Abune Gorgorios

@abugs


Abune Gorgorios

04 Aug, 18:19


የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን አስመረቁ፡፡
************* ************** ************
አስር ቅድመ አንደኛ ደረጃ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2016 ዓ.ም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ያጠናቀቁ ቁጥራቸው 2049 የሆኑ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ፣ በባህዳር፣ በድሬደዋ እና ወልዲያ በሚገኙ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች በተካሄደው የምርቃት መርሀግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደ የምረቃ ፕሮግራም ሲሆን በምረቃ መርሀግብሩም ተማሪዎች ለምረቃ መርሀግብሩ ያዘጋጁበትን ዝማሬዎች፣ በገና ድርደራ፣ በተለያዩ በኢትጵያ ቋንቋዎች የእንኳን ደህና መጣቹ መልክት፣ ልዩ ልዩ መነባንብ፣ ድራማ፣ ቅኔ፣ ግጥም፣ እንቆቅልሽ እና ወረብ ካቀረቧቸው ዝግጅቶች ይገኙበታል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios

03 Aug, 05:19


ለዚህ ወጤት መመዝገብ እንደዋነኛ ምክንያት የሆነው በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በ 2016 ትምህርት ዘመን የነበረው የትምህርት ማህበረሰቡ አስተዋጽፆ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌላው የተሰራው ከፍተኛ የስነልቦና እና ሁለንተናዊ ዝግጅት ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
 በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና
 የአክሲዮን ማኅበራችንንድረ ገፅhttps://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios

03 Aug, 05:19


የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ8ኛ እና በ6ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት አስመዘገቡ፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ካስፈተናቸው የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ውስጥ 99.46% እና 8ኛ ክፍል ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ 98.70% የሚሆኑት ከፍተኛ ውጤት ማስመዘገባቸው ተገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ክልል አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ 7 ቅርንጫፍ የሚገኙት የአዋሬ፣ የሲኤምሲ፣ የእግዚአብሄር አብ፣ የቃሊቲ፣ የለቡ፣ የሰንሻይን እና የወይራ ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከተፈተኑት 932 ተማሪዎች 927 ተማሪዎች (99.46%) ተማሪዎች ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት ማለፋቸው የታወቀ ሲሆን በ8ኛ ክፍል በ7ቱም ቅርንጫፍ ከተፈተኑ 785 ተማሪዎች ውስጥ 775 ተማሪዎች (98.70%) የሚሆኑት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸው ታውቋል፡፡

Abune Gorgorios

01 Aug, 08:18


የለቡ ቅርንጫፍ ተማሪዎቹ ተማሪ ትንሳኤ፣ ተማሪ ሶስና እና ተማሪ ረድኤት ከዚህ በፊት በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አውደርኢይና የፈጠራ ስራዎች በሚቀርቡበት ውድድሮች የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን በርካታ ሽልማት ያገኙ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ተማሪዎቹ በዓለም አቀፍ ውድድር ከመሳተፋቸውም በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሚዘጋጁ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ እና በከተማ ደረጃ የሚካሄዱ ውድድሮች ላይ የፈጠራ የስዕል ስራዎችን በማቅረብ አሸናፊ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios

01 Aug, 08:18


የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በዓለም አቀፍ መድረክ አሸነፉ፡፡
************* ************** ************
የየአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሩሲያው አርቲስት በተሰየመው አንቶን ቼክሆቭ ስራዎችን በሚዘክረው 12ኛው ዓለም አቀፍ የልጆች የስዕል ውድድር ላይ (International Children’s Art Contest “Anton Chekhov and Characters of His Works.” ስራዎቻቸውን በማቅረብ አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡
በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው በዚሁ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በውድድሩ ስራዎቻቸውን በማቅረብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሸነፋቸው የተገለፀ ሲሆን፣ በዚሁ ውድድር ከ14-17 ዓመት የእድሜ ክልል ውድድር የስዕል የፈጠራ ስራውን ያቀረበው የ14 ዓመቱ ተማሪ ትንሳኤ ዳባ የቤላሩስና የቻይና ተወዳዳሪዎችን በመብለጥ ሀገሩን ኢትዮጵያን በ1ኛ ደረጃ በማስጠራት ውድድሩን አሸናፊ ሆኗል፡፡
በዚሁ ውድድርም ከ11-13 ዓመት የእድሜ እርከን ያሉ ከቻይና፣ ቱርክና፣ ኦስትሪያና ቤላሩስ ተወዳዳሪዎች ጋር የቅረቡት ተማሪ ሶስና ባንታምላክ በውድድሩ በ2ኛነት እና ተማሪ ረድኤት ቴዎድሮስ 3ኛ በመሆን አሸናፊ ሆነዋል፡፡

5,500

subscribers

198

photos

43

videos