Afar People's Voice - APV

@afarpeoplesvoice


ይህ የቴሌግራም ቻናል ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች የሚያቀብል የእርሶ ገፅ ነው።

Afar People's Voice - APV

22 Aug, 09:44


#Egypt

በታሪክ የአስክሬን ማድረቂያ መድሀኒት(መሚ የተባለው ቅጠል) ያገኘቱትና ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙት ግብፆች መሆናቸው ይታወቃል።

የሚገርመው ከታች ያለው የደረቀ አስክሬን በወቅቱ የግብፅ ንጉስ የነበረው Tutankhamun አስክሬን ነው። ሰውዬው የሞተው ከ 5500 በፊት ነው። በ 19 አመቱ ነበር በቢላ ጀርባው ላይ ተወግ*ቶ የሞተው።

በቀኝ እጁ ላይ የበሬ ምስል ተነቅሶዋል። ንቅሳት(Tattoo) ሚባለው ነገር ያኔ ነው ግብፆች የጀመሩት። ያኔ በሬ የሀይልና የትልቅነት ምልክትም ተደርጎ ይወሰድ ነበር።

ታሪኩ የግብፅ ቢሆንም አስክሬኑ የሚገኘው ግብፅ ውስጥ እንዳይመስላቹ እንግሊዝ በሚገኝ ሙዚየም ውስጥ ነው ያለው። ከ 100 አመት በፊት እንግሊዝ ግብፅን ስትገዛ ያኔ የዘረፈችው ቅርስ ነው ማለት ነው።

Afar People's Voice - APV

21 Aug, 09:58


የየመን ድንበርን ለመሻገር የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች መገደላቸውን ሂዩውማን ራይትስ ዎች ገለጸ
=======#=======

ሰኞ ነሐሴ 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩውማን ራይትስ ዎች እ.ኤ.አ ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ወር ድረስ፤ የየመን ድንበርን ለመሻገር የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ዛሬ ነሐሴ 15/2015 ባወጣው የምርመራ ሪፖርት፤ “በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከየመን ለመሻገር ሲሞክሩ የሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል” ብሏል፡፡

መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፣ ኒውዮርክ ያደረገው የሰብዓዊ መብቶች ተከራከሪው ድርጅት፤ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሕጻናት እና ሴቶች ሞት፣ የአካል ጉዳት እና ስቃይ የሳዑዲ ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርጓል።

ድርጅቱ ከምስክሮች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፣ በሳተላይት ምስልና በቪዲዮ በታገዘው73 ገጽ ሪፖርት፤ “ግድያው ሰፊና ስልታዊ መሆኑን” ገልጿል፡፡

በዚህም እማኞች፤ “የሳዑዲ ወታደሮች ከባድ መሳሪያዎች በመጠቀም ድንበሩ ለማቋረጥ በሚሞክሩ ሰዎች ላይ ኹሉ ተኩስ እንደሚከፍቱና ጉዳት ደርሶባቸዉ ሕይወታቸዉ ያላለፈ ሰዎችንም እየፈለጉ ወደ ማጎሪያ ካምፕ እንደሚያስገቡ ነግረውኛል” ብሏል።

“የሳዑዲ ጦር፤ ድንበር ጠባቂዎችንና ምን አልባትም ሌሎች ልዩ ክፍሎችን ጨምሮ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመቶዎች ወይንም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መግደላቸውንና በሕይወት የተረፉትንም ለእስር፣ ለእንግልት፣ አስገድዶ መድፈርና ለሌሎች ኢ ሰብዓዊ ተዳርገዋል” ሲልም በሪፖርቱ ገልጿል።

አዲስ ማለዳ

Afar People's Voice - APV

21 Aug, 09:58


ከዛሬ 3,300 ዓመታት በፊት የተገነባው ዕድሜ ጠገብ የፈረስ ጋሪ መሸጋገሪያ ድልድይ ዛሬም ጥቅም ላይ እየሰጠ ይገኛል። በግሪክ የሚገኘው ይህ የአርካዲኮ ድልድይ በ1300 እና 1190 መካከል የተገነባ ሲሆን ይህም አሁንም አገልግሎት ከሚሰጡ ውስን ጥንታዊ ቅርሶች መካከል አንዱ ያደርገዋል።

Afar People's Voice - APV

18 Aug, 10:23


በጎረቤት ሀገር ኬንያ ዜጎች በየሳምንቱ ወደ አደባባይ በመውጣት መንግሥት ለኑሮ ውድነት ትኩረት እንዲሰጥ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ሲሆኑ በሀገሪቱ በሞምባሳ ነዋሪ የነበረ አንድ ወጣት በኑሮ ውድነቱ ተማርሮ አደባባይ ራሱን በእሳት አያይዟል፤ ይሁንና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ተረባርበው ህይወቱን ቢታደጉም ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰበት ታውቋል።

Afar People's Voice - APV

14 Aug, 20:10


በአማራ ክልል “ሁሉንም ኃይሎች” ያካተተ “ጊዜያዊ አስተዳደር” እንዲቋቋም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጠየቁ

የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአማራ ክልል “ሁሉንም ኃይሎች” ያካተተ “ጊዜያዊ አስተዳደር” እንዲቋቋም ጠየቁ። አቶ ገዱ በአማራ ክልል ያለውን “ችግር በቅንነት ለመፍታት” ፖለቲካዊ ንግግር መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን ያመጣውን “ለውጥ” ከመሩ ባለስልጣናት አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት፤ በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ከመጽደቁ በፊት ባስደመጡት አስተያየት ነው። የገዢው ብልጽግና ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ገዱ፤ ዛሬ በተካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የተገኙት፤ በአማራ ክልል ለተፈጠረው ችግር “በቅንነት” ሃሳባቸውን በማቅረብ “አስተዋጽኦ ለማበርከት” በማሰብ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአማራ ክልልን ለአምስት ዓመታት የመሩት አቶ ገዱ፤ በክልሉ በአሁኑ ወቅት ያለውን ችግር ለመፍታት መፍትሔው “የፖለቲካ ውይይት፤፡ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። “ይህን ችግር በቅንነት ለመፍታት ከተፈለገ መፍትሔው፤ እስካሁን በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲሞከር ከርሞ ሀገርን ወደ ከፋ ጥፋት ያመራው ወታደራዊ ኃይል መጠቀም ሳይሆን፤ የፖለቲካ ውይይት ነው የሚል እምነት አለኝ” ብለዋል አቶ ገዱ።

©️ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Afar People's Voice - APV

14 Aug, 19:31


#አፋር -#ረሔና👌

ይህ ከስር የምትመለከቱት ስፍራ በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታአሌ ወረዳ ዶሆ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን በዘንባባ ተክሎች የተከበበ ውብና ማራኪ የተፈጥሮ ገጽታ ያለው አስደናቂ ቦታ ነው😍

#VISIT_AFAR

Afar People's Voice - APV

14 Aug, 19:31


🗣️ ሪዮ ፈርዲናንድ እንዲህ አለ፡

«ሜሲ ወደ አሜሪካ በመሄዱ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመሄዱ ሚዲያዎች ምን እያሉ እንደሆነ ተመልከት።

አንድ ተጫዋች አሜሪካ ስለሄደ ብቻ ይበረታታል። ነገር ግን አንድ ተጫዋች ወደ ሳውዲ ሲሄድ ጥቃት ይደርስበታል። አሜሪካ ፍጹም ሀገር እንደሆነች ልትነግረኝ ትፈልጋለህ?

እኔ 100% ጡረታ ባልወጣ ኖሮ ሳላስብና ያለ ሳላመነታ ወደ ሳውዲ አረቢያ እሄድ ነበር። አሜሪካ? የለም! የሳውዲ ሻምፒዮና ከአሜሪካ ሻምፒዮና እጅግ በጣም የተሻለ ነው።»

ፈርዲናንድ

Afar People's Voice - APV

13 Aug, 18:27


ኢናሊላሂ ወኢና ኢሌይሂ ራጂኡን አሰቃቂ የመኪና አ ደ ጋ😭

ዛሬ አፋር ክልል በሚሌ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሶስት ሰዎችን ጨምሮ በ6ሰዎች ላይ ሞ*ት በሌሎች 7ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ!

ከሚሌ ከተማ 14 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ሰመራ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሺያ ዶልፊኝ መኪና ከከባድ መኪና ጋር በመጋጨቱ በተሳፋሪዎች ላይ ሞ*ትን ጨምሮ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ማድረሱን የአውሲ-ረሱ ዞን ትራፊክ ፖሊስ አስታወቀ!

በአደጋዉ የአንድ ቤተሰሰብ አባል የሆኑ አባት፣ እናትና የ4 አመት ህጻን ልጅን ጨምሮ 6 ሰዎች ሲ*ሞቱ ሌሎች 7 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

Afar People's Voice - APV

12 Aug, 19:27


የሳኡዲ አረቢያ ክለብ አል ናስር ሮናልዶ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች የአረብ ሻምፒዮንስ ዋንጫ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ግዜ አንስተዋል።

የሮናልዶ አድናቂዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ🥰

Afar People's Voice - APV

12 Aug, 11:36


ታዋቂው የአውስትራሊያ እሽግ ውሀ ኩባንያ #Organic_Springs የውሀው ማሸጊያ ፕላስቲክ ላይ የሐዲስ ጥቅስ አሳተመ።

ስለ ውሀ ቁጠባ የሚያስተምረው የረሱል (ሰ.አ.ወ) ሀዲስ ሲተረጎም እንዲህ ይላል.....

<<ወራጅ ወንዝ ላይ ሆነህ ቢሆን እንኳ ውሀን አታባክን>>

ኩባንያው ሀዲሱን እንደ ጥቅስ የፃፍኩት ውሀ ውድ ሀብት መሆኑን እና የአካባቢ ጥበቃን ፍንትው አድርጎ ስለሚያመልክት ነው ብሎዋል።

Afar People's Voice - APV

12 Aug, 09:54


ኢትዮጵያ ውስጥ ሀይማኖትን ሽፋን ያደረገ የጎጥ ፖለቲካ እንጂ በትክክል ለሃይማኖቱ መብትና መከበር ሲል የሚታገል ግለሰብም ይሁን ቡድን የለም።
ከሙስሊሙ መጠቃት ይልቅ ድርጊቱን የፈፀመው አካል ማንነት ነው የሚያሳስባቸው እሱ የሚጠላው አካል ከሆነ ብቻ እሪታውን ያቀልጠዋል ከዚያ ውጭ ግን ለሃይማኖቱም ይሁን ለመስጂዱ ምንም ደንታ የለውም።

በጣም የሚያሳዝነው ይህ ችግር የግለሰቦች ብቻ ሳይሆን እንደሙስሊም አለን የምንለው ተቋምን ጨምሮ በዚሁ የጎጥ ፖለቲካ የተጠለፈ መሆኑ ነው።

Afar People's Voice - APV

11 Aug, 18:54


ሳውዲ እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሆኑ Lucid መኪኖችን ማምረት መጀመሯን ገለፀች።

ታዋቂው የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አውቶሞቢል አምራቹ Tesla ኩባንያ ከሳውዲ በኩል ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋል እየተባለ ነው።

Afar People's Voice - APV

11 Aug, 18:54


#አሳዛኝ_መረጃ‼️

በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ ውስጥ ጉሓ በምትባል ቀበሌ ላይ የአገው ነፃ አውጪ በሚባል ታጣቂ ሀይል የሙስሊሞች ንብረት ሙሉ በሙሉ መዘረፉን እና በንፁሀን ላይም ጥ ቃ ት መድረሱ ታውቋል😥

አላህ ሆይ ሀገራችንን ስላም አድርግልን🤲

Afar People's Voice - APV

10 Aug, 17:55


ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ “የዓለም ባንክ ባህላችንን እና ሀይማኖታችንን በገንዘብ እንድንቀይር እያስገደደን ነው” አሉ

ፕሬዝዳንቱ ኡጋንዳ ያለ ዓለም ባንክ እርዳታም ታድጋለች ብለዋል። ዓለም ባንክ ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚከለክል ጠንካራ ህግ በማውጣቷ አዲስ ብድር እንደማይሰጥ አስታውቋል

ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ በበኩላቸው ኡጋንዳ ያለ ዓለም ባንክ ብድር ማደግ ትችላለች ብለዋል።
ምዕራባዊያን "አፍሪካን ዝቅ አድርገው መመልከት እና ጫና ማሳደር ይፈልጋሉ፣ እኛ ችግራችንን እንዴት መፍታት እንዳለብን እናውቃለን፣ እነሱም የእኛ ችግሮቻችን ናቸው" ብለዋል።

ኡጋንዳ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚከከለክል ህግን ያጸደቀች ሲሆን ፕሮዝዳንት ሙሴቪኒም ህጉ እንዲተገበር መፈረማቸው ይታወሳል።
ኣሜሪካ ኡጋንዳ ያጸደቀችውን ህግ ከመቃወም ባለፈ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን አሁን ደግሞ የዓለም ባንክ ተጨማሪ ማዕቀብ ጥሏል።

Afar People's Voice - APV

10 Aug, 12:39


እናንተ ደጋጎች እባካችሁ ሼር አድርጉለት🙏🙏🙏

ኢትዮጵያን ወክሎ ሲወዳደር የነበረው ስፖርተኛ መንገድ ዳር ቆሞ ሲያለቅስ ማየት ያማል! አባታችንን አለን እንበለው!

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ሲዘዋወር የታየው ታላቅ ሰው፤ በመንገድ ዳር ቆሞ ተክዞ ፤ እንባው እየወረደ አንድ ሰው አናገረው። ከዚህ ሰው የተረዳሁት፤ ሰው እርቦት፣ ሰው ጠምቶት ብቸኝነት አጎሳቁሎት እና ህመም ተደማምሮበት የቀን ጨለማ ሆኖበት ነው።

አይለምን ነገር የክብር ጉዳይ ይዞት፤ የሰው ፊት እሳት ሆኖበት፣ አይናገር ነገር ሰው የለው ብቻ እንባውና ገፁ ብዙውን ችግሩን አጉልቶ ይናገር ነበርና በሰዓቱ ያገኘው ሰው ተረድቶት ምስሉን አሳይቶናል። እኛም ምስሉን ስናየው በቀጥታ ሃዘኑ ተጋብቶብናል። ምስሉን አይቶ፣ ታሪኩን ተረድቶ እንዴት አለማዘን ይቻላል?

ይህ የተከፋ ሰው ማን ነው ያልን እንደሆነ:- ትላንት በወጣትነቱ አገሩን ያስጠራ፤ የአገር እና የህዝብ ባለውለታ ኃይላይ አርዓያ ነው። ይህ ታሪካዊ ጀግና ዛሬ የኛን ድጋፍ ይሻል። ምን ሆኖ?

ሁለት ጊዜ የታየ ብስክሌተኛው ኃይላይ አርአያን በተመለክልተ ከታች ያለውን መረጃ ለድጋፍ ከተያየዘው እና በማህበራዊ ሚዲያ ሲንሸራሸር ያገኘሁት ነው እነሆ:+

➸ ለ15 ዓመታት ያክል በብስክሌት ተወዳዳሪነት ለሀገሩና ለክለቡ ውጤታማ ጊዜን አሳልፏል።
➸ የትራንስ ኢትዮጵያ ብስክሌት ክለብ ከመሰረቱት ብስክሌተኞች አንዱ ነው።
➸ ለ15 ዓመታት በሚገርም ፍጥነት የብስክሌት ፔዳልን የረገጡ እግሮቹ ዛሬ ላይ ለህክምና የሚሆነው ገንዘብ ባለማግኘቱ እግሮቹን ለማጣት ተቃርቧል ።

በወጣትነት እድሜው ለአገሩ ኢትዮጵያ በብስክሌት የወከለው አትሌት ዛሬ ላይ በገንዘብ እጥረት ህክምናውን ማድረግ ተቸግሯል።

ኃይላይ ለአገሩ እና ለክለቡ በርካታ ድሎችን ያስመዘገበና የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘት የቻለ ውጤታማ ብስክሌታማ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ይህ ባለውለታ ትላንት የብስክሌት ፔዳሎቹን በሚገርም ፍጥነት ያሸከረከረበት እግሮቹ የሚያጣበት ሁኔታ ላይ ይገኛልና ይህንን ባለውለታ ልንደርስለት ይገባል።

ይህንን አንጋፋ የስፖርት ሰው መደገፍ ለምትፈልጉ ስፖርት ወዳዶች በ 0915815264 የእጅ ስልኩ በመደወል ማግኘት ትችላላቹሁ።

4,052

subscribers

4,072

photos

94

videos