ቀጥተኛ እምነት @fistumtehadiso Channel on Telegram

ቀጥተኛ እምነት

@fistumtehadiso


“እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።” ዮሐ 8፥32 ።

ቀጥተኛ እምነት (Amharic)

ከእነዚህ መነሻ ቀጥተኛ እምነት እባኽሉን፣ የሚገኙበት አስተያየት ስናመሠረት በቀላል የማናወጣው ነው። ምርጫ ምክንያት፣ ወርሃዊ ትንሳኤን እና አልተማረኩም ለምሳሌ፣ ቀላል ሕመምና ታሪክ ለምሳሌ፣ የአምልኮት ሰነዶችና በብዙ ጊዜ በዚህ በኩል የምንባርክልኝበት መልክ ነው። ከሌሎች ስለሆነ ቀጥተኛ እምነት ስለዚህ እናመሰግናለን። እጅግ የሚቀመጠውን ቴሌግራም አስተያየት ለምሳሌ፣ በእምነት እና አልተመሠረተበትን ወጣሩን መፈፀም ይችላሉ።

ቀጥተኛ እምነት

06 Dec, 12:04


ስለ ውሃ ጥምቀት በሚገባ እንዳልተረዳን አስተውያለሁ ። እኔም የተማርኩት የውሃ ጥምቀት አፍአዊ ምስክርነት ብቻ በማድረግ ነው።ማለትም ለሰዎች ጌታን ተቀብለናል ለማለት በውሃ ጥምቀት እንደሚናሳይ እንደሚንመሰክር ብቻ ማሰባችን ስህተት ነው።

የውሃ ጥምቀት ልዩና ድንቅ የእግዚአብሔር መለኮታዊ አሰራር የሚፈጸምበት ነው። አዳማዊነት ተነቅሎ ፥ የክርስቶስ ማንነት የሚተከልበት ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን የሚያስታራቅ አስታራቂ ነው።pdf ገጽ 31 ይመልከቱ!
[የተጨመረ ነው በበፊቱ ጽሑፍ ላይ]

ቀጥተኛ እምነት

06 Dec, 11:56


1.ስለ ትምህርቴ ሥላሴ https://t.me/FistumTehadiso/799
2.ስለ ቅድሜ መከራ ንጥቀት https://t.me/FistumTehadiso/1259
3. ስለ መዳንና ቅድስና https://t.me/FistumTehadiso/1294
አንብቧት!

ቀጥተኛ እምነት

24 Aug, 04:20


🌱ትምህርቴ ሦስትነት በአንድነት፣
🌱የቤተክርስቲያን ቅድሜ መከራ ንጥቀት አስተምህሮ በቃለ እግዚአብሔር ስመዘን፣
🌱ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን የሚያስታርቅ አስታራቂ ፣

እስካሁን እነዚህን መጻሕፍትን [በpdf] አቅርቤያለሁ ፦ https://t.me/FistumTehadiso ። ስለዚህም ነገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ። በትንሿ መክሊቴ ለማትረፍ ተጣጥርያለሁ። የነገውን ጌታ ያውቃል ።

ቀጥተኛ እምነት

23 Aug, 06:52


#መሰዊያ_ታቦት_አለን|| “መሠዊያ አለን፥ ከእርሱም ሊበሉ ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ መብት የላቸውም።” ዕብ 13፥10

የብሉይ መቅደስ አገልግሎት ሙሉበሙሉ ዋናው አካሉ እስኪመጣ ድረስ የሚያገለግል ስለኾነ፣ ለሐዲስ አገልግሎት ስፍሯን ለቋል፤ አገልግሎቱን ጨርሷል ። ጌታችንም ሊቀ ካህናት እንደመኾኑ መጠን መሰዋዕቱን በምድር ባለችው መቅደስ [ድንኳን] አላቀረበም ። ራሱ በሠራት በሰማያዊት መቅደስ ስለኛ መስዋዕቱን አቅርቧል ። በዚህም የብሉይን አገልግሎት አስረጅቶ የሐዲስ ኪዳንን አገልግሎት በሰማይ #በይፋ አስ|ጀምሯል ። ዕብ 8፤9።

ጌታችን በሰማይ መቅደስ ባስጀመረው አገልግሎት ከቀደሙት በሚልቅና በሚሻል መልኩ ፣በአንድ ጊዜ ባቀረበው መስዋዕት ብቻ እስከዛሬ ያገለግላል ። ጌታችን ድካምና ሞት የሌለው ስለኾነ፣ ሌላ አዲስ ሊቀ ካህናት ሳይተካ እስከዛሬ ድረስ በብቃት ያገለግላል ። አንድ ጊዜ በምድር ያለቀሰልን፣ የለመነልን ፤[ዕብ 5]፣ በሰማይ ያቀረበልን መስዋዕት ቅቡልነት ስላገኘ ፣ እንደገና እንደ አዲስ "ማሪልኝ ይቅርበላቸው" በማለት መለመን ሳይስፈልገው፣ ከአባቱ ጋር ቊጭ ብሎ ያስታርቃል ። ስለኛ ይነጋገራል ።1ዮሐ 2። ኢየሱስ ዛሬ ላይ ሳይለምን ስለሰው ልጆች አንድ ጊዜ፣ ባደረገውና በከፈለው መስዋዕት ያስታርቃል ። ኢየሱስ አኹንም ሊቀካህናት ነው። በሰማይ መቅደስ የሚያገለግል ።

በሰማይ መቅደስ አለ፤ በመቅደሱም መሰዊያ አለ፤ በመሰዊያውም መሰዋዕት አለ። ጌታችን እንደ መሰዋዕትነቱ በመሰዊያው [በታቦቱ] ያለ ፦መስዋዕት ነው። ጌታችን በጸሎት ጊዜ በምሳሌው [በቡሉይ] አገልግሎት እንደተገለጠው፣ ከመሰዊያው መስዋዕቱን በመንፈስ ለሕዝብ ይሰጣል ። ዘሌ 10። ቅዱስ ቁርባን ጌታችን ከዚሁ መሰዊያ የሚሰጠን መንፈሳዊ መብል ነው። ለመቀበል በጸለይን ጊዜ መብሉና መጠጡ ወደ አምላካዊ ሥጋና ደምነት ይቀየራል ። ይኽ ጥልቅና ታላቅ ምስጥር ነው።በገባኝ ልክ በመጽሐፌ ለማስረዳት ሞክሬያለሁ፦ https://t.me/FistumTehadiso/1294 ይመልከቱ።

መቅደሱና በውስጡ ያለው ታቦት [መሰዊያ] በሰማይ አለ። በምድር እነኚህን የሚወክል [ቁስ] የለም። "አለ" ከተባለም በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የመቅደሱ አገልጋይ ሊቀ ካህናቱም አንድ ብቻ ነው። አይተከው ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ነው። እስራኤላውያን ሰለሞን በሠራት መቅደስና በውስጥ ባሉት መሰዊያና በመቅደሱ እቃዎች ለመገልገል እንጂ ሌላ ለመሥራት አልከጀሉም። ስላልተፈቀደ፤ የተሻለ መሥራትም ስለማይችሉ። እኛስ ጌታ በሰማይ; ራሱ በሠራት መቅደስ ልንገባና ልንገለገል እንዴት አብልጠን መውደድ ይገባን ይኹን?
. . .

ቀጥተኛ እምነት

22 Aug, 18:31


በጣም ኮርቼባችኋለሁ። እናንተ የብዙዎች ተስፋ የሚታለመልሙ ብርቱዎች ናችሁ። ለብዙዎችም በረከቶች ናችሁ። የብዙዎች እንግልት ታስወግዳላችሁ ።የብዙዎችን ጉድለት ታሞላላችሁ፤ ትሸፍናላችሁ።

#እራሳችሁ በዚህ ልክ በመሥራታችሁ ተደነቅሁ ፤ የቤተክርስቲያን በረከት ናችሁ። እንግዲህ በርቱ፤አትታከቱ 👐
***
https://youtube.com/watch?v=s8aOzzREGoA&si=THaOdxU09GR69Kha&fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR2PfFGuapXG9VqtwMJBJMEHcSjy2UawULS-8wSMBZ6UTyZyZvUuZS7sr98_aem_mn21kIoV6s5ZR3AXSZNWuQ

ቀጥተኛ እምነት

14 Aug, 19:31


"የክርስቶስ ሥራ አለመረዳት በድንዛዜ እንዲኖርን ያደረገኝም ስለኾነ፣ ሌሎችን እንደኔ ለነበሩት ለማገዝ የአቅሜን ለማስረዳት ተጣጥሪያለሁ። ..

በዚህ ጽሑፍ ... ስለተቀበልነው ሕይወት እንደሚገባን በኃላፊነት መመላለስ እንደሚገባንና ከኃላፊነት የጎደለውን በማድረግ ከሕይወት መጉደል እንዳይመጣ ግንዛቤ ለመስጠት ጥረት ተደርጓል ። በክርስቶስ ለመኖር እግዚአብሔር ያደረገልንን የሰጠውን ስጦታ ለማስረዳት ብሎም #ስለ_ቅዱስ_ቁርባን ብዥታን የሚያጠራ ቀጥተኛ ትምህርት ለማቅረብ ተሞክሯል ።" [ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን የሚያስታርቅ አስታራቂ፤ ከመጽሐፉ መግቢያው የተወሰደ!]

ቀጥተኛ እምነት

13 Aug, 13:49


በትዕግሥት እንዲታነቡ በታላቅ ትህትና እጠይቃችኋለሁ። አንዳንድ ብዥታዎችን ለማጥራት ስለ ቅዱስ ቁርባን [ ] በቀጣይ አቀርባለሁ..

""በጌታ እራት ጊዜ መለኮታዊ አሠራር [መለኮታዊ ንክኪ] እንዳለው እንወቅ። የጌታ እራት እንደ ተዝካር ያለ መታሰቢያ አይደለም ። ቅዱስ ቁርባን ሰማያዊ መንፈሳዊ መብል ነው። በምንበላው እንጀራና በምንጠጣው ጽዋ የወልድ መለኮት ያርፍበታል፤ ለሰውነታችንም የሚያስፈልገውን ኹሉ ይሰጣል ።"
...

ቀጥተኛ እምነት

10 Aug, 17:26


ከማቴዎስ ወንጌል ጥናቴ [33]
“ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?” ማቴዎስ 6፥25፣26-34 ።

በዚህ ክፍል ላይ ጌታችን በተራራው ለተሰበሰቡት ሕዝብ፣ የሚበልጠውን ነገር እንዲያውቁ ትምህርትን ይሰጣል ። ደግሞም ስለ ፍላጎታችንም እዚሁ የሚቀረን ነገር ለማግኘት እንዳይኾን ያስገነዝበናል ። የሰማዩ ወፎች ለነገ መብል በመሰብሰብ በመጠመድ ባይጨነቁም እንኳ እንደሚመግባቸው እና የሚጠፋውን የሜዳ አበባ ከንጉሥ በላይ እንደሚያለብስ፣ እኛን ይልቁንም ከእነዚህ ፍጥረታት ለሚንሻል፣ የሚበልጠውን ነገር አብልጦ ልያደርግ' እንደሚችል ያስረዳል ። ይገርማል ።

ጳውሎስ “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ #ሁሉን_ለእግዚአብሔር_ክብር አድርጉት።” [1ኛ ቆሮ 10፥31]፣ እንዳለው ጌታችን በእያንዳንዱ ጉዳዮቻችን ለክብሩ እንዲናውል ጣልቃ ይገባል ።ለዚህም ነው ስለሚንበላው ኾነ ስለሚንለብሰው በመጠንቀቅ ለክብሩ መጠቀም ያለብን። ምክንያቱም ጌታችን ከእነዚህም ግል ጉዳዮቻችን [አካሄዶቻችንም] ክብርን ለማግኘት ይፈልጋል ። የሚፈልገውን ክብርን በመስጠት ስሙን ማክበርና ማስከበር ቀዳሚ ምርጫችን ልኾን ይገባል ።

እናም ዛሬ የነጣ የደኸየ ኹሉ፣ጌታ የተሻለ ነገር ልያደርግ እንደሚችል ልያምን ይገባል ።በብርቱ። እነዚህን ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት ብለን በመጎብጀት የሚናደርገው ነገር ኹሉ ለኃጢአት ተላልፎ የሚያሰጥ ስለኾነ፣ ነገሮቻችን እንደሚለወጡ በእርሱ በማመን ፣ ለዛሬ የሚያስፈልገንን በብርቱ እንደ ወፎች በመሥራት ማግኘት፤ደግሞም ለነገ የሚያስፈልገውን እንዲያሟላልን መከናወንን እንዲሰጥ በእርሱ ላይ ተስፋ መጣል ይገባናል ። የክፍሉ ሃሳብ ለዛሬ የሚበቃውን በርትቶ መሥራትን የሚያበረታታ ስኾን፣"ነገ ምን እኾናለሁ?" የሚለውን ጭንቀት እንዲናስወግድ ያስገነዝበናል ። ከመሠረቱ ለዛሬ በርትቶ የሚሠራ ለነገ በመጎምጀት [ቊጭ ብሎ እየተመኘ ለማግኘት] የሚጨነቅ እንደማይኾን ያውቋል። ለዛሬ የሚሠራ አዕምሮ; ከሰይጣን ክስ ይጠበቃል ።ለመጎምጀት ስፍራ የለውም ። ዛሬ በርትቶ በመሥራቱ ለነገ መሪ ያለውን ሕይወትን ያበጃል እንጂ አይጨነቅም፤ አይመኝም።

ወዳጆቼ ጌታ ዛሬ ላይ በርትተን ስንሰራ ነገሮቻችን እንደሚቀየሩ እንጂ ዛሬ ያገኘነውን ዛሬውኑ ጨርሶ ቤት መግባትን የሚያበረታታ አይደለም ።ምክንያቱም ኢየሱስ ቊጠባን አይቃወምም ። ይሁዳ ባንከሩ [ገንዘብ ያዡ] እንደኾነ ያውቋል ። ስለዚህም ዛሬን በርትቶ በእምነት መሥራት፣ ነገን ቊጭ ብሎ በመመኘት አለመጨነቅና ስለነገ በጌታችን ላይ መጣል ፤የጌታችን ትምህርት ነው። የጭንቀት ምንጭ አለመሥራት ነው።ምኞትን ይወልዳል። ዛሬን የሚሠራ ለነገ በር ይከፍታል እንጂ አይጨነቅም ። አዕምሯችን በራሱ ዛሬን አመስግነን እንድንኖር እንጂ ስለነጊያችን እንዲያስብ አልተፈቀደም ። ስለነገ በአግባቡም ልያስብም አይችልም ።ስለዚህ ወዳጆጄ ዛሬን በእምነት ብርቱ ኾኔን እንመላለስ። ተባረኩ። ቊ.32 https://t.me/FistumTehadiso/1279 ይመልከቱ።

ቀጥተኛ እምነት

09 Aug, 12:56


የተከዳው አገልጋይ ሊቀ ካህናት!

ጌታችንን በሰማይ ባለች በእጅ ባልተሠራች፣ ራሱ በተከላት በመንፈሳዊት መቅደስ "የሚያገለግል ሊቀ ካህናት ነው፣ ስለእኛ የቆመ የተቀመጠ የኛ ወክል ነው" ስንል ከክብሩ ዝቅ አድርጋችኋል፣ እርሱ ለመፍረድ የተቀመጠ እንጂ የሚያገለግል ሊቀ ካህናት አይደለም ይላሉ። በእርግጥም ጌታችን በመስቀል ላይ አንዴ ባቀረበው መስዋዕት፣ማንም ስለራሱ የቀረበ መስዋዕት አድርጎ ብቀበል በእምነት ፈውስን የሚሰጥ እንደኾነ እንጂ ልመና በእርሱ ዘንድ አኹን የለም። አብ በእርሱ በኩል የሚመጡትን ኹሉ፣ ስለከፈለው ዋጋ በቂነት ቅቡልነት ስለሰጠው እንዲያው ይምራል። በክርስቶስ ያለቀው ሥራ "ስለነ ነው" በማለት በማመን ብቻ ለተቀበለው ሰው የክርስቶስ ሥራ ይቈጥርለታል።

ጌታችን ሊቀ ካህናት እንደመኾኑ መጤን በኢኦተቤክ መከዳቱን ልገልጽ እወዳለሁ ። በተአምረ ማርያም በ7ኛው ተአምር የመጽሐፉ ጸሓፊ እንዳሰፈረው ፣ የማርያም ሥጋ ወደገነት ከፈለሰ [ከሄደ] በኋላ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ሥጋዋ ላይ #ገባሬ_ሠናይ_ቄስ ሁኖ አሁት። የዲያቆናትም አለቃ እስጢፋኖስ ከእርሱ ጋር #ስያገለግል ዮሐንስም ለእግዚአብሔር በፍርሃት ቁሙ ስል፣.." በማለት ይገልጻል [በ64ቱ ተአምር ገጽ 61 ከቊ.17-18]። በዚህ መጽሐፍ ላይ እንደተገለጸው ከኾነ፣ ጌታችን እንደ ሊቀ ካህናትነቱ የሚለምን[ቀዳሽ] ኾኖ የሚያገለግል እንጂ የተቀመጠ ኾነ የሚፈርድ አይደለም ። ጥያቄው እንዲህ በመጻሕፍት የኢየሱስን አገልግሎት "በቀዳሽነት ልመና አቅራቢነት" የሚትገልጹ ከኾነ "ኢየሱስ አማላጅ ነው" ስባል የሚጎረብጠው ስለምንድነው ? ይኽ ሥራ ከአምላክነቱ አያሳንስም?

ቀጥተኛ እምነት

09 Aug, 07:05


ድካም

በጌታ ለኾነ አማኝ ሥጋው ከኃጢአት በሂደት እየነፃ ይሄዳል ። ሥጋ ለጽድቅ ሕያው በመኾን በአማኙ ሕይወት መንፈሳዊነት እንዲገለጥ ያደርጋል ። በዚህ ሂደት ላይ አማኝ በአንድም በተለያየ ሁኔታዎች በተለያየ ጊዜያት፣ የሌለ የሚመስለው ሥጋዊ ባሕርይ ስገለጥ ድካም ይባላል ። የአማኙ ሥጋዊነት የተገለጠበት ኹኔታ ድካሙን ጉድለቱን ስያሳይ፤ ስህተት ልባልም ይችላል ። ይኽንንም ጉድለት ካጋጠመው ነገር በመረዳት፣ ያለበትን መንፈሳዊ ሁኔታ[ደረጃ] በማስተዋል የሚያስፈልገውን ጸጋ በመለመን ነፃ መኾን ይቻላል። በሕይወት እስካለን ድረስ ድካም አለ። ለዚህም ነው ፍጹም የኾነውን ነገር ለመልበስ የሚንቃትተው። ሥጋችን ኹሌም በባሕሪው ፍጹም ስላይደለ ። የማንም ።

ይኹን እንጂ ድካም በኃጢአት መመላለስ ማለት አይደለም ። ወይም ከኃጢአት ነፃ መውጣት አለመቻል ማለት አይደለም ። ድካም ሥጋችን ከያዘው ባሕርይ አንፃር መንፈሳችንን የሚያስጨንቅ ኃይል ነው። ገላ 5። አልፎ አልፎ ልገለጥ ይችላል ። ኾኖም የሚገዛ አይደለም ። ድካም እንዳንታበይ የሚያደርግ ትህትናን የሚያስተምር ነው። ድካም ይኽ ነው እንጂ በኃጢአት መጠመድ ተጠምደው መሞትን የሚያመላክት አይደለም ። በኃጢአት ተጠምደው መሞት በክርስቶስ ያለመኾን ኹኔኛ ማሳያ ነው። ጉድለት አይደለም ። ፍጹም ያለመዳን ምልክት ነው።
....
ድካም ለናንተ ምንድነው?

ቀጥተኛ እምነት

08 Aug, 16:37


"ጠበል ፈለቀ" በማለት በውሸት አጥማቂ ነኝ በማለት የሚሠሩት መኖራቸውን እኚህ አባት ይገልፃሉ ። ልክ ጴንጤዎች ጋ ባለራዕይ ነቢይ ሐዋርያ በማለት ኑሮ ስከብዳቸው የራሳቸውን አጥቢያዎችን የሚከፍቱ ግለሰቦች እንዳሉ።

ሃሰተኞች እንደ እምነታቸው ደካማ ጎን መሥራታቸው ይደንቃል ። መጠንቀቁ መመርመሩ አይከፋም!

ቀጥተኛ እምነት

07 Aug, 01:03


በስምንት መቶ ሜትር የብር መዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘችው ጀግናው አትሌት አነጋጋሪ ኾናለች። ኢየሱስ በተሰደበበት ኢየሱስ ጌታ ነው ማለቷ፣ በኢየሱስ መሰደብ ያዘኑትን አስደስቶአቸዋል። በሌላ በኲል ደግሞ ከለመዱት [ስዕለ አድኖ] ውጪ የኾነውን ስላሳየች አብዘኛውን የተዋሕዶ አማኞችን አላስደሰታቸውም ። ኢየሱስ ጌታ ነው ማለቷ ግን እንዲህ ምቾት መንሳቱ ይደንቃል ። ኾኖም አትሌቷ ከዚህ በፊት በሱራፌል ደምሴ "እግርሽ መለኮት ተቀላቅሎበታል ወርቅ፣ ዋንጫ ታመጭያለሽ" በማለት ዘይት በማፍሰሱና አትሌቷም ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለውን የተመለከቱት አማኞች ከደስታቸው ባሻገር ማዘናቸው አልቀረም ።

*በዚህ ውድድር ላይ ኾነ በስፖርት ባጠቃላይ ማንም ሰው በትጋቱ ልክ ዋጋውን ያገኛል እንጂ ምንም አይነት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት አንደኛውን በመርዳት ሌላኛውን በመቃወም የሚደረግ እንደሌለ ልገልጽ እወዳለሁ ። ሰው ልፋቱ ስሳካ የሚያምነው አምላክ ማመስገኑ ወጉ ነው[እንደ እምነቱ] እንጂ ልዩ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት የለውም። ስለዚህም ተውት፤ አይጠቅማችሁም እላለሁ!

ቀጥተኛ እምነት

05 Aug, 16:09


“የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥”
— 2ኛ ቆሮ 10፥5

ቀጥተኛ እምነት

04 Aug, 02:17


Channel photo updated

ቀጥተኛ እምነት

03 Aug, 10:54


ወንጌል መስክርያለሁ በሚል ምክንያት፣ ወደ ጌታ በመጣው ላይ እራስን መቁለል፣ ጭራ ይዞ ለዘላለም እንዲከተል ለማድረግ ፣ የሚለውን እየደገመ አሽቃባጭ አድርጎ ለማኖር የሚደረገው ጥሬት ከዛሬ አስተማሪ ነኝ ባይ ግለሰቦች መነሳት አለበት ። ወደ ጌታ የመጣውን ለጌታ ተውት። ለጠራው ጌታ በሰጠው ጸጋ ይመላለስበት ዘንድ፤ተውት። የናንተ ዓላማ አስፈጻሚ ለማድረግ አትጣሩ። የተፈታውን ለጌታ ተውት። እንደተፈታ ይመላለስበት። ምንም ብኾን የሚቀድመው እኔ ነኝ፣ ወደጌታ የጠራሁት እኔ ነኝ በሚል ተልካሻ ምክንያት ሰውን ከጌታ ለመቀማት የሚደረገው ጥሬት መቆም አለበት ። እናም ወዳጆቼ; ከአስተማራችኹ በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንደ ፊልጶስ ይንጠቃችኹ። እናንተም ከተማራችኹ በኋላ እንደ ኢትዮጵያዊ ጃንዴረባ ጌታን በእምነት እየተመለከታችኹ መጓዝ ይሁንላችኹ። አገልግያለሁ በሚል ተልካሻ ምክንያት የሰው ሰውን መኖሪያ አታድርጉ!

የዛሬ መምህራን ለሃሳባቸውን ድጋፍ ስትሰጥ፤ አብዝተው ይወዳሉ፣ ሃሳብህ ከሃሳባቸው ስለይ ደግሞ ያድቡብሃል፣ ቆፍጠን ብለህ በቃሉ ስትጨቅን ሃሳብህ ላይ ሳይኾን፣ #አንተነትህ ላይ ያድባሉ፤ ወርደው ሥጋዊ ወጊያ ይጀምራሉ። ለመምታት ወሽቀው ስህተትንም ፍለጋ ይንከራተታሉ ፤ይኳትናሉም ። የኛ አስተማሪዎች አብሮነታቸው እስከ ሃሳባቸው ድረስ ነው! ይኹና😓። ድሮስ ማንን አብቅተው ያውቃሉና 👐

*ታናሽን ስለሚያበቃ ጳውሎስ ግን እንዲህ ይናገራል፦ “ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ #ማንም_ታናሽነትህን_አይናቀው።” 1ኛ ጢሞ 4፥11-12 ። በከንፈራቸው የጌታ ደቀመዛሙርቱ ኹን ይሉና፣ በተግባር ግን የራሳቸው አሽቃባጭ ካልኾንክ ይላሉ!፤አትስማቸው እግዚአብሔር እራሱ ያስተምራል፤ ይመራል፤ ያሳድግሃል።

ቀጥተኛ እምነት

01 Aug, 11:05


ደግሞም ሌላ ብዙ ስጦታ ከእህቴ እታሌም ሸዋንዳኝ[https://www.facebook.com/profile.php?id=100082077650604 ] ተሰቶኛል ። ክበርልኝ እህቴ፤ በወጣ ይተካ። ከሚዲያ እየራኩ አሪፍ ጊዜ በጽሞና ለማሳለፍ ውዱን ምግብ የሚበልጠውን [መጻሕፍትን] አግንቻለሁ። እስከማነባቸው ጓግቻለሁ። እነዚህ መጽሐፍት ወደኔ እንዲደርሱ የረዳኸኝ ወንድም ደሳለኝ ሻምበል ከልብ አመሰግናለሁ ።በነገራችን ላይ ወንድም ደሱ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለአርባምንጭ አከባቢ ላሉ ሰዎች በትጋት ያቀርባል [https://www.facebook.com/desalegn.shambel.98] ።አርባምንጭ አከባቢ ያላችሁ ሰዎች የሚትፈልጉትን መጽሐፍ ጠይቃችሁ ግዙ፤ ከፖስታ ቤት ወጪ ያተርፋችኋል።

የኔ ነገር አልጨመረም ትላላችሁ 😂
ስለሰጠኸኝ ወዳጆቼ ተባረክ ። ከክፉ ኹሉ ጠብቃቸው። በውስጣቸው ስለሚባርኩም ወዳጆች ተባረክ። ለምልሙልኝ😓

ቀጥተኛ እምነት

01 Aug, 05:33


በአንድ አጥቢያ አንድ ዘማሪ ብቀጠር ...

ቤተክርስቲያኒቱ የመዝሙር አልበም እንዳለው ካመነች፣ መዝሙር ተሰርቶ ብወጣም ባይወጣም፣ ጸጋው መኖሩ ስለተረጋገጠ መቀጠር ብቻል መልካም ነበር። ይኽንን ማድረግ ቀላል የማይባል በጎ ተጽዕኖ ይፈጥራል ። ዝማሪያኑ በመዝሙር ዘወትር ስያገለግሉ ወንጌል ቀለብ ማስፈለጉ ጥያቄ ልኾን አይገባም ። [በመቅደሱ ሥራዓት እንኳን ዘማሪያን ካህናት ነበሩ]። ዘማሪያን አንድ የኾነ መድረክ ላይ ዘምረው የሚረሱ ከኾነ፣ ለዕለት እንጀራ ፍለጋ ውስጥ ገብተው እንዳይጠፉ የሚያስፈልጋቸውን ቤተክርስቲያን ቸል ባትል መልካም ነበር።
ይኽ ብደረግ ቤተክርስቲያን ዘማሪያኑን "ሃሰተኞች ናቸው" ካለቻቸው ጋር ሕብረት እንዳያደርጉና ከነርሱ ጋር እንዳይታደሙ ልታደርግ ትችላለች ። የዝማሬ አገልግሎት ጸጋው ባለው ሰው ላይ ብወድቅ፣ የሰንበት ተማሪዎች የሚዲያ ውጤት ከመኾን መጠበቅ ይቻል ነበር። ይኽ ዘርፍ እንዲሁ ለስሙላ እንደ ፕሮግራም ማሟምያ ተቈጥሮ በማንም እጅ ላይ ልወድቅ አይገባም ። በዝማሬያኑ ስር ሰንበት ተማሪዎች ብቧደኑ ብዙ ልምድ ይቀራመታሉ። ብዙ ፍሬዎችም ማግኘት ይቻላል ።ደግሞም ከዝማሬ አገልግሎት ጋር ተያይዘው የሚነሱት እንደ ሃገር ያሉ ችግሮችን ፣ወጥ በኾነ መልኩ መቅረፍ ይቻል ነበር።

ለትልቅ ችግሮች መዋቅራዊ የኾነ ሰንሰለታማ የኾነ አሰራር ያስፈልገናል! እናም እንደዚሁም ለትምህርት ችግሮች ዕቅበተ እምነት አደረጃጀት መዋቅራዊ ኾኖ ብደራጅ ማለቴን ያውቋል፣ https://t.me/FistumTehadiso/481

ቀጥተኛ እምነት

31 Jul, 17:38


አደባባይ ወንጌል መስካሪዎች አብዛኛዎቹ..

አኹን በሀገራችን ያደባባይ ወንጌል መስካሪዎች በአብዛኛው የብልጽግና ወንጌል [የቃል እምነት አስተማሪዎች ፍሬ] የሃሰተኛ ነቢያት ቀኝ እጅ ኾነው የሚመላለሱ ናቸው ። አገልግሎቱ ግን ትልቅ ዋጋ ያለው በእግዚአብሔር የተወደደ ሥራ ነው። ነገርግን በአደባባይ ስለወጡ ብቻ [ስሙን ስለጠሩ]፣ የክርስቶስ ወታደር አድርገን መመልከት ትልቅ ሞኝነት ይኾናል ። በሐዋርያቱ ዘመንም ከነርሱ ጋር ከነበሩት አንዳንዶች ፣ከመሃከል ወጥተው ልዩ ወንጌልን በየሰፈሩ በየሃገሩ እየዞሩ ያስተምሩ ነበር። ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲያ ያሉትን በመታለል እንዳይቀበሉ ምዕመናትን አስጠንቅቋል ።2ዮሐ።
እናም ምንም እንኳን ከባዱ መንገድ ብኾንም፣ በየመንገዱ ስለወጡ ብቻ የያዙትን መንፈስ ሳያጣሩ ፣የያዙትን ትምህርት ሳይፈትሹ መቀበል ኾነ መተባበር አደጋው ቀላል አይኾንም ። ምክንያቱም የክርስቶስ ጠላት የኾኑትም ፈረሳዊያንም አንድን ሰውን ለማሳመን በየመንደሩ በባሕርና በየፍስ ይሄዱ ነበር። እናም ወዳጆቼ; በሚዲያ ኾነ በአከባቢው የምታውቋቸውን ለዩ፤ ጨዋ በመኾን [ባለማወቅ] እንዳትታለሉ ። ተጠንቀቁ!

ቀጥተኛ እምነት

30 Jul, 02:56


የዓለም ጠቢባን የዓለም ፍጻሜ ልኾን እንደተቃረበ አምነውና ሰግተው፣ የራሳቸውን መደበቂያ በፍጥነት እየገነቡ ናቸው ። ጌታችንም አስቀድሞ እንዲያ እንደሚያደርጉ ለዮሐንስ በገለጠው ራእይ አመላክቷል [ራእ 6፥12-17]። ይኹን እንጂ ቊጣው ስገለጥ የሚሠሩት ዋሻ ኹሉ በላያቸው ይደራመሳል፤ ይኽንን አውቀው ከመከራው ለመትረፍ ወደ ጌታ ብመጡ፣ ባዘጋጀው ስፍራ ላይ በእንክብካቤ ይጠብቃቸው ነበር። የሰጠው ተስፋ አለና። ኖኅን በመርከብ የመከራውን ጊዜ እንዳሻገረ፣ ቅድስት ክብርት ምዕመናትን [ሴቲቱን] ባዘጋጀው ስፍራ ይሽሽጋታል። ራእ 12።

ቀጥተኛ እምነት

29 Jul, 02:09


ከማቴዎስ ወንጌል ጥናቴ [32]

ማቴዎስ 6፥¹⁹ ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤²⁰ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤²¹ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።²² የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤²³ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!²⁴ ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

ይኽ ክፍል [ከሉቃስ 16፥1-14]፣ ድረስ ካለው ክፍል ጋር ተመሳሳይ ነው። ገንዘብ; በአግባቡ ከተጠቀምን ምድራዊ እንቅስቃሴያችን ቀሊል ያደርግልናል ።
ጌታ ለምድራዊ አገልግሎት ይኾን ዘንድ ከሕዝቡ የሚሰበሰበውን ገንዘብ ማንም ለግል ጥቅሙ እንዳያውል ያስጠነቅቃል። "በምድር አታከማቹ" የሚለው ቃል አትቆጥቡ ማለቱ አይደለም ። መቆጠብን ሰርቶ ማደግን ባለጠጋ መኾንን ጌታችን አይጸየፍም። ራሱም ብኾን በምድር በሚመላለስበት ወራት ይቆጥብ ነበር። ይሁዳ ገንዘብ ያዡ ነበር ። ይሁዳ ግን በተሰጠው ኃላፊነት በታማኝነት ከማገልገል ይልቅ፣ ለግል ጥቅሙ በመስረቅ ምድር ላይ ሃብትን አከማቸ፤ ገንዘብን አገለገለ፤ አመለከ።

የገንዘብ ኃይል; በሰው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ከሌለ፣ ልመለክ ሰውን ልቆጣጠረው የሚችል ጣኦት ነው። የሰውነታችን መብራት መንፈስ ቅዱስ ከኾነ፣ ገንዘብ ኃይል አይኖረውም ። በዚህ ክፍል ላይ አገልጋዮች ለተሰጣቸው ኃላፊነት ታማኞች እንዲኾኑና የማይገባቸውን እንዳይቀበሉ ያስረዳል ። ይኽም ጽድቃችን ከፈረሳዊያን ጽድቅ እንዲበልጥ ጌታችን ያስተማረው ነው። ነገርግን አገልጋዮች የሚሰበሰበውን ገንዘብ 'ለራስ ባለጠጋ' ለመኾን ብጠቀሙ ይጸየፋል ። ከእግዚአብሔር ዘንድም ብድራት አይኖርም። እንዲሁም በአገልግሎት ስም በስሙ ገንዘብን ብሠሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ አንዳች ብድራት አያገኙም ።ወደ ውጪ ይጣላሉና። ስለዚህም የጌታችን መልእክት ዛሬም ይኽ ነው፣ በእግዚአብሔር ስም ለአገልግሎት ተብሎ የሚሰበሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅም በማዋል ጥሪት[ሃብትን] ለራሳችሁ የሰበሰባችኹ ወየውላችኹ። ጣኦትን አገልግላችኋልና ንስሐ ግቡ!
ቊ.31 https://t.me/FistumTehadiso/1267

ቀጥተኛ እምነት

28 Jul, 16:38


ከ"ኦርቶዶክሳዊት ተሃድሶ" ከሚባለው ተቋም ኾነ እንቅስቃሴ ጋር...

በልብሱ;በዚያ ሥርዓቱን ስላደግንበት፣ ራሳችንን ልዩ አድርገን ተመለከትን፣ ለሰው መዳን ይኽ ባሕል፣ ይኽን ያህል አስፈላጊ አልነበረም፤ ለኛ አዕምሮ እንጂ። ስለዚህም ከዱሮም; በዋህነት ስሙን ይዘው ፣ ያለ ሰው ሥራዓት [ዘዴ] ያለ ገደብ ጌታ የሠራባቸውን አስተዋልኩ ። በዚህ ሥራዓት እራሴን ማሰሬን ጠልቸዋለሁ። ከ"ኦርቶዶክሳዊት ተሃድሶ" ከሚባለው ተቋም ኾነ እንቅስቃሴ ጋር ሕብረት እንዳለኝ በየትኛው ኹኔታዬ እቈጥርና እናገር ነበር። እናንተም ይኽንን ታውቃላችኹ ።እስከ ቅርብ ቀናት ድረስ። ስለሚፈልግ ስለወደድኩ። ነገርግን ሕብረት የለኝም። ምንም አይነት ግንኙነት ኾነ ዓላማ ከማንም ጋር የለኝም!

*ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር ሕብረት እንዳለኝ በማሳበቀ ያተረፉኩት #በጎርጥ_መታየትና ብችኝነት ብቻ ነበር ።[በኹሉም😓] ። ፈለኩ ወደድኩ ግን በዚህ አልታደልኩም። ግን ጌታ አልጣለኝም፤ ይጎበኘኛል፤ ይሠራኛል፤ ያሳድገኛል፤ ይመራኛል።

ከእንግዲህ መሸሸጊያዬ የኾነችው ተቋም ማረፊያዬ ብቻ አትኾንም መኖሪያዬ ጭምር ትኾናልኛለች፤ የሰውኛ ተሃድሶ[ተቋም] ጋር ሕብረት የለኝም። እኔ ነኝ ራሴን ከእነርሱ እንደ አንዱ የቈጠርኩት እንጂ ከማነኛይቱም ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም፤ እነርሱም አያውቁኝም ። ከእንግዲህ እኔም እንዲሁ። እና የተሃድሶ ድርጅት ዓላማ የማራምድ አይደለሁም ። ተሐድሶ የሚለው ስም ከኔ ይፋቅ ዘንድ አሳውቃለሁ። እለምናለሁ🙏 ።በዚህ አታውቁኝ ።

*እኔ ያመንኩትን ከቃሉ በቅንነት የሚናገር፣ ድምፅ ብቻ ነኝ👐[የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን አባል ከኾንኩ 3 ዓመት ይኾነኛል፤ እዚህ የሚለጥፈው ግን የተቋሙን ትምህርት አይደለም፤ አቋሜም የራሴ ነው! ጥፋት ብገኝብኝ [ለሚናገረው ቃል] እኔው ብቻዬ ኃላፊነቱን የሚወስድ መኾኔን አሳውቃለሁ። እናም በጽሑፍ [በዚህም ገጽ] ትምህርት የማካፍለው፣ ሚዲያን ለወንጌል ብጠቀም መልካም ነው በሚልና ጸጋውን የሰጠው እርሱ ስለኾነ አተርፍበትም ዘንድ ነው፤ይጠይቀኛልና ። ይኸው ነው። እወቁልኝ ለማለት ነው፤ ይጠቅመኛል!

ቀጥተኛ እምነት

27 Jul, 01:06


የቤተክርስቲያን ቅድሜ መከራ ንጥቀት አስተምህሮ አትቃወም ይሉኛል፣ "ክርስቶስ ከመከራው በፊት በስውር መጥቶ በስውር ይወስደናል፣ አየር ላይም ለ7 ዓመት የበጉ ሰርግ ይደረግልናል " የሚለው #ባዶ_ተስፋ ብዙዎችን አደንዝዞ ጠፍሮ ይዟል ። የምሬን ነው የምላችኹ; በውሸት ተስፋ እግዚአብሔር ባልሰጠው እንዲያ ልሸነግላችኹ አልፈልግም!

“እንኪያስ እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን?” [ገላ 4፥16]