የምግብ አዘገጃጀት @foodrecipesone Channel on Telegram

የምግብ አዘገጃጀት

@foodrecipesone


Food recipes

የምግብ አዘገጃጀት (Amharic)

የምግብ አዘገጃጀት የባህል ዝግጅት በትምህርት ለማግኘት ስለ እናቃቤዎት ብሎን እንደምን በልም ስልክ ብሎን ኖህረ እግዚአብሔር በምግብ አዘገጃጀት ዳይት ማግኘት ይፈልጋሉ። ምን ነው ትንሹ? እራሳችን እና ባህል መጠነኛ እገዛ በአዝናኝ አ዁ንደር አስመልክቶ መሳሪያ ይሰጣል። ከዋናው እግር ላይ በሚቆጠሩ ገንዘብ ውስብስብና ቅባትና አጠቃናኝ የመረጃዎችን እንዲሁም በሌሎች ተወዳጁ በህብረት የቦታዎችም ጽሑፍ ምንጮብላችን ይሆንብኛል።

የምግብ አዘገጃጀት

13 Mar, 14:42


ከሱፍ የምናገኛቸው 16ቱ የጤና ሲሳዮች

ሱፍ ከፍተኛ ኃይል ወይም ካሎሪን፣ፕሮቲን፣ቅባት፣ቫይታሚን ኢ እና ቢ‐ኮምፕሌክስ፣ፎሊክ አሲድ እና አንቲ ኦክሲደንትን በውስጡ ይዟል፡፡ የሱፍ ፍትፍት፣ የሱፍ ጭማቂ እና ሱፍ በቆሎ ውስጥ ገብቶ በአገራችን ለምግብነት ይውላል፡፡

ሱፍን ብንመገብ ቀጥሎ ያሉትን በሳይንስ የተረጋገጡ የጤና በረከቶችን እናገኛለን

1. የልብ በሽታን ይከላከላል

2. የደም ቅባት ወይም የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል

3. የአጥንት መሰሳትና የአጥንት አንጓ ብግነት ይከላከላል

4. ድርቀትን ይቀንሳል

5. የአእምሮ ጤናን ይጠብቃል

6. የደም ግፊትን ይቀንሳል

7. አይነት ሁለት የስኳር ሕመምን ይቀንሳል

8. ለቆዳ ጤና ጥሩ ነው

9. የደም ማነስን ይከላከላል

1ዐ. የሕዋሳት ውድመትን ይከላከላል

11. የምግብ ስርዓተ ልመትን ያሻሽላል

12. የፅንስ ዕድገትን ያፋጥናል

13. ድባቴንና ጭንቀትን እንዲሁም የእንቅልፍ እጦትን ያስወግዳል

14. ክብደትን ይቀንሳል

15. የሆርሞን መጠንን ሚዛናዊ ያደርጋል

16. የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅምን ያሻሽላል

መልካም ማዕድ🍴

Join በማድረግ ጠቃሚ ነገሮችን ያግኙ

የምግብ አዘገጃጀት

04 Mar, 15:31


የዱባ ፍሬ የጤና ጥቅሞች

ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች፣ ዛሬ ስለ ዱባ ፍሬ ጥቅሞች እንንገሮት!!!
1. ለልብ ጤናማነት
የዱባ ፍሬ በቀን ውስጥ ልናገኘው የሚገባውን የማግኒዝየም መጠንን በግማሽ ስለሚይዝ ለልብ ጤናማነት ለአጥንት እንዲሁም ለጥርስ እና ለደም ስሮች ከፍተኛ ጠቃሚነትም አለው፡፡ ማግኒዝየም ድንገተኛ የልብ ሕመምን እና ስትሮክን የመከላከል ጥቅምን ይሰጣል፡፡
2. በሽታ የመከላከል አቅምን ማዳበር
ዚንክ የሚባለው ንጥረ ነገር በዱባ ፍሬ ውስጥ ይገኛል፡፡ ዚንክ ለሌሎች ዕድገትና ክፍፍል ውስጥ፣ እንቅልፍ፣ የማሽት እና የመቅመስ ችሎታችን እና ለዓይን ለቆዳ ጤና ጠቃሚ ነው፡፡
3. በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው
የዱባ ፍሬ እንደ ተልባ እና ሌሎች ፍሬዎች በጣም ጠቃሚ በሆነው በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው፡፡

4. ለፕሮስቴት ጤናማነት
ለወንዶች ጤንነት ጠቃሚነቱ የተረጋገጠው የዱባ ፍሬ በተለይም ለፕሮስጤት ጤናማነት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጥናቶች አሳይተዋል፡፡
5. ፀረ ስኳር ሚና
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የዱባ ፍሬ ኢንሱሊንን መጠን በማመጣጠን ከስኳር ሕመም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሕመሞችን ይከላከላል፡፡
6. ላረጡ ሴቶች
የተደረገ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የዱባ ፍሬ ጠቃሚ የሆነውን የኮሌስትሮል ዓይነት በመጨመር እና የደም ግፊት፣የእራስ ምታት፣የመገጣጠሚያ ሕመሞችን በመቀነስ ጠቃሚነትን ይሰጣል፡፡
7. ለጉበት እና ልብ ጤናማነት
በፋይቦር፣የአንቲኮክሲደንት እና ጤናማ ቅባት የበለፀገው የዱባ ፍሬ ለልብ እና ለጉበት ጠቃሚም ነው፡፡
8. ለጥሩ እንቅልፍ
በዱባ ፍሬ ውስጥ በብዛት የሚገኘው ትራይፕቶፋን የሚባል ኦሚኖ አሲድ ሰውነታችን ወደ ሴሮቶኒን ቀጥሎም ወደ ሜላቶኒን የእንቅልፍ ሆርሞን በመቀየር ይጠቀምበታል፡፡ ከእንቅልፍ በፊት የዱባ ፍሬን መመገብ ለሰውነታችን የሚገባውን ዕረፍት እንዲያደርግ ይረዳዋል፡፡

9. ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
የዱባን ፍሬ መመገብ ለጡት ካንሰር፣ለጨጓራ ካንሰር፣ለሳንባ ካንሰር፣ለአንጀት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ የስነ-ምግብ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
10. የውንድ የዘር ፈሳሽ ጥራትን ያሻሽላል (sperm quality)
በዱባ ፍሬ ውስጥ በብዛት የሚገኘው ዚንክ የተሰኘው ንጥረ ነገር ለውንድ የዘር ፈሳሽ ጥራትን ይጨምራል


ምንጭ ዶክተር አለ

የምግብ አዘገጃጀት

04 Mar, 15:25


https://t.me/+NeTUovV6lxBmYWY0
የማይረሳ ስጦታ መስጠት ካሠቡ መጀመሪያ ይሄን ፔጅ ይጎብኙ የቴሌግራም channel ከፍተዋል
👇👇👇👇

https://t.me/+NeTUovV6lxBmYWY0

የምግብ አዘገጃጀት

05 Dec, 21:00


ስኳር ድንች በ ሙዝ

      🥔  &  🍌

6 መካከለኛ ስኳር ድንች
3 ሙዝ
1 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
1 ኩባያ የፈላ ውሃ
እና ዝንጅብል

አሰራር
1  ስኳር ድንቹን ቀቅሎ መላጥ
2  የተላጠውን ስኳር ድንች በስሱ መክተፍ
3  ሙዙን በስሱ መክተፍ
4  ቅባት የተቀባ መጋገሪያ ላይ ስኳር ድንቹን እና ሙዙን በየተራ መጨመር
5  ቅቤ ትንሽ ዝንጅብል እና ውሃ ጨምሮ መክደን
6  ሙቀቱ 400 ዲግሪ ፋራናይት በሆነ ምድጃ ለ20 አምስት ደቂቃ ማብሰል
7  ክዳኑን ከፍቶ አጋም እስኪመስል ድረስ ምድጃው ውስጥ ማቆየት

                6 ሰው ይመግባል
        
         🍴መልካም ማዕድ 🍴
     
       🍴@የምግብ አዘገጃጀት🍴
Please Join❤️

የምግብ አዘገጃጀት

12 Jul, 12:28


አረንጓዴ ሻይ የመመገብ 15 ጤናማ ባህሪዎች
1- ፀረ-ሙቀት አማቂ ነው
2- ከአንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች ይጠብቃል
3- ለልብ ጥሩ ነው
4- የአንጎል ንክረትን ይከላከላል
5- ቆዳዎን ከፀሀይ ጨረር ይከላከሉ
6- የአዋቂዎችን እና አዛውንቶችን አካላዊ ብቃት ያሻሽላል
7- ኢንፌክሽኖችን እና ቫይረሶችን ይዋጉ
8- መጥፎ የአፍ ጠረንን ጨርስ
9- የማተኮር ችሎታዎን ያሻሽሉ
10- እንደ አልዛይመር ወይም ፓርኪንሰን ካሉ ከመሳሰሉት የነርቭ በሽታ አምጪ በሽታዎች ይጠብቅዎታል
11- የጭንቀት ደረጃን ይቀንሰዋል እንዲሁም ዘና ያደርጋል
12- የስኳር በሽታን ይከላከላል
13- የፀጉርን እድገት ያበረታታል
14- የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ላላቸው ህመምተኞች ጥሩ ማሟያ ነው
15- ፍሬያማነትን ይጨምራል

🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵
🍵🍵Join ማለት አይርሱ🍵🍵
🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵🍵

የምግብ አዘገጃጀት

19 Mar, 19:44


የምግብ አዘገጃጀት ቻናልን Join በማድረግ ይቀላቀሉ

የምግብ አዘገጃጀት

18 Mar, 10:55


🍋 የሎሚ ካችአፕ 🍋
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋

12 ትልልቅ ሎሚ
4 የሾርባ ማንኪያ ሰናፍጭ
1 የሾርባ ማንኪያ ዕርድ
1 የሾርባ ማንኪያ ነጭ ቁንዶ በርበሬ
1 የሻይ ማንኪያ ቅርንፋድ
2 የሾርባ ማንኪያ ስኳር
2 የሾርባ ማንኪያ ራዲሽ የተከፈተ
1 ቀይ ሽንኩርት ተልጦ የተከተፈ
2 የሾርባ ማንኪያ ጨው
  ትንሽ ሚጥሚጣ
       
              🥣 አሰራር
1, ሎሚውን አጥቦ መጭመቅ እና 
     ልጣጩን በደቃቁ መክተፍ።
2, የሎሚ ጭማቂውንና ልጣጩን ክዳን
    ባለው ዕቃ ውስጥ ጨምሮ ለሶስት
    ሰዓት ያክል ማስቀመጥ።
3, ከላይ የተዘረዘሩትን መቀላቅሎች
    በሙሉ በቁጥር 2 ከተቀመጠው
    የሎሚ ጭማቂና ልጣጭ ጋር ለሠላሳ
    ደቂቃ ያህል ማፍላት።
4, ከተቀቀለ በኋላ ለሁለት ሳምንት
    በደንብ በሚከደን ዕቃ ውስጥ ጨምሮ
   ማስቀመጥ። በየቀኑ እያማሰሉ መልሶ     መክደን።
5, የተዘጋጀውን ካችአፕ አጥልሎ ታጥቦ
    በተቀቀለ ጠርሙስ ውስጥ ጨምሮ
    መክደን።
6, ለጥብስ፣ ለሳንድዊች፣ ለሃምበርገር፣
    ለሰላጣ እንዲሁም ለሌሎች ምግቦች
    ጋር እንደማጣፈጫ ሆኖ ይቀርባል።

አንድ ሊትር የሎሚ ካችአፕ ይወጣዋል። 
       
                 🍋  መልካም ማዕድ! 🍋

የምግብ አዘገጃጀት

12 Aug, 07:33


ቴላቴሊ
Tagliatelle

★ 400 ግራም ፍርኖ ዱቄት (8 የቡና ስኒ)
★ 4 እንቁላል
★ ከ4-5 የሾርባ ማንኪያ ውሃ
★ ሩብ የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት፡-
🍁ዱቄት እና ጨውን ቀላቅሎ ንፁህ ጠረፔዛ ላይ ማስቀመጥ፡፡
🍁ዱቄቱን መሀሉን መክፈት፡ እንቁላል መጨመር፡ አና ማሸት (ለ 10 ደቂቃ መታሸት አለበት)፡፡
🍁ሲታሽ የመድረቅ ወይም መፈረካከስ ካመጣ ከ 4 - 5 የሾርባ ማንኪያ ውሃ መጨመር፡፡
🍁ከታሸ በኃላ 15 ደቂቃ በፌስታል ጠቅልሎ ማስቀመጥ፡፡
🍁ሊጡን ከ 3 ሚሊሜትር ውፍረት እና ከ ሀምሳ ሴንቲሜትር ቁመት እንዳይበልጥ አድርጎ መዳመጥ፡፡
🍁ሊጡን በግምት ከ አንድ ሴ.ሜ ርቀት በቢላዋ መቁረጥ፡፡
🍁ዱቄት የተነሰተሰበት ትሪ ወይም ጠረጴዛ ላይ በመዘርጋት ለአንድ ሰዓት መጠጥ እንዲል ማድረግ፡፡
🍁ሁለት ሊትር ውሃ አፍልቶ ጨው ጨምሮ ቴላቴሊውን ቀስ እያረጉ ውሃ ውስጥ መጨመር፡፡
🍁ለ 3 ደቂቃ ያክል ማብሰል እና በፓስታ ማጥለያ ማጥለል፡፡
🍁በመረጡት አይነት ሶስ ወይም ስጎ በመጠቀም ገበታ ላይ ማቅረብ፡፡

መልካም ማዕድ!
የምግብ አዘገጃጀትን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

የምግብ አዘገጃጀት

05 Aug, 18:22


የቲማቲም ሾርባ
ግማሽ ኪሎ የበሰለ ቲማቲም
2 እራስ ቀይ ሽንኩርት
5 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
2 ግንድ ባሮ ሽንኩርት
3 ግንድ የሾርባ ቅጠል
3 የሾርባ ማንኪያ በሶብላ
1 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ሚጥሚጣ
6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
ጨው እና ቁንዶበርበሬ
አሰራር፡
ቲማቲሙን አጥቦ ለ ሁለት ለ ሁለት መክተፍ
ቀይ እና ነጭ ሽንኩርቱን ልጦ ለሁለት ለሁለት መቁረጥ
ባሮውን ልጦ መክተፍ
መጋገሪያ ላይ ቲማቲሙን፡ ቀይ እና ነጭ ሽንኩርቱን፡ ባሮ ሽንኩርቱን፡ በሶብላውን፡ እና የሾርባ ቅጠሉን ማድረግ
ዘይት፡ ጨው እና ቁንዶበርበሬ ጨምሮ በደንብ ማደበላለቅ እና ለ 15 ደቂቃ በኦቨን ማብሰል
በስሎ ከቀዘቀዘ በኃላ በጁስ መፍጫ መፍጨት
በድስት ውስጥ የተፈጨውን ቲማቲም ጨምሮ እንደገና ማንተክተክ
ከወፈረ የአትክልት ማጣፈጫ ሾርባ ጨምሮ ማቅጠን
ሚጥሚጣ ጨምሮ ማቅረብ
🍽መልካም ማዕድ🍽

የምግብ አዘገጃጀት

05 Aug, 18:15


🍅🍅የቲማቲም ሾርባ🍅🍅

የምግብ አዘገጃጀት

04 Aug, 09:06


ለቤት ወይም ለስጦታ የሚሆን string art ከፈለጉት በውስጥ መስመር ያግኟቸው @sinoneart 0962277032
አፍሮአይገባ መስቀል 👇

የምግብ አዘገጃጀት

23 Jun, 11:05


ዱባ በጎመን ወጥ

ለ 6 ሰው የሚሆን

@---የሚያስፈልገው---@

#--5 መካከለኛ ጭልፋ (500ግራም) የተከተፈ ዱባ
#--2 መካከለኛ ጭልፋ (300ግራም) የተከተፈ የሀበሻ ጎመን
#--1 መካከለኛ ጭልፋ (150ግራም) የደቀቀ ወይ ሽንኩርት
#--4 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
#--4 ፍሬው ወጥቶ የተከተፈ ቃሪያ
#-- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
#--6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
#-- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው

አዘገጃጀት:-

1, ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ማብሰል
2, በደንብ ሲበስል ጎመኑን ጨምሮ እንዲበስል መተው
3, ጎመኑ ሲበስል ዱባ እና ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ እንዳይቦካ ቀስ ብሎ ማማሰል
4, ነጭ ቅመም እና ጨው ጨምሮ ሲበስል ቃሪያውን ነስንሶ ማውጣት

መልካም ማዕድ!

የምግብ አዘገጃጀት

19 Sep, 04:22


ገንፎ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የምግብ አይነት ሲሆን፣ የሚሰራውም ከስንዴ ወይም ገብስ ዱቄት ነው።
ዶሮ በልቶ ችክን ያለ ወጥ የመሥራት ያህል ከባድ ባይሆንም ልምድ ይጠይቃል፡፡ ገንፎ
አሠራሩ ብቻ ሳይሆን አቀራረቡም ልዩ ጥበብ አለው።
ገንፎ ውሃ አፍልቶ የተመጠነ የገብስ ዱቄት በመጨመር በወፍራሙ ውሃ ጠብ እያረጉ ከ 20 እስከ 30 ደቂቃ በማብሰል የሚገነፋ እና በቂቤ ፣ በዘይት ፣ በእርጎ ፣ በተልባ ተመጋቢው በወደደው ለውሶ የሚበላ ምግብ ነው።

የምግብ አዘገጃጀት

05 Apr, 21:37


.........በድጋሚ የተለጠፈ

፩ የቲማቲም ካችአፕ

9 ኪሎ ቲማቲም የበሰለ
ቀይ ሽንኩርት ተልጦ የተከተፈ
ትንሽ ነጭ ሽንኩርት ተልጦ የተከተፈ
ቀይ ቃሪያ ፍሬው የወጣና የተከተፈ
የሻይ ማንኪያ ነጭ አዝሙድ
የሾርባ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
የሾርባ ማንኪይ ጨው
የሾርባ ማንኪያ ቅርንፋድ
የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ
የሻይ ማንኪያ ቀረፋ
ኩባያ ስኳር
ኩባያ ኮምጣጤ
አሰራር
1. ቲማቲሙን አጥቦ መክተፍ
2. የተከተፈውን ቲማቲም ነጭ ሽንኩርት ቀይ ሽንኩርትና ቃሪያ በአንድ ብረት ድስት ውስጥ ጨምሮ ቲማቲሙን በደንብ እስኪበስል መቀቀል።
3. የበሰለውን የቲማቲም ድብልቅ በማጥለያ ማጥለል። ፍሬውንና በመጥለያ ያላለፈውን ቀሪ ነገር ማውጣት ፣ ቅመማቅመሞችን በሙሉ በትንሽ ደበላ ጨርቅ ቋጥሮ የቲማቲሙ ጭማቂ ውስጥ መጨመር። እንደዚሁም ስኳርና ጨውን አደባልቆ ከተጨመረ በኋላ እያማሰሉ እስኪወፍር ድረስ ማብሰል።
4. የቲማቲሙ ድብልቅ በደንብ ከወፈረ በኋላ ተቋጥሮ የገባውን ቅመም ማውጣት።
5. ኮምጣጤውን ጨምሮ ለአስር ደቂቃ ያህል አንተክትኮ ማውጣት።
6. የተዘጋጀውን ካችአፕ ታጥቦ የተቀቀለ ጠርሙስ ውስጥ ትኩሱን ጨምሮ ወዲያው መክደን።
7. ከጥብስ ከሃምበርገር ከሳንድዊች ከሰላጣና ከሌሎች ምግቦች ጋር እንደ ማጣፈጫ ሆኖ ይቀርባል።
አራት ሊትር የቲማቲም ካችአፕ ይወጣዋል።
---መልካም ምግብ---