Top መረጃ💥 @topmereja Channel on Telegram

Top መረጃ💥

@topmereja


የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09

ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Top መረጃ💥 (Amharic)

በተለያዩ የቴሌግራም አዳዲስ መረጃ ላይ ያለው ስብሰባ እናሳተ ውይይት ላይ በምንጮችዎ ደህንነት የሚያገኙበት 'Top መረጃ💥' በማንኛውም አካባቢ ያለው ተጽእን ቴሌግራሙን አስተያየታችሁን ይከታተላል። nn'ቶፍ መሬጃ💥' ለማስታወቂያ ሰጪዎች፣ የተዘጋጀም ቪዲዮዎች፣ እና የቴክኖሎጂ ምስጢሮች ለመታወቂያ ነው። ከዚህበላይ ከግለሰቦች እና ጥያቄዎች በእንቅስቃሴ፣ እንለንነትና ፍቅር እንዲሁም ከትምህርት የተደረገ እንዲሆኑ፣ 'ቶፍ መሬጃ💥' በዘመናዊ ትንሽ አዳዲስ መረጃዎች ማረጋገጥን እንችላለን። nnእናመሰግናለን፣ 'ቶፍ መሬጃ💥' ይህንን መረጃዎችን መጠቀም ለሚያነቡልን ቅሞ እንዴት እንደሚያስተዳደር እንችላለን።

Top መረጃ💥

26 Nov, 11:49


የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክርቤት ፕሬዝደንት እና የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን ወደ ኤርትራ አቅንተዋል

የሽግግር ምክርቤቱ ጀነራሉ በሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ዋና መቀመጫ ካደረጓት ፖርት ሱዳን ሲሸኑ የሚያሳይ ምስል ለቋል።

አል ቡርሃን በኤርትራ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ወይይት ያደረጋሉ ብሏል ምክር ቤቱ።

ጀነራል አልቡርሃን ወደ ኤርትራ ያቀኑት የባህልና ሚዲያ ሚኒስትሩን ካሊድ አል አሰር እና የደህንነት ኃላፊውን አውል አህመድ ኢብራሂም ሞፋዚልን አስከትለው ነው።

በሱዳን፣ ጀነራል አልቡርሃን እና ጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ በሚመራቸው ጦሮች መካከል የተጀመረው ጦርነት 2 1/2 በላይ አመት አስቅጥሯል።

ጀነራሎቹ ወደ ጦርነት የገቡት ከአልበሽር ውድቀት በኋላ የሱዳንን ሽግግር ይመራሉ ተብለው በተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳለ ሀምዶክ ላይ መፈንቀል መንግስት ካደረጉ በኋላ ነበር።

በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች
መገደላቸውን እና ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ በሀገር ውስጥ አለያም ድንበር አቋርጠው ወደ ሌሎች ሀገራት መሰደዳቸውን አለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መግለጹ ይታወሳል ሲል አል ዓይን ዘግቧል።

@topmereja

Top መረጃ💥

17 Nov, 10:07


ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀ

ከአዲስ አበባ እና ከሀገራችን ከተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሩጫው ተሳታፊዎች ደኅንነት ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን በሚገባ ተወጥቷል ፡፡

የበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ለሀገራችን መልካም ገፅታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመገንዘብ ለፀጥታ አካላት ትብብር ላደረጉት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እና ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃትና በትጋት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የላቀ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@topmereja

Top መረጃ💥

10 Nov, 08:57


ኢትዮ ቴሌኮም በቢሾፍቱ የ5ጂ ኢንተርኔት ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀመረ‼️

በቢሾፍቱ ከተማ የቱሪዝም ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ ለማሻገር ያስችላል የተባለው የ5ጂ አገልግሎቱን የቢሾፍቱ ከተማና የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች በይፋ አስጀምረዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህወት ታምሩ የ5ጂ አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ መጀመሩ ከተማዋ በቱሪዝም፣ በንግድና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ ዕድገት ለማምጣት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማዋ የ5ጂ አገልግሎት መጀመር ስማርት ቢሾፍቱን ለመገንባት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጨረሻው ፈጣን የሆነውን የ5ጂ አገልግሎት በከተማዋ መጀመር የቢሮ ስራዎችን ለማቀላጠፍ፣ ለተገልጋዩ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት፣ ስማርት ሲቲን ለመገንባት፣ የቢሾፍቱን የቱሪስት መስህብነት አቅም ለማሳደግና በርካታ አገልግሎቶችን ለማከናወን የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።

130 ዓመታት ለህዝቡ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ኢትዮ ቴሌኮም ዓለማችን የደረሰችበትን የ5ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለማስጀመር እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

@topmereja

Top መረጃ💥

10 Nov, 08:57


ጎግል ፕሌይ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል ጀመረ

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት፤ የጎግል ፕሌይ የአልሚዎች ምዝገባ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል መጀመሩ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ተጽእኖ የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ይህ ምዕራፍ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ባለቤቶች መተግበሪያዎቻቸውን በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ ዲጂታል መድረኮች ላይ እንዲያትሙ አዲስ እድሎችን እንደሚከፍትም ገልፀዋል።

መንግስት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት በርካታ ተነሳሽነቶችን በመተግበር እየሰራ መሆኑን ገልጸው ይህ አዲስ ጅማሮ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ነው ብለዋል።

የዘርፉ ባለሙያዎች ይህንን እድል ተጠቅመው ችግር ፈቺ መተግበርያዎችን በማልማት በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ሂደት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በሚኒስቴሩ አማካሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ለኢትዮጵያውያን ስታርታፖች ምቹ ሥነ-ምህዳርን ለማዳበር ከሚተገበሩ ሰራዎች መካከል በአለም አቀፍ የዲጂታል መድረኮች እንዲሳተፉ የሚያስችሉ አለማቀፋዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር ወሳኝ በመሆኑ እድሉን ለማመቻቸት የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

እያይዘውም ይህ አዲስ እድል ኢትዮጵያውያን ገንቢዎች የጎግል ፕሌይን አለምአቀፍ ታዳሚዎች በቀጥታ በማግኘት መተግበሪያዎቻቸው ሰፊ እይታን እንዲያገኝ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችላል ማለታቸውን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የሀገር ውስጥ ገንቢዎች ከአካባቢው፣ ከማህበረሰቡ ወግና አኗኗር ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን መተግበሪያዎች በማልማት እንዲሁም ለአለማቀፍ ገበያው የሚመጥን ስራ እንዲሰሩ እንደሚበረታቱም ገልፀዋል።

@topmereja

Top መረጃ💥

09 Nov, 05:08


https://t.me/Pandas_HouseBot?start=332377790
Who let the AGE out?

Top መረጃ💥

03 Nov, 12:14


https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=3wFfO3pQ
LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾

Top መረጃ💥

30 Oct, 11:48


#መገናኛ

" የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል ፤ ለገንቢው እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው 45 ቀናት ነው " - አቶ ጥራቱ በየነ

ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ፣ መኪና የሚበዛበትና የሚገናኝበት ፣ እጅግ በርካታ እግረኞችም የሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ነው " መገናኛ " አካባቢ።

በዚህ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመሬት ውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መሰራት ጀምሯል።

ይህ ፕሮጀክት ከቦሌ ኤርፖርት እስከ መገናኛ ባለው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ምን አሉ ?

" መገናኛ በጣም ብዙ ሰዎች ተሽከርካሪዎችም የሚገናኙበት በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ቀድም ብሎ የቀለበት መንገድ የሚባለው ስለነበር መንገዱ ለእግረኞች ማቋረጫ በቂ አልነበረም። በዚህም ህብረተሰቡ በርካታ ችግር እንዲያሳልፍ ሆኗል።

ይሄ ትልቅ ጎዳና እንደመሆኑ የሚሰራው እግረኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ሳይቸገሩ በመሬት ውስጥ መሻገር የሚችሉበት ነው።

የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናልም ይገነባል በማዶ በኩል። በሙልጌታ ህንጻ ስርም ሁለት ወለል ያለው ተርሚናል ይገነባል።

እግረኞች ከአንዱ ተርሚናል ወደሌላኛው ተርሚናል የሚገናኙት በመሬት ውስጥ ይሆናል።

ከላይ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ በማይኖርበት ወይም በኒቀንስበት ሁኔታ ነው እየሰራን ያለነው።

ገንቢው ተቋራጭ ይህንን ስራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው ጊዜ 45 ቀን ነው።

ትንሽ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ለ45 ቀናት መንገዱን ስንዘጋው የነዋሪዎች እና የመኪና እንቅስቃሴ በተለይ መገናኛ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት እንደመሆኑ ጫና መፍጠሩ አይቀርም።

ዛሬ የምንወስነው ውሳኔ ምናልባት ለወደፊቱ ለበርከታ ረጅም አመታት ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል።

ለ45 ቀናት በ3 ሺፍት ነው የምንሰራው። ከዛም ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ከሚሰሩት ኮንትራክተሮች ጋር ተግባብተናል " ብለዋል።

የግንባታ ስራውን የሚያማክረው ማነው ? ስራውን የሚያማክረው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።

ኮርፖሬሽኑ " የመገናኛ እግረኛ መተለለፊያ ስራ በአይነቱ የተለየ እና ዘመናዊ ነው " ብሎታል።

ሱቆችን ጨምሮ የተለያዩ የፅዳት ቦታዎችም ይሰራሉ ብሏል።

" ፕሮጀክቱን በተባለው በ45 ቀናት እንደሚያልቅ እርግጠኞች ነን ፤ 24 ሰዓት ነው የሚሰራው  ፣ በቂ ማሽነሪ አለ፣ በተጓዳኝ ብረትና ሌሎች ዥግጅቶች እየተደረጉ ነው " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤኤምኤን ቲቪ መውሰዱን ይገልጻል።

@topmereja

Top መረጃ💥

30 Oct, 11:25


#accident

" 7 ሰው ሞቷል ፤ 2 ሰው ተጎድቷል " - በወላይታ ዞን የካዎ ኮይሻ ወረዳ

በወላይታ ዞን፤ ካዎ ኮይሻ ወረዳ ላሾ 01 ቀበሌ እና ኮይሻ ላሾ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በቀን 19/02/2017 ዓ.ም ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት 7 (ሰባት) ሰው የሞተ ሲሆን በ2 ሰው ጉዳት ደርሷል።

በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በፊት በዛው በካዎ ኮይሻ ወረዳ ላይ ጤፓ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም ስሰራ ቢቆይም ተደጋጋሚ አደጋ በመከሰቱ ችግሩ እያባባሰው መምጣቱ ተገልጿል።

መረጀው የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ሥራ ሂደት ነው።

@topmereja

Top መረጃ💥

23 Oct, 13:00


#Update

እስራኤል አዲሱን የሂዝቦላህ መሪ ሀሽም ሳፊይዲንን መግደሏን አረጋገጠች

የእስራኤል መከላከያ ሃይል እንዳስታወቀው÷ የቀድሞው የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ የአጎት ልጅ የሆነው ሀሽም ሳፊይዲን ከሶስት ሳምንት በፊት እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በወሰደችው የአየር ጥቃት ተገድሏል።

ከሀሽም ሳፊይዲን በተጨማሪ የሂዝቦላህ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ሃላፊ አሊ ሁሴን ሃዚማ እና የቡድኑ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በጥቃቱ ተገድለዋል ተብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሂዝቦላህ የሰጠው ምላሽ አለመኖሩ ተገልጿል።

ቀደም ሲል በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ቀን 2024 የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ የእስራኤል መከላከያ ሀይል ሀሰን ሳፊይዲንን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ መሪዎችና ታጣቂዎች መገደላቸውን ተናግረው ነበር።

በወቅቱም ሀሰን ነስራላህን በመተካት ወደ ሂዝቦላህ መሪነት የመጣው ሀሽም ሳፊይዲን ሳይገደል እንዳልቀረ እየተነገረ ነበር።

ይሁን እንጂ በእስራኤል ጥቃት የመሪውን መገደል የእስራኤል መከላከያ ሃይል አዛዥ ሌተና ጄኔራል ሄርዚ ሃሌቪ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።

@topmereja

Top መረጃ💥

23 Oct, 12:59


ሂዝቦላ የኔታንያሁን የመኝታ ክፍል በድሮን መምታቱ ተዘገበ

ሄዝቦላህ ከሊባኖስ የተኮሰው ሰው አልባ አውሮፕላን ቅዳሜ እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በቂሳሪያ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት በመምታቱ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል። አስቀድሞ በእስራኤል ወታደራዊ ኃይሉ ሳንሱር እንዳይታተም የተከለከለው ምስል አሁን ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን የድሮን ተፅእኖ በቤቱ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ያሳያል።

ፍንዳታው በመኝታ ክፍል መስኮት ውስጥ መስታወቱ እንዲሰነጠቅ ያደረገ ሲሆን ወደ ቤቱ ውስጥ ግን አልገባም። በተጠናከረ መስታወት እና ሌሎች መከላከያዎች ምክንያት ወደ ውስጥ ዘልቆ መግባት አልቻለም።የመስታወት ቁርጥራጮች በግቢው ውስጥ በቤተሰቡ የውሃ ዋና ገንዳ ውስጥ እንዳረፉ ተነግሯል። በጥቃቱ ምንም ጉዳት በሰው ላይ አልደረሰም። ኔታንያሁ እና ባለቤታቸው በወቅቱ ቤት ውስጥ እንዳልነበሩም ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።ሂዝቦላህ ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ “በቂሳርያ በኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ ኢላማ ያደረገውን ኦፕሬሽን ሙሉ በሙሉ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ኔታኒያሁ በበኩላቸው ይህንን ጥቃት የፈፀመ ከባድ አፀፋ ይጠብቀዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

@topmereja

Top መረጃ💥

23 Oct, 12:58


#ኢትዮጵያ


ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ271 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተሰበሰበ

በጽ/ቤቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን ዳንኤል እንዳሉት፥ በ2017 በጀት ዓመት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

በሩብ ዓመቱም በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክትና በስጦታ ከ271 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በበጅት ዓመቱ የታቀደውን ድጋፍ ለማሰባሰብ በትኩረት ይሰራል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፥ ሕዝቡም እስከ ግንባታው ፍጻሜ ድጋፉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

መገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የገቢ ማሰባሰቢያ አማራጮችን ለሕብረተሰቡ በማሳወቅ ሚናቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@topmereja

Top መረጃ💥

21 Oct, 09:39


https://youtu.be/8vzJ8gqeiyc

Top መረጃ💥

19 Oct, 18:38


# Accident!!!!

በግንባታ ላይ ባለው የመቄዶኒያ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

በግንባታ ላይ ባለው የመቄዶኒያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋዊያን መርጃ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ ተከስቶ የነበረ እሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 መቄዶኒያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋዊያን መርጃ ማህበር እያስገነባ ባለዉ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ እሳት አደጋ መከሰቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ በደረሰዉ ጥሪ መሰረት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታዉ ፈጥነዉ በመድረስ እሳቱ ሳይስፋፋ በፍጥነት መቆጣጠር ችለዋል።

በእሳት አደጋዉ በመጋዘን ውስጥ የነበሩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ተናግረዋል።

@topmereja

Top መረጃ💥

18 Oct, 10:14


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል:-

1. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ - የቱርዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር

2. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ -  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር

3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ-  የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር

Top መረጃ💥

18 Oct, 08:49


የያህያ ሲንዋር መገደል የጦርነቱ ፍጻሜ አይደለም- ጠ/ሚ ኔታንያሁ


ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ÷ የያህያ ሲንዋር መገደል ከፍተኛ ድል ቢሆንም የጦርነቱ ፍጻሜ እንዳልሆነ አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በሀማስ እገታ ሥር የሚገኙ እስራኤላውያን እስከሚለቀቁ ድረስ ጦርነቱ ይቀጥላል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በርካታ እስራኤላውያን እንዲገደሉ እና እንዲታገቱ በተደረገበት የጥቅምት 7 ጥቃት የያህያ ሲንዋር ሚና ከፍተኛ እንደነበር አንስተው÷ የመሪው መገደል በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ሊቀይረው እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የያህያ ሲንዋር መገደል ለእስራኤል ብሎም ለአሜሪካ ትልቅ ድል መሆኑን ገልጸው÷ የመሪው መገደል ምን አልባትም ጦርነቱ በአጭር ጊዜ እንዲቋጭ ሊያደርገው ይችላል ብለዋል፡፡

በአንጻሩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢራን ልዩ መልዕክተኛ በበኩላቸው÷ የያህያ ሲንዋር መገደል እስራኤልን ከምን ጊዜውም በላይ ለመፋለም የሚያነሳሳ የመንፈስ ጥንካሬ ይሰጠናል ብለዋል፡፡

ሁኔታው ጦርነቱን ከማብረድ ይልቅ ሊያባብሰው እንደሚችልም ነው ያስረዱት፡፡

@topmereja

Top መረጃ💥

18 Oct, 07:48


#international news

የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል እስራኤል ገለጸች

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ጋዛ ውስጥ ባደረገው ኦፕሬሽን አዲሱ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት እና የደህንነት ኤጀንሲ በጋራ ባወጡት መግለጫ የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ጋዛ ውስጥ ባደረገው ኦፕሬሽን ሦስት የሐማስ ቁልፍ አመራሮች ተገድለዋል።

ከተገደሉት መሪዎች ውስጥም አንዱ ያህያ ሲንዋር ሊሆን እንደሚችል በመግለጫው ተጠቁሟል።

ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው የጥቅምት 7 ጥቃት ዋነኛ መሪ የነበረው ያህያ ሲንዋር እስራኤል ልትገድላቸው ከምትፈልጋቸው ሰዎች መካከል በግምባር ቀደምነት የሚጠቀስ ነው።

@topmereja

Top መረጃ💥

17 Oct, 12:49


ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ በአዋሽ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በአዲስ አበባ ተሰማ


በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6 ሰዓት አከባቢ በአዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል፡፡

ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በመዲናዋ አሁንም ዳግም መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።

ከቀኑ 6 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ9 ሰኮንድ በአዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶ/ር ኤሊያስ ገልጸዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በአካባቢው ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴ አሁንም እንዳልቆመ ዶ/ር ኤሊያስ ተናግረዋል።

አሁን የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት መጠኑ አነስተኛ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ኤሊያስ፤ በአዋሽ ፈንታሌ እና ሳቡሬ ከተማ መካከል ላይ ያለው የቅልጥ ዓለት እንቅስቀሴ እስከቀጠለ ድረስ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ የመቀጠል እድል እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

     @topmereja

Top መረጃ💥

17 Oct, 12:47


#accident

ድምፃዊው ህይወቱ አለፈ

የቀድሞው የ one direction አባል ድምፃዊ ሊያም ፓይኒ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ።

የ 31ዓመት እድሜ ያለው ድምፃዊው ፤ በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በመዝናናት ላይ የነበረ ሲሆን ፤ ከአንድ ሆቴል ወለል ላይ ወድቆ ህይወቱ እንዳለፈ ነው እየወጡ ያሉ መረጃዎች የሚናገሩት።

የአሟሟቱ መንስኤ ፖሊሶች እያጣሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

@topmereja

Top መረጃ💥

17 Oct, 12:42


#Ethiopia

ለማረፍ ሲዘጋጅ ጭስ የታየበት አውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ አርፏል- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 አውሮፕላን ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጭስ መታየቱ ተገልጿል፡፡

አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም በማረፍ መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡

አየር መንገዱ ጭሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ÷ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱ ይታወሳል፡፡

በወቅቱም አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በማረፍ መንገደኞቹ ደኅንነታቸው እንደተጠበቀ ማውረዱ ይታወቃል፡፡

Top መረጃ💥

16 Oct, 11:02


#AddisAbaba

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ አዲስ ታሪፍ ይፋ አድርጓል።

በዚህም በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በተሰማሩ ሚኒ-ባሶች ፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።

አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ጭማሪ በተደረገበት በአዲሱ ታሪፍ ዝቅተኛው 10 ብር ሲሆን ከፍተኛው 65 ብር ገብቷል።

" ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ ነበር ፤ ስሌቱም የነዳጅ ጭማሪ ዋጋን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነበር " ሲል ቢሮው ገልጿል።

@topmereja

Top መረጃ💥

16 Oct, 11:01


#ባሕርዳር

በባሕርዳር በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 3 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተያዘ

በባሕርዳር ዳር ከተማ ግሽ አባይ ክፍለ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 3 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተያዘ፡፡

ነዳጁ በሕገ-ወጥ መንገድ ከማደያዎች በሌሊት ተቀድቶ ሲወጣ በተደረገ ክትትል ከነተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ መያዙን የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት አስታውቋል።

10 በርሚል እና ከ50 በላይ ባለሁለት ሊትር ቤንዚን በክትትል ከተጠርጣሪዎቹ እጅ እንደተገኘም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡

@topmereja

Top መረጃ💥

16 Oct, 11:00


#Accident

#ባሕር_ዳር

የተወዳጇ ድምፃዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት እና የምግብ አዳራሽ ዛሬ ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ መውደሙ ተሰምቷል።

የባሕር ዳር ነዋሪ እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረገው ርብርብ ጥሩ ነበር። ሆኖም የእሳቱ ሁኔታ ከባድ ስለነበር ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በሰው ላይ እስካሁን ጉዳት አለማድረሱን ሰምተናል።

@topmereja

Top መረጃ💥

15 Oct, 13:01


#ዶላር

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ አሽቆለቆለ።

ባለፉት በርካታ ቀናት በንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112 ብር ከ3957 ሳንቲም እየተገዛ በ123 ብር ከ6353 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።

ዛሬ ባንኩ ይፋ ባደረገው የዕለታዊ የምንዛሬ ተመን አንዱን የአሜሪካ ዶላር የሚገዛበትን ዋጋ ወደ 113 ብር ከ1308 ሳንቲም አሳድጎ መሸጫውን ወደ 115 ብር ከ3934 ሳንቲም አውርዶታል።

እንደ ዛሬው የምንዛሬ ተመን ባንኩ ዶላር መግዣውን በ1 ብር ከፍ ያደረገው ሲሆን መሸጫው ላይ ካለፉት ቀናት የ8 ብር ቅናሽ አድርጎበታል።

@topmereja

Top መረጃ💥

14 Oct, 13:39


#Addis Abeba

እነ ጆን ዳንኤል የክስ መቃወሚያ አቀረቡ

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል በመንቀሳቀስ የተከሰሱ ስድስት ግለሰቦች ክሱ እንዲሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረበውን የክስ መቃወሚያ መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው ቀጠሮ የክስ መቃወሚያቸውን በጠበቆቻቸው አማካኝነት ያቀረቡት ተከሳሾቹ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በነ ዮሃንስ ዳንኤል መዝገብ በስድስት ተከሳሾች ላይ አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣ የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ ወንጀል ክስ በተጨማሪም በ1ኛ ተከሳሽ ብቻ ደግሞ የአየር መንገዱን መልካም ስም ለሚያጎድፍ በተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒዩተር ስርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ወንጀል የሚል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

ተከሳሾቹ የክሱ ዝርዝር ከደረሳቸው በኋላ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ዛሬ ከማረሚያ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ተከታትለዋል።

በዚህም የተከሳሽ ጠበቆች የክስ ዝርዝሩ እንዲሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ በጽሁፍ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች በኩል በቀረበው የክስ መቃወሚያን በሚመለከት ዐቃቤ ሕግ ከቀጠሮ በፊት መልሱን (አስተያየቱን) በሬጅስትራር በኩል እንዲያቀርብ በማለት በአጠቃላይ በመቃወሚያው ላይ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጥሯል።

@topmereja

Top መረጃ💥

14 Oct, 11:56


#ህገመንግስት

አንቀጽ 3: የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ 🇪🇹

1. የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ፣ ከታች ቀይ ሆኖበመሐሉ ብሔራዊ ዓርማ ይኖረዋል፡፡ ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ፡፡

2. ከሰንደቅ ዓላማው ላይ የሚቀመጠው ብሔራዊ ዓርማ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንጸባርቅ ይሆናል፡፡

3. የፌዴራሉ አባሎች የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ዝርዝሩን በየራሳቸው ምክር ቤት ይወስናሉ፡፡

17 ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮጵያ ተከብሮ ውሏል።

@topmereja