመንግስቱ የፈለገችውን የመልበስ መብት ማረጋገጥ በተጨማሪ ማለት ነው ። ታዲያ የአክሱም ከተማ ፅንፈኞች ለየትኛው ህግ ይሆን የሚገዙት ? ወይስ የኋሊዮሽ ተመልሰው የአፄዎቹ ዲስኩር መንዛት ነው የተያያዙት ?
በአሁኑ ጊዜ የዜጎች መብት መረገጥ በሌሎችም የእምነት ተቋማትም እየታየ ነው ። ከላይ የተጠቀሰውን አንቀፅና እንዲሁም ማንኛውም ዜጋ ለህጋዊ አላማ የመደራጀት መብቱ የተጠበቀ ነው የሚለውን የህገ መንግስቱ አንቀፅ 32 እንዲሁም መጅሊሱ በአዋጅ ሲፀድቅ ከዚህ በፊት የተቋቋሙ ወይም የተደራጁ ማህበራትን መከልከል አይችልም የሚለውን አዋጅ በመፃረር የአሁኑ የመጅሊስ አመራሮች በቁርኣንና ሀዲስ ሳይሆን በራሳቸው ልብ ወለድ የሚመሩት መጅሊስ ስር ያልሆነን ዜጋ አይደለም እስከ ማለት ደርሰዋል ። እነዚህን ከላይ የተገለፁ የዜጎችን መብት የሚረግጡ መመሪያዎችን የሚቃረን መመሪያ በማውጣት ይህን ተቀብሎ ተግባራዊ የማያደርግ በዚህች ሀገር መኖር አይችልም ሀገሩን ይፈልግ እስከማለት ደርሰዋል ።
ይህ ነው ይህች ሀገር ማን በየትኛው ህግ ነው የሚያስተዳድራት የሚል ጥያቄ የሚያስነሳው ። ዜጎች በጣም በሚገርም ተስፋ የጠበቁት ብልፅግና እንደነዚህ አይነት ተግዳሮቶችን በመዋጋት ወረቅት ላይ ያሉትን ፍትህ የናፈቃቸው ቃላት መሬት ላይ ወርደው ስራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ የመጀመሪያ ተግባሩ ሊሆን ይገባል እላለሁ ።

ፍትህ ለአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዮች ።

https://t.me/bahruteka

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

31 Dec, 05:07


መንግስት ፅንፈኝነትን የሚያራምዱ ፅንፈኛ ክርስቲያኖችን ከመንግስት ተቋማት ሊያስወግድና እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል!!
—————
ለመንግስት ተቋማት እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ብዙ ጊዜ ከሙስሊሙ የተለመዱ አይደሉም። ሙስሊሙ ምንም ያህል ቢጨቆንና ቢሰቃይ በዝምታ አለያም ለጊዜው ብቻ ጮሆ ያቆማል። እነሱ የመንግስት ተቋማትን ተደግፈው አገሪቷን እንዳሻቸው ለማተራመስ እንቅፋት የሚሆንባቸው አንድ ሙስሊም ባለ ስልጣን ካለ ከማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አልፈው በኤሌክትሮኒክስና በህትመት ሚዲያዎች ይዘምቱበታል። ምን ይህ ብቻ፣ የማይፈልጉትን ሙስሊም ባለ ስልጣን ከነበረበት ስልጣን ዘወር እስኪደረግላቸው ድረስ ሁሉ የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን ቢሮዎች በር ከማንኳኳት አይወገዱም።

እነሱ ግን ሙስሊሙ ግብር የሚከፍልባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶችን እና ትምህርት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ሙስሊሙን መጨቆኛና ማሰቃያ ልዩ መሳሪያ አድርገው ከያዟቸው ዘመናትን አስቆጥረዋል። መንግስት ት/ቤቶችንና ተቋማትን ሴኮላር ማድረግ እፈልጋለሁ ካለ በቅድሚያ እንዲህ ካሉ በተቋማት ስር ከተሰገሰጉ ፅንፈኞች ሴኮላር ያድርገው።

በተለያዩ ጊዜያት የሙስሊም ተማሪዎችን ሮሮ መስማት የተለመደ ቢሆንም የሰሞኑ ግን በአንፃሩ ለየት ያለ ነው።
ከዚህ ቀደም በነበሩ ጊዜያት ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን "ሙሉ ሃይማኖታችሁ የሚያዛችሁንና ግዴታ ያደረገባችሁን (ሙሉ ፊትን ጨምሮ) መሸፋፈኛ ሒጃብ አውልቃችሁ ተገላልጣችሁ ካልሄዳቹ አትማሩም" በሚል የተለያየ ስቃይ ሲደርስባቸውና የት/ት ፈተና በሚደርስባቸው ጊዜያት ጠብቀው ሲያስለቅሷቸው ቆይቷል። እንዲሁም ወንዶችን ግዴታ የሆነውን የጀመዓና ጁምዓ ሶላት አትሰግዱም እያሉ ሲያሰቃዩዋቸው ቆይተዋል።
አሁን ግን ጭራሽ የፀጉር መሸፈኛ ሻሻችሁን አውልቃችሁ እንደ እንስሳ እርቃናችሁን ሆናችሁ ካልሆነ አትማሩም እያሉ ነው። የከሀዲያን ምኞች ከዚህም ያለፈ እንደሆነ አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ በማለት ተናግሯል:-

وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ

«አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡» አል-በቀረህ 120
ይሄው ነው የእነሱ ምኞት።

በጭፍን ጥላቻ ተነሳስተው ፅንፈኛ ክርስቲያን ርእሰ መምህራን እና መምህሮች በእስልምና መተግበራቸው ግዴታ በሆኑ ተግባሮችና በሴት ልጅ ከሃይማኖቷም ባሻገር በተፈጥሮ ግዴታ የሆነባትን የመሸፋፈን መብቷን በመከልከል በ21ኛው ክ/ዘመን "ሰለጠን" የሚሉ ኋላ ቀር የሰው ሰይጣኖች አደገኛ ጭቆና ውስጥ ገብተዋል።

ይህ ፅንፍ የረገጠ ጭፍን ጥላቻቸው የወለደው የጭቆነ አይነት መሆኑ ነው። በቁጭት ነድደው ይከስሉ እንደሆን እንጂ ለአለማቱ ጌታ አላህ የላቀ ምስጋና ይገባውና ትላንት በተለያየ ጭቆና ከነ ፂማቸውና ኒቃባቸው ተምረው የጤና ባለ ሞያና መሀንዲስ ከሆኑ ብዙ ሙስሊም ወንድምና እህቶች የበለጠ ሙስሊሙ ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ የሚማርበት እድሉ ሰፍቷል። (ባይሆን ግን ከአሁን ቀደም በተለያዩ ጭቆናዎች ተምረው ጥሩ ደረጃ የደረሱ ሙስሊሞች በነሱ ላይ የደረሰው "በኛ ይብቃ" ብለው፣ ሸሪዓን በማይፃረሩ በተለያዩ ዘዴዎች በያሉበት ተቀናጅተውም ይሁን በግል ጭቆናው እንዲቀር ለማድረግ መታገል ይጠበቅባቸዋል።)

ገርሞ የሚገርመው! የከረረ ፅንፈኝነታቸውን እና የአፄ ሀይለ ስላሴን ሙስሊሙን ከትምህርት የማግለል እስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከራቸውን እያሳዩን መሆኑ ነው እንጂ የራሳቸውም እምነት መፅሃፋቸው ሴት ልጅ ፀጉሯን እንድትሸፈን ያዛል።

ሴቶች ኀፍረተ-ገላቸውን ተገላልጠው ወንዶችን ከመማር በሚረብሽ መልኩ ተራቁተው እየሄዱ "ነፃነትና መብት" የሚል ታፔላ ለጥፈውለት ሲያበቁ ሙስሊም ሴቶች ፀጉራቸውን እንኳን መሸፈኛ ሻሽ መከልከላቸው ጥላቻ ያወራቸው ባለ ዲግሪ ደደብና የሴቶችን ገላ የማየት ሴሰኝነት የተጠናወታቸው ርካሾች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። እንዲህ ያሉ ርካሽ ስነ-ምግባር ያላቸው መምህራን እና የት/ቤቶች ኀላፊ የሆኑ ሰዎች ለራሳቸው መልካም ስነ-ምግባር ሳይኖራቸው እንዴት የት/ቤት ኀላፊነት ይጣልባቸዋል?!

እደግመዋለሁ!፣ መንግስት እንዲህ ያሉ በሰዎች መብትና ነፃነት የግል ቂምበቀል የሚወጡ፣ መንግስትና ሕዝብን የሚያጋጩ ፅንፈኝነትን የሚያራምዱ ባለ ዲግሪ ደደብ ፅንፈኛ ክርስቲያኖችን ከተቋሙ ሊያስወግድና እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል!!

በተቻለ መጠን እንዲህ ያሉ ክስተቶችን ጊዜያዊ አጀንዳ ብቻ ከማድረግ ይልቅ በዘላቂነት መብት የሚከበርበትን መንገድ መፈለጉ ተገቢ ነው!።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ጁማዱል አኺር 28/1446 ዓ. ሂ
» » » ታህሳስ 20/2017
#Join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

26 Dec, 18:48


ስለ ትልቁ ትልልቆችን አዳምጥ
🏝🏝🏝🏝

🏖 ماذا قال العلماء الكبار في هذا الزمان عن الشيخ ربيع بن هادي عمير المدخلي -حفظه الله تعالى-؟
🏖 የዘመናችን ትልልቅ ኡለሞች ስለ ሸይኽ ረቢዕ ምን አሉ!?

🚥 جمع لبعض من أقوال المشايخ والعلماء

🎙 - عبد العزيز بن عبد الله بن باز،
🎙 - زيد بن محمد هادي،
🎙 - أحمد بن يحيى النجمي،
🎙 - صالح بن محمد اللحيدان،
🎙 - مقبل بن هادي الوادعي،
🎙 - محمد ناصر الدين الألباني،
🎙 - محمد عبد الوهاب مرزوق البنا،
🎙 - محمد بن صالح العثيمين،
🎙 - صالح بن فوزان الفوزان،
🎙 - عبيد بن عبد الله الجابري،
🎙 - عبد المحسن بن حمد العباد.


▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

25 Dec, 14:58


🟢 ገሳጭ ቲላዋ

በአሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሃዲይ አልመድኸሊይ (አላህ ይጠብቃቸው)

ጁመዐህ 09/06/1445


📍በአሸርበትሊይ መስጂድ


የሱረህ አተካሱር መልዕክት በአማረኛ ⤵️
https://t.me/Abuhemewiya/2705

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

24 Dec, 20:03


🔵 ምክር ለኢብኑ ሙነወር

🎙 በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አል-ሐበሺ አስ-ሲልጢይ አላህ ይጠብቃቸው!

የአኺ ኢብኑ ሙነወር ሆይ! ቆም በልና ራስህን ተመልከት ወላሂ ለነፍስህ መከላከል አይጠቅምህም፤ ምንም አያደርጉልህም!

ሱናን አስፋፋ፣ ተውሂድን አስፋፋ፣ አትዋሽ፣ አታጭበርብር እስኪ ራስህን ቆም ብለህ አስተውል!

ወላሂ እዚህ ያደረሰህ ለምን እንዲህ ይሉኛል የሚለው ራስን የመከላከል ዘይቤ ነው።

ለራስ ሲሉ መበቀል ሰለፍያን የበታተነ፤ በሰለፍዮች መካከል ጥላቻን ያስፋፋ እና አንድነታቸውን ያንኮታኮተ ነው።

በቢድዓ ሰዎች ላይ በፍትህ እና በመልካም ሁኔታ የተመዘዘ ሰይፍ ሁን! ይህ ካንተ የሚጠበቅ ነው። ከሸይጧን ውስወሳዎች ተጠንቀቁ!

📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
https://t.me/AbuImranAselefy
~~``~~~~~
https://t.me/YusufAsselafy

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

05 Dec, 11:56


🟢መጅሊሳችሁን ገምግሙት

በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ መጅሊስ የቋቋማችሁ ፣ የምትመሩት ባለስልጣናቱ ፣ አባላቱ ፣ አጋሮቹ እና ደጋፊዎቹ ሁሉ : መጅሊሳችሁ ከሚስተዋሉበት ጥፋቶች ውስጥ:-

1⃣ሰለፊያን ቀብሮ ሱፊያን አክብሮ ለመንገስ የቆረጠ መጅሊስ

በተደጋጋሚ የመጅሊሳችሁ መሪዎችና ተቀጣሪዎች የነቢያት ፣ የሰሃቦች እና የዑለማዎች መንገድ የሆነውን የሰለፊያን ደዕዋ ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን በግልፅ አውጀዋል:: ተቋማቸውም በተግባርም የሚችለውን ሁሉ እየጣረ ነው::የተዊሂድ ደእዋ ይከለክላል ፣ ቂርኣት ያግዳል ፣ ሀቅ ተናጋሪ ኢማሞችን እና ኡስታዞችን  ያባርራል እንዳይንቀሳቀሱ ያግዳል:: ይባስ ብሎም ለእስርና እንግልት አሳልፎ ይሰጣል :: በአላህ ይሁንብኝ ባጢል ሀቅን አያጠፋም:: ሱፊያ እና ድምሮቹ ፊርቃዎች ልብ ወለድ  ሲሆኑ ሰለፊያ ግን የአላህ ዲን ነውና የበላዓይነቱ የፀና ነው❗️
ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት:
( ... وَتَفْتَرِقُ أُمَّتِي عَلَى ثَلَاثٍ وَسَبْعِينَ مِلَّةً كُلُّهُمْ فِي النَّارِ إِلَّا مِلَّةً وَاحِدَةً ، قَالُوا : وَمَنْ هِيَ يَا رَسُولَ اللَّهِ ؟ قَالَ : مَا أَنَا عَلَيْهِ وَأَصْحَابِي )
(ህዝቦቼ ወደ ሰባ ሶስት መንገዶች ይላያያሉ:: አንዲት መንገድ ብቻ ስትቀር : ሁላቸውም የእሳት ናቸው:: ሰሃቦችም አሉ " ማነች እርሷ ያ ረሱለላህ ?"
አሉ : እኔና ባልደረቦቼ ያለንበት መንገድ::)

2⃣መውሊድን አድምቆ አክባሪ መጅሊስ
የሺርኮች እና ቢድዓዎች መናኸሪያ የሆነውን መውሊድን በድፍረትና በተደጋጋሚ ደምቆ እንዲከበር የሚሰራ መጅሊስ መሆኑን አሳያችሁ::
ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት:
(...وشرًّ الأمورِ محدثاتُها وكلَّ بدعةٍ ضلالةٌ  وكلَّ ضلالةٍ في النارِ )
(...የነገሮች ክፉ ፈጠራዎች ናቸው::ሁሏም ቢድዓህ ጥመት ነች ::ሁሏም ጥመት እሳት ውስጥ ታስገባለች::)

3⃣ሁሉም ለስሜቱ የመሰለውን እንዲሰራ የሚፈቅድ መጅሊስ
የፈለገ መወሊድ እንዲያወጣ ፣ የፈለገ ጫት እንዲቅም ያልፈለገ ሳይቃወም ሊተው ወዘተ እያለ ሸሪኣ በመደንገግ ከአላህ ጋር የሚፎካከር ደፋር ተቋም ነው::
قوله تعالى: ﴿أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ وَلَوْلا كَلِمَةُ الْفَصْلِ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ وَإِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ﴾
4⃣ በሸሪኣም ሆነ በሀገር ህግ ባልተሰጠው ስልጣን የሚጨቁን አምባገነን መጅሊስ

በመሰረቱ መጂሊሳችሁ አንድ ተቋም እንጂ አሚር ወይም መንግስት አልነበረም:: ነገር ግን መስጂዶችን አስገድዶ በቁጥጥሩ እያስገባ ፣ መድረሳዎችን እያዘጋ ፣ የግለሰብ መስጂዶችን ጭምር በጉልበት እያዘዘ ፣ ትእዛዙን አልቀበል ያለን እያሸማቀቀ ፣ ኡስታዞችና ደረሶችን እያስደበደበ ፣ እና እያሳሰረ በግፍ የተሞላ ጥቁር ታሪክ እያስመዘገባላችሁ ነው::

በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ  አጋዦች ፣ አድናቂዎች እና አጋሮች ሆነው ሲያበቁ መሰል የመጅሊሱን ጥፋቶችና ጉዶችን "እኛ አልሰራነውም" የሚሉ አይጠፋም:: በጋራ የገነባችሁት ቤታችሁ መሆኑን አትርሱ::

የሞተው ወንድምሽ
የገደለው ባልሽ
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ
ከቤትሽም አልወጣ

አላህን ፈርታችሁ ተመለሱ :: በምድር ላይም አታበላሹ:: ከግፈኞች ታሪክ ተማሩ::

  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ)
http://t.me/Abuhemewiya

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

25 Nov, 16:13


🎤በሸይክ አ/ሀሚድ አልተሚይ ሀፊዘሁላሁ ተኣላ

🏙በሀላባ ቁሊቶ ካተማ

👉ስለ አስከፊው ወንጀል ሽርክ እየተብራራ ነው

ገባ ገባ በሉ

ሼር ሼር በማድረግ ላልደረሳቸው እናዳርስ


https://t.me/Ibnushaffi?livestream=3b681fd395b14f5323

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

21 Nov, 19:11


🛑 بسم الله الرحمن الرحيم

السلام عليكم ورحمة الله وبركات
🔴ሰበር ብስራት
ለወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ሰለፊይ ተማሪዎችና በአከባቢዋ የምትኖሩ ሰለፊይ ነዋሪዎች
እንኳን ደስ አላችሁ
እነሆ የፊታችን እሁድ ማለትም በቀን 15/03/17 በአይነቱ ለየት ያለና አጓጊ የዳዕዋ ዝግጅት በወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች መድረሳ በሆነችዉ ዑመር አል-ፋሩቅ መድረሳ ተደግሶ ይጠብቃችሗል

🔴 የእለቱ ተጋበዥ እንግዶች


1🎙 لفَضِيلَةِ الشَّيخِ أبي عبد الحليم عبد الحميد بن ياسين السني السلفي السلطي اللتمي «حفظه الله ورعاه»

1ኛ 🌺ታላቁና የተከበሩ ሸይኻችን የሱናዉ አንበሳ አቡ አብድልሀሊም አብዱልሐሚድ ብን ያሲን አስሱኒ አስሰለፊ አስ-ስልጢ አላህ ይጠብቃቸዉ

2ኛ🌷የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ የዑመር አልፋሩ መድረሳ አስተማሪ የሆኑት ዉዱ ኡስታዛችን
አቡ ኑሰይባ ሰይፈዲን ሳኒ አልላህ ይጠብቃቸዉ

ሌላም ተጋባዥ እንግዶች ይኖራሉ
በእለቱ አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል

🕌አድራሻ ከዩንቨርሲቲዉ ዋናዉ በር ፊት ለፊት 200m ገባ ብሎ

💥ፕሮግራሙ ሚጀምረዉ ከጠዋቱ 2:30 ይሆናል
በአካል መገኘት ማትችሉ ወንድምና እህቶች ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል
ይህን ሊንክ በመጫን መከታተል ይችላሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuluqmanReslan
https://t.me/AbuluqmanReslan

የፕሮግራሙ አዘጋጅ የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ የዑመር አል-ፋሩቅ መድረሳ ሰለፊይ ተማሪዎች ጀመዓ
https://t.me/wsumtj
https://t.me/wsumtj
✳️ለመለጠ መረጃ
📲0948413261=ረስላን ነጃ
     0910560832=ሰሚር በድሩ

የሰማህም ስማ ያልሰማህ አሰማ ሶዶ ትደምቃለች ከለተሚ ጋራ :: ኢንሻአልላህ

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

05 Nov, 18:15


በሀበሻዊዩ ታላቅ ዓሊም

[لا إله إلا الله، كلمة التوحيد]
የተውሒድ ቃሏ «ላኢላሃ ኢለሏህ»

🎙 الشيخ محمد أمان الجامي رحمه الله.
🎙 በሸይኽ ሙሐመድ አማን አል-ጃሚ አላህ ይዘንላቸው!


🏝 በ«ላኢላሃ ኢለሏህ» ዙሪያ እንዲሁም ተውሒድና ሽርክን በተመለከተ ጥሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
👏 አረበኛቸው በጣም ገር ነው ሁላችሁም አዳምጡት!
ሀገራችን እንዲህ አይነት ምሁራንን የፈሩባት ነች። በጣም ደስ ይላል።

https://t.me/AbuImranAselefy/9335

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

23 Oct, 20:51


በሙስልሞች ላይ የሚደርሱ በደሎች ልብን ያሳምማሉ፣ ሀዘንን ያወርሳሉ። ነገር ግን "አሏህ እንዲህ ለምን ያደርጋል?! ፣ አሏህ የሚፈጠረውን እያየ የለ እንዴ?!" ማለት ተገቢ አይደለም። እንደውም ከዚህም አልፎ ወደ ኩፍር የሚያደርሰውን ነገር የሚናገሩም አሉ። የትኛውም ነገር ከአሏህ የተሰወረ አይደለም። አሏህ በነገራቶች ላይ ሁሉ የራሱ የሆነ ጥበብ አለው። ከኛ የምጠበቀው የሚከሰቱ ነገሮችን ሁሉ አሏህ አዋቂ እንደሆነ፣ እሱ እንዲቆም ማድረግ በፈለገ ሰዓት ማቆም የሚችልና ዝም ስልም የራሱ ጥበብ እንዳለው ማመን ነው። እንደዛውም አሏህ የተሻለውን እንዲያመጣ፣ ከሙስልሞች በላእና መሰል የሆኑ ነገሮችን እንድያስወግድ ዱዓእ ማድረግ ነው።
الشَّيْخُ عَفِيفُ الدِّينِ يُوسُفُ بْنُ الْبَقَّالِ

شَيْخُ رِبَاطِ الْمَرْزُبَانِيَّةِ، كَانَ صَالِحًا وَرِعًا زَاهِدًا، حَكَى عَنْ نَفْسِهِ قَالَ: كُنْتُ بِمِصْرَ فَبَلَغَنِي مَا وَقَعَ مِنَ الْقَتْلِ الذَّرِيعِ بِبَغْدَادَ فِي فِتْنَةِ التَّتَارِ، فَأَنْكَرْتُ فِي قَلْبِي وَقُلْتُ: يَا رَبِّ، كَيْفَ هَذَا وَفِيهِمُ الْأَطْفَالُ وَمَنْ لَا ذَنْبَ لَهُ؟

فَرَأَيْتُ فِي الْمَنَامِ رَجُلًا وَفِي يَدِهِ كِتَابٌ، فَأَخَذْتُهُ فَقَرَأْتُهُ، فَإِذَا فِيهِ هَذِهِ الْأَبْيَاتُ، فِيهَا الْإِنْكَارُ عَلَيَّ:

دَعِ الِاعْتِرَاضَ فَمَا الْأَمْرُ لَكْ...وَلَا الْحُكْمُ فِي حَرَكَاتِ الْفَلَكْ
وَلَا تَسْأَلِ اللَّهَ عَنْ فِعْلِهِ ... فَمَنْ خَاضَ لُجَّةَ بَحْرٍ هَلَكْ
إِلَيْهِ تَصِيرُ أُمُورُ الْعِبَادِ ... دَعِ الِاعْتِرَاضَ فَمَا أَجْهَلَكْ

[ابن كثير، البداية والنهاية ط هجر، ٤٨٠/١٧]

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

11 Oct, 15:08


ኮንፈረንሱ የሚካሄድበት ቀን መተላለፉን ስለማሳወቅ

ጥቅም 3 አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ኮንፈረንሱ የሚካሄድበትን ጊዜ ወደ ፊት የምንገልፅ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናስታውቃለን።

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

11 Oct, 05:01


👉 የሚሊኒየም ፕሮግራምና የበዋና ሐዲስ

አንዳንድ ወንድሞች የሚሊኒየሙ ፕሮግራም ከሸሪዓ ጋር ይጋጫል እየተባለ ነው መረጃው ደግሞ የበዋና ሐዲስ ነው እየተባለነው የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ስለሆነ የተወሰነ ነገር ለማለት ተገደድኩ ።
በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ነገር ይቻላል አይቻልም ወይም ከሸሪዓ ጋር ይጋጫል አይጋጭም ለማለት ስለዛ ነገር ማወቅ ግድ ነው ። በመሆኑም ስለሚሊኒየሙ ፕሮግራምና የበዋና ሐዲስን ለማገናኘት ስለነዚህ ማወቅ የግድ ይሆናል ።
🔹 የበዋና ሐዲስ ማለት ብዙዎቻችን ኪታቡ ተውሒድ ውስጥ " ባቡ ላዩዝበሑ ሊላህ ቢመካኒን ዩዝበሑ ፊሂ ሊጘይሪላህ " ( ከአላህ ውጪ ላለ ነገር በሚታረድበት ቦታ ለአላህ አይታረድም ) በሚለው ባብ እንደምናውቀው አንድ ሰው መጥቶ ለነብዩ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – በዋና በሚባል ቦታ ግመል ለማረድ ስለት አድርጌያለሁና ልረድ ወይ ብሎ ጠየቃች ።
የአላህ መልእክኛ ዞር ብለው ለባል ደረቦቻቸው ይህ የተባለው ቦታ የመሀይማን ህዝቦች ከሚያመልኳቸው ጣኦታቶች ውስጥ ነበረበትን ? አሉ ። አይ አልነበረበትም አሏቸው ። ሁለተኛ ጥያቄ እንዲህ ብለው አቀረቡ " ከመሀይማን ህዝቦች ዒድ ይከበርበት ነበርን ? ( በተወሰነ ጊዜ እየተመላለሱ ዒዳቸውን ያከብሩ ነበርን ) አሉ ። አይ አሏቸው ። ወደ ሰውየው ዞረው ስለትህን ሙላ ( እረድ ) አሉት ።
🔹 ከሐዲሱ የምንረዳው : –
አንደኛ – አንድ ሰው የሚያጠራጥረውነገር ሲኖር የእውቀት ባልተቤቶችን መጠየቅ እንዳለበት ።
ሁለተኛ – ስለአንድ ነገር የተጠየቀ ሰው የተጠየቀው ነገር ባህሪይ ወይም ሁኔታ ዝርዝር ነገር ማወቅ የሚያስፈልገው ከሆነ ስለዛ ነገር መልስ ከመስጠቱ በፊት ዝርዝር ሁኔታውን መጠየቅ እንዳለበት ።
ሶስተኛ – አንድ ከአላህ ውጪ ያለ ነገር ሊመለክበት በተዘጋጀ ቦታ ላይ ንያው ቢለያይም ተመሳሳይ የዒባዳ አይነት መስራት እንደማይቻል ና የመሳሰሉት ይገኙበታል ።
🔹 የሚሊኒየም አዳራሽ ሁኔታ
ብዙዎቻችን ሚሊኒየም አዳራሽ ሲባል አእምሯችን ላይ የሚመጣው ፈሳድ የሚሰራበት ቦታ መሆኑ ነው ። ምክንያቱ አንዳንድ ጊዜ የምንሰማቸው የፕሮግራሞች ማስታወቂያዎች ሊሆን ይችላል ።
ነገር ግን ሚሊኒየም አዳራሽ ማለት ለክራይ የተሰሩ ብዙ አይነት አዳራሾች ያሉበት ቦታ ነው ። ስለዚህ ሚሊኒየም የተዘጋጀው ለአምልኮ ወይም ለበአል ማክበሪያ ተብሎ ሳይሆን ለኪራይ ነው ማለት ነው ። የተከራየው ሰው የፈለገውን ነገር ይሰራበታል ። በውስጡ 5ሺህ, 3 ሺህ, 2ሺህ, 1ሺህ ሰው የሚዙ የተለያዩ አዳራሾች ያሉበት ሲሆን ዋናውና የሚሊኒየም አዳራሽ በመባል የሚታወቀው 5 ሺህ ሰው የሚዝ ሲሆን የቀን ኪራዩ ወደ ሁለት ሚሊየን ብር አካባቢ ይጠጋል ። ውድ ከመሆኑ የተነሳ በአብዛኛው ትላልቅ የመንግስት ተቋማቶች ስብሰባ ነው የሚደረግበት ። አንዳንዴ የሀብታሞች ሰርግና የሙዚቃ ዝግጅት ሊደረግበት ይችላል ። ሌሎቹ አዳራሾች ከዚኛው በብዙ ነገር አይገናኙም ኪራያቸውም ዝቅ ያለ ነው ። ነገር ግን ሁሉም ለኪራይ የተዘጋጁ የንግድ አዳራሾች ናቸው ።
🔹 የኛ ኮንፈረንስ ከበዋና ሐዲስ ጋር ምን ያገናኘዋል ከተባለ መጀመሪያ ስለ አዳራሹ ዝርዝር መረጃ ቦታው ሄደን ጠየቅን ። ቀጥሎ ከመሻኢኾቻችን ጋር በሸሪዓ እይታ ተነጋገርን ። ማለትም ዑለሞችን በዚህ ቦታ ላይ ፕሮግራም ስለማዘጋጀት ምን እንደሚሉ ጠየቅን ውጤቱ ልክ እንደ ቦዋና ሚሊኒየም የጣኦት ማምለኪያም ይሁን የከሀዲያን ዒድ ቦታ ስላልሆነና የኛ ፕሮግራም በባህሪይ ከየትኛውም ሌላ ፕሮግራም ጋር ስለማይገናኝ ሸሪዓዊ ክልከላ የለበትም ይካሄድ የሚል መልስ አግኝተን ነው የጀመርነው ።
በመሆኑም የበዋና ሐዲስ መረጃነቱ ቀጥሉ ለሚለው እንጂ ተከልከሉ ለሚለው አይደለም ማለት ነው ።
የሚሊኒየምን አዳራሾች ምሳሌ በሌሎች ኪራይ ቤቶችም ማየት ይቻላል ። ለምሳሌ አንድ ሰው ለኪራይ ብሎ ቤት ሰራና መጀመሪያ ዘፋኝ ተከራየው በሙዚቃ አካባቢውን ሲቀውጥና ሲለማመድበት ቀይቶ ለቆት ሄደ ። ቀጥሎ ሌላ ሰው ተከራየውና እየሱስ ጌታ ነው እያለ የተወሰነ ጊዜ ቆይቶ ወጣ ። ከዛ ሙስሊም ተከራይቶት ይቀራበት ፣ ይሰገድበት ፣ ዳዕዋ ይደረግበት ጀመር እንደማለት ነው ።
ውድ ወንድሞች በእንደነዚህ አይነት ትላልቅ ጉዳዮች ላይ የምናውቀውን ሐዲስ ወይም ቁርኣን በራሳችን ግንዛቤ መረጃ አድርገን ብይን ከመስጠታችን በፊት ከኛ በላይ ያሉ ዑለሞችን መጠየቅ ይኖርብናል እላለሁ ።
አላህ በሐቅ ላይ ከሚመካከሩ ባሮቹ ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

09 Oct, 19:12


ምስጋና መግለጽን ይመለከታል

የኢትዮዽያ አህሉሱና ኢስላማዊ ማህበር አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ ጥቅምት 3/2017 የሚያካሂደው ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረስ እንዲሳካ ከቀልጣፋ አገልግሎት ጋር ከፍተኛ ትብብር ላደረጉለት:–
➡️ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት
➡️  ለሰላምና አስተዳደር ቢሮ
➡️  ለመረጃና ደህንነት ዋና ቢሮ
➡️  ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና
➡️  ለአ/አ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
     በራሱና በሱናው ማህበረሰብ ስም ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል ።

https://t.me/bahruteka/5442

የኢትዮዽያ አህሉሱና ኢስላማዊ ማህበር

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

09 Oct, 16:43


🔷የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር አጭር መልዕክት
=========================

በኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር የተዘጋጀውና በአይነቱ ልዩ የሆነው  ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ፣ አዲስ አበባ ላይ ይታወቃል።
ስለሆነም የእሁድ ስለተዘጋጀው የሚሊኒየም ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍረንስ በተመለከተ በተከበሩ ሸይኽ ሐሰን ገላው ሀፊዞሁሏህ እና ኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ የሰጡት አጭር መልእከት።

በተጨማሪም:- በአሏህ ፍቃድ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ መሻይኾች፤ ኡስታዞች፣ ዱዓቶች፣ ይኖራሉ።

ቀን:- ጥቅምት 3/2017

ቦታ:- በሚሊኒየም አዳራሽ (ቦሌ ኤርፖርት አጠገብ)

ከአቅም በላይ በሆነ ኡዙር ምክናየትበአካል የማትገኙ የተላለፉ ጠቃሚ መልዕክቶችን በባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ የቀጥታ ስርጭት (online) በአሏህ ፍቃድ የሚተላለፍ ይሆናል ስለሆነም አስፈላጊዉን ዝግጅት አድርጋችሁ ለወዳጅ ዘመድዎ፣ ለጓደኛዎ፣ለስራ ባልደረባዎ በመጋበዝ ጠብቁን።

የኮንፈረንሱ መሪ ሀሳብ:-
'' ዲናችንን ማወቅ፣ መተግበርና ማስተማር'' በሚል

የመግቢያ ትኬትዎን ቶሎ ከእጅዎ ያስገቡ!

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

08 Oct, 19:08


በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ

የኮንፈረንሱ መሪ ቃል “ዲናችንን ማወቅ መተግበርና ማስተማር”

🏝 የኢትዮጵያ አህለ ሱና ኢስላማዊ ማህበር ታላቅ ሀገር አቀፍ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጥቅምት ላይ   በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ አስቧል።
ለዚህ ፕሮግራም የአዳራሽ ኪራይ፣ ለተሳታፊዎች ሻይ ቡና ፣ ለዑለማዎች ትራንስፖርትና ማረፊያ ወዘተ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል የአንድ ሰው መግቢያ ትኬት 1000 ብር ነው።

🔹 ስለሆነም ትኬት በአካል መግዛት ለምትፈልጉ፦
➡️  አል ኢስላሕ መድረሳ
➡️  ዳሩ ሱና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

🔹በባንክ አካውንት ለምትጠቀሙ
የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000650550718
          ሙሒዲን ሳሊሕ እና ዩሱፍ ኸድር

   የኢትዮዽያ አህሉ ሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

07 Oct, 04:45


👉 የመሬት መንቀጥቀጥ

የመዲናችን አዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢ ነዋሪዮች ለሊቱን በጭንቀትና በስጋት ከህንፃዎች ወርደው መሬት ላይ ሆነው የሚሆነውን እየተጠባበቁ እንደ ነበር ሚዲያዎች ዘግበዋል ። ይህም የሆነው የመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት በመታዩቱ መሆኑን አስረድተዋል ።
የመሬት መንቀጥቀጥ ማለት መቅሰፍት ሲሆን ሚዲያ ላይ አንብበንና ሰምተን ከሚሰማን ስሜት ፍፁም የማይገናኝ አላህ ባሮቹን ሊያስፈራራበት ፣ ወደርሱ እንዲመለሱና ካሉበት የአመፅ ማእበል ወጥተው ከሱ ጋር እንዲታረቁ የሚያደርግበት ነው ። ሲከሰት ነገሮችን በሽርፍራፊ ሰከንዶች ውስጥ ወደ አለመኖር ፣ የሰዎች መኖሪያዎችን ወደ ቀብርነት ፣ ሽማግሌ ህፃናት እናቶችና አረጋዊያን የጣር ድምፅ እያሰሙ የዘረጉት የአድኑኝ እጃቸው ደራሽ አጥቶ በሲቃ የሞት ፅዋ ተጎኝጭተው በፍርስራሽ ስር እንዲቀሩ የሚያደርግ ፣ ሰው መሸሻና መግቢያ አጥቶ የሚያተርፍና የሚተርፍ ሳይኖር ሁሉም በተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ ሆኖ ወዳልተቆፈረ ቀብር መግባቱን የሚያረጋግጥበት ፣ ማንም ማንንም ማዳን የማይችልበት ከተማ ከያዘችው ነገር ጋር ላይዋ ታች ታችዋ ላይ የሚሆንበት አስፈሪ መቅሰፍት ነው ።
ለፉጡራን አንድ እናት ለጨቅላ ልጇ ከምታዝነው በላይ አዛኝ የሆነው አምላካችን አላህ እንዲህ አይነት መቅሰፍት የሚያመጣው አመፅና ሀጢያት ሲበዛ መሆኑን በተለያዩ መለኮታዊ ቃሉ ይነግረናል ። ከእነዚህ ውስጥ የሚከተለው ቃሉን እንመልከት :–

« ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ»

زالروم ( 41 )
" የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ) ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና " ፡፡

እንደዚህ አይነት ምልክቶችን የሚልከው ሰዎች ፈርተው ከሀጢያት ርቀው ወደርሱ እንዲመለሱ መሆኑንም እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –

« وَمَا مَنَعَنَا أَن نُّرْسِلَ بِالْآيَاتِ إِلَّا أَن كَذَّبَ بِهَا الْأَوَّلُونَ ۚ وَآتَيْنَا ثَمُودَ النَّاقَةَ مُبْصِرَةً فَظَلَمُوا بِهَا ۚ وَمَا نُرْسِلُ بِالْآيَاتِ إِلَّا تَخْوِيفًا »

الإسراء ( 59 )

" ታምራቶችንም ከመላክ የቀድሞዎቹ ሰዎች በእርሷ ማስተባበልና (መጥፋት) እንጂ ሌላ አልከለከለንም፡፡ ለሰሙድም ግመልን ግልጽ ተዓምር ኾና ሰጠናቸው፡፡ በእርሷም በደሉ፡፡ ተዓምራቶችንም ለማስፈራራት እንጂ አንንልክም " ፡፡
አላህ በዚህ አንቀፅ በመካ ከሀዲያን ላይ ተአምራትን ከመላክ የከለከለው ከዛ በፊት የነበሩ ህዝቦች ተአምር መጥቶላቸው አለማመናቸውና በዚህም ምክንያት መጥፋታቸው መሆኑና የመካ ከሀዲያንም ተአምር መጥቶላቸው ካላመኑ ሊጠፉ መሆኑን ከነገረን በኋላ ተአምር የሚልከው ሰዎች ፈርተው እንዲመለሱ ለማድረግ እንደሆነ ነው ።
በምድር ላይ የመሬት መንቀጥቀጥም ይሁን አውሎ ንፋስ ወይም የውሀ ሙላት አሊያም ወረርሽኝ የሚከሰተው በግልፅ የሚሰራ ወንጀል ሲበዛ ነው ። ሰዎች ወንጀልን በግልፅ ሲሰሩና ተዉ የሚል ሲጠፋ አላህ መቅሰፍትን ያመጣል ። መቅሰፍት ሲመጣ ወንጀለኞቹን ብቻ ነጥሎ አይመታም ። በወንጀል ላይ ምንም አስተዋፆ ያልነበራቸውንም ህፃናትን ፣ እንሰሳትንና ንፁሀንንም ጭምር ነው ።
ይህንንም አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –

« وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ »

الأنفال ( 25 )

" ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ " ፡፡

በመሆኑም ይህ በመዲናችን የታየው የመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት የማንቀያ ደወል ነውና እንጠንቀቅ ። መጠንቀቅ ማለት በሙሶሶ ስር መደበቅ ሳይሆን ከግልፅ ወንጀልና ሀጢያት በመራቅ ወደ አላህ መመለስ ነው ። በግልም በጀማዓም ከሚሰራ ሀጢያት መራቅ የሚሰሩትን ተዉ ማለት ብቸኛው አማራጭ ነው ።
በተለይ በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ላይ እየተሰራ ያለው ሀጢያት ህዝቡ ተዉ ብሎ ማስቆም ካልቻለ ራሱን ከአላህ ለሚመጡ መቅሰፍቶች ማዘጋጀት ይኖርበታል ። ከእነዚህ መቅሰፍት ከሚያመጡ ሀጢያቶች ዋና ዋናዎቹ የጣኦት አምልኮ ፣ የወንድ ለወንድ ወይም የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ፣ የግፍ ግድያና የመሳሰሉት ይገኝበታል ።
አላህ በመልካም አዞ ከመጥፎ ከልክሎ ከሚድኑት ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

27 Sep, 11:14


🟢አዲሱ ፀረ ኢስላም ዘመቻ = መሰብሰብና ማጃጃል

🛜 የጥመት መሪዎች ማህበረሰቡን ያደነዘዙበት ዋነኛ ስልት

🛜 ከዚህ በላይ ኡማውን የሚጎዳ ተግባር የለም።

🛜 ጭፍን ተከታይነት ለዲን ሌቦች ያጋልጣል

🔊ከአሸይኽ አማን አልጃሚይ ጠቃሚ ትምህርት


  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ)
http://t.me/Abuhemewiya

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

26 Sep, 20:21


👉 ኢኽዋኖች ለምን ይሆን ሳውዲን የሚጠሉት ?


ኢኽዋኖች ሳውዲን አይጠሉም መሪዮቿን ነው ልትሉ ትችላላችሁ ። አው ኢኽዋኖች የሳውዲ መሪዮችን እያከፈሩ የግብፅና የቱርክ መሪዮች ወሰን ባለፈ መልኩ ያሞካሻሉ ። በዚህም ሰዎች በተለይ ቱርክን እንዲወዱ ያደርጋሉ ። እነርሱም ቱርክ ላይ መኖሪያ እየገዙ ልጆቻቸውን ለጉብኝት ወደ ቱርክ ይዘው ይሄዳሉ ።
ለልጆቻቸው ስለ ቱርክ መሪዮች አድናቆትና የሳውዲ መሪዮችን ጥላቻ ያስተምራሉ ። በዚህም ከሳውዲ ይልቅ ቱርክን እንዲወዱ ያደርጋሉ ። ኢኽዋኖች ከቱርክ ዲን እንደማያገኙ ግልፅ ነው ። ታዲያ ምን ፈልገውና ምን አግኝተው እንደሆነ አላህ ይወቀው ።
ስለሚወዱት ቱርክ ማውራቱን ልተወውና ስለሚጠሉዋት ሳውዲ ጥቂት ልበል ።
የሳውዲ መሪዮችን በማስጠላት ሳውዲ እንድትጠላ የሚያደርጉት ኢኽዋኖች ለምን ይሆን ? የሳውዱ መሪዮች የሚሰሩት ስራ ሳውዲን በጥሩም ይሆን በመጥፎ እንድትጠራ ያደርጋል ። በመሆኑም ስለመሪዮቹ ስናወራ ስለሳውዲ ነው የምናወራው ማለት ነው ።
መሪዮቹ ሀገራችንን ጨምሮ በዐለም ላይ ተውሒድ እንዲነግስና ሽርክ እንዲረክስ አላህ በብቸኝነት እንዲመለክ ከሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ ዘመን አንስቶ እስካለንበት ዘመን ድረስ የተውሒድና የሱና ዳዕዋ እንዲሰራጭ ሰለቸኝ ሳይሉ ይሰራሉ ።
መሊክ ፈህድ ባቋቋመው ሙጀመዕ መሊክ ፈህድ ( የመሊክ ፈህድ ማተሚያ ድርጅት) ላይ ቁርኣን ፣ የቁርኣን ተፍሲር ፣ የሰለፎች ዐቂዳ ኪታቦች ፣ የሐዲስ ኪታቦች ፣ የፍቅህ ኪታቦች እየታተሙ ለዓለም በነፃ ይከፋፈላል ። በድምፅ የቁርኣን ተፍሲር በተለያየ ሀገር ቋንቋ እንዲፈሰር አድርጎ የሙኻሊፎች ዐቂዳ የለበትም ከተባለ በነፃ ያከፋፍላሉ ። ለዚህም ከዛሬ 25 በፊት በኦሮምኛ ቋንቋ የተፈሰረ የድምፅ ካሴት በነፃ መሰራጨቱ ትልቁ ማሳያ ነው ። ሸይኽ ሰዒድ ሙስጠፋ ከሪያድ ወደ ማተሚያ ድርጅቱ የሳውዲ መንግስት እንዲመጣ አስደርጎት መኖሪያ ተሰጥቶት በየወሩ ደሞዝ እየተከፈለው በአማርኛ ቁርኣንን በሁለት አመት አካባቢ ተርጉሞ ሳይሰራጭ ቀርቷል ምን ተገኝቶበት እንደሆነ ባናውቅም ።
ከተለያዩ ሀገራት ዱዓቶችን አስተምሮ ወደ ሀገራቸው ልኮ ተውሒድና ሱና እንዲያስተምሩ ለማድረግ የመዲና ኢስላማዊ ዩንቨርሲቲን በመክፈት ከ130 ሀገራት በላይ ተማሪዮችን እየተቀበሉ በነፃ የወጪ እየሰጡ አስመርቀው ይሸኛሉ ። አብዛኛው ሹፌርና ነጋዴ እየሆነ ቢያከስራቸውም ። ሌላው ከግብፅ ሰርጎ በገባ የኢኽዋን አካሄድ ውስጥ እየገባ ዞሮ ቢያከፍራቸውና ቢረግማቸውም ።
በዐለም ላይ ለዱዓቶችና ኢማሞች ባጀት መድበው በቢሊየን ወጪ ያደርጋሉ ። ወደ ሀገራችን የሚመጣውን ባጀት ሳይነጋ በሳውዲ ኤምባሲ በራፍላይ በመሰለፍ የሚቀድማቸው ሳይኖር ተከፋፍለውት የበሉበትን ወጪት ቢሰብሩና ያጎረሳቸውን እጅ ቢነክሱም ።
የሱፍያ ፣ የአሕባሽ ፣ የሺዓ ፣ የሙዕተዚላ ፣ የጀህሚያ ፣ የሙርጂዓ ፣ የኸዋሪጅ ፣ የኢኽዋን ፣ የተብሊጝ ፣ የሀዳድያና የሙመዩዓ ዐቂዳ በሰለፎች ዐቂዳ ውስጥ ሰርጎ እንዳይገባ ዑለሞቻቸው ቀን ማታ ሳይሉ በለፉበት ከመሪዮቹ ጋር በኢኽዋኖች ካፊር ይባላሉ ።
ከአላህ እዝነት ቀጥሎ ሀገራችን ላይ የነበረውና ዛሬ በመደመር መርህ ደብዛው እንዲጠፋ እየተደረገ ያለውን ነገር ግን አላህ በመረጣቸው ጥቂቶች የሞት ሽረት ትግል በሚከፍሉ መሻኢኾች እየተጠበቀ ያለው የተውሒድና የሱና ብርሀን በሳውዲ መሪዮችና ዑለሞች ሰበብነት ነው ።
የኢኽዋን መሪዮች ሙሐመድ ሰልማንን ማሞ ሰለሞን እያሉ እያከፈሩ አሁንም ረመዳንና ዒደል አድሓ ሲመጣ የሳውዲ ኤንባሲን ያጨናንቃሉ ። በየወሩ ኮርስ እያሉ አሳፋሪ ፕሮፖዛል ያቀርባሉ ። የሚገርመው ዞር ብለው መሪዮቿን ያከፍራሉ ይረግማሉ
ኦሳማ ቢንላድን አሜሪካ ላይ ሁለት ፎቆችን ከማፍረሱ በፊት በዐለም ላይ መስጂዶችን ፣ መራኪዞችን ፣ መዳሪሶችን ፣ በመገንባት , የቲሞችን ማሳደጊያና አቅመ ደካሞችን መንከባከቢያ ተቋማትን በመክፈት የሳውዲ መሪዮች የሚቀድማቸው አልነበረም ። የኺዋን የፊትና ማእበል አብዛኞቹን ይዞ ቢጠፋም ።
በሐጅና ዑምራ ጊዜ የምእራቦችን ዐቅል ግራ በሚያጋባ መልኩ ከዐለም የሚመጣውን ሙስሊም እንበዝብዘው ሳይሉ ተቀብለው እየኻደሙ ይሸኛሉ ። የፀጥታ ሀይሎቻቸው ከሶስት ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሚያይን በሚያስደምም መልኩ ይንከባከባሉ ። በዚህን ጊዜ የሳውዲ መሪዮች የሚያከፍሯቸውን ኢኽዋኖች በክብር እንግድነት ይጋብዛሉ ።!!!!!
አሁንም የሳውዲ መሪቶች በሳውዲ ውስጥ ሽርክ የሚባል ነገር እንዳይተገበር የተውሒድን ዳር ድንበር ይጠብቃሉ ። ድግምት የሚሰራን አንገት ይቀላሉ ። ለሳውዲ ህፃናት ሙታን ይመለካል ማለት አምላኪው ዐቅል የለውም ወይም እብድ ነው እንደማለት ነው ። ታዲያ ኢኽዋኖች እነዚህን መሪዮች ለምን ይሆን የሚጠሏቸው ? መልሱ ለራሳቸው ። የኢኽዋን ሙሪዶች ከእንቅልፋችሁ ንቁ መሪዮቻችሁ የሚታገሉት ለኢስላም ሳይሆን ለስልጣንና ለግል ጥቅማቸው መሆኑን እወቁ ። !
የግብፅና ቱርክ መሪዮች ለሽርክ ተግባር የፀጥታ ሀይል አሰማርተው ባጀት እየመድቡ ዶሪሕ እንዲመለክ ሲያደርጉ ማሞካሸትና አላህ ብቻ እንዲመለክ የፀጥታ ሀይል አሰማርተው ባጀት የሚመድቡ የሳውዲ መሪዮችን መጥላት ጤንነት አይደለም ።

https://t.me/bahruteka

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

24 Sep, 13:37


የሰለፎች አረዳድ አስፈላጊነት
              ከነሱ መለየት ያለው አደገኝነት

👌ጠቃሚ ምክር ከጠቃሚ ሸይኽ

🫴 አሸይኽ ሙሀመድ አማኑልጃሚዩ ረሂመሁሏህ

Join👇

https://t.me/sead429

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

24 Sep, 13:34


Channel photo updated

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

22 Sep, 03:46


በየ ሚድያው አሰራጩልን
የአደራ መልእክታችን ነው
ጀዛኩሙላሁ ኸይረልጀዛእ

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

19 Sep, 14:38


👉 የኸድርና የነብዩላሂ ሙሳ ታሪክ

ክፍል አንድ

ቁርኣን ላይ ትኩረት ከተሰጣቸው አስተማሪ ታሪኮች ውስጥ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ ነው ። በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁ አስተማሪ ነገር ማንም ቢሆን በእውቀት ጥግ ደርሻለሁ ማለት እንደሌለበት አላህ ከባሮቹ ውስጥ ለሚሻው ሰው ጥበቡ ባስፈረደው የእውቀት አይነት ለየት እንደሚያደርገው ።
በዚህ ታሪክ ውስጥ ነብዩላሂ ሙሳ ረሱልና ከዛም ከፍ ባለ ደረጃ ዑሉል ዐዝም ከሚባሉት ውስጥ ናቸው ። ኸድር ደግሞ በቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶችና እስካለንበት ዘመን ባሉ ተከታይ የኢስላም ሙሁራኖች እንደተረጋገጠው ነብይ መሆናቸው ነው ። በመሆኑም ኸድር ማለት ከነብያቶች ውስጥ አንዱ ናቸው ። ይህ ማለት በደረጃ ነብዩላሂ ሙሳ ይበልጣሉ ማለት ነው ። ምክንያቱም የረሱልነት ደረጃ ከነብይነት ደረጃ የሚበልጥ መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ። ነብዩላሂ ሙሳ ደግሞ ከረሱልም በላይ አምስቱ ዑሉል ዐዝም የተባሉት ውስጥ ናቸው ።
ነገር ግን የጥመት አንጃ የሆኑት ሱፍዮችና ሺዓዎች ይህን አስተምሮ በማስተባበል ኸድር ወልይ ነው አሉ ። እዚህ ጋር ቢቆሙ አንድ ነገር ነበር ነገር ግን ከዚህም አልፈው ሄዱ ። ወልይ ከነብይም ከረሱልም ከዑሉል ዐዝም ይበልጣል አሉ ። ለዚህህ ስህተታቸው መነሻው ደግሞ አላህ ነብዩላሂ ሙሳን ኸድር ጋር ሄደህ ተማር ማለቱ ነው ። ይህ ማለት ኸድር አላህ ዘንድ በደረጃ ከሙሳ ከፍ ያለ ስለሆነ ነው ልዩ እውቀት ሰጥቶት ከሱ ተማር ያለው አሉ ። በመሆኑም የኸድር እውቀት የውስጥ እውቀት ( ዒልመል ባጢን) ነው የሙሳ እውቀት ደግሞ የውጭ እውቀት ( ዒልመ ዛሂር ) ነው የሚል ፍልስፍና ውስጥ ገቡ ።
ከዚህ በመነሳት በእነርሱ እምነት የነብያት ተከታዮች የውጪውን እውቀት ነው የሚያውቁት የወልይ ተከታዮች ደግሞ የውስጡን ነው የሚያውቁት በመሆኑም የነብያት ተከታዮች የሸሪዓን ሚስጥር አያውቁም ላዩን ነው የሚከተሉት እኛ ደግሞ የሸሪዓን የውስጥ ሚስጥር ስለምናውቅ የውስጡን ነው ምንከተለው አሉ ። በዚህም ነብዩን ጨምሮ ሶሓቦችንና አጠቃላይ ቁርኣንና ሐዲስን የሚከተሉ የኢስላም ሊቃውንቶችን አላዋቂ መሀይማን አደረጉ ።
ይህ እምነታቸው ነው ዛሬ ላይ እየታየ ያለውን የኩፍርና የሽርክ ተግባር እንዲፈፅሙ ያደረጋቸው ። ምነው ሲባሉ እናንተ ስለማታውቁ ነው ኩፍር የሚመስላችሁ ነገር ግን የሙታን መንፈስ ማምለክ ፣ በቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ ፣ ወደ እነርሱ የተለያዩ ቁሩባን በማቅረብ እነርሱን መለማመን ፣ እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ አሽሩኝ … ወዘተ ማለት ተውሒድ ነው አሉ ።
ይህ በተሳሳተ መነሻ ላይ የተመሰረተ የተሳሳተ እምነት ነው ። የዚህ ማሳያው እንደሚከተለው ነው : –
1ኛ – ኸድር ነብይ እንጂ ወልይ አይደለም ።
የነብይነትና የወልይነት ደረጃ አይገናኝም ። የነብይነት ደረጃ በጣም የላቀ ነው ።
2ኛ – አንድ ሰው ሄደህ ከእገሌ ተማር መባሉ ያ
አካል ከሱ መብለጡን አያሳይም ። ይበልጣል ቢባልም በዛ በሚያስተምረው ጉዳይ ነው ሊሆን የሚችለው ። ይህን ወደ ታሪኩ ስንገባ በግልፅ የምናየው ይሆናል ።
3ኛ – የነብዩላሂ ኸድር እውቀት ለራሱ የተሰጠው
እንጂ ሸሪዓ ሆኖ ሊሰራበት አይደለም ። ሸሪዓ ቢሆን እንኳን ለነብዩ ተከታዮች ከዛ በፊት የነበሩ ነብያቶች ሸሪዓ ከቁርኣንና ሐዲስ ወይም ከነብዩ ሸሪዓ ጋር ከተጋጨ አይሰራበትም ሸሪዓም አይሆንም ።
ሱፍዮችና አሕባሾች እያጨማለቁት ላለው ኩፍርና ሽርክ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ በፍፁም መረጃ ሊሆን አይችልም ። ምክንያቱም በባጢል ላይ የተመሰረተ ነገር ባጢል ነውና ።
አላህ ለነብዩላሂ ሙሳ ከኸድር እንዲማሩ የፈለገው እሱ ዘንድ ካለው እውቀት ለሳቸውም ይሁን ለኸድር የተሰጠው በጣም ኢምንት መሆኑን ለማሳየት ነው ። ለዚህ ማሳያ በታሪኩ ላይ ከባህር ላይ የምትጠጣዋን ወፍ ምሳሌ እንዳደረገው ሁሉ ።
የነብዩን ሸሪዓ በፍልስፍና ውድቅ ያደረጉና ኩፍርና ሽርክ ያነገሱ ሱፍዮችና አሕባሾች ታሪኩ በእነርሱ ላይ እንጂ ለእነርሱ መረጃ አይሆናቸውምና በደንብ እንወቀው ። አላህ ካለ ሠዒድ ኢብኑ ጁበይር ከዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ ዐብዱላሂ ከኡበይ ኢብኑ ካዕብ ይዘው ባስተላለፉትና ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገቡት ሐዲስ ላይ እንደተዘገበው ሙሉ ታሪኩን የምናይ ይሆናል ። በሱረቱል ካህፍ ላይ ይህ ታሪክ ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን በአቀማመጥ ሐዲሱ ላይ የመጣው ይበልጥ ቀለል ስለሚል የሐዲሱን እናያለን ።

አላህ ካለ ይቀጥላል ።

http://t.me/bahruteka

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

19 Sep, 04:44


🟢ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ

ለነሲሃ ቲቪ ተፃፈው የተባለው “በመውሊድ ስንጨፍር በካሜራ ቅረፁን” አይነት ደብዳቤ አሳዛኝም አስተማሪም ነው።

👉አሳዛኙ
በሱና ማማ ከፍ ካሉ በኋላ ወድቆ ለሙብተዲዕ መሳለቂያ መሆን እጀግ ያሳዝናል።
እነ አጅሬ "ነሲሃዎች" ከዚህ በፊትም በርካታ የተጠለፉባቸው ወጥመዶች በደብዳቤ የጀመሩ ናቸው። ከሱፊዮችና መሰሎቻቸው ጋር በተለያዩ የሙጃመላ መድረኮች ላይ ስለሚተዋወቁ ነው የተናቁት ።
“ ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ ” እንደሚባለው ነው። በሱና ላይ የነበራቸው አቋም እንደቀለጠ ከጀይላን ጀምሮ ወዳጅም ጠላትም ነገራቸው ። ከዚህም በከፋ ጉዳይ እንደለመዱት እንተባበር ይሉ ይሆናል።

👉አስተማሪው
1️⃣አቋም በወረደ ልክ በጠላት መደፈርና ውርደት ይመጣል ።የአላህ እርዳታም ይርቃል።
عَنْ ثَوْبَانَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " يُوشِكُ الْأُمَمُ أَنْ تَدَاعَى عَلَيْكُمْ كَمَا تَدَاعَى الْأَكَلَةُ إِلَى قَصْعَتِهَا ". فَقَالَ قَائِلٌ : وَمِنْ قِلَّةٍ نَحْنُ يَوْمَئِذٍ ؟ قَالَ : " بَلْ أَنْتُمْ يَوْمَئِذٍ كَثِيرٌ، وَلَكِنَّكُمْ غُثَاءٌ كَغُثَاءِ السَّيْلِ، وَلَيَنْزِعَنَّ اللَّهُ مِنْ صُدُورِ عَدُوِّكُمُ الْمَهَابَةَ مِنْكُمْ، وَلَيَقْذِفَنَّ اللَّهُ فِي قُلُوبِكُمُ الْوَهْنَ ". فَقَالَ قَائِلٌ : يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَمَا الْوَهْنُ ؟ قَالَ : " حُبُّ الدُّنْيَا وَكَرَاهِيَةُ الْمَوْتِ ".
أخرجه أبو داود (4297) وصححه الألباني

ሰውባን አሉ ፥ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)አሉ፦" የጥመት ህዝቦች (ለጥቃት) ሊጠራሩባችሁ ይቀርባሉ ፤ ልክ በላተኞች ተሻምተው ወደ ሚበሉት ማዕድ እንደሚጠራሩት ።" ጠያቂ እንዲህ አለ ፥ ያኔ በቁጥር አናሳ በመሆናችን ነውን ? ነቢዩ (ﷺ) አሉ ፦ " እንዲያውም የኔ ብዙ ናችሁ ፤ ነገር ግን እንደ ጎርፍ ግሳንግስ ደካማ ናችሁ ፤ አላህም በእርግጥ ከጠላቶቻችሁ ልብ ውስጥ ለእናንተ የነበራቸውን ክብር  ነቅሎ ያስወጣል ፤ አላህም በእርግጥ በልባችሁ ውስጥ ውርደትን ይጥልበታል ።" ጠያቂ እንዲህ አለ ፥ ከምን የመጣ ውርደት ነው ? ነቢዩም (ﷺ) አሉ ፦ "የዱንያ ውዴታ እና ሞትን መጥላት (አኺራን መርሳት) ።

2️⃣ለጠላት ማባበያና ማቀራረቢያ አንዴ በር የከፈተ ዲኑን እና ክብሩን ለአደጋ አጋልጧል።
ከዕብ ኢብኑ ማሊክ ከገሳን ንጉስ የመጣለትን ማባበያ ደብዳቤ ምን ነበር ያደረገው  ⁉️

  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ)
http://t.me/Abuhemewiya

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

18 Sep, 11:55


አስደሳች የደርስ ዜና ለዲን እውቀት ፈላጊዎች

منظومة البيقونية
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ (ሀፊዘሁላህ) ሸርህ ይደረጋል

ቀን:- ዘውትር ሐሙስና ጁምዓ
ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

ደርሱ በአላህ ፈቃድ ነገ ሐሙስ ይጀመራል
የኪታቡ መትን የሌላችሁ መርከዝ ይዘጋጃል

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

14 Sep, 13:47


📌ከቢድዓና ከቢድዓ ባለቤቶች ማስጠንቀቅ ግዴታ ነው

👉ፉዶይል ብን ዒያድ - ረሂመሁሏህ - የቢድዓ ባለቤቶችን አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግሯል:-
"أحب أن يكون بيني وبين صاحب بدعة حصن من حديد"
رواه اللالكائي في "شرح أصول الاعتقاد" رقم (١١٤٩)
"በእኔ እና በቢድዓ ባለቤቶች መካከል (ፍጹም የማየገናኝ) የብረት አጥር ቢኖር እወዳለሁ"

በዲን ላይ የሚፈበረኩ አዳዲስ ፈጠራዎችን መራቅና ማስጠንቀቅ ግዴታ ነው። ምክንያቱም ከቢድዓ ባለቤት ጋር ወዳጅነት መፍጠር ልቦና ወደ ንፍቅና ፣  ሀላሉን እንደ ሀራም ፣ ሀራሙን እንደ ሀላል ፤ ቢድዓውን እንደ ሱና ፣ ሱናውን እንደ ቢድዓ ፤ ሽርኩን እንደ ተውሂድ ፣ ተውሂዱን እንደ ሽርክ ወደ መመልከት ይቀለበሳል።
አሏህ እኛንም እናንተንም ከልቦና መቀልበስ ይጠብቀን!

በቢድዓና በቢድዓ ባለቤቶች ላይ ያለውን የሰለፎችን  ፣ የቁርዓንና የሱናን አቋም ስናጠናው በእነርሱ ላይ ጠንካራ እርምጃ መወሰድ ፣ ከእነርሱ ማስጠንቀቅ እንደሚገባ ነው የሚጠቁመው።

ረሱል - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ቢድዓ ከመከሰቱ በፊት ነው ስለቢድዓ አስከፊነት ፣ መንገዱ ጠማማ እንደሆነ  በኹጥባቸው ያስጠነቀቁት።

በአገራችን የሚገኙ  የሙስሊሞች መሪ ነን ባዬች ግን በረሱል ተቃራኒ መድረክ ላይ ወጠው መውሊድ መልካም ተግባር እንደሆነ ፣ በተሻለ፣ በተጠናከረ ፣ በደመቀና  ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ በዓሉ እንደሚከበር ይደሰኩራሉ። ቢድዓን ያጠናክራሉ - አሏሁል ሙስተዓን -

ተወጋጅ ለሆነችው የአጭር ጊዜ ስልጣን ብለው በዚህ ድርጊታቸው ከሞት በኋላ የሚከሰተውን የአላህን ከባድ የሆነ የእሳት ቅጣት እንዴት ነው የማይፈረት?! ለምን ሀቁን ተናግረው ከመሸበት አያድሩም?  ህዝብን እያጭበረበሩ እስከመቸ ነው የሚኖሩት? እስኪ መውሊድን በተመለከተ ከተማሩት ከሚያስተምሩት ከቁርአን ከሀዲስ ከፉቀሀዎች ኪታቦች መረጃ ያቅርቡ። "ባቡል መውሊድ አንነበውይ" የሚል ረሱል የተወለዱበትን ቀን ማክበር በተመለከተ አንድ ርዕስ ወይም ክፍል ማቅረብ ይችላሉ?

ነገ የቂያማ ቀን ከአላህ ፊት ሲቀርቡ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ምን አይነት ምላሽ ይሰጡ ይሆን?

ህዝበ ሙስሊሙ ሆይ!  እነዚህ መሪዎች እስካልቶበቱ ድረስ ልትርቃቸው  ይገባሀል እንላለን!!
ለመውሊድ በምታወጣው ገንዘብ ፣ በምታባክነው ጉልበትህና ጊዜ ከአላህ ፊት ተጠያቂ ትሆናለህ እንላለን!!! ገንዘብህን ፣ እውቀትህን፣ ጊዜህን ፣ ጉልበትህን ለሱና አውል!!! አደራ! አደራ!ከአሏህ ዘንድ የተነባበረ ምንዳ ታገኛለህና

ረሱል - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ቁርዓንን ፣ ሱናቸውን ፣ በቅን ጎዳና ላይ የነበሩትን የነ አቡበክርን የነ ኡመርን የነ ኡስማንን የነ አልይን ሱና አጥብቀን እንድንይዝ ፣ በልዩነት ሰዓት ማንኛውም ሙስሊም ሱናቸውን በመንጋጋ ጥርሱ ነክሶ እንዲይዝ ፣ ቢድአንና የቢድዓን ባለቤት እንዲርቅ ነው የመከሩን።

የቢድዓን ባለቤት መራቅ አለብን።
ወደ ቢድዓ ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ከወዲሁ መሸሽ አለብን።

ከነዚህ መካከል ከሙብተዲዕ ጋር የሚደረገው መቀላቀል ነው። "መውሊድ አይለየንም" የሚለው የኢኽዋን መፈክር አይሸውድህ።ከመውሊድ  ሰዎች ጋር አትቀላቀል - እሳት ያገኝሀልና ፣ ጥመት ውስጥ ትገባለህና።

ይህ በብዛት ሰዎችን ቢዳዓ ላይ እንዲወድቁ የሚያደርግ ነው። እንዲህ አይነቱ ሰው ቆይቶ የለየለት ሙብተዲዕ ይሆናል።  ለሱና እና ለሱና ባለቤቶች ተቃራኒ ይሆናል። የሱና ሰዎችን ያነውራል ፣  ኢልም ፈላጊዎች ከሱና አሊሞች እንዳይማሩ ፣ የነሱን ዳዕዋ እንዳያዳምጡ ቅስቀሳ ያደርጋል ፣  ሰዎችን  ከሀቅ ጎዳና ያግዳል። የኢብሊስ ተባባሪ ይሆናል።

ከቢድዓ ከጥመት ከንፍቅና ከክህደት እንዲጠብቀን ፣ በእውነተኛው ዲን ላይ እንዲያጸናን አላህን እንማጸናለን


https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

13 Sep, 16:19


رسالةٌ جديدةٌ لأبي طلحةَ أبي ذر بن حسن الولوي

ننصَحُ كلَّ طالبِ علمٍ شرعيٍّ أن يّطّلِعَ على هذه الرسالةِ النافعةِ بإذن الله

1,828

subscribers

229

photos

45

videos