Arba Minch University @arbaminch_university Channel on Telegram

Arba Minch University

@arbaminch_university


The official telegram channel of Arba Minch University

Arba Minch University (English)

Are you looking to stay updated with the latest news and events from Arba Minch University? Look no further than our official Telegram channel, @arbaminch_university! As one of the leading educational institutions in Ethiopia, Arba Minch University is dedicated to providing quality education and research opportunities to its students. Our channel serves as a hub for important announcements, upcoming events, and insightful discussions related to our university. Whether you're a current student, alumni, or simply interested in learning more about our institution, our channel has something for everyone. Join us today and become a part of our vibrant community of learners and educators at Arba Minch University!

Arba Minch University

13 Feb, 09:23


A Public Lecture: Language, Gest, Gesture and Images Shaping the “White Savior” in Cinema and Action Movies

Arba Minch University (AMU) Internationalization and Collaboration Directorate in collaboration with Charles University Faculty of Arts of Czech Republic held a public lecture on how language, gest, and visuals shape the “White Savior” in action films on February 11/ 2025 at Chamo Campus. Staffs from English language and Literature Department and others were in attendance.

AMU Academic, Internationalization and Collaboration/AMU-AIC/ Coordinator Adanech Zemede (PhD), during opening the program, said, the narrative trope of the “White Savior” is one way of the mass communication of cinema representing the sociology of race and ethnic relations by presenting abstract concepts; the morality and characteristics of the white races were exposed as if they were not to be found in non-white races; therefore, the aim of this public lecture is to aware the scholars and strengthen the ties between AMU and Charles University Faculty of Arts, Czech Republic. Dr. Adanech hoped that the collaboration will continue working on language and literature, culture, geology, and other areas according to the MoU inked in between the universities, she noted.

The Public speaker and a lecturer at Charles University Faculty of Arts, Czech Republic, Vojtëch ŠarŠe (PhD), speaking on his analyses of the post of the “White Savior” or the major character in cinema and action movies, said, the concept of the “White Saviorism” is used to build the white character to be depicted as if innately having heroic character traits of superiority and any sort of goodness whereas the non-white (black and caucasian) is to the post of evil generally and all sorts of weaknesses and inferiority in “The great Wall”, “The Last Samurai”, “Avatar”, and in many other action movies professionally enforcing the language, gest, gesture, and visuals to shape the “White Savior”.

The “White Saviorism” refers to the belief that the white people have a responsibility to save and protect the non-white indigenous peoples because of their superiority even though they often end up causing more harm than good, he remarked. The “white saviorism” ideology is a symptom of continued interest of racism and white supremacy which places the non-white in a position under the rule of the savior, the white, leaving the non-whites to oppression and exploitation, he added.

The attendees raised different questions for explanations and insights were shared during the discussion; it also significantly enriched the teaching experience offering a unique perspective on the future of literature in AMU in particular and Ethiopia in general.

Arba Minch University
The Center of Bright Future!


For more Information Follow us on:-

Website - https://www.amu.edu.et/
Telegram - https://t.me/arbaminch_university
Facebook - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

Public and International Relations Executive

Arba Minch University

12 Feb, 14:03


AMU Officials Attend a Conference on Irrigation and Climate Resilient Production

Arba Minch University/ AMU/ higher officials attend a conference on Irrigation and Climate Resilient Production 2025 commenced on February 12, 2025. The conference, organized by the Ministry of Irrigation and Lowlands (MILLs), aims to foster discussions on innovative strategies for climate-resilient agricultural practices, bringing together policymakers, ambassadors, and representatives from international organizations and development partners. The participation of AMU is a testament of its commitment to addressing critical issues in irrigation and sustainable production in the face of climate change.

Arba Minch University
The Center of Bright Future!


For more Information Follow us on:-

Website - https://www.amu.edu.et/
Telegram - https://t.me/arbaminch_university
Facebook - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

Public and International Relations Executive

Arba Minch University

08 Feb, 12:03


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 8ኛውን ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የውሃ ዋና ምዘና ውድድር አስተናገደ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 8ኛውን ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የውሃ ዋና ምዘና ውድድር በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በሚገኘው ኦሎምፒክ ስታንዳርድ መዋኛ ገንዳ ከጥር 29 - የካቲት 1/2017 ዓ/ም ድረስ አስተናግዷል።

በውድድሩ ከ6 ክልሎች የተገኙ ከ100 በላይ ተወዳዳሪ ስፖርተኞች ተሳትፈዋል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

07 Feb, 14:06


የዕጩ ዶ/ር ነስረዲን ተማም የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ ተገመገመ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በማኔጅመንት ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው የዕጩ ዶ/ር ነስረዲን ተማም የመመረቂያ ጽሑፍ ዛሬ ጥር 30/2017 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር ነስረዲን የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት እንዲሁም የ2ተኛ ዲግሪውን ህንድ ሀገር ከሚገኘው "Andhra University" በ"Financial Management and International Business" ትምህርት ያገኘ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርት ሲከታተል ቆይቶ የመመርቂያ ጽሑፉን "Financial and Marketing Approach to Export Performance,Empirical Evidence from Ethiopian Manufacturing Indusry" በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር ነስረዲን ተማም ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

03 Feb, 09:27


Vacancy Announcement for the Director position

Arba Minch University

03 Feb, 08:55


የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ግምገማ መርሃ ግብር

Arba Minch University

02 Feb, 16:22


23rd International Symposium on Sustainable Water Resources Development

May 23-24/2025

Selected Paper will be published on special issues for Journal of Water Management Modeling’s

Arba Minch University in Ethiopia is hosting the 23rd International Symposium on Sustainable Water Resources Management, a premier global conference for scholars, practitioners, decision-makers, and stakeholders dedicated to sustainable water resource management. This symposium provides an interdisciplinary platform for discussing the latest innovations, challenges, and solutions in water sustainability, with a focus on both regional and global perspectives.

Key Themes Include:

Ø Hydrology and integrated water resources management
Ø Renewable Energy
Ø Irrigation and Drainage
Ø Water Supply and Sanitation
Ø Climate change, variability and impacts
Ø Emerging issues

The symposium will feature keynote presentations, technical sessions, panel discussions, and networking opportunities, providing attendees with insights into cutting-edge research, real-world case studies, and best practices in water management. Special attention will be given to the African context, with Ethiopia’s rich water resources and diverse challenges serving as a focal point for discussions.

Why You Should Attend:

Discover cutting-edge research and innovative solutions for sustainable water management.
Connect with leading experts, policymakers, and industry professionals from around the world.

Engage in vital discussions on urgent water challenges and the future of global water security.
Explore the latest technologies and strategies for effective water conservation and management.
Help shape policies and practices that will influence sustainable water management for future generations.

Join us in Arba Minch for a transformative experience that brings together research, practical solutions, and collaboration towards a sustainable water future.

Important Dates:

Abstract Submission Deadline: February 15, 2025

Notification of Acceptance: February 22, 2025

Full Paper Submission: April 7, 2025


Submit your abstract to:

[email protected] or [email protected] , [email protected] , [email protected] , [email protected], [email protected]

Contact Person

1. Dr. Eng. Tamru Tesseme Aragaw (PhD. P.E)
Scientific Director for Arba Minch Water Technology Institute, Arba Minch University

2. Dr. Elias Gebeyehu Ayele
Water Research Center Director for Arba Minch Water Technology Institute, Arba Minch University

3.Daniel Reddy Thota
Senior Lecturer in Faculty of Water Supply and Environmental Engineering
4. Abebe Temsegen (Assistant Professor)
Academic Director for Arba Minch Water Technology Institute

Arba Minch University

21 Jan, 17:36


Menzies Monitoring Team Evaluates Collaborative Malaria Research

A monitoring team from the Menzies School of Health Research recently evaluated the ongoing "A Revised Tafenoquine Dose to Improve Radical Cure for Vivax Malaria" (TADORE) study at Arba Minch General Hospital. This project is a collaborative initiative involving the College of Medicine and Health Sciences at Arba Minch University, the Menzies School of Health Research in Australia, and Arba Minch General Hospital, formalized through an agreement signed in September 2024.

Dr. Zerihun Zerdo, Research Director of the College of Medicine and Health Sciences at Arba Minch University, highlighted the importance of collaborative research. "Collaborative efforts like the TADORE study are crucial for tackling complex health issues such as Vivax Malaria. Our college is dedicated to supporting these initiatives by providing the necessary resources and expertise to ensure their success. Additionally, as Arba Minch University strives to become a research-led autonomous institution, such collaborations are vital for strengthening our research capacity, expanding global partnerships, and establishing ourselves as leaders in health research."

Dr. Tamiru Shibiru, the Principal Investigator of the project, stated that following the signing of the agreement, the research required approval from the Ethiopian Food and Drug Authority. Once this approval was obtained, patient enrollment for the clinical trial commenced on December 20, 2024, and 30 patients have been enrolled so far. The study is designed to be conducted across four countries: Ethiopia, Brazil, Indonesia, and Papua New Guinea. The team in Brazil has already initiated their work and has enrolled 80 patients to date.

Dr. Tamiru emphasized the importance of monitoring in ensuring the integrity and reliability of clinical trial data. "The TADORE study aims to refine Tafenoquine dosing for a more effective radical cure of Vivax Malaria, a major public health concern," Dr. Tamiru explained. "Given that this is a clinical trial, it requires meticulous attention and thorough care. Rigorous monitoring by our Menzies partners ensures strict adherence to the highest standards, which is crucial for the safety of patients, integrity of the data and the success of the trial, ultimately leading to improved treatment outcomes for patients."

According to Dr. Tamiru, the three-year study focuses on Vivax Malaria, which can persist in the liver and cause recurring infections. The goal is to identify more effective treatments and develop faster-acting cures.

The monitoring team, led by Clinical Research Expert Hellen Mnjala and Clinical Trial Data Manager Grant Lee, reviewed the study’s data accuracy, participant safety, and adherence to protocols, regulatory standards, and ethical guidelines.

Hellen Mnjala, Clinical Research Coordinator, shared insights on malaria research at sites in Brazil, Indonesia, Papua New Guinea, and Ethiopia, all of which comply with local requirements and undergo rigorous monitoring. This research is expected to advance healthcare practices and modernize malaria treatment options, benefiting communities and improving health outcomes.

Grant Lee in his part highlighted his team’s role in ensuring high-quality data collection throughout the trial. He noted that his presence in Arba Minch is dedicated to supporting quality data collection, ensuring effective patient safety.

The study’s impact is highlighted by the involvement of 450 patients, a 6-month follow-up, and a team of 14 research experts. With $377,002 USD in funding, this collaboration is a crucial step in advancing malaria treatment and improving patient care in the region.

Arba Minch University
The Center of Bright Future!

For more Information Follow us on:-

Website - https://www.amu.edu.et/
Telegram - https://t.me/arbaminch_university
Facebook - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

Public and International Relations Executive

Arba Minch University

18 Jan, 11:40


የበዓል መልካም ምኞት መግለጫ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ በመላው ዓለም ለምትገኙ ለዩኒቨርሲቲው የቀድም ምሩቃን እንዲሁም ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል

Arba Minch University

17 Jan, 06:51


በ‹‹GIS›› ምንነትና አጠቃቀም ላይ ሥልጠና ተሰጠ

በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል ከጋሞ ዞን ከተማና ፕላን መምሪያ ጋር በመተባበር ከጥር 5-8/2017 ዓ/ም ለዞን፣ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር ስታትስቲክስ ባለሙያዎች በ‹‹GIS›› ምንነትና አጠቃቀም ላይ በኮሌጁ የGIS ማዕከል ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አበራ ኡንቻ ት/ክፍሉ የመረጃ አያያዝን በቴክኖሎጂ የታገዘና ቀልጣፋ አሠራር የተከተለ ለማድረግ የባለሙያዎችን አቅም የሚያሻሽሉ ሥልጠናዎችን በመስጠት የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑንና ኮሌጁ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ በኮሌጁ የሚገኘውን የGIS ማዕከል ከክልል ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ የGIS ሥልጠና የልኅቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል ኃላፊ መ/ር አደፍርስ ተፈራ እንደገለጹት ሥልጠናው የስታትስቲክስ ባለሙያዎች በGIS የታገዘ ቀልጣፋና ተአማኒነት ያለው መረጃ የመሰብሰብ፣ የማደራጀትና የመተንተን እንዲሁም የተሻለ የውሳኔ አሰጣጥ ክሂሎት እንዲኖራቸው በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሻሻል፣ የግብርና ምርትና ሥርጭትን አስመልክቶ ለሚመለከተው አካል መረጃ ለመስጠት፣ በቂ ጥናትና ምርምር ለማካሄድና ዕውቀትን ለማዳበር ሥልጠናው የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሰሲቲው የ‹‹AMU-ESRI›› ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊና በጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል መምህር ኃይለማርያም አጥናፉ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው አሜሪካ ከሚገኘው ‹‹ESRI›› የተሰኘ የGIS ሶፍትዌር አቅራቢ ድርጅት ጋር ስምምነት በመፍጠርና ነጻ ፈቃድ በማግኘት ላለፉት አራት ዓመታት በሶፍትዌሩ አጠቃቀም ላይ ለማኅበረሰቡ ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግንባር ቀደም የGIS ማሠልጠኛ ማዕከል ያለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መሆኑን የጠቆሙት መ/ር ኃይለማርያም ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር በመሥራት ሥልጠናዎችን ወስደው ሙያዊ ክሂሎታቸውን ማዳበር ለሚሹ ተቋማትና ባለሙያዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል ረ/ፕሮፌሰር ዓለሙ አሰሌ GPS በተለያየ መልክዓምድራዊ አቀማመጥ የሚገኙ መረጃዎችን በተገቢው መንገድ መሰብሰብ የሚያስችል ዘመኑ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን ተናግረው በGPS የተሰበሰበውን መረጃ ወደ GIS ሶፍትዌር በመቀየር የተለያየ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
በጋሞ ዞን ፕላንና ከተማ ልማት መምሪያ የስታትስቲክስና የGIS ቡድን መሪ አቶ ደግፌ ደምበላ በበኩላቸው የዞኑ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃ አሰባሰብና አመዘጋገብ ስኬታማ እንዲሆን ሥልጠናው የላቀ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተሻለ ትብብር በመፍጠር የዞኑን ባለሙያዎች አቅም የሚያጎለብቱ ሥልጠናዎች እንደሚመቻቹም ተናግረዋል፡፡

በገረሴ ከተማ አስተዳደር የከተማው ፕላንና ልማት ቡድን መሪ አቶ ደሣለኝ ዳዊት በበኩሉ ሥልጠናው የከተማዋን የ10 ዓመት እቅድ በምናዘጋጅበት ወቅት እና የተሻለ የከተማ ካርታ ለማዘጋጀት የሚያግዝ መልካም አጋጣሚ መሆኑንና ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰቡን አቅም ለማሻሻል የሚያከናውናቸው ተግባራት የሚበረታቱ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ቅድመና ድህረ ምዘና፣ መሠረታዊ የGIS እና የGPS ምንነት፣ ሳይንሳዊ የመረጃ አሰባሰብ፣ አደረጃጀት እና አተናተን እንዲሁም የመሬት ይዞታ ካርታ አዘገጃጀት በሥልጠናው ከተዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች መካከል ናቸው፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

16 Jan, 14:13


Global Spotlight on Enset!

We are thrilled to announce that La Croix International, a renowned French newspaper, has featured Arba Minch University's work on enset! This highlights the growing international recognition of enset’s crucial role in building sustainable and inclusive food systems.

Thank you to our dedicated researchers and partners for making this possible. Together, we’re shaping a better future!

Arba Minch University
The Center of Bright Future!
https://international.la-croix.com/laudato-si/ethiopia-bets-on-the-false-banana-that-could-help-combat-hunger

Arba Minch University

16 Jan, 13:30


የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ከሳውላ ካምፓስ ኃላፊ ጋር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ተፈራረሙ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ከሳውላ ካምፓስ ኃላፊ ጋር በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረግ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ተፈራርመዋል፡፡

በም/ፕሬዝደንት ማዕረግ የሳውላ ካምፓስ ኃላፊ አቶ ገብረመድኅን ጫሜኖ በዩኒቨርሲቲው ተቆጥረውና ተለክተው እንደ ካምፓስ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የተሰጡንና ቁልፍ ተግባራት ለመፈጸም በመስማማት ተፈራርመናል ብለዋል፡፡

ቁልፍ ተግባራት ላይ በትኩረት መሥራት አለብን ያሉት ኃላፊው የተሠሩ ሥራዎች በአግባቡ ተለቅመውና የሪፖርት አካል ተደርገው መቅረብ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ ከትምህርት ክፍልና ከአስተዳደር ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይቶችን በማካሄድ የውል ስምምነቱን እስከ ታችኛው ፈጻሚ አካል ድረስ በማውረድ ለተግባራዊነቱ እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

06 Dec, 15:02


የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዲስ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተወያዩ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር አመራሮች ቀደም ሲል ያሉ አሠራሮች፣ ተሞክሮዎች፣ ተግዳሮቶች፣ አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ወሳኝ መረጃዎችን አስመልክቶ ኅዳር 27/2017 ዓ/ም አዲስ ከተመደቡ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ነባር የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች ከዚህ ቀደም ለነበራቸው አገልግሎት ምስጋና በማቅረብ ከኃላፊነት ያነሱ ሲሆን አዳዲስ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን በተጠባባቂነትና በውክልና መድበዋል፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱና ቦርዱ በጻፉት ደብዳቤ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር)፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዓለማየሁ ጩፋሞ (ዶ/ር)፣ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት በኃይሉ መርደኪዮስ (ተ/ፕ) እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን ከአመራርነት መነሳታቸውን ያሳወቀ ሲሆን በምትካቸውም ኢ/ር አብደላ ከማል (ዶ/ር) በተጠባባቂ ፕሬዝደንትነት እንዲሁም ኢ/ር ቦጋለ ገ/ማርያም (ዶ/ር) የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት፣ ተክሉ ወጋየሁ (ዶ/ር) የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም ፕ/ር ጳውሎስ ታደሰ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ሆነው ከታኅሣሥ 01/2017 ጀምሮ በውክልና እንዲሠሩ ተመድበዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

06 Dec, 12:03


19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ተማሪዎች የጽዳት ዘመቻ አከናወኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ት/ክፍል ተማሪዎች 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ኅዳር 27/2017 ዓ/ም የጎዳና ላይ የጽዳት ዘመቻ አከናውነዋል፡፡

የዝግጅቱ አስተባባሪ የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ት/ክፍል ኃላፊ ዳመነ ቦጋለ የበዓሉ መከበር ከቱሪዝም የልማት ሥራዎች ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው መሆኑን ጠቅሰው ጎዳናዎችን ለጎብኚዎችና ለበዓሉ ተሳታፊዎች ጽዱና ምቹ ለማድረግ በማለም የጽዳት ዘመቻው መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ‹ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በአርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይከበራል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

22 Nov, 16:19


የዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፋራ የ3ኛ ዲግሪ መመርቂያ ጽሑፍ ተገመገመ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በ"Geography and Environmental Studies" ትምህርት ክፍል በ"Environment and Natural Resource Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፋራ የመመረቂያ ጽሑፍ
ህዳር 13/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፋራ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ"Geography and Environmental Study" እንዲሁም የ2ኛ ዲግሪውን ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ ከ "Geography and Environmental Study" ትምህርት ክፍል በ "Physical Geography" ያገኘ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመርቂያ ጽሑፉን"CLIMATE VARIABILITY AND LAND USE/COVER CHANGE IMPLICATIONS FOR RURAL HOUSEHOLD FOOD SECURITY AROUND GHIBE III DAM, SOUTHERN ETHIOPIA" በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፍራ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሰኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

22 Nov, 05:56


Will be commenced soon!

Arba Minch University

21 Nov, 13:44


የ2017 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ኅዳር 11/2017 ዓ/ም የካውንስል አባላት በተገኙበት ገምግሟል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን መሠረታዊ መረጃዎች፣ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ ዋና ዋና ስትራቴጂክ ጉዳዮችና አፈጻጸማቸውን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች፣ የመፍትሔ እርምጃዎችና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን የዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰሎሞን ይፍሩ ለካውንስሉ አባላት አቅርበዋል፡፡ በዚህም መሠረት ዩኒቨርሲቲው በዝግጅት ምዕራፍ ትምህርት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የኮርስ ድልድል ሥራ በመሥራትና የonline ምዝገባ ሂደት ለማቀላጠፍ ተማሪዎች በክረምት የወሰዷቸውን ኮርሶችን ለመምህራን በማድረስ የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ትምህርት በወጣው የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲከናወን መደረጉ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ጥራት፣ አግባብነት፣ ተደራሽነትና ፍትሐዊነትን ከማረጋገጥ አንጻር የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ፣ የተማሪዎችና መምህራን የትምህርት ደረጃ ስብጥር፣ የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ እና የድኅረ ምረቃ ትምህርትን ማሳደግ ላይ ዕቅዱን መሠረት አድርጎ መከናወኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የምርምር እና ፈጠራ ሥራዎች ተደራሽነትና ፍትሐዊነት እንዲሁም የሀገር በቀል ዕውቀትን ማጣጣምና ማሳደግን በተመለከተ በሩብ ዓመቱ 22 ነባር ምርምሮች የተጠናቀቁ ሲሆን ጭብጥ ተኮር ምርምርን በሥራ ላይ ለማዋል ዘጠኝ የምርምር ጭብጦች /Research Thematic Areas/ ተለይተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር የምርምር ሲምፖዚዬምና የትብብር ምርምር ግራንት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሮችን ማካሄዱ በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ለተቋራጮች እና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የማማከር አገልግሎቶችን መስጠት፣ ነፃ የሕግ ጥብቅና ፣ የምክር አገልግሎትና የሰነድ ዝግጅት ድጋፍ፣ በ‹‹STEM›› ማዕከል የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎችን ማሠልጠን፣ እንዲሁም በተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርትና ሥልጠና በደረጃ አንድና ሁለት ጎልማሶችን ማሠልጠን ከማኅበረሰብ ጉድኝትና የሳይንስ ባህል ግንባታ ተደራሽነትንና ፍትሐዊነትን ማሳደግ ጋር ተያይዞ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በዚሁ ዘርፍ በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት በጀመረው የዩኒቨርሲቲው የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታል 1240 ተጠቃሚዎችን የሕክምና አገልግሎት መሰጠቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የተቋማት ትስስርና ተሳትፎ፣ ሥራ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ማሳደግን አስመልክቶ በሩብ ዓመቱ አንድ ቴክኖሎጂ ለማኅበረሰቡ የተሸጋገረ ሲሆን አጫጭርና ረዣዥም ሥልጠናዎች፣ የወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ውድድርና ሽልማት እንዲሁም ከሴክተር መሥሪያ ቤቶችና ኢንደስትሪዎች ጋር የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ ተከናውኗል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በዕውቀትና ቴክኖሎጂ የተደገፈ የፍትሕ ሥርዓት ለማስፈን የሚረዳ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል ሥራ ማስጀመሩም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ የትምህርት አመራርና አስተዳደርን ከማጠናከር አኳያ ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝ አስተዳደር ትግበራን ለማከናወን ተቋማዊ ራስ ገዝ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በማቋቋም ወደ ሥራ የገባ ሲሆን ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የዩኒቨርሲቲውን ሴኔት መተዳደሪያ ደንብና ስትራቴጂክ ዕቅድ የመከለስ ሥራ መጀመሩ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማዊ አቅምና ብቃት ለማጎልበት እንዲሁም የትምህርት መሠረተ ልማትና ፋሲሊቲ እና የሀብት ምንጭና አጠቃቀም ውጤታማነትን ለማሳደግ በሩብ ዓመቱ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የመምህራን የትምህርት ዕድል፣ የመምህራን አካዳሚክ ማዕረግ እድገት፣ ከሳይት ርክክብ ጀምሮ በተለያዩ ሂደቶች ላይ ያሉ ግንባታዎች ክንውን በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር)የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸሞች በአብዛኛው የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች መሆናቸውን ጠቁመው በሪፖርቱ ከዕቅድ በታች የተከናወኑ እና ከመድረኩ እንደ ክፍተት የተነሱ ጉዳዮች በቀጣይ የአፈጻጸም ወቅት በሚገባ አካትቶ መሥራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

የአፈጻጸም ሪፖርቱን የተመለከቱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ጥቆማ ከተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡ አስቸኳይ የማሻሻያ እርምጃ የሚሹ ጉዳዮችን አሰመልክቶ ቀጣይ የጋራ ውይይትና ትግበራ ለማድረግም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

18 Nov, 16:44


Public Lectures: African Biomass Burning & its Global Impact and Crafting a Successful Grant Proposal

AMU hosted insightful Public Lectures on biomass burning & its impact on climate change and air quality and crafting a successful grant proposal on November 14, 2024 in AMU, Main Campus.

Thomas Torora (PhD), underscoring the importance of such initiatives in enhancing awareness of climate-related issues and crafting a successful grant proposal, emphasized the event’s alignment with AMU’s research priorities.

The first lecture presenter, Solomon Bililign (Full Professor of Physics) at Applied Sciences and Technology /A & T/ State University at North Carolina, USA, presented his research on “Characterizing the Optical and Chemical Properties of Biomass Burning Aerosols derived from African Biomass Fuels - Implications to Global Climate and Air Quality’. In his Lecture, Prof. Solomon highlighted the urgent need for comprehensive research on biomass burning aerosols focusing on their role in climate dynamics and public health. His presentation detailed laboratory studies examining how factors such as relative humidity, burn conditions, and fuel types affect biomass burning aerosol properties. He pointed out the significant gap in research on African biomass fuels compared to North American and western world sources calling for enhanced data collection and monitoring systems in Ethiopia.

The second presenter, Addisu Fekadu (PhD and associate professor of Biology) from AMU, discussed his point on 'Crafting Winning Proposals and Enhancing Networking Skills". He shared practical tips for researchers on securing grants and building partnerships drawing on his own experience in the field.

Following the presentations, the participants of the two lectures expressed their concerns about and posed queries on each topic ideas; thus, they noted the lack of data and technology for monitoring emissions from biomass burning regarding the first lecture. The also mentioned need for key policy introductions, improving data collection and monitoring systems, developing robust regulatory frameworks, promoting public awareness campaigns focused on the health impacts of air pollution and the need for collaboration between researchers and local communities. As for the second lecture, the participants confirmed that the lesson learned from Dr. Addisu's presentation will undoubtedly resonate and inspire a new generation of scholars to pursue innovative projects with confidence.

Vice President for Research and Collaboration Office, Behailu Merdekios (Associate Professor), closing the public lectures virtually expressed AMU's dedication to organize events that not only promote academic involvement but also establish the university as a leader in tackling crucial environmental problems in Ethiopia and beyond. This determination in developing practical strategies signifies a hopeful trajectory toward a greener and more sustainable future where research and community initiatives align to effectively fight climate change. He also extended his gratitude to the initiators, organizers, and presenters emphasizing on their efforts.

Arba Minch University
The Center of Bright Future!

For more Information Follow us on:-

Website - https://www.amu.edu.et/
Telegram - https://t.me/arbaminch_university
Facebook - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

Public and International Relations Executive

Arba Minch University

16 Nov, 13:14


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተመደቡለትን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዛሬ ህዳር 7/2017 ዓ/ም ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል፡፡

ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ውቢቷ አርባ ምንጭ እንዲሁም ወደ አንጋፋው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሠላም መጣችሁ እያልን በዩኒቨርሲቲው የሚኖራችሁ ቆይታ የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን::

እንኳን ይህና መጣችሁ!!
Hashshu saaro Yideta!!

Arba Minch University

15 Nov, 13:13


የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ግምገማ መርሃ ግብር

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በ‹‹Geography and Environmental Studies›› ትምህርት ክፍል በ‹‹Environment and Natural Resource Management›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ እጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፋራ ኅዳር 13/ 2017 ዓ/ም ከ ጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በጫሞ ካምፓስ አዳራሽ ያቀርባል፡፡
እጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፋራ ‹‹CLIMATE VARIABILITY AND LAND USE/COVER CHANGE IMPLICATIONS FOR RURAL HOUSEHOLD FOOD SECURITY AROUND GHIBE III DAM, SOUTHERN ETHIOPIA›› በሚል ርእስ ያከናወነውን የመመረቂያ ጥናት ጽሑፍ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

15 Nov, 12:46


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹e-SHE›› የተሰኘ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ማስጀመሪያ ኦሬንቴሽን ሰጠ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ‹‹MasterCard Foundation››፣ ‹‹ASU›› እና ‹‹SYS›› ዓለም አቀፍ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ‹‹e-SHE›› የተሰኘ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ማስጀመርና የተጠናከረ የትምህርት ሥርዓት መፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክትን አስመልክቶ ጥቅምት 28/2017 ዓ/ም በሁሉም ካምፓስ ለሚገኙ መምህራን ኦሬንቴሽን ሰጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመማር ማስተማር በማካተት ዘመኑ የደረሰበት የእድገት ደረጃ መድረስ ይገባል ብለዋል፡፡ እንደ ሀገር በዲጂታል ቴክኖሎጂ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ መምህራን በቴክኖሎጂ የታገዘ ሳቢና ማራኪ የትምህርት አሰጣጥ ሂደት መከተል እንደሚገባቸው ፕሬዝደንቱ አሳስበዋል፡፡

የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትግበራና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሠረቀብርሃን ታከለ በበኩላቸው ሥልጠናው የከፍተኛ ትምርትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው መምህራን ቴክኖሎጂውን በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በማካተት ለትምህርት ጥራት የበኩላቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ‹‹e-SHE›› ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር መሐመድ አበበ እንደተናገሩት ዲጂታል ቴክኖሎጂውን ከትምህርት ሥርዓቱ ጋር በማጣመር አሁን ያለውን መማር ማስተማር የተሻለና ዘመኑን የዋጀ ማድረግ የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ ነው፡፡ በመሆኑም በዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቱን ለማስጀመር የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን መስጠት፣ በ‹‹e-SHE›› አተገባበር ላይ መረጃ የሚሰጥ ‹‹course.amu.edu›› የተሰኘ ድረ ገጽ መፍጠር፣ መሠረተ ልማቶችንና ግብኣቶችን ማሟላት፣ ለፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ኮርሶችን መለየት እንዲሁም ‹‹e-SHE››ን ተቋማዊ የማድረግና ለውጤታማነቱ መምህራንና ተማሪዎች የሚኖራቸውን ድርሻ አስመልክቶ ሕገ ደንብ የማውጣት ሥራ ተሠርቷል፡፡ ዶ/ር መሐመድ አያይዘውም ለዲጂታል ቴክኖሎጂው አመቺ የትምህርት ይዘት ለማዘጋጀት፣ ዘርፉ የሚጠይቀውን ዕውቀት ለማዳበርና የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሻሻል ‹‹Master class›› የተሰኘ የ25 ሰዓት ሥልጠና ለመምህራን ይሰጣል፡፡

መምህራን በሰጡት አስተያየት ፕሮጀክቱ ለትምህርት ጥራት መሻሻል ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም የሚያስችል በቂ ግብኣት ማሟላትና ሥልጠናዎችን መስጠት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

የአምስት ዓመት ፕሮጀክት የሆነው ‹‹e-SHE›› 50ዎቹ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ አልያም በከፊል በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ መማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር የሚሠራ ሲሆን ግቡን ለማሳካት ‹‹MasterCard Foundation›› ድጋፍ በመስጠት፣ ‹‹SYS SHAYASHONG›› የማማከር ሥራ በመሥራት እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና ‹‹ASU›› የተሰኘ ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋም የምስክር ወረቀት በመስጠት በአጋርነት ይሠራሉ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

14 Nov, 13:09


የግርጫ ደጋ ፍራፍሬ እና አትክልት ምርምር ማዕከል

Gircha Highland Fruits and Vegetables Research Center of AMU

Arba Minch University

14 Nov, 11:53


አስቸኳይ ማስታወቂያ

ለሁሉም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕረነርሺፕ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ11ኛ ጊዜ ከኅዳር 9 - 15/2ዐ17 ዓ/ም የሚከበረውን የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት ምክንያት በማድረግ በዩኒቨርሲቲያችን ለ3ኛ ጊዜ ተማሪዎችን ባሳተፈ ሁኔታ የቢዝነስ ዕቅድ ውድድር እና የኢንተርፕረነርሺፕ ሥልጠና በሁሉም ግቢዎች ይከናወናል፡፡

ስለሆነም ቅዳሜ በቀን 07/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡3ዐ ጀምሮ የሚሠጥ የአንድ ቀን የኢንተርፕረነርሺፕ ሥልጠና ስለተዘጋጀ በዚህ ሥልጠና ላይ እንድትሳተፉ ለሁሉም ተማሪዎች ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሥልጠናውን በተገቢው ሁኔታ ለሚከታተሉ ደረጃውን የጠበቀ ሰርትፊኬት የሚሰጥ ይሆናል፡፡


የሥልጠና አዳራሽ/ቦታ
ግቢ አዳራሽ
ዋናው ግቢ አዲሱ አዳራሽ ከዋናው በር አጠገብ
ጫሞ ካምፓስ ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
ሳውላ ካምፓስ ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
ኩልፎ ካምፓስ ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
አባያ ካምፓስ ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
ነጭ ሳር ካምፓስ ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ



የአ/ም/ዩ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት እና ማበልፀጊያ ማዕከል

Arba Minch University

11 Nov, 14:25


‹‹ብርታት ጀነሬሽን›› ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሱስ አስከፊነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር አካሄደ

‹‹ብርታት ጀነሬሽን›› ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከ‹‹አብሪ ማይንድ›› እና ‹‹በርቺ›› ከተሰኙ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹በዛሬ ማንነታችን ነጋችንን እንሥራ!›› በሚል ርእስ ኅዳር 1/2017 ዓ.ም በሱስ አስከፊነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር አካሂዷል፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ጉድኝትና የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ሴዳ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ለአካባቢው ወጣቶች ከሥነ ባሕርይና ሥነ ምግባር ጋር የተገናኙ ሥልጠናዎችን ሲሰጥ እንደቆየ ጠቁመዋል፡፡ ከብርታት ጀነሬሽን ጋር በመተባባር ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተሰጠው የግንዛቤ መስጫ መርሃ ግብር ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ከአልኮል መጠጥና ሌሎች ሱሶች ነጻ ሆነው በትምህርታቸው እንዲጎብዙና ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

የብርታች ጀነሬሽን መሥራችና ማኔጀር ዮናዳብ ግርማ የመረሃ-ግብሩ ዋነኛ ዓላማ ከ21 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎችን አልኮል መጠጥ እንቢ እንዲሉ በማስቻል በዓላማ የሚመራ ባለ ራእይ ትውልድ ማፍራት ነው ብለዋል፡፡

የአብሪ ማይንድ መሥራችና ማኔጀር ወ/ሮ ሀና ኃይሉ ወጣቶች ወደ ስኬት ለመድረስ ከተለያዩ ሱሶችና ከአልኮል መጠጦች መራቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ተማሪዎች ወደ ስኬት ለመድረስ ወዴት እንደሚሄዱ፣ ከየት እንደተነሱና የት ለመድረስ እንዳለሙ፣ አሁን ላይ የት እንዳሉና የመጡበት መንገድ ምን እንደሚመስል ማወቅ እንዳለባቸውና ይህም የነገ ስኬታቸውን እንደሚወስን ገልጸዋል፡፡

የብርታት ጀነሬሽን አምባሳደር አርቲስት ሸዊት ከበደ ባስተላለፈችው መልእክት ከሱስ የሚጎል እንጂ የሚተርፍ ምንም ነገር እንደሌለ ተናግራ በተለይ ከ21 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊ ወጣቶች ወደ ሱስ ውስጥ ሲገቡ መላ ሕልውናቸውን እንደሚያጡ ተናግራለች፡፡

በመሰል ጉዳዮች ላይ ለወጣቶች ሥልጠናዎችን በመስጠት የሚታወቁት የዩኒቨርሲቲው ባለሙያ አቶ መርክነህ መኩሪያ በበኩላቸው በአብዛኛው ወደ ስህተት የገባንበት መንገድ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ከስህተታችን ተምረን ከተመለስን ጥሩ ሰው መሆን እንችላለን ብለዋል፡፡ በጎ ነገር የሚፈልቀው ከበጎ ሕሊና ነው ያሉት አቶ መርክነህ በጎ እሳቤ እንዲኖረን አንጎላችንን ከተለያዩ ሱሶች መጠበቅ መቻል አለብንም ብለዋል፡፡ በዓለም ላይ ብዙ ሰዎች እየጠፉ ያሉት በገዛ ምርጫቸው በመሆኑ ምርጫን በማስተካከል ሕይወትን ማስተካከል እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ለተማሪዎች ልምዱን ያካፈለው ወጣት ሙጡ ማዜ ወደ ሱስ ዓለም የገባው በ18 ዓመቱ እንደሆነና ከሱስ ያተረፈው ምንም ነገር እንደሌለ ተናግሯል፡፡ በሱስ ምክንያት ራሴንና ቤተሰቤን አጥቻለሁ የሚለው ወጣት ሙጡ የዕድሜውን ግማሽ በእስር ማሳለፉንም ተናግሯል፡፡ ተማሪዎች የሱስን አስከፊነት ከእኔ ተምራችሁ ከማንኛውም ሱስ የጸዳችሁ በመሆን ራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን እንዲሁም ሀገራችሁን የምትጠቅሙ ሆኑ ሲልም መክሯል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

10 Nov, 08:03


በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በ2016 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በ2016 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላ ቅዳሜና እሁድ ህዳር 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሰኞ እና ማክሰኞ ኅዳር 9 እና 10 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀምረው ረቡዕ ኀዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ Q የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣ እንዲሁም የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ R እስከ Z የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጂስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች እየቀረባችሁ በተጠቀሰው ቀን ሪፖርት እንድታደርጉና ምዝገባ እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡፡
 
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ
https://www.amu.edu.et
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

08 Nov, 07:30


Dr. Addisu Receives Prestigious ‘Outstanding Presentation Award’ at ICGEB CRP Awardees Meeting in Cape Town

Dr. Addisu Fekadu, an esteemed researcher from Arba Minch University, has been honored with the ‘Outstanding Presentation Award’ at the recent ICGEB CRP Awardees Meeting held in Cape Town from November 5-7, 2024. Presented by ICGEB Director General Dr. Lawrence Banks, this prestigious award recognizes Dr. Addisu's exceptional research contributions, distinguishing him among a group of accomplished international scholars.

The event brought together 80 delegates from 19 countries, fostering a vibrant environment for scientific exchange and collaboration. Dr. Addisu expressed his gratitude for the recognition and the opportunity to engage with such talented peers, emphasizing the collaborative spirit of the conference. This accolade underscores his commitment to innovation and reflects the high standards upheld by Arba Minch University in the global scientific community.

Arba Minch University
The Center of Bright Future!

For more Information Follow us on:-

Website - https://www.amu.edu.et/
Telegram - https://t.me/arbaminch_university
Facebook - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

Public and International Relations Executive Office

Arba Minch University

07 Nov, 13:12


AMU, UK CGHR hold Meeting; Grant Proposal Document Reviewed

Arba Minch University (AMU) along with UK Center for Global Health Research (CGHR) held a two day Consultative meeting on grant proposal review from 31st October to 1st November, 2024.

Dr. Endrias Liranso, coordinator of team, presented the major challenges related to Skin Neglected Tropical Diseases (NTDs) in Southern Ethiopia regional state based on his team assessment report. The aim of the meeting was to get feedback on the proposal, reshape it and submit the final to the funding organizations individually or jointly.

Prof. Gail Davey, who is a medical epidemiologist specializing in skin-related NTDs, and manager of CGHR, shared her experience to the team regarding the funding organizations and NTDs. She gave feedback on methodology, literature review, overlapped research questions, objectives, mapping and other gaps of the grant proposal document. Finally, she decided to contribute her part by playing a significant role until the proposal gets completed and submitted.

Behailu Merdekios (Assoc. Prof.), vice president for research and collaboration office and the team member, said in his closing remarks that connected to and working with NaPAN (Ethioian National Podoconisiosis Action Network) is a big opportunity and it is a great honor to have Prof. Gail Davey among the team. We as a team appreciate all the feedbacks given and would like to work together in the future.

Arba Minch University
The Center of Bright Future!


For more Information Follow us on:-


Website - https://www.amu.edu.et/
Telegram - https://t.me/arbaminch_university
Facebook - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

Public and International Relations Executive Office

Arba Minch University

07 Nov, 08:50


ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ

ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት ከኅዳር 9 - 15/2017 በመላው ዓለም ይከበራል። ይህን ታሳቢ በማድረግ የአምዩ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል በተማሪዎች መካከል የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር አዘጋጅቷል። ስለሆነም የቢዝነስ ሃሳብ ያላችሁ ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) https://forms.gle/ayoEzKtEYfWHQ35MA በመጫን እንድትመዘገቡ እየጋበዘን ሃሳባችሁን በግልም ሆነ በቡድን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ለአሸናፊዎች የማበረታቻ ገንዘብ እና የምስክር ወረቀት የምንሸልም መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡
• የምትወዳደሩበት የቢዝነስ ሃሳብ ከዚህ በፊት ተወዳድራችሁበት ሽልማት ያገኛችሁበት መሆን የለበትም፡፡
• ውድድሩ አሁን በትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎችን ብቻ የሚመለከት ይሆናል፡፡
• የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 28/2017 እስከ ኅዳር 5/2017 ዓ.ም ነው፡፡

የአምዩ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከ

Arba Minch University

05 Nov, 11:34


https://youtu.be/-pP8neKetcI

Arba Minch University

04 Nov, 13:12


ለ2017 ተመራቂ ተማሪዎች "Dereja Academy Accelerator Program (DAAP)" ሥልጠና እየተሰጠ ነው

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ማበልጸጊያ ማዕከል ከደረጃ ዶት ኮም /Dereja.com/ እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው የ2017 ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የ "Dereja Academy Accelerator Program (DAAP)" ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የሥልጠናው የመጀመሪያ ክፍል ሰዋዊ ክሂሎት (Soft Skill) ማለትም ‹‹Self Discover››፣ ‹‹Building Self-image››፣ ‹‹Communication Skill›› እና ሌሎችም ርዕስ ጉዳዮች ዙሪያ ለስምንት ሳምንታት የሚሰጥ ነው፡፡ የሁለተኛው ክፍል ሥልጠና ድግሞ ሙያዊ ክሂሎት (Professional Skill) ላይ ያተኮረ ሲሆን በዚህም ‹‹Customer Service››፣ ‹‹Sales and Marketing››፣ ‹‹Finance and Accounting›› እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች የሚዳሰሱበትና ለአንድ ወር የሚቆይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ሥልጠናው ተማሪዎች በትምህርት ከሚያገኙት ዕውቀት በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት ቀጣሪ ድርጅቶች ከተቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀትና ከሂሎት የሚያስጨብጥና በሥራ ዓለም ተወዳዳሪና አሸናፊ እንዲሆኑ የሚስችሉ ግንዛቤዎችን የሚፈጥር እንደሆነም ታውቋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

04 Nov, 12:05


2ኛ ዙር የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ውድድር ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥራ ፈጠራና ልማት ማበልጸጊያ ማዕከል ‹‹SNV/RAYEE/›› ከተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር ሲያካሂዱት የቆዩት 2ኛ ዙር የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ውድድር ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ጥቅምት 22/2017 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ተ/ፕሮፌሰር በኃይሉ መርደኪዮስ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ ሥራዎችን ከማገዝ አንፃር ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን የማፍራትና የፋይንንስ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሥርዓት ለመፍጠር ትኩረት ያደረጉ ተግባርትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ም/ፕሬዝደንቱ በውድድሩ ለተሳተፉ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶቹ ተደጋግፎና ተያይዞ የማደግ ባህልን እንዲሁም ልምዳቸውን ለሌሎች የማካፈል ልማድን ማዳበር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የሥራ ፈጠራና ልማት ማበልጸጊያ ማዕከል የሥልጠና ክፍል ኃላፊ መ/ር አበበ ዘየደ በበኩላቸው ማዕከሉ በቢዝነስ ሃሳብ፣ በቢዝነስ ፕላን አዘገጃጀትና አቀራረብ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥልጠናዎችን ለጀማሪና በሥራ ላይ ለሚገኙ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ጀማሪ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታታትና መደገፍ ዘላቂነት ያለው የሥራ ፈጠራ ሥርዓተ-ምኅዳር ለመፍጠር ቁልፍ ሚና እንዳለውም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ከተማ የ ‹‹SNV/RAYEE/›› አስተባባሪ አቶ አብነት ጴጥሮስ በበኩላቸው ‹‹SNV/RAYEE/›› በኔዘርላንድ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር ያለ እና አስቀድሞ በበጎ ፈቃደኞች ስምሪት የተጀመረ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። እንደ አስተባባሪው ገላጻ ድርጅቱ በግብርና፣ ኢነርጂ እንዲሁም በውሃ ልማትና አካባቢ ንጽህና ላይ ትኩረት በመስጠት በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት መስኮች ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታታትና መደገፍ ድርጅቱ በትኩረት ከሚሰራባቸው መስኮች መካከል አንዱ እንደሆነም አቶ አብነት ጠቁመዋል፡፡

የዶሮ ጫጩት መፈልፈያ ማሽን እና የዶሮ ኩስን አድርቆ ለእንስሳት መኖ አገልግሎት መስጠትን ትኩረት ባደረጉ የቢዝነስ ሃሳቦች ተወዳድረው የ100,000 እና የ80,000 ብር አሸናፊ የሆኑት ወጣት በኃይሉ ዳንኤል እና ወጣት ፋሲካ ደስታ ከዩኒቨርሲቲውና ከድርጅቱ ያገኙት የሥልጠናና የገንዘብ ሽልማት ሃሳባቸውን ወደ ተግባር እንዲቀይሩና በሥራቸው መሻሻል እንዲሁም በኢኮኖሚ ደረጃም ይብለጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓቱ እንደተገለጸው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ ‹‹SNV/RAYEE/›› ጋር የፈጠሩት ጠንካራ ትስስር ጀማሪ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን በፋይናንስ በመደገፍና ምቹ የገበያ ትስስር ከመፍጠር አንጻር የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከቱ ተመላክቷል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

31 Oct, 14:41


ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች ሥልጠና እየተሰጠ ነው

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምርምርና ማኀበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባ ምንጭ ዲስትሪክት ጋር በመተባበር ከቅርንጫፉ ለተወጣጡ የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ከጥቅምት 21-23/2017 ዓ/ም የሚቆይ የሙያ ብቃት ማሻሻያ ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ሥልጠናው ንድፈ ሃሳብንና ተግባርን በማቀራረብ በሠራተኛውና በሥራው ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መቅረፍ፣ የባለሙያውን አቅም በማጎልበት ለማኅበረሰቡ ደረጃውን የጠበቀና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ ከኢንደስትሪው ጋር በትብብር የሚሠራቸውን የምርምር ሥራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል ነው።

ሥልጠናው “Transmission line Models”፣ “Electric Safety”፣ “Synchronization” እና “Load balancing” የሚሉ ዐበይት ርእሶችን ይዳስሳል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

31 Oct, 14:32


ሀገር አቀፍ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ወርክሾፕ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞችን በመገምገም በስያሜ ማስተካከያ የተዋሐዱ የፕሮግራሞች ሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ወርክሾፕ ከጥቅምት 19-20/2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞችና ሥርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያና የወርክሾፑ አስተባባሪ አቶ አድነው ኤርበሎ ከዚህ ቀደም በርካታ ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው የትምህርት ፕሮግራሞች የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥቷቸው በዩኒቨርሲቲዎች ሲተገበሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለሆነም በተለይ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተመራቂ ተማሪዎች ወደተለያዩ አካባቢዎች ለውድድር ሲሄዱ ገበያው ቅጥያ የሌለውና ቀጥተኛውን የትምህርት ዘርፍ በመፈለጉ ገበያውን መቀላቀል አዳጋች ሆኖባቸው መዝለቁን አስተባባሪው ጠቅሰዋል፡፡

እንደ አቶ አድነው ተማሪዎች በተደጋጋሚ ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሔ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ነባሩን የትምህርት ፕሮግራም መከለስ በማስፈለጉ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በየጊዜው እየከለሰ 151 የነበሩት ወደ 69 ዝቅ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከመካከላቸው ባጠቃላይ 60 የሚሆኑት ወደ አንድ ተመሳሳይ ይዘት መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
አስተባባሪው የተቀሩትን የትምህርት ፕሮግራሞች ሥራ ለማጠናቀቅ፣ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለውድድር ሄደው የሚያባክኑትን ጊዜና ገንዘብ እንዲሁም የመንግሥትን አላስፈላጊ ወጭ በመቀነስ የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በአጠቃላይ ሀገሪቱ የያዘችውን የልማት ዕቅዶች ለማሳካት እንዲቻል ወርክሾ ከፍተኛ አስተዋተጽኦ አለው ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እንደ ሀገር ከዚህ ቀደም ተቀራራቢ ይዘትና ስያሜ ያላቸው በርካታ ፕሮግራሞች በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አንድ እንዲመጡና እንዲቀንሱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ተመሳሳይ መስኮችን የማዋሐድ ሥራው በስያሜ እንጂ በሥርዓተ ትምህርት ደረጃ ባለመሠራቱ የተዋሐዱና የተጣጣሙ ፕሮግራሞች ሥርዓተ-ትምህርታቸውን በማስተካከል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን አጠናቆ ወደ ተግባር መገባት እንዳለበት ም/ፕሬዝደንቱ ጠቁመዋል፡፡

የአካዳሚክ ፕሮግራሞች፣ ግምገማና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሠረቀብርሃን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አስተናጋጅነት ከዚህ ቀደም ከተዋሐዱት 69 የትምህርት ፕሮግራሞች መካከል ለ60 ፕሮግራሞች ከስያሜ ባሻገር የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ተካሂዶ ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን በተቀሩት ዘጠኝ ፕሮግራሞች ላይ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳውን ለማጠናቀቅ ወርክሾፑን ማካሄድ ማስፈለጉን ገልጸዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

30 Oct, 07:40


ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸው የምርምር ሥራዎች የተቋሙን ዓለም አቀፋዊ እይታ እንዲጨምሩ ማስቻላቸው ተገለጸ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚያከናውናቸው ውጤታማ የምርምር ተግባራት የተቋሙን የዓለም አቀፍ እይታ እንዲጨምር ማስቻሉን የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝንት ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት በኃይሉ መርደኪዮስ (ተ/ባ ፕሮፌሰር) እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውጤታማነት የሚረጋገጠው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን በሚከናወኑ ምርምሮች የማኅበረሰቡን ችግር በዘላቂነት በመፍታትና ሀገራዊ የልማት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ የልማት አቅጣጫዎችና ተልእኮዎች ላይ ትኩረት በማድረግ እና ጠንካራ የኢንደስትሪ ትስስር በመፍጠር ውጤታማ ምርምሮችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለዚህም ም/ፕሬዝደንቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና በሌሎች እንሰት አብቃይ አካባቢዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የምግብ ዋስትና በዘላቂነት ማረጋገጥና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማሻሻል የሚያስችል ምርምርና የእንሰት ቴክኖሎጂዎች ፈጠራና ሽግግርን እንዲሁም የማዕድን አለኝታ ጥናቶችን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ም/ፕሬዝደንቱ ዩኒቨርሲቲውና ማኅበረሰቡ በፈጠሩት የጉድኝት እሳቤና የማኅበረሰቡን የመልማት ጥያቄ መሠረት በማድረግ በተለያዩ የገጠር ቀበሌያት በሚገኙ ት/ቤቶችና የጤና ተቋማት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግና የመብራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን አስመልክቶ በቂ መረጃ የሚሰጥ ድረ ገጽ ማበልጸግ በዩኒቨርሲቲው ከተከናወኑ ተግባራት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ተመራማሪዎችና የአካዳሚክ ክፍሉ በፈጠሩት ጠንካራ ጥምረት የተከናወኑ ውጤታማ የምርምር ተግባራት የዓለም አቀፍ እይታ እንዲጨምር ማስቻሉን የገለጹት ተ/ባ ፕሮፌሰር በኃይሉ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በተከናወኑ ውጤታማ የምርምር ፕሮጀክቶች ከ4,500 የአፍሪካ ተወዳዳሪዎች መካከል አሸናፊ መሆን ተችሏል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲው በእንሰት ፕሮጀክት የ380,000 ዩሮ ግራንት በቅርቡ አሸናፊ መሆኑን የጠቆሙት ም/ፕሬዝደንቱ በዚህም የዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የትብብር ፕሮጀክቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲሁም የኅትመት ውጤቶች እየጨመሩ መምጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የመሰል ተግባራት ሥራ በየጊዜው እያደገ መሄድና መጨመር የዩኒቨርሲቲውን ዓለም አቀፍ ዕይታን ከመጨመራቸው ባሻገር ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ያግዛሉ ብለዋል፡፡

የአውሮፓና የአፍሪካ ሕብረት፣ የጀርመኑ GIZ፣ የአማሪካን ልማት ተራድኦ ድርጅት፣ ክርስቲያን ኤይድ፣ ቤልጂየም ሀገር የሚገኙ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ አልባስተር ኢንተርናሽናል፣ የጆሞ ኬኔያታ የግብርና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ካንሳስ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ከሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

30 Oct, 06:57


የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲኖችና ፕሬዝደንቶች

Arba Minch University

29 Oct, 13:00


ሀገር አቀፍ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ወርክሾፕ እየተካሄደ ይገኛል


በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞችን በመገምገም በስያሜ ማስተካከያ የተዋሐዱ የፕሮግራሞች ሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ወርክሾፕ ከጥቅምት 19-20/2017 ዓ.ም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ስያሜ ያላቸው 151 የሚሆኑ የትምህርት ፕሮግራሞችን አጥፎ 69 እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር እየሠራ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ተመሳሳይ ስያሜ ያላቸውን በ9 ዘርፎች የተበታተኑ የተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ወጥነት ወዳለው ተመሳሳይ ስያሜ ለማምጣት ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡

በምክክር መድረኩ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከ26 ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የየዘርፍ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛል፡፡


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Arba Minch University

28 Oct, 13:32


ዕጩ ዶ/ር አስናቀው ሙሉዓለም የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ ተገመገመ

በአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ‹‹Water Resources & Irrigation Engineering›› ፋከልቲ በ ‹‹Ground Water Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር አስናቀው ሙሉዓለም የመመረቂያ ጽሑፍ ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጹሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር አስናቀው ሙሉዓለም የመጀመሪያ ዲግሪውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ‹‹ Water & Resource Engineering›› እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከጂማ ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹Hydraulic Engineering›› ያገኘ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጹሑፉን ‹‹Evaluation of Groundwater Potential and Quality in The Guna-Abay Watershed: Upper Abay (Blue Nile) Basin, Ethiopia›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር አስናቀው ሙሉዓለም ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-


ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት