Lesperance 2015 @lesperans Channel on Telegram

Lesperance 2015

@lesperans


Lesperance 2015 (French)

Vous cherchez un endroit pour partager vos espoirs et vos rêves pour l'avenir? Rejoignez-nous sur le canal Telegram Lesperance 2015! Le canal Lesperance 2015, géré par le username @lesperans, est un espace en ligne dédié à l'inspiration et à la positivité. Que vous soyez à la recherche de motivation, d'encouragement ou simplement d'un endroit pour partager vos aspirations, ce canal est fait pour vous. Qui est Lesperance 2015? C'est une communauté passionnée par le potentiel humain et la puissance des rêves. Notre objectif est de créer un environnement où chacun peut s'exprimer librement, trouver le soutien nécessaire pour poursuivre ses objectifs et célébrer les succès de chacun. Qu'est-ce que Lesperance 2015? C'est un lieu d'échange et de partage d'idées, de conseils et d'histoires inspirantes. Vous y trouverez des discussions sur la croissance personnelle, la réalisation de soi, la confiance en soi et bien plus encore. Nous organisons également des événements en ligne, des séances de coaching et des ateliers pour vous aider à atteindre vos objectifs. Rejoignez-nous dès aujourd'hui sur le canal Lesperance 2015 et faites partie d'une communauté engagée à vous aider à réaliser vos rêves. Ensemble, nous pouvons créer un avenir meilleur et plus lumineux pour tous. Vivez l'espoir avec Lesperance 2015!

Lesperance 2015

07 Feb, 12:08


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 3/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

(ጥር 30/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 3/2017 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc

Lesperance 2015

05 Feb, 15:56


ጥር 26/2017ዓ.ም
አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ስለማድረግ
ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በተላለፈው መመሪያ መሰረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ወላጆች ኮሚቴዎች በድጋሜ ማደራጀት አሰፈልገዋል።በመሆኑም እሁድ የካቲት 02/2017ዓ.ም ልክ 2:30 በሌስፔራንስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝታችሁ የክፍለ ከተማ/የወረዳ ተወካዮች በተገኙበት የሚወክሏችሁ ወላጆች እንድትመርጡ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለዕቅዱ መሳካት ለምታደርጉ የተለመደ አስተዋፅኦ በቅድሚያ እናመሰግናለን ።
ማሳሰቢያ :_ በቀኑ የልጆቻችሁን ውጤት ካርድ መውሰድ ይጠበቅባችኋል ።ነገር ግን በቀኑ ተገኝታችሁ ውጤት ባትወስዱ ግን በስራ ቀን ማንም መምህር ማስተማርን ትቶ ውጤት የማይሰጥ መሆኑን ከወዲሁ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያሳውቃል። ልክ 4:00 ሰዓት አዳራሹ ለሌላ ስብሰባ ስለሚፈለግ ሰዓት ይከበር!
የእሁድ ማጠናከሪያ ይቀጥላል።

Lesperance 2015

03 Feb, 15:46


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች
መፅሐፍ ግዢ ለመፈፀም ብር ከፍላችሁ ነገር ግን መፅሐፍ ያልወሰዳችሁ ወላጆች የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ ከጥር 28/2017ዓ.ም _የካቲት 7/2017 ዓ.ም ብቻ ብሩን ከት/ቤቱ ሒሳብ ክፍል በስራ ሰዓት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ት/ቤቱ ያሳውቃል ።

Lesperance 2015

01 Feb, 11:14


🔤ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና

አዘጋጅ
👉አራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት

⛔️መንፈቀ አመት
👉የመጀመሪያ መንፈቀ አመት 

⭐️የትምህርት አይነት
👉ሁሉም

⭐️አመት 👉2017

⭐️ክፍል 👉8️⃣

0️⃣ለሌሎች ማጋራት አንርሳ

🔠🔠🔠🔤 🔠🔠🔠
ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇👇
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/dam76

Lesperance 2015

01 Feb, 11:12


🥰6️⃣ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና

አዘጋጅ
👉🔤🔤🔤🔤🔤ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት

⛔️መንፈቀ አመት
👉የመጀመሪያ መንፈቀ አመት 

⭐️የትምህርት አይነት
👉ሁሉም

⭐️አመት 👉2017

⭐️ክፍል 👉6️⃣

📘ለሌሎች ማጋራት አንርሳ‼️

🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤
ቻናላችን ይህ ነው
🫴🫴🫴🫴🫴🫴
https://t.me/dam76

Lesperance 2015

01 Feb, 11:11


☝️8️⃣ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና

አዘጋጅ

👉🔤🔤🔤🔤🔤🔤 ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት

⛔️መንፈቀ አመት
👉የመጀመሪያ መንፈቀ አመት 

⭐️የትምህርት አይነት
👉ሁሉም

⭐️አመት 👉2017

⭐️ክፍል 👉8️⃣

🚗ለሌሎች ማጋራት አንርሳ‼️

🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤

ቻናላችን ይህ ነው
🐦‍⬛️🐦‍⬛️🐦‍⬛️🐦‍⬛️🐦‍⬛️
https://t.me/dam76

Lesperance 2015

22 Jan, 16:43


የተከበራችሁ ወላጆች የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከጥር16/2017ዓ.ም ጀምሮ ስለሚሰጥ በወጣው ፕሮግራም መሰረት ድጋፍ እና ክትትል አይለያቸው።

Lesperance 2015

16 Jan, 17:22


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረ ሞዴል ፈተና በሰላም ተጠናቋል ።

Lesperance 2015

12 Jan, 09:26


20 questions about parts of atoms:

1. Which part of the atom contains protons and neutrons?
A. Electron Cloud
B. Nucleus
C. Proton Shell
D. Neutron Field

2. What charge does a neutron carry?
A. Positive
B. Negative
C. Neutral
D. Variable

3. Electrons are found in which part of the atom?
A. Nucleus
B. Electron Cloud
C. Proton Shell
D. Neutron Field

4. What is the charge of a proton?
A. Positive
B. Negative
C. Neutral
D. Variable

5. Which subatomic particle determines the identity of an element?
A. Proton
B. Electron
C. Neutron
D. Quark

6. What is the overall charge of an atom with equal numbers of protons and electrons?
A. Positive
B. Negative
C. Neutral
D. Variable

7. What is the smallest subatomic particle?
A. Proton
B. Neutron
C. Electron
D. Quark

8. Which part of the atom has the most mass?
A. Proton
B. Neutron
C. Electron
D. Nucleus

9. What holds electrons in orbit around the nucleus?
A. Magnetic Force
B. Strong Nuclear Force
C. Electromagnetic Force
D. Gravitational Force

10. Which subatomic particle is responsible for chemical bonding?
A. Proton
B. Neutron
C. Electron
D. Quark

11. How many protons does an atom of Carbon-12 have?
A. 6
B. 12
C. 18
D. 24

12. Isotopes of the same element differ in the number of which particle?
A. Protons
B. Electrons
C. Neutrons
D. Quarks

13. What is the charge of the nucleus of an atom?
A. Positive
B. Negative
C. Neutral
D. Variable

14. What particles are involved in radioactive decay?
A. Protons and Electrons
B. Neutrons and Electrons
C. Protons and Neutrons
D. Neutrons and Photons

15. What type of bond involves the sharing of electrons between atoms?
A. Ionic
B. Covalent
C. Metallic
D. Hydrogen

16. If an atom has 7 protons and 10 neutrons, what is its atomic mass?
A. 7
B. 10
C. 17
D. 14

17. Why are electrons not considered in calculating atomic mass?
A. They are too small to have mass.
B. Their mass is negligible compared to protons and neutrons.
C. They are outside the nucleus.
D. They have a variable mass.

18. What determines the chemical reactivity of an atom?
A. Number of protons
B. Number of neutrons
C. Arrangement of electrons
D. Total mass of the atom

19. What is the term for atoms of the same element with different numbers of neutrons?
A. Ions
B. Isotopes
C. Molecules
D. Compounds

20. Which subatomic particle is most involved in ion formation?
A. Proton
B. Neutron
C. Electron
D. Photon


🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
https://t.me/dam76

Lesperance 2015

11 Jan, 17:31


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች ከጥር 6/5/2017ዓ.ም ጀምሮ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና እንደሚጀመር ይታወቃል ።በመሆኑም የነገ የእሁድ ማጠናከሪያ ትምህርት ለክላሳ እንዲረዳቸው 5:15 መውጫ የነበረ 5:45 ከትምህርት ቤት መውጫ ሰዓት ይሆናል።
ማሳሰቢያ :_ የሚኒስትሪ ፎርም እየሞላን እንደምንገኝ ይታወቃል ።በመሆኑም ስህተት እንዳይፈጠር የልደት ካርድ ያለው ዕድሜ እና ስም ተመሳሳይ መሆን አለበት
የእናት ስም ሙሉ ይላክልን።
መልካም አዳር

Lesperance 2015

07 Jan, 17:29


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደሰሳችሁ አደረሰን።

Lesperance 2015

03 Jan, 15:00


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች በቀን 25/2017ዓ.ም በወረዳ ደረጃ ማለትም በክላስተር ማዕከል ደረጃ የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ሚንስትሪ ፈተና የሚፈተኗቸው ሁሉም የትምህርት ዓይነቶች በአምስት(5) ት/ቤቶች መካከል የጥያቄ እና መልስ ውድድር ተከናውኗል ። በመሆኑም
የትምህርት ቤታችን ተማሪ የሆነችው የ8ኛ ክፍል ተማሪ ቤተልሔም አስፋው ከተጠየቀችው 12 ጥያቄዎች 12ቱ በመመለስ የወርቅ መዳሊያ ተሸላሚ በመሆን ለወደፊት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚከናወነው የጥያቄና መልስ ውድድር ወረዳ ወኪላ የምትወዳደር ይሆናል።
ተማሪ ኢዮስያስ መሰረት ከ6ኛ ክፍል ት/ቤታችን ወክሎ በ6 ት/ቤቶች መካከል በተደረገው የጥያቄ እና መልስ ውድድር 2ኛ በመወጣት የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል ።በአጠቃላይ የት/ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ ብሎናል።

Lesperance 2015

30 Dec, 14:24


ከትምህርት አገልግሎት ክፍያ ጋር ተያይዞ ጥያቄ ካላችሁ የቂሊንጦ ቅርንጫፍ አዋሽ ባንክ ማናጀር ማነጋገር ይቻላል በ0913149508/ 0910533136

Lesperance 2015

30 Dec, 14:18


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች በቀን 21/4/2017ዓ.ም በወረዳ 9 በ8ኛ እና በ6ኛ ክፍል መካከል በተካሄደው የጥያቄ እና መልስ ውድድር
1.በ8ኛ ክፍል በ5 ትምህርት ቤቶች መካከል በሒሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች የትምህርት ቤታችን ተማሪ የሆነችው ተማሪ ቤተልሄም አስፋው 1ኛ በመውጣት በክፍለ ከተማ ለሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ተሳታፊ ትሆናለች
2. በ6ኛ ክፍል ተማሪ ኢዮስያስ መሰረት በ6 ትምህርት ቤቶች መካከል በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር 2ኛ ወጥቷል ።በመሆኑም አጠቃላይ ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ውድድሩ የሚቀጥል ይሆናል።

Lesperance 2015

29 Dec, 14:07


📩ማሳሰቢያ

በ2017 ዓ.ም ለ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞች

የ6ኛ እና8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሚዘጋጀው የ6ኛክፍል ፈተና( ከ5ኛ እና 6ኛ ክፍል) እንዲሁም የ8ኛ ክፍል(7ኛ እና 8ኛ ክፍል) መሆኑን አውቃችሁ ት/ቤቶችና ወላጆች ለተማሪዎቻቹህ አስፈላጊውን እገዛ አድርጉ

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያካትተው የ9ኛ ክፍል አሮጌው ስርዓተ ትምህርት እና የ11ኛእና 12ኛ ክፍል ከአዲሱ ስርዓተ ትምህርት  መሆኑ ታውቆ ለተፈታኝ  ለተማሪዎች አስፈላጊው ዝግጅት አድርጉ!!10ኛ ክፍል አያካትትም ምክንያቱም 10ኛ ክፍል አብዛኛው ተማሪ  በአሮጌው ስርዓተ ት/ት የተማረ ሲሆን የተወሰኑ ትምህርት ቤት ተማሪዎች   የፓይለት ሙከራ ሆነው በአዲሱ ስርዓተ ት/ት በመማራቸው ነው! !


መረጃው ከየካ/ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የተገኘ ነው።

Lesperance 2015

25 Dec, 09:01


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች የኢትዮጵያ ታላቁን ህዳሴ ግድብ ከ 96% በላይ መጠናቀቁን ይታወቃል። በመሆኑም በልጆቻችሁ ስም ቦንድ በመግዛት የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ት/ቤቱ ይጠይቃል።

Lesperance 2015

14 Dec, 07:30


የተከበራችሁ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች በተላከው ደብዳቤ መሰረት ታህሳስ 6/4/2017ዓ.ም የእሁድ ማጠናከሪያ ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እየገለፅን የሰርቢስ መነሻ ቦታ16 ሆኖ ልክ 2:00 ይሆናል። ትምህርት የሚጠናቀቀው ልክ 5:15 ይሆናል። ክፍያ የሚከፈለው እስከ ታህሳስ 11/4/2017 ዓ.ም ብቻ ይሆናል።

Lesperance 2015

11 Dec, 09:46


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች ተማሪዎች እስከአሁን ያላቸውን ውጤት በጊዜያዊ ወረቀት ት/ቤቱ ስለላከ ውጤቱን በመመልከት ድጋፍ እና ክትትል አይለያቸው።

Lesperance 2015

26 Nov, 17:25


Reference!

Lesperance 2015

26 Nov, 08:59


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች ከህዳር 18 ደምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት 5:30 የመጀመሪያ ዙር ሰርቢስ ከት/ቤቱ ግቢ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።

Lesperance 2015

25 Nov, 15:26


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች የእስካውት ክበብ አባላት ት/ቤታችን ፅዱ እና ማራኪ እናደርጋለን በማለት የፅዳት ንቅናቄ ሲያከናውኑ የሚያሳይ በምስል

Lesperance 2015

21 Nov, 14:06


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች
ከህዳር 16____ ህዳር20/2017 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና ስለሚሰጥ በፕሮግራሙ መሰረት ድጋፍ እና ክትትል አይለያቸው።

Lesperance 2015

13 Nov, 12:48


ማስታወቂያ
ለተማሪ ወላጆች
የጃኬት ቀብድ በመክፈል የተለኩ ተማሪዎች በነገው ዕለት ማለትም በቀን 5/3/2017 ዓ.ም ስለሚመጣ ቀሪ ክፍያ በመክፈል ጃኬቱን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ት/ቤቱ ያሳውቃል።

Lesperance 2015

13 Nov, 08:09


+251913149508 awash bank

Lesperance 2015

13 Nov, 08:08


ከትምህርት ክፍያ ጋር ተያይዞ ጥያቄ ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው ስልክ መነጋገር ይቻላል።

Lesperance 2015

09 Nov, 05:21


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች ከህዳር 4 ____6/2017 ዓ.ም ወርሀዊ ፈተና ስለሚሰጥ በፕሮግራሙ መሠረት ልጆቻችሁ ድጋፍ እና ክትትል አይለያቸው።

Lesperance 2015

29 Oct, 14:02


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች አጋዥ መፅሐፍ መግዛት የምትፈልጉ ካላችሁ ነገ የመጨረሻ ቀን መሆኑን ት/ቤቱ ያሳውቃል።

Lesperance 2015

27 Oct, 09:43


ከቅድመ 1ኛ -12ኛ ክፍል የተማሪዎችን መጽሀፍት በሚከተሉት ሊንኮች ማግኘት ትችላላቹህ

የቅድመ 1ኛ መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3693?single

⭐️የቅድመ አንደኛ የእንግሊዘኛ መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/4609?single

የ1ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3716?single

የ2ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3709?single

የ3ኛ ክፍል  መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3702?single

የ4ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3685?single

የ5ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3678?single

የ6ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3670?single

የ7ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3659?single

የ8ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3641?single

Afan Oromo Grade 3-8 text books
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3099?single

Afan Oromo grade 6-8
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3047

📘ከ9ኛ-12ኛ ክፍል መጽሀፍ ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3720

🔤🔤🔤🅰️ 🔤🔤🔤
ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇👇
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/dam76

Lesperance 2015

18 Oct, 15:37


1.የተማሪ መፅሐፍ ክፍያ የፈፀማችሁ መፅሐፉ ስለመጣ ደረሰኝ በመያዝ ሰኛ 4:00 መውሰድ የምትችሉ መሆኑን
2. የጃኬት ቀብድ በመክፈል የተለካችሁ ቀሪውን ክፍያ በመፈፀም ሰኞ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

Lesperance 2015

15 Oct, 16:43


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች ጥቅምት 3/2/2017 ዓ.ም ከመማር ማስተማር ጋር ተያይዞ ከወላጆች ጋር ውይይት መደረጉ ይታወቃል።በመሆኑም መማር ማስተማሩ ሰላማዊ እና በውጤት የታጀበ እንዲሆን ለወደፊት መስተካከል ያለባቸው የተለያዩ ሀሳቦች በማንሳት የት/ቤቱ አስተደደርም ለዕቅዱ መልካም የሚባሉ ግበአት ያገኘበት የተሳካ ውይይት በማድረግ የተጠናቀቀ ሲሆን በሰርቪስ አሰጣጥ ዙሪያ ለተነሱ ቅሬታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት የመፍትሄ አቅጣጫ የተሰጠው መሆኑን የት/ቤቱ አሰተዳደር ያሳውቃል።

Lesperance 2015

10 Oct, 17:03


የአራትዮሽ ስምምነት መፈራረሚያ በት/ቢሮ የተዘጋጀ

Lesperance 2015

10 Oct, 12:53


የከበራችሁ ወላጆች ነገ አጠቃላይ የመምህራን ስብሰባ ስላለን ትምህርት ግማሽ ቀን መሆኑን እናሳውቃለን።

Lesperance 2015

07 Oct, 18:21


የጥንቃቄ መልዕክት ‼️

የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ ርምጃዎች፦

📌  ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሰሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እንዲሁም ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

📌  በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

📌  በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ - ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

📌  መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ - የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሰሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽከርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

Lesperance 2015

04 Oct, 11:15


የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች ከእንግሊዝኛ 4 ,6 እና ከሒሳብ 1---6 ክፍል ውጭ መፅሐፍ የከፈላችሁበት ስሊፕ/ደረሰኝ ሰኞ ማለትም እስከ መስከረም 27/1/207ዓ. ም እንድትልኩልን ት/ቤቱ ያሳስባል። ከቅዳሜ ማለትም መሰከረም 25/2017ዓ.ም ውጭ ምንም ዓይነት የመፅሐፍ ክፍያ መክፈል የማይቻል መሆኑን ት/ቤቱ በድጋሜ ያሳውቃል ።