𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪 @eslmnan_teqebelu Channel on Telegram

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

@eslmnan_teqebelu


ቻናሉ የተከፈተበት ዋና አላማ ሚሽነሪዎች እስልምና ላይ ለሚቀጥፏቸው ቅጥፈቶችም ሆነ ሊሚያነሷቸው
ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጥበታል
እዲሁም ክርስትና እና እስልምና ይነፃፀርበታል
ኑ እስልምናን ተቀበሉ in box እጠብቃቹሀለው👇👇

in box👉 @Yarebi_12

ነይ 👆👆👆

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪 (Amharic)

ቻናሉ የተከፈተበት ዋና አላማ ሚሽነሪዎች የእስልምና ላይ መሸገምና ማህበረሰብ መነቀጥ ላሉትን ቅጥፈቶችም ሆነ ሊሚያነሷቸው፡፡ ብለው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጥበታል ፡፡ ይህንን እስልምናን በአገር መሸገምና ማህበረሰብ እና ይነፃፀርበታል፡፡ እባኮ እስልምናን በምሳሌ በማስጨበጥ ካልኦሊ ጥያቄዎችን መልእክት በመስራት ይጠቀሙ፡፡ እጠብቃችሁ እንጠቀምባታለን👇👇፡፡ በማንኛውም ስህተትከፈታችሁ አላየንም፡፡ ለምሳሌ ሊሾሙ ያለብን እናቱ እሳን በማካበር ከርመር እና እስልምናን እንከፍላለን፡፡ እባኮ ይህን ቢሆን ወይም በአጭር የእስልምና የህያው መሥዋዕት እንዲሁም ጉዞ በሚከተለው ክፍል እገናኛለን፡፡

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

24 Nov, 12:52


ጥያቄ እውነት ወይስ ሀሰት?

የእስልምናን ጥሩ ገፅታ ለማሳወቅ ንፅፅር ትምህርት ጉልህ ቢና አለው

ጥያቄ ትክክለኛው መልስ ሰታገኙ የሚያመጣላችሁን add አድርጉለት

     ✍️በወድም ሙስጠፋ

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

17 Nov, 06:30


እኔ የምለው እቺን ምክር ትፈልጋላቹ

https://vm.tiktok.com/ZMhtNDsap/

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

17 Nov, 05:24


እኚህን ፅሁፎች ማርያምን ለሚያመኩ አካላት ላኩልኝ 🥰

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

17 Nov, 05:20


ከላይ ለማየት እደሞከርነው ካቶሊክ፣ ኦርቶዶስ፣ አንግሊካን ማርያምን ለአምላክ የሚገባውን ባህሪ እና መስዋዕት እያቀረቡላት አምልኮ እደሚፈፅሙ አይተናል አሁን ደሞ በግልፅ መፅሀፍቶቻቸው ማለትም ከባይብል ቀጥሎ ተቀባይነት ያላቸው መፅሀቶቻቸው ገድላትና ድርሳናት በተላይ በኦርቶዶክስ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው ሆኖም እነዛህ መፅሀፍት ላይ ማርያምን በግልፅ እደሚያመልኳት እንመለከታለን ማርያም በሌለችበት እንዲህ ጸሎት፣ ስግደት እና መገዛት ይቀርብላታል፦

ዚቅ ዘየካቲት ኪዳነ ምህረት ገፅ 144
*“ብቻዋን ታላላቅ ብርሃናትን ለፈጠረች ለመድኃኒት ድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለእርሷም እንገዛ”*
መጽሐፈ ሰአታት ገፅ 31
፦ *“በብርሃን ጌጥ ያጌጥሽ ወርቅ ዘቦ ግምጃን የተጎናፀፍሽ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ተገዛንልሽ ለአንቺ እንገዛለን”*
፦ *“አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ብርሌ ካህናት የሚያሹትሽ የሽቱ ሙዳይ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺን ፈፅመን እንገዛለን”*
፦ *“የታተምሽ የውሃ ጉድጓድ የተዘጋሽ የተክል ቦታ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ የነብያት ልጆቻቸው አንች ነሽና ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንገዛለን”*
፦ *“በብርና በወርቅ የተሸለምሽ አዲስ የጣሪያ ዋልታ ሚስጥር ማደሪያ የዳዊት ልጅ እመቤታችን ሆይ ተገዛንልሽ ለአንቺ ፈፅመን እንሰግዳለን”*

ይሄ ከማርያም ይልቅ ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት ነበር የሚገባው ሆኖም ማርያምን ከሱ እኩል ያመልኳታል አረ እንደውም ትበልጠዋለች ከላይ ፅሁፋችን ላይ በመስዋት ደረጃ እራሱ ኢየሱስን ትበልጠዋለች ሆኖም እኛ ማርያምን አናመልካትም እንገዛሻለን ስንል እኮ እናመልክሻለን እያልን ሳይሆን እንታዘዝሻለን ነው ይሉናል ይሄ አመለካከታቹን እራሳቹን ሸውዱበት እንገዛሻለን ስንል እንታዘዝሻለን በሚል ከፈታቹልን እናመልክሻለን ስትሏት በምን ልትፈትሉን ነው ከላይ ፎቶ ላይ እዳስቀመጥኩት ኦርቶዶክሶች ማርያምን በግልፅ እናመልክሻለን ይሏታል ፎቶውን ለማየት
👉 [ PHOTO ] እንዲህ ብሎ ያስቀምጣዋል

98 እመቤቴ ማርያም ሆይ የኢያሪኮ አበባ ቡቃያ አንቺ ነሽ። አውሎ ነፋስ ያላበላሸው ደም ግባትሽም ያማረ ነው። ለአንቺም የምስጋና እጅ መንሻን አቀርባለሁ። በመፍራት እገዛልሻለሁ በመስገድም እጅ እነሣሻለሁ።
#የአምልኮ #መሥዋዕትንም #ለአንቺ #እሠዋለሁ። ሆድሽን አወድሰዋለሁ። ማሕፀንሽንም አመሰግነዋለሁ። የአምላካችን የእግዚአብሔር መጠጊያው አድርጐታልና። ደግነትሽን እናገራለሁ። ቸርነትሽንም እሰብካለሁ። ቅድስት ሆይ ዛሬ የምወደውን የምለምን አይደለም ጽድቅሽን ሰላምሽንም ጨምረሽ ፤ ስጭኝ። ለዘለዓለሙ አሜን።
[ሀማኖት አበው ላይ- እንዚራ ስብሀት 12-98]

ይሄን ስታነቡ ምን ይውጣቹ ይሆን ይሄ ብቻ አይደለም ለማርያም ስዕል ስግደት ግዴታ ነው ልብ አድርጉልኝ ለማርያም ሳይሆ ለስእሏ መስገድ ግዴታ ነው ለስእል መስገድ ደሞ ጣዎት አምኮ ነው እኔ አላልኩም ባይብላቹ ነው ከዛ በፊት ግን ይሄን እዩልኝ

ነገረ ማርያም ምዕራፍ  1
“ሰማይ ምድር ሳይፈጠሩ የገነት ምድርም ሳትፈጠር ቡሩክትና ክብርት የሆነች ማርያም ነበረች፡፡

እዳያቹት ከአምላክ እኩል ሰማይ ምድር ሳይፈጠሩ የገነት ምድርም ሳትፈጠር ነበረች ስለዚህ አምልኮ ይገባታል እያለን ነው እዴት ነው የሚባለው ሲባል ጭራሽ ከፈጣሪ ጋር ፈጥራለች ብሎ ቢያርፈውስ

መፅሀፈ ዚቅ ዘየካቲት ኪዳነምረት 144
ብቻዋን ትላልቅ ብርሃናትን ለፈጠረች ለመድኃኒታችን ለድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለእርሷም እንገዛ

እንስገድ ለእሷ እንገዛ የሚለውን አስምሩልኝ የሚሰግዱት የምር ለአክብሮት ከሆነ እናመልክሻለብ አለማት ሳይፈጠሩ ነበረች ብሎ ማመን አምልኮ አይደለምን ከአምላክ እኩል እያደረጋቹሀት አይደለምን? ግርም የሚለው ለማርያም ሳይሆን የሚሰግዱት ለስእሏ ነው

ተአምረ ማርያም በአማርኛ 2
፴፭ በሥዕሏም ፊት ስገዱ ለሥዕሷ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ ።

የሆሣዕና ምንባባት 1
፳፭፡ በሥዕሏም፡ ፊት፡ ስገዱ፤ ለሥዕሏም፡ ያልሰገደ፡ ግን፡ ከቆመበት፡ ቦታ፡ ይጥፋ፤ ስም፡ አጠራሩም፡ አይታወቅ።

ለስዕል መስገድ ደሞ ጣዎት አምልኮ ነው
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ *”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ*።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 *”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ*”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

ነቢያትም የተቀረጸውን ምስል ሠራተኛ እንደሚሰራው፣ የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱ እንደኾኑ እና ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ ፍርድ በእነርሱ ላይ እንደለ ተናግረዋል፦
ኢሳይያስ 40፥19 *የተቀረጸውንስ ምስል ሠራተኛ ሠርቶታል*፥ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፥ የብሩንም ሰንሰለት አፍስሶለታል።
ኢሳይያስ 44፥9 *የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው*፥
ኤርምያስ 1፥16 ስለ ክፋታቸውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተው ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ *ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ*።

ሰው ለሠራው የእጅ ሥራ እንዴት ይሰገዳል? በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለስዕል የጸጋ ስግደት ይሰገዳል፤ ልብ አድርግ የጸጋ ስግደት ስገዱ የሚል ትእዛዝ የለም። በተቃራኒው ለተቀረጸ ምስል "አትስገድላቸው" የሚል ትእዛዝ ቢኖር እንጂ። ነገር ግን ይህ ግዑዝ ነገር በዐበይት ክርስቲያኖች ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል፤ ታዲያ ለምን ይሆን አበይት ክርስቲያኖች በጣዎት አምልኮ ውስጥ የተዘፈቁት እንግዲያውስ ኢየሱስ እኔን እና እናቴ አምልኩ ሳይሆን ያለው አንዱን አላህ ነው
ሱራ 5፥117
ኢየሱስ የሰበከው አላህን እድታመልኩ እንጂ እሱን ወይም ስላሴን ወይም ማርያምን  ፍጡራንን እድታመልኩ አይደለም ይህንን አስፈሪ ወንጀል እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ጾታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። ይህንን ፍርድ እያወቀ ወደ ኢሥላም የማይመጣ በእሳት የሚጫወት ነው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ *ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”*፡፡

" እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። በኢሥላም ፈጣሪ ከሆነው ከአንዱ አምላክ ከአላህ ውጪ የሚሰገድለት ማንነት ሆነ ምንነት የለም። ስዕል የሰው እጅ ሥራ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ። ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦
7፥197 *እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም*።

ስለዚህ ክርስቲያኖች ሆይ ማርያምን ከማምለክ ወታቹ አንዱን እና ብቸኛውን አላህን አምልኩ አላህ ሂዳያ ይስጣቹ ለእኛም በቅኑ መንገድ ላይ ሆነን ፅናቱን ይስጠን አሚን

ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

17 Nov, 05:20


ተመላኪዋ ማርያም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

ማርያም በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን "ኩሪያ" κυρία ትባላለች። "ኩሪያ" κυρία ማለት ደግሞ "ሴት ጌታ" "እመቤት" ማለት ነው፥   በአገራችን በግዕዝ "እግዚእ" ማለት "ወንድ ጌታ" "አባ ወራ" ማለት ሲሆን "እግዚእት" ማለት ደግሞ "ሴት ጌታ" "እመቤት" ማለት ነው፥ ኢየሱስን "ጌታችን" ለማለት "እግዚእነ" ሲሉ ማርያም ደግሞ "ጌታችን" ለማለት "እግዚእትነ" ይሏታል። ክርስቲያን ወገኖቻችንን ማርያምን እደ አምላክ ይዛቹሀል ስንል ብለን ይሄን የቁርአን ክፍል ስንጠቅስ
5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

አይ ቁርአን ዋሽቷል እኛ ማርያምን አናመልካትም ይሉናል ሆኖም እነሱ ህሊናቸውን ቢዋሹትም እደሚያመልኳት መፅሀፍቶቻቸው ይናገራሉ ይሄ ፅሁፍ በዋነኛነት ኦርቶዶክስ ካቶሎክ እና በአንግሊካን ላይ ያውጠነጠነ ፅሁፍ ነው እውን ማርያምን አታመልኳትምን? በመጀመሪያ አምላክ ማድረግና አምላክ አድርጎ መያዝ ይለያያል አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ሒሳብ መረዳት ይቻላል። በተመሳሳይ ጳውሎስ፦ "ሆዳቸው አምላካቸው ነው" ብሏል፦
ፊልጵስዩስ 3፥19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው።

ያ ማለት  ሆዳቸውን "አምላኬ" ብለው ጠሩ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሆዳቸው ቅድሚያ ሰጡ ማለት ነው፥ የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ስሌት መረዳት ይቻላል።

"አምላክ" የሚለውም ቃል "መለከ" ማለትም "አመለከ" ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚመለክ" ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የዐማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

ታዲያ በኦርቶዶክስ በካቶሊክ እና በአንግሊካን ማርያም ለአምላክ የሚሰጠውን ክብርና አምልኮ አላደረጉምን እናየዋለን ከዛህ በፊት ግን አላህ ሱብሀነ ወተአላ በቅዱስ ቃሉ ቁርአን ከኢየሱስ ቀጥሎ ማርያምን እደ አምላክ አድርገው ያዙ ብሎ እደሆነ የሚጠይቀው ማርያምን እደ አምላክ የሚያመልኳት አካላት ስላሉ ነው ነገር ግን ኢየሱስ እኔንም ሆነ ማርያምን አምልኩ ብሎ ስላላስተማረ በፍፁም ይላል
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩት ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

ሆኖም ማርያምን በግልፅ ትመለካለች በካቶሊክ ማርያም፦ “ሰማይ ላይ ኖራ በኃላ ስጋ የለበሰች አርያማዊት ማለትም ሰማያዊት ናት፤ ከዚያም ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል፤ በኦርቶዶክስና በአንግሊካንም፦ “ሞታ ሳትበሰብስ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለች” ተብሎ ይታመናል።
በ 375 AD የተነሱት ኮላደሪያን ክርስቲያኖች ማርያምን በግልጽ፦ “ቴአ” Θεία ማለትም “ሴት አምላክ” ብለው ይጥሩአት ነበር።
በ 431 AD የኤፌሶን ጉባኤ ማርያምን “ቴኦቶኮስ” Θεοτόκος ማለትም “የአምላክ እናት” ብለዋታል።
ካቶሊክ፣ ኦርቶዶስ፣ አንግሊካን ማርያምን በግሪክ “ኪርያ” κυρία ማለትም “ሴት ጌታ” ይሉአታል፣ “ኩርዮስ” κύριος ማለት “ወንድ ጌታ” ማለት ነው። በአገራችን ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚኢት” ትባላለች፥ “እግዚኢት” ማለት “ሴት ጌታ” ማለት ሲሆን “እግዚእ” ደግሞ “ወንዱ ጌታ” ማለት ነው፤ ኢየሱስን “እግዚኢነ” ማለትም “ጌታችን” እንደሚሉት ሁሉ ማርያም “እግዚኢትነ” ማለትም “ጌታችን” ይሉአታል። ከዚህ የበለጠ ማርያምን አምላክ አድርጎ መያዝ አለን? ይህ አምልኮ ካልሆነ ምን ይባላል? ከአስራ አራቱ ቅዳሴ ሁለቱ ቅዳሴ ማለትም ቅዳሴ እግዚእ እና ቅዳሴ ማርያም ለኢየሱስ እና ለማርያም የሚቀርብ ቅዳሴ ነው። በዚህ ቅዳሴ ጊዜ ለኢየሱስ እና ለማርያም የመስዋዕት ቁርባን ይቀርብላቸዋል። ቁርባን የአምልኮ አስኳሉ ነው። ይህ ቁርባን ህብስትና ወይን መባ በማቅረብ፥ በከንፈር በማወደስ፥ ጧፍ በማብራት፥ ዕጣን በማጨስና በሰውነት በመቆም የመባ መስዋዕት፣ የከንፈር መስዋዕት፣ የመብራት መስዋዕት፣ የዕጣን መስዋዕት እና የሰውነት መስዋዕት ነው።

ቅዳሴው ሲጀምር ለኢየሱስ የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፦
*"አኮቴተ ቁርባን ዘእግዚነ፣ ወአምላክነ፣ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ"*

ትርጉሙ፦ *"የጌታችን፣ የአምላካችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቁርባን አኮቴት"*

ቅዳሴው ሲጀምር ለማርያም የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፦
*"አኮቴተ ቁርባን ዘእግዚትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ-አምላክ"*

ትርጉሙ፦ *"የአምላክ እናት የጌታችን የድንግል ማርያም የቁርባን አኮቴት"*

ለማርያም በወር ውስጥ ከኢየሱስ በላይ መስዋት ይቀርብላታል ለኢየሱስ ሶስት ቀን በ6 - በ27- በ28 ነው የሚከበርለት

በኦርቶዶክስ እራሱ
6:- ኢየሱስ
27:-መድሀኒአለም
28:-አማኑኤል በአለ ወልድ እየተባለ ይከበርለታል የአኮቴት ቁርባን ይቀርብለታል

ለማርያም ግን በወር ውስጥ 6 ቀናትን ያከብራሉ
ማለትም
1:-ልደታ ማርያም
3:-ባህታ ማርያም
6:-ጉስቃን ማርያም
10:-ፀደኒያ ማርያም
16:-ኪዳነ ምህረት ማርያም
21:-ቅድስት ማርያም
እየተባለ አኮቴት ቁርባን ይቀርብላታል

"አኮቴት" የሚለው ቃል "አዕኮተ" ማለትም "አመለከ" "አመሰገነ" "አወደሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምልኮ" "ምስጋና" "ውዳሴ" ማለት ነው። ለምሳሌ "አእኲትዎ ለአምላክ" ማለት "ለአምላክ አምልኮ አቅርቡ" ማለት ነው። ቅዳሴ እግዚእ እና ቅዳሴ ማርያምን ተመልከት። ታዲያ ወገኖቻችን እውን ማርያምን አናመልካትም ነው የምትሉን እደዛ ከሆነ ይሄን ቀጣዩን አንብብ
👉 [ አምልኮ ማርያም ]

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

06 Nov, 16:02


ወደ ቲክቶክ ተመልሰናል እየገባቹ ፎሎ አድርጉኝ😘እስኪ ለላይቭ ለመክፈት እዲመቸን  ቶሎ ፎሎ አድርጋቹ 1K እንግባ ዳይ ወደ ፎሎ👇

https://www.tiktok.com/@yarebena34?_t=8rAgJLylDq3&_r=1

¶[SHARE]¶ AND ¶[ Follow]¶

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

03 Nov, 05:26


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እንዲሁም ክርስቲያን ወገኖች ሰላም ብያለው

አመጣጤ ሙስሊምም ሆናቹ ክርስቲያን ኢስላም ላይ የሚነሱ ማንኛውም ጥያቄ ካሎት አላህ ባሳወቀን እና በተማርነው ልክ የምንመልስ ይሆናል ስለዚህ ማንኛውንም ጥያቄ እከሌ ስለዚህ ብጠይቅ ምን ይሉኛል በሚል ፍርሀት ውስጣቹ ጥያቄዎን እዳቲዙት ስለዚህ በኢስላም ላይ የተጠየቀ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጋቹ in box አናግሩኝ


ማሳሰቢያ

¶የፈትዋ ጥያቄዎችን አናስተናግድም!!
¶መጠየቅ የሚቻለው በንፅፅር ዙሪያ የሚነሱትን ማንኛውንም ጥያቄ!!
¶በግል ጥያቄ ብቻ ነው የምናስተናግደው ለስድብም ሆነ በግል ለመወያየት መምጣት አይቻልም!!
¶ጥያቄዎቹን ሙስሊምም  ክርስቲያንም መቶ መጠየቅ ይችላል
¶ክርስቲያኖች ለመጠየቅ ስትመጡ ለማዳረቅ ሳይሆን እውነታውን ለመቀበል ኑ ካሎነ ከነ ጭራሹ አትምጡ

ከላይ ባስቀመጥናቸው ማሳሰቢያዎች ከተስማሙ in box መምጣት ይችላሉ👇


IN BOX👉 [ @Yarebi_12 ]

ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

01 Nov, 09:16


👆ይሄን ሼር አድርጉ እየገባቹም ስሞቹብ በመጫን አንብቡ👇
[ ምርጫውን ለማግኘት ]

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

30 Oct, 08:40


𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪 pinned «                ¶[SHARE]¶ AND ¶[ JOIN ]¶ 📚.𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪              ውስጥ የተለቀቁ መጣጥፍት  📚                በፅሁፍ ደረጃ ለማንበብ 📕 1▸ ኢየሱስ አምላክ አይደለም 2▸ የኢየሱስ ስም የፍጡር ነው!! 3▸ እዴት ማወቅ ተሳነው! 4▸ ለእስራኤል የተላከ ነቢይ! 5▸ የማርቆስ 16-:-9-20 ጭማሪ 6▸…»

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

30 Oct, 08:40


                ¶[SHARE]¶ AND ¶[ JOIN ]¶

📚.𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

             ውስጥ የተለቀቁ መጣጥፍት  📚

               በፅሁፍ ደረጃ ለማንበብ 📕

1▸ ኢየሱስ አምላክ አይደለም
2▸ የኢየሱስ ስም የፍጡር ነው!!
3▸ እዴት ማወቅ ተሳነው!
4▸ ለእስራኤል የተላከ ነቢይ!
5▸ የማርቆስ 16-:-9-20 ጭማሪ
6▸ እኔና አብ አንድ ነን ለምን አለ
7▸ እየፈተነው ወይስ እየተጫወተበት
8▸ የነብያችን ሙሀመድ(ሰዐወ)ተአምር 1
9▸ የነብያችን ሙሀመድ(ሰዐወ)ተአምር 2
10▸የነብያችንሙሀመድ (ሰዐወ)ተአምር3
11▸ ዘማወዛገብ ውይይት
12▸ የሴት ልጅ ክብር በባይብል 1
13▸ የሴት ልጅ ክብር በባይብል 2
14▸ የነቢያት ደረጃ በባይብል!
15▸ ድንቄም ለሰላም መምጣት 1
16▸ ድንቄም ለሰላም መምጣት 2
17▸ ወፍዋን ማን ፈጠራት?
18▸ መልእክት እስልምናን ለምትፈልጉ
19▸ ኢሳ ቃል አይደለም!
20▸ በስም ብዛት አምላክነት
21▸ ህሊና የማይቀበለው ሥላሴ 1
22▸ ህሊና የማይቀበለው ሥላሴ 2
23▸ ህሊና የማይቀበለው ሥላሴ 3
24▸ ህሊና የማይቀበለው ሥላሴ 4
25▸ ህሊና የማይቀበለው ሥላሴ 5
26▸ ህሊና የማይቀበለው ሥላሴ 6
27▸ ይገለጥልናል ክፍል 1
28▸ ይገለጥልናል ክፍል 2
29▸ ቁርአን የማን ቃል ነው?
30▸ የኢሳን አምላክነት ከቁርአን ወፍ
31▸ ፍቅርና ሰላም በቁርአን
32▸ የኢትዮጲያ እና የግሪክ ሥላሴ
33▸ ስለ ቃል በዮሀንስ 1:1 ማብራሪያ
34▸ እኔ እና አብ አንድ ነን በጥራት
35▸ የማን መንገድ ነው ?
36▸ ካረገማ በቃ አምላክ ነው😁
37▸ የክርስቲያኖች ውዝግብ!
38▸ ፍትህ ወይስ በደል🥺
39▸ ወንድ እያመለኩ ድህነት የለም
40▸ በተበረዘ መፅሀድ ድህነት የለም p1
41▸ በተበረዘ መፅሀፍ ድህነይ የለም p 2
42▸ በተበረዘ መፅሀፍ ድህነይ የለም p 3
43▸ በተበረዘ መፅሀፍ ድህነይ የለም p 4
44▸ በተበረዘ መፅሀፍ ድህነይ የለም p 5
45▸ በተበረዘ መፅሀፍ ድህነይ የለም p 6
46▸ የስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ ማነው?
47▸ ክርስቲያን ከመሆናቹ በፊት አስቡ
48▸ የስም ማጥፋት በእግዚአብሄር ላይ p 1
49▸ የሰው ስጋ መብላት በኢስላም እና ክ/ር
50▸ ከበላማ እንዴት አይፀዳዳም?
51▸ የሙስሊሞች መጨረሻ የት ነው?
52▸ ቸር ሲባል ለምን ተቃወመ?
53▸ መልእክት ለሙስሊሞች!!
54▸ የእግዚአብሄርና የኢየሱስ ልዩነት
55▸ ለኢየሱስ አምላክ አለው!
56▸ መላጣው ሰውዬ እና ብላቴናዎቹ
57▸ ኢየሱስ አምላክ ላለመሆኑ 10 ማስረጃ
58▸ የቁርአን እና የባይብል ምስክርነት
59▸ አላህ ወንድ አይለም!!
60▸ የቻናሉ ማብራሪያ
61▸ ነገረ ዕብራውያን
62▸ አስክሮተ ሀጥያት
63▸ የነቢያት ሀጥያት በክርስትና 1
64▸ የነቢያት ሀጥያት በክርስትና 2
65▸ ቶማስ ጌታዬ እና አምላኬ ማንን...
66▸ የኢየሱስ ነፍስ መጨረሻው የት ነው?
67▸ ለምን እንሞታለን?
68▸ አላህ ለምን አይታይም?
69▸ በስብሶ ሊቀር የነበረው አምላክ
70▸ በቻናሉ ውስጥ የሚሰጡ  አገልግሎቶች

               ¶[SHARE]¶ AND ¶[ JOIN ]¶

📚.𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

30 Oct, 08:35


በስብሶ ሊቀር የነበረው አምላክ😳

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

26፥81 ያም የሚያሞተኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡ وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ


ይሄን ጉድ ሰምተው ይሆን ክርስቲያኖች አምላካችን ብለው የሚይዙት ኢየሱስ ሞቶ በስብሶ ሊቀር እንደነበር አብዛኛው ክርስቲያን ወገኖቻችን ከሚፎክሩበትና ኢየሱስ አምላክ ለማድረግ ከሚጥሩባቸው መፈክሮች ውስጥ ዋነኛው ኢየሱስ ሞቶ ተነሳ የሚል ነው ሰው ሞቶ አይነሳም ስለዚህ ኢየሱስ ከሞት ሞትን ድል አድርጎ ስለተነሳ አምላክ ነው ይሉናል ነገረ የሚያስቅ ነው ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ እንደማይችል በራሱ አደበት ነግሮናል
ዮሐንስ 5፥30 “እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤

አዎ ኢየሱስ በራሱ ምንም ማድረግ አይችልም ችሎም አያውቅም ለምን ከተባለ ክርስቲያኖች የሚፎክሩበት ኢየሱስ ከሞት ተነሳ የሚባለው እንኳን እራሱ ሳይሆን የተነሳው እግዚአብሄር ነው ያም እግዚአብሄር ሞቶ ከመበስበስ አድኖታል በሰፊው እናየዋለን ነገሩ እንዲህ ነው እደ ክርስቲያኖች አሳብ ከሆነ ኢየሱስ አዳም ለሰራው ሀጥያት ምክንያት እኛን ሊያድን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞተልን ይሉናል ማገናዘብና ማስተንተን ያቃተው ጭንቅላት የአምላክን ሞት ከህሊናው ተጣልቶ አምኖ እደኛው ሞቶ ከመበስበስ ያዳነው አካል እዳለ ብትሰማ ምን ሊውጥህ ይሆን ያው አምላክ አይሞትም ግልፅ ነው የሞተው ፍጡር ነው ሆኖም ክርስቲያኖች አምላክ ብለው ስለሚቀበሉት እስኪ አምላክ ሞተ ብለን እናስብና ሙግታችንን እናቅርብ ኢየሱስ ሞተ ከዛ እግዚአብሔር አስነሳው
ሐዋርያት 2፥24 “እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።”
ሐዋርያት 2፥32 “ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤”
 
አዎ ወደድክም ጠላህም ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ አልተነሳም እግዚአብሄር አስነሳው እንጂ እግዚአብሄር ከሞት ባያስነሳው ኖሮ የኢየሱስ መጨረሻው ከላይ ፎቶው ላይ እንዳለው ነበር ፎቶውን መመልከት ትችለለህ
👉 [ PHOTO ]
ፎቶው ላይ እዳያቹት እንግዲህ የኢየሱስ መጨረሻ ሊሆን ነበር ለትንሽ ተርፏል ታሪኩ እንዲህ ነው ኢየሱስ ከሞተ ቡሀላ እግዚአብሄር ሞቶ ከመበስበስ አዳነው ጥቅሱን በሐዋርያት 13:34-37 ላይ ታገኙታላቹ እስኪ ጥቅሱን በታትነን እንየው

ሐዋርያት 13፥34  “እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል።”

እንደገናም ወደ መበስበስ እዳይመለስ ከሙታን አስነሳው የሚለው ይሰመርበት እግዚአብሄር ኢየሱስን ባያስነሳው ኖሮ መጨረሻው በስብሶ አጥንት መሆኑ ነበር እኔ አላልኩም ጥቅሱ እራሱ ይቀጥልና መበስበስ ምን እደሆነ ያስረዳናል
ሐዋርያት 13፥36 “ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤”
 

ዳዊትን አንቀላፋ ሲል ያው ግልፅ ነው ሞተ ነው  ታዲያ ዳዊት ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ ሲል ሞቶ ስጋው በሰበሰ እንጂ በውሀ ረጠበ እዳልሆነ ግልፅ ነው ሆኖም ዳዊትና አባቶች ሞተው ስጋቸው በስብሶ ነበር ታዲያስ ከተባለ ኢየሱስ ግን ሞቶ ከመበስበስ እግዚአብሄር አዳነው
ሐዋርያት 13፥37 ይህ እግዚአብሔር ያስነሣው ግን መበስበስን አላየም።”

ቁጥር 34 ላይ ያለውን እና ቁጥር 37 ላይ ያለውን ስንደምረው ፍቺው እንዲህ ነው ሌሎች ነቢያቶችም ሆኑ ሰዎች ሞተው በስብሰዋል ነገር ግን ኢየሱስን እግዚአብሄር ስላስነሳው አልበሰበሰም ኢየሱስን እግዚአብሄር ባያስነሳው ምን ሊውጠው ነበር
                          [ጥያቄ]
¶እግዚአብሄር ለኢየሱስ አዝኖ ባያስነሳው የኢየሱስ መጨረሻ በስብሶ መቅረት ነበር? ይሄ ለአምላክነት በሀሪ ተገቢ ነውን?
¶ኢየሱስ አምላክ ነው ካላቹን በራሱ መነሳት እዴት አልቻለም?ሌላ አምላክ እዴት አስነሳው?
¶ያ ኢየሱስ ያስነሳው አምላክ ኢየሱስን በስልጣን ይበልጠዋል?

መልሱ አዎ ነው ይበልጠዋል ምክንያቱ ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም ከሞት ሊያስነሳ የሚችል አንዱና ብቸኛው አምላክ አላህ ብቻ ነው
26፥81 ያም የሚያሞተኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡ وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሚያሞት" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሚቱ" يُمِيتُ ሲሆን በዐማርኛ "የሚገል" በሚል ተቀምጧል። በተመሳሳይ በባይብል በሞት የሚያሞት አንድ አምላክ ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥6 ያህዌህ ያሞታል፥ ሕያው ያደርጋል። ወደ መቃብር ያወርዳል፥ ያወጣል። יְהוָ֖ה מֵמִ֣ית וּמְחַיֶּ֑ה מֹורִ֥יד שְׁאֹ֖ול וַיָּֽעַל׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያሞታል" ለሚለው የገባው ቃል "መሚት" מֵמִ֣ית ሲሆን በዐማርኛ "ይገላል" በሚል ተቀምጧል፥ አምላክ ወደ መቃብር በማውረድ እንደሚያሞት ሁሉ በትንሳኤ ቀን ከመቃብር በማውጣት ሕያው ያደርጋል። ሲቀጥል ደሞ ኢየሱስ ከነ ጭራሹ አልሞተም
4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

ስለዚህ ኢየሱስ አምላክ ለማድረግ ሲሉ ለአምላክ የማይገባውን በሀሪ አላብሰውት ጫፉን ያልተነካውን ኢየሱስ ተገደለ ለእኛ ሲል ሞተ እያሉ የማይገባውን እርክሰት እያላበሱት ከሱም ብሶ ከመበስበስ እደተረፈ ይተርኩልናል ታዲያ እርሶ ምን ይጠብቃሉ ከዚህ ሁሉ ትርምስ ወተው ቀጥተኛውን መንገድ ኢስላምን ተቀበሉ
17፥18 በልም፦ *"እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና"*፡፡ وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا
34፥49 *«እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም ተወገደ»* በላቸው፡፡ قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ

አላህ ሂዳያ ይስጣቹ ለእኛም በቅኑ መንገድ ላይ ሆነን ፅናቱን ይስጠን አሚን

ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

29 Oct, 16:06


ማበረታታት

አንድ ሰው በሚሠራው መልካም ሥራ ስናበረታታው በውስጥ ደስታ እና ፈገግታ የሚያመነጩ ሆርሞኖች አሉ፥ እነዚህ ሆርሞኖች ለውበት፣ ለጤና፣ ህመም ለማስታገስ እና እርጅና ለማደስ የሚረዱ ፍቱን መድኃኒት ናቸው። ሰውን ማበረታታት አንርሳ!
አሏህ መልካም ሥራችሁን በኢኽላስ ይቀበላችሁ! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

29 Oct, 15:46


ክርስቲያን አቃቢያን(ሚሺነሪዎች) የኑሮ ውድነት ተጨምሮ እኛ ሙስሊሞች ጋር ላይቭ ላይ ሲፋጠጡ

ሥላሴን አስረዱን ስንላቸው እያስረዱን መስሏቸው ግን ለእኛ የሚሰማን😁😁


😜ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም


             ¶[SHARE]¶ AND ¶[ JOIN ]¶

𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

26 Oct, 09:28


አሰላሙ አለይኩም ወራመቱላሂ ወበረካትሁ በተለያየ ሀገር የምትገኙ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እዲሁም ክርስቲያን ወገኖች ሰላም ብያለው

[በቻናላችን የምንሰጣቸው አገልሎቶች ]

¶ ስለ ክርስትና ንፅፅራዊ ፅሁፎች ይፃፍበታል
¶ ኢስላም ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ይመለስበታል
¶ አልፎ አልፎም ጥያቄና መልስ እንጠያየቅበታለን
¶ በክፍል በክፍል ክርስትና እና እስልምና እናጠናለን
[አድራሻ]
𓆩𝄽𝐍𝐞𝐣𝐚 𝐂𝐨𝐦𝐩𝐚𝐫𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞 & Faith Defender 𝄽𓆪

ስለዚህ ዳይ ወደ ሊንክ ተቀላቀሉ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን ይሄን ማስታወቂያ ባላቹበት ግሩፕ እና ያላቹ ሰዎች ጋር ሼር እያደረጋቹ እድትጋብዙ ስል በትህትና እጠይቃለው ጀዛኩሙላህ ኸይር
የቻናሉ ሊንክ
👉 ¶[ @eslmnan_teqebelu ]¶

ከወንድም NEJA 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕 🇵🇸
@eslmnan_teqebelu
ወሠላሙ ዐለይኩም


¶[SHARE]¶ AND ¶[ JOIN ]¶

2,834

subscribers

65

photos

31

videos