✅ አስር ( 🔟 )
ጥሩ! በአንድ ሰው ላይ ሁለት ምስክሮች ቢመጡ መግደሉን ለመመስከር ይህ ሰው
ለመግደሉ ሁሉም ማህበረሰብ የግድ በአጠቃላይ መስማማት አለበት! ማለቴ እከሌ እከሌን ገድሎታል ብሎ በእከሌ ላይ ለመመስከር ሁሉም ማህበረሰብ የግድ በአጠቃላይ መስማማት አለበት! ዳኛው አንድም በዲያ (በካሳ ክፍያ) ወይም በቂሷስ (በማመሳሰል እርምጃ) ላይ በአላህ ህግ መዳኘት ግዴታ አለበት፡፡ የአላህን ሸሪዓ ተፈጻሚ ማድረግ አለበት፡፡ ሙብተዲዕን ሙብተዲዕ ከማለት በጣም አደጋ በሆነው በዚህ ጉዳይ ላይ ሁሉም መስማማት መስፈርት ነው!? እነዚህ ሙመይዓ ፣ የባጢል ባለቤቶች ፣ የተንኮል ተጣሪዎች ፣ እንደሚባለው በደፈረሰ ውሃ አዳኝ ናቸው፡፡ ይህን የተበላሽ ንግግራቸውን አትስሙ፡፡ አንድ እውቀት ያለው ዓሊም ሲተች - ባረከሏሁ ፊከ - ይህን ትችት መቀበል ግድ ነው፡፡ አንድ ፍትሀዊ የሆነ ፣ ችሎታ ያለው ዓሊም ከተቃወመ ደግሞ የሁለቱ ንግግር ይጠናል ፣ ትችቱም ውዳሴውም ይታያል፡፡ ትችቱ የተተነተነ እንዲሁም ግልጽ ከሆነ የሚያወድሱት ቁጥራቸው ቢበዛም ፣ ትችቱ ከውዳሴው ይቀደማል፡፡ አንድ ዓሊም አስር ወይም አምሳ አሊሞች - ውጫዊ ገጽታን በማየትና በመልካም በመጠርጠር
ምንም አይነት ማስረጃ ሳይዙ አንድን ግለሰብ ቢያወድሱ -ስለዚህ ሰው የተተነተነ ትችት ይዞ የመጣው ሰው- ማንም ቢቃወምም - ትችቱ ይቀደማል፡፡ ምክንያቱም ተችታ ከእርሱ ጋር ማስረጃ አለ ፤ ማስረጃ ደግሞ ሊቀደም ይገባዋል፡፡ ምድርን የሚሞላ ሰው ቢቃወም ማስረጃን እናስቀድማለን ! ማስረጃው ከእርሱ ጋር ሆኖ የምድር ባለቤቶች ሁሉ ቢቃረኑት ፣ ምንም ይሁን ምን ሀቁ ከእርሱ ጋር ነው፡፡ ጀማዓ ማለት ደግሞ ብቻውን እንኳ ቢሆን በሐቅ ላይ የሆነ ሰው ነው፡፡ አንድ ሰው በሱና ከሆነ ሙብተዲዕ የሆኑ የሁለት ወይም የሶስት ከተማ ሰዎች ቢቃረኑት ሀቁ ከእርሱ ጋር በመሆኑ ፣ ከሌሎች ጋር ያለው ባጢል በመሆኑ መረጃ ይቀደማል፡፡ ሀቅን
ማክበር ግዴታችን ነው ፤ ማስረጃን ማክበር ይገባል፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
(قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ)
“እውነተኞች እንደሆናችሁ አስረጃችሁን አምጡ” በላቸው፡፡ (አል በቀራህ፡111)
(وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ مَن فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ )
“በምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡”
(አል አንዓም፡116)
ማስረጃ አልባ የቁጥር ብዛት ዋጋ አይስሰጠውም፡፡ ትንሽ ቁጥር ካላቸው ውጭ የምድር ሰው በአጠቃላይ በውሸት ቢሰባሰብ ማስረጃ አልባ ከሆኑ ግምት
አይሰጠውም፡፡ አንድ ወይም ትንሽ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እንኳ ተቃራኒ ቢሆኑም
ከማስረጃ ጋር እስከሆነ ድረስ ሀቅን በማወቅ ፣ እርሱን አጥብቃችሁ በመያዝና
ሐቅን በመቀበል አላህን ፍሩ አላህን ፍሩ !! አላህ ለሁሉም ሀቁን ይግጠም!”
(شريط المنهج التميعي وقواعده للشيخ
حفظه هللا)
-አሁንም ተጠየቁ፡ “አንድ ግለሰብ ከፊሉ ሙብተዲዕ ፣ ከፊሉ ደግሞ ሙብተዲዕ
አይለውም አንዳንድ ተማሪዎች ሙብተዲዕ ያላሉትን ሰዎች ንግግር ይከተላል፡፡
እርሱን ማውገዝ ይበቃልኛል?”
መልስ፡ “በርካታ ወጣቶች ሀቅን ከማወቃቸው ጋር ይህ በአሁኑ ሰዓት በአካባቢያችን የሚገኝ ፈተና ነው፡፡ ባረከሏሁ ፊከ በእርግጥ ረዘመች! በእርግጥ ረዘመች! አንድን ሰው ሙብተዲዕ ለማለት ወይም ለመተቸት የዑለሞች ስምምነት መስፈርት አይደለም፡፡ ይልቁንም ለመተቸትም ይሁን ለማወደስ የአንድ ሰው ንግግር በቂ ነው፡፡
ጀማዓዎች ከተቹት ወይም ሙብተዲዕ ካሉት ሀቅን ለሚፈልግ ሰው በቂው ነው፡፡
ዝንባሌውን የሚከተለው ሰው ከሆነ ግን በሸረሪት ድሮች ይንጠለጠላል እንጅ
አንድም ነገር አይበቃውም፡፡ ሰዎች ይህን ትችት የሚባለውን ነገር አላወቁትም፡፡
ሰዎች ተጠምደዋል፡፡ ሰዎች ይህ ሰው የተተቸ መሆኑን መተቸት የሚገባው
መሆኑንም ተምረዋል ፣ አውቀዋል፡፡ ምክንያቱም ውሸታም በመሆኑ ፣ ዑለሞችን በመዝለፉ ፣ የሰለፎችን መንሐጅና ባለቤቶች በመቃወሙ ፣ የተበላሹ መሰረቶችን በማበጀቱ ፍትሀዊነቱ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ይህን ሁሉ አውቀዋል፡፡ ከምክር በኋላ አይዘንም ይላሉ፡፡ መከሩ ፣ አብራሩ ይህ ሰው እምቢ አለ፡፡ እርሱን ሙብተዲዕ ለማለት ተገደዱ! በዚህ አይነት የቀረ በሸረሪት ድሮች የሚንጠለጠል ሰው ምንድን ነው ምክንያቱ? (ወላሂ እከሌ አወድሶታል!) (ወላሂ በሙብተዲዕነቱ ዑለሞች አልተስማሙም!?) ይላሉ! ሙብተዲዕ ያላሉ ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ፡ አንደኛው ያልተማሩ ሰዎች ናቸው ፣ እነርሱም ምክንያት ይሰጣቸዋል፡፡ ሁለተኛው የተማሩ ፣ ለውሸት የሚከላከሉ ናቸው፡፡
ከእነርሱ ዘንድ ያለውን ውሸት ምን እንደሆነ ያውቃሉ ፣ እምቢ ብለው ለዚህ
ሙብተዲዕ መከላከል እንጅ ሌላ አላማ የላቸውም፡፡ እነዚህ ምንም ዋጋ አይሰጣቸውም፡፡ ዝም ባዮች ዝምታቸው መረጃ አይሆናቸውም፡፡ እነዚያ ከሰውዬው ላይ ያሉ ነገሮችን
ሁሉ የተቹ ፣ በሚገባው ያብራሩ መረጃው ከእነርሱ ጋር በመሆኑ ከዚህ በፊት
እንደጠቆምኩት ሐቀኛ ለሆነ ሰው ከአላህ -ዓዘ ወጀለ- ዘንድ ምንም አይነት
ምክንያት የሌላቸው ለሆኑትና በሸረሪት ድሮች ላይ ለሚንጠለጠሉት ሳይሆን (መረጃው ከእነርሱ ጋር የሆነውን) ሐቅን መያዝ ግዴታ አለበት፡፡
✍🏼 ፀሀፊ የተከበሩ ሼኽ ሁሴን ሙሀመድ አስልጢ (ዶ/ር)
✍🏼 ተርጓሚ ኡዝታዝ ዩሱፍ አህመድ