Ãmìn ßrá Aşk♡ @aysaita_fikr Channel on Telegram

Ãmìn ßrá Aşk♡

@aysaita_fikr


╔┓┏╦━━╦┓╔┓╔━━╗ ║┗┛║┗━╣┃║┃║╯╰║ ║┏┓║┏━╣┗╣┗╣╰╯║ ╚┛┗╩━━╩━╩━╩━━╝
ይህ Channal ኢስላማዊ ግጥሞችን የፍቅር ግጥሞችን ከሽነን እናዘጋጃለን በፍቅር ያበዱ ጥቅሶችን እልህ አሰጨራሺ ደስ የሚሉ የፍቅር ታሪኮችን እናቀርባለን! Channalሉን join በማድረግ ይቀላቀሉ።
Share Share


💬 @Amin_faruq 💬 👈inbox

Ãmìn ßrá Aşk♡ (Amharic)

የፍቅር ግጥሞች ከሽነን እናዘጋጃለን! 'Ãmìn ßrá Aşk♡' ለመሆን በዚህ አማርኛ በተጠቃሚ በሚቀጥለው የትምህርት መረጃ እስኪያከናውን ልክ ይወዳል። ይህ አስተማሪ ጉዳይ ለፍቅር ታሪኮች እና ጥቅሶች የሚል ውጤታውን የታወሳለች። እንደተሳተፉት መከላከል ለተከታታይ መረጃ እንደምንወዳቸው የፍቅር ግጥሞች ምርጫን በአጠቃላይ መረጃ እና መልክዕ ይቀጥላቸዋል። በዚህ Telegram ቻንሎችዎን እናመሰልናለን። የምንባርከውን ስራዎች መረጃ እና ጥቅስ ባጠቃላይ ሊከተለው ይጠብቃል። ከዚህ በላይ እንጠቀማለን።

Ãmìn ßrá Aşk♡

06 Oct, 04:13


🌾ጌታዬ ሆይ
ላንተ ስል ወደድኳት
ከኔ ጋር እንድትሆን
እኔም ከሷ ጋር መሆንን
እንጂ ሌላ ምንም አልፈልግም
ጌታዬ ሆይ እሷን ለኔ ኸይር
እኔም ለሷ ኸይር አድርገን
በፊርደውስም የኔ አድርጋት!!

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

30 Sep, 17:05


#አንቺ_የመጣሽለት @Aşk
.
መሽቶ ነጋ ደግሞ ለሊቱ ማለደ
ጨለማ ለብርሀን ቦታ ለቆ ሄደ
መምጣትሽ ብርሃን ነው መሄድሽ ጨለማ
ቀኑም እደሌት ነው ከሌለሽ አንችማ
----
እጥፍ ድርብ ሆኖ ለሊቱ ረዘመ
ልቤ ጠፍተሽበት አንችን ሲል ቆዘመ
ያኮረፍሽኝ ሰሞን አንቺን እያሰብኩኝ
ናፍቆትሽ በዛና በፍቅርሽ ታመምኩኝ
----
ዛሬ ግን ዛሬ ግን አለሜ
ይሄው መሳቅ ጀመርኩ በፍቅር ታክሜ
ማበድ የጀመርኩት ሰው ሆንኩኝ ደግሜ
መመለስሽ በጀኝ ሳልሞት ደረስሽልኝ
ሂደሽ አልቀረሽም ይሄው መጣሽልኝ
የጎደለኝ የለም ካለኝ ያንቺ ፍቅር
አንች ካለሽልኝ ሁሉም ጉዳይ ይቅር
መመለስሽ ካሰኝ መሄድሽ ቢጎዳኝ
ይቅርታሽ ፈወሰኝ እንድድን እረዳኝ
ምንኛ ደስ ይላል ያጡትን ማግኘት
ሳቅን ተቀብሎ ጭንቀትን መሸኘት
----
ሰው ግን ምቀኛ ነው
መተከዝ አቁሜ መጫወት ባበዛ
ብለው አወሩልብኝ ምን ተገኘ ዛሬ
ጥቁር ፊቱ ወዛ
ሄደሽብኝ ሳዝን ምን ሆንክ ያላለኝ ሰው
መጥተሽልኝ ብስቅ ምን አገኘ ብሎ ሰፈሩን አመሰው
ብቻ ሁሉም አልፎል እንኮን መጣሽልኝ
ሄደሽ ያጣሁትን ዛሬ መለሽልኝ

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

22 Sep, 17:28


🌾ወንድ ማለት ይህ ነው አቦ
ሚስቱን የትም ሁሌም
የሚጠብቃት የሚቀናባት
ከደዩስነትም እራሱን ያገለለ

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

21 Sep, 18:45


#ተቀየረ_ነገር @Aşk
.
እያደር እያደር ዱሮ ዱሮ ዱሮ ገና ሳንጀምር
ባፌ ነበር እንጂ አልወድሽም ነበር
አሁን ግን እያደር ለዛና ቁም ነገር
ቁንጅና ሲደመር እያደር እያደር ተቀየረ ነገር
ሲጨምር ሲጨምር አድናቆቴ ሲንር
የተፈጥሮሽ ማማር የአንደበትሽ ማር
እየዋለ እያደር ቀን በቀን ሲጨምር
ሲደመር
ሲደመር
አሁንም ሲደመር
አጠለቅልቆ ሞልቶት
የልቤን ላይ አገር
ከነብሴ አስበለጥኩሽ አረኩሽ ፍቅርቅርቅር
እያደር እያደር ተቀየረ ነገር

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

20 Sep, 17:23


🌾ከቁጥጥር በላይ የሆነ ደስታ
ማለት ፊቱን ስታይ ድምፁን
ስትሰማ ሀዘንህን የምትረሳበት
ወዳጅ ሲኖርህ ብቻ ነው!!

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

19 Sep, 16:53


#አታፍቅሪኝ_አንቺ @Aşk
.
ተኝቸም ቁጭ ብየ በሃሳብ ሳስብሽ
ለኔ ትንሽ ቦታ በልብሽ ባይኖርሽ
ወረተኛ ሁነሽ ለፍቅር ሳትሞቺ
ተይ እኔ ላፍቅርሽ አታፍቅሪኝ አንቺ
----
መለየት አቅቶኝ ቀን መሽቶ መንጋቱን
አንገቴን ደፍቸ ስገፋ ጊዚያቱን
በሳቅ በጫዋታ ሰፈሩ ሲቦርቅ
ፍቅርሽ ፍቅሬን ሰብሮ ከካላቴ ሲርቅ
----
ሊያፅናናኝ የሚያስብ ባገር ቢሞላም ሰው
የፍቅርሽን ስቃይ ብቻየን ልቅመሰው
የሚያስተሳስረን ያቀን እስኪመጣ
አንቺ ሰላም ሁኒ እኔ ሰላም ልጣ
እስከማገኝ ድረስ እንግድህ አቻየን
ባክሽ አታፍቅሪኝ ላፍቅርሽ ብቻየን

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

13 Sep, 11:03


#የፍቅር_ቃል @Aşk
.

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

07 Sep, 09:10


#ሂዱና_ንገሮት @Aşk
.
ኑሮዋን እየኖረች ካለኔ አይኖርም ላለችው መሰሪ
ሂዱና ንገሮት ለዛች ቀባጣሪ
ጨረቃዋ ደም ለብሶ ፀሃይ ልትወጣ ነው
አዝመራው አፍርቶ እሸት ሊበላ ነው
ብላችሁ ነገሮት
ያለሷ እንደምኖር ሂዳችሁ አስረዶት
----
ደግሞም እንዲገርማት…!
ፀሃይን አግብቶል በደመቀ ድግስ
ሂዱና ንገሮት በቃጠሎ ብዛት ከሷ እንደምብስ
ውበቷ የደመቀ ጨረቃ ምትባል ውሽማ አለችው
ይህን ድንቅ ውበቷን ሌላ ጋር ስላጣች ካንቺ ተዋሰችው
ብላችሁ ንገሮት
ወበቷ እንዲገርማት
----
እሳትና ውበት ባንድዮሽ ተገምዶ አንቺ ጋ አይቻለሁ
እንዳይግርም ውዴ አንቺ ስትሄጂ ግን ፀሃይና ጨረቃን ይሄው አግብቻለሁ
ብላችሁ ንገሮት
አማራጭ እንዳለ ሁሌም እንዲገባት

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡

Ãmìn ßrá Aşk♡

05 Sep, 11:41


መብሩክ አልፍ መብሩክ
ባረከላህ ሀቢቢ

ባረከላሁ ለኩማ
ወባሪክ ዓለይኩማ
ወጀመዐ በይነኩማ
ፊል ኸይር

❤️ለወንድማችን መሀመድ አቡበከር😍
እና
❤️ለእህታችን ኡኩቢ አሊ😍

ያማረ ትዳር ይሁንላችሁ !!

Ãmìn ßrá Aşk♡

04 Sep, 05:53


#አጃዒብ @Aşk
.
ቆንጆ ቃሉ የማይበቃት
ውበት ከኢማን የሞላት
ሱብሃነከ ረቢ አጃዒብ አቋሟ
ከንስቶች ሁሉ የተለየ ስሟ
መሽቀርቀር ሂጃቧ በሀያዕ ተውባ
ከቤቶ ብደርስ…
ሂክማ በተሞላው በለዛ አንደበቶ አርሂብ ግባ ግባ
ተብዬ ብገባ አየሁ መስተንግዶ ተባልኩ እሷን ጀባ

Join👉 @Aysaita_fikr
@Aysaita_fikr

#Amin_Faruq ♡ ⅡአይሰዒታⅡ♡