ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ @ethelzetewahido Channel on Telegram

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

@ethelzetewahido


💚💛❤️ኢትኤል ዘተዋሕዶ ገፅ💚💛❤️
ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።
የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፩ : ቁጥር ፫

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሀን : ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ!
ትንሣኤሽን ያሳየን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ

በተጨማሪ ግሩፑን ይቀላቀሉ👉👇
https://t.me/Ethel_Ze_Tewahido

💚💛💚💛💚💛

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ (Amharic)

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ ገፅ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው። የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፩ : ቁጥር ፫ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሀን : ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ! ትንሣኤሽን ያሳየን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በተጨማሪ ግሩፑን ይቀላቀሉ እባክዎት በተከታዮች ላይ ብፁዓን እና አወለድለው ከግሩፑንን ይበልጥጠን ፣ በመስማትም እንጠቀማለን። ለተጨማሩ ግሩፑን እና ተጨማሪ ስለ ብፁዓን በትንቢት ያሟሉ። ምንም ማህበር እንኳይ ነበርና ይህ ገፅ በቀዳዳ ውስጥ ያግዳል። ከእኛ ያለይን ምንም እናነብሩ። የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፩ የሚገኝ የትምህርት ሥራ በአንተ ደም ወዳሉበት የቀን ብፁዓን የሚሰማ ወዲለ በግሩፑን የተጠብቀው ብፁዓን ታነሱ።

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

22 Nov, 08:50


🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🟢.ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር ።

🟢.ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም

🟡.ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን

🔴.ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ
     
➻ሠላም እንዴትሰነበታችሁ እኛ ደና ነንን ልዑል እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን።ዛሬ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ አባት ገድላቸው ላይ የተገለጸውን እስኪ አንብበነው እንማርበት ከበረከታቸውም እናገኝ ዘንድ እንማጸናቸው።

➻እንደ ነብዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማህፀን የተመረጡ ናቸው ብሉይንና ሀዲስ ኪዳንን ያጠናቀቁት በ12 ዓመታቸው ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን አሰናብችኝ ብለው ጠይቀዋል ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደ ሚገኘው ደብረ ፀራቢ ወደ ሚባል ገዳም ገቡ።

➻ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስ የምንኩስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ የከበደ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢነግሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኩስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነግረዋቸው ከብዙ ፈተና በኋላ ጽናታቸውን አይተው አመንኩሰዋቸዋል።

 ➻በገዳሙ እንጨት እየለቀሙ ውኃ እየቀዱ የክርስቶስን ሕመሙንና ሞቱን እያሰቡ በፀሎት ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦ ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ከነገራቸው በኋላ በሽሬ አዲ አቦ በተባለ ስፍራ ሂደው ብዙ አስደናቂ ታምራትን ካደረጉ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡት 16 መነኮሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ።

    ➻ጻዲቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባህር በታምራታቸው ያቃጠሉ አባት ናቸው።
በንጉሡ በአፄ ዳዊት ዘመን ሰንበት አንዲት ናት እያሉ በሰንበት ስራ እንደሚሰሩ ሰምተው ሰንበት አንዲት ናት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው ከግብፅ የመጡት ጳጳሳትም ቀደም ብለው ከአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ አሁን ደግሞ ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ አፄ ዳዊት አከራከሯቸው ጳጳሱም ተረቱ ።

➻ክፉዎችም በአቡነ ፊልጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው በአቁማዳ ጠቅልለው ሀይቅ ውስጥ ጣሏቸው።በዚህ ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባህር በእሳት ተቃጥሎ እንዲታይ አደረጉ።በጽኑ ሥልጣን ህዝቡንም መንግሥቱንም ረገሟቸው።

🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

➻ይህ ውግዘት ለቀድሞዋ ኢትዮጵያ ለአሁኗ ደግሞ ኢትዮጵያና ኤርትራ (ባህረ ነጋሽ) ልጆች የተላለፈ እርግማን ነው።

 ➻ በዚህ ጊዜ ንጉሡም ህዝቡም ሁሉም ተረበሸ።
እንደ ምጽአት ቀን ያስፈራ ነበር። እርግማናቸው ከመባርቅት ጎልቶ በሚያስፈራ ነጎድጎድ ይሰማ ነበር።

 ➻.ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባህር ዳርቻ ላይ የተቃጠሉ ድንጋዮች ይገኛሉ።

➻.በወቅቱም የንጉሡ ሚስት በዋናተኞች አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አሰወጥታቸው እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው።ወዲያውም ከማህፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ይወጣል ብለው ትንቢት ተናግረዋል።በትንቢቱም መሰረት ንጉሡ አፄ ዘርዓያዕቆብ ተወለደ።

➻.በወቅቱ በተፈጠረ አለመግባባትና ክፉዎችም በባህር ውስጥ ስለጣሏቸው እርግማንን በህዝቡ ላይ አምጥተዋል።
ንጉሡ አፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያውም ታርቀዋል።
በዘመናቸውም ርሃብ ስለነበረ ፃዲቁን ከገዳማቸው አስጠርተው ምን ባደርግ ይሻለኛል ብለው አማክረዋቸዋል።
ጻዲቁም የጌታችንን መስቀል ያስመጡ ብለው መከሯቸው ንጉሥ አፄ ዳዊትም በአቡነ ፊልጶስ ምክር መሠረት ከእየሩሳሌም መስከረም 10 ቀን አስመጥተውታል።

➻.አቡነ ፊልጶስ በደብረ ቢዘን ገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኑረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብለዋል።
ላንተ የተሰጠህ ቃል ኪዳን ለማንም አልተሰጠውም
➻.ክብርህ ገናና ነው።

➻.በቃል ኪዳንህ ለተማፀነ የማልፈጽምለት የለም።
➻.ገዳምህን ዘወትር በበረከት ደመና ከብቤ አኖረዋለው ።

➻.ምሕረትን ፈልጎ ደጅህን ለረገጠ አንተን ባከበርኩበት ልክ አከብረዋለሁ።
➻.አስተዋይ ልቦናን እሰጠዋለው።

➻.የኢትዮጵያን ምስጢር እገልጥለታለው ብሎ ጌታ ቃል ገብቶላቸዋል ።

➻.ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር አርፈዋል !!!
           
➻.እንግዲህ ዛሬም እየሆነ ያለውን ማየት ነው እየተፈጸመ ነው እንሰደዳለን :ሀገር እንጠላለን ከውስጥ ይልቅ ውጭነት ይማርከናል ።

➻.እንደ ሀገር እንደ ህዝብ ታመናል ብሎ የሚመረምር ትውልድ እንኳ ጠፍቷል።

 ➻. የእውነተኛ አባቶቻችን ውግዘት ምን ያህል ከባድና ለቅጣት እንደሚዳርግ ከዚህ መረዳት ይቻላል።ዛሬም በዚህ ዘመን የተላለፈውን የአባታችን ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘትን የማናከብር ከሆነ ከዚህ የከፋ መከራ ውስጥ እንገባለን ማለት ነው።ያው እንደምናየው ህዝቡም እያከበረው አይደለም ያው የሚሆነውን ማየት ነው እንግዲህ።
➻. እግዚአብሔር ይመስገንና እኛ ግን እውነትን ሰምተናል በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እውነት እስከመጨረሻው ያጽናን!
➻.የጻዲቁ አቡነ ፊልጶስ በረከታቸው ይደርብን።

➻.በአንድ ወንድም ምክንያት ገድላቸውን ሠማሁና ለሁሉም አስተማሪ ስለሆነ ነው ያጋራሁአችሁ


.ሠላመ እግዚአብሔር ቅን፣ የዋህ፣ ትሁት ከሆነ ኢትዮጵያን ከልቡ ከሚወዳት ጋር ይሁን።
13/03/2017 ዓ.ም

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

13 Nov, 03:23


🟢የአብርሃሙ ሥላሴ እናቱን ያዳምጣል አንዲት ነጥብ ከእናቱ እንድትወድቅበት አይፈልግም።

🟢
ፍላጎቷ የሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ፈጻሚ ስለሆነ ይህን ልብ ልትሉ ይገባል።አታማልድም እያልህ ምትጨማለቅ የዲያብሎስ ግልገል ጠፊ ትውልድ ሁሉ ዋጋህን ታገኛለህ እዚህ ላይ ነው የምነግርህ።በድንግል ላይ አላግጠህ በድንግል ላይ አሹፈህ ክብሯውን ሁሉ ቀንሰህ ያፌዝህ ሁሉ ትውልድ ሁሉ በዚህም ሰዓት አረጋግጥልህአለሁ ዘር ማንዘርህ ሁሉ አያልፍም ትጠረጋለህ።
🟡
እኔ ባሪያው የእግዚአብሔር ባሪያ ለአንዳችሁም አላልፋችሁም። ስትጠናቀቅ ነው ሕሊናዬ ሚያርፈው በእናቴ በድንግል ድርድር አላቅም። ወዮልህ እኔ ፊት አትድረስ ያኔ የሞትህን ብዜት ነው እንጅ ምታየው እሳት እንደሚበላህ ነው እንጅ ምታየው ሌላ ከእኔ ምሕረት የምትባል ለሰንከንድም አትታለምም።
🟡
በእናቴ የመጣ ርህራሄ የለኝም በአይኔ የመጣ ነው።በእምነቴ የመጣ በአይኔ የመጣ ነው።ይህንን እንድናገር አልፈልግም ነበር ግን ሰዓቱ ነውና ግድ መናገር ያስፈልጋል።
እግዚአብሔር እንደ ቃሉ በአደረሰኝ ስፍራ ላይ ስደርስ ወይም አገልግለኝ ባለኝ ቦታ ላይ ሳገለግለው ይህ መመሪያ ነው የማይናወጽ አቋሜ ነው።ዛሬም እንደ አቅሜ በትንሽነቴ አገለግላለሁ እግዚአብሔርን ።
🔴
እግዚአብሔር ደግሞ ነገ እዚህ ጋ ስፍራ አገልግል ባለኝ ስፍራ ስሆን ግን የእምነቴ ጠላት የሆናችሁ በእናንተ በተለይ እናንተ መናፍቃን እናንተ ካቶሊካውያን በተለይ በክርስትና ስም ያላገጣችሁ ክፉ ጠላቶች በቤቱም በልጽጋችሁ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ውስጥም ሁናችሁ ይህንን እርኩሰት ያነገሣችሁ ሁሉ ውዮላችሁ።
🔴
አሁንም ደግሜ ነው ምነግርህ ወዮልህ ለዘርህ ሁሉ ለራስማ ተወው ለዘር ማንዘርህ የሚተርፈውን እሳት ትቀበላታለህ።ደግሜ ነው ዛሬ ምነግርህ ምንም ርህራሄ እንደለለ እስከ ዛሬም እስከዚች ሰዓት ድረስ እግዚአብሔር በትዕግስት እጁን የያዘው መጪውን እሳት ክፋቱን ጥንካሬውን ብርታቱን ስለሚያውቀው የሚያደርጋትን ስለሚያቅ ነው።እኛ ባሮች እጅ ደግሞ የእግዚአብሔር ኃይል ገባ ማለት ወዮልህ ወዮልህ መጥፊያህ...

4/03/2017 ዓ.ም

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

01 Nov, 17:28


ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ pinned an audio file

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

01 Nov, 15:13


📌ማስታወሻ

ክፉ ትውልድ እንዲህ ይላል እስከ ዛሬ ለ18 ዓመት ለፍልፋችኋል የምትመኩበት አምላክ እስከ ዛሬ መቸ መጣ :ምንስ አደረገን:እናንተ ትጮሃላችሁ የእግዚአብሔር ቁጣ ፍርድ ትላላችሁ ጆሮአችን እስከሚታክተው ሰማናችሁ ምንም የሚመጣ የለም።እኛም ለሥልጣኔአችንም ስለሥልጣኔአችንም ጉልበታችንም ሀብታችንም በዓለም የዘረጋነው ሥርዓታችንም ሁሉ አንዳች የሚነካው የለም።የእናንተን ሥላሴ: የእናንተን መድኃኔዓለም: የእናንተን ማርያም:የእናንተን መልአክ:የእናንተን ቅዱሳን ታሪክም ገድልም ሁሉንም አናውቃቸውም ።ግብረሰዶምነት መብታችን ነው ዓለምንም ሁሉ ከድኗል የምንሻውን ከመፈጸም የሚያግደን የለም።ዘወር በሉ አናውቃችሁም ብላችሁ ቁማችኋል ዲያብሎስን ታምናችኋል አምላካችሁ አድርጋችሁታል ፤በአዘዛችሁም ቁማችኋል ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋል።ልብ በሉ ምስክሩ እኛም ነንን ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ :ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ እንግዲህ እውነቱ ይለያል።እኛ የሥላሴ ባሮች: የድንግልም ልጆች:የሊቀ መላእክቱም ወዳጆች የቅዱሳንም ፍሬዎች የታመንበት አምላክ የአብርሃሙ ሥላሴ በእኛ አንደበት እንደተናገረው እንደ መልዕክቱ አገላለጽ :እንደ ደብዳቤዎቹ አገላለጽ:እንደ መግለጫዎቹ እንደ ትምህርቶቹ እውነትነት:የእኛም ታማኝ አገልጋይነት ይታወቅና እና ይገለጽ ዘንድ እግዚአብሔር በታላቅ የበቀልና የፍርድ ሂደት በታላቅ ቁጣ ትቢያ ሊያደርጋችሁ ደርሷል በደጃችሁም ነው።
ከዲያብሎስ የታጠቃችሁትን ትዕቢታችሁ ክህደታችሁ ንቀታችሁ እኒህ ሁሉ በምድር እንደጸኑ ያኖሯችኋል እንደሆነ እነሆ ልናይ ነው።የእኛ አምላክ ስለባሮቹ ስለቃሉ ስለትዕዛዙ ስለሥርዓቱ ሲል በቅናት እና በቁጣ ካልተነሳ እርምጃውንም በማትገምቱት በማታስቡት መልኩ ይዞት ካልመጣ በእርግጥ እንዳላችሁት እኛ አምላክ የለንም ውሸታም ነንን ማለት ነው።
ስለዚህ የእናንተ አምላክ ከእግዚአብሔር ታግሎ ከአሸነፈ እኛም ተሸንፈናል ማለት ነው።እንግዲህ ሜዳውም ፈረሱም እነሆ ተዘርግቷል ሁሉንም እናየዋለን።ሲድራቅ: ሚሳቅ :አቢዲናጎምን ከእሳት ያወጣው አምላካችን: በእርግጥ ለአምላክነቱ: ለስሙ: ለክብሩ: ለፈቃዱ ቀናይነቱን ለልጆቹ ፈራጅነቱም በግልጽና በማትክዱበት መልኩ ሲውጣችሁ ተረት ብላችሁ የናቃችሁት ቃሉ ሲተገበርባችሁ አይ ተሳስተናል ማሩን እ ከልሉን አስጥሉን ማለት የለም።የለም የለም።መዳንም የለም።ከእነ ክህደትህ ከእነ ትዕቢትህ ሰዶሞን የበላው እሳት በሺ እጥፍ ተባዝቶ ይበላሃል።ፌዝህ ንቀትህ ያድንህ በቃ እሱኑ ተማመን ።ያ የተማመንህበት ዲያብሎስ እሱ ያድንህ በቃ።
ያሳደድኸን የገደልኸን የአሰርኸን እኛ የልዑልም የድንግልም ታማኝ ባሮች ብትጮህ ብታቅራራ ሺ ጊዜ ብትኳትን ከእንግዲህ አታገኜንም ለአንዴም ለመጨረሻም ተሰነባብተንሃል።

📌የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በእምነታችሁ ጽናት በምክር መስማታችሁ ምክንያት አሸናፊ ሁናችኋል።ዓለምን አሸንፋችኋል። ኮንናችሁታል ታገሱ በጾም በጸሎት ትጉ።ለእኛም ደካማ አገልጋዮቻችሁ ጌታ ምሕረቱን :ቸርነቱን :ፀጋውን አብዝቶልን በትህትና እንድናገለግላችሁ ፀልዩልን።

📌ክርስቲያን መሠል አስመሳዮች ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን የምታመልኩ ወዮላችሁ! የሚገርም ክርስቲያን ተብየ ምዕመን ፡በተለይ ሴቶች አንድ ሊቅ ነኝ ሊቃውንት ነኝ የሚሉ እግር ስር ወድቃ አባቴ በእርስዎ እግር ሥር በመባረኬ እጅግ ተደስቻለሁ ብላ እንደ ምሳሌ በማሕበራዊ ሚዲያ ስታስተጋባ ሰማናት።እሺ አምላክስ መቼ ነው እግሩ ስር ወድቀሽ የሚባርክሽ እ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰው የሰጠሽ አባት ተብዮች ያጠፉሽ ከንቱ ትባያለሽ።እንደ እሷ መሰል የሆናችሁ ሁሉ ከንቱ ተብላችሁ ፍርዳችሁን ታገኛላችሁ።
በቀን 21/02/2017 ዓ.ም ከወጣው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ ከ46 እስከ 51 ደቂቃ ላይ የተወሰደ።
22/02/2017 ዓ.ም

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

01 Nov, 11:23


እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ። ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፤ ከፊቴ ጣላቸው፤ ይውጡ።
እነርሱም። ወዴት እንውጣ ቢሉህ፥ አንተ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥
ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥
ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥
ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላቸዋለህ።
ሰይፍን ለመግደል ውሾችንም ለመጐተት የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማነ ነው?

ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 15:1-5

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

31 Oct, 15:30


ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ፍርድ አዘል መግለጫ
21/02/2017 ዓ.ም

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

30 Oct, 15:51


🇨🇬 ልዩ ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20
20/02/2017 ዓ.ም

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

17 Oct, 08:35


🫴🌹 የአባት ምክር ለልጆች!

የሐዋርያት ሥራ ትምህርት ክፍል 7ለ ላይ ካለው የተወሰደ!

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

09 Oct, 08:42


መልክአ አቡነ ገብረ ናዝራዊ

ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ

09 Oct, 08:42


መልክአ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማእት