ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ @ferehaymanot Channel on Telegram

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

@ferehaymanot


የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፍሬ-ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ (Amharic)

የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፍሬ-ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት "ferehaymanot" በመነሻ የእናቴዎችን ለማህበረሰብ የሚያስችል መዳብ እና በስልት ጥንካሬዎች ያስተላለፉን የትምህርት ቤት ነኝ። ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ደግሞ ከማህበረሰብ እና ስነ-ሥርዓት በፊት እንደአክራሪ የመምህር ናት። በማንኛውም አካባቢ በተመሳሳይ አሠሮ ይሁን።

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

26 Jan, 19:28


በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ  ዝረወተ ዐፅም በዓል ዋዜማ ሥርዐተ ማኅሌት።

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

01 Jan, 08:09


https://www.ferehaymanot.org/

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

26 Dec, 12:35


1.​​የጥበብ ሰዎች መጡ
የጥበብ ሰዎች መጡ (፪)ሰምተውት በዜና
እያበራላቸው ኮከቡ እንደፋና(፪)


ሰማይና ምድር የማይወስኑት (፪)
ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት (፪)
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ (፪)
አገኘነው ዛሬ ከበረት ተኝቶ (፪)   

ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ (፪)
ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ (፪)
ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድኅን (፪)
ኩነኔን አጥፍቶ ክብሩን ሊያወርሰን (፪)
     አዝ = = = = =
ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም (፪)
ኀዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም (፪)
እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት (፪)
ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት (፪)
     አዝ = = = = =
ሰብአሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ(፪)
የእሥራኤል ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ (፪)
እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ (፪)
ዕጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግሥቱ (፪)

2.ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ

አንዲት ብላቴና የአስራ አምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ
በህቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ
       አዝ = = = = =
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ
ዐየነው አምላክን ሥጋን ተዋሕዶ
       አዝ = = = = =
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማሕፀን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ጌጠ የሔዋን አለኝታ
       አዝ= = = = =
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንዳንች አልተገኘም
በሀሳብ በግብር ንጹሕ ስለሆነች
የአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
      አዝ = = = = =
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማሕፀን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደቸው ድንግል የሔዋን አለኝታ
               
3.መድኃኒነ
መድኃኒነ ተወልደ ነዋ(፪)
ይእዜኒ ለሰላም ንትልዋ(፬)

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

22 Dec, 18:17


<ቡሩክ ዘወሀበነ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ>

"... እግዚአብሔር እኛን አገልጋዮቹን በሰላም ይባርከን ። የተቀበልነው ሥጋህና ደምህ ለሥርየት ይሁነን። የጠላትን ኃይል ሁሉ በመንፈስ እንረግጥ ዘንድ አሠልጥነን። ምሕረትን የተመላች ክብርት የምትሆን የእጅህን በረከት ሁላችን ተስፋ እናደርጋለን። ከክፉ ሥራ ሁሉ አርቀን። በበጎውም ሥራ ሁሉ አንድ አድርገን ።

ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም የሰጠን ቡሩክ ነው። ጸጋን ተቀበልን። ደኅንነትንም በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ኃይል አገኘን። አቤቱ ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ጸጋን ተቀብለን አንተን እናመሰግናለን።... "

                          ♦️(ቅዳሴ ሐዋርያት)


በሥጋ ወደሙ ከብራችሁ የክርስቶስ ሙሽሮች የሆናችሁ ሁሉ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ!!!
የጋራ ቁርባን መርሐ ግብሩ ሳምንት እሑድ ታኅሣሥ ፳ ቀን ፳፻፲፯ዓ.ም ይቀጥላል!

በሒደት ላይ ያለነውም የሚገባውን ሁሉ አድርገን ሥጋውን መብላት ደሙን መጠጣት ይገባናል! ይህ የክርስቲያን ሁሉ ቀዳሚ ተግባር ነውና!

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

20 Dec, 03:43


ንስሐ


ወንድሞቼ ሆይ! ጊዜ ሳለልን #ንስሐ እንግባና ለንስሐ የሚገባ ፍሬ እናፍራ፡፡ ጌታችን ምን እንዳለ እስኪ አድምጡ፡- “ንስሐ
ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይኾናል” /ሉቃ.15፡7/፡፡

ወንድሞቼ ሆይ! ስለምን ታድያ በኃጢአት፣ በስንፍና፣ በንዝህላል እንደተያዘዝን እንቆያለን? ስለምንድነው ተስፋ ቆርጠን የምንቆዝመው? በእኛ ንስሐ መግባት ምክንያት በሰማያት ታላቅ ደስታ የሚሆን ከሆነ ምንድነው የሚያስፈራን? ቅዱሳን መላዕክት ስለ እኛ ንስሐ እጅግ ደስ የሚላቸው ከሆነ ስለምንድነው እኛ ልል ዘሊል፣ ደንታ ቢስና ፈዛዛ የምንሆነው? የመላዕክት ጌታ ንስሐ ግቡ እያለ አስተምሮን ሳለ ምንድነው የምንፈራው? የማይከፈሉ ሦስት፣ የማይጠቀለሉ አንድ የሚሆኑ ሥላሴ ንስሐ እንገባ ዘንድ እየጠሩን ሳለ እኛ ያለምንም የንስሐ ፍሬ እንቆይ ዘንድ አግባብ ነውን?

ተወዳጆች ሆይ! በዚህ ጊዜአዊ ዓለም ርኵሰት ጣዕም አንታለል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳቱ የማይጠፋ ትሉ የማያንቀላፋ ምረረ ገሃነም ይጠብቀናል፡፡ ስለዚህ ከዘለዓለማዊው እሳት እንድን ዘንድ አሁን ጥቂት ብናለቅስ ይሻለናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! እስኪ እናስተውል፡፡ ስለምንናገረው ነገርም ችላ የሚለው ሰው ከቶ አይገኝ፡፡ ክርስቶስ ድንገት እንደ ብርሃን ብልጭታ ይመጣልና፡፡ ክርስቶስ ድንገት በመጣ ጊዜ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦም ለሁሉም እንደየሥራው ሲከፍለው ማየት አያስፈራምን? የዚያን ጊዜ ሁሉም የየራሱን ሸክም ይሸከማል፡፡እያንዳንዱ ሰው በዚህ ምድር የዘራውን ያጭዳል፡፡ ሁሉም ዕራቆቱ ይቆማል፡፡ ሁሉም ወደ ክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ይቀርባል፡፡ የዚያን ጊዜ ማንም ማንንም መርዳት አይችልም፡፡ ወንድም ወንድሙን ወይም ጓደኛ ጓደኛውን መርዳት አይችልም፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ልጆች ወላጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ባሎች ሚስቶቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ሁሉም በፍርሐትና በረዐድ በመንቀጥቀጥም የእግዚአብሔርን ፍርድ ይጠብቃል እንጂ ማንም ማንንም መርዳት አይችልም፡፡

ወንድሞቼ ሆይ!ታድያ ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የምንሰንፈው? ለምንድነው ልል ዘሊል የምንሆነው? ለምንድነው በምግባር በሃይማኖት የማንዘጋጀው? ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የማናስተውለው? ለምንድነው ቃለ ሕይወትን ለመስማት የማንቻኰለው? ስለምንድነው ቃለ እግዚአብሔርን የማንሰማው? ስለምንድነው ቃለ ክርስቶስን ችላ የምንለው? ቃሉ በዚያ ሰዓት እንደሚፈርድብን አትገነዘቡምን? ቃለ ነቢያት ቃለ ሐዋርያት በዚያ ሰዓት እንደሚፈርድብን አታውቁምን? ካላወቃችኁ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ያላቸውን አድምጡ፡- “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል” /ሉቃ.10፡16/፡፡ ዳግመኛም በሌላ አንቀጽ እንዲህ ብሏል፡- “የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው ርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርኩት ቃል ርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል” /ዮሐ.12፡48/፡፡ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድብን ቃሉስ የትኛው ነው? በወንጌሉ እንዲሁም በሐዋርያትና በነቢያት አድሮ የተናገረው ቃሉ፡፡ እንኪያስ ወንድሞቼ ሆይ! ቃሉን ችላ የምንለው አንኹን፡፡ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም” ያለውን አንርሳው /ማቴ.24፡35/፡፡

እንኪያስ እጅግ የምወዳችሁ ሆይ! ኑ! አስፈሪው ቀን ሳይመጣ ቃሉን ሰምተን ንስሐ እንግባ፡፡ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንቀበል፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ ምሕረቱን እንድንቀበል እንዲህ እያለ ያበረታታናልና፡- “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ” ማቴ.11፡28፡፡ በዚህ ቃሉ ትዕግሥተኛው፣ አፍቃሪውና ሰው ወዳጁ ጌታ ሁላችንም እንድን ዘንድ ይጠራናል፡፡ የጠራው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ አይደለም፤.“ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ” ብሎ ሁላችንም እንጂ፡፡ “ባለጸጋም ቢሆን ድኻም ቢሆን ሁሉም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፡፡ ወደ እኔ የሚመጣውስ ማን ነው ትዕዛዛቴን የሚጠብቀው፤ ቃሌን የሚሰማው፤ በላከኝም የሚያምነው፡፡” የክርስቶስን ቃል ሰምቶ ንስሐ የሚገባው ንስሐም ገብቶ የንስሐን ፍሬ የሚያፈራ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ የማይሰማው ግን እጅግ ጐስቋላ ሰው ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው” /ዕብ.10፡31/፡፡

ቅዱስ_ኤፍሬም

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

22 Nov, 05:22


የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ፡፡

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ዛሬ ኅዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሃይማኖት መምህር ኢሳይያስ ቸርነት እና የወረዳ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ ክፍላት ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

በዕለቱም የደብሩ ሊቃውንት
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኀይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤ
ይህ የኀይል የብርታት አለቃ የሆነ ሚካኤል በችግራችን ጊዜ ይለምንልን ረዳትም ይሁነን በሚል ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን
የሰንበት ትምህርት ቤቱ መዘምራንም
ባሕረ ግርምተ ገብረ ዐረፍተ ሊቀመላእክት ወሴሰዮሙ መና ሕብስተ ኪነጥበቡ ዘአልቦ መስፈርተ
"አስገራሚዋን ባሕር ግድግዳ አደረገ  የመላእክት አለቃ መና እንጀራን መለኪያ በሌለው ኪነጥበቡ መገባቸው"
የሚል ዝማሬን አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም መጋቤ አእላፍ ኤፍሬም በየነ
"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል" በሚል ኃይለ ቃል ወንጌልን አስተምረዋል።

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

08 Nov, 03:20


በፍሬሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍትና ቤተመዛግብት ክፍል ለ12ኛ ጊዜ የተዘጋጀው የመጻሕፍት ዳሰሳ መርሐ ግብር ተካሔደ።
በዛሬው ዕለት 28/02/2017 የተካሔደውን ዳሰሳ ያቀረቡልን የደብራችን አገልጋይ የሆኑት ርእሰ ደብር መንግሥቱ ዘለዓለም( የሐዲሳትና የአቋቋም መምህር) ሲሆኑ በአባጽጌ የተደረሰው ማሕሌተ ጽጌ ደግሞ ለዳሰሳ የተመረጠው መጽሐፍ ነበር። በወርኀ ጽጌ አገልግሎት ላይ የሚውለውና በምእመናንና በሊቃውንቱ በታላቅ ፍቅርና ደስታ ለምስጋና የሚውለው መልክአ ማኅሌተ ጽጌ ከነገረ ሃይማኖት; ከነገረ ማርያም;ከነገረ ቅዱሳንና ከጸሎት አንፃር ይዘቱ በሚገባ በመምህሩ የተብራራ ሲሆን በሥርዓተ ማሕሌቱ ዙሪያም ከተሳታፊዎች የተነሡ ጥያቄዎችን ትንተና ሰጥተውበታል። በዕለቱም የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም  ቤተክርስቲያን ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት አባል የሆነው ዘማሪ  ዲያቆን ኢዮብ ካሳ ዝማሬዎችን ያቀረበ ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል ዲ/ን ኢዮብ ካሳዬ ዝማሬዎቹን በመሰንቆ አጅቧል። የንባብ ባህል እንዲያድግ ጠቃሚ የሆነው ይህ መርሐግብር በቀጣይ 13ኛ ዙር መርሐግብሩን በኅዳር 26 2017 እንደሚያደርግ ቤተመጻሕፍት ክፍሉ ገልጿል። ለዳሰሳ የተመረጠውም መጽሐፍ በዲያቆን አቤል ካሳሁን የተጻፈው "መላእክት" የተሰኘው መጽሐፍ ሲሆን የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች አስቀድመው መጽሐፉን አንብበው
ለውይይት እንዲዘጋጁ ተገልጿል።

ፍሬ ሃይማኖት ዘ ደብረ ይድራስ

10 Oct, 19:53


በፍሬሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍትና ቤተመዛግብት ክፍል ለ11ኛ ጊዜ የተዘጋጀው የመጻሕፍት ዳሰሳ መርሐ ግብር ተካሔደ።
በዛሬው ዕለት 30/01/2017ዓ.ም የተካሔደውን ዳሰሳ ያቀረበልን የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል የሆነው ዲያቆን ናትናኤል ወንድሙ ሲሆን በብጹዕ አቡነ መቃርዮስ(የግብፅ ጳጳስ)
ተጽፎ በአዜብ በርሄ የተተረጎመው ኢትዮጵያዊው መናኝ የተሰኘው መጽሐፍ ደግሞ ለዳሰሳ የተመረጠው መጽሐፍ ነበር። በኢትዮጵያዊው ጻድቅ መነኵሴ በአባ ገብረክርስቶስ ሕይወትና ተጋድሎ ላይ የሚያተኩረው ይህ መጽሐፍ በተለይ ለወጣት ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሕይወት ትልቅ ትምህርት የሚሰጥና መንፈሳዊ በቍዔት ያለው በመሆኑ ሊነበብ የሚገባ እንደሆነ የማጠቃለያ ሐሳብ የሰጡት የሰንበት ትምህርት ቤቱ አንጋፋ አባል የሆኑት መምህር ተስፋዬ የኔዓለም አሳስበዋል። በዕለቱም የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም  ቤተክርስቲያን ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት አባል የሆነው ዘማሪ ያሬድ አበበ ዝማሬዎችን ያቀረበ ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል ዲ/ን ኢዮብ ካሳዬ ዝማሬዎቹን በመሰንቆ አጅቧል። የንባብ ባህል እንዲያድግ ጠቃሚ የሆነው ይህ መርሐግብር በቀጣይ 12ኛ ዙር መርሐግብሩን በጥቅምት 28 2017ዓ.ም እንደሚያደርግ ቤተመጻሕፍት ክፍሉ ገልጿል።