ማቲ ሸገር - Mati Sheger® @matiosbirhanu Channel on Telegram

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

@matiosbirhanu


ስለ ፍትህ ስለ እኩልነት እና ስለ ዲሞክራሲ

ማቲ ሸገር - Mati Sheger® (Amharic)

ማቲ ሸገር - Mati Sheger® ቢበየት ነው የሚሞላው ርዕሶች እና ሥርጄኝች አወዳለሁ :: ይህ ቤት ከመፍታት ሳርኦን እና መዘናግታቸው ከሌላው አለም አድራሻዎች ጋር በተመኘነ ትንቢት ነው :: ማቲ ሸገር በTelegram ኦን ቐደሬን በተመለከተ ትንቢት አገናኝ ምንም ነገር የለውም ነው :: ስለዚህ ይህ ቤት ከትዝብት መስሪያቸው ላልተሻለ መኖሩ እየፈለጋቸው እንደሆኑ፣ የቤታቸውን ታክሲፎስ ሞባይል ተደመራረና መስራት አያሸነፉም እያልኩ ነው ማቲ ሸገር - Mati Sheger® በTelegram መዝገበ ቃላት ውስጥ ይድረስባችኋል ::

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

14 Feb, 12:24


ዛሬ የተወለድኩበት ቀን ነው😍

ብዙ መውደቅ ብዙ መነሳት ሄድ መለስ በሆነ የህይወት ጎዳና ዛሬ ላይ ደርሻለሁ🙏

ባለፉት ግዜያቶች ብዙ አስተማሪ ነገሮች ገጥመውኛል በዚች ትንሽ እድሜዬ ብዙ ችግሮች እና መለራዎችን አሳልፏለሁ ዛሬ ሆኜ እነዛ የማያልፉ የሚመስሉ ግዜያቶችን ሳስባቸው ፈጣሪ ለኔ ያደረገልኝን እንዳስብ ያደርገኛል።

ተመስገን ስለ ሁሉም ነገር🙏

ዛሬ የተሻለ ኑሮ ሰቶኛል የነገን ደግሞ ከፈጣሪ ጋር እጀመወረዋለሁ🙏

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

09 Feb, 15:46


ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት የበረከት ስራ ተካፋይ ሁኑ🙏😍

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

07 Feb, 13:07


የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የፆመ ነነዌ መልእክት!...👇

"...ከየካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ..."

***
"ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤ ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤"

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

05 Feb, 19:03


ከጠዋቱ 1:30 ሽሮ ሜዳ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የቪዛ ማመልከቻ ቀጠሮ ላይ ተገኝቻለው።

ብርዱ አይጣል ነው። አካባቢው በመኪናና በሰው ተሞልቷል።

1:45 ቀጠሮ ያላችሁ በዚህ ረድፉ ተሰለፍ አለች አስተናባሪዋ።

ልጄ 1:45 ነው ያለችው አሉኝ አንድ ተለቅ ያሉ ሴት የሀገር ባህል ልብስ ለብሰዋል፣ በእጃቸው ቢጠየቁ የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች የያዙበት ዳጎስ ያለ ካኪ ወረቀት ሸክፈዋል።

አዎን እናቴ ብዬ ከፊት እንዲቀድሙኝ አደረጉኝ።
አመስግነው ፍተሻውን አልፈን ከእኛ ቀድመው ገብተው የሚወጡ የተከፉና የተደሰቱ ፊቶችን እያየን ዞር ብለው

አማርኛ አስተርጓሚ እንዳላቸው ልጆቼ ነግረውኝ ነበር የት ይሆን የማገኛቸው አሉኝ

ካለኝ ልምድ ውስጥ መስኮት ላይ ሲደርሱ አልኳቸው

ተቁነጠነጡ አይገልፀውም
ጉጉት ይሆናል አልኩኝ በሆዴ

ሰልፍችን ደርሶ ከፊቴ ካለ ኦፊሰር ጋር ሲደርሱ የጠበቃቸውን አሜሪካዊ ኦፊሰር አስተርጓሚ ጠየቁት

አንዲት ወጣት ኢትዩጵያዊ መጥታ ከጎኑ ቆመች

ይኸውልሽ ልጄ ይሄ ሰው የመሄጃውን ፍቃድ እንዲሰጠኝ አልፈልግም። ንገሪው። ልጆቼ ጭቅጭቅ አድርገውኝ ነው የመጣሁት። ዝም ብሎ ብቻ ወረቀት ላይ ፃፍ ፃፍ አድርጎ ተከልክላለች የምትል ትንሽ ብጣሽ ማስታወሻ ቢጤ ፅፎ እንዲሰጠኝ ንገሪው።

ደነገጥኩ።
አስተርጓሚዋ ፊቷ ላይ ግራ መጋባቷ ያስታውቃል።

ኦፊሰሩ ያሉትን ቃል በቃል ጠየቃት መለሰችለት

እስኪ የያዙትን ፍይል ይስጡኝ ምንድነው አለ

ያልኩትን ፅፎ ይስጠኝ እንጂ ይሄ ምን ይሰራለታል አሉ ሴትዩዋ

ለእሱም ቢሆን ማየት አለበት ብላ በሰነድ መክተቻ ሳጥን ውስጥ እንዲያስቀምጡ አስደረገቻቸው

ፖስታውን ከፍቶ ተመልክቶ
ፈገግ ብሎ አሜሪካ መግቢያ ፍቃድ ቪዛ እንደሰጣቸው ነገራቸው።

ሴትዩዋ ተበሳጩ። ነግሬሽ አሉ።

ኦፊሰሩ ለምን እንዳልፈለጉት ጠየቃቸው

አየህ እኔ አሮጊት
በራሴ እንቢ አልመጣም ካልኩ ይቀየሙኛል።
እናንተን ምክንያት ባደርግ ግን በቃ ሞክረናል ብለው ይተውኛል።
ልጆቼ በአካል ካየዋቸው አስር አመት ሞላቸው። እኔን አሮጊቷን አየር ላይ ከሚያንጠለጥሉኝ መጥተው ቢያዩኝ መልካም ነበር። ግን እኛ አንችልም አንቺ ነይ ነው ንዝንዛቸው።

ኦፊሰሩ ማሰረዳቱን ቀጠለ

ይሂዱና ይሞክሩት። ይዩት አሜሪካንን ይወዷታል።
ካልፈለጉ ደግሞ ይመለሳሉ።

ከኃላቸው የተሰለፍኩ እኔ በአግራሞት ተመለከትኳቸው።
እዚህ ቦታ ስንቱ አምላኩን እየለመነ ይሆን።

በል ደህና ዋሉ ብለው ፓስፓርታቸውን አስረክበው ሌላኛውን ወረቀታቸውን ተቀብለው ወደመወጫው ተራመዱ።

ተረኛው ገባው ምን ይለኝ ይሆን. . .

ደግ አይለፍችሁ❤️
By Tesfaye Haile

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

05 Feb, 12:32


መቼም ቢሆን እግዚአብሔር የሰው እጅ ላይ አይጣላችሁ🙏
አሜን🙏

ሰው😡

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

04 Feb, 13:17


የ4 ወር ፍርድ ተወስኖባቸዋል︎

በቅዱስ ሚካኤል ታቦት ሲያሾፉ የነበሩት 3ቱ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በእስራት ተቀጡ
1ኛ. ተማሪ ገመቹ ምትኩ
2ኛ. ተማሪ ካሳን አድቬንቸር
3ኛ. ተማሪ ጋዲሳ ኢቲና

በአምቦ ዳዳቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን እያንዳንዳቸው በ4 ወር እስር እንዲቀጡ ተወስኗል::

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

28 Jan, 21:08


ዛሬ 21 ነው እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የምትታሰብበት አመታዊ ክብረ በዓል (አስተሪዮ ማሪያም) እመቤቴ ያሰባችሁትን ሁሉ ትሙላላችሁ🙏
አሜን🙏😍

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

26 Jan, 15:59


ትንንሽ ነገሮችን እንኳን ብናስተውል ......

ቤተሰቦቼ በሃይማኖት እና የእግዚአብሔር አማኝ ስላልነበሩ እኔ ወደዛ በቀረብኩ ቁጥር ደስ አይላቸውም ነበር :: ልጃችን ደሃ ሆኖ ሊቀር ነው ይሉ ነበር ከዛ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳልሄድ መከልከል ጀመሩ እኔም ተደብቄ መሄድ ጀመርኩኝ ከዛም ስመለስ እራት እከለከል ነበር
ከዛም አንድ ቀን ጫማ አለቀብኝ እና አባቴን ግዛልኝ ስለው እግዚአብሔር ይግዛልህ አለኝ የዛን ሳምንት የሆነ የጣልያን ጫማ ይዞ መጣ የመረጥኩትን መንገድ የተቀበለልኝ መስሎኝ ደስ አለኝ እና ስጠየቀው ለካ ለራሱ ነበር የገዛው
ጠዋት አድርጎት ወጣ ከዛ ሲመለስ እግሩን ልጦት ነበር እና አውልቆት ይሄን ጫማ ሁለተኛ እንዳላየው ውሰዱና ለዛ ቄስ አሸናፊ ስጡት አለ:: የጣልያን ጫማ አድርጌ ቤተክርስትያን ሄድኩ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር እንደሆነ አወቅኩ ትንንሽ ነገሮችን እንኳን ብናስተውል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሆነ እንረዳለን
በመንፈሳዊ ትምህርት እያደኩ ስመጣ ቤተሰቦቼ እንዳስተምራቸው ፈቀዱልኝ እና በጌታ እርዳታ ተምረው ንስሃ ገብተው ለቅዱስ ቁርባን በቅተዋል

ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

26 Jan, 13:22


ለደብረ ከዋክብት ዳጋ እስጢፋኖስ አንድነት
ገዳም የጀልባ ስጦታ ተበረከተ

ለዳጋ እስጢፋኖሰ ገዳም በ26 ሚሊዮን ብር ነው። አቶ ካሳሁንና
አቶ በላቸው በተባሉ በጎ አድራጊ ምዕመናን ተገዝተው ለዳጋእስጢ
ፋኖስ አንድነት ገዳም በስጦታ ተበርክቷል።

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

26 Jan, 13:21


የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛ ፓትርያርክ በዓለ ሢመት ተከናወነ

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በዓለ ሢመት በአሥመራ ቅድስት ማርያም በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በበዓለ ሢመቱ ላይ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቅን ጨምሮ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ከግብፅ ፣ ከሩሲያ ፣ ከግሪክ ፣ ከአርመን ፣ ከሶሪያ እና ከሕንድ የተውጣጡ የውጭ ሀገር ልዑካን ፣ የሀገሪቱ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የዲፕሎማቲክ ቡድን አባላት ፣ የሁሉም አህጉረ ስብከትና የዋና ዋና ገዳማት ተወካዮችና ምእመናን ተገኝተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ታኅሣሥ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ እንዲሆኑ መመረጣቸው ይታወሳል።

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

የቴሌግራም ቻናል T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

21 Jan, 15:07


" የትግራይን ህዝብ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል" - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች መልእክት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለዋል።

ሰልፉን የጠራው የትግራይ ርስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያዘጋጀው መልእክት የተቀበሉት ፕሬዜዳንቱ አቶ ጌታቸው ፥" ከጦርነት ወጥተን በተነፃፃሪ ሰላም በምንገኝበት ጊዜ ሴት ሙስሊም እህቶቻችን በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ሲከለከሉ ማየት በጣም የሚያሳዝን ነው " ብለዋል።

" ችግሩ ገና ከጅምሩ ከትምህርት ቤቶቹ አመራሮች ፣ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ በመነጋገር ለመፍታት ጥረት ሲደረግ ቆይተዋል። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ያልነበረት ጉዳይ ነው። አሁንም የትግራይ ህዝብ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል " ብለዋል።

" ጉዳዩ ቶሎ መታረም እንዳለበት የሚያግባባን ቢሆንም ፤ ከስሜት በፀዳ አስተዋይነትና ዘላቂነት ባለው መንገድ መሆን እንደሚገባ ሁላችንም መገንዘብ ያስፈልጋል " በማለት አክለዋል።

ችግሩ በፍጥነት እንዲፈታ አስተዳደራቸው ዝግጁ እንደሆነና እንደሚሳራም አመልክተዋል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የተነሳ ጥያቄ አጀንዳ መሆን አልነበረበትም ብሎ እንደሚያምን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተባባሪዎቹ እና ተሳታፊዎቹ ላሳዩት ጭዋ የሆነ ባህሪ ምስጋና አቅርበዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ፍፁም ሰላም በሆነ መንገድ መጠናቀቁን የአባይ ሚዲያ ቤተሰብ ገልጿል።

@tikvahethiopia እንደዘገበው

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

21 Jan, 15:07


👇👇👇👇👇

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

21 Jan, 12:31


ፖሊስ ስራውን እየሰራ ነው

ሁለቱ ተይዘዋል አንዱ ፈተና ላይ ስለሆነ እየተጠበቀ ነው በዩኒቨርሲቲው ፀጥታ እና በ አምቦ ከተማ ፀጥታ ቁጥጥር ስር ውለዋል

ማንም ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጭ ድርጊት ፈጽሞ ዝም አይባልም የህግ የበላይነት ይከበራል

ቀጣይም ያለውን ሁኔታ እየተከታተልኩ አሳውቃችኋለሁ🙏

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

20 Jan, 07:55


"ማረግና ስልጣኔ አንተ ፊት ለመንበርከክ አያግደኝም"

እግሮች ሁሉ በቃልኪዳኑ ታቦት ፊት ይንበርከኩ

ተባረክ ዘመንህ ይባረክ🙏

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

19 Jan, 13:57


መልእከተ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፣የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣
ክቡራን የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣
ክቡራን አምባሳደሮችና የኮር ዲፕሎማቶች፣
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች፣
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣
የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣

በአጠቃላይ በቅርብና በሩቅ ሆናችሁ የ2017 ዓ.ም በዓለ ጥምቀት እያከበራችሁ የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያኖች በሙሉ፣

በመጠመቁ የክዋኔ ልጅነቱን አስመስክሮ የጸጋ ልጆች እንድንሆን ያበቃንን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመት ምሕረት የጥምቀተ ክርስቶስ  በዓል  አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

ወመጽአ ቃለ እግዚአብሔር ኀበ ዮሐንስ ወልደ ዘካርያስ፤የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ  ዮሓንስ መጣ (ሉቃ ፩÷፪፤)  የመሲሑ መንገድ ጠራጊ ሆኖ እንዲያገለግል በእግዚአብሔር ዘንድ ከዘመናት በፊት የተመረጠው ዮሓንስ ወልደ ዘካርያስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ነበር፣ ቅዱስ ዮሓንስ በዮርዳኖስ በረሃ በብሕትውና ሕይወት በነበረበት ወቅት የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ፣ ወደ እርሱ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ የሚል ነበር፡- ‹‹የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ፣ዓዘቅቱ ሁሉ ይሙላ፣ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን ፤ሸካራውም መንገድ ይስተካከል፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ››፣

መጥምቁ ዮሐንስ ይህንን የድኅነት መልእክት ከእግዚአብሔር የመጣለት በገዳመ ዮርዳኖስ ባሉ ከተሞች እያስተማረና ሕዝቡን ለንስሐ እያዘጋጀ በነበረበት ጊዜ ነው፤ የትምህርቱ ዋና ይዘትም የጌታ መንገድ የሰው አእምሮ መሆኑን በማስገንዘብ ጌታ በዚህ መንገድ እንዲጓዝበትና እንዲመላለስበት በደንብ ይዘጋጅ የሚል ነው፣የዝግጅቱም ሁናቴ በዝርዝር ሲገለጽ ተስፋ በመቁረጥ እንደ ዓዘቅት የጐደጐደውና የጨቀየው አእምሮ በተስፋ ድኂን ቀና ይበል፣

በሥልጣን፣ በዕውቀት፣በሀብትና በወገን ከሁሉ የላቀ እንደሆነ የሚያስብም እንደማንኛውም ሰው መሆኑን ተረድቶ እኩልነትን ተቀብሎና ኣክብሮ ይኑር፤ በክፋትና በምቀኝነት፣ በተንኮልና በሴራ አተርፋለሁ የሚል ጠማማ አእምሮም ወደ ቅን አስተሳሰብ ይመለስ፤ በቂም፣ በበቀልና በጥላቻ ተዘፍቆ የሚኖር ልብም በሰላም በፍቅርና በስምምነት ወደሚገኝ የተስተካከለ ጣዕመ ሕይወት ይግባ ማለት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የተከበራችሁ የበዓሉ ተሳታፊዎች!

እግዚአብሔር ምድርና ሠማየ ሠማያት የማይችሉት ምሉእ፣ረቂቅና ስፉሕ ነው፤ ይሁን እንጂ በቅዱሳን ሰዎች አእምሮ ውስጥ ማደርና ማረፍ በእጅጉ የሚሻ አምላክ እንደሆነ ደጋግሞ ገልጾአል፣መመላለሻውም በሰው ኅሊና፣ በሰው ልቡና እና አእምሮ ውስጥ እንደሆነ አልሸሸገም፣ያም በመሆኑ መንገዱና ጥርጊያው የሆነ የእኛ አእምሮ ቀጥ ያለና ይማይጐረብጥ እንዲሆንለት ያዘናል፡፡

መጥምቁ ዮሐንስም ይህ ዓይነቱ ዝግጅት በሰው አእምሮ ውስጥ እንዲኖር ለመቀስቀስ ተልኮአል፣ዝግጅቱ የጠቅላላ ስራው መቋጫ አልነበረም፣የዝግጅቱ ዋና መቋጫ ሰው ሁሉ እንደ ስምዖን የእግዚአብሔርን ማዳን በዓይኑ አይቶ በአእምሮው አስልቶ በልቡ አምኖ የድኅነቱ ባለቤት መሆን ሲችል ነው፣ የእግዚአብሔር ፈቃድና ፍላጎትም ይኸው ነው፣ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችንኢየሱስ ክርስቶስ የኛን ሰውነት በመዋሐድ አምላክና ሰው ሆኖ በዚህ ዓለም እንዲገለጥ ያስፈለገበት ዓቢይ ምክንያትም ይኸው ነው፣ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በዛሬው ዕለት በፈለገ ዮርዳኖስ የፈጸመው ምስጢረ ጥምቀት ሰው የሚያድንበት ዕድል ምን እንደሆነ ለማስረዳት ነው፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የተከበራችሁ የበዓሉ ተሳታፊዎች!

ሰው በራሱ ዘላቂ ሕይወት የለውም፣የሕይወት ምንጭ እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ሰው ዘላቂ ሕይወትን ማግኘት የሚችለው የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ ግንኙነት ሲኖረውና በግንኙነቱ አማካኝነት ዘላዓለማዊ ሕይወት ከእግዚአብሔር ሲቀዳጅ ነው፣ይህንንም ልዩ ግንኙነት የሚያገኘው ከእግዚአብሔር ሲወለድ ነው፣ለመወለድ ደግሞ በእግዚአብሔር የማዳን ስራ ማመንና መጠመቅ ሲቻል ነው፣ሰው ሲጠመቅ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል፡፡

እግዚአብሔርም በልጁ አእምሮ ውስጥ በሃይማኖት በአምልኮና በምስጋና ይመላለሳል፣ያድራል፣ያርፋልም፣ ሥጋ የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ የተባለውም ይህንን ልጅነት ነው፣በዚህ ልጅነት ምክንያት ሰው የዘላለም ሕይወት ባለቤት ሆኖ ይኖራል፣ጥምቀት ለሰው ልጆች የሚያስገኝልን ጸጋ ይኸው ነው፣

ታዲያ የእግዚአብሔር የዝግጅት ጥሪ ዘላዓለማዊ ሕይወትን ለማደል ሆኖ ሳለ የተጠበቀው ዝግጅት ግን ከሰው እየታየ ኣይደለም፣ዛሬም እኛ ሰዎች አእምሮችን ጐድጓዳ ዓዘቅት ሆኖ በመቀጠሉ ለጉዞ አልተመቸውም፣ዛሬም ልባችን ከተራራና ኮረብታ ባልተናነሰ ሁናቴ ትዕቢት እንደተሞላ ነው፣ከቅንነት ይልቅ ጠማማነት፤ ከእውነት ይልቅ ማሴር የየዕለት ተግባር አድርገነዋል፣በዚህም እግዚአብሔር ከኛ እንዲርቅ አድርገናል እሱም በኣጸፋው ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጥቶናል፣ ዓለማችን በአሁኑ ጊዜ ያላት ምስል ይኸው ነው፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የተከበራችሁ የበዓሉ ተሳታፊዎች!

ዓለማችን አሁን ያለችበት ምስል ለሰው ልጅ ሁሉ በጣም አሳሳቢና አስፈሪ ነው፣ለእግዚአብሔር አልታዘዝም ብሎ በነውረ ኃጢአት መጋለብና ለጦርነትና ለዕልቂት የሚሆን መሳሪያ በማምረት መሽቀዳደም የሚበጅ አይደለም፣ከዚህ ይልቅ ዓለማችን አሁንም ቆም ብላ ብታስብና ሕይወት ወደ ሆነው እግዚአብሔር እንድትመለስ በእግዚአብሔር ስም እንመክራለን፣በሰው ልጆች የሚታይ መሠረታዊ ችግር ከእግዚአብሔር መለየትና ለእሱ ያለመታዘዝ እንጂ የሀብት ዕጥረት አይደለም፡፡

ምድሪቱ ኁልቈ መሥፈርት የሌለው ሀብት በውስጥም በውጭም አጭቃ ይዛለች፣እሱን በፍቅርና በስምምነት ብናለማው ከበቂ በላይ ነው፣እሱም ቀርቶ ያለውን ለጦርነትና ለዕልቂት ከምናውለው ለልማት ብናውለው ችግርና እጦት ከምድራችን በጠፋ ነበር፣አሁንም ራሳችንን በራሳችን ከማጥፋት ተቆጥበን የምድራችንን የአየር ንብረትና የተፈጥሮ ሥነ ምኅዳር በመጠበቅ ግጭትንና ጦርነትን በማስቆም ለተመደበልን ሰላማዊ ሕይወት ልንተጋ ይገባል፡፡

በመጨረሻም፡-
በዓለ ጥምቀቱ ከእግዚአብሔር የምንወለድበትን ዕድል የከፈተ ነው፣በዚህም ዕድል የእግዚአብሔር  ልጆች ለመሆን በቅተናል፣
ስለሆነም የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆናችን ልዩ ምልክታችን የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነት፣የፍትሕና የእኩልነት ሰዎች ሆነን እንድንገኝ ነውና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ ልጆቻችን ሁሉ በሃይማኖት ጸንታችሁ ለሰላምና ለአንድነት ከምንጊዜውም በላይ የበኩላችሁን ጥረት ታደርጉ ዘንድ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡  

በዓለ ጥምቀቱን የሰላምና የበረከት ያድርግል
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት
ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ  ዘአኲስም ወዕጨጌ
ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

19 Jan, 13:57


👇👇👇👇

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

19 Jan, 13:48


አብሮነት!
ወንድማማችነት!
እህትማማችነት!
ህብረብሔራዊ አንድነት!

በመዲናችን አዲስ አበባ

ጥምቀት 2017

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

19 Jan, 10:53


ወንአምኒ በሀቲ ጥምቀት🙏😍

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ🙏

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

18 Jan, 07:16


"እኔስ የታቦት ስራ አለብኝ"

ማልደን ተነስተን ከ4ኪሎ እስከ 6 ኪሎ የሚገኘውን ለከተራው ዝግጅት አስፋልቱን አጥበን አዋራው እንዳያስቸግር ውሃ እንዲጠጣ አድረወገናል።

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

17 Jan, 13:51


ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት የነበራቸው የቅድመ ሥራዎች ጉብኝት አድርገዋል🙏

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

17 Jan, 07:14


ዛሬ ከ4ኪሎ ወደ 6ኪሎ የሚወስደው የቅድስት ስላሴ የግቢ ገብርኤል እና የበዓታ ማሪያም ታቦተ ህጉ የሚያልፍባቸው ቦታዎች በኮሊደር ልማት ምክንያት በእድሳተወ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ መንገድ ላይ ታቦተ ህጉ ሲያልፍ አዋራ እና ሌሎች እንቅፋት የሚሆኑ ድንጋዮች የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ማልደን ተነስተን የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር አባላቶች መንገዱን ምቹ የማድረግ ስራ ጀምረናል።

በነገው እለት ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ አስፋልቱን የምናጥብ ሲሆን በ4ኪሎ እና በ5ኪሎ አከባቢ የምትገኙ ወጣቶች የዚህ የበረከት ስራ ተካፋይ እንድትሆኑ ጋብዘናል።

ሁሌም በስራ ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 🙏

ማቲ ሸገር / Mati Sheger

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

02 Jan, 05:01


ዛሬ ታህሳስ 24 ነው የአባታችን ኢትዮጵያዊው ጻዲቅ አቡነ ተክለሃይማኖት ልደት ነው
የአቡነ ተክለሃይማኖት ጸጋና በረከት በናተ ላይ ይሁን🙏
አሜን🙏

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

31 Dec, 07:25


የታዳጊ ህጻን የተማሪ ህይወት ላይ የሚቀልዱ የመንግስት ት/ት ቤት አስተዳደሮች ማነው አቤት ሚላቸው...?
በዝርዝር እመጣበታለሁ ይህ ጨዋታ አደለም የህይወት ጉዳይ ነው

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

27 Dec, 17:03


ታህሳስ 19 የሊቁ መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል ነው
መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ሰልስቱ ደቂቅን ከእሳት እንደታደጋቸው ካላችሁበት ማንኛውም ችግር ታድጎ ያውጣችሁ🙏
አሜን🙏

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

26 Dec, 14:13


ከኢሳት ጋር ከነበረኝ ቆይታ የተቀነጨበ🙏

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

26 Dec, 12:53


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለቁልቢ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በአል ድሬዳዋ ገቡ

ድሬዳዋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፣የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
እና የቅዱስ ሲኖዲዎስ አባል ብጹህ አቡነ በርተሎሜዎስ እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

በድሬዳዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስትያን በሀይማኖታዊ ስርአት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

25 Dec, 13:09


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ከሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ጋር ተወያዩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መሀመድ እድሪስን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።

በውይይቱ ወቅትም በሀገሪቱ የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ለማሰቀጠል በጋራ ምክክር ያደረጉ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኗ ከመንግሥት ጋር በመደጋገፍና በመቀራረብ በሰላም ዙሪያ በትጋት እንደምትሠራ ቅዱስ ፓትርያርኩ በማረጋገጥ የሰላም ሚንስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ለትውውቅና ለመወያየት ወደ መንበረ ፓትሪያርክ በመምጣታቸው አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ክቡር ሚንስቴሩ በበኩላቸው አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት ቤተ ክርስቲያኗ በሰላምና በሀገረ መንግሥት ግንባታ ካላት ልምድ እየታዩ ያሉ የሰለም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ ሀገራዊ የሰላም ጸሎት ጥሪ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

24 Dec, 06:38


https://youtu.be/Pp5_vxnqaYc?si=DMxKC5RVJKfIwCKo

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

22 Dec, 12:40


እሁድ በቤተ ክርስትያን እንባረክባት ዘንድ ከአምላክ የተሰጠችን ቀን ናት

እኔም እሁድን (ሰንበትን) በቃጥላ ጺዮን ማሪያም ከልጄ ጋር🙏

📸ትንሹ አኩሩፎ ነው ጸበል ተጠምቆ😂

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

21 Dec, 13:03


አንበሳ ባስ ውስጥ ዋሌቱን ከ860 ብር ጋር በቅፅበት የተሰረቀው ግለሰብ እንዲህ እያለ ሲጮህ ተደመጠ:-

" እዩ ተናግሪያለሁ ! ዋሌቴን አሁን እዚሁ ነው የተነጠኩ። ብትመልሱልኝ ይሻላል። ካልመለሳችሁልኝ በ1993 ዓ.ም ህዳር 14 አባቴ የሠራውን ታሪክ እደግመዋለሁ"

በማለት በቁጣ ተናገረ፤ ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ተደናገጡ።
ሰውየው በመቀጠል...
"አባቴ ይሙት ባሱ ሳይንቀሳቀስ ህዳር 14/1993 የሞተውን የአባቴን ታሪክ እንዳልደግመው ለመጨረሻ ጊዜ ተናግሪያለሁ"

እያለ ሲዝት 5 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዋሌቱን ገልጦ ለማየት እንኳን ፋታ ያላገኘው ፍሬሽ ሌባ መሬት ላይ ይጥለውና እራሱ አንስቶ "ይሄው ዋሌትህ" በማለት ይመልስለታል።

ባሱ ውስጥ የነበሩ በእድሜ ገፋ ያሉ ተሳፋሪዎችም
"እሰይ ተመስገን ሊጨርሰን ነበር" እየተባበሉ ኣውቶብሱ ጉዞውን ቀጠለ።

የባሱ ተሳፋሪዎች ሰውየው መረጋጋቱን ካስተዋሉ በኋላ የ1993ቱን ታሪክ ለመስማት ቋምጠው :-
"አባትህ በ1993 ህዳር 14 ምን ነበር ያደረጉት እባክህ ?" በማለት ፈራ ተባ እያሉ ሲጠይቁት ምን ብሎ ቢመልስላቸው ጥሩ ነው ?

"አባቴ ዛሬ በህይወት የለም። ነፍሱን ይማረውና ህዳር 14/ 1993 ላይ እንዲህ እንደኔ አንበሳ ባስ ወስጥ ለታከሲ መሳፈሪያ እንኳን ሳያስቀሩ ሌቦች ገንዘቡን ሰርቀውት ጃኬቱን እንደ እብድ እያውለበለበ ከሳር ቤት ፈረንሳይ ድረስ በእግሩ ነበር የሄደው።

እኔም ዛሬ ብሬን ባትመልሱልኝ ኖሮ ያው የታክሲም ስለሌለኝ በእግሬ ወደ ቤቴ በመሄድ የአባቴን ታሪክ እደግመው ነበራ" ብሏቸው እርፍ፡፡

Via አሌክስ አብረሀም

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

20 Dec, 14:10


ዛሬ ከኢሳት ቴሌብዥን ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገናል ፕሮግራሙ በቅርቡ ይተላለፋል።

#ማቲ_ሸገር

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

18 Dec, 11:46


የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሕንጻ እድሳት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ︎

ከሁለት ዓመት በላይ የቆየው የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ እድሳት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል።

ካቴድራሉ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በአሁኑ ወቅት 95% ሥራው የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በቀጣዩ አንድ ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እና ከጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተነግሯል።

የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በፌደራል ቅርስ ባለሥልጣን መስሪያ ቤት እና በጠቅላይ ቤተክህነት የእድሳት ፈቃድ አግኝቶ መታደስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሲታደስ ቆይቷል። አሁን እስከተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ 124,827,576 ብር ወጪ እንደተደረገበት፤ ሆኖም ከተፈራረመው የኮንትራት ብር 47 ሚሊዮን ቀሪ ክፍያ ስላለበት ምእመናን አሁንም እገዛና ድጋፋቸው እንዳይለይ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ሢራክ አድማሱ ገልጸዋል።

ቀሪ ክፍያውን ለማጠናቀቅ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር እንዲሁም ታኅሣሥ
28 ቀን ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ልዩ የምስጋና መርሐግብር መዘጋጀቱን ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።

በተያያዘም ከጥር 1 እስከ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ዓውደ ርዕይ እና ጥር 4፣ 5 እና 6 ቀን የምሽት ጉባኤ በካቴድራሉ ግቢ ውስጥ እንደሚደረግ ተነግሯል።

#ማቲ_ሸገር

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

30 Nov, 15:20


ባለስልጣን መሆኑን አትርሱ
ፖለቲካ ሌላ ይህ ሌላ

ይህ በስካይ ላይት ሆቴል የመጽሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ነው በቦታው ደግሞ ዲ/ን ዳንኤል ንግግር እንዲያደርግ ተጋብዞ ተገኝቶ ነው

መዝሙሩ የመጽሐፉ አዘጋጆች የወንጌል አማኝ ስለሆኑ በመዝሙራቸው ጀመሩ :: ይችን ቪድዮ ቆርጠው ሌላ ነገር ማሰብ ስህተት ነው ዲ/ን ዳንኤል ክብረትም በቦታው ሲዘምርም ሆነ ሲያመልክም አይታይም

የተለያዩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ባለስልጣናት እንዲሁም ሌሎች ፓስተሮች (ፓ/ር ቸሬ )በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ልዩ ፕሮግራሞችን እንደሚታደሙ ይታወቃል ለዲ/ን ዳንኤል ሲሆን ግን ሌላ ነገር መታሰቡ ስህተት ነው ባለስልጣን መሆኑን አትርሱ

ፖለቲካ ሌላ ይህ ሌላ

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

30 Nov, 04:17


"የናቁሽ ሁሉ ወደ እግሮችሽ ጫማ ወድቀው ይሰግዳሉ"
እንኳን ለህዳር ጺዮን ማሪያም አደረሳችሁ🙏
እመቤቴ በጎደለ ነገራችሁ ሁሉ ትሙላላችሁ🙏
አሜን

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

29 Nov, 11:52


የሌሊት ወፍ

"የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡

የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡

ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡

ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡

ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡

የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡

ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ

የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡"
(ብላቴን ጌታ ኅሩይ)

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

23 Nov, 13:24


ህዳር 15 የጌታችን የመድሃኒታችን የልደት (የገና) ጾም ይገባል
ሳላውቅ በስህተት አውቄ በድፍረት ያስቀየምኳችሁ ሁሉ ይቅር በሉኝ እኔም ይቅር ብያችኋለሁ🙏

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

21 Nov, 04:10


ዛሬ ሊቀ መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል ነው ቅዱስ ሚካኤል በነገሮች ሁሉ ይባርካችሁ ወደ ከፍታው ይምራችሁ🙏
አሜን😍

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

07 Nov, 16:07


⭐️  በጋዜጠኛው እና በገበሬዎቹ መካከል የተፈጠረው አስደናቂ ነገር⭐️
  እንዲህ ነው የሚካኤል ወዳጅ ረዳቱን የሚያውቅ።

   የቀጭን ወንዝ አጣብቂኝ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ ርቀት በመንዝ ማማ ምድር የሚገኝ ከ100ዓመታት በላይን ያስቆጠ በጸሎት ሰሚነቱ እና በፈዋሽ ጸበሉ የሚታወቅ ሲሆን በጣልያን ወረራ ጊዜ ንጉሱ ይህን ታቦት ይዘው ተስለው ተዋግተዋል።በታቦቱ እርዳታ በአማራ ሳይንት በማይጨው፣በወሎ፣በይፋት፣በመንዝ ጌራ ምድር እና ማማ ምድር ጠላትን ድል ነስተውበታል።ሲመለሱም አሁን ያለውን ሕንጻ መቅደስ አሰርተው አክብረውታል።በፍቅሩ ብዛት እየተመላለሱ ሳሉ ፍቅርህ አጣበቀኝ ሲሉ "አጣብቂኝ ቅዱስ ሚካኤል" ብለው ሰይመውታል።
    ይህ በንጉሱ የተሰራው ሕንጻ ቤተ-መቅደስ ከዘመን ብዛት ከማርጀቱ እና ለምዕመናን ከማነሱ የተነሳ አዲስ ሕንጻ ቤተ-መቅደስ መስራት አስፈላጊ ሆኖ ይኸው ከተጀመረ 6 ዓመታትን አስቆጠረ። ይህንንም ሥራ ወደ ገዳማት ከሚጓዙ ምዕመናን በመንገድ ላይ ልመና እና በማስተባበር የምናከናውን ቢሆንም አሁን ካለው ወቅታዊ ችግር የተነሳ ምዕመናን ከአመት በላይ ወደ ገዳማት የሚያደርጉት ጉዞ የተቋረጠ በመሆኑ ሕንጻውን ለመጨረስ ከመቸገራችን አልፎ አዲሱም ሕንጻ ለአደጋ ሊዳረግብን ነውና የእርስዎን ትብብር እንሻለን።እርስዎም ድጋፍዎትን በቤተ ክርስቲያኑ አካውንት

      1,በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ   ➯1000529855196
      2,በአቢሲኒያ  ባንክ ➯130222398
   
  "የቀጭን ወንዝ አጣብቂኝ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል" ብላችሁ ማገዝ ትችላላችሁ።
 
🤲በጸሎት እንድናስባችሁ ያገዛችሁ ወዳጆቹ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ስመ ክርስትናችሁን ላኩልን።
   
ቴሌግራም  ➯@Omichaelll    

ዋትስአፕ ➯https://Wa.me/+251980291967  


ለበለጠ  መረጃ  📱 +2519 16 55 80 80
                       📱 +2519 33 03 83 34

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

07 Nov, 16:07


👇👇👇👇👇👇

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

04 Nov, 19:33


"ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ነው"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመልእክታቸውም "ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ነው ብለዋል።

የቅዱስነታቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

"ሰላምየ አኀድግ ለክሙ ወሰላመ አቡየ እሁበክሙ፡- ሰላምን እተውላችኋለሁ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፡፡" ዮሐ. ፲፬፥ ፳፯

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ሥጋ ለብሶ በሚታይ ሰውነት የተገለጠው ሰላምን ለማምጣት ነው፡፡ የማዳን ተግባሩን አከናውኖ፤ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በምድርና በሰማያት ላሉ ሰላምን አድርጎ ባረገ ጊዜም ዓለም እንደምትሰጠው ሰላም ያይደለ ልቡናን የሚያሳርፍ፣ መንፈስን የሚያረጋጋ እውነተኛ ሰላምን ሰጥቶናል፡፡ ልዑል አምላክ ትሑት ሥጋን በመዋሐዱም ታላላቆች ለይቅርታ ዝቅ በማለት የሰላም ምክንያት መሆን እንደሚችሉ በተግባር አስተምሮናል።

ሰላም የሰው ልጆች ፍላጎት፣ የብዙ ምንዱባን የየዕለት ናፍቆት ነው። የበርካታ ዘመናት ቅርሶች፤ ጊዜ፣ ገንዘብ እና የሰው ጉልበት የፈሰሰባቸው ግንባታዎች በሰላም ማጣት በቅጽበት ይፈርሳሉ። ሰላም ካለ የዓለም ሀብት ለሁሉም በቂ ነው። ሰላም ማጣት ግን ብዙ ሠራዊት፣ ብዙ የጦር መሳሪያ እንዲዘጋጅ እያደረገ ሀብትን ያወድማል። ጦርነት ማለት ሀብትና ሕይወትን ወደሚነድ እሳት ውስጥ መጣል ነው። የአንደኛና የሁለተኛ ዓለም ጦርነት፣ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ጠባሳው አሁንም የዓለምን መልክ አበላሽቶታል። ሰላም በውስጥዋ ገራምነት፣ ትዕግሥት፣ ታዛዥነትና በትህትና ዝቅ ማለት ስለሚገኙ መራራ ትመስላለች፤ በውጤቷ ግን ሀገርን ከጥፋት፣ ሕዝብን ከመከራ ማትረፍ የሚቻል በመሆኑ ዋጋዋ ከፍ ያለ ነው።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላም የሆነው ክርስቶስ የሚሰበክባት፣ የሰላም መልእክተኞች በውስጥዋ የሚመላለሱባት፣ በግብረ ኃጢአት የወደቁት በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁባት የሰላም ድልድይ ስለሆነች በሥርዓተ ቅዳሴዋ ሰላምን ደጋግማ ታውጃለች፤ በጸሎቷ ለመላው ዓለም ሰላምን ትለምናለች፤ በጉልላትዋ ላይ የሰቀለችው መስቀልም ሰላምን የሚሰብክ ነው፤ የመስቀሉ ቅርፅ ወደ ላይና ወደ ጎን መሆኑም ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ሰላም መሆን እንዳለብን የሚያስገነዝበን ነው። ታሪካችን እንደሚነግረን ወንድማማቾች ሲጋደሉ፣ በሕዝብ መካከል መተላለቅ ሲመጣ ቤተ ክርስቲያን ታቦት አክብራ፣ በእሳት መካከል ገብታ ሰላምን ስታወርድ የኖረች ናት። በሀገር ውስጥ ግጭቶች በተፈጠሩበት ጊዜም የሰላም ጥሪን ያላስተላለፈችበት ቀንና ሰዓት አይገኝም፡፡

ሰላምን የመወያያ ርእስ አድርገን ስንሰባስብ በጦርነት መካከል የተጨነቁ ሕዝቦች፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ እና ምን እየተደረገ እንዳለ በውል የማይገነዘቡ ደካሞች ተስፋ ያደርጉናል። ስለዚህ ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ስለሆነ ይህ ጉባኤ ከውይይት ባሻገር በተግባር ጭምር የሰላም ተምሳሌት መሆን እንደሚገባው ለማሳሰብ እንወዳለን።

ዓለም በዚህ ወቅት አስጊ በሆኑ ጦርነቶች ውስጥ እያለፈች ነው፡፡ በሩሲያና በዩክሬን ያለው ጦርነት የዓለምን ኢኮኖሚ አናግቷል፤ ከሁሉ በላይም ክቡር የሆነውን የሰው ሕይወት እየቀጠፈ ነው። በእስራኤል፣ በፍልስጤም እና በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ያለው አለመረጋጋት ሁሉንም የሚነካ ነውና በጦርነቱ የሚሳተፉት በሙሉ ወደ ሰላም እንዲመለሱ፤ የዓለም መሪዎችም ልበ ሰፊ ሆነው ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በመጨረሻም በሀገራችን ውስጥ ያሉት ግጭቶች የመቆሚያ ድንበራቸውን ያገኙ ዘንድ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር የተባረከ ጉባኤ ያድርግልን!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
©የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ/ጽ/ቤት፤

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

27 Oct, 18:30


ጥሩ ጨዋታ ነበረ በ2-2 ተጠናቋል

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

27 Oct, 15:26


ዛሬ አርሰናል በሰሜን ለንደን 3 ነጥባችንን ይዘን እንወጣለን
ቃል ቃል ነው

ወጥር💪

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

25 Oct, 18:38


ዜና ዕረፍት‼️

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በአሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ተሰምቷል።

#ማቲ_ሸገር

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

24 Oct, 15:38


ከአምላክ ጋር ተርፋለሁ🙏😍

ተመስገን🙏

#ማቲ_ሸገር

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

21 Oct, 19:23


መርካቶ የተፈጠረውን እሳት አደጋ ለመቆጣጠር በሪኮፍተር ጭምር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ታውቋል
እግዚአብሔር ይርዳችሁ🙏

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

21 Oct, 15:54


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ' የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና አስተዳዳሪዎች ካህናት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት በቅዱስናቸው የመክፈቻ ንግግር የሚጀምር ይሆናል፡፡

#ማቲ_ሸገር

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

20 Oct, 13:09


ምንም ተፈጠረ ምን ህይወት ይቀጥላል

ህይወት የምትሸነፈው በትምህርት ብዛት ወይም ረቂቅ እውቀቶችን በመረዳት አይደለም። ኑሮን የተሻለ ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ እራስን የተሻለ አድርጎ መገኘት ነው። በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በስነልቦና፣ የአላማ ሰው በመሆን የተሻለ ሆኖ መገኘት። የስልጠና ብዛት፣ አስተማሪ ፕሮግራሞችን ደጋግሞ መከታተል፣ ብዙ ራስ አገዝ መፅሃፍትን ማንበብ፣ አነቃቂ ንግግሮችን ደጋግሞ ማድመጥ ራስን ገዝቶ እውቀቱን መኖርና የተማሩትን መሬት ላይ ማውረድ ከሌለበት የማያባራ ቅዠት ውስጥ መክተቱ አይቀርም። ከቅዠት ለመውጣት ሞክሩ፣ ህይወትን በሚያሳምኑ ተጨባጭ ክስተቶች መሙላት ጀምሩ። እራሳችሁ አምናችሁበት ማድረግ ከቻላችሁ ማንንም የማሳመን ግዴታ የለባችሁም። ከጎናችሁ የሚቆም ሰው ፍለጋ አትድከሙ፣ የሚረዳችሁን ሰው ጥበቃ ቆማችሁ አትቅሩ፣ እውቀታችሁ የሚወራ ብቻ ሆኖ እንዲቀር አትፍቀዱ። መነቃቃት የእድገትን ጉዞ የሚያስጀምራችሁ ነዳጅ ሲሆን እውቀት ደግሞ ወደ ከፍታው የምትወጡበት ደረጃ ነው። ብዙ ባወቀ ቢሆን ህይወትን ለመቀየር እውቀት ብቻውን በቂ ይሆን ነበር።

ከእውቀት በላይ የምትኖሩት እውቀት ላይ አተኩሩ፣ ከመረጃው ብዛት በላይ ያላችሁን መረጃ፣ የተረዳችሁትን ነገር ለማድረግ ሞክሩ፣ ደጋግሞ ከመማር፣ አብዝቶ ከማጥናት በላይ የተማራችሁትን እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ፣ ያጠናችሁትን መቼ መጠቀም እንዳለባችሁ ጠንቅቃችሁ እወቁ። የናንተ ህይወት 100% የእናንተ ሃላፊነት ነው። የማይቀይራችሁን መረጃ ከማሳደድ ባላችሁ መረጃና እውቀት እራሳችሁን ቀይራችሁ ተገኙ። ዘወትር በመማማርና በማወቅ ከመጠመድ በጥቂቱም ቢሆን ያወቃችሁትን ለመኖር ሞክሩ። በስተመጨረሻ የማይኖር እውትም ሆነ ትምህርት ከብክነት በቀር ሌላ ትርጉም ሊኖረው አይችልም። እውቀት የሚኖር እንጂ ልብ ውስጥ ተቀብሮ ለአመታት በሃሳብ የሚያስጨንቀን ነገር አይደለም። ማንም ሰው ህይወቱን የመቀየር ሃይል ያለው እውቀት ችግር የለበትም፣ ሁሉም ሰው ምን ቢያደርግ ምን እንዴትና በምንያህል ፍጥነት መቀየር እንደሚችል በሚገባ ያውቃል። ችግሩ እውቀቱ ባዶ እውቀት ብቻ መሆኑ ነው። ያውቃል ነገር ግን ፍረሃቱን ማሸነፍ አልቻለም፣ ነገሮች ገብተውታል ነገር ግን ለገባው ነገር እራሱን ማስገዛት አልቻለም፤ የተረዳው ነገር አለ ነገር ግን መረዳቱን ከማውራት በቀር የመኖር ብርታቱን አጥቷል።

የመረጃው ብዛት ሳያሰክርህ፣ የእውቀቱ ብዛት ሚዛንህን ሳያስትህ ባለህ መረጃ ወደፊት ተራመድ፣ እውቀትህን በጥበብ ተጠቀም። ብዙ ማወቅ ክፋት የለውም እውቀቱ ተግባር አልባ ከሆነ ግን አንድ ቀን መሰልቸቱ አይቀርም። ከአሰልቺ ፍሬ አልባ እውቀትና ትምህርት ይሰውርህ፣ ምንም ሳታደርገው እንዲሁ ከጊዜው ጋር ከሚያረጅ መረጃ ይሰውርህ። ህይወትን በሚገባ እየኖሩ፣ በእውቀት ላይ እውቀትን እየጨመሩ፣ በየጊዜው ጥበብን እየተላበሱ ልክ እንደ አዋቂና እንደ ጠቢብ መኖር ሲቻል በስንፍናና በፍራቻ ቁጥጥር ስር ወድቆ ከሚገባን በታች መኖር ከቁጪትም በላይ የጭንቀታችን መንስኤ መሆኑ አይቀርም። ጠቢባን ጠቢብ የተባሉት ያላቸውን ጥበብ መኖር ስለቻሉ ነው፤ አዋቂዎችም አዋቂ የተባሉት እውቀታቸውን መኖር እስከቻሉ ነው። ለማወቅ የከፈልከውን መሱዓትነት ማንም አይቆጥርልህም፣ ለመማር የፈጀሀውን ጊዜ ማንም ከግምት ውስጥ አያስገባልህም። ዋናው ጥያቄ፦ "ምን ተማርክ? ምን ታውቃለህ? ምንስ አድርገሃል?" የሚለው ነው። እውቀትህን ኑር፣ የተረዳሀውን በተግባር ግለፅ፣ በእርግጥም ይህ ህይወት የሚኖር ህይወት እንደሆነ ለራስህ አረጋግጥ።

ግሩም ሰንበት ቀን ይሁንልን!

#ማቲ_ሸገር

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

16 Oct, 14:00


አባ መፍቀሬ ሰብዕ - ስማቸውን በተግባራቸው የለወጡት የሁሉ አባት

ከ73 ዓመታት በላይ ዛፎችን ሲተክሉ ኖረዋል። ለእርሳቸው ዛፍ የሚቆርጥ ቀርቶ ቅጠል የሚበጥስም የማርያም ጠላት ነው ይባላል። "‘የሀገሬ መራቆት የኔ መራቆት ነው’ ብለው ዛፍ ሲተክሉ እና ሲንከባከቡ ይኖራሉ" በማለት ነው ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሚገልጿቸው።

ተፈጥሮን አብዝተው በመንከባከብ፣ ችግኞችን በመትከል በርካታ ሰው ሰራሽ ደኖችን በመፍጠር ይታወቃሉ የደሴው አባት አባ መፍቅሬ ሰብዕ።

“መፍቅሬ ሰብዕ” ማለት ሰውን የሚወድድ በሰዎችም ዘንድ የሚወደድ ማለት ነው፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብዕ የሚለው ስም የተሰጣቸው ከተግባራቸው ተነስቶ ነው፡፡ እሳቸው ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ የሚወድዱ ነው ብለው ያምናሉ። በዚህም ምክንያት ሁሉም ሰው ስለሚወዳቸው ስሙን ሕዝቡ አውጥቶላቸዋል፡፡

ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ አባ መፍቀሬ ሰብዕ በጻፉት ጽሁፍ፣ “ለእርሳቸው ዘርና ሃይማኖት ሰውን ለመርዳት መመዘኛዎች አይደሉም። ሰውነት ብቻ ይበቃቸዋል። ይህ ርዳታቸው ከመከራ ያወጣቸው፣ ከችግር የታደጋቸውና ሕይወታቸውን ያቀናላቸው ሰዎች ስለ እኒህ አባት ሲያወሩ ከማያቋርጥ ዕንባ ጋር ነው። አንዳንዶች እንዲያውም ከንግግር ይልቅ እርሳቸውን እያሰቡ ዝም ብለው በማልቀስ ይገልጧቸዋል። መቼም ለአንዳንዱ አብዝቶ አይደል የሚሰጠው። እርሳቸው የአካባቢ ጥበቃ አርበኛም ናቸው" ብለዋል።

ሙዓዘ ጥበባት ስአባ መፍቅሬ ሰለ ብዕ የአካልና የመንፈስ ጥንካሬ ሲገልጹ በአድናቆት ነው፡፡ በእርጅና ዕድሜያቸው እንኳን መቆፈሪያ እና መኮትኮቻ፣ አካፋና ባሬላ ይዘው በደሴ ተራሮች ላይ ዛፍ ሲተክሉ እንደሚውሉ ነው የሚገልጹት፡፡

በማኅበራዊ ኑሮ ላይ ያላቸው ንቁ ተሳትፎ በድፍን የደሴ ከተማ ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ አድርጓቸዋል፡፡ የታመመ መጠየቅ፣ የሞተን መቅበር፣ ሀዘን መድረስ፣ በደስታ ጊዜ መገኘት፣ በበዓላት “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህዝባዊ በዓላት ላይ በማስተባበር እና በማስተማር የሚያደርጓቸው ተሳትፎዎችም መቼም ከሕዝቡ ልብ እንዳይጠፉ አድርጓቸዋል።

ውልደታቸው ሰሜን ሸዋ ልዩ ስሙ ተጉለት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲሆን፣ ከ1945 ዓ.ም ጀምሮ ደሴ ከተማ ኖረዋል፡፡ ደሴን ሙስሊም ክርስቲያን ሳይሉ በተግባራቸው በፍቅር የገዙት አባ፣ “የደሴ ከተማ ህዝብ ከህዝበ ክርስቲያኑ ባልተናነሰ ሙስሊሙ ማኅበረሰብም ለኔ ያለውን ፍቅርና አክብሮት ይገልጽልኛል፤ ያገኙኝ ሁሉ 'አላህ ረዥም እድሜ ያኑርህ' እያሉ ይመርቁኛል” በማለት የደሴ ሕዝብ ለሳቸው ስላለው ፍቅር ተናግረዋል።

#ማቲ_ሸገር

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

16 Oct, 14:00


👇👇👇👇👇

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

11 Oct, 14:09


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ከገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም የገቢ አሰባሳቢ የልማት ኮሚቴ ለ ሁለተኛ ግዜ የተሰጠ መግለጫ

ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እጅግ የተወደዳችሁ የገዳሙ አበው መኖኮሳት ሰባኪያነ ወንጌል ዘማሪያን በወጣትነታችሁ እግዚአብሔርን የምታገለግሉ ወንድሞችና እህቶች እንዲሁም ጥሪያችንን አክብራችሁ የመጣችሁ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች፣ ዩቲበሮች! ቲክቶኮሮች: ዛሬ በዚህ ስፍራ ለተቀደስ ስራ እንድንሰባሰብ የፈቀደልን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን እያልኩ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በባህርዳር ዙሪያ የሚገኘው የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በፃድቁ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል አቅኚነት ገዳሙ ከተመሰረተ ከ አራት መቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠረና ለፃድቁ አቡነ ሐራ ድንግል ከፈጣሪያቸው በተገባላቸው ቃልኪዳን መሰረት ደዌን ሲፈውስና ታምራት ሲሰራ የቆየ እድሜ ጠገብ ጥንታዊና ታሪካዊ የአንድነት ገዳም ነው፡፡

በዚህ እድሜ ጠገብ ገዳም ላይ በአላዊያን መንግስታት ዘመን በደረሰበት መከራና ፈተና ተዳክሞ መቆየቱ ከመላው አገሪቱ ጠበል ለመጠመቅ በፃድቁ የመቃብር አፈር እምነት ከተለያዩ ደዌዎች ለመፈወስ በርካቶች ወደ ገዳሙ ይጎርፋሉ፡፡ በገዳሙም ከ ሰማንያ እስከ መቶ ሃያ እድሜ ያላቸው መኖኮሳትና መነኮሳይያት በተጣበበ ሁኔታ በአስቸጋሪ መንገድ አሁንም ለሀገርና ለወገን ፀሎት ሳያቋርጡ እየፀለዩ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ልጆቻቸው አባቶቻቸው እናቶቻቸው እንዲሁም ወንድም እህቶቻቸው በተለያየ ህመም የሚሰቃዩባቸው ቤተሰቦቻቸውን ይዘው የፃድቁን የፈዋሽነት ገድል በመስማት ከሩቅም ክቅርብም ወደ ገዳሙ ለፀበል ይተምማሉ። ግማሾቹ ፈውስ አግኝተው ወደየመጡበት ሲመለሱ ገሚሶቹ ገፃድቁ ቦታ ላለመራቅ እዝያው ጎጆ እየቀለሱ ቤተሰብ እየመሰረቱ ለረጅም አመታት ስለዘለቁ በዚህ ምክንያት በአካባቢው የሚኖረው ህዝብ እየበዛ የገዳሙ ርስት እየጠበበ መጥቶ አሁን ላለበት መጨናነቅ የደረሰ ሲሆን የገዳሙም መነኮሳት ለፈውስ ከተለያዩ ሀገርም ሆነ ከውጪ ፈውስ ፈልገው ለሚመጡ ምእመናን በቂ ማረፊያ በማጣት ህሙማኑ በየቁጥቋጡ ስር እየተኙ ለመጠመቅ ሲገደዱና ሲሰቃዩ ማየት ስለከበደቻው ዘመናቸውን ሁሉ በጭንቀትና በሃሳብ እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ገዳሙ ሌላ ችግር ተጋርጦበታል። ይህም ችግር በአካባቢው ነዋሪዋች ለቅድስና የማይመች የመጠጥ ቤቶች በመክፈት በቃላት መግለጥ የማይቻል አስነዋሪ ተግባር በየመንደሩ እየፈፀሙ በመሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አስቸጋሪ አድርጎታል። በዚሁ ምክንያት የገዳሙ አበው መነኮሳትና መነኮሳይያት ለክልሉ መንግስት የገዳሙ ቦታ እንዲመለስ ለብዙ አመታት አቤቱታ ሲያቀርቡና ሲማፀኑ አርመው በመጨረሻ መንግስት ገዳሙ ለነዋሪዎቹ ካሳ እንዲከፍል ውሳኔ በማስተላለፉ ገዳሙም ይህን ውሳኔ ተስማምቶ ተቀብሏል፡፡

ምንም እንኳን ገዳሙ አቅም ባይኖረውም ከምንም ይሻላል በሚል የልመማት ኮሚቴ አቋቁሞ ለተነሺዎች ካሳ እና ለመልሶ ማልማት የሚያስፈልገውን ወደ 120 ሚሊየን ብር በውጭም በሀገር ውስጥም ከሚገኙ የፃድቁ ወዳጆች ምእመናን ላይ ለመሰብሰብ ሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ሙከራዎች መካከል ሁለት ጊዜ በቀጥታ ስርጭት ሁለት ግዜ የምሳ ግብዣ በማድረግ ቀጥታ ወደተከፈተው የገዳሙ የልማት ኮሚቴ አካውንት የገባ 12,563, 763 190 ብር ተገኝቷል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የተገኘው ገንዘብ ለካሳና ለመልሶ ማልማት ከሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን አንፃር እዚህ ግባ የሚባል ባለመሆኑ ገዳሙ ሌላ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ለማዘጋጀት ተገዷል፡፡

በመሆኑም የፊታችን ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ "በእንተ አቡነ ሐራ ድንግል" የተሰኘ ታላቅ የበረከት ጉባኤና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል። በዚሁ መርሐ ግብርም ላይ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ሰባኪያነ ወንጌል ዘማሪያን የገዳሙ አባቶች በፃድቁ የተፈወሱ ሰዎች ምስክርነት ለመስጠት ይገኛሉ፡፡

ስለዚህ እርስዎም ከቀኑ ከ6፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ እንዲገኙ እያሳሰብን ለመግቢያ የሚሆን ትኬቶችን መሸጥ ጀምረናል። ትኬቶቹም 3 ዓይነት ሲሆኑ VVIP 1000 ብ፣ Vip 500 ብር እንዲሁም መደበኛ በ 200 ብር እየተሸጠ ነው ።

ትኬቶቹም የሚገኙበት ስፍራ፡-

*በማህበረ ቅዱሳን ሁሉም ሱቆች

*በቦሌ መድሐኒአለም ሰንበት ት.ቤት

*በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች

*ስድስት ኪሎ ማርቆስ በሚገኘው የገዳሙ ሱቅ

*በአባይ ባንክ ቅርንጫፎ

*ጎዮርጊስ አካባቢ በቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል

*በአጋፔ መዝሙር ቤት መርካቶ

*ሜክሲኮ በሚገኘው ልሄም በርገር ቤት

*በዩሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ዩሐንስ መዝሙር ቤት

እና በአዲስ አበባ ወጣቶች በየአድባራቱ በመሸጥ ላይ ይገኛል ስለዚህ እዚህ የበረከት ጉባኤ ላይ በመገኘት የበኩላችሁን ተሳትፎ በማድረግ የገዳሙን ህልውና እንድንታደግ በማለት የልማት ኮሚቴው በፃድቁ አቡነ ሐራ ድንግል ስም ይማፀናል፡፡

ማቲ ሸገር

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

11 Oct, 14:09


👇👇👇👇👇