እመብርሃን @gebrehana21 Channel on Telegram

እመብርሃን

@gebrehana21


መንፈሳዊ - ምስሎች
-ጹሑፎች
-ግጥሞች
-ልብ-ወለዶች
-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች
እና ሌሎችም





ላሎት አስተያየት
@ene_ehonen

እመብርሃን (Amharic)

እመብርሃን የመንፈሳዊ ምስሎች, ጹሑፎች, ግጥሞች, ልብ-ወለዶች, መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች እና ሌሎችም በአሰተያየት በመመዝገብ ባለፈው የዲሲ፣ ሳይቲ፣ እና ፔርሲኮ፣ በየአለም ከከንፈሮቹ ጋር በአካባቢዎች ብቻ ቆሞ እንዲደርስላችሁ እመብርሃን እንዲያደርጉ ለመረጃዎች መንፈሳዊ የግንኙነት ማስተዳደሪ ስንትና ለጠቀሙት በመጠቀም በሚያሳየና በሚታይ የአፕስፖርትምልክ አገልግሎት ላይ ስለ ተለያዩ መረጃዎች እና ተጠቃሚዎች እንድትመላለሱ ማስተዳደሪ በሆነ ነው። በአብንቴክ እና ላቀረበለት ቃላቲክ በሚመጣው ስለምታመለከተው የዲሲ፣ ሳይቲ፣ እና ፔርሲኮዎች እንዲወክሉ ስሞችን እመብርሀን አብንቴክ እና ቃላቲክ በሚመጣው ላይ መጠን እና የምደግፈው ቃላቲካችን በሚያስተምሩ ጊዜዎች በማያደርግ አካባቢውን በዘልቀው ማስተዳደሪችን ከእኛ እና ቅርብ የሼር ምልክ ቀርበዎን ለመከታተል ይህን መገኛ እና ስለ ለላሊት እንቋዕ በመሆኑ ማስተማር በማድረግ እናት እመብርሃንን ከብትሎ መዝገብ ለማየት እንችላለን።

እመብርሃን

17 Jan, 08:30


ለካ.... እግዚአብሔር መኖሩ ያጽናናል፤
ጌታችን ከጎናችን መሆኑ ይጠግናል፤
ፈጣሪን መምረጡ ከሁሉ ይበልጣል።
:
ሰው ምን ቢጓዝ ቢኳትን ለብቻው
ባለው ጥሪት፣ክብር ሁሉን የገዛ ቢመስለው
ጌታ ከሌለበት... ፈጣሪ ከሌለው
ሁሉ መና
የማይጥም ኦና
:


ለእኛስ ለክርስቲያኖች ምርጫችን እግዚአብሔር
ብቸኛው አማራጭ መይገባ ከድርድር
እርሱን ሳንይዝ ማንጓዝ አንድ እርምጃ
የኑሯችን መሪ እርሱ ብቻ

Σίρακ

እመብርሃን

07 Jan, 06:56


ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
¹² ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
¹³ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦
¹⁴ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።

እንኳን አደረሳችሁ❤️❤️

እመብርሃን

25 Dec, 06:20


ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

እመብርሃን

21 Dec, 05:10


የዕለቱ ስንቅ

“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥6

እመብርሃን

18 Dec, 11:16


መወያያ ግሩፓችንን ተቀላቀሉ ቤተሰብ👇👇👇

https://t.me/+2eZWoUCA-IlmNmJk

እመብርሃን

07 Dec, 04:47


ከእራሳችን በላይ አሳቢ ለስጋ ለነብስ፤
እየሱስ ክርስቶስ መጋቢና የፅድቅ ልብስ።
መጨነቅ ፣መተከዝ፣ መፍራት አሁን መች አለ፤
ከእስትንፍስ በላይ የቀረበ ጌታችን እያለ።

Σίρακ

እመብርሃን

06 Dec, 05:55


“እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7

እመብርሃን

30 Nov, 08:11


ህዳር ጽዮን ❤️

እመብርሃን

10 Nov, 06:12


ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ

እመብርሃን

06 Nov, 08:18


" የፍቁር ጌታ ሕማማት በተነገር ጊዜ ልብ ይለያል፤ ኅሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እመብርሃን

04 Nov, 08:20


"እኔ እለምናለሁ አቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል። የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል። እኔ ቁስለኛ ነኝ አቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ። ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡"
አርጋኖ፣ ዘሐሙስ

እመብርሃን

01 Nov, 05:46


የዕለቱ ስንቅ

ይህን ያህል ቀን ጾምኩ አትበሉኝ፡፡

ይህን አልበላሁም ወይም

ያንን አልበላሁም፣ የወይን ጠጅ አልጠጣሁም አትበሉኝ።

ይልቁንስ ከግልፍተኝነት ወደ ገርነት፣

ከጭካኔ ወደ ደግነት የተሸጋገርኽ እንደሆነ አሳየኝ፡፡

በአንተ ውስጥ ጥላቻና ቂም ቢኖሩ፣

በወይን ፋንታ ውኃ ብትጠጣ ምን ይጠቅማል? ጾም ብቻውን ስማያዊ ምንዳ አያስገኝምና፤

ትርጉም በሌለው በባዶ የፆም ሥርአት ራስህን አታስገዛ።"

        ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


ሠናይ ዕለተ ዐርብ

እመብርሃን

31 Oct, 03:45


የዕለቱ ስንቅ

“ደጋግመህ ኃጢአት ብትሠራም

ደጋግመህ ንስሐ ግባ፡፡

ቤተ ክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡

   ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሠናይ ዕለተ ኀሙስ

እመብርሃን

30 Oct, 05:30


የዕለቱ ስንቅ

"በጾም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን በሌላ ጊዜ ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡
እነርሱም፡-
 ✞ ክፉ ከመናገር መከልከልን

✞ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
 ✞ እንደልምድ አደርጋችሁ ከያዛቸሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ፡፡

"
            ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሠናይ ዕለተ ረቡዕ

እመብርሃን

13 Oct, 04:37


መልካም ዕለተ ሰንበት❤️

እመብርሃን

09 Oct, 19:34


#repost

እመብርሃን

09 Oct, 19:33


ውበትም ሀሰት ነው ደምግባትም ከንቱ፤
እያለች ታመነች አርሴማ ጀግኒቱ።

የአምላክ መሆን ይሻል ለሰው ከመታዘዝ፤
ቀን ብርሃን ሆኖ ማታ ከሚደበዝዝ።

መንግስት ቢሰጣት፤
ሀብት ቢያመጡላት፤
በቃለት ቢሸነግሏት፤
ከክርስቶስ ፍቅር፤
ከቶ አልበልጥ አላት፤


ቢወርድባት የመከራ ናዳ፤
ቢያሰቃዩአትም ሳይኖርባት እዳ፤
ፀናች ባለችበት፤
አጸናት ያመነችበት።


ሰማእት ሆና አክሊል የተቀዳጀች፤
የአምላኳን ልእልና የገለጠች፤
አርሴማ እኮ በእውነት ልዩ ነች፤



በእርሱ ስላመነች እስከ መጨረሻ ፤
በቀኙ ሆኗል የእርሷ መዳረሻ ።

አርሴማ❤️


C-raክ

እመብርሃን

09 Oct, 10:20


(የተሰዋ - ይዌድስዋ)

ኤልያስ ሽታኹን

-    -        -       -      -      -

ሰውነቱ  ወልቋል።

ተንበረከከ አጥንቱ ከወለሉ ሲጋጭ ይሰማል።

የሚናገረው ነገር ጠፋበት።

ልጅነቱ ትዝ አለው። በጣም ጎበዝ ተናጋሪ ነበር። ዛሬ አፉን የፈታበት ቋንቋው ጠፋው።

ፀጉሩን እየጠቀለለ
"ብሬን ስጨርስ መጣሁ"  አላት

ዝም አለችው።

"ደስታዬን ስጨርስ መጣሁ" አላት

ዝም።


"መልኬ ሲረገፍ መጣሁ
ጉልበቴን ስጨርስ መጣሁ
ጤናዬን ስጨርስ መጣሁ"
ብሎ  ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ!

ዝም አለችው።

ከውስጡ አንድ ድምጽ ሰማ

"እድሜህን ሳትጨርስ መምጣትህ ነው ደስታዬ" አለችው።

ጭራሽ ከፋው።

ዝም ብላ አየችው።

ዝም ብሎ አያት።

ሳቀ።

የልጅነቱ የአብነት ተማሪ እያለ የነበረው ስም ትዝ አለው። "ቄሴ"

እየሳቀ አለቀሰ።

የማይቆረጠው ፀጉሩ ትከሻውን ነክቶታል።

በፊት ተዓምረ ማርያም ሲነበብ ነበር ጃንጥላ የሚይዝበት እጁ አሁን
በሲጋራ የሚይዝበት  ጠቁሯል።

ሱሪውን ዝቅ አርጎት ሊወልቅ ደርሷል።

ለሎቲ የተበሳው ጆሮው ተደፍኗል።


ቅዱስ ዳዊት ከጠላቶቼ የተነሳ አረጀሁ እንዳለ
ገና በወጣትነቱ አርጅቷል።

ፊቱ ላይ አጥንት አለ።
ራሱን አየው።
አፈረበት በራሱ።

ጥግ ላይ የተቀመጡት ሽማግሌ ጋ አይኑ ተጋጨ። በግንባራቸው ጠሩት።...


"ጉዴ ነው" አለ በውስጡ።

"አቤት አባቴ...  እንኳን መጣህላት"

"ለማን"

"ለማርያም"

"ሰምተውኝ ነበር ማለት ነው አለ" ለራሱ

"ምን ዋጋ አለው ብለው ነው...አሁንማ ከረፈደ"

"እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ፍቅሩ ለምን እንደማይቀንስ ታውቃለህ ?"

ዝም አላቸው።

"በፀጋ ስለሚያየን።
በዛሬ ማንነታችን ሳይሆን በፈጠረን ፀጋ ነው የሚያየን።  በልጀነት ንጽህናችን በበፊቱ ቀናነታችን በትንንሹ አግልግሎታችን ነው የሚያየው። አይኑ እስከዛሬ ከፀጋችን ተነስቶ አያውቅም።"

ልቡንም ጆሮውንም ሰጣቸው።

"በኛ ተስፋ የማይቆርጠው የልጅነት ፀጋችንን ስለሚያውቅ ነው። ሌብነትህን ሳይሆን ልጅ ሆነህ የዘመርከውን ዘማዊነትህን ሳይሆን ድሮ ፀበል የቀዳኸውን ገዳይነትህን ሳይሆን ቤተመቅደስ  መጥረግህን ነው የሚያየው። እግዚአብሔር ሰውን የሚያየው በፀጋው ነው።"

"እኔ ምን አለኝና ታዲያ ?"

ካንተ በላይ ያውቅሀል።
በፀጋህ ነው የሚያይህ ባሁኑ ኃጢያትህ አይደለም። እናት ልጇ ቢታሰር አትክደውም ልጅነቱን አስታውሳ ታዝናለች። ድሮኮ ተምሮ እንደዚህ ይሆንልኛል ብዬ ነበር የማስበው ብላ ልጅነቱን ነው የምታስታውስለት። አየህ እግዚአብሔር ልጅነታችን ጋ ነው አይኑም ልቡም።

ዕንባው ወረደ።


"ልጠይቅህ" አሉት

"ገብርኤል ማርያምን ከሰላምታ  በፊት ምንድነው ያላት"

ይዌድስዋ ትዝ አለው።
"ፀጋን የሞላብሽ ሰላምታ ይገባሻል"

"ጎበዝ
ማርያምም ፀጋን የሞላባት መንፈስ ቅዱስ ያደረባት ናት። ሁሉንም የምታየው በፀጋ ነው። እንኳን አንተን ለሚቃወሟት ሳይቀር ሩህሩህ ናት። ለምን በልጅነት ፀጋቸው ነው የምታውቃቸው። ክፋት አታውቅም ቂም አታውቅም ለምን ፀጋን የሞላባት ናት።"

ጉልበታቸው ስር ወደቀ።
እጣን እጣን ሸተተው።

(ተፈጸመ)

እመብርሃን

07 Oct, 11:11


የሰዎችን ኃጢአት ለማየት ሰርስሮ የሚገባው አእምሯችን የራሱን ስህተት ለመረዳት ግን እጅግ የዘገየ ነው።
- ቅዱስ ባስልዮስ

እመብርሃን

06 Oct, 10:54


እንኳን አደረሳችሁ።❤️❤️❤️

እመብርሃን

27 Sep, 13:37


"ስለመስቀል መመስከር የእርሱ ጥፋት እንደሆነ ያውቃልና፣ ማንም ቢሆን መስቀልን ሲክድ የዚህ ዓለም ገዢ ደስታን ያደርጋል። መስቀል በዲያብሎስ ኃይል ላይ የተነሳ የድል ምልክት[ዋንጫ] ነው። ስለእርሱ በሰማ ጊዜ ይፈራል፣ በሚያየው ጊዜም ይርዳል" -
ቅዱስ አግናጥዮስ ጸዋሬ እግዚአብሔር

እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

እመብርሃን

21 Sep, 17:41


"ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው።እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።"

ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

መልካም ምሽት❤️

እመብርሃን

15 Sep, 05:10


"ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸውና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ፀሎት ይሁን፡፡"


ቅዱስ አግናጥዮስ

በቸር ዋሉሉልኝ🙏

እመብርሃን

11 Sep, 07:21


እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ

እመብርሃን

09 Sep, 08:52


በአዲሱ ዓመት ፤ በአዲስ ጉልበት ፣በአዳዲስ መርኋግብራት እንገናኛለን ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።🙏🙏🙏

እመብርሃን

09 Sep, 08:32


ደስ የምንል 2ሺ💫 ቤተሰብ ሆነናል። 🙏

ለማንኛውም አስተያየት @ene_ehonen ለይ ሊያስቀምጡልኝ ይችላሉ።

እመብርሃን

19 Aug, 18:12


ውዳሴ ማርያም የሚጸልይና የማይጸልይ

የእመቤታችን ውዳሴ ማርያም የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በየዕለቱ የሚጸልይ ሰው የእናት አባቱን ርስት የወረሰ ይመስላል።

የሰባቱን ዕለት ውዳሴ ማርያም በእድሜዋ ልክ በየዕለቱ  የሚጸልይ ደግሞ የዘመዶቹን ጨምሮ የወረሰ ይመስላል።

እመቤታችን ሳያመሰግን የሚውል ሰው ምን ይመስላል ቢሉ፦

ከሰው ቤት ድግስ ተጠርቶ ሂዶ በር ላይ ሲደርስ ውኃ ተደፍቶበት፥ ተቆጥቶ የሚመለስ፤  እንቅፋት እየመታው እየወደቀ እየተነሣ እየተሰበረ የሚሄድ ይመስላል።

ያ ሰው ካለመብላቱ በላይ እየተሰበረ እንደሄደ እመቤታችን የማያመሰግንም በመከራ ሥጋ ላይ መከራ ነፍስ ይጸናበታል። በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ይጨመርበታል።
      
      ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

እመብርሃን

17 Aug, 17:08


"ያለ እግዚአብሔር ብቻ ኃጢአትን ይቅር ማለት ለማን ይቻለዋል? ሥጋን መዋሀዱ ከሰው ወገን ባይሆን ኖሮ የኢያኢሮስን ልጅ ልጄ ብሎ ባልጠራ ነበር፣ በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን ኖሮ ከሞተች በኋላ ለህይወት ባላስነሳት ነበር፣ ሥጋን መዋሀዱ ከሰው ወገን ባይሆን ምራቁን ከአፈር ላይ ባላደረገ ነበር በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን ምራቁን በመቀባት ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው ዓይን ባላበራ ነበር ሥጋን መዋሀዱ ከሰው ወገን ባይሆን ማዕበል ሲነሳ በጀልባ ውስጥ ባልተኛ ነበር፣ በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን ባህሩን ነፋሳትን በመገሰጽ ጸጥ ባላሰኘ ነበር፡፡ ሥጋን መዋሐዱ ከሰው ወገን ባይሆን መንገድ በመሄድ ባለደከመ ነበር፣ በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን መሄድ የተሳናቸውን ባላዳናቸው እንደጐበዝ ተራማጅ ባላደረጋቸው ነበር፣ ሰው መሆኑ ከሰው ወገን ባይሆን ኖሮ ባልተራበ፣ በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን አምሰት ሺ ርኁባንን በአምስት ኅብስትና በሁለት ዓሣ ወራት መቶ ርኁባንን በሰባት እንጀራና በጥቂት ዓሣ ባላጠገበ ነበር፣ የክርስቶስ ክብር ከራሱ እንጂ ከሌላ የተገኘ አይደለም፡፡"

(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ - መጽሐፈ ምስጢር)

እመብርሃን

16 Aug, 05:35


ጌጣችን ሆነህ ፡ ተዋብንብህ፣
አለታችን ሆነህ ፡ የተሸሸግንብህ፣
መጠጊያችን ሆነህ ፡ የተጠለልንብህ፣
በመስቀል ተሰቅለህ ፡ የዳንብህ፣
እንወድህ ዘንድ ደምግባት ፡ የሌለህ፣
አባትም አምላክም ፡ ገዢም አንተ ነህ....

:
ክብርህን አተህ፡ ያለበስከን ክብር፣
ወለታህ ግሩም ነው ፡ማይተመን በብር፣
ፍቅር እየለገስክ ፡ስቃይ ያገኘኸው፣
ጌታ ሆይ አምለክ ፡ሆይ ለኛ እኮ ነው፣
በፈጠርከው ፊት፡ የተናነስከው ፣
ውሃን ፈጥረህ ውሃን፡ የለመንከው፣
ጉሮሮህ ደርቆ ሆምጣጤ፡ የጠጣሀው ፣
አሁንም ለእኛው ነው........

:

በቃል ተነግሮ ፡ለማያልቀው ውለታ፣
ምን እንስጥህ መለሰን ፡የእኛ ጌታ.....

:

ምንም ምን ብናስብ፡ ለመስጠት ላንተ፣
ሁሉም እርካሽ ለክብርህ፡ ማይመጥን ባንተ ።

:

እንግዲያስ ላንተ ታዛዥ፡ በፍቅረህ ኗሪ አድርገን፣
ቢያንስ እራሳችንን እንስጥ፡ በንስሀ ተመልሰን።


Σίρακ

እመብርሃን

15 Aug, 14:39


ለማንኛውም አስተያየት ፣ጥቆማ፣ጥያቄ ፣እንዲለቀቅ የምትፈልጉት ነገረ ካለ፣

@ene_ehonen ማናገር ይችላሉ

እመብርሃን

13 Aug, 04:00


❤️

እመብርሃን

20 Jul, 05:01


“እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥19

እመብርሃን

12 Jul, 05:36


❤️

እመብርሃን

11 Jul, 14:17


መሠረቶቿ የተቀደሱ የኖሩ ለእግዚአብሔር
እናት አባቷ የተመረጡ የፃድቃን ብሔር
እርሷ ጨረቃ የፀሃይ አናት
የችግር መፍቻ ቁልፍ አቁራሪተ መዓት




ለእኔ ጉያዬ ከአለም ቁር ማምለጫ
ለወየበው ህይወቴ አብሪ ማጣፈጫ
ሲጨንቀኝ ስጠራት አቤት የምትለኝ
በስሟ የከበርኩ የልጇ ልጅ ነኝ


ለአለሙ መክበሪያ ትውልድ ለተባሉት
የክርስቶስ አካል በፀጋው ለዳኑት
ፅኑ ነው ልመናዋ ሚያስመልጥ ከጥፋት
እንኳንስ......
ብጽይት ላሉ`ት ለሰገዱ ለእርሷ
ለከዷት እንኳ አይቀርም ማጉረሷ


አይ ምኑን ትቼ ምኑን ልናገር
የቀመሰ ያውቀዋል የማርያምን ክብር

Σίρακ

2,348

subscribers

541

photos

6

videos