''ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ሆሳዕና ካምፓስ''ከመንግሥት ዕውቅና በመግኘት በጤናው ዘርፍ ትምህርት ለማስጀመር ያደረገው ቅድመ-ዝግጅት በባለድርሻ አካላት ተጎብኝቷል።
በጉብኝት መርሃግብር የተገኙት የሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ በዓሉ በቴቦ መንግሥት መንግስት የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል በዘርፉ ብቁና የሰለጠነ ባለሙያዎችን ለማፍራት በርካት ስራዎችን እየሰራ እንደምገኝ ገልፀው ከዚህ ጎን ለጎን ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ከዚህ ቀደም በትምህርቱ ዘርፍ የመማር ማስተማር ስራዎችን በውጤታማነት እየሠራ ያለዉ ተቋም እንደሆነ ጠቁመው፣በጤናዉ ዘርፉ ለመሰማራት ያደረገው ጥረት በእጅጉ የሚበረታታ መሆኑን አመላክተዋል።
በጤናው ዘርፍ በቂ ባለሙያዎችን የማብቃት ጉዳይ በመንግሥት ብቻ የሚሸፈን ባለመሆኑ ኮሌጁ ከመንግሥት ዕውቅና ባገኘባቸው ዘርፎች ትምህርት ለማስጀመር እያደረገ ያለው ጥረት አገልግሎትን ለባለሙያዎች በቅርበት ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት ።
የጤናው ዘርፍ ሰው ተኮር እና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ኮሌጁ ተገቢውን ግብዓት ለማደራጀት ያደረገው ዝግጅት የሚበረታታ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ተገቢው የክትትልና የድጋፍ ስራዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አቶ በዓሉ ጠቁመዋል።
''የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዕጩ ዶ/ር ተሰማ አበራ በበኩላቸው ኮሌጁ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከድፕሎማ እስከ ማስተርስ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማበርከት ረገድ የበኩሉን ስወጣ መቆየቱን ገልፀው በአሁኑ ወቅት አድማሱን በማስፋት ከትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን ዕውቅና ባገኘዉ በጤና የትምህርት ዘርፍ ተማሪዎችን ተቀብሎ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል።
እንደ ሀገር የጤናው ዘርፍ የሰዉን ህይወት የመታደግ እና ጤና ለመጠበቅ የሚሰራ ዘርፍ በመሆኑ በዚህ ተሰማርቶ ሥልጠና መስጠት ልዩ ትኩረት የሚሻ፣ በርካታ ሥራና ኃላፊነት የሚሰጥበት ነዉ ያሉት የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ይህንንም ከግምት ዉስጥ በማስገባት ላለፉት ዓመታት ሰፍ ጥናት በማካሄድ የሰው ኃይልን በሟሟላትና ተገቢውን ግብዓት የማደራጀት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
ዘገባው:- የኮሌጁ የህዝብ ግንኙነት ዳይርክቶሬት ነው::
09/03/2016 ዓ/ም