ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ @haletapt Channel on Telegram

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

@haletapt


Get healed!!

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ (Amharic)

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ ላይ የተናገረ ሰምተኛ ማስታወሻ ቤተሰባችንን ሰላም! ከኦርጋንድ እስከ ንዑር፡ቢቢ እና ለምለም፡ስልካችን በእናቶችና ካልሲን፡፡ ከየትምህርት ፍቃድ እና ትምህርት፡ልዩም ሰራዳ የግቢ፡አፕሎን ሊኪኒክ በኤክሶደስ ፊዚዮ ለመከታተል በህግ ውስጥ የሚገኝ እና ወደውኃለሁ! ለአስተያየት መረጃዎችና አባልንና ድምጽዎን ለማሳለጠ፡፡ የእንቅስቃሴ ሙዚቃችንን በተነገርኋቸው ቀን ለመጣል የፈለገ ይሆናል! እስከ ሌላ መስፈር፡፡ እናታችን በኤክሶደስ የተለያዩ ልዩነቶችን ምን እንላል? እንዴት እንመናህል፡፡ እንደምንበርሽህ እንፀዲ፡፡

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

18 Dec, 08:01


ለጠቅላላ እውቀት!
ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች
8 ምርጥ ምግቦች

1) ገብስ:- ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።

2) ባቄላ እና ዘሮቹ:- ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

3) እንቁላል(በመጠኑ):- እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።

4) አሳ:- የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።

5) የአበሻ አይብ:- የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።

6) የወይራ ዘይት:- በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ ዘይት ከፍተኛ anti inflamatory ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የሚዋጋ ባህሪይ አለው ማለት ነው።

7) ስኳር ድንች:- ለምሳሌ ያህል በድንች ፋንታ ስኳር ድንች መብላት ደም ውስጥ ያለው ስኳር 30% ያህል ከፍ እንዳይል ያግዛል። ስኳር ድንች በበሽታ ተከላካይ ፋይበር የበለጸገ ነው። ከዛ ውስጥ 40% የሚሟሟና ኮለስተሮልን የሚቀንሱና digestion በፍጥነት እንዳይካሄድ የሚረዱ ናቸው። ሌላ ደግሞ በ ኦሬንጅና ቢጫ carotenoids የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም ሰውነታችን ለ insulin respond እንዲያደርግ ይረዳሉ። ከዛ በተረፈ በ chlorogenic acid የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም የስኳር በሽታ መንስኤ የሆነውን insulin resistance ይዋጋሉ።

8) ቀይ ስጋ በመጠኑ:- ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

10 Sep, 17:11


ለመላው የሀገራችን ኢትዮጵያ ህዝቦች መልካም አዲስ አመት እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችን ነው!!
~ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በውቢቷ #ባህርዳር ቀበሌ 14 አካባቢ መክፈቱን በደስታ እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን 0979099909 / 0985048080 ይደውሉ!

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

19 Aug, 03:40


Best sleeping positions 👇👇
for more information 0979099909 / 0911039377

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

12 Aug, 11:01


የስትሮክ ምልክቶችን ያውቃሉ?
〰️🔹〰️💎▪️💎🔸〰️

F.A.S.T = ሲተነተን ይህን ይመስላል:-

F: Face (ፊት)
A: Arm (እጅ)
S: Speech (አነጋገር)
T: Time to Hospital (ሆስፒታል የምደርስበት ሠዓት)

ፊት - Face
▪️

🔹የፊት አንድ ጎን መደንዘዝ

👉🏿 ፈገግ ለማለት ሲሞክሩ ፈገግ ማለት አለመቻል ወይም አንድ የከንፈር ጫፍ ወደላይ ሌላኛው ወደታች መቀልበስ።

እጅ - Arm
▪️

🔹የአንድ እጅ መዛል

👉🏿 ሁለቱንም እጅ ከፍ ለማድረስ ሲሞክሩ አንድ እጅ አልታዘዝ ማለት።
👉🏿 ሁለቱንም እጅ ከፍ ማድረግ ይችላሉ፤ ነገር ግን አንድ እጅ ዝሎ ወደታች ይወርዳል።

አነጋገር - Speech
▪️

🔹የአነጋገር መጎተት

👉🏿 መናገር ይከብዳል።
👉🏿 የሚናገሩት ነገር ትርጉም አይሰጥም።
👉🏿 ቀላል ዓረፍተ ነገር ደግመው እንዲናገሩ ሲጠየቁ ለመድገም ይቸገራሉ።

ሠዓት - Time to hospital
🔺▪️▪️🔺

🔹በተቻለ ፍጥነት ሆስፒታል መሄድ።

👉🏿 እነዚህ ለውጦች በድንገት ሲታዩ ቶሎ ወደ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል።

ከእነዚህ ውጭ ሌሎች የስትሮክ ምልክቶች
🔺▪️▪️🔺💎🔺▪️▪️🔺

ድንገት የሰውነት መደንዘዝ ወይም በግማሽ የሰውነት ክፍል ሰውነትን ማዘዝ አለመቻል።

▪️ድንገተኛ የማገናዘብ ችሎታ መቀነስ፣ ለመናገር መቸገር ወይም ሌላ ሰው የሚናገረውን መረዳት አለመቻል።

▪️ድንገት የማየት ችሎታን ማጣት።

▪️ድንገት መራመድ አለመቻል ወይም የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል።

▪️ድንገተኛ፣ ምንም ምክንያት የሌለው ሀይለኛ ራስምታት ናቸው።

ጠቃሚ ምክሮች
▪️

💎 ህክምና ለማግኘት የሚፈጀው እያንዳንዱ ደቂቃ ለውጥ ያመጣል!

💎 በአንጎል ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እና ህክምና ለማግኘት፤ ምልክት ከታየ በኋላ ባሉት ሶስት ሠዓት ውስጥ ሆስፒታል መድረስ ያስፈልጋል።

🔺▪️▪️🔺🔸💎🔸🔺▪️▪️🔺

መልካም ጤንነት!!

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

27 Jul, 05:10


ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ ከዲስክ መንሸራተት ጋር ለሚመጡ የነርቭ ጉዳቶች መፍትሄ ያግኝ ይዳኑ ይልዎታል!!
አድራሻችን አዲስ አበባ 22 መክሊት ህንፃ አካባቢ ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን
~በቅርቡ በውቢቷ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ሁለተኛ ቅርንጫፋችንን በይፋ እንጀምራለን
~ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን 0911039377 / 0979099909 ይደውሉ!

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

26 Jul, 04:51


#ለጠቅላላ_እውቀት
ከሽንት ቀመሳው ታሪክ ስንመለስ...

#ስለስኳር_ህመም (#Diabetes_Melitus)

#ክፍል_አንድ


ምነው ስኳር ስኳር ብላችሁ ሞታችሁ? የሚል ሰው ካለ

በአሁኑ ወቅት:

👉422 ሚሊዮን የዓለም ሕዝብ ስኳር አለበት (በ1980 ይሄ ቁጥር 108 ሚሊዮን ገደማ ነበር!)

👉በዓመት ከ>1.5 ሚሊዮን በላይ ለሆነ ሞት ምክንያት ነው።

👉ከአደጋ ቀጥሎ ዋና የእግር መቆረጥ መንስኤ ነው።

👉ግንባር ቀደም የኩላሊት መድከም ምክንያት ነው።

👉ከሌሎች አጋር ህመሞች ጋር በመሆን (የደም ግፊት) ደም ስሮች እንዲጠቡና እንዲስተጓጎሉ ያረጋል።በዚህም በርካታ የሰውነት ክፍለች ይጐዳሉ።

👉ከሁሉ የሚበልጠው ጉዳይ ግን ይህንን ሁሉ የሚያደርገው የስኳር ህመም በአብዛኛው ምልክት አልባ ሆኖ ሳይታወቅ መቆየቱ ነው።

⚠️ለመሆኑ ስኳር ለምን ይከሰታል⁉️
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘

🟤አብዛኛው የምንመገባቸው የምግብ አይነቶች በካርቦሃይድሬት የበለፀጉ ናቸው።
🟤እንጀራ፣ዳቦ፣መኮሮኒ፣ሩዝ፣ፓስታ፣ድንች፣ኬክ፣ቸኮሌት ወዘተ በካርቦሃይድሬት የበለፀጉ ምግቦች ናቸው።

🟤አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ከነዚህ ውስጥ አንዱን ሳይመገብ አይውልም።

🟤እነዚህ ምግቦች ከተበሉ በኋላ ወደጥቃቅን የካርቦሃይድሬት ደቃቅ ሞለኪዩሎች ይለወጣሉ።

🟤የሁሉም መጨረሻ ግን #ግሉኮስ (#ስኳር) በመሆን ወደ ህዋሳት መድረስ ይሆናል።

🟤ህዋሳት ግሉኮስን(#glucose) በመጠቀም ለህልውናቸው የሚያስፈልጋቸውን ሀይል ያገኛሉ።

🟤ግሉኮስ ወደ ህዋሳት ገብቶ የተፈለገውን ሀይል ያመነጭ ዘንድ አንድ #አስተናባሪ ያስፈልገዋል።

🟤ይሄ አስተናባሪም #ኢንሱሊን (#Insulin) የሚባለው ነው።

🟤ኢንሱሊን ከቆሽት የሚመነጭ ቀላል መዋቅር ያለው ፕሮቲን ነው።

🟤ቆሽት (#Pancreas) ከኢንሱሊን ውጪ የተለያዩ ተግባር ያላቸውን ቅመም ኢንዛይሞችንና ሆርሞኖችን የሚያመርት ወሳኝ ክፍለ አካል ነው።

🟤አብዛኞቹ በቆሽት የሚመረቱ ቅመሞች ምግብ የሚያልሙ (የሚፈጩ) በመሆናቸው በተፈጥሮ እያንዳንዱ ቅመም ከተመረተ በኋላ ወደ ሚፈለግበት እስኪሄድ በየራሱ ከረጢት ተቋጥሮ ይቀመጣል።በተለያዩ ችግሮች ከተቋጠሩበት ከረጢት ከፈሰሱ ግን ራሱን ቆሽቱን ያሳርሩታል።

ምናልባት እናቶቻችን ቆሽቴን አታሳርረው ሲሉ ይሄ ገብቷቸው ይሆን🤫🤫

❇️ከስኳር አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ሌላ የሚነሳው ክፍለ አካል #ጉበት ነው።

❇️ጉበት የተለያዩ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ማቀነባበሪያና ማምረቻ ሆኖ ያገለግላል።

❇️በተጨማሪም የተለያዩ መድሃኒቶችን ጨምሮ ሌሎች ቆሻሻዎችን ላወጋገድ እንዲመቹ አርጎ ያበጃጃቸዋል።

❇️ብዙ ካርቦሃይድሬት (#ሀይል_ሰጪ) ከተመገብን በኋላ ህዋሳት ከሚጠቀሙት የሚተርፈውን አቀነባብሮ #ግላይኮጅን(#Glycogen) ወደሚባል የክፉ ቀን ስንቅ ለውጦ ያኖረውና ሰውነታችን በቂ ምግብ በማያገኝበት ወቅት ያን የተከማቸ ግላይኮጅን መልሶ ወደ ግሉኮስ ስኳር እየቀየረ ሴሎች እንዲጠቀሙት ያረጋል።

ይቀጥላል !!
✍️ Dr Wihib Gebrehiwot

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

20 Jul, 13:15


ለጠቅላላ እውቀት!!

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

01 Jul, 06:16


#ለጠቅላላእውቀት
#ኤክሶደስ_የፊዚዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክን
ሄፓታተስ ቢ ምንድንነው?

ሄፓታይተስ ቢ ጉበትን የሚያጠቃ ቫይረስ ሲሆን ለጉበት በሽታ /Chronic liver disease/ መንስኤ የሆነና የማያቋርጥ ዓለም አቀፍ ችግር ነው።

ኢትዮጵያ በጣም ከተስፋፋባቸው ሀገራት ውስጥ ትመደባለች፡፡ በኢትጵያ የአንድ ሰው የዕድሜ ልክ ሄፓታይተስ ቢ ኢንፌክሽን መያዝ እስከ 80 በመቶ ይደርሳል::

በሄፐታይተስ ቢ ከሚያዙ አዋቂዎች 90 በመቶ ሙሉ በሙሉ ይድናሉ:: በተወለዱበት ጊዜ ወይም ከአንድ አመት በፊት ከተያዙ ሕፃናት መካከል ደግሞ 90 በመቶ የሚሆኑት ሥር የሰደደ በሽታ ይከሰትባቸዋል፡፡

ሄፓታይተስ ቢ እንዴት ይተላለፋል?

በተበከለ ደም እና ሌሎች የሰውነት ፈሳሾች መጋለጥ
በወሊድ ጊዜ ከእናት ወደ ልጅ መቆረጥ ፣ መቧጨር፣ ንክሻ ባላቸው ልጆች መካከል በማህበራዊ ግንኙነት ወቅት; በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ከሰው ወደ ሰው፣
ደህንነቱ ባልተጠበቀ መርፌ እና/ወይም ደም በመስጠት፣

በአጠቃላይ ሄፓታይተስ ቢ ከኤችአይቪ ከ 50 እስከ 100 እጥፍ በበለጠ ይተላለፋል::

የሄፐታይተስ ቢ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

አጣዳፊ የሄፐታይተስ ቢ ኢንፌክሽን (Acute hepatitis B) ምልክቶች: ድካም, ማቅለሽለሽ, ማስታወክ, የሆድ ህመም እና የቆዳ ,የሽንት እና የዓይን ቢጫ መሆን

ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ ቢ(Cirrhosis) ሕመምተኞች
የሆድ እብጠት, ያልተለመደ ደም መፍሰስ እና የአዕምሮ ሁኔታን መለወጥ ያስከትላል፡፡ cirrhosis, የጉበት ካንሰር ቀጥሎም ሞት ያስከትላል፡፡

ሄፓታይተስ ቢ የሲርሆሲስ በሽታ በማይኖርበት ጊዜም እንኳ የጉበት ካንሰር (Hepato cellular carcinoma) ያስከትላል ስለዚህ ቢያንስ በየ 6 ወሩ የህክምና ክትትል እና የአልትራሳውን ድምርመራ ያስፈልጋል

የሄፓታይተስ ቢ መከላከያ?

ሄፓታይተስ ቢን በክትባት መከላከል ይቻላል።

ክትባቶች መቼ ይሰጣሉ?
በብሔራዊ የክትባት መርሃ ግብር በተወለዱ፣ በ6 ፣ በ10 ፣ በ14 ሳምንታት ዕድሜ እንደ ፔንታቫለንት ጥምረት
ሄፕቢ- ወሊድ ክትባት፣በተቻለ ፍጥነት ከተወለደ በኋላ (በተወለደ በ24 ሰዓታት ውስጥ)።

ነገር ግን ሄፕቢ-ቢዲ በ24 ሰዓት ውስጥ ካልተሰጠ አሁንም ውጤታማ ሊሆን ይችላል እና ከተወለደ ሁለት ሳምንታት ውስጥ መሰጠቱን መቀጠልአለበት።

የሄፐታይተስ ቢ ክትባቶች (ብዙጊዜ በ 0÷1እና 6 ወር )
ለነፍሰጡር እናቶች÷ ብዙ ጊዜ ደም መውሰድ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎችን÷የዲያሌሲስ በሽተኞችን÷ የጤና ባለሙያዎች ወዘተ…

ለሄፐታይተስ ቢ ሕክምናው ምንድነው?

ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ አይድንም (no cure) ነገርግን በአብዛኛዎቹ ታካሚዎች የቫይረሱ መራባት መጠን መቀነስ እና የጉበት አሰራር መስተካከል በማምጣት የህመሙን ተፅዕኖ ይቀንሳል፡፡

ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ

በሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ መያዝን ተከትሎ ከ50 እስከ 85 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሥር በሰደደ ሄፓታይተስ ይያዛሉ;: ይሁን እንጂ ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ አብዛኛውን ጊዜ ቀስ በቀስ እያደገ የሚመጣ በመሆኑ በብዙ ታካሚዎች ግልጽ የሆነ የጉበት በሽታ ምልክት ላያመጣ ይችላል፡፡

ከ5 እስከ 30 በመቶ የሚሆኑት ሥር በሰደደ በሽታ የተያዙ ሰዎች ከ 20 እስከ 30 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ የሲርሆሲስ በሽታ ይያዛሉ፡፡

የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የመተላለፊያ መንገዶች የተበከሉ የሕክምና መርፌዎች ወይም መሣሪያዎች
ከተዛማች ለጋሽ ደም መውሰድ
በስራ ላይ የደም መጋለጥ (የመርፌ ጉዳት)
በበሽታው ከተያዘች እናት መወለድ; የእንሽርት ውሀ ለረጅም ጊዜ መፍሰስ
በበሽታው ከተያዙ አጋሮችጋር ልቅ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት
መነቀስ እና አካል መበሳት
በሄፐታይተስሲቫይረስየተበከሉመሳሪያዎች

የሄፐታይተስ ሲቫይረስ ህመም ምልክቶች
አብዛኛዎቹ በአጣዳፊም ሆነ ሥር በሰደደ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የተጠቁ ታካሚዎች ምንም ምልክት ላይኖራቸው ይችላል፡፡

የአጣዳፊኤሄፐታይተስሲ ምልክቶች
ማቅለሽለሽ፣ሽንት መጥቆር፣የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም፣መጠነኛ የሆነ ትኩሳት፣ብርድብርድ ማለት፣የምግብ ፍላጎ መቀነስ፣ሰውነትን ማሳከክ፣የጡንቻን የመገጣጠሚያ ህመም፣የስሜት መረበሽ ሊኖራቸው ይችላል።
አጣዳፊ ሕመም አብዛኛውን ጊዜከ 2 እስከ 12 ሳምንታት ይቆያል፡፡

ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክቶች
ድካም የተለመደ ምልክትነው.
አንዳንዴ ማቅለሽለሽ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣የጡንቻ እና መገጣጠሚያ ህመም፣ክብደት መቀነስ
ምልክቶቹ እንደ ድብርት ካሉ ሌሎች በሽታዎች ጋር ስለሚመሳሰሉ ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ::

ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ህክምናው

ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ከሰውነታችን በመድሀኒት መጥፋት የሚችል (curable) ህመም ሲሆን መድሀኒቶችን በአብዛኛው ለ12 ሳምንታት በመውሰድ መታከም ይቻላል፡፡

ለሄፐታይተስ ቢ እና ሲ ቫይረስ ምርመራ ቅድሚያ መመርመር የሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፤
የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ ልምምዶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ በሚሆኑባቸው ቦታዎች ህክምና የተደረገላቸው ሰዎች
ነፍሰጡር እናቶች
ከሄፐታይተስ ቢ ወይም ከሄፐታይተስ ሲ ከተያዙ እናቶች የተወለዱ ልጆች
ኤች.አይ.ቪ.በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች
የጤና ባለሙያዎች
ደም ወይም የደም ተዋጽኦ ያገኙሰዎች
እስረኞች
ቤተሰብ ወይም የትዳር አጋር ህመሙ ካለባቸው
Commercial sex workers
በርካታ የወሲብ አጋሮች ያለው/ላት ወይም የአባላዘር በሽታ ያለበት/የታከመ
የኩላሊት እጥበት ላይያ ሉታካሚዎች
የበሽታ መከላከያ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች
ዶ/ር ይፍሩ አንዱዓለም: የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

30 Jun, 08:42


💢 Metatarsalgia is a foot condition that causes pain and discomfort in the ball of the foot, typically just behind the toes.

It is often described as a burning or aching sensation and can be exacerbated by activities such as running or jumping.

Metatarsalgia is usually caused by excessive pressure on the metatarsal bones, which are the long bones in the foot that connect the toes to the rest of the foot.

This pressure can be caused by a variety of factors, including high-impact activities, ill-fitting footwear, foot deformities, or even just standing or walking for prolonged periods of time.

Treatment for metatarsalgia typically involves resting the foot and avoiding activities that exacerbate the pain.

Ice and anti-inflammatory medications can also be helpful in reducing inflammation and pain.

In addition, proper footwear and orthotic inserts can help distribute pressure more evenly across the foot and provide support to the arch and ball of the foot.

In more severe cases, physical therapy or surgery may be necessary to alleviate symptoms and correct any underlying issues.

It is important to seek medical attention if you experience persistent or severe pain in the ball of your foot, as early intervention can help prevent the condition from worsening.

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

28 Jun, 14:17


የስኳር በሽታ ምንድን ነው?

አንድ ሰው የስኳር በሽተኛ ነው የምንለው በሰውነቱ ውስጥ የሚገኘው የደም ግሉኮስ(ስኳር) በጣም ሲጨምር ሲሆን ይህም ሊከሰት የሚችለው አንደኛ የሰውነታችን የኢንሱልን የማምረት ብቃት በቂ ሳይሆን ሲቀር፣ ሁለተኛው ደግሞ ሰውነታችን የተመረተውን ኢንሱሊን በአግባቡ መቀበል ሳይችል ሲቀር ወይም ሁለቱም ባንድ ላይ ሲከሰት ነው።

እዚህ ላይ ኢንሱሊን ምንድንነው ብላችሁ ካላችሁ፡ ምግብ ስንበላ ሰውነታችን ምግቡን ወደ ስኳር ይቀይረዋል፤ በዚህ ሰዓት የሰውነታችን ጣፊያ (pancreas) ኢንሱሊን የሚባለውን ነገር ያመነጫል፤ ይህ ኢንሱሊን የሰውነታችን ህዋሶች እንዲከፈቱ በመርዳት የተመረተው ግሉኮስ (ስኳር) ወደ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ለሀይል ምንጭ እንድንጠቀምበት ይረዳል።

ሁለት አይነት የስኮር በሽታ አይነቶች አሉ፦

1. አይነት አንድ (Type 1) የስኳር በሽታ
በጣም ከባዱ የስኮር በሽታ አይነት ሲሆን ከኢንሱሊን አመራረት ጋር የተያያዘ ነው።
አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው በሕጻንነትና በጉርምስና (teenager) ጊዜ ነው። ሆኖም ግን በሌላ የእድሜ ክልል ውስጥ አይከሰትም ማለት አይደለም።
በዚህ አይነት የስኳር በሽታ ላይ የሰውነታችን አሰራር የራሱን ጣፊያ የሚያጠቃበት ሁኔታ አለ። ተመራማሪዎች ለምን እንደሆነ እስካሁን እርግጠኛ ባይሆኑም የሰውነታችን የመከላከሊያ ስርዓት (immune system) በስህተት በጣፊያ ውስጥ የሚገኙትን ኢንሱሊን የሚያመርቱ ህዋሶች እንደውጭ አካል በመመልከት ያጠፋቸዋል። ኢንሱሊን የለም ማለት ደግሞ የስኳር ክምችት ጨምሮ ወደ ግሉኮስ ሳይቀየር ይቀርና ሰውነታችን የሚያስፈልገውን ግሉኮስ ሳያገኝ ይቀራል። በህክምና ካልታዩት ይህ የበዛ የስኳር ክምችት አይንን፣ ኩላሊት፣ ነርቭን እና ልብን በመንካት ሞት ድረስ የሚደርስ አደጋ ሊያደርስብን ይችላል።

2. አይነት ሁለት (Type 2) የስኮር በሽታ
ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ ደግሞ ከኢንሱሊን ጋር ብዙም ያልተያያዘ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የሚያጠቃው ከ35 ዓመት በላይ ያሉ ጎልማሶችን ነው። በዚህ በሽታ የተጠቁ ህመምተኞች ከፊሉን ለሰውነታቸውን የሚያስፈልገውን ኢንሱሊን ማምረት የሚችሉ ሲሆን ችግሩ ብዙውን ጊዜ የኢንሱሊኑ መጠን በቂ ሆኖ አለመገኘቱ ነው። ቅድም እንደተገለፀው ኢንሱሊኑ የሰውነታችንን ህዋሶች በመክፈት ግሉኮስ እንዲገባ ሙከራ ቢያደርግም አይሰራም።

አብዛኛውን ጊዜ በዚህ የሚጠቁት ከሚፈለገው በላይ ክብደት ያላቸው ሰዎች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ እንደ ስፖርትና የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር መከላከል ሊቻል ይችላል።
👉ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ከማንኛውም የነርቭ፣የጡንቻ፣የመገጣጠሚ እና የስፖርታዊ ጉዳቶች #ኤክሶደስ_የፊዚዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክን ምርጫዎ ያድርጉ
👉በስልክ ቁጥሮቻችን 0979099909 / 0911039377 ይደውሉ
👉በአካል 22 አካባቢ ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ያገኙናል።

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

28 Jun, 09:10


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለታላቁ የዒድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ ።

ኢድ ሙባረክ !
#ኤክሶደስ_የፊዚዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ

ኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ልዩ ክሊኒክ

25 Jun, 04:42


#ለጠቅላላእውቀት
የመርሳት ችግር አለቦ?

የመርሳት ምክንያት ብዙ ቢሆንም ዋነኛው የሚባሉት :-

1) ከመጠን ያለፈ ጣፋጭነት ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር
ከመጠን በላይ የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች ባዘወተርን ቁጥር የምንመገባቸው ምግቦች ውስጥ ያሉት ፕሮቲኖች እንዳይሰባበሩና ሰውነታችን ወደጉልበትነት እንዳይቀይራቸውና ጥቅም ላይ እዳይውሉ ያደርጋል ነው፡፡

ይህም እየቆየ በፐሮቲን እጥረት ምክንያት ለሚመጣ የሰውነት መጎዳት ይዳርገናል፡፡

2) በመኝታ ሰዓት ጭንቅላትን መሸፈን
በምንተኛበት ግዜ በኮፍያ ወይም በወፍራም ሻሾች ጥንቅላታችን በምንሸፍንበት ሰዓት ከሰውነታችን የ የሚወጣው የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን እንዲጨምርና የ ኦክስጅን መጠን እንዲቀንስ እንደምናደርግ ጥናቶች ያመለክታሉ።

3) ቁርስ አለመብላት

ጠዋት ቁርስ አለመብላታችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለአዕምሮዋችን እድገትና ለብቃት ማነሰ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ቁርስ አለመብላታችን የደማችንን የስኳር መጠን የሚቀንስ ሲሆን ይህም ለጭንቅላታችን የሚደርሰውን የስኳር መጠን በመቀነስ ለሊቱን ሙሉ ቀን ያጠራቀመውን ብቻ ሲጠቀም በስራ ላይ የቆየው አዕምሮዋችን እንዲራብ ያደርጋል፡፡

4) የእንቅልፍ መዛባት

እንቅልፍ ሰውነት ራሱን የሚያጠንክርበት የሚተካበትና የሚያርምበት የማሰተካከያ ግዜው ነው፡፡

ይህ የማስተካከያ ግዜ ከተዛባና ሰውነት የሚያስፈልገውን ያህል ካላረፈ በቀላሉ ለአዕምሮ መድከምና ለሰውነት መዛል ይዳረጋል ይህም በቀጥታ የአዕምሮ ንቃትና የአስተሳሰብ ብቃታችንን ይቀንሳል፡፡

5) በህመም ሰዓት ስራ መስራት፤ ማንበብ፤ ማጥናት
በህመም ሰዓት ትኩረትና ጉልበትን የሚጠይቁ ተግባራትን ማከናወን የሰውነታችንን የማገገሚያ ግዜ በማዘግየት አዕምሮዋችን እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡

6) ማጨስ

ከሰውነታችን ውስጥ አብዛኛውን የምንተነፍሰውን አየር የሚጠቀመው አዕምሮዋችን ነው ስለሆነም
ሲጋራም ሆነ አንዳንድ አደንዛዥ እጾችን ስንጠቀም የጭንቀላት ሴሎች ኦክስጀንን እንዲራቡና አላስፈላጊ ኬሚካሎች የጭንቅላት ሴሎች እንዲጎዱ ያደርጋል፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ለረጅም ግዜ ሲጋራና አንዳንድ አደንዛዥ እጾችን የሚጠቀሙ ሰዎች እየቆዩ Alzimer ለተባለ ለመርሳት ችግር እንደሚጋለጡ ጠቁመዋል፡
👉ሄሎ ዶክተር
~ለተለያዩ የነርቭ፣የጡንቻ፣የመገጣጠሚያ ችግሮች #ኤክሶደስ_የፊዚዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክን ምርጫዎ ያድርጉ
~አድራሻ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊትለፊት ባሮ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ወይንም በስልክ ቁጥሮቻችን 0979099909 / 0911039377 ይደውሉ።