ፍቅር እስከ መቃብር @fkreskemekabr Channel on Telegram

ፍቅር እስከ መቃብር

@fkreskemekabr


ምርጥ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ
መሳጭ የፍቅር ግጥሞች
በሳቅ የሚገሉ ገራሚ ቀልዶች
እያየን እንጨምራለን

ፍቅር እስከ መቃብር (Amharic)

ፍቅር እስከ መቃብር አዲስ ታሪኩ ለሁሉም ፍቅር የተመረጡ ማንኛውም እናት ወይም እናቶ ላይ በተጻፉ ልብ አንጠልጣይዎች እና ቋንቋዎች የፍቅር ታሪክ ለመስጠት እና ለመረጠው በመቃብሩ ላይ ተመሳጠናል። ስለዚህ የፍቅር ግጥሞችን ለመስጠት ብቻ ሳይከብርና የሚያስችል፣ ማህበሩን እና ሁለቱን ሰነድ የሚያመልጠውን በሳቅ የሚገሉ ገራሚ ቀልዶች በቅርብ ውስጥ እንደኛ ምሥጢር ለመክፈት ቅርብ ነን። በእያየን እና በእንጨምር በመቃብሩ በብዛት ቦታ የሚገፉ ሁሉም በድጋፍ እና በተመሳሳይ ገንዘብ እንዲያወሩ ለማገልገል እንደሚረዳን ድምፅ አሉ።

ፍቅር እስከ መቃብር

17 Oct, 19:34


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 17 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.

ፍቅር እስከ መቃብር

06 Jan, 18:50


🎅🎅🎅
💚የኔ ውድ የቻናሌ ተከታታዮች❤️
🎄የዘንድሮው የ ገና በዓል
😊የደስታ
😌የጤና
🤑የብልጽግና
😘መልካም ነገሮች ሁሉ ወዳንተ/ቺ/ ሚመጡበት
🎅ስኬታማ ምትሆንበት/ኝበት/
🎄🎄🎄🌲🐓ይሁንላቹ🐓🎄🎄🎄🎄
❤️
💛
💚

@fkreskemekabr
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

30 Dec, 17:14


❤️ፍቅር በዚህ መንገድ📖
❤️❤️ በ ፍቅር እስከ መቃብር❤️❤️
❤️ክፍል-2

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ
.
ሁሴን ዕድሜው ከ 35 ትንሽ ቢዘልም ፈርጣማ የሆነው የስፖርት ሰው
የሚያስመስለው ፈርጣማ ተክለሰውነቱ እና ግንባሩ ላይ የተደፋው ጥቁር
ሉጫ ፀጉር የሃያ አምስት አመት ወጣት ያስመስለዋል፡፡ የመጀመሪያ
ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሥነ ጹሁፍ ከአስር ዓመት በፊት
ሲቀበል፣ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ ከፈረንሳይ አገር በፍልስፍና ከሦስት
ዓመት በፊት አግኝቷል፡፡ አሁን የሚኖረው እናትና አቧቱ ባወረሱት ልደታ
በሚገኘው ባለ ሦስት መኝታ ክፍል ቪላ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ወላጆቹ
ሞተዋል፡፡ እሱ ደግሞ ብቸኛ ልጃቸው ነበር፡፡በአሁኑ ሰዓት አብራው
የምትኖረው ፎዚያ ነች፡፡ ሁሴን ፎዚያን እንደእህቱ ቢያያትም ምንም አይነት
የስጋ ትስስር ግን የላቸውም ፡፡
ሁሴን ዋና አዘጋጅ ሆኖ በሚሰራበት ፍኖተ ጥበብ በተሠኘ ተነባቢ የግል
ጋዜጣ ውስጥ ስልሳ ፐርሰንት የአክሲዬን ድርሻ አለው፡፡ ጋዜጣው ሳምንታዊ
ሲሆን አንድ መቶ ሺ እትም በየሳምንቱ በመላው አገሪቱ ያሰራጫል፡፡
ጋዜጣው ትርፋማ ነው ብሎ ለመናገር ባያስደፍርም …. በጣም ተወዳጅና
ተነባቢ መሆኑን ግን አስረግጦ መመስከር ይቻላል፡፡
ሁሴን በህይወቱ ብዙ ሴቶች ገብተው ወጥተዋል፡፡ አብዛኞቹ ተስፋ
አስቆርጦቸው ትተውት ሔደዋል፡፡ .. ጋብቻ አይፈልግ… ልጅ መውለድ
አያጓጓው... ቃል አይገባለቸው .. ተስፋ አይሰጣቸው .. በቃ ፍቅርና ወሲብ
ብቻ! ታዲያ ጫንቃቸው ደህንነትን የሚሻው ሴቶች ከተወሰነ እርቀት በላይ
አይታገሱትም፤ ጥለውት ይሔዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በጭቅጭቅና በንዝንዝ
ፋታ ስለሚነሱት ያንገሸግሹታል፤ሲያንገሸግሹት ደግሞ ፊቱን ያዞርባቸዋል..
ይተዋቸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በህይወቱ ውስጥ ሦስት ሴቶች ቀርተዋል፡፡ አንደኛዋ በንግድ
ስራ የምትተዳደረውና አምስት ዓመት በጓደኝነት ስምንት ዓመት በፍቅረኝነት
አብራው የዘለቀችው ኤደን ስትሆን ሁለተኛዋ አዕምሮውን ዘና ማድረግ
ሲያሠኘው የሚፈልጋት የቡና ቤቷ ትዕንግርት ነች፡፡ ሦስተኛዋ ደግሞ
አዕምሮውን ጠቅላላ ጠፍንጋ የያዘችው በፍቅር ሊቀውስላት ጥቂት የቀረው
በአካል የማያውቃት የጋዜጣው አምደኛ ሚስጥር ነች፡፡
ስለ ምስጢር ሲያስብ አንገሸገሸው፡፡ ለወትሮው ምቾትን የሚለግሠው የቤቱ
ሶፋ ዛሬ ቆረቆረው፡፡ ሞባይሉን ከኪሱ አወጣና መጎርጎር ጀመረ፡፡ ቀን
ደውላለት ነበር… ያደረጉትንም የስልክ ልውውጥ ቀድቶታል፡፡ ከፈተው፡፡
ደጋግሞ ሲያዳምጠው ይሄ ለ 13ኛ ጊዜ ነው፡፡ እያንዳንዷን ከአንደበቷ
የወጡትን ቃላቶች ሸምድዳቸው ተብሎ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈበት
ይመስላል፡፡ ሞባይሉ ማውራት እሱ ማዳመጥ ጀመረ፡፡
‹‹ከየት ነው ምትደውይው?››
‹‹ከየትስ ቢሆን ምን ይፈይድልሃል?፡፡.ይልቅ ለምን ደወልሽ?... የሚለውን
ጥያቄ አይቀልም›› ‹‹እንደዛ ብዬ እንኳን አልጠይቅሽም፤ ዋናው መደወልሽ
ነውእንጂ የደወልሽበት ምክንት ብዙም አያስጨንቀኝም››
‹‹የውክልናው ወረቀት ደረሠህ?›› ቀጭን ማራኪ ድምፅ
‹‹አዋ ደርሶኛል…ታደርጊዋለሽ ብዬ ግን አላመንኩም ነበር››
‹‹ለምን?››
‹‹እኔ እንጃ፡፡ ይሄን ያህል እንዴት ልታምኚን ቻልሽ… ግራ የሚገባ ነገር ነው፡፡
በነገራችን ላይ እስከ አሁን በእኛ ጋዜጣ ላይ ከታተመልሽ ሃያ ሰባት የሚሆኑ
አጫጭር ልብወለዶች መካከል አስራ ሁለቱን መርጬ ለሁለት ታዋቂ
ደራሲያን ሠጥቼያቸው ነበር፤ አንብበው አስተያየታቸውን እንዲሠጡኝ››
‹‹ጥሩ ነዋ›› ጉጉት በማታይበት የቀዘቀዘ ድምፅ፡፡
‹‹አንደኛው ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? ‹ይሄ ድርሠት በአማተር ፀሐፊ ተጻፈ
ብትለኝ ፍፁም አላምንህም፤ እርግጠኛ ነኝ ፀሐፊው አንተ ራስህ ነህ፤
በስምህ ላለማሳተም መቼም በቂ ምክንያት ይኖርሃል፤ ምስጢር የሚለውን
የብዕር ስም ግን ለምን መጠቀም እንደፈለክ ፍፁም አልገባኝም ፡፡›ነበር
ያለኝ›
‹‹ታዲያ ለምን በራስህ ስም አታሳትመውም?››
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ?››
‹‹እውነቴን ነው፡፡››
‹‹ቀልዱን አቁሚ በዚህ ወር መጨረሻ መፅሐፍሽ ይታተማል፤ የምረቃ
ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስቢያለሁ፤ዝግጅቱ ላይ መቼም ትገኚያለሽ?››
‹‹ኪ…ኪ..ኪ.›› ከት ብላ ሳቀች፡፡ደነገጠ፡፡ ሣቋ ከሆነ ከሚያውቀው ሳቅ ጋር
ተመሳሰለበት፡፡
‹‹ምን ያስቅሻል?››
‹‹አታስብ አልመጣም››
‹‹ኦ! ….ኸረ በፈጠረሽ ልታቀውሽኝ ነው፡፡ ስራዬን በትክክል መስራት እንኳን
እየተሳነኝ ነው፡፡››
‹‹የማይመስል ነገር፤ በአካል እኮ አታውቀኝ፡፡››
‹‹ምንም ሁኚ ምንም አፈቅርሻለሁ፡፡ ፍፁም ልረሻስ አልችልም…ነፍስሽን ነው
ያፈቀርኳት፡፡ እስቲ በፈጠረሽ ስለ ራስሽ ጥቂት ንገሪኝ…››
‹‹ስለ አቋሜ ማለትህ ነው?››
‹‹ይቻላል... አዋ፡፡››
‹‹እንግዲህ እኔ ሦስት አይነት ሰዋ ነኝ...እንደ አያቴ ..እንደ ጓደኞቼ...እና እንደ
አፋቃሪዎቼ...››
‹‹ብታብራሪልኝ››
‹‹አያቴ ነፍሶን ይማርና... የእኔ መላአክ ነበር የምትለኝ ..እሷ ስታደናንቀኝ
ክንፍ ሁሉ ያበቀልኩ መስሎ ይሰማኝ ነበር...እንደሷ እንከን አልባ አይነት ነኝ፡፡
እንደ ጓደኞቼ ደግሞ ቆንጆም ያልሆንኩ ...የማላስቀይምም እንደው በድርባቡ
አርገው ነው የሚገልፁኝ፡፡አፍቃሪዎቼ ደግሞ አያቴ እንደምትለው መላአክ
ነበርሽ ይሉና…. ዳሩ ምን ያደርጋልን? ይጨምሩበታል››
‹‹ምን ማለት ፈልገው ነው?››
‹‹ቆንጆ መሆኔን አረጋግጠው …እውር በመሆኔ የተሰማቸውን ቅሬታ
ለመግለፅ ፈልገው ..››ንግግሩ ተቋረጠ፡፡
‹‹ ትሁን .. እውርም ትሁን፡፡ ከፈለገች በዊልቸር ትሂድ፡፡ የፈለገችውን ትሁን ፡፡
እወዳታለሁ…. አፈቅራታለሁ፡፡ ከራሱ ጋር ሲያወራ በእጁ ያንከረፈፈው
ሞባይሉ ጮኸ፡፡ኤደን ነበረች፡፡
‹‹ደህና ዋልሽ?››
‹‹ደህና ነኝ..ምናው ጠፋህ?››
‹‹ስራ በዝቶብኝ ነው››
‹‹የት ነህ?››
‹‹እቤት ነኝ››
‹‹እየመጣሁ ነው››
‹‹ወዴት?››
‹‹አንተ ጋር ነዋ››
‹‹የተጨናነቀ ስራ ላይ ነኝ፡፡ ብቻዬን መሆን ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹ከናፈኩሽ ነገ እንገናኛለን… ከደበረሽ ደግሞ ጓደኞችሽ ጋር መሄድ ትችያለሽ፤
እኔን ግን ተይኝ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ… ቻው፡፡››ብሎ ስልኩን ጆሮዋላይ
ጠረቀመባት
እንዲህ አዕምሮው በተጨናነቀበት ወቅት ከኤደን ጋር መገናኘት ፍፁም
አይፈልግም፡፡ በጭቅጭቋ ይበልጥ ታበግነዋለች፡፡ ‹‹ቅራቅንቦ ጥያቄዎቿን
መመለስ ከቀን ስራ በላይ ይከብዳል›› ይላል፡፡ ‹‹ምን ሆነሃል? … ምነው
ጠቆርክ?...ከማን ተጣለህ?..ካመመህ ሃኪም ቤት እንሂድ..››
ወዘተ..ሳይለያዩ ይሄን ሁሉ ዘመን እንዴት አብረው ሊቆዩ እንደቻሉ ግርም
ይለዋል፡፡ ስለ አብሮነታቸው ዘውትር እቅድ እንዳወጣች ነው፡፡ አንድም ጊዜ
ግን ተሳክቶላት አያውቅም፤ያም ሆኖ ግን ተስፋ አትቆርጥም፡፡
ከተቀመጠበት ተነሳና ሳሎን ውስጥ ተንጎራደደ፡፡ አዕምሮው ፍፁም
ሊረጋጋለት አልቻለም፡፡ ወደ ውጭ ሊወጣ ፈለገ፡፡ ሠዓቱን ተመለከተ ሁለት
ሠዓት ተኩል ይላል፡፡ ሃሳቡን ቀየረና ስልኩን ደወለ፡፡ ዘና የሚያረገው ሰው
ፈለገ፡፡
‹‹ሄሎ... ትንግርት››
‹‹እሺ የኔ ፍቅር››
‹‹አለሁልሽ .. የት ነሽ?››
‹‹ቤተ መንግስት የራት ግብዣ ላይ ነኝ››
ፈገግ አለ ‹‹ከምሬ ነው››
‹‹አንድ ደንበኛዬ ጭን ላይ ቁጭ ብዬ እያጋልኩት ነው››
‹‹መምጣት አትችይም?››
‹‹ቢዝነስ እኮ ተነጋግሪያለሁ፡፡››
‹‹ስንት?››
‹‹የዛሬው ዋጋዬ ሀለት-መቶ ሃምሳ ነው….. ከትላንቱ ትንሽ ረከስ ብያለሁ››
‹‹ወደ ትላንቱ ዋጋሽ ልመልስሻ ..እኔ ጋር ነይ፡፡››
‹‹ቀነዘረብህ እንዴ?››
‹‹ብዙም አይደል .. ብቻ አስፈለግሽኝ፡፡ ያቺን
ክፍል 3 ይቀጥላል
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

20 Dec, 15:33


❤️ ፍቅር በዚህ መንገድ📖
❤️❤️❤️ፍቅር እስከ መቃብር❤️❤️❤️
🌹ምዕራፍ አንድ
#ክፍል-1

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ


ውጫዊ አካሏ በቀይ ቀለም የተሸፈነ ቪታራ መኪና ውስጥ ገብቶ ሞተሩን
ለማስነሳት ቁልፉን ሲነካካ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ተንጣረረች፡፡ አነሳው፡፡ ደዋዩ
ኢንጅነር ሠሎሞን ነበር፡፡
‹‹ሄሎ..››
‹‹የት ነህ ወንድም ጋዜጠኛ?››
‹‹ባክህ ገና ከቢሮ እየወጣሁ ነው፡፡ ላብድልህ ነው፤ ግራ ተጋብቻለሁ››
‹‹ደሞ ምን ገጠመህ?›› ሠሎሞን ነበር ጠያቂው
‹‹ሌላ ምን ይገጥመኛል …የዛችው ልጅ ነገር ነዋ፡፡››
‹‹ኦ!! የደንበኛህ?››
‹‹አዎ››
‹‹ዛሬም ፖስታዋ ደርሶሃል ማለት ነው?››
‹‹አዎ!! የዛሬው ደግሞ የተለየ ነው፡፡ ልብን ስውር ሚያደርግ ፁሁፍ ነው
የላከቸው….››
‹‹የላከቻው ፁሁፍ ነው ወይስ አንተ ለእሷ ያለህ ስውር ፍቅር ልብህን
የሰወረህ››
‹‹ሁለቱም ምክንያት ትክክል ነው››
‹‹በቃ በቃ አንተ እንደው ስለእሷ ማውራት ከጀመርክ ማብቂያ የለህም
አይደል፤ልታወራኝ ከፈለክ የመጠጥ ግብዣ እፈልጋለሁ፡፡ የተለመደው ቤት
ተጐልቼ እየጠበኩህ ነው ፡፡››
‹‹እንዴ በቀኑ! ? ገና አስራ አንድ ሠዓት እኮ ነው፤ ››
‹‹ባክህ አትጨቅጭቀኝ…. ምትመጣ ከሆነ ና›› ሠሎሞን ተበሳጨ
‹‹እሺ ጌታው ከሃያ ደቂቃ በኃላ እጎንህ እገኛለው… እስከዛው ቻው››ስልኩን
ወደ ኪሱ መልሶ ሞተሩን አስነሳና ወደ ሜክሲኮ ከነፈ፡፡ ከሠሎሞን ጋር ከሃያ
ዓመት በላይ በጓደኝነት አሳልፈዋል፡፡ በባህሪ፣ በስራ፣ በእምነትና በኑሮ
ፍልስፍናቸው በጣም በተለያየ መንገድ የሚጓዙ ቢሆንም ይህ ልዩነታቸው
ግን ጓደኝነታቸውን ለመበረዝ ጉልበት አልነበረውም፡፡
ኢንጅነር ሠሎሞን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፡፡ የሃይማኖቱን ህግና
ሥርዓት ለማክበር ዘወትር ከልብ ይጥራል፡፡ ግን አይሣካለትም፡፡ ህግጋቱን
ይጥሳል፤ ደንቦቹን ያፈርሳል፤ ከዛም በፀፀት ይቃጠላል፡፡ እግዚአብሔርን
በማስቀየሙ እራሱን ይቀየማል፡፡ብዙውን ጊዜ ለሥህተት ተጋላጭ እንዲሆን
መነሻ ምክንያት የሚሆኑት ሁለት ነገሮች ሚስቱና ስራው ናቸው፡፡ ከየውብዳር
ጋር ከተጋቡ አስር ዓመት አልፏቸዋል፡፡ በዚህ የጊዜ ሂደት ውስጥ
የተትረፈረፈ ሀብት ባለቤት መሆን ከማቻላቸውም በተጨማሪ ሁለት ሴት
ልጆችንም ማፍራት ችለዋል ፡፡ ሠላም ግን አልነበራቸውም፤ ሦስት ቀን
በሠላም ቢያሳልፉ ተከታዮቹን ሦስት ቀናት በጥልና በኩርፊያ ጀርባ
ተሠጣጥተው ይከርማሉ፡፡ በዚህ ወቅት ታዲያ ሰሎሞን ቤቱ ያስጠላዋል፡፡
ጥሎ ይወጣል…. ከወጣም ይጠጣል….. ብክት እስኪል ይጠጣል..ሲጠጣ
ደግሞ ብዙ ይሳሳታል .. ሠው ያስቀይማል፣ ከሴት ይዳራል፣ ብር
ይረጫል፤ከዛ በማግስቱ ናላው እስኪዞር በጥልቀት ይፀፀታል፡፡
ስራውን በተመለከተ ደግሞ ደረጃ ሦስት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ
(ኮንትራክተር) ነው፡፡ ሥራ ለማግኘት ጉቦ ይሰጣል፡፡ ..ሥራው ሲበላሽበት
ሥህተቱን ለመሸፈን ጉቦ ይሠጣል፡፡ ካደረገው በኃላ ግን እንቅልፍ እስኪያጣ
ይበሳጫል…. ያፀፀታል፤ ደግሞ ላለማድረግም ይምላል.. ይገዘታል፡፡ ግን
መልሶ መላልሶ በተመሳሳይ ስህተት ውስጥ ዘወትር ይዘፈቃል ፡፡ሠሎሞን
ማለት ይሄ ነው፡፡ጥፋት..ፀፀት፤ጥፋት…ፀፀት፡፡
ሁሴን ስለ ሠሎሞንን እያሠላሠለ ሣይታወቀው የተቃጠሩበት ቦታ ደረሠ፡፡
መኪናውን ተገቢው ቦታ ካቆመ በኃላ ወደ ውስት ዘለቀ፡፡ ቡና ቤቱ ጭር
ብሏል፡፡ ታዳሚዎቹ በቁጥር ናቸው፡፡ ወንድ አስተናጋጆች እዚና እዛ
ተሠባጥረው ቆመው የሚሠጣቸውን ትዕዛዝ እየተቀበሉ ክብር ደንበኞቻውን
በታሪነት ለማስተናገድ ሲጣጣሩ ይታያሉ፡፡
እንደገባ ነበር ሠሎሞንን የለየው፡፡ አጭር ሠላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ፊት
ለፊቱ ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡
‹‹ሙሽሮቻችን አልገቡም እንዴ?›› ሁሴን ነበር ጠያቂው፡፡
‹‹አንተ ደግሞ እነሱን ካለየህ ጉሮሮህ ለመጠጥ አይከፈትም፡፡ ከደቂቃዎች
በኋላ ይንጋጉልሃል፡፡ ንስርህም እንደ ንግስት ታጅባ ከች ማለቶ አይቀርም››
ሁሴን አስተናጋጁን ጠራና ውስኪ አዘዘ፡፡
‹‹ምነው ውስኪ?›› ጠየቀ ሠለሞን
‹‹እንዴት?››
‹‹ለስላሳ የምታዝ መስሎኝ ነበር፡፡ ሃይማኖትህ ይፈቅድልሃል እንዴ?›› ይሄ
የሠሎሞን የሁልጊዜ ትችቱ ነው፡፡
‹‹ሃይማኖቴ ምንድነው?›› ሁሴን ነበር
‹‹መቼም ሁሴን ብሎ ክርስቲያን የለ››
‹‹ይሄው እንግዲህ የአንተ ችግር እዚህ ጋር ነው፡፡ እርግጥ ማንም
እንደሚያውቀው ቤተሰቦቼ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነበሩ፡፡ በዛ
ምክንያት እኔ ስወለድ ምንም ሳይጠረጥሩ ልጃችን እንደኛው ሙስሊም
ስለሚሆን የሙስሊም ስም እንሸልመው ተባባሉና ሁሴን አሉኝ፡፡ እኔ ግን
እንደምታውቀው ሙስሊምም፤ ክርስቲያንም ፤ቡዲስትም መሆን
አልቻልኩም፡፡ በዚህም ተነሳ የቤተሠቦቼ ትንቢት አከሸፍኩባቸው ማለት ነው
፡፡ ይሁን እንጂ ለዚህ ስህተታቸው መታሠቢያ ይሆን ዘንድ ሙስሊማዊ ስሜን
ይዤ ይሄው እየኖርኩ ነው፡፡››
አስተናጋጁ የታዘዘውን ውስኪ አምጥቶ ፊቱ አቅርቦለት ወደ መቆሚያ ታው
ተመለሰ ፡፡ ሠሎሞን የተቋረጠ ጫወታቸውን አራዘመው፡፡‹‹ግን ለዚህች
ሚስኪን ነፍስህ አንዲት ማረፊያ ብታበጅላት ምን አለበት?››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ማለት አንድ የራስህ ሃይማኖት ቢኖርህ?››
‹‹እሺ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ሃይማኖቱ ያስፈልገኛል ብዬ ልመን፡፡ እስቲ ይሄኛው
ሃይማኖት ትክክል ነው ብለህ አሳምነኝ እና እሱን ልከተል….››
‹‹እኔ ይሄኛው ትክክለኛ .. ያኛው ደግሞ በስህተት የተሞላ ነው አልልህም፡፡
ሃይማኖት የምርምር ሳይሆን የእምነት ውጤት ነው፡፡ መቼም ማስተርስህን
የሠራኸው በፍልስፍና እንደመሆኑ መጠን የአብዛኞቹን ሃይማኖቶች
ፍልስፍናዊ ፍሬ ሀሳባቸውን የመመርመር እድሉ እንደነበረህ እገምታለሁ፡፡
ስለዚህ ከዛ በመነሳት አንዱን መምረጥ የሚያቅትህ አይመስለኝም፡፡››
ሁሴን ፊቱ የተቀመጠውን የውስኪ ብርጭቆ አነሳና አንዴ ጠቀም አድርጎ
ከተጎነጨለት ቡኃላ መልስ መስጠት ቀጠለ፡፡
‹‹እርግጥ እኔ በእግዚአብሔር አምናለሁ፡፡ የእኔ እግዚአብሔር ግን
በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ እስካሁን አላገኘሁትም፡፡ የእኔ እግዚአብሔር
ፍፁም የተለየ ነው፡፡››
‹‹ለምሳሌ …?››
‹‹ለምሳሌ ሁሉም ሃይማኖቶች ማለት በሚቻልበት ደረጃ በሲኦልና ገነት
ያምናሉ፡፡ ይሄንን ፅንሰ ሀሳብ የእኔ አዕምሮ ደግሞ ፈፅሞ ሊቀበለው
አይችልም፡፡እግዚአብሔር ፈጥሮናል ብለን የምናስብ ከሆነ እኛ በዚህች
ምድር ላይ ለምንፈፅመው ሥህተት ሀላፊነቱን ብቻችንን መውሰድ ያለብን
አይመስለኝም፡፡ የሥህተታችን ዋና ምንጩ አፈጣጠራችን (የተሠራንበት
ንጥረ ነገር) ነው ብዬ ስለማም ..እኛ አሁን የሆነውን የሆነው በእግዚአብሔር
ፍቃድና ምርጫ ነው፡፡ ስለዚህ አፈጣጠራችን ለስህተቶች ተጋላጭ
እንድንሆን ሆኖ መሆኑን ገና ከመፈጠራችን በፊት ዲዛይኑን የሠራው
እግዚአብሔር በደምብ ያውቃል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይሄ እውነት ከሆነ ደግሞ
የተሳሳተውን ለማጥቃት ሲኦልን መገንባት ለምን አስፈለገ? አለዚያማ
እግዚአብሔር የእነ ሂትለር ግልባጭ ነው ማለት ይሆናል፡፡ ሂትለር አይሁዶችን
አይሁድ ስለሆኑ

ክፍል 2...ይቀጥላል ....
ለወዳጆ ያጋሩ!
@fkreskemekabr
@fkreskemekabr
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

20 Dec, 15:27


❤️❤️❤️❤️እሚገርም የፍቅር ታሪክ ስሜቱን ኣጣጥሙት❤️❤️😍👍👍
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

13 Sep, 13:27


ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚአብሄር፦

•ከተፈታኞቹ መካከልም ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ አምጥተዋል።

•75 ነጥብ 5 በመቶ ያህል ተፈታኞች ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያመጡ ናቸው።

•ሁለት ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ አለው።

•ከተፈታኞቹ መካከል ወንዶች 682 ሺህ 572 ሲሆኑ 572 ሺህ 997 ሴቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል 894 ሺህ 318 በመደበኛ፣ 354 ሺህ 782 በግል እና 6 ሺህ 469 ደግሞ በማታው ክፈለ ጊዜ ተፈታኞች ነበሩ።

በዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን የኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል። ባለፈው አመት ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡት ተፈታኞች 71 በመቶ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

Via #FBC

@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

30 Aug, 20:31


📖📖📖📖📖
በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢራናውያን በእውቀት ጫፋቸው የሚደርስ አልነበረም ይባላል። ምናልባት ጀርመኖች።
ኦመር ኻያም ታዋቂ የፋርስ (የኢራን) ባለቅኔ፣ ገጣሚ፣ ፈላስፋ፣ ሳይንቲስት እና የተዋጣለት የሂሳብ ሊቅ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን በሚኖርበት ከተማ በሚገኝ ስመጥር ዩኒቨርስቲ በር ላይ ኻያም ያቋርጣል። በዩኒቨርስቲው በር ላይ ድንጋይ የተሸከመች አህያ በዱላ የሚቀጠቅጥ ሰው ያያል። ሰውየው አህያዋን በቀጠቀጣት ቁጥር አህያዋ ይባስ ብላ ድንጋዩን እንደተሸከመች ዩኒቨርስቲው በር ላይ ትተኛለች። ጅራቷን በጥርሱ ይነክሳታል።
ኻያም ጠጋ ብሎ "አህያዋን ለምን
ትቀጠቅጣታለህ?" ይለዋል። ዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተጎዳ ህንፃ ለመጠገን ጨረታ አሸንፎ ለጥገና የሚያገለግለውን ድንጋይ ለማስገባት ፈልጎ አህያዋ አሻፈረኝ አልገባም ማለቷን ለኻያም ይነግረዋል።
ኦመር ኻያም ፈጠን ብሎ ወደ አህያዋ ጆሮ ጠጋ አለና የሆነ ነገር ሹክ ሲላት አህያዋ ፈትለክ ብላ ተነሳችና ወደ ዩኒቨርሲቲው ተንደርድራ ገባች።
በዚህ ወቅት የአህያዋ ባለቤት "ጌታዬ ምን ብለዋት ነው? እባክዎ ይንገሩኝ ተመልሼ ተጨማሪ ድንጋይ ለማስገባት ስመለስ እምቢ እንዳትለኝ።" ብሎ ኻያምን ይለምነዋል።
"ዝም ብለሽ ግቢ ከአንች ያልተሻሉ አንዳንድ "ምሁር ነን" ባይ አሉበት። ከእነሱ አታንሽም" ብያት ነው።" አለው ይባላል።
============
(ቀልድን በቁምነገር)
😁 😁 😁


Join.us
@fkreskemekabr
@fkreskemekabr
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

25 Aug, 20:07


💚" #ትዕግስት የታላቅነት ድልብ ነው!!💚

የሰው ልጅ መልካምን ነገር ሁሉ የሚያገኘው የተወሰኑ ሰአታትን በመታገሱ ነው።
የምትሰጠው ነገር ብዙም ይሁን ትንሽ ፈገግታ ጨምርበት።
ለማንኛውም ሠው ጆሮህን ስጥ ድምፅህን ግን ቀንስ
ሁሉንም ውደድ ጥቂቶቹን እመን ማንንም ግን አትበድል!h
የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ።

ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው
መልካም ስም ለሰው ልጅ የመንፈስ ምግብ ነዉ።
የማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነዉ💌

ፍቅር እስከ መቃብር

02 Feb, 22:29


ጋይስ ሁሉ ፒስ እንዴት በቴሌግራም ያገኘነውን ቢትኮይን እንደምናስቀምጥ አሳያቹሃለው
ማለትም እንዴት የቢትኮይን ባንክ አካውንት እንደምንከፍት
2 አይነት መንገዶች አሉ የመጀመሪያው
1⃣#Block chain ላይ ማስቀመጥ
አጠቃቀሙም
1 አፑን ከፕለይ ስቶር ያውርዱ አፑን(ከስር ለቅቄላችሁዋለሁ)

2 install ያርጉት.

3 #sign up አድርጉ።

4 በመጨረሻ የሚሰጣቹን wallet adress #copy አድርገው የትም ቦታ ስትጠየቁ ኮፒ ያረጋቹትን መስጠት ነው።👉ልክ እንደ ባንክ አካውንት ቁጥር ማለት ነው

ማሳሰቢያ
ይህ አፕ ስልካቹ #root ከሆነ አይሰራም

2⃣ local bitcoin በሚባል ዌብሳይት ማስቀመጥ
🌐 https://localbitcoins.net

አጠቃቀሙም
1 በዌብሳይቱ ገብተው አካውንት ይክፈቱ ።

2 ከከፈታቹ በኋላ #wallet የሚለው ውስጥ ገብታቹ recive bitcoin የሚለውን ምረጡ ። ከዛም wallet adress ሲሰጣቹ ኮፒ አድርጋቹ የትም ቦታ ሲያስፈልጋቹ መጠቀም ትችላላቹ.

ማሳሰቢያ 👇
የምትጠቀሙበት #Browser update መሆን አለበት።

ከላይ ባሳየኋቹ መሰረት ያላቹን #btc ማስቀመጥ ትችላላቹ። እስከዛ ከስር የምልክላቹን ሊንክ Start
ያድርጉ 2019 ላይ ብር የሚከፍል ቦት ነው እኔ ቻናሎች ጋ ሸር በማረግ 10,271 ብር አግንቻለሁ ያለ ምንም ድካም ብሮን ይሰብስቡ👇👇👇 ቢያንስ ለካርድ አና 8000 ሰው በናንተ ሊንክ ከተመዘገበ የ iphone x ባለቤት ይሆናሉ ምን ይጠብቃሉ እሂን በመንካት እድሎን ይሞክሩ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/BTC_Hourly_freebot?start=545384143
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
ሼር @fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

02 Feb, 21:31


ደባሎቹ 9
❤️ክፍል 9❤️

<<አቤት ጉድ! እትየ ፀዳለ! አቤት!ምን ትለኝ ይሆን? ለመሆኑ ነግረሀት ነው ወይስ ሰትወጣ አይታት?>> መልስ ከመስጠቴ በፊት በመልሱ ተገረምኩ << ወ/ሮ ፀዳለ ወይስ ህሉ! እ?>> ስል ጠየኩት።
<<ህሉን ተዋት!>>
"ለምን?"
<<እኔ ለሷ አልገባትም እንዳንተ አይነት ሰው ነው የሚገባት ለምን አንተ አትጠብሳትም?>>
ቀልዱን ተናደድኩበትና በሶፋው ትራስ ወርውሬ ፊቱን ጠለዝኩት። ሳቀብኝ። "እኔ ነገ ስለምሞት ነው ካንተ የምሻለው?" አልኩት ያላሰበው መልስ ስለነበረ ፊቱን ባንዴ ቅጭም አርጎ ቁም ነገር ማውራት ጀመረ። ብዙ ነገር ተመካከርን። ምግብ አብሳያችን ለመታረቃችን የደስ ደስ ነው ብላ ቡና አፈላችልን። የዛሬውን ነገር ለማንም እንዳታወራ አስጠነቀቅናት። ግን አፏ እንደማይቋጥር ስለምናውቅ ከስጋት አሁንም ቢሆን ከስጋት አንድንም። ቢሆንም ለሆሜር ስለሴቷ እንደማታውቅ ስነግረው ቀለል አለው። ከቡና በውሀላ የደስ ደስ በሚለው ሆሜርም የመጨረሻኛየ ነው በማለት ኮንትሮል ብፌዉ ላይ የነበረውን ውስኪ አውርዶ ነገ እንተካለን አለና ለሶስታችንም በረዶ አድርጎ ለምግብ አብሳያችንም ጭምር ቀዳላት። እኔ መዳኒት ስለምወስድ ይቅርብኝ አልኩ። እዚ ሆኖ ቢጠጣ ያን አይሆንም ስል ላሰቡት ቆመው አልፈለኩም። ሰዎች በባህሪያቸው ወደተከለከሉት ነገር ይሳባሉና። አዳምስ በገነት ምን ጎደለበት እግዜር ያማረውን ሁሉ ይሞላለት አልነበር ብቸኛ መሆኑን ሲያይስ አልነበረም ሄዋንን የሰራለት አዳም ከራሱ የበለጠ የሚያስብለት አምላክ እያለው አንድ ፍሬ በለስ ተከለከልኩ ብሎ አደል መሬት ወርዶ የሱ ፍዳ ለኔ እዳ ሆኖ ሰው በመላይክት ክንፍ መሔድ ሲያቅተው መኪና ሚባል መጋዣ ፈጥሮ እግሬን ያስገጨኝ ስንቱስ የሚሞተው። ስለዚ ጫን ብሎ በመከልከል አላምንም። ሆሜር ለኔ ከቀዳው ብርጭቆ ላይ ወደራሱ ገለበጠና የብርጭቆው ቂጥ ላይ ትንሽ ስትቀር ይቺን ብቻ ብሎ ሰጠኝ። እኔም ለመሳሰል ተቀበልኩት። ምግብ አብሳያችንም ትንሽ ለወጉ ያህል ተግደርድራ ተቀበለችው። ጨዋታችን ደራ! እኔም ግማሽ ብርጭቆ ያህል ደገምኩኝ። ጠርሙሱ ከግማሽ ወርዶ አሽቆለቆለ። ምግብ አብሳያችን ሙሉ ትባላለች። የፍቅር ታሪኳን ቀበጣጠረችልን አገሯ የምታውቀውን ፍቅረኛን ተማምና ቤተሰቦቿን ትታ እዚ ድረስ ለሱ ብላ መጥታ በችግራቸው ጊዜም እንደምንም አንድ የምግብ ስራ ማሰልጠኛ ውስጥ ፅዳት እየሰራች ለ6 ወራት በነፃ አስተምረዋት ስራ ያልነበረው ፍቅረኛዋን ለሁለት አመት እንደ እናት ስትንከባከበው አንድ አሮጊት ፈረንጅ በላዯ ላይ አግብቶ ፈረንሳይ እንደገባና እስካሁን ወሬውን እንኳን ሰምታ እንደማታውቅ እሷም የወንድ ነገር እያለች እስካሁን ለአምስት አመት ያህል እንደቆየች ወደፊትም ወንድ የሚባል እንደማታስጠጋ ተረከችልን። ባይኗ ሞልቶ የነበረውን እንባ የሆሜር ድንገተኛ ሳቅ ባይነጥቃት ልታዘንበው ነበር። "ምንድነው የሚያስገለፍጥህ?"
አልኩት። <<ባክህ እስካ..ሁን ያወራችው ምንም ስላል..ገባኝ ነው ኪኪኪኪ>> አፈር ብየ ስመለከታት እሷም ልቧ እስኪወለልቅ አብራው ትስቅ ጀመር። በሳቃቸው ተሳቀቅኩ እኔም ብሰክር እንዲ እስቅ ነበር? በማያስቀው ሰለሰቁ መንፈስ መሰሉኝ።እኔም መተኛት ፈለኩና << በቃ እንተኛ ይበቃናል!>> አልኩ።
<<እሺ ወን..ድሜ ግን እ..ንዴ ..ት አንደ..ምወድክ ነግ..ሬህ አቃለው?>> አለኝ ሆሜር አንደበቱ እየተሳሰረ። "አዎ በቃ ሂድና ተኛ!" <<በፍ..ፁም አንተን ትቼ ካ..ሁን በው..ሃላ የትም አሌድም!>> ትንሽ ተከራከርንና<< በቃ እሺ ላስተ..ኛክ>> ብሎ የተኛሁበት ሶፋ ላይ ብርድ ልብሴን አስተካክሎ ቅር እያለው መንገድ ጀመረ። እዚና እዛ ሲረግጥ ምግብ አብሳያችን ሙሉ ልትደግፈው ተነሳች። እሷም ግን ከሱ ብሳ ነበር። መሳቅ አብዝታ ነበር ተደጋግፈው ሲወጡ <<ጥፋት ባታ..በዛ ጥሩ ሰው ነበርክ 'ኮ ወይ..ኔ ወድ..ቄ ነበር ቂቂቂቂቂ>> እያለች ድምጻቸው እየራቀ ሄደ በሩ መለስ እንዳለ ቢሆንም ተመልሳ እስክትመጣ ተነስቼ ለመዝጋት ሳልሞክር ጠበኩ ነገር ግን በቶሎ አልመጣችም። ከጎኔ ከተቀመጠው ውስኪ ቀዳሁ መስከርና ደስተኛ መሆን አማረኝ መጥታ እንዳታስቆመኝ ፈጠን ፈጠን አድርጌ ጠጣሁ። ምን ያህል እንደቆየች ሳስብ እንቅልፍ የት እንዳለሁ እስክረሳ ድረስ ይዞኝ ጭልጥ አለ።......
ይቀጥላል
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

30 Jan, 01:19


ደባሎቹ 8
❤️ ክፍል 8❤️
<<ቲናየ ኧረ በናትሽ ስታካብጂ ሌላ ሰው እየመስልሽኝ ነው>> "

"የሆነነ ነገር ልነግርህ እያሰብኩ ነበር"
<<ደስ ይለኛል የኔ ወሬኛ ምንድነው?>>
ከት ከት ብላ ሳቀች መሰደብ ያስቃል እንዴ? ይቺን ኮስታራ ልጅ የሚያስቃት ስድብ ከሆነማ ደገም ደገም ማድረግ ነው ብየ ለራሴ ፈገግ አልኩ፡፡ እንደዚ እያልን ምንም የረባ ነገር ሳታወራኝ ከአንድ ሰዓት ያላነሰጊዜ በስልክ አወራን። <<እረስቼው ለመሆኑ ቅድም እነግርሃለሁ ብለሽ የረሳሽው ነገር አለ መሰለኝ?>> አልኳት ሀሳብ ስላለቀብኝ መነሻ ወሬያችን ትዝ ብሎኝ።
"እ! አዎ ልነግርህ ብየ እየረሳሁትኮ ነው በናትህ!"
<< እሺ አሁን ሳትረሺው ንገሪኝ አስታወስኩሽ>>

" ካሁን በውሀላ ቲና ብለህ ስትጠራኝ ምንም አልልህም አላኮርፍህም እንዳውም ቲና ብለህ ብቻ እንድትጠራኝ ነው ምፈልገው ይሄው ነው።" ሳቅ አፈነኝ አሁን እንደትልቅ ሰው ስታናግረኝ የነበረቺው ያስደመመችኝ ቲና መልሳ ' መቼስ የልጅ ነገር' አስባለችኝ፡፡
"ምነው ዝም አልክ?"
<< አይ ደስታው ከቁጥጥር ውጪ ስላረገኝ ነው>> ስል አሾፍኩባት።እሷ ግን አመነችኝ መሰል።
"ከምርህን ነው!"

'ኧረ ሳቄ ሆይ ተመለስ' እያልኩ <<አዎ!>> አልኳት። እኔ ስጠራት እንደምታኮርፍም ገና አሁን ማወቄ ነው ሆሜር ነው ባይሆን ሴቶችን በማየት ብቻ የሚያነባቸው። 'ቲና ብለህ አትጥራኝ አለችኝ' ብሎኝ የነበረውም እሱ ነው ለካ መልክቱ ለሁለታችንም ነበረ። እስክነግረው ቸኮልኩ ስልኩን ዘግቼ እግሬን ዘርግቼ በሳቅ ተፍለቀለኩ። ሳቄን አለመስማቷ በጀ!
ሆሜርን ወደኔ ሲመጣ አየሁ። አጠገቤ መጥቶ ቆመ። አንገቱን ደፋ አርጎ በደፈረሱ አይኖቹ ሰረቅ አረጎ ተመለከተኝ።

ስላኮረፍኩ አላናገርኩትም። <<መቼ ነው ግን ሰው የምሆነው?>>ቲቪውን ሲል ጠየቀኝ "ቴሌቪዥኑን ከለልከኝ!" አልኩት በቀጥታ 'ዞር በል ከፊቴ' ላለማለት። ሪሞቱን አነሳና ዘጋው። <<አይኔን ማየት ነው አይደል ያስጠላክ?>> ዝም አልኩት። << እንዴት አያስጠላው? እ! እዚ በረንዳ ላይ ድፍት ብሎ ሲያድር ብርድ እንደ ወባ እያንዘፈዘፈው አንተ ግን እስካሁንም ዞር ብለህ ልታየው አልመጣህም! ደሞ ትንሽ እንኳን አታፍርም?>> እያለች ምግብ አብሳያችን ከጓዳ ወጣች በቀኝ እጇ የያዘችውን ማማሰያ ትማታበት ይመስል ጠበቅ አድርጋ እየያዘች።

<<ምን?!>> ብሎ አንባረቀ። <<እናስ? እስካሁንም እኔ ባልመጣ ደጅ ወድቆ አልነበረ? ለያውም በህይወት መቆየት ከቻለ!>> እንባው እንደመስከረም ዝናብ ጉንጩን እያራሰ ወረደ። አሳዘነኝ! ማስመሰል አይችልበትም ከልቡ ነው። የሚሆነው ነገር አጣ። ምንም መናገር አቃተው ፀፀቱ ግንባሩ ላይ በጉልህ ተፃፈ።

ግን በቃ እንደዚ ነው ቀድሞ አያስብም። <ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ> የሚለው ብሒል ለሱ ግልፅ ሆኖለት አያውቅም። ዝም ብሎኝ ሄደ በሩጋ ሲደርስ "ጥሪው! የትም እንዳይሄድ" አልኳት።
ስትጠራው ባልሰማ መንገዱን ቀጠለ። "ሆሜር!" ብየ ተጣራሁ። በድንገት ፍሬኑ እንደተረገጠ መኪና ጀርባውን እንደሰጠ ቀጥ አለ።


ከዛም ጊዜ ሳያጠፋ እየተንደረደረ ወደኔ መጣና << አቤት ወንድሜ አንተ ነህ የጠራኸኝ? እ! ጠራኸኝ?>> አለ ሽቁጥቁጥ ብሎ። ሁኔታው ፈገግ ቢያስብለኝም ኮስተር ለማለት እየሞከርኩ "የትም እንዳትሔድ?" ስል አስጠነቀኩት። ቁጭ አለ። ከሱጋ ስንፋጠጥ ቴለቪዥኑን አበራሁና አይኔን ወደ ቴሌቪዥኑ መለስኩ። እንዲ እንዲ እያልን ሳናውቀው ወሬ ጀመርን። ከዛ ይቅርታም ሳይለኝ እንደበፊቱ መሳሳቅ ጀመርን። ስለማታው ሳይቀር እያነሳን በሳቅ ተንተከተክን።

ሴትዮዋን የትና እንዴት እንዳገኛት አጫወተኝ። ባሏ ሌላ ሴትጋ በመሔዱ በንዴት ጨርቅ የጣለች ወይዘሮ በድንገት ከቤቷ ወጣ ብድሯን ስትመልስ ማደሯን አወኩ። 'ባሌን ጎዳሁ ብላ..." ነው ነገሩ። በብዙ ነገር ሲያስቀኝ ቆየ። ምግብ አብሳያችን ስትመጣ ጨዋታችን ደርቶ በማየቷ ግርም አላት <<እንዳው እናንተ ሰዎች ግን ትገርማላችሁ ከምኔው ተታረቃችሁ>> ብላ ተመልሳ ወደ ጓዳዋ ገባችና ምግብ ይዛ መጣች። << ለመሆኑ አውቃች እንዴ?>> ሲል ጠየቀኝ። "ምኑን?"


<<ሴት ይዤ መምጣቴን?>> " አዎ!" አልኩት ይደንግጥ ብየ፤ <<አቤት ጉድ! እትየ ፀዳለ አቤት!ምን ትለኝ ይሆን? ለመሆኑ ነግረሀት ነው ወይስ ሰትወጣ አይታት?>> መልስ ከመስጠቴ በፊት በመልሱ ተገረምኩ << ወሮ ፀዳለ ወይስ ህሉ! እ?>> ስል ጠየኩት።
<<ህሉን ተዋት!>>
"ለምን?"............
ይቀጥላል
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

27 Jan, 01:45


ደባሎቹ 7
❤️ ክፍል 7
<<...... ሴቷ የተንጨባረረ ፀጉሯን እያስተካከለች በጥድፊያ ወደ ውጪው በር ስታመራ በመስኮቱ በኩል ተመልክቼ ምግብ አብሳያችን እንዳታያት ስል እየጮህኩ "አመመመኝ ውሀ! ውሀ! አልኳት። አይኗን አፍጥጣ <<ኧረ ከቅዝቃዜ ላይ ተነስተህ?....>>
"ይሁን ፍጠኝ! ፍጠኝ!"ስላት መድፍ የሚያክል መቀጫዋን እያላጋች ወደ ፍሪጁ ተንደረደረች። ስትመለስና ሴቷ በሩን ዘግታ ስትወጣ ለጥቂት ተሸዋወዱ <<ከጊቢው የወጣ ሰው አለ ልበል?>> አለችኝ በመስኮቱ አሻግራ ስታይ በሩ ሲዘጋ እንደ ውልብታ ስለታያት። "ኧረ የምን ሰው? ሆሜርም ጥንብዝ ብሎ ስለገባ እስካሁንም የወደቀበትን አያውቅም እኔም ወጥቼ ስቀር ያላየኝ በጠዋት ሊነሳ ነው!?" ስላት ያየችው ስለመሰላት ነገር ሳይሆን ሆሜር ስላደረገው ነገር መቆጣት ጀመረች ወ/ሮ ፀዳለ ቢሰሙ ምንኛ እንደሚበሳጩ አኩተመተመችና እስኪመለሱ ድረስ እኔን በጤናየ ለማስረከብ እዚሁ እያደረች ልትንከባከበኝ ወሰነች። "ኧረ ግድ የለም ምግብ ካበሰልሽልን ይበቃናል መሄድ ትችያለሽ አትቸገሪ" አልኳት። አሻፈረኝ አለች። ያመጣችልኝን ቀዝቃዛ ውሀ በይሉኝታ ግማሽ ብርጭቆ ያህል እንደጠጣሁ ብርዱ በመላ ሰውነቴ ተሰራጭቶ ወባ እንደያዘው ሰው መንዘፍዘፍ ጀመርኩ። ደነገጠችና ሀኪም ቤት ካልሔድን አለችኝ። ገና ሀኪሙን ሳየው እግሬን ለመቁረጥ መጋዝ የያዘ ይመስል ያስፈራኝ ጀምሯል። በእንቢታ ስለፀናሁባት ቋጥኝ እስክመስል ድረስ ያገኘችውን የሚለበስ ነገር ሁሉ እላየ ላይ ጫነችብኝ። በምግቡም በመጠጡም ብላ ወደ አራት ሰዓት ገደማ ወደትላንቱ ጤንነቴ መለሰችኝ። ሴቶች ብልሀተኞች ናቸው። እንዲያም ሆኖ ሁለት አይነት ልብ አላቸው። አንደኛው ነፍስ የሚያድኑበት ጥበብ ሲሆን ሁለተኛው ነፍስ የሚያጠፋበት ብልሀታቸው ነው።
ስረጋጋ ህሉጋ ደወልኩላት። ከአጠገቧ የሚሰማው የሰርግ ዘፈን ውስጤን አመሳቀለው እንባየ ባይኔ ሞላ ለዚ ወግ እንደማልታደል ተሰማኝ። ድሮ ድሮ ለሰርግ ግድ አልነበረኝም አሁን ግን በፍላጎቴ ሳይሆን በግዴታ አለማግባቴን ሳውቀው አዘንኩ። እንደቀልድ የምንቆጥረውን ነገር ያጣነው ዕለት ምን ያህል ትልቅ ዋጋ እንደነበረው ይገባናል። የምኖርባት እድሜ ትንሽ በመሆኗ ማንንም ሴት አታልየ በማግባት ነገ በመለየት ልጎዳት አልወድም። ብታረግዝስ አባት የሌለው ልጅ እንድታሳድግ የምጨክንባት ሴትም ሆነ ልጅ ሊኖረኝ የሚገባ አይመስለኝም። በየትኛዉም ምክንያት የማያሳድጉትን ልጅ ከመውለድና አብረዉት ለረጅም ዘመናት በደስታ የማይኖሩበትን ትዳር መመስረት በጎነቱም አይታየኝም። በየቀኑ እየሞትኩ የማድር ይመስለኛል። 'እስካሁን ህመሜ የቱጋ ደርሶ ይሆን?' እላለሁ።
<<እንዴት አደሩ ወይዘሪት ህሉ!>> አልኳት "ሄሎ እንዴት አደርክ፤ የሚገርምክ ልደውልልክ ነበር ከጫጫታው ቦታ አሁን መውጣቴ አይቀርም ብየ ነው የቀደምከኝ" አለችኝ
"ወዴት ነው ምትወጪው ደግሞ?" አልኳት በዛውም የት እንደምትሄድ ለማረጋገጥ <<ወይ አንተ ልጅ ትላንት ነግሬህ ዛሬ ረሳኸው ለመሆኑ እንዴት ነህ እየተሻለህ ነው?>> አለችኝ።የሙዚቃው ድምፅ ቀስ እያለ እየቀነሰ መጣ። <<ተሽሎኛል። ከሰርጉ ቤት ወጣሽ እንዴ?>>
"አዎ ልጁ 'ፒያሳ ብለሽ በታክሲ ነይ አዛጋ ቆሜ እየጠበኩሽ ነው' ብሎኝ ወደዛዉ እየሔድኩኝ ነው!"
<<እንዴ ፒያሳ?! የምን ፒያሳ?>> "ኪኪኪኪ 'ባክህ እዚህም ፒያሳ ሚባል ቦታ አለ"
<<እ! ነው እንዴ! እኔኮ ይቺ ልጅ ሀሳቧን ዝም ብላ ነው የምትቀያይረው አዲስአበባ ቀርታ ነው እንዴ? ብየ'ኮ ነው።>>
"ኪኪኪኪ ከምር እኔም ስሰማ ገርሞኝ 'ምንድነው መኮረጅ' ብየ ነበር። ባይሆን አይቼው በንፅፅር እነግርሀለሁ። ባጃጅ ባጃጅ...."
<< ታክሲ አገኝሽ እንዴ? በቃ በኃላ እንደዋወላለን>>
"ሙሉ ዘገባው ማታ ከሀዋሳ ከትንታኔ ጋር ኪኪኪ"
እሺ እሺ ተባብለን ስልኬን ዘጋሁት። ህሉ ግልፅ ነች ምንም ሳታስቀር ማታ እንደምትነግረኝ አልጠራጠርም። ደግሞም ሚስጥረኛዋም ነኝ።
ስልኩን ከዘጋሁት ከጥቂት ደቂቃዎች በዉኀላ ቲና ደወለችልኝ። <<ሄለዉ>> አልኳት ይቺ ልጅ ቁም ነገረኛ እየሆነች ነው ለማለት እየዳዳኝ፡፡
"ሄሎ እንዴት ነህ?" አለችኝ
<<ደና ነኝ ሀዋሳ እንዴት ናት?>> " እስካሁን አላየኃትም ወደ ዉጪ ወጥቼ ዞር ዞር አላልኩም። ተሻለህ?"
<<ኧረ በደንብ ድኛለሁ። ለምን ከህሉጋ አብረሻት አልወጣሽም?>>
"ባክህ እሷን ተዋት ግን ሁላችንም ጥለንህ ስለመጣን ተፀፅቻለሁ ብታይ ህሉ ስትመጣ ቢያንስ እኔ መቅረት ነበረብኝ በጣም ይቅርታ!" አለችኝ <<ቲናየ ኧረ በናትሽ ስታካብጂ ሌላ ሰው እየመስልሽኝ ነው>> "
"የሆነነ ነገር ልነግርህ እያሰብኩ ነበር".

..ይቀጥላል
ቶሎ እንዲደርሳቹ ሼር ማድረግ እንዳትረሱ
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

23 Jan, 12:23


ደባሎቹ6
❤️ክፍል 6❤️

<<...... እናም ብቻውን አልነበረም። አጠገቡ ከሱ የባሰ ጥንብዝ ብላ የሰከረች ዳሌዋ እንደ ዳሽን ተራራ የተቆለለ የለበሰችው ቀሚስ ከእጥረቱ ስስነቱ በእርቃኗ ቆማ ያለች ያስመሠላት፤ ከንፈሯን ወደ ጥቁር ባደላ ቀለም አድምቃ የተቀባች፤ ወገቧ ቀጠን ብሎ ዳሌዋን ቁልቁል እየገረመመ ነፍስ እንዳለው ነገር ለብቻ የሚወዛወዝ መቀመጫዋ ላይ እያላገጠ የሚመስል፤ ቀይ ከወጣትነት ወደ ጎልማሳነት በመተላለፍ ላይ ያለች እንስት አብራው ነበረች። የመተዛዘል ያህል ተደጋግፈው ገርበብ ብሎ የተከፈተውን በር ለመገንጠል እስኪመስል ድረስ በርግደውት ሲገቡ ካንገቴ ብቻ ሳይሆን ከወገቤም ጭምር ቀና ብየ ተመለከትኳቸው። << አ..የ..ህ አይደ...ል! ህ..ሉ ን ረስቻ...ታለሁ!>> አለኝ እጁን በሴቷ ትከሻ ላይ አሳልፎ ጡቶቿን እያሻሸ። ከመደንገጤ የበዛ ቃላቶች ካፌ ነጠፋ። እዚህ ቤት ከገባን እስካሁን በእንደዚ ዓይነት መልኩ ሴት አስገብተን አናውቅም።ምክንያቱም ጊቢውን የቤተሰባችን ጊቢ ያህል በመቁጠር እናከብረው ነበር።እየተንገዳገዱ ከኔ በትንሽ ርቀት ካለው አልጋው ላይ ተሽቀዳድመው ወደቁ። ወዲያውኑ ሆሜር መብራቱን አጠፋው ። ነገር ግን ሴቷ ስካሯ የለቀቃት ያህል ደንብራ መብራቱን አበራችውና <<መብራት ሲጠፋ በጣም ነው የምፈራው ድጋሜ እንዳታጠፋው!>> ብላ አንባረቀችበት። 'ጭለማ ከፈራሽ ታዲያ በዚ ሌሊት እዚ ድረስ ስትመጪ እንደ ሰባ ሰገል ኮኮብ እያበራልሽ ነበር?' ስል በሆዴ አጉተመተምኩ። ልብሱን ማወላለቅ ሲጀምር ቀጣዩን ጉዳይ እንዴት ላስተወው እንደምችል ቸገረኝ። እየተጣደፈች ከንፈሩን ትመጠምጠው ጀመር፤ በቦታው መኖሬን ብቻ ሳይሆን ከነመፈጠሬም ጨርሰው እረሱኝ። ጥያቸው ለመውጣት ሞከርኩ ግን አቃተኝ በዛ ላይ ሌሊት ሌሊት ሀይለኛ የሚጠዝጠዝ ቁርጥማት ያሰቃየኝ ነበር። ያለኝ አማራጭ አይኔን መከልከል ነው ብየ እንደ አንድ አማራጭ ሞከርኩት። ነገር ግን አይኔን ስከለክለው ባሰበት። መላላሱ ሲበቃቸው ሴቷ ገልበጥ አደረገችውና ከላይ ሆና ከራሷ ስሜት ጋር እያጣጣመች ብልቱን ወደብልቷ ለማስገባት ልኳን እየመጠነች ይመስል እየተሳቀቀች ማለማመድ ጀመረችና አፍታ ሳትቆይ ሙሉ ለሙሉ ተቀምጣበት ከባድ የሲቃ ድምፅ እያወጣች እንደሰጋር በቅሎ ትጋልበው ጀመር። በጣም የሚፈታተን ስሜት ተሰማኝ። ድንገት ወደኋላ ገፍተር ሲያደርጋት አንድ ላይ እንደተሰፉ ሁሉ ሳይላቀቁ እሱ ከላይ ሆኖ ሁለቱንም እግሮቿን ትከሻና ትከሻው ላይ ሰቅሎ በፍጥነት እንደ ባንዲራ ሲወለበለብ እሷም ስልቱን እየጠበቀች አፀፋውን ትመልሳለች። እፍረቱም ውጥረቱም ስላላስቻለኝ ብርድ ልብሴን ተሸፋፈንኩኝ። ከመጀመሪያው ይልቅ እየባሰና እየፈጠነ የመጣው የሲቃ ድምፅ የባሰ ረበሸኝ። ገና ይሄ የመጀመሪያ ዙራቸው ነው። እስከመቼ እታገሳለሁ?ለመነሳት ያለኝን አቅም በሙሉ አጠራቅሜ ተነሳሁ። ዱላውን፣ አልጋውን፣ግርግዳውን ሁሉ እየተደገፍኩ በአንድ እግሬ ብርታት እየተረዳሁ የሞት ሞቴን ወደነ ወ/ሮ ፀዳለ ቤት አመራሁ። እንደምንም ከደጃፉ ላይ ደርሼ አንደኛውን ደረጃ ወጣሁና ሁለተኛውን ደረጃ ልወጣ ስጣጣር አደናቅፎኝ ከበረንዳው ላይ ባፍጢሜ ተዘረጋሁ። መነሳት ስላቃተኝ እስኪነጋ ድረሰ ብርድ እያንቀጠቀጠኝ ከዛው ከወደኩበት ወለል ተኝቼ አደርኩ። ሆሜር ከልቡ ክፋት የለበትም ግን ስለሚያደርጋቸው ነገሮች ቀድሞ ምን እንደሚያስከትል ሳያስተውል የመሰለውን አድርጎ የኃላ ኃላ በፀፀት ይሰቃያል። የሱ አይነት ፀባይ ያላቸው በየቤቱ ስንት አሉ ይሆን? ሲነጋ ምግብ አብሳያችን መጥታ "ምነው? ምን ሆነህ ነው? " እያለች እየተርበተበተችና በጥያቄ እያጣደፈችኝ በሴት ጉልበቷ የቻለችውን ሁሉ አድርጋ ወደ ክፍሌ ልትወስደኝ ስትል ሆሜርን በዛ ሁኔታ እንድታየው ስላልፈለኩ 'እዚ ይቀርበናል' ስል እነ ህሉ ቤት ይዛኝ ገባች።
ምግብ አብሳያችን ለምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉታ ብትጠይቀኝም ልነግራት ፍቃደኛ አልሆንኩም። ሴቷ የተንጨባረረ ፀጉሯን እያስተካከለች በጥድፊያ ወደ ውጪው በር ስታመራ በመስኮቱ መስታወት በኩል ተመልክቼ ምግብ አብሳያችን እንዳታያት ስል እየጮህኩ "አመመመኝ ውሀ! ውሀ! አልኳት። አይኗን ........ ይቀጥላል
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

21 Jan, 15:05


ደባሎቹ 5
ክፍል 5
በናታን አዱኛ
<<...... ይህቺ ልጅ ስሜት አላት ማለት ነው ብየ ፈገግ ስል ሆሜር ሹክክ ብሎ በሀዘን የዳመነ ፊቱን ይዞ ገባ። ፊቱ የተጨማደደ የጠላ ጣሳ መስሏል። ስብር ብሎ አይን አይኔን አየኝና <<መቼ ነው?>> አለኝ ቃላቶችን ማውጣቱ ከብዶት።አስከትሎም <<ይቅርታ! ይሄ ሁሉ በኔ ምክንያት ነው!>>አለኝ። ፈገግ ብየ ተመለከትኩት አይኖቹ መድሻ አተው ተቅበዘበዙ። አሳዘነኝ! ምን ያህል ፀፀት እንዳለበት ገብቶኛል ቢሆንም ይሄ ክስተት እንጂ ሴራ አይደለምና ማንንም መውቀስ አይቻልም። ሹፌሩ ፍሬን እምቢ ብሎት እንደነበር ተረጋግጧል፤ መፈተሽ የነበረበት ሲነሳ ቢሆንም ሆን ብሎ እኔን ለመግጨት አስቦ ከቤቱ ወቶ አይደለም መቼስ እሱም እየተንገላታ ያለው። ቸልተኝነት የሚያስከትለው መዘዝ ጥግ ባይኖረውም ሆን ብሎ አልነበረምና ለወደፊቱ ራሱን ካረመ ባይታሰርም ራሱ አጉል ደግ ለመሆን ብየ ሳይሆን የልጆች አባት በመሆኑ ብቻ በእኔ በኩል ፍቃደኛ ነኝ። በርግጥ የቀረችኝን የምርቃት ዘመኔንስ የማይሆን ቂም በመያዝ ማባከንስ ነበረብኝ? ታዲያ ሆሜር ምን አገባው ስላመነጫጨቀኝ እና ስለተከተልኩት ነው? ለይቅርታ የሚያበቃና እሱን የሚያፀፅት ነገር እንደሌለ እኔም መከተሌ ጥፋት አለመሆኑን ነግሬ ላሳምነው ሞከርኩ።
ህሉና ቲና ትንሽ ካዳመጡን በውኀላ ወሬአችን አልገባ ቢላቸው ፍሬ ነገርም ሲያጡበት ቲና ጣልቃ ገባችና "ለማንኛውም ጓደኛህን አንድ በለው ዶክተሩን አልሰማም ሞት ይሻለኛል እያለልህ ነው።" አለችው። <<ምን?>> ብሎ ጮኸ። <<በቃ? ለምን በህይወት መኖርህን እንዲ ጠላህ ስራ መሔድ እንኳን ባትችል እኔ እስክሞት ድረስ አለሁልህ ምንም አይቸግረንም ደሞ አንተ ጠንካራ ነህ ስራህን ከመስራት አያግድህም እባክህ?>> አለኝ ምን ያህል ደረቅ መሆኔን ስለሚያውቅ እየተለማመጠኝ። ወ/ሮ ፀዳለም ገብተው ኖሮ ሁሉም ሊያሳምኑኝ ጣሩ እኔ ግን ለወላጆቼ ይህን ነገር ሳይናገሩ ሚስጥረኞቼ እንዲሆኑልኝ ብቻ በሚያምኑት ሁሉ ለመንኳቸው።
ይህ ካለፈ ከሳምንት በኃላ እየተመላለስኩ እንድታይ ተነግሮኝ ከሀኪም ቤት ወደ መኖሪያ ቤታችን ተወሰድኩኝ። እጠገን ዘንድ አርብና ህሮብ ቀናት ሁሉ ሳይቀር ሾርባና ስጋ ቋሚ ምግቦቼ ሆኑ። እንደ አራስ ተኝቼ መቀለብ ጀመርኩ። እውነትም ምግብ ፍቱን መድሀኒት ነው ቤቴ በገባሁ በሳምንቴ አገግሜ ሰውና ዱላ እየደገፈኝ ትንሽ ትንሽ እራመድ ጀመር። የኔና የሆሜር ጭቅጭቅ ግን እንደ ክፉ ባልና ሚስት መሰለብን። ምክንያታችን አሁንም ጉንጭ አልፋ አስቆርጠው አላስቆርጠውም ነው። ለኔ መኖር ብሎ ቢሆንም ሊስማማልኝ ባለመቻሉ እኔም እነጫነጭበታለሁ። እሱም አዳዲስ ባህሪ አመጣ። አምሽቶና ጠጥቶ መግባት የየለት ተግባሩ ሆነ።
አንድ ቅዳሜ ቀን ጠዋት ይሄን የተሳሳተ መንገዱ ወደ ቀናው መንገድ ለመለስ እንደሚከብደው እየነገርኩት እሱም እንደሚተው ቃል እየገባልኝ እያለ ህሉ ዘው ብላ ገባችና "ዛሬ ሀዋሳ ልንሄድ ነው!" አለችን እየተፍለቀለቀች። ወ/ሮ ፀዳለ ሰርግ እንዳለባቸው ከነገሩን ሁለት ቀን ሞልቷቸዋል። ምግብ አብሳያችን በመጣች ቁጥርም አደራቸውን ጫን አድረገው ነው <<እስከ ሰኞ ነው ሰኞ ወደ ማታ እኛም እዚ ነን ህሉየም ስላለች ታግዝሻለች>> እያሉ አደራ ሲሉ ከአራቴ በላይ ሰምተናቸው ነበር። ህሉ ታዲያ እንዴት ሀሳቧን ቀይራ ለመሔድ ወሰነች? እኔና ሆሜር ተያየን <<ለምንድነው በድንገት ለመሄድ የወሰንሽው?>> ሲል ሆሜር ጠየቃት። "አዎ ባክህ እኔም ትላንት ሌሊት ነው የወሰንኩት እማየና ቲና ብቻቸውን ከሚሔዱ በዛውም በኢንተርኔት የተዋወኩት ልጅ ትላንት ሲያዋራኝ ሀዋሳ በጣም አጓጓችኝ። እሱም እያዞርኩ አሳይሻለሁ ብሎኛል ልጁ ፎቶውን ሲልክልኝ አማላይ ነገር ነው ከሱጋ መዞር ራሱ ደስ ይላል። ደሞኮ አምስት ወር ሙሉ የልባችንን ስናወራ እስካሁን በአካል አልተያየንም።>> አለች ጉጉቷ ከአይኗ ላይ እየተነበበባት። ህሉ እንደዚ ነች ከኛ የተደበቀ ሚስጥርም የላትም። 'አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ይረዳል' ይሉሃል ይሄ ነው! በዝምታ አፍጥጠን ስንመለከታት ቆየንና እኔ መናገር ጀመርኩ ምንም ቢሆን ህይወቴ አደጋ ውስጥ የገባባት የጓደኛየ ፍቅር ነች <<ለምን በኢንተርኔት ካወቅሽው ሰው ጋር ትሽከረከሪያለሽ ከጠሯቸሁ ዘመዶችሽ ውስጥ ለምን አንዳቸውን አስጎብኙኝ አትይም? ....>> የባጥ የቆጡን እያወራሁ ልጁን እንዳታገኘው ላሳምናት ሞከርኩ፤ምክር ብቻም ሳይሆን ቁጣም ጨመርኩበት። "ውይ አንተ ልጅ ሆሜር ወዶ አደለም ከአደጋው በውሀላ ጨቅጫቃ ሆነሀል መሰለኝ እራሴን እጠብቃለሁ ነዝናዛው ወንድሜ!" ብላኝ ጉንጬን ለቀልድ ያህል በጥፊ መታ አድርጋኝ ለጉዞ ዝግጅቷ ወደ ቤቷ ሔደች። ሆሜር አንገቱን እንደደፋ ቆየና ወ/ሮ ፀዳለ ሲወጡ አይቶ ሊሸኛቸው ሔደ።
ሲመለስ ከሌሊቱ ሰባት ሰዐት አልፎ ነበር። እናም ብቻውን አልነበረም። አጠገቡ ከሱ የባሰ ጥንብዝ ብላ የሰከረች ዳሌዋ እንደ ዳሽን ተራራ የተቆለለ የለበሰችው ቀሚስ ከእጥረቱ ስስነቱ.....
ይቀጥላል

ያነበባችሁትና የወደዳችሁት ቶሎ እንዲደርሳችሁም share
@fkreskemekabr

ፍቅር እስከ መቃብር

19 Jan, 11:40


MIT
ሁሉም ሰው ይወዳት የነበረች ልጃገረድ ታሪክ !
ነገር ግን ማን አገባት ??
አብረን እናንብበው ...
አንድ ወጣት ለአባቱ እጅግ በጣም ቆንጆና ልቡ የተረታላት ፡ ልጃገረድ እንዳየና እርሷን ማግባት እንደሚፈለግ ይነግረዋል ።
አባትም በጣም በመደሰትና በመጓጓት የታለች ይህቺን ልጃገረድ አሁን አጭልሃለው ይለውና ተያየዘው ወደ ልጅቷ ዘንድ ያመራሉ ፡ እዛም እንደደረሱ አባትየው ያያትና : ልጄ ሆይ ! ለዚህች ልጃገረድ አንተ አትሆናትም ለርሷ የሚያስፈልጋት እንደ እኔ ጠንካራና ልምድ ያለው ሃላፊነት ሊጣልበት የሚችል ሰው ነው ሊያገባት የሚገባው ይለዋል ! ልጁ በአባቱ ሁኔታ በጣም ግራተጋብቶ የለም አባቴ ይህችን ልጃገረድ እኔ ነኝ ማገባት ያለበኝ ይለዋል ! ሳይግባቡ ይቀሩ እና ህግ እንዲዳኛቸው ወደ ፖሊስ ጣብያ ያመራሉ ! እዛም እንደደረሱ ሁኔታወን ለጣብያው አዛዥ ያስረዱታል ! የጣብያው አዛዥም ልጅቷ እንድት ቀርብና ከሁለት አንዳቸውን እንደትመርጥ በማለት ጣብያ ድረስ እንደትመጣ ያደርጋል ! አዛዡም ልጅቷን ሲያያት በውበቷ እጀግ በጣም ይማረክና ፡ ይህች ልጃገረድማ ለእናንተ አትገባም እርሷ ምትገባው እንደኔ የሃገረን ሃላፊነት ለተረከብ ሰው ነው የምትገባው ! እኔ ነኝ ማገባት ያለበኝ ይላቸውና ሳይግባቡ ስለቀሩ ፡ እንዲዳኛቸው ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር ያመራሉ !! ሚኒስቴሩም ልክ እንዳያት ልቡ ይደነግጥላታና እንደዝች አይነቷን ውብ ልጃገረድማ እንደኔ ሚንስቴር የሆነ ብቻ ነው ሊያገባት የሚገባው ! ሰለዚህ እኔ ነኝ የማገባት ይላቸውና ሳይግባቡ ስለቀሩ ነገሩ ፕሬዝደንቱ ቢሮ ይደርሳል !! ፕሬዝደንቱም ልክ ሲመለከቷት ልባቸው ውስጥ ትገባለች ! እርሳቸውም እኔ ነኝ የማገባት እርሷ ምትገባው ለኔ ብቻ ነው !! ይሉና ሁሉም ሲጨቃጨቁ ፡ ልጅቷ ሃሳብ እንዳላት ትነግራቸዋለች ፦ ሁላቸውም ከርሷ ስር እንዲሮጡና የደረሰባት ሰው እንደሚያገባት ትነግራቸዋለች !! በዚህ ሃሳብ ሁሉም ተስማምተውበት ሩጫ ላይ ሳሉ ! ሁሉም ተራ በተራ እየወደቁ ጉድጓድ ውስጥ ይገባሉ ! ታድያ ከገቡበት ጉድጓድ ላይ ቆማ ማን እንደሆንኩ አወቃችሁኝ ? እኔ ዱንያ ነኝ !! እኔ ነኝ ሁሉም ሰው ከስር ስሬ የሚሮጠውና እኔን ለማግኘት የሚሽቀዳደመው !!ለኔ ሲሉ ከዲናቸው የሚዘናጉት ሞኝነታቸው !! እኔንም ሳያገኙኝ አኺራቸውንም ያጣሉ ትላለች !!
እኛስ😞?

ከወደዱት ለሚወዱት ሼር
https://t.me/joinchat/AAAAAFTWwW99dDx_whZ3xw

ፍቅር እስከ መቃብር

19 Jan, 11:37


Mearg Zekarias:
ሰላም ኣሕዋት አዚ ቻነል እዚ ብዛአባ ቴክኖሎጂ ሓበሬታት ዝህበና ብቪድዮን ጽሑፍን ስእልን መረዳእታታት ዝህበና ቻነል እዩ Admin ናይዚ ቻነል ድማ ወዲ ኣህፈሮም እዩ ስለዚ ኩልና ናብ ናይ ሓውና ቻነል join ገርና ሓበሬታታት ንርከብ ሊንክ
https://t.me/joinchat/AAAAAFTWwW99dDx_whZ3xw

ፍቅር እስከ መቃብር

18 Jan, 13:38


ደባሎቹ 4

❤️ ክፍል 4❤️
<<...... ሆሜር ፊት ላይ የመሸበር
ስሜት ስላየሁ ምክንያቱን እንዲነግረኝ አይን አይኑ አየሁት። እሱም ስጋቴ ስለገባው <<አይ የሚታዘዝልህ መድሀኒት ቢኖር ነው እንድገዛ ይመስለኛል ለማንኛውም መጣሁ>> ብሎኝ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ለመሔድ ካጠገቤ ተነስቶ ወጣ።
ሆሜር በቶሎ አልተመለሰም ነበር። ከሱ ቀድማ ሙቅና የሚበላ አንዳንድ ነገር ይዛ የመጣችው ህሉ ነበረች። "እሺ እንዴት ነህ ተሻለህ?" አለችኝ አጠገቤ ካለችው ኮመዲኖ ላይ ያመጣችወን እቃ እያስቀመጠች። <<እግዚአብሔር ይመስገን እስካሁን አልሞትኩም!>> አልኳት በቀልድ። ፈገግ ብላ ጉንጬን ሳም አድርጋ ወንበሩን ጠጋ አድርጋ ካጠገቤ ተቀመጠችና "ያ ቀውላላ ወዴት ጥሎክ ሄዶ ነው?" አለችኝ። <<ዶክተሩ ጋ ነበር የሔደው ለምን እስካሁን እንደቆየ እኔ እንጃ!>> አልኳት።
ካመጣችው ፔርሙዝ ላይ ሙቅ እየቀዳች እንድጠጣ ስታበረታታኝ ሆሜር በሩን ከፍቶ ገባ። በግድ በሩን ተደግፎ ቆመ። ስክር ጥንብዝ ብሎ ጠጥቷል። ክፍሉ በአልኮል ሸታ ሲናወጥ ደነገጥኩ! ከተዋወቅን ጀምሮ ቁጥብ ሁሉንም ከገደብ የሚያደርግ ልጅ እንደሆነ ነው የማውቀው። እንዲ ለመስከር የሚያበቃ ሰዓት ያህልስ አብሮኝ አልነበረም እንዴ? ከሔደ ከሁለት ወይም ከሶስት ሰአት የበለጠ አይሞላውም። በምን አይነት ፍጥነት እንዴት ቢጠጣ ነው? እያልኩ ብዙ ተመራመርኩ። ዝም ብሎ ሲመለከተን ቆየና አንድ እጁን በግድ አንስቶ የሌባ ጣቱን ወደ ህሉ ቀስሮ << አ. ን.ቺ ጦሰ.ኛ!>> አላት። ህሉ ደንግጣ ልታቀብለኝ የነበረው ሲኒ ከእጇ ላይ አምልጧት ወደቀ። ተነስቼ እየገፋሁ ይዤው ወደቤት ልወስደው ባለ መቻሌ ባይኔ እንባየ ግጥም አለ። እሱ ወሬውን ሲቀጥል ህሉ አይኗንም አፏንም ከፍታ ታዳምጠው ነበር።<< ባን.ቺ ምክን ያት ነው ወንድሜ....>> አለና ከሚንተባተብ አንደበቱ ቃላቶች ነጠፋበትና በሩ ስር ቀዝቃዛው ወለል ላይ ግርግዳውን ተደግፎ በቂጡ ዘጭ ብሎ ተቀመጠና ስቅስቅ እያለ ማልቀስ ጀመረ። ህሉና እኔ ከመፋጠጥ በቀር ምን እንደሆነ አልገባን አለ። ዝም ብሎ ሲያለቅስ ቆየና በጎልዳፋ አንደበቱ <<እኔ ምን ያህ.ል እንደም..ወድህ አታውቅም አደል?>> አለኝ ለመነሳት እየተጣጣረ፤ ግርግዳውን ተደግፎ
ተነስቶ አጠገቤ መጥቶ ቆመና በተሰፋ መቁረጥ ቁልቁል እየተመለከተኝ ስልል ባለ ድምፅ <<ምን..ም ማድረግ አል..ችልም>> ሲል ለራሱ በሚመስል ድምፅ አጉረመረመ። እንዲ ሚናገረው መቼም ከህሉጋ ጠርጥሮኝ አይሆንም ቢሆንማ በዛሬ ቀን ጥንብዝ ብሎ አይመጣም። ከዶክተሩ ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለ ሳስብ የልብ ምቴ ለሌላ ሰው እስከሚሰማ ድረስ ድው ድው ትል ጀመር ። ህሉ በጣም በብሸቀት እየተመለከተችው "በቃ ነገ ና፤ ዛሬ እኔ አድራለሁ" አለችዉ ወደ ውጪ እንዲወጣ እጁን ይዛ እየገፈተረችው።
<<ዞር በይ አትን.ኪኝ አን...ቺ! እኔ ራሴ እሔዳለሁ ጓደ..ኛየ መሮጥ ሳይጀምር ነ. ገ እግሩን መቁ..ረጥ አለብን አሉኝኮ>> አለና ተንሰቅስቆ እያለቀሰና እየተንገዳገደ በሩን አልፎ ወጣና ጥሎን ሔደ። ካንደበቱ እስኪወጣ ድረስ ለመስማት ፈልጌና ልቤ ለማመን ቸግሮት ነው እንጂ ይሄ ሊሆን እንደሚችል ልቦናየ ጠርጥሮ ነበረ። ስሰማው ግን ለምን እንደ አዲስ እንደሆነብኝ አልገባኝም አናቴ ላይ ዱላ የወረደብኝ ይመስል ብዥ ብሎብኝ ደነዘዝኩ። ህሉ ለራሷ ሳትፅናና እኔን ለማፅናናት በመሞከር ተሰቃየች "አይዞህ ፈጣሪ ያውቃል ስለሰከረም ሊሆን ይችላል።" ስትለኝ ይሰማኛል። ከአይኖቼ ቁጥጥር ውጪ የገነፈሉ እንባዎቼን ስታይ አንገቴን አቅፋ የእሷም ትኩስ እንባዎች በማጅራቴ ቁልቁል እየወረዱ ለአንድ እግሬ የስንብት ሙሾ አወረድንለት። እንቅልፍ አልወስድ ስላለኝ እስከሌሊቱ እስር ሰዓት ድረስ ከህሉጋ ስናወራ አድረን ሲነጋጋ እንቅልፍ ወሰደን። ዶክተሩ በተለመደው ሰዓት መጣ። <<እንዴት አደርክ?>> አለኝ የተለመደውን ምርመራና አዲስ ግሉኮስ ቀይሮ መድሀኒት በሲሪንጅ እንደ ቋሚ የደም ስር በተተከለልኝ መርፌ አማካኝነት ወደ ደም ስሬ እየጨመረብኝ። "አንዳንዴ ከሚጠዘጥዘኝ በስተቀር በጣም ደና ነኝ"አልኩት በፈገግታ ተሞልቼ። <<ጎበዝ ወጣት ነህ ፈገግታህ ብሩህ ነው። ከወንድም ጋር ተነጋገራችሁ አይደል?>> ሲል ጠየቀኝ። "አዎ ግን የግድ መቆረጥ አለብኝ?" ስል አስረግጬ ጠየኩት። እኔ ለነገሩ ሌሊት ነበር ውሳኔ ላይ የደረስኩት። የዛሬውም ፈገግታየ በውሳኔየ ከመደሰቴ የመነጨ እንጂ ከጭንቀት የተወለደ ያልሆነው ለዛ ነው። <<በትክክል! አሁን ካልተቆረጠ ይህ አሁን የታየብህ የጋንግሪን ምልክት በቅርቡ ነርቮችህንና ወደ ልብህ ተዛምቶ እድሜህን ሊያሳጥረው ይችላል ከወሰናችሁ ዛሬውኑ መከናወን አለበት።ብዙ ጊዜ ሚሠጥ አይደለም>> አለኝ። "አዎ ወስነናል ዶከተር ስላሰብክልኝና ስለተጨነክልኝ በጣም ነው ማመሰግነው!" አልኩት። <<ጥሩ ቀዶ ጥገናውን ከጥቂት ሰዐት በውሀላ ማከናወን እንችላለን አይዞህ!>> ብሎኝ እንደተለመደው ተጣድፎ ሊወጣ ሲል "ዶክተር ባይቆረጥ ግን ልራመድበት እችል ነበረ አይደል?" ስል ጠየኩት <<ይሄውልህ አሁን ወደኋላ አትመልከት እሱ ዋጋ የለውም እድሜህን የሚያሳጥር አደገኛ ነገር ነው!>> አለኝ። "እኔኮ የወሰንኩት ከነ እግሬ ለመሞት ነው መሞት ከነበረብኝ
አደጋው የደረሰ ቀን እሞት ነበር ስለዚ በዚ በሽታ የምሞት ከሆነ የተቀሩትን ጊዜዎቼን ከእግዜር እንደተመረቁልኝ ቀናት ቆጥሬ በሁለቱም እግሬ ቦርቄ ደስ ብሎኝ እሞታለሁ እንጂ እግሬን ቆሜ አልቀብረውም!" አልኩት ፊቴ ላይ ያለው ኩራት ከልቤ እየፈሰሰልኝ። በዚ ሰዓት ወ/ሮ ፀዳለና ቲና መጥተው ገብተው ነበር። ዶክተሩ ህይወቴን ከማጣ አንድ እግሬን ማጣት ቀላል እንደሆነ ብዙ የአካል ጉዳተኞች እንዴት በቀላሉ ተቀብለውት ለትልቅ ደረጃ እንደደረሱ እየነገረ ሊያሳምነኝ ሞከረ። 'ወይ ፍንክች' አልኩኝ። በድጋሚ እንድንመካከርበት ነግሮን ወደ ቀጣዪ ስራው አመራ ወ/ሮ ፀዳለ እንባቸውን እያዘሩ ተከትለውት በመውጣት ሊየናግሩት ሔዱ። እኔን ደናደርክ ለማለትም ጊዜ አልነበራቸውም። ቲና በተጋደምኩበት ጉንጬን ስትስመኝ ትኩስ እንባ ጉንጬን ሲነካኝ ተሰማኝ። 'እንዴ ቲና አልቅሳ እንዳይሆን ብቻ!' ብየ ቀና ከማለቷ አይኗን አየሁት። "እንዴ ቲና!" አልኩኝ ካንደበቴ አሟልጮኝ። << ከምር ያሳዝናል! ግን መኖርህን ማስቀደም አለብህ።>> አለችኝ። ይህቺ ልጅ ስሜት አላት ማለት ነው ብየ ፈገግ ስል ሆሜር ሹክክ ብሎ በሀዘን የዳመነ ፊቱን ይዞ ገባ.....ይቀጥላል

ከወደዳችሁት ቶሎ እንዲደርሳችሁ Share
@mearg9900
@mearg9900

ፍቅር እስከ መቃብር

12 Jan, 17:38


ደባሎቹ 3
❤️ክፍል3❤️
<<...... እኔና ሆሜር ለብቻችን ተገናኘን <<ቀመሻት አይደል መታመምን?>> አለኝ። "አንተ የታባህ ታመህ ታውቅና ነው?" አልኩት <<እኔም 'ኮ ልቤ ቆስሎ እንዲ ነበር የሚሰማኝ ልዩነቱ አንተ ቁስልህን ሰው ስለሚያየው እግዜር ይማርህ ይልሃል>> አለኝ። "ታዲያ እንዲ ካመረርክ ለምን አልጋ ይዘህ ከጎኔ አትተኛም! የልብ ህመምተኞችም ይታከማሉኮ" አልኩት። <<አሁንም ትቀልዳለህ በነገራችን ላይ የፋሚሊዎችህ ስልክ እምቢ አለን። ያው እንደምታውቀው ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት ክፍለ አገር ኔትወርክ ነጥፏል በሚያስብል ሁኔታ ጠፍቷል።>> አለኝ፡፡"እሰይ እንኳን የጠፋ ቤት ከሠሙ የምተርፍ ስለማይመስላቸው ችግርና ግርግር ከመፍጠር ነው ያዳነኝ ለቴሌ ምስጋና ይግባው!።" አልኩት። <<በዛው ብታርግስ ኑሮ?>> "ያኔማ በቁርጡ ታረዳቸዋለሀ!"፤ ከምሬን ነበር ቤተሰቦቼ ባለመስማታቸው ደሰ ያለኝ። እኔ እንደሁ እናት ወ/ሮ ፀዳለ ወንድም ሆሜር እህት ህሉ አሉልኝ ካስፈለገም በውበቷ ተመፃዳቂዋና ኩራተኛዋ የህሉ ታናሽ እህት ቲናም አሉልኝ። "ቲና መጥታ ነበር?" ስል በድንገት ጠየኩት። ቅንድቦቹን እያርገበገበ ሲስቅ ቆየና << ከሷ አለመምጣት ያንተ መጣች ወይ ጥያቄ ነው ያሳቀኝ >> አለኝ። "ምናባህ ነው ሚያስቅህ ምንም ቢሆን ሰው ናት አታዝንም ብለህ ነው?" አልኩት አለመምጣቷ ቢገርመኝም ለሰው ይህን ያህል ቁብ አለመስጠቷ እየደነቀኝ። <<ባለፈዉ ...>> አለኝና ቀጠለ ሆሜር ፊቱ ላይ የሳቅ ግርታ እየተንጋጋበት << ባለፈዉ ቲና ሰላም ነው! ስላት 'ካሁን በውሀላ ቲና ብለህ እንዳትጠራኝ ህፃን ልጅ አደለሁም! እሺ ስሜ ያኔት ነው' አትለኝ መሰለህ ቂቂቂቂ>> ትን እስኪለው ሳቀና ቀጠለ <<በጣም ስላናደደችኝ ኧረ! እኛ በር ላይ እየመጣሽ ሽንትሽን ስትሸኚና ሌላ ቦታ አትሸኚም ብየ ሳባርርሽ እና ደግሞ ስታለቅሺ በቃ ቸኮሌት እገዛልሻለሁ ብየ ሳባብልሽ የነበረውን ባንዴ ረሳሽው እንዴ? ልላት ነበር።!>> "ኧረ ባክህ ልትላት ነበር!" ብየ ከአወራሩ አጨራረሱ ስላሳቀኝ ከት ብየ ሳኩኝ። እውነቱን ነው ቲና አትለውም አይባልም ትንሽ ቢያጋንነውም ልጅ እያለች ነው የምናውቃት፤ አሁን ስትጎረምስ ምናልባትም እራሷን ለማስከበር ይሆናል ከኛ ጋር ቀርቶ ከቤተሰቦቿም ጭምር ራሷን በማግለል የራሷን ነፃነት የምታውጅ ልጅ ሆናለች። የቤቱ የመጨረሻዋ ልጅ በመሆኗ አፈር አይንካሽ ተብላ ስላደገች ቤተሰቦቿም ለዘላለም እንደህፃን እንደሚቆጥሯት ግን እሙን ነው። አባታቸውን በአካል ከሶስት ጊዜ የበለጠም አይታው ባታውቅም ከካናዳ ሆኖ በሚልክላቸው አልባሳት ስትደምቅ ከቁመናና ከመልኳ ጋር የሚያክላት የለም። እንዳውም አንድ ቀን እኔና ሆሜር ከስራ ወተን የሰፈራችንን ኩብልስቶን ስንያያዘዉ ከፊታችን አስደንጋጭ ዳሌና የሚደንቅ ቁመና አየንና ወደኋላ ከተያዘው ፀጉሯ ተሰፈንጥረን እኔ ልቅደም እኔ ልቅደም እየተጋፋን አልፈን መልኳን ስናየው የኛዋ ሚጢጢ አማላይ ቲቲ ሆና ተገኘችና ትንግርት ሆነብን፤ እስከዛሬም እኔና ሆሜር ስለውበት ስናነሳ መስፈርት የማውጫ መሰረታቻችን ከሷ አድርገንላታል።
ስስቅ እግሬን በጣም ስላመመኝ የለበስኩትን አንሶላ ገለጥ አድርጌ ተመለከትኩት። የሆነ ነገር ሰውነቴን ነዘረኝ። እግሬ በጀሶ ታጥኖ(ታጅሎ) ዝሆኔ የያዘው ሰው መስያለሁ።
"እግሬ !" አልኩት ሆሜርን ወደ ግራ እግሬ እየጠቆምኩትና አይኖቼ ከቁጥጥሬ ውጭ እየፈጠጡ። ሆሜር ከሳቁ ለዛ በቅፅበት ወቶ በሀዘን ድባብ አይኖቹ እንባ አቅረው እሱም እግር እግሬን ያይ ጀመር። ወዲያው ዶክተሩ በነርሶች ታጅቦ ገባና የተወሰነ እርዳታ ካደረገልኝ በውሀላ ግሉኮሱ ውስጥ በሲሪንጅ የሆነ መድሀኒት ጨምሮ <<አንተ ምኑ ነህ?>> ሲል ሆሜርን ጠየቀው <<ወንድሜ ነው>> በማለት ሳልጠየቅ ቀልጠፍ ብየ ተናገርኩ። << ጥሩ አንዴ ወደ ቢሮየ ናና እንነጋገር፤ የምናወራው ጉዳይ አለ!>> ብሎት ዶክተሩ እንዳገባቡ ሁሉ በትንሿ ጋሪ መድሀኒት የህክምና ቁሳቁስ ይዘው እየገፉ በሚያጀቡት ነርሶች ተከቦ ወጣ። ሆሜር ፊት ላይ የመሸበር
ስሜት ስላየሁ ምክንያቱን እንዲነግረኝ አይን አይኑን አየሁት....
ይቀጥላል
ከወደዳችሁት ቶሎ እንዲደርሳችሁ Share
@mearg9900
@mearg9900

ፍቅር እስከ መቃብር

10 Jan, 18:01


❤️❤️❤️ደባሎቹ2❤️❤️❤️
ክፍል 2
<<...... እንዲ እየተጨቃጨቅን በድንገት ህሉ ገባች። እንደሰማች ጠርጥረን ሁለታችንም በድጋጤ ተያየን። ቀበጥባጣነቷ ምንም አልተቀየረም። "እ! እናንተ ሰዎች ዛሬ ማን መከራችሁ ምን ተገኝቶ ነው በጠዋት የለባበሳችሁት" አለች ድንቅ ብሏት። <<እስከዛሬ በጠዋት ተነሱ ስትይን የነበረው ምክርሽ ዛሬ በድንገት ሰራ>> አልኳት በአሽሙር ሆሜርን ለመንካት ፈልጌ የጎሪጥ እያየሁት። እሷም "ኧረ ባክህ እስካሁን የትነበራችሁ?" እያለች ከትከት ብላ ሳቀችብን። ሆሜር አይኑ ቀልቶ ምንም ሳይናገር ጥሎን ወጣ። "ምንድነው በጠዋቱ ተኮራርፋችኃል እንዴ?" አለችኝ ህሉ ባልተለመደ ሁኔታው ግራ ተጋብታ። "ባክሽ ስራ ከመግባታችን በፊት የምንሔድበት ቦታ አለን በሩን ዝጊው ብያት እኔም ተከትየው ወጣሁ። እየተጣደፍኩ ደረስኩበትና "ሆሚ" ከማለቴ <<ምንም እንዳታወራኝ አፍህን ዝጋልኝ!>> አለኝ ብስጭት ብሎ። 'ኦው ይሄ ነገር' አልኩ በልቤ። "ባክህ አንዴ እዘለኝና መስሪያቤት ከዘበኛው በስተቀር ሌላሰው እንዳለና እንደሌለ ላረጋግጥ" አልኩት በየቀኑ ቀውላላ ቁመናውን ስለማሾፍበት። ሰዓቱን አየ። እንኳን እንደወትሮው ሊስቅልኝ የባሰውን ፊቱን ቅጭም አርጎ ተኮሳተረ። ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገመትኩ። "ሆሜር" አልኩት እንዴት እንደሆነ የመፍትሔው ሀሳብ ገና ባይመጣልኝም ከጎኑ በመሆን እንደማግዘው ልነግረው ፈልጌ። "ያንተ ምክር ሰልችቶኛል ተወኝ ደነዝ!" አለኝ። "አግዝሀለሁ በቃ!" አልኩት። አላመነኝም የምሬት ሳቅ ከት ብሎ ሳቀና <<ጎበዝ! አንዳንዴ ቀልድህ ቦታ የለውም።>> ብሎኝ በሌላ አቅጣጫ ካጠገቤ በረጃጅም ቅልጥሞቹ እየተሳበ ፈትለክ ብሎ ጠፋ። ስሙን እየጠራሁ በፍጥነት አስፓልቱን ስሻገር ከየት መጣ ሳይባል አንድ የቤት መኪና አስፓልቱ ላይ ዘረረኝ። ለሁለት ቀናት ሆስፒታል ተኛሁ። ስነቃ ወ/ሮ ፀዳለ ከአልጋየ ጎን ተቀምጠው፤ አይናቸው ከማልቀስ ብዛት ኳስ አክሎና በርበሬ መስለው ፀጉሬን ሲያሻሹ ተመለከትኳቸው። አይኔን መልሼ ጨፈንኩና ምን እንደተከሰተ ሳስታውስ ሁሉም ነገር ወለል ብሎ እንደፊልም ተከሰተልኝ። አሳዘኑኝ! ልጃቸውን አስታውሻቸው እንደሆነ ሳስብ አንጀቴ ተላወሰና እንባየ ወደ ጆሮዎቼ ተንቆረቆረ። ፈገግ ብለው ከአይናቸው እንባ እያፈሰሱ <<አይዞህ ተርፈሀል ልጄ ጠንካራ ነህ! ጎሽ!>> አሉኝ ፀጉሬን ማሻሸቱን ትተው እንባየን በፎጣ ከአይኔ ላይ እያደራረቁልኝ። "ሆሜር የታለ?" አልኳቸው እሱ የት ሔዶ እሳቸው ከዚ እንዳሉ ለማወቅ ጓጉቼ። ወዲያው ግን ከህሉ ጋር በሩን ከፍተው ሲገቡ ታዩኝ "ነቃህ እንዴ!?" አለችና ህሉ እየተፈለቀለቀች ጉንጬን ሳመችኝ። ሆሜር በፈገግታ ተውጦ ካይኖቹ እንባ እያረገፈ << እንዴት ነው ያማል አደል?>> አለኝ ሁላችንም ፈገግ አልን፤ "ቆይ ልነሳ አለቅህም!" አልኩት። "እማየ በቃ ወደቤት መሔድ አለብሽ ሁለት ቀን ሙሉ እንቅልፍ አልተኛሽመኮ!" አለች ህሉ ወ/ሮ ፀዳለን በሀዘን እያየች። ደነገጥኩ። "እንዴ ለምን?" ስል ሆሜር ላይ አፈጠጥኩ። <<እምቢ አሉ!>> 'ታውቅ የለ' በሚል አይነት ጠቀሰኝ። ለነገሩ ይህን በማድረጋቸው የህሊና ሰላም ይሰማቸው ይሆናል ብየ ምላሴን ሰበሰብኩ። ከዛም በስንት ውትወታ አሳምነናቸው ህሉ ወደ ቤት ይዛቸው ሔደች። እኔና ሆሜር ለብቻችን ተገናኘን....ይቀጥላል

ከወደዳችሁት ቶሎ እንዲደርሳችሁ
Share
@mearg9900