ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት @semirahalalfood Channel on Telegram

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

@semirahalalfood


ሀላል ምግቦች ፣ጣፋጭና ለጤና ተስማሚ

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት (Amharic)

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት የሀላል ምግቦችን የተስማሚ እና የጤና ቅኝቶችን በመምራት በማስተዋወቅ የማዋጣው ታሪክ ነው። የአሰላምና ለብዙ ሰዎች የሚያጽናና የሚቆጣጠር ከሆነ ምግብ እና ኬክ አዘገጃጀት ታሪክ እንዴት መከላከል እንዲችል የምግቦችን ምክር በመምራት የታሪኩን የተከታታይ ስራ እና ጤና ቅኝቶችን በተለያዩ ዕድሜ ተጠቃሚ ሰጥተዋል። semirahalalfood ለምግቦችና ኬክ አዘገጃጀት መስራት ከሆነ ሀላል ምግቦችን ለጤና ቅኝቶችን መፈጸም የሚያስችለውን ታሪክ፣ ምርጫና የታሰር እናት ከተደቡብ ቦታ በተለያዩ አሰልጣኞች ተነስቷል። ከዚህም የጤናውን ሰዎች ለማስተዋወቅ ከጤና ቅኝቶችን ካሉ ምግቦችና ኬክ አዘገጃጀት እና ቫይረስ በጣም ማሳወቅ እንዲችል በማቅረብ የጤናውን መሳሪያ ለትምህርት እንዳለመኖሩ፣ ፍቺዎችን ለነጻነት ለየአረፍተኞች እና ለመግዛት እነሆ።

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

17 Jul, 08:30


ታክሲው ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ የሚሄድ ነው እና ሁሌም ከታች ሞልቶ መጥቶ አዲስ ሰፈር ሚካኤል በትርፍ ይጭናል። እና እንደተለመደው ሲመጣ ከረዳቱ ፊት ለፊት ሞተሩ ላይ የተቀመጠች ሴት ነበረች እና ስገባ ተነስታ የመጀመሪያው ወንበር ላይ ከተቀመጡት ሁለት ወንዶች መሀል ገባች እኔ እሷ የነበረችበት ተቀመጥኩ ከኔ በኋላ የሆነ ልጅ ገባ እህቴም ነበረች ገባች እና አብረን እንደሆንን ስላወቀ ልጁን በቃ ሞላ ብሎ አስወረደው ከሱ በኋላ የገባችውን እህቴን ግን ዝም አላት ሁለተኛው ወንበር ላይ ተደርባ ተቀመጠች እኔ ቦርሳዬ በእጅ የሚያዝ ነው እና ዚፑ ወደውጭ ነው የዞረው የመጀመሪያው ወንበር ላይ ጫፍ ላይ የተቀመጠው ሰውዬ ቦርሳ ይዟል። 1. የታክሲው በር አይዘጋም ወይም እንዳይዘጋ አርገውታል እና እንዳትወረወሪ ብሎ ወደ እነሱ ተጠጊ አለኝ ሞተሩ ላይ ማለት ነው
2. ልጠጋ ስል ያ ቦርሳ የያዘው ሰውዬ ቦርሳዬን ሊተባበረኝ መስሎ ሊቀበል እኔ ደሞ አይ ብዬ እንደያዝኩት መጠጋት
3.መሀል የተቀመጠችው ሴት ነይ እዚ ጋር ግቢ መሀል ማለት አራተኛ ወይም ልቀይርሽ እኔ ደሞ አይ ቅርብ ስለሆንኩ ችግር የለውም አልኳት አይ "ሞተሩ እንዳያቃጥልሽ" አለች አይ አልኩና በሆዴ እሷን አያቃጥላትም እንዴ...እያልኩ አደያበባ ደረስን ኢሄ ሁሉ አንድ ፌርማታ ነው ከገባሁ ጀምሮ ከዛ ደሞ እህቴን ትራፊክ አለ ብለው ወደ 3ኛ ወንበር ወሰዷት ከኔ ራቀች አታይም በዛ ላይ ረዳቱ ምን ያክላል እና ትንሽ ስለሆነ ሚቀረን ትራፊክ ከሚይዝህ እንውረድልህ ልለው እኔን ብሎ አዛኝ እያሰብኩ በሩን ይታገላል ለመዝጋት በዛ መሀል እጄን ቆረጠኝ ፎጣ ስጠኝ አለው ሹፌሩን እኔሆዬ የቱ ጋር ብዬ ትኩረቴ ወደ እሱ ሚስ ዳይሬክሽን በዛች መሀል ቦርሳ የያዘው ሰውዬ ቦርሳዬን በቦርሳው ሸፍኖ የተወሰነ ከፍቶታል እና ሳብ ሳረገው የተወሰነ ተከፍቷል ቀና ብዬ ሰውየው ላይ ማፍጠጥ እሱ ባላየ ገዛ ከፍቼ ሳይ ሁሉም ነገሬ አለ አዲስ ሰፈርም ደረስን ወረድን ፍጥነታቸው ያላወጣው ቦርሳዬን ማንጠልጠያውን ይዤው ስለነበር እስከመጨረሻው አልከፈተውም ስልኬን የከተትኩበት ኪስ ደሞ በተቃራኒው ነው እና አላገኘውም እና በጠዋቱ ቀልቤን ገፈፉኝ።
እህቴ ደሞ ታጥፎ ሚዘጋ ነበር ቦርሳዋ እና አልተመቻቸውም እንጂ አራተኛ ላይ ከሚቀመጡት ውስጥ በጣም ወደኔ ሲጠጋ ነበር አለች እሷ አልነቃችም እኔም ቦርሳዬ ተከፍቶ ሳይ ነው ያ ሁሉ ድራማቸው እንደሆነ የገባኝ

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

26 May, 12:35


ሰላም ሰላም ዛሬ ዋፍል ይዠላችሁ መጥቻለሁ ወደ አሰራሩ ስንሄድ
5/6 እንቁላል
300 ስኳር
250 ( ሩብ ሊትር ) ዘይት
1 ማማ ወተት ግማሽ ሊትር
750 ሩብ የጎደለው ለአንድ ኩሎ ዱቄት
2 የሾርባ ማንኪያ ፔኪን ፓውደር
1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
ትንሽ ጨው
ወደ አሰራሩ ስንሄድ
*መጀመርያ እንቁላሉና ስኳሩን በደንብ እንመታዋለን
ከዛ ዘይቱን እና ወተቱን ጨምረን እናዋህደዋለን
ሲቀጥል ዱቄቱንና ፔኪንግ ፓውደሩን ቫኒላውንም ጨውኑም አንድላይ ነፍተን እንቁላሉ ላይ ቀስ አርገን እየጨመረን በደንብ  እናዋህደዋለን
*መጨረሻ ላይ የምንጋግርበት የዋፍል መስርያችን አግለን አንዳንድ ጭልፋ እየጨመር ን መጋገር
#ሊጡ ከቀጠነብን ትንሽ ዱቄት እንጨምራለን

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

16 May, 16:38


ለመክሰስ በቀላሉ የሰራሁት ምርጥ ቆቀር
2 ተኩል የውሃ ብርጭቆ ዱቄት
2የሾርባ ማንኪያ ዘይት
1ሾርባ ማንኪያ እርሾ(ቤኪንግ ሶዳ)
3 ሾርባ ማንኪያ ስኳር
ትንሽ ጨው
ዱቄቱን አየር እንዲያስገባልኝ ነፋሁትና ሁሉንም አንድላይ ጨማምሬ ውሃ ሳላደርግ በደንብ አሸሁት ተዋህዶ ፍርፍር ፍርፍር እሰከሚል ከዛ ትንሽ ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ጠብ እያደረኩ በደንብ እንዲዳመጥ አድርጌ አሸሁትና ለ1 ሰአት ሸፍኜ ሞቃት ቦታ አስቀመጥኩት ከዛ መዳመጫዬ ለይ በቁመቱ በእጄ አሽከርክሬ(ፎቶ ላይ እንዳለው)በቢላ ቆራርጬ በጣም ባልጋለ ዘይት ጠበስኩት ሲጠበስ እራሱ ይሰነጣጠቃል ዘይት አይጠጣም ውስጡ ክፍትፍት ይላል ሞክሩት በጣም ቀላልና ጣፋጭ ነው😋😋😋

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

11 May, 11:33


ቀሲል ዱቄት ለፀጉር ያለው ጥቅም

1, ለፀጉር እድገት

የቀሲል ዱቄት በ ውስጡ የ ዚንክ ንጥረ ነገር ስላለ ለፀጉር እድገት ጥሩ ነው :: ቀሲል በተፈጥሮ አንቲ ኢንፍላማቶሪ በሃሪው የፀጉርን መነቃቀል እና የ ራስ ቅላችንን ጤና ይጠብቅልናል ::

2,ፎሮፎርን ይከላከልናል

ቀሲል እንዳልነው አንቲ ኢንፍላማቶሪ በኃሪ አለው ብለናል እሱ የፀጉር ቆዳችንን ጤና ይጠብቅልናል ::

ለፊታችን ያለው ጥቅም

1, ለፊት መታጠቢያ

2, ለብጉር

3,ለፊትን ልስላሴ

4, ለፊትን መሸብሸብ

5,ለጥቁር ነጠብጣብ

6,ፊት መቅላት ይቀንሳል

7,የፊታችንን ቃና (tone) ይጠብቅልናል።

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

09 May, 15:57


#አቮካዶን የመመገብ ጥቅሞች በጥቂቱ🥑🥑🥑🥑

🍁 የኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል

አቮካዶ በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር (betasisterol) በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘዉን የኮሌስትሮል መጠን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

🍁ለዓይናችን ጤና ጠቃሚ ነው

በውስጡ የሚገኘው ካሮቲኖይድ ሉቲየን (carotenoid lutien) ዓይናችንን ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት የሚመጡ ሕመሞችን እንድንከላከል ይረዳል፡፡

🍁 በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል

በአቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው (folate) ፎሌት በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን እንደሚቀንስ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

🍁ከካንሰር ይከላከላል

አቮካዶ የሚመገቡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስና ወንዶችን ደግሞ ከፕሮስቴት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

🍁መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል

አቮካዶ ተፈጥሮአዊ ከሆኑ የመጥፎ አፍ ጠረን መከላከያዎች አንዱ ነው፡፡

🍁 ለቆዳችን ጥቅም

የኦቮካዶ ቅባት በብዙ የውበት መጠበቂያዎች ውስጥ የሚገባና ለቆዳ ተስማሚ እና ጤናማነት ጠቃሚነት ያለው የፍራፍሬ ዓይነት ነው፡፡

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

01 May, 12:06


🔶የእንጆሪ ጁስ
👇የተጠቀምኩት
🔸እንጆሪ
🔸ቴምር ወይም ስኳር
🔸ወተት ወይም ውሀ
በስኩዋር ፋንታ ቴምር ተጠቅሜ ነው የሰራሁት መጠኑን እንደምትፈልጉት በወተት ፋንታ ውሀ ማድረግ ይቻላል
መልካም ቀን የኔ ውዶች

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

27 Apr, 12:07


እቺን ቸኮሌት😍😍😍 እናንተም ሞክሩት😋 ወድጃታለሁ
አሰራር
4 የሾርባ ማንኪያ ካካዎ ፓውደር
1ማንኪያ የበቆሎ ዱቄት
1 የቡና ሲኒ ስኳር
1 ሲኒ ወተት
ቫኒላ በክዳኑ
ሁሉንም ካቀላቀልን በኋላ አነስ ባለ እሳት ላይ ጥደን እስከሚወፍር ማማሰል ወይም በጁሰር መፍጨት  ሲወፍር አውጥተን ትነሽ ቀዝቀዝ ሲል በፈለግነው ቅርፅ ወይም እቃ አድርገን ፍሪጅ ማስገባት ሲደርቅ አውጥተን ትንሽ አቆይተን ማጣጣም ነው😋😋😋

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

23 Apr, 05:49


ሰላም ሰላም ብዙዎቻችሁ ስጠይቁ ነበር የሽምብራ ዱቄቱ እንዴት እንደሚዘጋጅ ሽምብራውን ይታመስና እንደሽሮ ክክ አስከክተን አበጥሮ ከዛ ትንሽ ኮረሪማና ስጋ መጥበሻ ጨምሮ አስፈጭው ከዛ ተነፍቶ በሚፈለገው መጠን ትንሽ ጨው ጨምሮ በወፍራሙ አቡክቶ በስሱ እያድበለበሉ በዘይት መጥበስ ነው ❤️❤️

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

21 Apr, 15:35


5 ኩባያ ዱቄት
1 ኩባያ ዘይት
1 ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
10 ማንኪያ ስኳር
ሁለት ሲኒ ወተት
ትንሽ ጨው አብኩቶ ዳምጦ በቢላ በአራት መዓዘን ወይም በዳይመንድ መቁረጥ በመቀስ ከመድከም በጣም ቀላል ጊዜ ቆጣቢ ነው በዚህ ድካም ላይ ስለውበቱ መጨነቅ አያስፈልግም😊በኦቭን ወይም በእንጀራ ምጣድ መቁላት
👉የፆም ከፈለጋችሁ ወተቱን መተውና በውሃ መጠቀም

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

16 Apr, 16:05


የሽንብራ ዓሳ ወጥ
አሰራሩ👉ለብስኩቱ 👉
የሽንብራ ዱቄት
👉ኮረሪማ
👉የተፈጨ ዝንጅብል
👉ጨዉ
ለስልሱ
👉ቀይ ሽንኩርት
👉ዘይት
👉ቲማቲም እንደ ፍላጎታችሁ
👉በርበሬ
👉ነጭ ሽንኩርት
ወደ አሰራሩ ስንመጣ
👉በጎድጓዳ ሳህን የሽንብራ ዱቄቱን ዝንጅብሉን ኮረሪማና ጨዉን ጨምሮ ማቡካት👉ያቦካነዉን በፈለግነዉ ቅርፅ ማዉጣት 👉 መጥበሻ ላይ ዘይት አግለን መጥበስ ወይም በምጣድ ማብሰል👉ጠብሰን ከጨረስ በኋላ ሳህን ላይ እናቆየዋለን👉እላይ እንደገለፅኩት ሽንኩሩቱን ዘይቱን እያደረግን በቅደም ተከተል እናቁላላለን ከተቁላላ በኋላ የጠበስነዉን ብስኩት እንጨምራለን ብስኩቱ በሰል ሲል ነጭ ሽንኩርትና ጨዉ ጨምረን እናወጣዋለን 👉ብስኩቱ መፍረስ የለበትም።

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

12 Apr, 15:40


በጣም ቀላል ነው የምትፈልጉትን አትክልት ለየብቻው በጣም ሳይበስል ዘይት ሳይበዛ ትጠብሱና ለብቻው ማስቀመጥ።
በመቀጠል ሽንኩርት በቁመቱ ከትፎ ማቁላላት ትንሽ ቢጫ ሲሆን ነጭ ሽንኩርት እና ዝንጅብል የተፈጨ ጨምሮ አንድ ላይ ማቁላላት ከዛ ከሙን ፥ቁንደ በርበሬ፥ጨው፤ ትንሽ የተፈጨ ቀረፋ ፤ኬሪ ቅመም ካለ ትንሽ፥እርድ፥ ፓአፓሪካ በመጨመር አንድ ላይ ማቁላላት በመቀጠል ቲሚቲም የበስለውን ትንሽ ቲማቲም ድልህ ጨምሮ በደንብ ካቁላላን በኋላ የሩዙን መጠን ያህል ውሀ ከልሶ ውሀው ሲፈላ እሩዝ አጥቦ መጨመር ትንሽ ሲመጥ የጠበስነውን አትክልት ከላይ አድርጎ ጋዝ በመቀነስ ማብስል ።
#yummi yummi