TEKVAH-ETHO @tikvahethiopia1p Channel on Telegram

TEKVAH-ETHO

@tikvahethiopia1p


Addis Ababa, Ethiopia
➠ ፈጣን እና ታማኝ መረጃ፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃ
🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO (Amharic)

በቅርብ ላይ ለውጥ የተመሠረተው TEKVAH-ETHO ትክክለኛ ቤተሰብ ላይ ይዘት አለው። ይህ ማህበረሰብ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ያለው፣ ወደ ስኬቶች እና ሰላም አቅማቸው ። TEKVAH-ETHO የዜናዉና መረጃው ዘርፉዋል፣ ሙሉ መረጃዉን ከሚያሰራጭ ሚሊዮን እስከ ዚህ ዐመት ዳግም ፊት መሰለፍ የሚችል ። መረጃው በየአርበኞችና የትግራይ እና አማራ ስኬት የተገኘ ። TEKVAH-ETHO የዜና ምርጫዉን ብቻ ማንኛውም ሰው በእንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚሰፋ አለው ። አገልግሎትም ላይ በማሠራጨት TEKVAH-ETHO ከጠበቁት ሰዎች ጋር ፈጣንና ታማኝ መረጃዋን ለማንበብ ዝርዝር እንችላለን።

TEKVAH-ETHO

03 Mar, 00:14


#Update : ኮልፌ አጣና ተራ ታይዋን ገበያ አከባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም በቁጥጥር ስር መዋሉን በአከባቢው ያሉ የቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀውናል።

📹 Fasil/ #TikvahFamily

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

18 Oct, 04:02


"...ችግሩ የቦረና ወንድም ህዝብ ህመም ነውና እኛም ታመናል" - አቶ ዳዊት ገበየሁ

የኮንሶ ዞን አስተዳደር በበልግ ዝናብ መጥፋት ምክንያት የእንስሳት መኖና ውሃ መጥፋት ለተጎዳው የቦረና ህዝብ ድጋፍ አደረገ።

ዞኑ ዛሬ 18 የጭነት መኪና የእንሰሳት መኖና 2 ቦቲ ውሃ በድርቅ ለተጎዱ እንሰሳት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እና አማካሪዎቻቸው እንዲሁም የዞን ካቢኔ፣ ከተማና ወረዳ መዋቅር አስተዳዳሪዎች ያቤሎ ድረስ ይዘው ሄደው አስረክበዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ድጋፉን አስመልክተው በሰጡት ቃል፥ " ችግሩ የቦረና ወንድም ህዝብ ህመም ነውና እኛም ታመናል፤ የጎረበ ወገን ችግር ነውና አስከፊነቱ አሳዝኖናል፤ የእንሰሳት ሞት የቤተሰብ ጉዳት ነውና አብረን ተጎድተናል" ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው፥ የኮንሶ ዞን ለወንድም ህዝቦቹ ችግር ለመድረስ የተደረገው ይህ ድጋፍ የመጀመሪያ እንደሆነ ተናግረዋል።

አክለው፤ "የተከሰተው ጉዳት ሠላምና እንቅልፍ የሚነሳ፣ ኢኮኖሚን የሚያቃውስ፣ አንገት የሚያስደፋና ለችግር የሚዳርግ አሳዛኝ ክስተት መሆኑን የኮንሶ ወንድም ህዝብ ልባዊ መልዕክቱን ይገልፃል" ብለዋል።

"ኦሮሞና ኮንሶ አንድ ህዝቦች ናቸው" ያሉት አቶ ዳዊት፥ "የቦረና ህዝብ ችግር የኮንሶ ህዝብ ችግር ነው፤ ስለሆነም አስደንጋጭ የእንሰሳትን ሞት ከሰማን ቀን ጀምሮ እኛም በአካል ራቅናችሁ እንጂ የህሊና ተጎጂዎች ነበርን" ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ዳዊት፥ " በዝናብ መጥፋት ምክንያት የተከሰተው የእንሰሳት ሞትና ድካም ችግር እጅግ አሳዛኝ ቢሆንም ከመከራ የምንማርበት፣ የጉዳቱ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦቻችን ስነ ልቦናቸውን የሚንገነባበት ወቅት እንዲሆን ብርታትን ከልብ እንመኛለን" ብለዋል።

መረጃው የኮንሶ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።
@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

16 Oct, 19:49


#ItsMyDam🇪🇹

በታላቁ የኢትዮጵያ🇪🇹ህዳሴ ግድብ ጉዳይ የጅማ፣ አዲስ አበባ፣ እና ባህር ዳር ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች በውጭ ካሉ ተመረርማሪዎች ጋር የሚመክሩበት ሲምፖዚም ይካሄዳል።

ሲምፖዚየሙን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ውሃ ጉዳዮች መማክርት ነው።

ይህን ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ለማካሄድ መነሻ ሃሳቡን በተመለከተ ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት ፕ/ር አቻምየለህ ደበላ እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል ፦

" ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው አንድ ተለቅ ያለ ይዘት ያለው ጉባኤ ብንፈጥር በዛ ጉባኤ አማካኝነት በተለይ ኢትዮጵያውያኖችን እና የውጭ ሰዎችን ጋብዘን የኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች ድምፅ የሚሰማበትና በተለይ እውነታው ከምን ጋር እንደሆነ እንዲያውቁ ይረጋል በሚለው የተነሳነው። "

በሲምፖዚየሙ ላይ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ የኢትዮጵያን ትርክት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስረዳት በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ህጋዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ ታልሟል።

ይህን ሲምፖዚየም በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች እና የህዳሴድ ግድብ ዋና ተደራዳሪ እና አማካሪ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ነው ይከፍቱታል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ሲምፖዚየሙ የአባይን ጉዳይ ከብዙ አቅጣጫ ለማየት የሚሞክር መሆኑን ደግሞ ከአስተባባሪዎች መካከል አንዷ የሆኑት መቅደላዊት መሳይ ተናግረዋል።

አስተባባሪዋ ሲምፖዚየሙ ኢትዮጵያውያን ስለህዳሴ ግድቡ በሚገባ አውቀው ለሀገራቸው ትልም እንዲሞግቱ ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል።

ሲምፖዚየሙ ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ እንዲሁም በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ (ለ4 ቀናት) በኦንላይን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደሚካሄድ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ዶቼ ቨለ) ከአስተባባሪዎች መስማቱን ዘግቧል።

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

16 Oct, 19:49


#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 28 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 28 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,591 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 394 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 613 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

15 Oct, 08:49


#Kombolcha : በኮምቦልቻ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

ኮምቦልቻ ከተማ አስተደደር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ፥ ለከተማው ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት እና በህወሓት ቡድን ከቤት ቀያቸው ተፈናቅለው በከተማው ለሚገኙ ወገኖች አጠቃላይ ደህንነት ሲባል እንቅስቃሴዎች በሰዓት እንዲገደቡ መወሰኑን አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ከፀጥታ አስከባሪዎች ውጭ የትኛውም ዓይነት የግለሰቦች እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

2ኛ. ለወቅታዊ ሰራ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ተቋማትና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጭ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እንቅስቃሴአቸው እንዲገደብ ተወስኗል።

3ኛ. የፋብሪካ ሰርቪስ በመስጠት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች ከሚያገለግሉበት ተቋም የመውጫ እና የመግቢያ ስዓት በተቋሙ ህጋዊ ደብዳቤ ለሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

መላው የኮምቦልቻ ነዋሪዎች ለሁሉን አቀፍ ትብብር እራሳቸውን ዝግጁ እንዲያዲያደርጉ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

15 Oct, 08:49


አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መሞቱ ተገለፀ።

የናይጄሪያ ጦር ፤ የምዕራብ አፍሪካ የISIL ከፍተኛ መሪ መሞቱን አስታወቀ።

የናይጄሪያ ጦር ኃይል ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ላኪ ኢራቦር ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ፥ " አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መሞቱን አረጋግጥላችኃለሁ ፤ ሞቷል እንደ ሞተም ይቀራል" ብለዋል።

ጄኔራሉ ፤ አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መቼ እና እንዴት እንደሞተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የምዕራብ አፍሪካ የISIL ከፍተኛ መሪ የሆነው አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ በ2009 የተገደለው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም የታጠቀ ቡድን መስራች መሀመድ የሱፍ ልጅ ነው።

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

13 Aug, 11:37


"በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበት ሁኔታ አመቻቻለሁ።" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

ተመራቂ እና ያልተጠናቀቀ የትምህርት ተግባር ያላቸው ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበትንና የሚመረቁበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፦
- ከዓዲግራት 2,355
- ከአክሱም 2,992
- ከመቐለ 3,668
- ከራያ 1,149 በድምሩ 10 ሺህ 164 ተማሪዎችን ማስወጣቱን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ተማሪዎቹ እስከ ነሐሴ 06/2013 ዓ.ም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በኩል ወደ አዲስ አበባ ተጓጉዘዋል፡፡

የክረምት ተከታታይ ትምህርት ያላቸው እና በፀጥታ ችግር ወደቦታው መሄድ ያልቻሉ በቀጣይ በሚቀመጥ አቅጣጫ መሰረት ትምህርት የመከታተል እድል ይመቻቻላቸዋል ብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በኩል መከታተል ትችላላችሁ : t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity

TEKVAH-ETHO

13 Aug, 01:34


የተፈናቃዮች ቁጥር 300 ሺህ ደርሷል።

በአማራ እና አፋር ክልሎች የተፈናቀሉ ሰዎች 300 ሺህ መድረሱ ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው ዛሬ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት የውጭ ቋንቋዎች እና የዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ የሆኑት ቢልለኔ ስዩም በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

ቢልለኔ ስዩም ህውሃት የተናጠል ተኩስ አቁም ስምምነቱን ባለመቀበል በአፋር እና በአማራ ክልሎች ላይ ጥቃት በመፈፀም 300 ሺህ ዜጎችን እንዲፈናቀሉ እና የተለያዩ ሰብዓዊ ጥሰቶች ፈጽሟል ብለዋል።

እነዚህ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ቢያስፈልጋቸውም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት አልሰጣቸውም ሲሉም ገልፀዋል።

ችግሩም ለመፍታት መንግስት ከአለም ምግብ ድርጅት (WFP) ጋር በመሆን ምግብና ምግብ ነክ የሰብዓዊ እርዳታዎችን እያቀረበ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ቢልለኔ ወደትግራይ ከሚገባው እርዳታ ጋር በተያያዘ እስከ ትላንት ድረስ 277 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ወደ ወደ መግባታቸውን አሳውቀዋል።

በሌላ መረጃ ደግሞ ከቀናት በፊት በጠ/ሚ ጽ/ቤት ይፋ የተደረገው ብሔራዊ ጥሪ ከትግራይ ህዝብ ጋር የተገናኘ ሳይሆን በመንግስት በሽብር የተፈረጀውን ቡድን አውዳሚ እንቅስቃሴ ለማስቆም ነው ብለውታል።

በትግራይ ክልል ውስጥ "የትግራይ ኃይል" በሚል በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚዘገበው ከፋፋይ መረጃ ትክክል አይደለም ያሉት ቢልለኔ ስዩም፥ "አሁን ላይ መንግስት እየተፋለመ ያለው በትግራይ ክልል እና አጎራባች አካባቢዎች ከሚንቀሳቀሰው ህወኃት ከተባለ የሽብር ቡድን ጋር ነው" ሲሉ አስገንዝበዋል።

"አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና መንግስትም እየተዋጋ ያለው ከትግራይ ህዝብ ጋር ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ውስጥ ተደብቆ ከሚንቀሳቀሰው የሽብር ቡድን (ህወሓት) ጋር ነው" ሲሉ ቢልለኔ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopia

TEKVAH-ETHO

13 Aug, 01:34


"...ህወሓት እና ሸኔ አብሮ ለመስራት መስማማታቸው አዲስ ነገር አይደለም " - ቢልለኔ ስዩም

መንግስት " ሸኔ " እያለ የሚጠራው እና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) የሚለው በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው ቡድን ከሌላኛው ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ከተፈረጀው ቡድን ህወሓት / TPLF ጋር አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ትላንት መግለፁ አይዘነጋም።

በዛሬው ዕለትም ህወሓት በይፋዊ መግለጫ ከOLA ጋር ለመስራት መስማማቱን አሳውቋል።

ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢልለኔ ስዩም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዛሬው መግለጫቸው ላይ ትላንት ከተሰማው የስምምነት ዜና ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ቢልለኔ ፥ "ህወሓትና ሸኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በጋራ ሲሰሩ የቆዩ የሽብር ቡድኖች ናቸው፤ ጋብቻቸው አዲስ ጉዳይ አይደለም" ብለውታል።

ህወሃት በተለይ በኦሮሚያ አካባቢ ሸኔን በመጠቀም የሽብር ስራውን ሲያከናወን መቆየቱን አስታውሰዋል። መንግስት ሁለቱ ቡድኖች ሀገር ለማፍረስ በጋራ እየሰሩ መሆኑን በተጨባጭ መረጃ በመገንዘብ በአሸባሪነት ፈርጇቸዋል ብለዋል።

ከዚህ ህወሓት እና ሸኔ ቡድኖች "ጋብቻ" መፈጸማቸውን ማወጃቸው አዲስ ጉዳይ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኖቹ ሀገር ለማፍረስ በጋራ እንደሚሰሩ በግልጽ ያረጋገጡበት ሆኗል ብለዋል።

መንግስት 2ቱን የሽብር ቡድኖች በሚለከት ያለውን ምልከታ ትክክለኝነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያረጋገጠ ክስተት መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ቢልለኔ ስዩም ሁለቱ ቡድኖቹ ቆምኩለት የሚሉትን ህዝብ በመግደልና በማሰቃየት ይታወቃሉ ሲሉ አስታውሰው የፈጠሩት ጋብቻ የትግራይ እና የኦሮሞ ህዝቦችን አይወክልም ሲሉ አስገንዝበዋል።

ፎቶ ፦ ኢብኮ

@tikvahethiopia

TEKVAH-ETHO

12 Aug, 09:54


#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ በኢትዮጵያ " ዴልታ " የተሰኘውን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መመርመር አለመጀመሩን አሳውቀዋል።

ምርመራው እስካሁን ያልተጀመረው ዝርያውን ለመመርመር የሚያስፈልገው ኬሚካል ወይም " ሪኤጀንት " እስካሁን አገር ውስጥ ባለመኖሩ ነው ብለዋል።

መስሪያ ቤታቸው ኬሚካሉን ከውጭ አገር ለማስገባት በሂደት ላይ በመሆኑን የገለፁት ዶ/ር ሊያ ፥ በቅርቡ ምርመራው ይጀመራል ብለዋል።

በሌላ በኩል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር በአዲስ አበባ 59 በመቶ ከአዲስ አበባ ውጪ 20 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ሊያ ፥ ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ ዜጎች፣ በቫይረሱ የሚያዙ እና ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ፦
• ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ ዜጎች በ2.5 በመቶ ጨምሯል።
• በቫይረሱ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር ከ2.8 በመቶ ወደ 7.4 በመቶ ከፍ ብሏል።
• ህይወታቸው የሚያልፍ ዜጎች ቁጥር ከ13 በመቶ ወደ 36 በመቶ አሻቅቧል።

የመረጃ ባለቤት ፡ አል አይን

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

12 Aug, 03:24


በኮምቦልቻ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ።

ለኮምቦልቻ ከተማ ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት እና የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል በከፈተው ጥቃት ከቤት ቀያቸው ተፈናቅለው በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች አጠቃላይ ደህንነት ሲባል በከተማይቱ እንቅስቃሴዎች በሰዓት እንዲገደቡ መወሰኑን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. ሁሉም የከተማው ነዋሪዎች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው።

2ኛ. ለወቅታዊ ሰራ ከተፈቀደላቸው ፀጥታ ተቋማት እንዲሁም የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጭ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ እንቅስቃሴአቸው እንዲገደብ ተወስኗል።

3ኛ. የሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

ይህ ውሳኔ ከዛሬ ነሀሴ 05 /2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል።

@tikvahethiopia1p

TEKVAH-ETHO

12 Jul, 03:21


#Euro2020

የጣልያን ብሄራዊ ቡድን የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድንን #በፍፁም_ቅጣት ምት በማሸነፍ የEuro 2020 ሻምፒዮን ሆኗል።

በEuro 2020 የፍፃሜ ጨዋታ 2ቱ ብሄራዊ ቡድኖች ባደረጉት ፍልሚያ በመደበኛው እና በጭማሪው ሰዓት መሸናነፍ ባለመቻላቸው (1 ለ 1) ጨዋታው ወደፍፁም ቅጣት ምት አምርቷል።

ጣልያን እንግሊዝን በፍፁም ቅጣት ምት ድል አድርጋታለች።

በእንግሊዝ በኩል ሳንቾ፣ ራሽፎርድ እንዲሁም ሳካ የፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር አልቻሉም።

TEKVAH-ETHO

12 Jul, 02:50


#AWLO #EthioForum

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰኔ 23፣ 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር የሚገኙትን፦
- በቃሉ አላምረው፣
- ያየሰው ሽመልስ፣
- ፋኑኤል ክንፉ፣
- አበበ ባዩ፣
- መልካም ፍሬ ይማም፣
- ፍቅርተ የኑስ፣
- ዊንታና በርሄ እና ምህረት ገብረክርስቶስን ጨምሮ 21 የኢትዮፎረም እና የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞችና ሰራተኞች አያያዝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በቅርበት ሲከታተል መቆየቱን ገልጿል።

ከእነዚህ ታሳሪዎች መካከል ሦስቱን እና አንድ ሌላ ታሳሪን ጨምሮ አራት እስረኞች ማክሰኞ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ መለቀቃቸውን ኢሰመኮ ገልጿል።

ቀሪዎቹ ታሳሪዎች በወንጀል ስለተጠረጠሩ ለምርመራ ስራ በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ትዕዛዝ መሰጠቱን ፖሊስ እንደገለፀለት ኢሰመኮ አድረድቷል።

ነገር ግን ኮሚሽኑ እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2013 ዓ/ም ምሽት ድረስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አለማየቱና ታሳሪዎቹን ለመጎብኘት አለመቻሉ፤ እንዲሁም ታሳሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከጠበቆቻቸው ሳይገናኙ ከአንድ ሳምንት በላይ መቆየታቸው እጅግ የሚያሳስበው ጉዳይ እንደሆነ ገልጿል።

በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮ-ፎረም እና የአውሎ ጋዜጠኞችና ሰራተኞች አያያዝ ሕግን የተከተለ ሊሆን ይገባል ያለው ኢሰመኮ የፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ ካልቀረበ በአፋጣኝ ሊለቀቁ እንደሚገባ አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia