ጋሜል Media @gamel_media Channel on Telegram

ጋሜል Media

@gamel_media


✍️ "ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው። ✍️
✍️ "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።" ✍️
✍️ "Gamel" means "God is wonderful beyond measure." ✍️
መዝሙረ ዳዊት (Psalm) 118÷7

Youtube - https://www.youtube.com/channel/UCHxwszkxLPFCFKAOf1WtaDw

ጋሜል Media (Amharic)

ጋሜል Media የምርጥ የመረጃችን ድምፅ፣ ምርጥ አስተያየቶችና የእናቴዎቹን አዝናኝ የግሩም ድንቅ ፍላጎት ያዳምጡ። ለምን ማመልከት እንደሆነ፣ ጋሜል በተመረጠው መልኩ የእግዚአብሔር ሊመረመር የሚቻል ግሩም ድንቅ ነው። የጋሜል ብሂል ግሩም፣ "ሥራውን እንዴት አስገኝታለው" የሚል አንድ መልእክት ነው። 'Gamel' ወይም "እግዚአብሔር በባኦቻው ግሩም እንዴት እንመሰረታለን" በአለም አቀፍ ነገር ይታይ። በነጻ የሥራው አካል ራሱን መረጠን በብሂል ግሩም ድንቅ በማነሳስ በመፅናናት፣ በማድረግ፣ በማስረጃ፣ እና በማሳል የተለያዩ ድንቅ ፍላጎችን ምርጥ መረጃዎችን በምሳሌ ሰጥቷል። የሚልኩትን በትክክለኛ መረጃ ውስጥ ያግዛሉ። ሐሰተኛ ከታማኝነት፣ እና አናንተው በበለጸ አጽናኝ የማንከለከል አስራር። ተጨማሪ እንችላሊ የግሩሙ ድንቅ ነው።

ጋሜል Media

29 Jan, 04:45


አስተርዮ ማርያም

በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡

የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡

እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡

ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡

ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት፣ ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡

የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!!!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

25 Jan, 14:55


ሊኖሩበት የሚገባ መርህ

በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ከብጽዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ንግግር የተሻለ መርህ ለማግኘት ከባድ ነው። ይህንን መርህ ሁላችንም ብንከተል እግዚአብሔር የሰጠንን መክሊት ተጠቅመን ያለምንበት መድረስ እንችላለን። የአባት ምክር እነሆ:-

"እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል፤ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያቢሎስ ሥራ ነው፡፡

በእርግጥ ሥራው እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡ የሐሜት ጐርፍ ያስወርድብሃል፡፡

ደራስያን እንዲጠይቁህ፥ እጅግ ስመ ጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡

ጲላጦስ፣ ሄሮድስ፣ ሐናንያ፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ፡፡
ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሠላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል፡፡
ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዘብ አትችልምን?

አንተ ግን ሥራህን ሥራ!

አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፣
የሰይጣንን ውሻዎች ለመውገር አትቁም፡፡
ጥንቸሎቹንም በማባረር ጊዜህን አታጥፋ፡፡

ሥራህን ሥራ!

ዋሾች ይዋሹ፣
ጠበኞች ይጣሉ፣
ማኀበሮችም ይወስኑ፣
ደራሲዎችም ይድረሱ፣
ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ፣
አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈጸም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ፡፡

ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክም፣
እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣
ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልነገረህም፣
ሰይጣንና አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅክም፤
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሰራ አትችልም።
ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለእግዚአብሔር አልሠራህም፡፡

ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን፤ ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ፣ ይጨቃጨቅ፣ ጥቃት ይድረስብህ
ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፣ ትቆስልና፣ ትናቅ ይሆናል፡፡
ኃይለኛ ያጐሳቁልህ፣ ወዳጆች ይተዉህ፣ ሰዎችም ይንቁህ ይሆናል፡፡

አንተ ግን በጸና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ጸንተህ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል!"

📝ብጽዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

@Gamel_Media

ጋሜል Media

23 Jan, 02:54


አብርሃምም ሸመገለ በዘመኑም አረጀ፤ እግዚአብሔርም አብርሃምን በሥራው ሁሉ ባረከው።

አብርሃምም ሎሌውን የቤቱን ሽማግሌ የከብቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦
"እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ተወላጆቼ ትሄዳለህ፥ ለልጄ ለይስሐቅም ሚስትን ትወስድለታለህ።"

ሎሌውም፦ ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ አገር ከእኔ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደ ሆነ ልጅህን ወደ ወጣህበት አገር ልመልሰውን? አለው።

አብርሃምም አለው፦
ልጄን ወደዚያ እንዳትመልስ ተጠንቀቅ፤
ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ ይህችንም ምድር እሰጥሃለሁ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።

ሴቲቱም ከአንተ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደ ሆነ ከዚህ ካቀረብሁህ መሐላ ንጹሕ ነህ፤ ልጄን ግን ወደዚያ አትመልሰው።
ሎሌውም ከጌታው ከአብርሃም ጭን በታች እጁን አደረገ፤ ስለዚሁም ነገር ማለለት።

ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል አሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ መስጴጦምያ ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።

ሲመሽም ሴቶች ውኃ ሊቀዱ በሚወጡበት ጊዜ ከከተማይቱ ውጪ በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ግመሎቹን አስበረከከ።

እንዲህም አለ፦

የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እለምንሃለሁ፤ መንገዴን ዛሬ በፊቴ አቅናልኝ፥ ለጌታዬም ለአብርሃም ምሕረትን አድርግ።

እነሆ፥ በዚህ የውኃ ምንጭ አጠገብ እኔ ቆሜአለሁ፥ የዚህችም ከተማ ሴቶች ልጆች ውኃውን ሊቀዱ ይመጣሉ፤

ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርስዋም፦ አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፥ እርስዋ ለባሪያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።

ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ፥ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፤ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት።

ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች፤ ወደ ምንጭም ወረደች እንስራዋንም ሞላች፥ ተመልሳም ወጣች።

ሎሌውም ሊገናኛት ሮጠና፦ ከእንስራሽ ጥቂት ውኃ ታጠጪኝ ዘንድ እለምንሻለሁ አላት።

እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ጠጣ አለችው፤ ፈጥናም እንስራዋን በእጅዋ አውርዳ አጠጣችው።
እርሱንም ካጠጣች በኋላ፦ ለግመሎችህ ደግሞ ሁሉም እስኪረኩ ድረስ ውኃ እቀዳለሁ አለች።

ፈጥናም ውኃውን ከእንስራዋ በማጠጫው ውስጥ ገለበጠችው፥ ደግሞም ልትቀዳ ወደ ጕድጓዱ ሮጠች፥ ለግመሎቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች።

ሰውዮውም ትክ ብሎ ይመለከታት ነበር፤ እግዚአብሔር መንገዱን አቅንቶለት እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ ለማወቅም ዝም አለ።

ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሰውዮው ግማሽ ሰቅል የሚመዘን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም አሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፤

እንዲህም አላት፦ አንቺ የማን ልጅ ነሽ? እስኪ ንገሪኝ፤ በአባትሽ ቤት የምናድርበት ስፍራ ይገኛልን?

አለችውም፦ እኔ ሚልካ ለናኮር የወለደችው የባቱኤል ልጅ ነኝ።

በእኛ ዘንድ ገለባና ገፈራ የሚበቃ ያህል አለ፥ ለማደሪያም ደግሞ ስፍራ አለን።

ሰውዮውም አጎነበሰ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገደ።

ዘፍጥረት 24÷1-26

ለባለ ትዳሮች መልካም ጋብቻ!

ላላገባችሁ እግዚአብሔር መልካም ሰው ይስጣችሁ!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

19 Jan, 17:42


ሠርግ በሰው ልጅ ሕይወት የሚፈጸም ልዩ ምሥጢር ነው። መድኃኔ ዓለም እና እናቱ አንዲት ዕለት በሙሽሮቹ ቤት ታድመው የቃና ዘገሊላው ድንቅ ተአምር ታየ ፤ የጎደለው ሞላ ፤ ያስጨነቃቸው ተፈታ ፤ ያላሰቡት ያልጠበቁት ተሰጣቸው ፤ የደስታው ጥሪ የደስታ ሆኖ ተደመደመ።

የእኛ ሕይወት ቃና ዘገሊላ ነው በክብር እናትና ልጁን ወደ ሕይወታችን ብንጠራቸው ፤ የጎደለው ይሞላል ፤ ያስጨነቀን ይፈታል ፤ ያላሰብነው ያልጠበቅነው ይሰጠናል።

አባ ጊዮርጊስ በሰዓታት ምስጋናው ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን "ቃልኪ መናዝዝ(ቃልሽ የሚያጽናና ነው) ገጽሽ ጨለማን የሚያርቅ መብራት ነው ፤ እንደ ቀን ዘወትር ያበራል ፤ ልጅሽም ማጣትን የሚያስረሳ በረከት ነው" ይላታል።

+ እናቱና ልጁን አክብረን የምንጠራቸው አንድ ዕለት እንዲታደሙ ሳይሆን እስከ መጨረሻው በእኛ ሕይወት እንዲኖሩ ቢሆን ደግሞ ፤ ሕይወታችን ምን ሊመስል ይችል ይሆን? ምን አይነት ድንቅ ይታይበት ይሆን? ለምን ያህል ዘመናት በትውልድ የሚነገር የሚታወስ ይሆን?

+ ድንግል ሆይ! በእምነትም በእውቀትም የጎደልን ልጆችሽን ፤ አምላከ ብርሃን የተባለ የእውቀት የእምነት ባለቤት ልጅሽ በእምነትና በእውቀት እንዲሞላን አሳስቢልን! ልጅሽ የሕሊናችንን ጨለማነት አርቆ ተናግረን የምንደመጥ ለቀመሱን እርሱ የሚመሰገንብን በጎ ባሪያዎቹ ያድርገን።

መልካም የቃና ዘገሊላ በዓል ይሁንልን!
ጥር 12 2017 ዓ.ም
https://t.me/Gamel_Media

ጋሜል Media

18 Jan, 19:10


#ታቦት_ ለምን_ ተከትለን_እንሄዳለን?

"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት።"
ኢያ 3÷3

@Gamel_Media

ጋሜል Media

17 Jan, 20:09


ጋሜል Media pinned «#ከተራ #ከተራ ምን ማለት ነው? ከተራ 'ከበበ' ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ትርጓሜውም ውኃ መገደብ ማለት ነው፡፡ በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር በየአጥቢያው የሚገኙ ሰዎች ተሰብስበው በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ይጥላሉ፡፡ በጥር 11 ለሚኖረውም የጥምቀት ሥነ-ስርዓት ጉድጓድ እየቆፈሩ ውኃው እንዳይሄድ…»

ጋሜል Media

14 Jan, 19:51


እንኳን አደረሳችሁ!
ጥር 7 2017ዓ.ም

@Gamel_Media

ጋሜል Media

13 Jan, 17:28


ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።”

ሉቃስ 2፥21


¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
መልአኩም እንዲህ አላት፦

ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።

እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ

ሉቃስ 1÷30

እንኳን አደረሳችሁ!

ይህ ቀን (ጥር-6) አምላካችን ከስም ሁሉ በላይ በሆነው ፍጥረት ሁሉ በሚሰግዱለት ስም የተጠራበት ዕለት ነው።


በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤

ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

ፊልጵስዩስ 2፥9-11

@Gamel_Media

ጋሜል Media

11 Jan, 04:46


@Gamel_Media

ጋሜል Media

08 Jan, 18:20


🕯🕯

የጌታችን ልደት በአበው

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “የቅድስና ኹሉ ሰጭ ወደዚህ ዓለም የገባው በንጹሑ ልደት በኩል ነው። የቀደመው አዳም ከድንግል መሬት ተገኘ፤ ከእርሱም ያለ ሴት ዕርዳታ ሴት ተገኘች። ልክ አዳም ያለ ሴት ሴትን እንዳስገኘ፤ ድንግልም ያለ ወንድ በዚህ ዕለት ወንድን አስገኘች። ስለዚህ ሴቶች ለወንዶች ዕዳቸውን ከፈሉ፤ አዳም ብቻውን ሔዋንን እንዳስገኘ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። አዳም ያለ ሴት ሴትን ስላስገኘ ሊኩራራ አይገባም፤ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። በምሥጢሩ ተመሳሳይነት የተፈጥሮው ተመሳሳይነት ተረጋገጠ። ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወሰደ ነገር ግን አዳም ጉድለት አልተገኘበትም÷ በተመሳሳይ ከድንግል ወንድ ልጅ ተወለደ ድንግልናዋ ግን አልተለወጠም” እያለ በሚያስደንቅ መንገድ የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልናን በአዳም ኅቱመ ጎን በኩል ያሳየናል”። ይህ የልደት ቀን የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከማሳየቱም አልፎ ሴቶችን እንዴት እንደካሰቻቸው ፍንትው አድርጎ ያመለክተናል። የጌታችን የልደት ዕለት ማለት የሴቶች ክብር የተገለጠበትና ወንድና ሴት እኩል መኾናቸው የተረጋገጠበት ዕለት ነው። “ሴቶች ሆይ የሴትነትን ክብር ያስመለሰችላችሁን ቅድስት ድንግል ማርያምን ትረሷት ይኾንን?”። ድንግል በድንግልና ወለደች ሲባል ሰምተን እንዳንደናገጥና ወደ ጥርጣሬ ባሕር ውስጥ እንዳንገባ አስቀድሞ አዳም ብቻውን ሔዋንን ሲያስገኝ ያለውን ነገር በመጽሐፍ አጻፈልን። አዳም ሔዋንን ብቻውን ከጎኑ እንዳስገኘ አምኖ የተቀበለ ሰው እንዴት ድንግል ማርያም በድንግልና ወለደች ሲባል ለማመን ይከብደው ይኾን? በጣም የሚያስገርመው ሔዋን ከአዳም ጎን ብትወጣም ለአዳም ውድቀትም ምክንያት ኾና ነበር፤ ድንግል የወለደችው ግን ዓለምን በሙሉ የሚያድን አምላክ ነው።

🕯🕯
በዓለምም ከዓለም ውጭ ያለው ጌታ በቤተልሔም የታየበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ሲባል አጥርተው ማየት በማይችሉ ዘንድ ውስን ብቻ የሚመስል÷ ነገር ግን በቅድስና መስታወት ለሚያዩት በአርያምም እየተመሰገነ በቤተልሔም የተወለደበት ዕለት ነው። ሰይጣን የደነገጠበትና ኃይሉ የደከመበት ዕለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በልደቱ ስፍራ መኾን አጋንንትን እንዳይቀርቡን ያደርጋል እልፍ አእላፋት መላእክት በዚያ ከበው ይጠብቁናልና። ተፈጥሮአዊውን ሕግ የገለበጠው ጌታ የተፈጥሮን ሕግ የሠራውና እንደፈቃዱም የሚያደርገው እርሱ መኾኑን ያወቅንበት ዕለት ነው። እንኳን በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!

📚ትምህርተ ጽድቅ
📝ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

🕯🕯

ጋሜል Media

04 Jan, 05:33


🗣 የበግ ቆዳ ያለው?

ለገና በዓል በቤትዎ ወይም በአካባቢዎ ከሚከናወኑ እርዶች የበግ እና የፍየል ቆዳን ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ፣ ትውፊት እና ታሪክ ያስቀጥሉ።

የመቀበያ ቦታዎች ፦

📍ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት
📍ሰአሊተ ምሕረት
📍አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት
📍መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል
📍ጀሞ መድኃኔዓለም
📍ገላን ልደታ ለማርያም


ለበለጠ መረጃ፦

09 66 76 76 76
09 44 24 00 00
09 09 44 44 55
09 44 17 61 26

https://t.me/Hamerebirhan

ጋሜል Media

03 Jan, 07:05


እግዚአብሔር ለቅዱስ ዳዊት የሰጠውን ሰባቱን  ሀብታት ያውቁ ኖሯል?

፩) ሀብተ ኃይል:-
አንበሳና ድብ በጡጫ መትቶ መግደል ነው። [፩ሳሙ. ፲፯:-፴፬]

፪) ሀብተ መዊዕ:-
የጠላትን ጦር በተሰለፈበት ፣ የጦር አለቆቹም በሰፈሩበት ገብቶ የጦሩን መሪ መግደል። [፩ሳሙ.፲፰]

፫) ሀብተ በገና:-
እንጨቱን ጠርቦ፣ ቁርበቱን ገልቦ፣ ጅማቱን ወጥሮ መደርደር።  [፩ሳሙ ፲፮]

፬) ሀብተ ፈውስ:-
በመዝሙርና በበገና ድውያን፣ ሕሙማንን መፈወስና ጭንቀትን ማስወገድ።  [፩ሳሙ.፲፮÷፳፫]

፭) ሀብተ መንግሥት:-
እስራኤልን አንድ አድርጎ መግዛት ነው።

፮) ሀብተ ክህነት:-
በስብሐተ ክህነት እግዚአብሔርን ማመስገን።

፯) ሀብተ ትንቢት:-
"ናሁ ሰማእናሁ በኤፍራታ" [መዝ.፻፴፩÷፮]  ብሎ ልደቱን፣
"ዮርዳኖስኒ ገብአ ድህሬሁ" [መዝ.፻፲፫] ብሎ ጥምቀቱን፣
"ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ" [መዝ ፳፩÷፲፮] ብሎ ስቅለቱን፣
"ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም" [መዝ.፸፯] ብሎ ትንሣኤውን

አስቀድሞ የተናገረ ታላቅ ነቢይ ነውና።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

29 Dec, 10:06


ህይወተ ወራዙት 1

ጋሜል Media

28 Dec, 07:19


እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሰን!

አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን እንዲሁም ዳንኤልን የረዳ መልአክ እኛንም ይርዳን፣ ይባርከን፣ ከኃጢአት በቀር የልቦናችንን ፍላጎት ይፈጽምልን!

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።”

መዝሙር 34፥7

@Gamel_Media

ጋሜል Media

25 Dec, 09:23


ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አግናጢዮስ ኤፍሬም በተገኙበት በሶርያ ደማስቆ በሚገኘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ተከበረ !



ታኅሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

@Gamel_Media

ጋሜል Media

22 Dec, 18:16


<<እመቦ ዘወድቀ በኃጢኣት ኢይርሳዕ እስመ ዘኢይትረሳዕ>>

<<በኃጢኣት የወደቀ ሰው ቢኖር አይርሳ የማይረሳ ነውና>>


ቅዳሴ እግዚእ

@Gamel_Media

ጋሜል Media

22 Dec, 01:50


እንኳን ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

21 Dec, 08:09


በቃሽ በለኝ

ስንቴ ሸፈትኩ ከቤት ወጣሁ፣
ስንቴ ካድኩህ ስንቴ ጠፋሁ።

ተዛነፍኩኝ ከመንገዴ እርምጃዬ ተታለለ፣
የዓለምን ምቾት ሲያስብ ልቤ ለሁለት ተከፈለ።

የኃጢአት ቀንበር ተሸክሜ ስንት ዘመን ደም ፈሰሰኝ?
ከሕመሜ እንድፈወስ ቀሚስህ ስር ማን ያድርሰኝ?

እንዴት ልቅረብ እንዴት ልንካህ?
በምን ልይህ እንዴት ልጥራህ?
አቅም አጣሁ ሳየው ነውሬን፣
በየት በኩል ልዘርጋ እጄን?

አውቅሀለው ትምራለህ፣
አምንሃለው ታድናለህ።

አፍሬ እንጂ ማጎንበሴ ተዘቅዝቄ የማነባው፣
አይቻለው ያን ወንበዴ ቀድመህ ገነት ስታስገባው።

አውቅሀለው

እንኳን መጥተህ እንኳን ዳብሰህ፣
በቃል ብቻ ታድናለህ።

እንደ መቅደላዊት ሰብሬ ሽቶዬን
ባልዳብሰው እንኳን በእንባዬ እግሮችህን

የዘመናት በደል
ሸክሜ እንዲቀልልኝ
ልንካው ቀሚስህን?

አትንቅም ፍጥረትህን እልፍ ኃጢአቱ ቢገለጥም፣
በደል ሞልቶ ቢትረፈረፍ ከምሕረትህ ከቶ አይበልጥም።

እንዴት ልጥራህ መድኃኒቴ?

ናልኝ አልል ዳብሰኝ አልል እድፍ ልቤን ላጨቀየው
ምነው ላንዴ እድል ቀንቶኝ ቀሚስህ ስር በተገኘው

አውቅሀለው ትምራለህ
አምንሃለው ይቅር ባይ ነህ

አሁንም ማረኝ

በክፉ ሀሳብ ተተብትቤ እየወደቅኩ አልቸገር
የኃጢአት ደሜን ተሸክሜ ሌላ ዘመን አልሻገር

ስንቴ ሸፈትኩ ከቤት ወጣሁ
ስንቴ ካድኩህ ስንቴ ጠፋሁ

ማረኝ አንተ

በአጉል ምቾት እየተሳብኩ የዓለም ገመድ አይጥለፈኝ
ለአንዴ በቃሽ በለኝና ከድካሜ አሳርፈኝ

ይቅር በለኝ🙏

© ታደሉ ተረፈ(ሂያብ)

@Gamel_Media

ጋሜል Media

18 Dec, 06:27


ወዳጆቼ ሆይ
«ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ
ሚያሳፍር ነገርም
የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና።»
(ኤፌ. 4፥29፣ ኤፌ. 5፥4)

እንዲህ ካሉ ከንቱ ንግግሮችና ተራ አባባሎች ራሳችንን እናርቅ።
እንደዚህ ያሉትን አባባሎች እኛ አለማለት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሲሏቸው ብንሰማም ዝም እንዲሉ እንንገራቸው
።በብርቱ እየተቃወምናቸውም አሳፋሪ አንደበታቸውን እንዲገቱ እናድርጋቸው፡፡

@Gamel_Media

ጋሜል Media

15 Dec, 07:24


እንኳን አደረሳችሁ።
🙏🙏🙏

ጋሜል Media

12 Dec, 03:18


          ።።።።   እንኳን አደረሳሽሁ።፡።።።።

እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት (በዓታ ለማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ) ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

10 Dec, 20:11


✍️ አንድ አንድ ሰዎች በጾም ወቅት የሚሰሯቸው ስሕተቶች

- ጸበል ጠጥቶ መጾም ይቻላል ብሎ መተግበር።

- ካላስቀደስኩ አልጾምም ማለት።

- ጾም በመጣ ቁጥር ዓሳ ይበላል ወይስ አይበላም የሚል ክርክር።
የሚገርመው ደግሞ የሚከራከሩት ሰዎች የበሬውንም ሥጋ የሚጾሙ አለመሆናቸው ነው።

1ኛ ቆሮ 15÷39 ነገር ግን ሥጋ ሁሉ አንድ አይደለም!

- በሥራ ምክንያት ስለሚደክመኝ አልጾምም ማለት።

ቅዱስ ጳውሎስ ግን ረሃብን እና ጾምን ይለያቸዋል።

በድካምና በጥረት
ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት
በራብና በጥም
ብዙ ጊዜም በመጦም
በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።
2ኛ ቆሮ 11፥27

ስለዚህ መራብ እና መጾም ይለያያልና ስለምራብ መጾም አያስፈልገኝም አይባልም።

ማስታወሻ:

- ነፍሰ ጡር፣ አራስ እና በንስሃ አባት የተፈቀደላቸው ሕመምተኞች መመገብ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሌላውን እንዳያሰናክሉ በአደባባይ እየታዩ መሆን የለበትም።

- የጾም ሰዓትን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን የምታዝዘው ቢያንስ ቢያንስ እስከ ቅዳሴ ማለቅያ ነው፤ አቅም ያለው ሰው ግን ሌላውን ሳይነቅፍ ለራሱ አብዝቶ መጾም ይችላል።

አቅመ ደካማ እና ሕጻናትም እንደ አቅማቸው ይጹሙ!

- በጾም ወቅት የባል እና የሚስት ተራክቦ ይቻላል ወይ? ለሚለው

ግንኙነት መፈጸሙን ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር እና መገዛት እንዲገልጡበት ሲባል ተፈቃቅደው በጾም ወቅት መታቀብ ይገባል።

ጾሙ ሲፈታ ይደረስብታል!

በአጠቃላይ......

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጾም ይናገራል ሥርዓቱ ግን በሥርዓት መጻሕፍት ነው የተቀመጠው።

ማለትም ቅዱስ መጽሐፍ "ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው!" ይላል እንጂ
ምን ተብሎ ይጸለይ?
እንዴትስ ሆኖ ሕብስቱ እና ወይኑ ሥጋ እና ደም ይሆናል?
የሚለው ዝርዝር ጉዳይ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ እንደሌለ ማለት ነው።

ይቆየን!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

09 Dec, 11:17


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምድረ ቻይና የመጀመሪያዋን ደብር በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወነች።

የእንግሊዝ፣ አየርላንድ፣ ሩቅ ምሥራቅና አካባቢው አህጉራተ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቻይና ምድር የመጀመርያዋን ቤተ ክርስቲያን ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ብለው በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈጸም ምእምናንን አቁርበዋል።

በዕለቱም አንዲት በሌላ ሃይማኖት ትኖር የነበረችን እህት እና ሕፃን በማጥመቅ የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ ያደረጉ ሲሆን በቻይና የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆን ሾመዋል።

በተጨማሪም ከቻይና የተለያዩ ክፍላተ ግዛት የተሰባሰቡ ምእመናን፣ ቻይናውያን እና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው ተሳትፈዋል፡፡

የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት

ጋሜል Media

04 Dec, 11:31


#መድኃኔዓለም

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

1. የእርጋታ መምህር ነው።

ከእርጋታው የተነሣ "የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤስን የጧፍ ክርም አያጠፋም" ተብሏል (ማቴ.12፥20)።

2. የትሕትና መምህር ነው

"ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።" (ማቴ.11፥29)

3. የይቅርታ መምህር ነው።

በመስቀል ተሰቅሎ ይቅርታን ለሰው ልጅ ያደለ እርሱ ነው።
"ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።" እንዲል (ሉቃ.23፥34)።

4. የሰላም፣ የፍቅር፣ የትዕግሥት፣ የሰማዕትነት በጠቅላላው የመልካም ሥራዎች ሁሉ መምህር እርሱ ነው።

እርሱን ሁልጊዜ ማሰብ ለነፍስ ዕረፍት ነው። እኛም ዋና አብነታችን እርሱ ስለሆነ መልካም ሥራዎችን ሁሉ አባታችንን እርሱን መስለን እንሥራ።

እንኳን አደረሳችሁ
@Gamel_Media

ጋሜል Media

23 Nov, 22:09


እንግዲያስ ስንጾም

👉 ድኻውን እንደ አቅማችን እየረዳን

👉 ከተጣላነውን ሰው ጋር ፈጥነን በመታረቅ

👉 በባልጀራችን ላይ ሳንቀና በመዋደድ እና በመከባበር።

👉 ቆነጃጅት በመንገድ ሲያልፉ ስናይ በዝሙት ዓይን ባለመመልከት።

እንዲህ እንዲህ እያልን ከፍ እንላለን።

በሌላ አገላለጽ

👉 አፋችሁ ብቻ ሳይሆን ዐይናችን፣ እግራች፣ እጃችን፣ በአጠቃላይ የሰውነታችን ሕዋሳቶች በሙሉ መጾም አለባቸው፡፡

       + እጆቻችን ከመስረቅ እና የእኛ ያልሆነውን ከመውሰድ ይጹሙ!

       + እግሮቻችን የኃጢአት ሥራን ለመፈፀም ከመጓዝ ይጹሙ!

       + ዐይኖቻችን ውጫዊ በሆነ ውበት ምክንያት ከመቅበዝበዝ ይጹሙ!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

23 Nov, 22:09


✍️ ጾም መድኃኒት ነውና ጥቅም ለማግኘው አወሳሰዱን በትክክል ማወቅ ግድ ነው።

አንድ መድኃኒት የሚወስድ ሰው

👉 መድኃኒት የሚወስድ በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደሆነ
👉 ለምን ዓይነት በሽታ እንደሚጠቅም
👉 ከመድኃኒቱ ጋር የሚኼዱ እና የማይኼዱ ምግቦች ምን ምን እንደሆኑ
👉 እንዲሁም ከመድኃኒቱ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡

እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስድ ሰው ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝንበታል።

አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የሥጋ ህመም መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው እንደሚያስፈልግ ሁሉ ከነፍሳችን ደዌ እና በአእምሮአችን ውስጥ ካሉ ቁስሎች ለመፈወስ ብለን ለምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡

@Gamel_Media

ጋሜል Media

23 Nov, 14:46


✍️ በከንቱ እንዳንደክም መጾም እንደሚገባን እንጹም።

በመጾም እየደከምን ሳለ የጾምን አክሊል ካላገኘን፥ እንዴትና በምን ዓይነት አኳኋን ይህን ልንፈጽመው እንደሚገባው ልንረዳ ያስፈልጋል።

ፈሪሳዊዉም ጾሞ ነበር

ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤቱ የሄደው ባዶ እጁንና የጾሙን ፍሬ ሳያገኝ ነው።
ሉቃ.18፡12

ቀራጩ ደግሞ አልጾመም ነበር

ነገር ግን ከጾመው ፈሪሳዊ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እርሱ ነው።

ይህም የኾነበት ምክንያት

👉 ቀራጩ ባይጾምም ተጠቀመ፤ ለመጪው ሕይወቱም ጾም አላስፈለገውም ለማለት ሳይኾን ከኃጢአት ተከልክለው ካልጾሙት በቀር ጾም ብቻውን ጥቅም እንደሌለው እና ትሕትና አስፈላጊ መኾኑን ለማሳወቅ ነው።

የነነዌ ሰዎች ጾመዋል፤ የእግዚአብሔር ምሕረትንም አግኝተዋል።
ት.ዮና 3÷10

እስራኤላውያንም ጾመው ነበር፤ ነገር ግን እያጉረመረሙ ተመለሱ እንጂ በመጾማቸው አንዳች ጠቀሜታን አላገኙም።
ኢሳ 58÷3-7
1ኛ ቆሮ 9÷26

ስለዚህ እንዴት መጾም እንዳለብን ማወቅ ያስፈልጋል።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

23 Nov, 13:59


ከህዳር 15 (እሑድ) ጀምሮ የገና ጾም (የነቢያት ጾም) ይጾማል።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

21 Nov, 10:31


ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል" ዳን 12፥1።

ቅዱስ ሚካኤል ለእኛም ይቁምልን።

መልካም በዓል ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

12 Nov, 16:26


የጥበበኛ ነፍስ መገለጫዋ ይሄ ነውና ሁል ጊዜ የምታመሰግኑ ሁኑ።

👉 ክፉ ደረሰባችሁን?

ይህስ እናንተ ከፈቀዳችሁ ክፉ አይደለም።

ሁል ጊዜ አመስግኑ፤ ክፉ የሆነባችሁም መልካም ይሆንላችኋል።

ከተወደደው ኢዮብ ጋር ሆናችሁ “የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።” እያላችሁ አመስግኑ። /ኢዮብ ም1፥21/፡

እስኪ ንገሩኝ! ደረሰብኝ የምትሉት ክፉ ነገር ምንድነው?

👉 በሽታ ነውን?

ታድያ ይሄ እኮ አዲስ ነገር አይደለም።
ምክንያቱም ሥጋችን ሟች እና ለስቃይ የተጋለጠ ነውና።

👉ሀብት ንብረት ማግኘት አለብኝ የሚል መሻት ነውን?

ታድያ ይሄ እኮ ማግኘት የሚቻል ነው፤ ካገኙት በኋላ ግን መልሶ የሚጠፋና በዚህ ዓለም ብቻ የሚቀር ነው።

👉 ከወንድሞች የሚደርስ ሐሜትና የሐሰት ወቀሳ ነውን?

ታድያ ተጐጂዎቹኮ የሚያሙንና በሐሰት የሚመሰክሩብን እንጂ እኛ አይደለንም።

“ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች!” እንደተባለ ተጐጂዎቹ ይህን ኃጢአት የሚሠሩት እንጂ እኛ አይደለንም። /ሕዝ ም18፥4/

ተጐጂው ምንም በደል ሳይኖርበት ክፉ የሚደርስበት ሰው ሳይሆን ክፉ የሚያደርሰው ሰው ነው።

ስለዚህ በዚህ ሟች በሆነ ሰው ልትቈጡ አይገባም፤ ከዚያ ይልቅ ከሞት ይድን ዘንድ ልትጸልዩለት ይገባል፡፡

ንብ መቼ እንደምትሞት አይታችሁ ታውቃላችሁን?

👉 የምትሞተው ሌላውን ስትናደፍ ነው።

እግዚአብሔር በዚህች ፍጥረት በወንድሞቻችን ላይ ልንቈጣ እንዳይገባን ያስተምረናል።

እኛ የምንቈጣ (የምንናደፍ) ከሆነ ግን ቀድመን የምንሞተው እኛው ነን።

ስንቈጣቸው የጐዳናቸው ይመስለን ይሆናል፤ ነገር ግን እንደዚያች ንብ ተጐጂዎቹ እኛው ነን፡፡”

@Gamel_Media

ጋሜል Media

10 Nov, 07:39


ተመስገን! 🙏

ጋሜል Media

09 Nov, 10:41


ማህሌተ ጽጌ

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤
ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤
ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤
ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤
ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡

👉ትርጉም

እጅግ ብዙ የማያልቅ ምስጋናሽን እያመሰገንኩኝ : የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በስዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም : ማርያም ተዓምርሽ እንዳስረዳ ስምሽን መጥራት የወደቀን ያነሳል : ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ።

👉ምስጢር

የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም ማለቱ ከመስከረም 26 - ኅዳር 5 የቆየው የጽጌ ወቅት ቢያልፍም እኔ ግን ምስጋናሽን አላቋርጥም ይላል የዚህ ክፍል ጥንተ ነገሩ ዘካርያስ የሚባል ሰው የእመቤታችንን ሥዕል ያገኛል ፤ በጣም ተደሰተ ፤ የእመቤታችን ፍቅር አደረበትና ምን ላድርግላት ብሎ ተጨነቀ ።

ወቅቱ የጽጌ ነበርና እለት እለት 50 አበባ ለሥዕሏ አደርጋለሁ አለ ። እንዳለውም በየቀኑ ሀምሳ ጽጌሬዳ እየቆረጠ ለሥዕሏ ያደርግ ነበር ። በኋላ የአበባ ጊዜ ሲያልፍ አበቦችን ማግኘት ስለማይችል ምን ላድርግ ብሎ አሰበ ፤ በአበቦቹ ፈንታ ሀምሳ ጊዜ በሰላመ ቅዱስን አደርሳለሁ ብሎ ማድረስ ጀመረ ።

ከእለታት በአንዱ ቀን ወደ ሌላ ሀገር ሲሄድ መንገድ ላይ ሽፍታዎቹ አግኝተውት እርሱ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ እያለ ይጸልያል ፤ እመቤታችን ለሽፍቶች ተገልጣ አንድ በሰላመ ቅዱስ ሲል አንድ አበባ ስትቀበል ይመለከታሉ ፤ ሀምሳውን ሲጨርስ ሀምሳ አበባ ።

የዚህን ጊዜ ሽፍታዎቹ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱለት ፤ በኋላም አምነው መነኮሳት ሆነዋል ። እናም ይህ የጽጌ ምሥጋና ቢያልቅም የእመቤታችን ምሥጋና እንደማይቋረጥ ሲገልጽ ነው ፤ በውዳሴ ማርያም ፣ አርጋኖን ፣ ማኅሌት ፣ ሰዓታቱ ትመሰገናለችና ።

ስምሽን መጥራት የወደቀን ያነሣል ማለቱ አንድ እመቤታችን የሚወድ ሰው ነበር ፤ ከተወደደ ልጇ ጋር ሥዕሏን ስሎ በመሰላል ወጥቶ ዲያቢሎስ በሲኦል ነፍሳትን መከራ ሲያጸናባቸው እየሣለ እያለ ዲያቢሎስ ተናድዶ መሰላሉን መትቶ ሊጥለው ወደ ታች ሊወድቅ ሲሄድ ከሳላት ሥዕል የእመቤታችን እጅ ወጥቶ ይዞ አድኖታል ።

ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ሲል በቃልኪዳኗ ልጄ ወዳጄ ማርልኝ ብላ ስትለምን ስለ እናትነቷ ይምራልና ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ብሏል ።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

05 Nov, 18:27


በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለው ዓርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር አባቶቻችን ሥርዓት ሠርተዋል፡፡

መጋቢት 27 ቀን በዓቢይ ጾም ላይ ስለሚውል በዓቢይ ጾም ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ በደስታ እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታልናለች።

ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ

👉 ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤
👉 ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤
👉 በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፡፡
እንዳለ።

መጋቢት 27 ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ

👉 ፀሐይ ጨልማለች
👉 ጨረቃ ደም ሆናለች
ከዋክብት ረግፈዋል

👉 በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀዷል፤
👉 ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤
👉 መቃብራት ተከፍተዋል፤ ሙታን ተነሥተዋል፡፡

ስቅለቱን በዲሜጥሮስ ቀመር አውጥተን የጌታን መከራውን አስበን በስግደት ሕማማቱን እናስባለን በዝክረ ጥንተ ስቅለቱ በጥቅምት 27 ደግሞ በመስቀል የተደረገልንን አስበን እናመሰግነዋለን፡፡

የመድኃኔዓለም ይቅርታውና ቸርነቱ ሁላችንንም ይጠብቀን!
አሜን!

እንኳን ለክብረ በዓሉ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡

@Gamel_Media

ጋሜል Media

27 Oct, 07:07


እንኳን ለሊቀ ዲያቆናት እና ለቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ የሹመት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም ይገብር መንክረ፣

እንዘ ፃዕረ ሞት ያረስዕ ወያስተጥዕም መሪረ፣

በመዓዛ ጽጌኪሰ ለዘበዓውደ ስምዕ ስክረ፣

ውግረተ አዕባን ይመስሎ ኀሠረ፣

እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ፡፡

ማርያም  ሆይ የፍቅርሽ ተአምር የሞት ጣርን  አስረስቶ፣ መራራውንም አጣፍጦ ድንቅ ተአምርን ያደርጋል

በልጅሽ መዓዛ (ከልጅሽ መዓዛ የተነሣ) በሰማዕትነት አደባባይ ለተመሰጠ ሰው፣ በድንጋይ መወገር ገለባንእሳትም የቀዘቀዘ የባሕር ውሃን ይመስለዋል፡፡

ሰማዕቱ እስጢፋኖስ፣ ከ7ቱ አገልጋይ ዲያቆናት አንዱ ሆኖ፣ ጥቅምት 17 ቀን የተሾመና ከጌታ ዕርገት በኋላ 2 ዓመት ክርስትናን አስተምሮ በተወለደባት ጥር 1 ቀን በ35 ዓ.ም በወጣትነት እድሜው ከጌታ ቀጥሎ፣ ከሐዋርያት ቀድሞ ሰማዕትነትን የተቀበለና በኢየሩሳሌም  የክርስቶስ የመጀመሪያው ሰማዕት ነው፣

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 7

እስጢፋኖስ ማለት፣ በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

27 Oct, 06:54


ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤

ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤

ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል።

ስለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት፤

ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።

ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤

በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

ከራሳችሁም አንዲት ጠጉር ስንኳ አትጠፋም፤

በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ።

ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ።

የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፥ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ፤

የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና።

በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤

በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።

ሉቃስ 21÷12

@Gamel_Media

ጋሜል Media

25 Oct, 04:39


በትግራይ ክልል የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት የራሳቸውን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ገለጹ

በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ያቋቋሙት “መንበረ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት” ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ” በሚል መቋቋሙን አስታወቀ።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ላይ ጉዳይ ላይ እስከ አኹን የተባለ ነገር የለም። ኾኖም ቤተ ክርስቲያኒቱ በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቻቸው መግለጫዎች ግን፥ እንቅስቃሴው ቀናኖውን የሚፃረር ሕገ ወጥ እንደኾነ አውግዛ፣ “አንድ መንበር አንድ ሲኖዶስ እና አንድ ፓትርያርክ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ እና ቀኖና ሊከበር እንደሚገባው በአጽንዖት አሳስባ ነበር።

ዘገባው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ነው።
@Gamel_Media

ጋሜል Media

23 Oct, 19:01


ጥቅምት 14

የነገሥታት ልጅ የሆኑት አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት፤

ሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ 30 ዓመት ተጋድሎ ያረፈበት፤

ከ72ቱ አርድዕት አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ያረፈበት፤

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ የሚታሰብበት ዕለት ነው።

ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያካፍለን!

መልካም በዓል!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

22 Oct, 03:11


በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል

ዳንኤል 12፥1

በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥”

ራእይ 12፥7

ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁከክብሩም የተነሣ ምድር በራች

ራእይ 18፥1

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

16 Oct, 14:56


ማንም፦
እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው።

ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

1ኛ ዮሐንስ 4÷20

@Gamel_Media

ጋሜል Media

11 Oct, 20:19


#የያዕቆብ_ሌሊት ያድርግልን ማለት ምን ማለት ነው?
            
    በመጀመሪያ ያዕቆብ ማነው?

ቅዱስ ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ ማለትም የአባታችን የአብርሃም የልጅ ልጅ ነው።

የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ርብቃን አገባ ርብቃም መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራትምና አባታችን ይስሐቅ ስለ ሚስቱ እግዚአብሔርን ለመነ እግዚአብሔርም ተለመነው ርብቃ ሚስቱም ፀነሰች።

ልጆቹም በሆዷ ውስጥ ይገፋፉ ነበር ርሷም እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች።

እግዚአብሔርም እንዲህ አላት ሁለት ወገኖች በማህፀንሽ ናቸው ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።

ትወልድ ዘንድ ዘመኗ በተፈፀመ ጊዜም እነሆ በማህፀኗ #መንታ ነበሩ።

በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ ሁለንተናውም ጠጉር ለብሶ ነበር ስሙም #ዔሳው ተባለ።

ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር ስሙም #ያዕቆብ ተባለ።

አባታቸው ይስሐቅም ዔሳውን ይወድደው ነበር
እናታቸው ርብቃ ግን ያዕቆብን አብልጣ ትወደው ነበር።

ስለዚህም አባታቸው ይስሐቅ በሸመገለ ጊዜ በጣም አርጅቶ ነበርና ለሚወደው ልጁ ሊባርከው (ሊመርቀው) አሰበ።
ነገር ግን እናታቸው ርብቃ የዔሳውን ምርቃን ለያዕቆብ በመምከር የዔሳውን በረከት አስወሰደችበት።

ዔሳውም በጣም ተናዶ ወንድሙ ያዕቆብን ለመግደል ወሰነ በረከቱን ወስዶበታልና።

እናቱ ርብቃም ይህ የታላቁ ልጇ የዔሳውን ቃል ደረሰላት ታናሹንም ልጇን ያዕቆብንም አስጠርታ እነሆ ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ይፈቅዳል።

ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነስና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድለት ጥቂት ቀናት በዚያው ተቀመጥ ብላ አሳመነችው።
ያዕቆብም እሺ ብሎ መንገዱን ጀመረ።

ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሄደ።

ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ ከእርሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።

ሕልምም አለመ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደረሰ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበርና።

እነሆም እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር እንዲህም አለ የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጥሃለሁ።

ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምስራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ የምድርም አህዛብ ሁሉ ባንተ በዘርህም ይባረካሉ።

እነሆም እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ በምትሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ ወደዚችም ምድር እመልስልሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።

ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነስቶ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው እኔ አላወቅሁም ነበር አለ።

ፈራ እንዲህም አለ "ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው።"

ያዕቆብም ማልዶ ተነሳ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው በበላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።

ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ቦታ ስም ሎዛ ነበረ።

ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ።

"እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን በምሄድበትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥

ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል።

ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአስር እጅ አነዱን እሰጥሃለሁ።" ብሎ ቃል ገባ።

✝️ ስለዚህም እኛም #የያዕቆብ_ሌሊት ያድርግልን የምንባባለው

👉 እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር ከእኛ ጋር እንዲያድርና ጥሩ የሰላም እንቅልፍ እንዲያስተኛን ቅዱሳን መላእክትን በሕልማችን እንዲያሳየን ከመጥፎ ህልም እንዲጠብቀን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዲሆን ከመጥፎ አጋንንት እንዲጠብቀን #የያዕቆብ_ሌሊት ይሁንልን እንላለን።

              ወስብሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን!!!
         ለበለጠ ኦሪት ዘፍጥረት (26-30) አንብቡት
ምንጭ: - Mule Ze Kdst Ldeta

ጋሜል Media

10 Oct, 03:39


ትመጫለሽ_አይደል?

ቤተመቅደስሽን ከበን አለን - መቅደስ ገላችን ቢረክስም

በሕንጻ መቅደስሽ ከትመናል - ሕንጻ ሥላሴን ብናፈርስም

በልማድና በእምነት መሐል – በተወጠረ መንፈሳችን

በጎጥ በጎሳ በታጠረ - በተፍረከረከ አንድነታችን

ስቀለው ስቀለው እንጂ – ምን በድሎ? በማይል ልሳናችን

ለክፋት ባደገደገ - በጎ ግብር በራቀው

ኃጢአት ባጠራቀመ – የጽድቅ መንገድ በናፈቀው

ነውርን መግለጥ እንጂ - ከባቴ አበሳነት በማያውቀው

በረከሰ ማንነት ነው – ንዒ ማርያም የምንልሽ

ከልዑሉ ሚካኤል ጋ ከደስተኛው ገብርኤል ጋ

            ጽጌ ጸዐዳ ልጅሽን ይዘሽ
            ነይ ርግባችን የምንልሽ

በሚገባ ንጽህና – ሆነን አይደለም ድንግል

ግን ነይ ስንልሽ አትቀሪም.... ትመጫለሽ አይደል?

ልባችን ቂምን ቋጥሮ በአፍ ዜማ ብቻ - ብንጠራሽም ንዒ ብንልም ድንግል

ርሕርሕተ ሕሊና እመ ትሕትና.....

ትመጫለሽ አይደል?

ስለተጠራው ስምሽ
ድንግል ትመጫለሽ አይደል?

ስለኪዳንሽ
ድንግል ትመጫለሽ አይደል?

አልቦ ምግባር ብንሆንም - እንደ ቃና ማድጋ
ማርያም አትቅሪ እኛ ጋ

ንዒ ስንል
አዛኝቱ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

@Gamel_Media

ጋሜል Media

06 Oct, 18:02


እንኳን አደረሳችሁ!

ጋሜል Media

26 Sep, 20:11


የመስቀል በዓል በረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን።

ጋሜል Media

26 Sep, 16:58


ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።

ገላትያ 6፥14

እንኳን አደረሳችሁ! 🙏🙏🙏

ጋሜል Media

25 Sep, 02:42


እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት እና ለአቡነ ገብረ ማርያም ዘሐንታ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት

በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር::

ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::

በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን: ዻውሎስን: ናትናኤልን: ኒቆዲሞስን . ..) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::

በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ:: ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በኋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::
"ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: (ሉቃ. 10:17)

ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኳል:: በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት: ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ::

በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7 ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል:: 8ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር' ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5)

አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም::

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማሕበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ' አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት::

እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::

ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመታት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም ሉክያኖስ ይባል ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም ደስ ብሎት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል (የመምሕሩ ርስት ነው) ሔደ:: ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ:: መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ መላእክትም ተሰማ:: ሕዝቡና ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ ጽዮን (በተቀደሰችው ቤት) አኖሩት:: እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ ክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ5 ዓመታት በኋላም እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን ስለ ፍቅሩ አኖሩት:: ሚስቱ ወደ ሃገሯ ቁስጥንጥንያ ስትመለስ የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው:: መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ አላት: አምላክ ለዚህ አድሏታልና:: እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም ታላቅ ሐሴት ተደረገ::

ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች:: በዚያም ላይ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲመቱ ጥቅምት 17: ዕረፍቱ ጥር 1: ፍልሠቱ ደግሞ መስከረም 15 ቀን ነው::

††† @Gamel_Media †††

ጋሜል Media

11 Sep, 18:40


2017 ዓ.ም

ጋሜል Media

10 Sep, 18:31


የባሕሩን ጥልቀት የሞገድንም ጩኸት ታናውጣለህ።

ከተአምራትህ የተነሣ አሕዛብ ይደነግጣሉ

በምድር ዳርቻም የሚኖሩ ይፈራሉ

የጥዋትን እና የማታን መውጫ ደስ ታሰኛቸዋለህ።

ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም
ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ

የእግዚአብሔር ወንዝ ውኃን የተመላ ነው

ምግባቸውን አዘጋጀህ
እንዲሁ ታሰናዳለህና።

ትልምዋን ታረካለህ
ቦይዋንም ታስተካክላለህ
በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ
ቡቃያዋንም ትባርካለህ።

በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።

የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ
ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።

ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ
ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ
በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም።

መዝሙር 65÷7

እንኳን ከ2016 ዓ.ም ወደ 2017 ዓ.ም በሠላም አሸጋገረን!

@Gamel_Media

ጋሜል Media

21 Aug, 19:26


ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ
አንተ ወታቦተ መቅደስከ።

“አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።”
መዝሙር 131፥8

ታቦት ማደርያ ማለት ሲሆን
መቅደስ የሚባለው ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ነው።

“ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።......... እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።”

ዮሐንስ 2፥19-21

የመቅደስህ ታቦት ማለት ደግሞ የሥጋህ ማደርያ ማለት ነው 9 ወር ከ 5 ቀን አድሮባታልና።

ስለዚህ ቅዱስ ዳዊት በትንቢት መነጽር ተመልክቶ በተናገረው መሠረት እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለችና

"አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።” እያልን እንደ ቅዱስ ዳዊት እናመሰግናለን።

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የእርገት መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

@Gamel_Media

ጋሜል Media

19 Aug, 01:09


+ የሐዲስ ኪዳን ደብረ ሲና +

አይሁድ ‘እኛ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደተናገረው እኛ እናውቃለን ይህ ሰው ግን  ከወዴት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው ክርስቶስን ሊያቃልሉ ሞክረው ነበር፡፡

ዛሬ በደብረ ታቦር የተከናወነውን ቢያውቁ ምን ይሉ ይሆን? እነርሱ ሕጉን እንጠብቃለን ብለው የሚመኩበትና የእርሱን ሕግ እየጠቀሱ ክርስቶስን ሊነቅፉ የሚሞክሩበት ሙሴ ዛሬ በታቦር ተራራ ከጌታ ፊት በፍርሃት ቆመ፡፡ አይሁድ ይህንን ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን? ፈሪሳውያን ሆይ ወደ ደብረ ታቦር ብቅ ብትሉ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ነን ብላችሁ የምትመኩበት ሙሴን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ የሕግ ፍጻሜ ክርስቶስ የሕጉን ተቀባይ ሙሴን ጠርቶ እያነጋገረው ነው፡፡ ሙሴም በሲና ተራራ በዛፍ ላይ ሲነድ ካየው እሳት ጋር እየተነጋገረ ነው፡፡

አይሁድ ሆይ በጌታ ፊት በትሕትና ብትቀርቡ ኖሮ የት እንደተቀበረ እንኳን የማታውቁትን ሙሴ ለማየት በታደላችሁ ነበር፡፡ የሙሴን መጻሕፍት በቃላችሁ የምታውቁ ሕግ አዋቂዎች ሆይ እናንተ ቁጭ ብላችሁ ክርስቶስ ለሦስት ትሑታን ዓሣ አጥማጆች ሙሴን እያሳያቸው ነው፡፡ ‘ኤልያስ ይመጣል’ የምትሉ ጻፎች ሆይ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ብትሆኑ ኖሮ ኤልያስን በታቦር ተራራ ባያችሁት ነበር፡፡ ደብረ ታቦር ብትገኙና ኤልያስን ብታዩት ኖሮ መስቀሉ ሥር ቆማችሁ ኤሎሔ ሲል ስትሰሙ ‘ኤልያስን ይጠራል ያድነው ከሆነ እናያለን’ ብላችሁ ባልሰማ ጆሮአችሁ ከፈጣሪ ጋር አትጣሉም ነበር፡፡

ደብረ ታቦር የሐዲስ ኪዳን ደብረ ሲና ሆነች፡፡ ሙሴ ሕዝቡን ከተራራ በታች ትቶ ከኢያሱና ከወንድማማቾቹ አብዩድና ናዳብ ጋር ወደ ሲና ተራራ ይወጣ እንደነበር ክርስቶስም ከጴጥሮስና ከወንድማማቾቹ ያዕቆብና ዮሐንስ ጋር ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ ሙሴ በሲና በደመና መካከል የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደሰማ በታቦርም የአብ ቃል ተሰማ፡፡ የታቦር ድምፅ ግን እንደ ሲና ‘ባሪያዬ ሙሴ’ የሚል ሳይሆን ‘የምወደው ልጄ’ የሚል ነበር፡፡ ሙሴ በሲና ተራራ ባየው የእግዚአብሔር ክብር ምክንያት ፊቱ እስራኤል ተሸፈንልን እስኪሉት ድረስ አበራ፡፡ የታቦር ተራራው ግን የተለየ ነበር ፤ ብርሃኑ ከውስጡ የፈለቀው ጌታ ፊቱ ከሙሴ ይልቅ አበራ በልብሱ እንዳይሸፍነው ልብሱም ብርሃን ነበረና ተማሪዎቹ ወደቁ፡፡

ታቦር እንዴት ያለች ‘እግዚአብሔር የወደዳት’ ተራራ ናት? [ደብር ዘሠምሮ እንዲል] ሐዋርያትና ነቢያት በአንድነት ቆመው የሚተያዩባት ፤ ብሉይና ሐዲስ የተዋወቁባት ፤ ጥላና አካል የተጋጠሙባት ይህች ተራራ እንዴት የተመረጠች ናት? ‘ታቦርና አርሞናዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል’ እንደተባለ ነቢያትና ሐዋርያትን በግራ በቀኙ አድርጎ በሰማያዊ አባቱ ‘የምወደው ልጄ’ ተብሎ ሲጠራ ስሙን ሰምታ ታቦር ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት አጣን እንጂ ነቅለን ወደ ሀገራችን ከምናስገባቸው ተራሮች አንዱ ታቦር በሆነ ነበር፡፡

በታቦር ተራራ ሐዋርያትና ነቢያት በአንድ ወንበር ከሊቀ ሊቃውንት ክርስቶስ ትምህርት ተምረው ተመለሱ፡፡ ሐዋርያቱ የነቢያት ጌታ መሆኑን ሲማሩ ነቢያቱ ደግሞ የሐዋርያት አምላክ መሆኑን አወቁ፡፡ ነቢያት ደክመው የዘሩትን ከሚያጭዱ አጫጆች ሐዋርያት ጋር ተዋወቁ፡፡
ነቢያት አምላክነቱን ያውቃሉ ፤ ሐዋርያት ደግሞ ሰውነቱን ያውቃሉ፡፡ በታቦር ተራራ ግን  አዲስ ትምህርት ተማሩ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ፦ ‘‘ነቢያቱ አይተውት የማያውቁትን ሰውነቱን አይተው ተደሰቱ ፤ ሐዋርያቱ አምላክነቱን አይተው ተደሰቱ’’

       ሐዋርያት ደነገጡ ፤ እነርሱ ባልነበሩበት በዮርዳኖስ የተናገረውን የእግዚአብሔር አብን ድምፅ በታቦር ተራራ ሰሙ ፤ ጴጥሮስ ‘አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ’ ያለው በሰማይ ያለው አብ ገልጦለት ነበረ ፤ አሁን በልቡ ያንን ቃል ያስቀመጠውን የአብን ድምፅ ሰምቶ ዓለቱ ስምዖን በፍርሃት ወደቀ፡፡ የጌታን ፊት አብርቶ ሲያይ ሳያይ ያመነውን አምላክነቱን አወቀ፡፡ ‘ሐዋርያት በአንድ ቀን ሁለት ፀሐይ ወጥቶ አዩ ፤ አንደኛው የተለመደችው ፀሐይ ስትሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚያበራው የጌታ ፊት ነበር’ ይላል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡ እውነትም ስሙን ለሚፈሩ ሐዋርያት የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ላይ ወጣላቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም በታቦር ተራራ ነቢያትና ሐዋርያት መገናኘታቸውን እንዲህ ሲል ያደንቃል ፦
‘የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ኤልያስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!’

ሐዋርያት ወድቀው ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት’ የሚል ቃል ከሰሙ በኋላ ሲነሡ ከክርስቶስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡ በእርግጥም ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው’ ተብለው ማሳሰቢያ ከተሠጣቸው በኋላ ቀና ሲሉ ማግኘት ያለባቸው ‘የሚወደው ልጁን’ ክርስቶስን ብቻ ካልሆነ አዋጁ ስለማን እንደሆነ ግራ ይገባቸው ነበር ይላል ማር ኤፍሬም፡፡

    ሐዋርያት ቀና ሲሉ ሙሴ የለም ፤ ኤልያስም የለም፡፡ ለነገሩ ከሙሴም ከኤልያስም የሚልቀው ጌታ ከእነርሱ ጋር ካለ ምን ይፈልጋሉ? ባልወለደው ፈርኦን የልጅ ልጅ ተብሎ ከተጠራው ሙሴ ይልቅ ባልወለደው ዮሴፍ የዮሴፍ ልጅ ተብሎ የተጠራው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ከፈርኦን ሰይፍ ተርፎ እስራኤልን ነጻ ካወጣው ሙሴ የሚበልጠው ከሔሮድስ ሰይፍ ተርፎ ዓለምን ነጻ ያወጣው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር አለ፡፡ እናቱ ሞግዚቱ ሆና ካሳደገችው ሙሴ በላይ ‘እናትና ገረድ ማርያም ደስ’ ብሏት ያሳደገችው ክርስቶስ አይሻላቸውም? ግብፃዊውን ገድሎ ለማንም አትናገሩ ከሚለው ሙሴ ይልቅ ዕውራንን አብርቶ ለምፃምን አንጽቶ ፊቱ እንደ ፀሐይ አብርቶ ለማንም አትናገሩብኝ የሚለው ክርስቶስ አብሮአቸው ካለ ምን ይፈልጋሉ፡፡ ‘የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ’ ተብሎ ከተነገረው ሙሴ ይልቅ ‘የጌታ እግር በሚቆምበት እንሰግዳለን’  ‘የጫማህን ጠፍር እንኳን ልፈታ አይገባኝም’ እየተባለ የተዘመረለት ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነውና ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የሙሴ መሔድ አላስደነቃቸውም፡፡

ኤልያስንም ስላላዩ አላዘኑም ፤ በእሳት ሰረገላ ከሔደው ኤልያስ በላይ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት የሆነው አምላክ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ኤልያስ ለደቀ መዝሙሩ ወደ ሰማይ ሲሔድ መጎናጸፊያውን ትቶለት ሔዶ ነበር፡፡ የሐዋርያት መምህር ክርስቶስ ግን ሲያርግ ልብሱን አልወረወረላቸውም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለ እርሱ ሲያርግ ለደቀ መዛሙርቱ የተወላቸው ልብሱን ሳይሆን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ነው፡፡ ስለዚህ ኤልያስ ቢሔድ ሙሴም ቢሰወር ደቀ መዛሙርቱ ጌታችንን ከብበው ከታቦር ተራራ በደስታ ወረዱ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ!

@Gamel_Media