ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል @fikee21 Channel on Telegram

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

@fikee21


........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል (Amharic)

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል አፈፃፀም በማህበር እና በምርምር ማህበረሰብ የሚሰራበት ማኅበረሰብ የነበረ ነው። 'ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል' በጥልቅ የሚሆነው ቡድን ከፍተኛ መረጃ እንዲሆን ለመከታተል ከእርስዎ ጋር በመጣጠም ነው። በዚህ ቪዲዮ ቤተሰብ እና ዜና ምንድን ነው ይመልከቱ፣ ምን ይሻላል፣ እና ምን ማግኘት ያለበት ምርጥ ጊዜዎች እንደምንመለከተው እየታሻሻ በማስቀመጥ የተጠቃሚ ነው። 'ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል' ከህይወት ገፅ ጋር ከፍተኛ ተለዋዋጮችን በጥልቅ ውስጥ እንጀምራለን። እናም ተጨማሪ ነገሮችን እንመለከታለን። የተለያዩ ዜናዎችን ለማነጋገር ወደ ቤተሰብ ላይ ይመልከቱ።

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

24 Jan, 18:34


t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

22 Jan, 04:29


አወይ እድል እድል አይባልም ከቶ
ስው የዘራውን ነው ሚበላው ፈትፍቶ ።

ዘ-በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

19 Jan, 07:30


እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ።

መልካም በዓል ።

t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

16 Jan, 19:16


Ok

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

13 Jan, 06:55


#ዋጋህን_ስታውቅ_ጩኸት_አያስፈልግህም!

ታዋቂዎቹ ብራንዶች ሮልስ ሮይስ እና ቤንትሌይ የንግድ ማስታወቂያ አይሰሩም።

ምክንያቱም፦

ምርታቸው ገዥዎችን እንደሚያመጣላቸው እርግጠኞች ናቸው።

ዋጋህን ስታውቅ ሰዎች፦
👉 እንዲወዱህ
👉 ወዳጅህ እንዲሆኑ
👉 አብረውህ እንዲሆኑ

ምናምን አትለምንም!!

በማንነትህ ተማመን።
ሁሉም ሰውም ወዳጅነትህ አይገባውም!

t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

04 Jan, 05:32


Channel photo updated

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

04 Jan, 05:32


Channel photo removed

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

28 Dec, 18:26


አትሸወዱ

ስዎች በእናንተ ደረጃ መምጣት
ካልፈለጉ እዛው በደረጃቸው
ይቀመጡ ተዎቸው ።
ምን ግዜም እራሳችሁን ተከላከሉ
ሁሉም የሚሳካው እናንተ ጤነኛ
ስትሆኑ ነው ።
የአእምሮ ሰላማችሁን በደንብ
ተቆጣጠሩት አእምሮ የስው ልጅ
ትልቁ ስጦታ ነው ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fkee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

24 Dec, 17:02


አንቺ እንከን የለሽ የጥቅምት አበባ
እንደ ንብ ልቀስምሽ...... ?
ከልብሽ ቤት ልግባ
ክፈቺልኝ በሩን የፍቅርን አዳራሽ
አብሪ እንደ ፀሃይ ሌሊቱ እንዳይመሽ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

24 Dec, 16:34


አንተ ጎበዝ ልቤ
ምንድን ነው መልፈስፈስ ?
ጠንክር እንደ ብረት ፣
ሲቀጠቅጡት ነው.....
መጥረቢያ በእራሱ የሚሆነው ስለት ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

22 Dec, 19:03


እራስን ከሰጡ ቢገፉም እንደ ጉድ
አብዝቶ ነው ማፍቀር አብዝቶ መውደድ።

ዘ - በኩር


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

20 Dec, 16:48


በህይወት መንገድ ለይ ትልቅ ዋጋ ትከፍላለህ ከፍታው ለይ መወጣት የሚፈልግ ሰው መውደቁን መቁጠር የለበትም ። ሁሉም እንደሚያልፍ በእግዚአብሔር ለይ ፅኑ ተስፋ በመያዝ ሰራውን ብቻ መስራት ነው ተስፋ ደግሞ አያሳፍርም ። ዋጋ መክፈላችን ካልቀረ ደግሞ ነጌ ለሚጠቅመን ነገር ቢሆን መልካም ነው ። በዚሁ ለይ አንድ ነገር ልጨምርልህ ማንንም አትጠብቅ ማንንም ለምን መሰለህ ሁሉም የእራሱ የሆነ ሕይወት አለው ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

17 Dec, 02:45


ሰው አንተን ሲርቅህ እግዚአብሔር ደግሞ እንዴት እንደሚቀርብህ ታያለህ አብዝተው ባዶ ሊያደርጉህ ሲሞክሩ እግዚአብሔር አብዝቶ ሲሞላህ ታያለህ መውደቅህን በጉጉት ሲጠብቁ እግዚአብሔርን እዘህ ስትነሳ ያፍራሉ ሊስቁና ሊሳለቁብህ ሲሰለፉ እግዚአብሔር ታሪክህን ቀይሮ ተዓምር ያደርግባቸዋል እና ምን ልልህ ፈልጌ ነው አብሮነትህ መብዛት ያለበት ከእግዚአብሔር ጋር ነው የኔ ጀግና ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

14 Dec, 17:04


አንዳንድ ነገሮችን የግድ ሙጥኝ ባንልባቸው መልካም ነው ። ለምን እንደዚህ አይነት ነገሮች የመሄድ እድላቸው ሰፊ ነው ። ታዳ እንዲህ ሙጥኝ ያልንበት ነገር ደግሞ ሲሄድ በጣም ውድ የሆኑ ነገሮች እንደጠፉ ትዝ ይልሃል ። ሌላውን ተወው ከሁሉም በላይ ግዜህን ታጣለህ ። ስለ እውነት ነው የምልህ ከቀመስኩት ነገር ነው እየነገርኩህ ያለው ። እየተፀፀትኩ ግን አደለም ። Be learn your mistake ሰምተሃል ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

09 Dec, 18:08


ከልብ ማፍቅር ሞኝነት ሆኖ አያውቅም ሞኝነት ከልብ እንደተፈቀረ እያወቀ ለሚሽሽ እንጂ ።

ልብ ከፍተው ያስገቡት ልብ ከፍቶ ቢወጣ አይደንቅም ድሮም '' የአህያ ስጋ አልጋ ቢሉት መሬት '' አደል የሚሉት አበው ።

ግልፅነትህን ርካሽ አድርገው ከገመቱት እንኳን ደስ አለህ ለምን ፅልመታቸው ለይ ያንተ ብርሃን ስለከበዳቸው ነው አባቴ ።

ሀሳብህን ስታወራቸው ተረት ከመሰላቸው ስማኝ ፈጥነህ ፈቀቅ በል ለአንተ የታየህ ለነሱ አልታይ ስላላቸው ነው ። ክብድ በልባቸው ።

ማፈቀር ትልቅ ፀጋ ነው አብዝተህ ውደድ አብዝተህ አፍቅር ሁሌም ቢሆን በፍቅር ውስጥ ኑር በቃ የፍቅር ጥግ የለውም ዝም ብለህ አፍቅር ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

08 Dec, 13:46


ቴዲ አፍሮ

የኃላው ከሌለ የለም የፊቱ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

06 Dec, 09:02


መዝ 6 : 9
እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ እግዚአብሔር ፀሎቴን ተቀበለ ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

01 Dec, 18:14


አምላኬ ሆይ አንተ ያልከው ይሁን 🙏🙏🙏

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

01 Dec, 07:31


አዘልኩሽ
አቀፍኩሽ
ሲበዛ ሳሳሁሽ
አይኔ ብሌኔ አልኩሽ ።

አንድ አለሜ ብዬ ወስኜ ቆርጬ
አንቺን አፈቀርኩኝ ከራሴ አብልጬ

ግና አንቺ ዛሬ.....
ገፋሺኝ እንደ ጉድ ረሳሺው ትላንትን
ረገጥሺው መወደዴን
አደማሺው ልቤን ።

እናም የኔ ቆንጆ....
ሰላም ግቢ አንቺ መሄድሽም ቢያመኝ
አመሰግናለሁ ስላጠነከርሺኝ ። 🙏

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

30 Nov, 10:33


ሰማሽ አደል

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

29 Nov, 04:15


ጨካኔ መጣብን
ሸሸነው አምላክን
ረሳን ተመስገንን
ለብቻ ታገልን
ላንሰራ አንድ ቀን
ጨነቀን ጠበበን ።
አናም.......
ስፎክር ሳቅራራ
እያልኩኝ ሀገሬ ፣
እንዴት ስው አያለ
ሰው ይራበኝ ዛሬ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

27 Nov, 16:44


መጣሁ ሰልችቶኛል
መጠበቅ ደክሞኛል
ቀጠሮ መሰረዝ
ቀን መቁጥር እንደርጉዝ
እመጣለሁ ብቻ የቃላት ጋጋታ
መማል መገዘቱ ለሌለው እውነታ
አልይዝም ቀጠሮ.....
ቋሚነት ለሌለው መጥቶ ለሚጠፋ
ሰልችቶታል ልቤ ወዶ እየተገፋ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

26 Nov, 18:09


ስማኝማ.....

ሁሉንም ነገር ለማወቅ አትባክን የራስ የሆነ ነገር ለይ ብቻ አተኩር እንጂ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

25 Nov, 04:02


ሞኝ አትሁን !

ማንም ሊያድንህ አይመጣም

ወላጆችህም
ወዳጆችህም
አጋርህም ሆነ
ወይም ሌላ ተዐምር አያድንህም ።

አንተን የምታድነው አንተ ብቻ ነህ አባቴ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

24 Nov, 18:02


አይዞህ
የምን ተስፋ መቁረጥ
ሞክር ደግመህ ደግመህ
ሰነፍ አይደክመውም....
ሊሳካልህ ሲል ነው ፣
አለመቻልህን አብዝቶ 'ሚነግርህ ።

አይዞህ !

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

24 Nov, 11:09


ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል pinned «እውነት ከልባችሁ ለምትናፍቁን ስዎች ግን ክብሩልን ። ምንም ነገር ሳንነግራችሁ ለምትረዱን ስዎች ታላቅ ክብር አለኝ 🙏 ማደጋችን የሚያሳስባችሁ ስዎች እግዚአብሔር አምላክ እናንተንም በከፍታ ለይ ያኑራችሁ ። ሲደክመን ተስፋን ላሳያችሁን በሙሉ ከልብ እናመስግናለን ። ደግሞ ልብ እንበል ሰውን መጥቀም ካልቻልን አንጉዳው 🙏 ዘ - በኩር t.me/fikee21 t.me/fikee21 t.me/fikee21»

ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል

24 Nov, 11:09


እውነት ከልባችሁ ለምትናፍቁን ስዎች ግን ክብሩልን ።

ምንም ነገር ሳንነግራችሁ ለምትረዱን ስዎች ታላቅ ክብር አለኝ 🙏

ማደጋችን የሚያሳስባችሁ ስዎች እግዚአብሔር አምላክ እናንተንም በከፍታ ለይ ያኑራችሁ ።

ሲደክመን ተስፋን ላሳያችሁን በሙሉ ከልብ እናመስግናለን ።

ደግሞ ልብ እንበል ሰውን መጥቀም ካልቻልን አንጉዳው 🙏

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21