የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔 @brocknhearts Channel on Telegram

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

@brocknhearts


የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔 (Amharic)

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔 አባንዳዴ መረጃዎችን የሚሠሩ በአምላክ መሃለ የግል ጥያቄዎችን የሚሰማባቸውን አስተያየታቸውን ማግኘት ይችላል። አምላክ ያለብን ማፈናዎች ለባለቤቱና ለባለቤቱዎች እንኳን ያበረታሉ። ከዚህ በኋላ ውይይቶ በዚህ ላይ ያለውን መልከስ ማፍረድ ይችላሉ። ዓይኖቹን ለማንኛውንም ወይም ማስፋፋት እንችላለን። ሌቦቹን እና በእናምናለን።

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

04 Dec, 17:37


አንዳንድ ሰዎች እንባቸውን ስታብስላቸው እነሱ ደግሞ በተቃራኒው ደስታህን ያብሱታል https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

02 Dec, 20:49


የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔 pinned «ገላሽ ክቡር ነው ገላሽ ያንቺ ነው.. ያለፍቃድሽ ማንም ሊዘልበት አይችልም ከትዳር አጋርሽ ውጭ መሆን የለበትም ገላህ ኩቡር ነው ገላህ ያንተ ነው... ያለፍቃድህ ማንም ሊያዘልለው አይችልም ከትዳር አጋርህ ውጭ መሆን የለበትም https://t.me/BrocknHearts»

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

02 Dec, 20:22


ገላሽ ክቡር ነው ገላሽ ያንቺ ነው.. ያለፍቃድሽ ማንም ሊዘልበት አይችልም ከትዳር አጋርሽ ውጭ መሆን የለበትም

ገላህ ኩቡር ነው ገላህ ያንተ ነው...
ያለፍቃድህ ማንም ሊያዘልለው አይችልም
ከትዳር አጋርህ ውጭ መሆን የለበትም https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

30 Nov, 17:34


የሀራም ግንኙነት
አሁን አሁን የስልጣኔ ጥግ ተደርጎ የሚወሰደው የወንድ እና የሴት ግንኙነት ሁኖ በአደባባይ ሲሰበክ እና ትውልዱ ሲከስም እየተመለከትን ነው ስንት እህቶቻችን በሀራም ግንኙነት ውስጥ ህይወታቸው ወደ ሲኦል ተቀይሯል ምስቅልቅሉ ወጧል? በሀራም ግንኙነት ስንት እህቶቻችን ህይወታቸው ወደ ሀዘን እና ስቃይ ተቀይሯል ክብራቸውን አጥተዋል ከአላህ ጋር እና ከወላጆቻቸው ጋር ተጣልተዋል ንፁሃን እና ፈሪሃ እህቶች በትንሽ አጋጣሚ መግባባት ቅፅበት በህይወታቸው የሚፀፅታቸውን ነገር ለማድረግ ተገደዋል ኸይር ነገር ሁሉ ለመስራት እስኪያቅታቸው ድረስ በአታላይ ወንዶች ጣፋጭ ቃላት ተመርዘው ሂወታቸው ምስቅልቅሉ ሲወጣ እየተመለከትን እንገኛለን
وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاء سَبِيلًا ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና መንገድነቱም ከፋ! (17:32)
ውድ እህቴ ሆይ ሀያእ መኖርሽ የአንቺ መጠበቂያ ምልክት ነው ቢክራነትሽ የሂወትሽ የመታመን አንዱ መንገድ ነው አንቺን የሚፈልግሽ ወንድ ከሆነ አልጋ ቤት ሳይሆን የሚቀጥርሽ ቤትሽን በክብር ያንኳኳል እንጅ አላስፈላጊ ወሬዎችን እና ወደ አላስፈላጊ ግንኙነቶች አይመራሽም
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

28 Nov, 14:27


https://t.me/BrocknHearts
ለወዳጆቻቹ የዚን ቻላል ሌንክ ሸር አድርጉ

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

26 Nov, 19:55


ንደት ውስጥ ሁነህ ልጆችህን አትማታ/ቺ እንቅልፍ ሲወስዳቸው ፀፀት እንዳይዝህ ጤነኛ ልጆች ባይሆኑ ኖሮ ቤትህ/ሺ በጫጫታቸው ባልደመቀ ነበር ስለዚህ አመስጋኝና ታጋሽ ሁን/ኚ https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

24 Nov, 12:20


#ሴት ስትሆኚ ሰውነትሽ አዞሽ ውስጥሽ ተቀብሎት ሌላ አንድ ነገር የምነግርሽ ፍቅር ያለ ወሲብ አለ ያሰብሽውን ሰው ማፍቀር የለብሽም ሙዱ ከተመቸሽ አልያም ትከሻው ወንዳወንድነቱ ከተመቸሽ ለትዳር መጠየቅ በቂ ነው
ከዛ በተረፈ ሩም አብረሽው መግባትሽ consent የሴትነት በረከትሽን ነው የምታጪው አንተም ብትሆን አትጎፍጥጥ የስሜት ባሪያ አትሁን መቼም ቢሆን አስገድደህ! እንዳታረግ ከዝና ተሰተር ጹም
Lastly እባካቹ ከትዳር በፊት ፖስት ፒል መቃም እና በትዳር አጋር ላይ መማገጥም እርድና አይደለም ወደዳችሁም ጠላችሁም HIV Ethiopia ውስጥ በወረርሺን ደረጃ እየተስፋፋ ነው እጂግ ማመን ከሚከብድ በላይ ብዙ ስው በHIV ተይዙዋል ከዚሁም ውስጥ የ highschool ተማሪዎች ከፍተኛ ድርሻን ተቆጣጥረዋል ከ15 ደቂቃ ለማይዘል ደስታ ብላችሁ ቀሪ ዘመናችሁን አታበላሹ
በህይወታችው ቁማር አትጫወቱ ከጊዜያት በኋላ የሚመጣው ቁጭት መራር ነውና እንደው በፈጠራችሁ እራሳችሁን ከትዳር በፊት ከወሲብ/ዝና ጠብቁ.. naturally የሰው ልጅ አይምሮውንም ይሁን ማንኛውም ስሜቱን.. control ማድረግን ይችላል እሄ ደሞ ፈጣሪ ሲፈጥረን የሰጠን ልዩ ጥበብ ነው..👐🏿
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

23 Nov, 15:49


💔ጥበቃም ህመም ነው በልኩ ካልሆነ💔
ምን ያደርጋል ተስፋ እድሜን ከበተነ
ይኸው.....
እኔ አንቺን ስጠብቅ ካስቀመጥሽኝ ስፍራ
ሜዳ መሆን ሻተ ተናደ ተራራ
እኔ አንቺን ስጠብቅ እንደ ሎተሪ ዕጣ
ዳዴ ባዩ ህፃን አትሌት ሆኖ መጣ

እና እንደነገርኩሽ ጠብቄሽ
ነበረ ተስፋዬን አፅንቼ
እቅፍ ሙሉ አበባ ጨብጠው እጆቼ…
አንቺ በምትወጃት
በጨረቃ እንዳይሽ ከቤቴ ወጥቼ
ጠብቄሽ ነበረ ማንነቴን ክጄ
ላንች ስል መፅውቼ
ታቻምና ለአምና ስትቀጥሪኝ ቆይተሽ
ዘንድሮም አለፈ አንቺ ግን አልታየሽ
ጥሩ ሙያተኛ እንደ ፈተለችው
እንደ ጥጥ ባዘቶ
አምላክ እንደሠራው
የደመና ርብራብ ነጥቶ
እንደ በረዶ ጥቁሩ ፀጉሬ እንኳ
ከከዳኝ ቆይቷል ማንነቱን ትቶ

ዜግነት ቀይሯል
ተመልከችው ገፄን ተመልከችው ፊቴን…
በዘመን ጥበቃ ጭርምትምት ማለቴን
ልጅነቴ አብቅቶ ማርጀት መጃጃቴን

ላንቺ ለማበርከት ያቀፍኩት አበባ ደርቆ እየረገፈ…
እንጨቱ ቀረና ቆዳዬን ሸልቶ ደሜን አጎረፈ
እንደውም ይግረምሽ....
እንኳን እኔ ቀርቶ ጨረቃም ከፍቷታል
ለማይነጋ ነገ ማለም ሰልችቷታል
ነይና ተመልከቻት ዝላ መዳከሟን
ከሰማይ መንበር ቁልቁል
ተወርውራ እንክትክት ማለቷን
እኮ ነይ ጠይቂያት የጥበቃን መዘዝ
በተስፋ መሰነቅ እድሜ እየሞተ ለቀብር ሲገነዝ

ህመሙን ታዋይሽ ግልፁን ታወራለች
ግን ተይዟል ልሳኗ ጥበቃ ቢፀና ወድቃ ተሰብራለች

እኔ ግን ተነሳሁ ጉዞ ልጀምር ነው
መድረሻዬን እንጃ ርቄ መጓዜ ነው
ትዝታ አልባ ስፍራ ተስፋ የለሽ ምድር
ባገኝ እንደው ብዬ በውስጧ ልቀበር
አዎን መሄዴ ነው መድረሻ አልባ ወሰን
በደካማ ጎኔ አንቺን እያለምኩኝ ስቃዬን አልተምን

ምናልባት አንድ ቀን… ትዝ ካልኩሽ ድንገት
ካስቀመጥሽኝ ስፍራ ፍለጋ አትሂጂ
እዛ ህይወት ጠፍቷል ነገን የሚናፍቅ
እዛ ዕድሜ አልፏል ፍቅርን በመጠበቅ

ፍቅርሽ ወዴት አለ ብለው ቢጠይቁሽ!
ጠብቆኝ ነበረ ምሎዕ ተስፋ ይዞ
ናፍቆት ተሸክሞ በፍቅር ተማርኮ
ሆኖም ብቀርበት መንገዱን ጀመረ
ተስፋ ባጣ ተስፋ መኖርን ታከተ
ከኔ ተለይቶ ላይመለስ ሄደ
ብለሽ ንገሪያቸው
በአንቺ መታከቴን ፍፁም አብስሪያቸው!
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

21 Nov, 06:48


💔 ብቻህን ትቶህ የማያውቅ
ማን እንደሆነ ታውቃለህ…?
#አላህ ነው
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

20 Nov, 14:41


/#ይቅርታ #በሉልኝ 💔
ሲወደኝ ስኮራ ሲቀርበኝ ስርቀው
ክብር እየሰጠኝ ደርሼ ስንቀው
ሳጠፋ ታግሶ ሳኮርፍም አባብሎ
እኔን አስቀድሞ እንዳልሽ ይሁን ብሎ

ሁኖልኝ ሳለ አልጋ
ስሆንበት ቀጋ
ደከመው መሰለኝ ብዙ መታገሱ
ታከተው መሰለኝ ጥፍቴን ማበሱ
የለም ጠፍቶብኛል ካየሁት ሰንብቷል
ስልኩንም ሞከርኩኝ አይሰራም ተዘግቷል እንጃ ውስጤ ሰግቷል
ምናልባት እናንተ ድንገት ካያቹህት
አደራ አደራ ይህንን ንገሩት

"እያለህ ያልታያት የሰጠሀት መውደድ
ስትሄድ ገብቶታል ስትጀምር መንገድ!
አልራቅክ እንደሆነ ልብህ ካልቆረጠ
ተመለስ ልካስህ_ካንተ በበለጠ
ብላለች በሉልኝ ካያቹህት ድንገት
አደራ ንገሩት ካሁኑ አቅቶኛል
ያለሱ መኖሩ ዳገት ሆኖብኛል!

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

20 Nov, 14:35


አንድ አንድ ወዳጅነት ጊዜያዊ ሰዎችን እንድንለይ እድሉን ይሰጠናል
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

15 Nov, 15:44


ከማይበጅህ ሰውጋ ከመሆን ይልቅ ከማንምጋ አለመሆን ይሻላል
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

12 Nov, 10:34


💔 አንዳንዴ ከሞኝነትህና
ከየዋህነትህ ነቃ እንድትል
የሚደርስብህ መሠበርና ህመም
ያስፈልጋል ።

      
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

10 Nov, 13:22


ስደውል አታንሽው

ስደውል አታንሽው ዝጊው እንደ ወትሮሽ
ቴክስቱንም ተይው አይተሽ እንዳላየሽ

ላግኝሽም ስልሽ አታግኝኝ ይቅር
ለረፈደ ፍቅር ዳግም ለሚሰብር
ይሁን በግድ ብዬ እኔ አልሰኝም ቅር

ዛሬም የደወልኩት አይደለም ልወቅስሽ
ግን ውዴ በሞቴ አንዴ ላስቸግርሽ
"እወድሃለው" ብቻ በይኝ ናፍቆኛል ውሸትሽ
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

08 Nov, 14:07


አንድ አንዴ ይቅርታ የነበረውን ነገር አይመልስም ንፁህ ልቦች ከቅጣትና ከበቀል ይልቅ ይቅርታን ያስቀድማሉ ለይቅርታ ልባቸው ቅርብ ስለሆነ ሁሌም ለሰው ይራራሉ ጥፋት ሲደጋገምባቸው ግን ስህተት መሆኑ ቀርቶ ውሳኔ ይሆናልና ያኔ ጥፋትህን ብቻ ሳይሆን አንተንም በመርሳት ነው ይቅር የሚሉህ አንድ አንዴ ይቅርታ የነበረውን ነገር አይመልስምና …… መጀመሪያ እንጠንቀቅ https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

30 Oct, 21:54


እሷ ትዳርን ትሻለች ከዛም አልፎ አግብታ ጓጆ መስርታ የሞቀ ህይወትን ታልማለች። 
አንተ ግን ፍቅር ትላለህ ወዳ ይመስልሀል እንዴ ብቸኝነትን ጌጧ አድርጋ የተቀመጠችው?
ልንገርህ ሁሉንም ብዬ ባልደመድምልህም ብዙ ሴትኮ ''አጓጉል ጥንድነትን ሽሽት'' እንጂ ''ከራሷ ጋር እንድትቆም ያደረጋት
#ከፍቅር_ጋር_ቂመኛና ደመኛ ሆና አይደለም ከትዳር በፊት ግኑኝነት ሀይማኖቷ ስለ ከለከላት እንጂ..!ወዳ ይመስልሀል እንዴ!?

እድሜዋ እየጨመረ ጊዜዋ እየበረረ ልቧ እየተሸበረ ብቸኛ የሆነችው
#ታማኝ_ወንድ በማጣት ነው የውስጥ ስሜቷን እና ፍላጎቷን ሳታደምጥ ለውሳኔ አትቸኩል!

ደግሞ በብዙ እህቶች የልብ ስብራት ግንባር ቀደም ተጠያቂወች እኛው ወንዶች ነን ..ከትዳር በፊት ለኛም አስፈላጊ እንዳልሆኑ እያወቅን ስሰበሩን ስያገቡ የኛን ጥፋት ወደእነርሱ እያጣበቅን ስህተታችንን ለማድበስበስ አንሞክር::
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

29 Oct, 13:27


ተገኘልህ ማለት ርካሽ ነው ማለት አይደለም!

ትገኛለህ ማለት ርካሽ ነህ ማለት ሳይሆን የተሻልክ ነህ ማለት ነው ለሰዎች ለመገኘት ቅንነት ራስ ወዳድ አለመሆን እና መልካምነት ነውና ሰዎች በቀላሉ ካገኘነው ነገር ይልቅ ዋጋ የሚያስከፍለንን ነገር ስንወድ እንገኛለን እንዲሁ ለሚገኙልን ነገሮች ቦታ አንሰጥም ማወቅ ያለብን በህይወታችን የተገኙልን ሰዎች ርካሽ ስለሆኑ ሳይሆን መልካም ስለሆኑ ነውበምንፈልገው ግዜ ከሚገልኝልን ወዳጅ ይልቅ አዲስ ላወቅነው ሰው ትልቅ ግምት ስንሰጥ እንገኛለን

ፈጣሪ የሚባርከን በሰዎች ጭምር ነው ሰዎች ተሰተውሃል ማለት ከፈጣሪ ጋር ያላችሁ ግኑኝነት የበለጠ ጠንክሮዋል ማለት ነው! ስለዚህ ወደ ህይወታችን የሚመጡትን ሰዎችን መረዳት ብልህነት ነው ሰዎች ሲርቁን ወይም በስጋ ሲያልፉ ማድነቅ እንወዳለን አጠገችን ሳሉ በህይወታችን ያላቸውን ቦታ መንገር አንወድም :/

አጠገባችን ያሉትን ሰዎች ከእኛ ጋር ስለተገኙ ብቻ መሄጃ የሌላቸው ምንም ማድረግ የማይችሉ አድርገን መመልከት እንጀምራለን ይህ ደሞ ጤናማነት አይደለም ሰዎች ሲወዱን ሌላ ምርጫ እንደሌላቸው ማሰብ ፍቅር ሲሰጡን እንደ ሞኝ ማሰብ🫤ዋጋ ሲከፍሉልን ቦታ አለመስጠት እጅግ የሚያሳዝን ሞኝነት ነው ሰው ለእኛ ከሆነ እንዴት ነው ለራሱ መሆን የማይችለው? ምን አልባት የሚጠበቅበት ፊቱን ዞር ማድረግ ብቻ ሊሆን ይችላል
ሰዎች ሲገኙልህ አመስግናቸው ዋጋቸውን ንገራቸው የተጠቀማችሁን ጥቅም ንገሩአቸው ሰዎች ሲገኙላችሁ አመስግኗቸው ለመልካምነታቸው እውቅናን ስጡ
የወደዱን ሰዎች የሰጡንን ፍቅር ከማቃለል እንቆጠብ ፍቅራቸውን እንደ ሞኝነት አንመልከት!

በምድር ላይ ከሰዎች በላይ በረከት በህብረት በላይ ከፍታ የለም::

በህይወታችን ላሉ ሰዎች እውቅና እንስጥ!
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

29 Oct, 07:49


ፈጣሪ..

መጀመሪያውን ሳይሆን መጨረሻውን ያሳምርላችሁ

have a nice day🖤

https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

28 Oct, 15:05


👉መልካም ጓደኞች
👉ድክመትህን ፊትለፊትህ ይነግሩሃል
👉ጥንካሬህን ከበስከ ጀርባህ ያወሱልሃል
👉መጥፎ ጓደኞች ደግሞ መልካምነትህን
ፊትለፊትክ ሲነግሩህ 👉ድክመትህን ከ ጀርባህ ያወራሉ. https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

26 Oct, 15:45


ስንቱን የፍቅር ቃል ያዘነበ አንደበት
ዛሬ ጠላውህ ቢል ድሮስ ምን ሊያምርበት!
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

15 Oct, 09:28


እናልፋቸዋለን

ከትናንትም ከዛሬም የበለጡ ችግሮች ይመጣሉ። ካለፍናቸው የገዘፉ ውጣውረዶች ይጠብቁናል ከጠበቅነው የተለየ አስፈሪ ጭጋጎት ያጋጥመናል ያሰብነው ቀርቶ ያላሰብነው ይከሰታል ግን እንዴትም ይሁን እንዴት እናልፋቸዋለን እናም እንስቃለን
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

11 Oct, 03:43


ከራሴ አንድ በጣም የምወድው
ባህሪ አለኝ ሰው ቶሎ አልወድም
ከወደድኩም በኔ ስህተት እንዳላጣው የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለው #ነገር_ግን_የእኔን_ዋጋ_ለአንዴ_ከዘነጋ #ላይመለስ_ከህይወቴ_አስወጣዋለው
https://t.me/BrocknHearts
💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

07 Oct, 20:27


"እኔን" የማላምንበት ቀን አለ። ፍርሃቴ ህልሜን ሊነጥቀኝ የሚታገልበት።  ያ ሁሉ የሃስብ ጋራ እንደበጋ ቅጠል ረግፎ እግሬ ስር የሚከመርበት ።

ምናቤ ከሚከተለዉ ህልም በላይ እዉነታዉ ዉስብስብ ነው። "መሆንን" ከማሰብ በላይ .....ማረጉ የስቃይ ስልቻን ይሞላል።

እንደዚህ አይነት ቀናት መቻላችንን ከቢጤዎቻችን አፍ መስማት የምንሻበት ነው። መቆም መቻላችንን በቃላት እስክንሰማዉ የምንጠራጠርበት። ከከበበን የሳቅ ፣ የአብሮነት ግለት ዉስጥ የአንዱን እስትንፋስ የምንሻበት ፤ የፍርሃት እፉዬ ገላችንን እፍ ቢልልን ብለን። 

ምን አልባት ዛሬ ያ ቀን ይሆናል።
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

06 Oct, 15:43


እኔ የኖርኩበት ህይወት
ጨለማና ጭንቀት የበዛበት 🕊
ብዙዎች እያዩኝ የሚራገሙበት
ትላንት የኖርኩት ህይወት
ያስመኘኝ ነበረ ባጭሩ መሞት
እኔ ግን..
እድፌን አጥቦ የሚያነፃኝን
ወንጀሌን ወስዶ ቀና የሚያደርገኝን
የምድነበትን ቀን የምጠባበቅ
ዛሬ ይሁን ነገ ተስፋን ምሰልቅ
ማንም የለሌለኝ ብቸኛም ነበርኩ
ከወገን ከዘመድ አዝማድ የተገለልኩ
«ህይወት አልገባኝም»
አንድ ላይ ከዋሉ ዝምታ እና ሀሜት
ጥምረት ከፈጠሩ እውነት እና ስሜት
እቅድ ከኑሮ ጋር ካልተገጣጠሙ🤗
በኔ ይሁን ትግል ሁሉም ከተጠሙ
ኑሮዬ እቅዴ ላይ
ቂም እየቋጠረ በቀስቱ ከወጋው
ደስታ ከየት ይምጣ
በየትኛው ሚዛን ስኬቴን ልለካው
ትርፍ የለው ኪሳራ
መሀል ሰፋሪ አለም እስር አይሉት ነጃ
ተደናግሬያለሁ
አገኘሁ ስላላልኩ ያጣሁትን እንጃ
አጣሁም አገኘሁ ትርጉም የሚኖረው
ወደ ነገ ተስፋ የማሸጋግረው🕊
ዛሬ የሚወጠን ተስፋ ሲኖረኝ ነው
እኔ ግን...!?
Plan to be human ተደነጋግሮኛል
በንፁህ አዕምሮ ሰው መሆን አምሮኛል
ነገዬ ላይ ክፉ ክስተት ባልመኝም
በአሁኑ ወጥኔ ህይወት አልገባኝም

https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

05 Oct, 19:48


ደስ አለንም ተሰቃየንም

ምስጋና እናብዛ ከሱ በቀር ሁሉም ከሃዲ ነውና

አልሃምዱሊላህ


Sweat dreams fellows💙

https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

04 Oct, 19:26


መናገር ፈልገህ ቃል ማውጣት ይከብዳል?😪

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

02 Oct, 11:42


ይቅርታ ማለት ጊዜው እና ሁኔታው ተመልሶ ቢመጣ እንኳ ያንን ተግባር አልፈጽመውም ማለት ነው። (ለሁለተኛ ጊዜ ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ!)

ከዚህ የበለጠ ትርጉም ሊኖረው ይችላል ልያንስ ግን በጭራሽ አይችልም!
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

30 Sep, 11:12


መቆየትን ለፈለገ ልብህን አስፋለት ..
መሄድ ለፈለገው ደግሞ መንገዱን አስፋልት .. https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

28 Sep, 22:05


ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይ ወፎችም መሳፈሪያ አላቸው። ለሰው ልጅ ግን...

ከፈጣሪው ውጪ ራሱን የሚያስጠጋበት ምንም የለውም!!💙

https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

25 Sep, 21:40


ታማኝነት በእኔ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር የሚያይ ሰው አያስፈልገኝም።

በእኔ ውስጥ ያለውን መጥፎ ነገር የሚያይ፣ አሁንም የሚፈልገኝ እና የተሻለ የሚያደርገኝ ሰው እፈልጋለሁ❤️

😍መልካም ምሽት
https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

20 Sep, 15:29


ሙሉ በሙሉ በተሰበሩበት ቅጽበት ፈገግ ማለት ከቻሉ; )

እንግዲህ አስታውስ በዚህ አለም ላይ አንተን የሚሰብር ምንም ነገር እንደሌለ 🖤

https://t.me/BrocknHearts

የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

17 Sep, 14:25


የአንዳንድ ግንኙነት መድሃኒቶች መፍረሳቸው ነው።

ያ መፍረስ ሊጎዳን ይችላል ፀፀት እና ህመም ሊያሰማን ይችላል..ትዕግስታችንንም ብሎም የህይወት ዘመናችንን ያቃጥለዋል

ግን መዳንህ የምጀምረው ህመምህን በሰዎችን ከማሰበብ ይልቅ..ያን ህመምህን እንደ እራስህ ወደሀው ስትቀበለው ነው..

https://t.me/BrocknHearts

2,834

subscribers

1,461

photos

7

videos