Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ @getnetalmawt Channel on Telegram

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

@getnetalmawt


ውይይት፣ መደማመጥና በኃሳብ ብዝሃነት ማመን የስልጡን ማኀበረሰብ መገለጫዎች ናቸው!!

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ (Amharic)

ጌትነት አልማው ጥሩነህ - አስተዳደርን እና መደማመጥን በባህርዳር ብዝሃነት ውስጥ ማመነኝን ማኀበሪያን ድረገፍ ያለን የስልጣን ማኀበረሰብ መገለጫዎችን በነጻ ማንበብን ለማዳን እና ለወቅታዊ ሀምሌነታቸው እናውቃለን። የጌትነት አልማው ጥሩነህ ማደምሰስ እና ማግባት አሁን ይችላል። እናውቃለን ከንጋት እንድናችሁ።

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

16 Aug, 11:45


አላችሁ ወይ

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

27 Feb, 16:50


አድዋ የጥቁር ህዝቦች የሰውነት ማረጋገጫ ማህተም ነው !!

|አድዋ 0 0 ፕሮጀክት ስንል ምን ማለታችን ነው? ....📖|

✌️

ከታች በምስሉ የሚታየው አዲስ አበባ/አራዳ ከአጼ ምኒልክ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት አጠገብ በመገንባት ላይ የሚገኘው የአድዋ ዜሮ ዜሮ የግንባታ ፕሮጀክት ጠቅላላ ፊዚካል አፈጻጸም 78.2% ደርሷል !!

“ኢትዮጵያን የያዘ ዓባይን ይይዛል፤ ዓባይን የያዘ ግብጽን ይይዛል፤ ግብጽን የያዘ ስዊዝ ካናልን ይይዛል፤ ስዊዝ ካናልን የያዘ ዓለምን ይይዛል” በሚል ዘመን አይሽሬ ዕሳቤ በየዘመኑ በየዘመኑ የተነሱ ኃያላን ኢትዮጵያን ለመውረር ጦር ሲስበቁ የኖሩ ሲሆን ኢትዮጵያዊያንም ዳር ድንበራቸውን ላለማስደፈር በጽንዓት ቆመው ሲዋጉ ኖረዋል። አባቶች ለፈጣሪያቸው ጸሎት ሲያደርሱ “አገራችን ኢትዮጵያን ዳሯን እሳት መሃሏን ገነት አድርግልን” የሚሉት ለምን እንደሆነ ግልጽ የሆነልዎት ይመስለኛል። በዚህ የተነሳ የኢትዮጵያ ታሪክ በየዘመናቱ ያለፉ የኢትዮጵያ ትውልዶች የአገራቸውን ዳር ድንበር ላለማስደፈር ያደረጉት የጦርነት ተጋድሎ ታሪክ ሆኖ እናገኘዋለን። እንሆ ታሪካችን የጦርነት ታሪክ ቢሆንም በየዘመኑ የነበሩ ተከታታይ የኢትዮጵያ ትውልዶች የአገራቸውን ዳር ድንበር በውጭ ወራሪ ላለማስደፈር ሲዋደቁ የተገለገሉባቸውን የጦር መሳሪያዎች (Military armament) የሚያሳይ “የጦር ሙዚየም (War museum)” የለንም። ይህ የታሪካችን አንዱ ጎደሎ ክፍል ነው፤ በነበር ሊቀር ወራቶች ብቻ ይቀሩናል !!

በግንባታ ሂደት ላይ ያለው የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነ “#የጦር_ሙዚየም (War museum)” ባለቤት በማድረግ የታሪካችንን ጎደሎ ክፍል ለመሙላት የበኩሉን አይነተኛ ሚና እንደሚያበረክት ይጠበቃል — ብዙ የጦር ሙዚየም እንደሚያስፈልገን ልብ ይሏል!!

🐎

አድዋ 0 0 ፕሮጀክት (KM 0 Adwa Project) ስንል !...
~

የኢትዮጵያ የቦታ እርቀት መለኪያ ነጥብ (0 ነጥብ) አዲስ አበባ/አራዳ ነው። በዚህ መሰረት በአራቱም አቅጣጫ ያለ ቦታ/ከተማ ከአዲስ አበባ ያለው እርቀት የመነሻ መለኪያ (ዜሮ ነጥብ) የአራዳ ጊዮርጊስን ጨምሮ የአጼ ምኒልክ ሐውልት ያለበት ሥፍራ ነው። የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የከተሞች እርቀት መነሻ በሆነው ስፍራ ላይ በመገኘቱ የአድዋ ሙዚዬም ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት (Kilometer Zero Adwa Project) ተብሎ እንዲጠራ ሆኗል (ዜሮን በሌላ አግባብ የወሰዱ አንዳንዶች ያለባቸውን ብዥታ ለማጥራት ጭምር ነው 😂)።


የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የጋራ ድል ታሪክ ነው !!

የአድዋ ድል ከሮማዊያን ሥልጣኔ ማግስት ጀምሮ “ነጭ የሰው ዘር የሁሉም የሰው ዘር የበላይ ነው” የሚለውን ለዘመናት የገነገነ ስሁት ዕሳቤ ከመሰረቱ በመናድ “ጥቁር የሰው ዘር ከሁሉም የሰው ዘር ጋር ዕኩል መሆኑን” በደምና አጥንት የተጻፈበት የመላው የጥቁር ህዝቦች ሁሉ አንጸባራቂ የጋራ ድል ነው (Adwa victory is more than victory in a war. It is a milestone victory in the fight against racial inequalities between black and white race)። ታዲያ #አደዋ_ዜሮ_ዜሮ የሚለው ቃል የጥቁር ህዝቦች “የሰውነት ታሪክ” መነሻ/ጅማሮ በመሆኑ ስያሜው የድሉን ፋይዳ በትክክል የሚገልጽ አይደለምን?

🥢

ይኸው ነው

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

25 Feb, 18:32


Nobel Prize Award, American Academy of Achievement Award... Open Magazine List of African Democratic Leaders Recognition...

የዶ/ር ዐብይ አህመድ ሽልማት የኢትዮጵያ ሽልማት ነው !!

👇

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚ/ር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አለቃ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ሲያጠፋ የሚገስጸው/የሚቀጣው ጥሩ ሲሰራ “በርታ ከጎንህ ነን!” የሚለው የበላይ አለቃ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው — አለቀ፤ደቀቀ !!

“ሰላማዊ የመንግስት ሽግግር በመምራቱ፤ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ‛ሰላም አልባ ጦርነት አልባ’ የነበረውን ግንኙነት ትንግርት በሚመስል ሁኔታ ለፈታበት ጥበብ (ኢሱ እያለ አለ ደጺ🤣)፤ በመንግሥት ተይዘው የነበሩ ግዙፍ የልማት ተቋማት ውስጥ የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ ቆራጥ አመራር በመስጠት ለግሉ ዘርፍ መነቃቃት ለሰጠው የላቀ አመራር፤... ወዘተረፈ” በሚል ለዶ/ር ዐብይ አህመድ #የኖቬል_ሽልማት ሲበረከት እውቅና የተበረከተው ለኢትዮጵያ ነው/ነበር። መሰረታዊ ቁም ነገሩን ሆን ብለው በማዛባት ሽልማቱ በግሉ ለዶ/ር ዐብይ አህመድ እንደተሰጠ አስመስለው ሽልማቱን እንደ መያዣ በመቁጠር (በእነሱ ቤት በኖቤል ሰንሰለት አስረው ተጠሪነቱን ለእነሱ ለማድረግ ነበር🤣) ኢትዮጵያ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተከፈተባትን ጦርነት ተከትሎ “የኖቤል ሽልማት የተሰጠው መሪ ጦርነት ሊያውጅ አይገባም፤🤣 የወሰደውን የኖቤል ሽልማት ይመለስ፤ 😂...ወዘተረፈ” ሲሉ የአብቹ መልስ “በኢትዮጵያዬ ከመጣችሁ አንገቴን እሰጣለሁ” የሚል ነበር !! 💪 ስናሳጥረው በአካል ጦር ሜዳ ወርዶ የእነሱን ተላላኪ እንደ ነዶ አበራይቶ ኢትዮጵያን በጽኑ መሰረት ላይ አቆማት — ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነዋ !!

ለኢትዮጵያ መሪዎች (መለስ ዜናዊም ይሁን ፕ/ት መንግስቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይሁን ዶ/ር ዐብይ...) የሚሰጥ ቀጠናዊ፣ አሕጉራዊም ሆነ አለም ዓቀፋዊ እውቅና/ሽልማት በግለሰብ ደረጃ ለመሪዎች የተበረከተ/የሚበረከት እውቅና ብቻ ሳይሆን እንደ አገር ለኢትዮጵያ የተሰጠ እውቅና ጭምር ነው። የአገራት መሪዎች Figurehead role (a complex role that involves a leader acting as a representative for a nation in all its formal matters) እንደሚጫዎቱና ለእነሱ የሚሰጠው ሽልማት ለአገር የሚበረከት ሽልማት መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው — አውቀን እንታረም !!

ኢትዮጵያን የሚወድ ዜጋ ሁሉ በመሪዎቿ ሽልማት ሐሴት ያደርጋል !! የተሸለመው የሚወደው ወይም የሚጠላው መሪ ብቻ ሳይሆን የሚወዳት እናት አገሩ ኢትዮጵያም ነች !!

🦅

ይኸው ነው

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

23 Feb, 17:43


ከኤሌክትሪክና ስንዴ ሽያጭ እስከ አውቶብስ ግዥ —የድንቁርችን ይታወቅልን ጩኸት

በር !...🔑

.... ማነወር እንጂ መማር በማይፈልግ የጉግማንጉግ ሰፈር ከበር ላይ ቆመህ መጮኸ እንጂ ወደ ውስጥ ገብቶ መነጋገር እርባና ቢስ ነው። ተናጋሪ እንጂ አድማጭ በሌለበት ህዝብ መሃል ቆሞ በመስበኩ “ሙሴ በምድረ በዳ ይሰብክ ነበር...” ተብሎ ተጽፎለታል። በምድረ በዳ ውስጥ ለመከበር #ቦዳና_ቦንዳ መሆን በቂ ነው። ለማንኛውም በሩን ገርበብ አድርገን ወደ ውስጥ እናጮልቅ!... 🗝️ 👨‍👩‍👧

1] The ABC of International Economics/Trade
📚

°° ስለ አለም አቀፍ ንግድ (International trade/economics) ጽንሰ-ሃሳብ/ምንነት፣ ፍቺ፣ ጥቅሞች፣ ወደ አለም አቀፍ ንግድ መግብያ አማራጮች፣ የዘርፉ ጥቅሞችና ፈተናዎች፣... ወዘተረፈ ማተት በቻልን ነበር !...

2] የአለም አቀፍ ንግድ ኀልዮቶች/Theories of International Trade
📖

°° “ያለህን ምርትና አገልግሎት ሁሉ ወደ ውጭ ገብያ አቅርቦ ከፍተኛ የውጭ የምንዛሬ ሪዘርቭ የሚይዝ በተቃራኒው ምንም አይነት/ትንሽ ምርትና አገልግሎት ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባ አገር ጠንካራ ነው” ከሚለው ክላሲክ ከሆነው የሸቀጥ ኀልዮት (Mercantilism theory) ተነስተን አሁን ባለንበት ዘመን በሚንሸራሸሩት የውጭ ንግድ ኀልዮቶች ዙሪያ በተመላለስን ነበር። ታዋቂው እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት አዳም ስሚዝ “አንድ አገር ሃያል የሚባለው ምርትና አገልግሎቱን ከሚሸጥላቸው አገራት አኳያ ሲመዘን ውጤታማና ምርታማ (effective and efficient) የሆንባቸውን ሸቀጦችና አገልግሎቶች ሁሉ ወደ ውጭ ገብያ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ መያዝ ሲችል” ነው በማለት ያቀነቀነው ኀልዮት (Theory of Absolute Advantage) መነሻው አስቀድመን የጠቀስነው የሸቀጥ ኀልዮት (Mercantilism theory) ነው። ከ 18 በላይ የአለም አቀፍ ንግድ ኀልዮቶች መኖራቸውን ልብ ይበሉ!...

¢¢ የአዳም ስሚዝ ኀልዮት “የኢንዱስትሪ አብዮትን ተከትሎ ለተፈጠረው የቅኝ ግዛት መስፋፋት ወሳኝ ምክንያት ነው” የሚል ክርክር አለ።

¢¢ የኢፌዲሪ ጠ/ሚር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው “ድሃ አገር ሉዓላዊነት የለውም” ሲሉ የእውቀት ድሃ የሆኑት ማሽሟጠጣቸው አይረሳም... ለነገሩ እሳቸውም “ኢኮኖሚስት ነኝ የሚል መኪና ግን የሌለው ሰው አለ... በማለት ኢኮኖሚስት ነን የሚሉትን በሳማ ገርፈውልኛል !...🤺

፫| የግብይት ልውውጥ ሚዛን/ Balance of Payment

💰

°° በአንድ የበጀት አመት ውስጥ ምርትና አገልግሎትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ በሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ግኝት (Value of Exports) እና ከውጭ ለተገዙ ምርቶችና አገልግሎቶች የዋለውን ክፍያ (Value of Imports) በማቀናነስ ስለሚመዘገበው የግብይት ልውውጥ ሚዛንና (aka Balance of Payment and it can be positive, negative, or zero) ጉድለቱን ለመሙላት መወሰድ ባለባቸው ስልቶች ዙሪያ መተንተን በወደድን ነበር !...
🚌

2.1| ከእራሳቸው ተርፏቸው ወደ ውጭ ገብያ የሚልኩ አገራት ውስን ናቸው። የሾርት ሚሞሪ ባለቤት መሆንህን አስታውሸህ ኢትዮጵያ ለሱዳን፣ ለጅቡቲና ለኬንያ ኤሌክትሪክ የሸጠችው ኤሌክትሪክ ተርፏት ነው ወይ? ኢትዮጵያ ለጅቡቲ ውሃ የሸጠችው ውሃ ተርፏት ነው ወይ? ታዲያ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ስንዴ አቀረበች ስትባል አይንህ ደም ለብሶ አፍህን የመረረህ የድንቁርና መጠንህ ከፍ በማለቱ ነው ብልህ ይከፋሃል ወይ?... ጓዶች!...በተለይም “ተምረናል” የምንል ሰዎች አደባባይ ላይ እርቃናችንን ቁመን “ድንቁርናችን ይታወቅልን” የሚለው መንገላጀጅ የሚያበቃው መቼ ነው? ኧረ መቼ ነው? 👁️

2.2 ከሰሞኑ ጋቢየን አቀብሉኝ እያልክ የምትነፋርቅበት #የባስ_ግዥ ቁልፍ ጉዳይ ያለው እዚህ ጋ ነው። የተማረና ተምሮ ያልተማረው በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ሳይገባ በጋራ ውጭ ላይ ቆሞ የሚነፋረቅበት ጉዳይ !! በባሶች ግዥ ዘረፋ ተፈጽሟል ብሎ በአደባባይ የሚጽፍ ሰው ለከት የለሽ ድንቁርናውን አደባባይ ላይ አስጥቶ ሳቁብኝ/ተሳለቁብኝ የሚል ጅላንፎ ነው — Period 💪

2.3| ቻይና ተከታታይነት ያለው ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ግኝት (High positive BOB) በማስመዝገቧ ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የቅነሳ እርምጃ በመውሰድ በተቃራኒው ውስብስብና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በሚጠይቁ (Capital intensive) ቴክኖሎጂዎችና መሰረተ-ልማቶች ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በተጠና ሁኔታ እድገታቸውን እየቀነሱ ነው (ቀጣይነት ያለው ጤናማ ኑሮ ለመኖር ለጊዜው የገጠመኸን ከፍተኛ የደም ግፊት ከመቀነስ ሂደት ጋር አጢነው 💉)

🦅

ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትቀጥላለች

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

17 Feb, 18:19


የሚያላዝነውን ውሻ ሰንሰለት የያዘው ጌታ መቐለ ይኖራል !!

🐕

በቀን 01/06/2015 ዓ.ም በብጹዕ ፓትሪያርክ አባ ማትያስ ለተጻፈው የሰላም ንግግር ጥሪ በዛሬው ዕለት ማለትም በ 10/ 06/2015 ዓ.ም በ 06 ገጽ አባሪ ምላሽ ያቀረቡ በትገራይ የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት “...ለዘመናት ተዳፍኖ የነበረውና ዳግም የተደራጀው መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ትግራይ ጽ/ቤት የሚፈርሰው በትግራይ በምንገኝ ሊቃነ ጳጳሳት መቃብ*ር ላይ ነው” የሚል ምላሽ አቅርበዋል — No more, no less!

መቐለ ከሚገኝ ዋና ሰርቨር በሚወረወርለት ሴራ 24/7 ሰለሜ የሚጨፍረው ጀንፈል በአካል አግጦ አፍጦ የቆመውን “መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንን” አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ኬሪዳሽ ብሎ በማለፍ “በኦሮሚያና ብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” ላይ ይጮሃል፤ ይራገማል፤ አመድ ነስንሼ ማቅ ለብሼ እንከባለላለሁ፤ ሰልፍ እወጣለሁ ሰማዕት እሆናለሁ፤... ጲሪሪም ታንታራም ይላል። 😔

“በትግራይ የተመሰረተው መንበረ ሰላማ በምሥረታ ሂደት ላይ ላለው “የኦሮሚያና ብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” እውቅና እንሰጣለን፤ ለኋላ-ቀር አሃዳዊያን መስሚያችን ጥጥ ነው...” የሚል አዲስ የፖለቲካ አሰላለፍ ለማነበር እየተሰራ ስለ መሆኑ ጉግማንግጉ አይገባውም...

በአንገቱ ሰንሰለት የገባለትና የጌታውን ፊት እያነበበ በአላፊ አግዳሚው ላይ የሚጮኸው የውሻው ጌታ መቐለ ከትሟል!!

🦅

ጥርስና ጥፍሩ የወላለቀ ጌታው በአንገቱ ላይ የገባለትን ሰንሰለት ይዞ ቻዝ እያለ በሚያስጮኸው ውሻ የሚገታ ጉዞ የለም — ግመሉ ጉዞውን ቀጥሏል!! 🐪

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

15 Feb, 17:19


እውነትን አጥብቀህ ያዛት፤ በመጨረሻ አሸናፊ ናትና!!

🕊️

በእቅፏ ያሳደገችኝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያጋጠማትን ችግር በድርድር እንደምትፈታው አስቀድሞም ሙሉ እምነት ነበረኝ። እንሆ እምነቴ እውነት ሆነ!!

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የገጠመውን የውስጥ ችግር ወደ ቤተ መንግስት ለመግባት አቋራጭ/ማሳላጫ አድርገው ለመጠቀም የሞከሩ የከሰሩ ፖለቲከኞች በእኛ ላይ መጠነ ሰፊ የተቀነባበረ የሥም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብን ነበር!!

የትናት እስረኞች ሆነን የነገ ተስፋችንን የምናጨልም የዋሆች አይደለንምና እንሆ ትናንትን ለትናንት አስረክበን ትኩረታችንን በነገ ብሩኀ ተስፋችን ላይ ብቻ እናደርጋለን!!

📺

የዛሬ ሣምንት ማለትም በ 30/05/2015 ዓ.ም በፕራይም ሚዲያ/ PRIME MEDIA የነበረኝን ሙሉ ቆይታ ይሰሙት ዘንድ በታላቅ አክብሮት እየጠየቅሁ ጊዜ ከሌለዎት ከ 14፡22 ደቂቃ እስከ 30፡20 ያለውን እንዲያምጡ እጠይቃለሁ!!


በመጨረሻ ዘላለማዊ አሸናፊዋ እውነት አሸነፈች

🦅

https://www.youtube.com/live/CUtmfGtN1iM?feature=share

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

15 Feb, 16:11


“ሰላምን ሻት ተከተላትም” መዝሙር ፴፫፥፲፬

🕊️

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

11 Feb, 17:26


ጉዳዩን ዘግቼ ከማለፌ በፊት!...

🥢

የገብያ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንዲሉ አበው ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኀዶ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያጋጠማትን ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ የወሰዱ “ጥንብ አንሳ ፖለቲከኞች” ሰማያዊ ተልዕኮ ባላቸው አባቶች ልብሰ ምንኩስናና አክሴማ ጀርባ ተሸሽገው ምድራዊ የሥልጣን ዘውድና ካባ ሊጭኑ ሲራኮቱ መሰንበታቸው የሚታወስ ነው።

ጥበብ በተሞላበት እልኸ አስጨራሽ ትንቅንቅ የጥንብ አንሳዎችን መንቁር ከቤተ ክርስቲያኗ ላይ በማንሳት የቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ ጉዳይ በእራሷ በቤተ ክርስቲያኗ አባቶች እንዲፈታ አቅጣጫ በመቀመጡ “የጠላቴ ጠላት የእኔም ጠላቴ ነው” በሚል የተሰባሰቡ ጥንብ አንሳዎች በአረጀ መንቁራቸው እርስ በእርስ መንቆራቆስ ጀምረዋል - ኧረገኝ ገና ምኑ ተነካ 😂

የመንጋው አዝማቾች ከትናንት በቀጠለ መሰሪ አካሄዳቸው “እኔን ጨምሮ የተወሰኑ ሐቀኞችን ፀረ-ኦርቶዶክስ አድርገው” ለማቅረብ የተጓዙበት ርቀት አግራሞት ጭሮብኛል። “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው” የሚል ጸሎት በማቅረብ እንሆ ፋይሉን ዘግተነዋል!!

🦅

ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትቀጥላለች!!!

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

11 Feb, 16:39


የቴሌቪዥን ጣቢያችሁን ወደ OBN Horn Africa ብትቀይሩ በዚያ እየተደመጥን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው!... 📺

🥢

ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትቀጥላለች!!

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

11 Feb, 16:16


በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ በተለይም በዋናነትም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኀዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጠረው የውስጥ ችግር ዙሪያ ከሁለት ቀን በፊት በ Prime Media/TV የነበረንን ቆይታ እንዲከታተሉ በታላቅ አክብሮት እንጋብዛለን!!🙏

https://www.youtube.com/live/CUtmfGtN1iM?feature=share

🥢
ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትቀጥላለች!!!

Getnet Almaw Tiruneh — ጌትነት አልማው ጥሩነህ

11 Feb, 13:13


በአንድ ወቅት የየመን የታሪክ ተራኪ አሁን የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን ግዕዝ በማስረጃ የመን ዲንጋይ ላይ ተፅፈው ሲያሳየን አጋዚያን የተባለው ህዝብ የሚጠቀምበት ቋንቋ መሆኑን ለአረብ መሪዎችን ሲያስተምራቸው በምስል አይቸ ገርሞኝ አላበቃ ብሎ ነበር። አሁን አረብ ኤምሬትስ በሀይል የያዘችው የሶቆጥራ ወደብ የሀበሻ ወደብ መሆኑንና አሜሪ የተባሉ ጥቁር የአጋዚ ዘሮች ነን የሚሉ ህዝቦች የሚኖርበት አገር መሆኑን ፕሮፌሰር ዛህራኒ ሰንዶት አይተናል። ሀበሻ ወይም በነሱ አጠራር ( ሀበሸት) አገር ሁሉ የአማርኛ ፊደሎችና አስገራሚ ቅርሶችን የያዘ ትልቅ ተራራ አለ እሱም አሁን ኢትዮዽያ ኤርትራ ጅቡቲ ሱማሊያ ተብለው የተከፍፈሉ ነገር ግን መነሻ አገራቸው የመን የሆኑ ህዝቦች ናቸው ብለው የመኖች የሰየሙት አገር ነው። በሳኡዲ ጅዛን ክፍል የተገኙ የድንጋይ ላይ ፁሁፎች ግዕዞች ናቸው።

በዚህ ብቻ አልበቃ ያለው የሀበሻ ታሪክ ከ5 ቀን በፊት 40 አመት የፈጀው የሳኡዲ የታሪክ ተመራማሪዎች በነብዮ መሃመድ (ሰአወ) ዘመን የነበረውን ትልቁን የሀበሻ የገበያ ማዕከል አገኘሁት ስትል አውጃለች። ከሶቆጥራ እስከ አደን ከጅዛን እስከ መካ ድረስ የኛ ታሪኮች አሉ።

ሱሌማን አብደላ

🦅

የታላቋን ኢትዮጵያ ደረጃ የሚመጥን ታሪክ ለመስራት ቆረጠን ተነስተናል!!!