ፍልስፍና philosophy @yefkrterkoch Channel on Telegram

ፍልስፍና philosophy

@yefkrterkoch


ፍልስፍና philosophy

ፍልስፍና philosophy (Amharic)

ዘናጩ ፍሽን ፍልስፍና philosophy የሚናገረው በመሆኑ አዲስ አሳይ አይነሳ ትምህርት ከፈለን። ይህ ትምህርት ከተለያዩ አስተዳዳሪዎች ጋር አንዱን እናመጣለን: እንደ ሰነዲ አበበ, ሽለላ ተምሪ። የፍልስፍና ትምህርት ካለበት ምክር አስቀድሞ ሁኔታን የጠራ ሰልፍ ነን። ይሄ ሁኔታ ማገልገል, መሳሪያዎችን ያለማሳየት በመጠቀም በአንቀጽ ሁኔታ እንደዚህ መላክ ያለ ግንዛቤ ሳይሆን ይሁንልን። ዘናጩ ፍሽን በትንሹም ምስጢርና ምግብ የሚሆነውን ሲሆን የምግባር ቅንፍ የሚቀጥለውን የሆኑ ፍልስፍና ታሪካም አገልግሎቶችን ማድረግ እና ይህን ሳንሆን እናየማየል እንደዚህ የፍልስፍና ትምህርት የቻለ ፍልስፍና ታሪካም አገልግሎቶች ስለግንኙነ እንደሆነ ለማስተካከል በመቀጠል አዲስ እና ምንም አስራት ብቻ በመረጃ እና ትልማ በጥረት ይበልጣል።

ፍልስፍና philosophy

26 Dec, 17:53


“እግዜርና ዳዊት አብረው ተቧደኑ
ብቻውን ታጠቀ ጎልያድ ምስኪኑ
አንዳንዱ ተገዶ ለሽንፈት ሲፈጠር
በጥቅሻ ይወድቃል እንኳንስ በጠጠር”    

             ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም

ፍልስፍና philosophy

23 Dec, 15:05


"ታላቅ ዘፋኝ የሚባለው ዝምታችንን የሚያዜምልን ነው።"
              

ፍልስፍና philosophy

21 Dec, 15:05


ፍልስፍና እና ሴት??

የፍልስፍና ርእስ ናት ብዙ ፈላስፎች ስለ ስንተ-አለሙ ሲዳስሱ አብረው ሀሳባቸውን አስቀምጠዋል፤አንዳንድ ፈላስፎች እንደውም ከሰው ዘር ለይተው ያዩታል-ሴት! ፍልስፍና ሆነ ዘመናዊው ሳይንስ በተለይ የስነ-ዝግመተ ለውጥ ሳይኮሎጂ የሴትን አፈጣጠር እና ባህሪ በተመለከ ቁጭ ብለው እንዲያስቡ አስገድዷቸዋል!-(ግን ለምን ወንድ እንዲ አላስጨነቃቸውም?)።

ከመጽሀፍ ቅዱስ ዘፍጥረት ጅማሮ ጀምሮ ፈላስፎች እረፍት አልሰጣቸውም በተለይ የሴቷ አንዴ"ከአዳም እኩል መፈጠሯ" (ዘፍ፥1:27) በሌላም ጊዜ "የግራ አጥንቱውጤት" (ዘፍ፥2:22-23) የመጀመሪያዋ ወዴት ሄደች?ከሁሉ በላይ ግን ሁለተኛዋ ለምን አስፈለገች?..የሚሉት ጥያቄ በደንብ አብላልተው የሀሳባቸው አስፈሩ አንዳንዶች"ሴት የህይወት ሙላት ስለሆነች ባይሆን ኖሮ ባላስፈለገች ነበር!" ሌሎች"ለወንድ ስራ የተገባች ስለሆነች ነው!" በሚለው የሚስማሙሙ አሉ።"የለም የለም! ለወንድ የምድር ሲኦልን ለማሳየት የተፈጠረች ስጋ ለበስ ሰይጣን ነች!" የሚሉ አልታጡም።

ጥንተ ፈላስፎች የሴትን ልጅ ጉዳይ ከወንድ ልጅ ባህሪ እና የህይወት አላማ ነጥለው ነበር የሚያዩት።የሶቅራጠስ ሚስት የነበረችው ዛንቴፔ (Xanthippe) የምእራባውያን የፍልስፍና አመለካከት ሲቀይር የገዛ ሚስቱን ማረጋጋት አለመቻሉ ሁሌም ጥያቄ ይሆንብኛል!።ሲበዛ አናዳጅ የነበረች ሴት እንደሆነች ሶቅራጠስ ራሱ ይመሰክራል ግን ከአባባል የዘለለ ትኩረቱ ጥያቄ ላይ ለነበረው ሶቅራጠስ ችግር አልነበረም።አንድ ታዋቂ አባባል አለችው እንዲ የምትል"ጥሩ ሚስት ካገኘህ ደስተኛ ትሆናለህ፤ መጥፎ ሚስት ካገኘህ ፈላስፋ ትሆናለህ(By all means marry; if you get a good wife, you'll become happy; if you get a bad one, you'll become a philosopher)

የእርሱ ደቀመዝሙር እና ፀሀፊው የነበረው ፕሌቶ The Republic በሚለው መፅሀፉ ሆነ በተለያዩ ቃለምልልሶች ፁሁፉ በሴት እና ወንድ እኩል የሚያይ ነው።ይሄም የሆነ theory of form እያለ የሚሰብከው ማለትም "ይሄ አለም ጥላ ነው አንድ እውነተኛው አለም አለ እሱ ውስጥ ደግሞ ነብስ አለ/ች ነብስ ደግሞ ፆታ የላትም!"ብሎ ያምን ነበር፤ በዚህም "ከወንድ ጋር እኩል መብት በትምህርት ሆነ ፖለቲካ እንዳላት" ያምነ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ ፕሌቶ "ወንድ ሆኖ ስለተፈጠረ ያመሰገን" ነበር!

የፕሌቶ ተማሪ የነበረው ከመምህሩ ጋር ብዙ ጊዜ በመሟገት የሚታወቀው መምህሩ ፕሌቶ እራሱ ስለ ተማሪው እውቀት የመሰከረለት አርስቶትል እናገኘዋለን።እሱ ደግሞ "ሴት ማለት ተሰርቶ ያላለቀ ወንድ ናት!" ሲል ይሰማል።አርስቶትል "የሰው ማለት  የአካል እና ነብስ ወህድ ነው!(Human beings are the union of body and soul)" ይላል ነገር ግን ሴቶች ከአንዱ ብቻ (ከአካል) የተገኙ እንደሆነ ያስባል በዚህ ምክንያት "ሴቶች በወንዶች ህግ መተዳደሪያ ስር መሆን እንዳለባቸው" አበክሮ ያስጠነቅቃል። ፈላስፋው አርስቶትል , Politics በተሰኘው ድንቅ ስራው እንዲ ይላል"[T]he relation of male to female is by nature a relation of superior to inferior and ruler to ruled."

ወደ መካከለኛ ዘመን የፍልስፍና ታሪክ ብዙም የሴት ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት አይታይም በተለይ ከዳግም-ውልደት(Renaissance) በኋላ ፍልስፍናው ሰውን ያተኮረ(Humanism) እና17ኛው ክፍለ ዘመን ማገባደጃ የአርት እና ኪነ-ጥበብ ስራዎች ላይ ነበር በዚህም የፍልስፍናና "ሴት" ጉዳይ ወደ ጎን የተባለ ነበር...

በቅርብ ጊዜ ወዲ በዘመናዊው ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ስለ"ሴት" የምንለው አለ ብለው መድረኩን ተቀላቀሉ በተለይ የስነ-ህይወት ጥናት(Biology) እና ሳይኮሎጂ (psychology)።የስነ-ህይወት አጥኚዎች ስለ"ሴት" ተፈጥሮ የሚያቀርቡበት መንገድ የዳርዊን ዝግመተ-ለውጥን ተከትለው ነው በመጀመሪያ ራሱ ዳርዊን ስለ"ሴት"ያሰፈረውን እንመልከት። በእርግጥ የዳርዊን ሀሳብ ለመረዳት መጀመሪያ ስለ"ፆታዊ ምርጦሽ(Sexual Selection)" መረዳት ያስፈልጋል።ፆታዊ ምርጦሽ ማለት አንድ ፆታ ሌላ ጥሩ(ምርጥ) ዘርን መርጦ ትውልድን የማስቀጠል ሂደት ነው። ምርጦሹ በተክለ-ሰውነት፣የቀለም አይነት እነዲሁም ሌላ ሌላም ነገሮች የተሻለ ዘርን መርጦ ከዛ ጋር ርቢ በመፈፀም የተሻለ ዘር የማስቀጠል እና ከትግል መድረክ (Survive of the fittest) አሸናፊውን ማደን እና *በተፈጥሮ ምርጦሽ*  የሚካሄድ ነው።ዳርዊን ሴት እና ወንድ በፆታዊው ምርጦሹ(Sexual Selection) የተለያዩ እንደሆኑ ይናገራል።ወንድም ሆነ ሴት በዚህ የፆታዊ ምርጦሽ ምክንያት የተለያየ የህይወት ማንነት ያላቸው ናቸው(Difference biological identity) ያላቸው እንደሆኑ ይናገራል።(የዳርዊን በዚህ አያበቃም ይቀጥላል....እኛ ይቺን ካልን ወደ ቀጣዮቹ እንለፍ)

የስነ-ህይወትን በትንሹ አይተን ወደ ሳይኮሎጂስቶቹ  ፍሮይድ እና ዊልያም ጀምስ እንለፍ! ሳይኮሎጂስቱ ሲግመን ፍሮይድ ስለ"ሴት" እንደሚለው ከሆነ "ሴቶች ከወንዶች በላይ ለስሜታቸው ቅርብ ቢሆንም በዚህም ከወንድ የበታችነት ስሜት ቢመስላትም እንዴት ወንድን ማሽከርከር እንደምትችል ታውቃለች!" ፍሮይድ ለወጣት ሴቶች የሚሰጠው የቴራፒ አገልግሎት ነበር።ሴቶች በጊዜውም ሆነ በማህበረሰቡ አመለካከት "ሴት"በመሆናቸው ብቻ የንቀት እና የበታችነት ስሜት ይታዩ ነበር፤ በዚህም "Penis envy" የሚባለውን ለሴት የሚሰጠውን ቦታ ለማከም እና የግድ ለክብር ወይም ጭንቀት ለመቀነስ ነበር ፍሮይድ ፅንሰሀሳቡን ያቀረበው ቢሆንም ግን በነካረን ሆርኒ፣ ኤርነስት ጆንስ፣ሄሌነ ዶይች እና ሜላኒ ክላይን ተቃውሞ ደርሶበት ነበር።

ሌላው ፈላስፋና ሳይኮሎጂስቱ ዊልያም ጀምስ ነው።ጀምስ "ሴት"ን ከፍሮይድ ሀሳብ በተመሳሳይ ቢያያትም በእኩልነታቸው ያምናሉ ሂደቱ ይለያይ እንጂ..!የ"ሴት" ባህሪን ጀምስ የሚያየው ከተግባር-ተኮር ሴትነት (pragmatic feminism)።ወደ ፈላስፎቹ ስንመለስ ደግሞ ሂግልን እናገኘዋለን። ለጀርመኑ ፈላስፋ ሂግል "ሴት" ማለት "በቤት ውስጥ ያለች 'ሰው' ነች!" ማለትም ሴቶች ብዙ ጊዜዋን በቤት ውስጥ ስለምታሳልፍ ስለሆነች ስራዋና ተፈጥሮዋ ለዚሁ ነው ይለናል።ከዚህ ጋር ተያይዞ በሁለተኛው አለም ጦርት ጊዜ በጀርመን ነግሶ የነበረው የናዚ ፓርቲ አመለካከት እንዲሁ የጀርመን ህዝብም ያምንበት ነበር፤"ሴት ልጅ አስፈላጊነቶ ለ3C ነገሮች ነው..." ይላሉ ለምን.... ለምን..... ሲባሉ "Children,Cooking,for Controlling house!" በማለት ይናገሩ ነበር።ሌላው የሀገራቸው ልጅ በፍሬድሪክ ዊልያም ኒቼ ደግሞ አለ ይሄንሰ ሰው ነውጠኛ ማለት ይቀላል በስሙ ከመጥራት..!ኒቼ the Spoke of Zarathustra በሚለው ተወዳጅና አድናቆት ባተረፈው መፅሀፉ ከዛራቱስትራ የምታወራ አንዲት ሴትዮ ለዛራቱስትራ እንዲ ትለዋለች"you are going to women? Do not forget the whip(ወደ ሴት ትሄዳለህ?እንግዲያውስ ጅራፍህን አትርሳ!)" የኒቼ ተምሳሌት የነበረው ለአርተር ሾፐንሀወር "ሴት" ይጠላ ነበር ምክንያቱም ህይወትን ይጠላ ስለነበር ውበትም አያደንቅም ነበር። ሌላው ኦስካር ዋይልድ ነው እሱም ሴትን ማመን ቀብሮ ነው የሚል ፈላስፋ ነው "ሴት ለመፍቀር እንጂ

ፍልስፍና philosophy

21 Dec, 07:52


ቡድሀ አንዴ ስለዝምታ ምን አለ መሰላችሁ ወዳጆቼ !

«ዝምታ የአብርሆት ጉዞ እና አንድን ሀሳብን ማዕከል ማድረጊያ መንገድ ነው.   .  .  .

[Silence is a path to enlightenment and a way to center one's thoughts]»

ፍልስፍና philosophy

21 Dec, 04:08


እግረ መንገድ ከተሰኘው የጋሽ ስብሀት መጽሐፍ የተቆነጠረች ንባብ...



<<…ልጅ ሆኜ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ጢቢ፣ ጢቢ ስጫወት ነበር። ጎረምሳ ሆኜ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ሴት ልጅን ሳቅፍ ነበር። ዛሬ አርጅቼ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ልጄ ስትስቅ ሳይ ነው። አሁን እነዚህን ሶስት እኔዎች ሳስተያያቸው አንድ ሰው ናቸው? እርግጠኛ መሆን ያስችላል። እኔ ሽማግሌውስ አንድም፣ አራትም ብሆን ይኸው እዚህ አለሁ። ያ እኔ የምለው ልጅና ያ እኔ የምለው ጎረምሳ ግን የት ሄዱ? የኔ ትውስታ ውስጥ ከልጅየውም ከጎረምሳውም ከብዙ በጥቂቱ እንደ ፊልም ተቀርፆ ይገኛል እንጂ እነሱ ግን የሉም። እኮ እንዴት እኔ ውስጥ ተቀርፀው ሊገኙ ቻሉ? ያን ጊዜ ልጅየው ሆነ ጎረምሳው ሲኖሩ እኔ እዚያ አልነበርኩም'ኮ። ገና አልመጣሁም ነበራ። ያን ጊዜ ያልነበርኩ ሰውዬ ትውስታ ውስጥ አሁን የሌሉ ያን ጊዜ የነበሩ ሰዎች ተቀርጸው ይገኛሉ። ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? የጊዜና የትውስታ ምስጢራዊ ምትሀት ነው። ለመሆኑ ጊዘና ትውስታ ምንና ምን ናቸው?...>>



ምንጭ ፦ እግረ-መንገድ...ገጽ 206-207

ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር
ጋሽ ስብሃት እቺን መጠይቃዊ ሃሳብ ያሰፈራት ከጆ እና ሀሪ "አራቱ እኔዎች" ፍልስፍና ተነስቶ ነበር...እኛም በጋሽ ስብሀት ሀሳብ ውስጥ እራሳችንን ልንመለከትበት እንችላለን...እሄንን ስናነብ ያለንበትን የዕድሜ ደረጃ እና ያ ካለፈ በኋላ የሚኖረን ስሜት...አሁን በአፍላነታችን የምንመለከትበት አይንና በዕሜው በሰል ስንል የሚኖረን ትርጓሜ ልዩነት እንደሚኖረው የሚካድ አይደለም...

እግረ-መንገድ የሀሳብ እና የፍልስፍና ባህር ነው...እስካሁን ያልሰጠማችሁ ስመጡበት ለማለት እወዳለሁ...!

ፍልስፍና philosophy

18 Dec, 18:28


_
፩ – አካል እንደ ማንነት
~
ለምሳሌ ‘የኔ እጅ’ ትላለህ እንጂ ‘እጄ እኔን ነው’ አትልም… ‘ዓይኑ የእኔ ነው’ ትላለህ እንጂ ‘እኔ ዓይኔን ነኝ’ አትልም… እግርህን፣ ልብህን፣ ጸጉርህን፣ የሰውነት ክፍልህን እያንዳንዱን እየቆረጥክ ብትቀንሰው ‘ያንተ የሆነው’ ተቀነሰ እንጂ ‘አንተ ራስህ’ ግን አልጠፋህም… ታዲያ ‘የኔ’ የሚለው ‘እኔህ’ የት ነው ያለው?
_
ነገሩን መረር እናድርገው… ልብህን ብታወጣት ‘እሞታለሁ – ከሞትኩ የለሁም’ ትል ይሆናል… አርቴፊሻል ልብ ቢገጠምልህ ግን ‘ሞት’ ይሉትን ታፔላ መዝለልህ አይቀርም… እስኪ አንገትህን እንቁረጠው…. ኦው… ይሄማ ከባድ ነው… እስትንፋስህ ትሰናበታለች… ታዲያ ‘እኔህ’ ያለው ጭንቅላትህ ውስጥ ይሆን እንዴ?… ግን የቱ ጋ?…
_
ነገሩን በደንብ ካሰብከው እኔ ባዩ ማንነት ‘ተጨባጭ’ አይደለም… ከአካል መዋቅርህ ጋር ስታያይዘው ብትቆይም በመጨረሻ የሚገባህ ‘የእኔ’ የምትለው አካል እንጂ እኔህን የሆነ አካል እንደሌለ ነው… እኔታ ከአካላዊ ኑረት ሳይነጠል በሕላዌው ግን ሳይንጠለጠል የሚኖር ነው…
_
የአካል ጠጣር መምሰል ‘በማየት ማመን ነው’ ሲያጸናን የእይታ ውስንነት ደግሞ ከሚታየው ጀርባ ካለው እውነት አፋትቶናል… እንደ እውነቱ ከሆነ አካላችን እንደምናስበው Solid አይደለም… በአንድ ፊዚስት ዓይን ስንታይ በተንተን ብለው ከሚታዩ Electrical discharges ውጭ ያለው ሰፊ ቦታ ባዶ /Void/ ነው…
_
ሰውነታችን የተሰራው ከአተም ነው… አተም ደግሞ ለአዕምሮ በማይመጠን ፍጥነት እባዶው ላይ በሚሾሩ ፓርቲክሎች [leptons, quarks, እና mesons] የተገነባ ነው… እኒህ ፓርቲክሎች ጠጣር አይደሉም… ይልቁንም 99.99% ይዞታቸው ባዶ ነው… ችግሩ የስሜት ሕዋሶቻችን ይዋሻሉ… ‘የሌለ’ እንዳለ እንድናምን ያደርጉናል… በዚህ ምክንያት እንኳን ‘ሞተህ’ እያለህም ‘የለም’ በሚባል ሥጋ ላይ ማንነትህን ገንብተሃል ማለት ነው…
_
እንዲህ ዓይነቱ ማቀናነስ ወደ ስምህ፣ ስራህ፣ ዝናህ፣ ክህሎትህ… ወዘተ ሲመጣ ተመሳሳይ ውጤት ነው ያለው… አንተ ይህን ሁሉ አይደለህም… ያለነዚህ ሁሉ ‘እኔ’ አለና… የድርጊት ተመልካች – የኑረት ታዛቢ ሆኖ… ስለዚህ አካላዊ መገለጥ ውስጥ የሚታዩት የቆዳ ቀለም፣ ጾታ፣ አቅምና ዕድሜ ማንነት አይደሉም ማለት ነው…
_
ማወራረጃ…
~
“Reality is merely an illusion, albeit a very persistent one.” ~ Albert Einstein

    ይቀጥላል…

ፍልስፍና philosophy

15 Dec, 10:42


ስብሀት ወዶ አይደለም!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ስብሀት የማይለው፣
ወይ ትርጉም አቶ ነው፣ ወይ አግኝቶለት ነው።

"ጋሽ ስብሀት ወደህ አይደለም አይደል.....?"

"አዎ ልጄ።..... ወድጄ አይደለም።"

"አስቲ ተረት አውራልኝ..?"

"ተረት..?"

"አዎ ተረት"

"እኔ ተረት አልችልም።"

"ያው ትፅፍ የለ..?"

"ተረት...?"

"አዎ ተረት"

"ተረት እኮ አይደለም"

"እና ምንድነው ..?"

"ህይወት ነው"

"ህይወት ይፃፋል እንዴ...?"

"ሁሉም አይደለም እንጂ...."

"ለምን ሁሉም አይፃፍም..?"

"ሁሉም አይገኝማ ልጄ።"

"ታድያ ጎዶሎ ህይወት አለ...?"

"ለዚህ እኮነው ተረት ያላኳት።"

"ማንን...?"

"ህይወትዋን...."

"አይ ጋሼ..."

"አይ ልጄ..."

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እንዲህ የሚፅፈው፣
ሰውን አንዳይመረው ነው፣ እሱን የመረረው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ድሀ ድሀ ያለው፣
አሄን ድህነት፣ ገልጦ ስላየው ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ጋሽ ስብሀት ባለጌ ነህ አይደል...?"

"ሰው ብቻውን አይባልግም"

ማለቴ የምትፅፈው እርቃንን ነው..?"

"ታድያኮ እሱ እውነት ነው።"

"ፅሁፍህ ሁሉ እውነት ነው ማለት ነው..?"

"አይደለም ውሸትም አለበት አንዳንዴ እኮ ሰዎችን ልብስ አለብሳቸዋለሁ።"

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እርቃንን የፃፈው፣
አዳምና ሄዋን፣ ትዝ ብለውት ነው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ወሲብ ወሲብ ያለው፣
የጉድ መፈልፈያ መሆኑ፣ ገብቶት ነው።

ፍልስፍና philosophy

14 Dec, 18:47


It is Suicide⁉️
••••••••••••
አመጣው ጨዋታውን። እግዚአብሔር ራሱ ከፈጠረው ሰይጣን ሊያድነን ብሎ ራሱን ወልዶ ራሱን ወደ አለም ላከና ራሱን በራሱ ገደለ። እናንተን ለማዳን ሞተ ተሰቀለ ?

አንዳንዱ በሚድያ  ላይ ሀይማኖቴን አትንካ ሲል መፅሀፍ ቅዱስና ቁርአን ሲፃፍ አሳብ ያወጣ ነው የሚመስለው ። ክርስትና ኒቂያ ጉባኤ ላይ ሲፀድቅ የጉባኤው ተሳታፊ ነው የሚመስለው።  በሰው አስተሳሰብ ለዛውም የጋራ በሆነ ሀይማኖቴን አትንካ ብሎ ሲከራከር በሊዝ ተከራይቶት ነው ያሰኛል። 

አልበርት አነስታይን የለፋበት ቲዮሪ ሲብጠለጠል እንደዚህ የባለቤትነት መብት አልተሰማውም። በሀይማኖት ስም ያደነቁራሉ። አገር ያጀዝባሉ። መከራው ለኛ ነው የሚተርፈው ይሄ ነገር ስህተት ነው ሲባሉ ሀይማኖቴ ተነካ ይላሉ። (በምን ተነካ በእንጨት ነው የተነካው!? ወይንስ በሪሞት ጉድ እኮ ነው) ሁሉም ሀይማኖቱን ሲከላከል ለፈጣሪ ተቆርቁሮ እንዳይመስልህ። ሀይማኖቴ ተነካ የሚለው የራሱን ድንቁርና ለመከላከል ነው። ምክንያቱም ድንቁርና ምቾት አለው። ስለዚህ ሀይማኖቴ ተነካ የሚለው ይቺን ምቹ ስሜት ለመጠበቅ ብቻ ነው።

የእናንተ አምላካችሁ ፆም ፁም ምግብ ብሉ አትብሉ ምስር ሽሮ ብሉ: ስጋ ወተት አትብሉ፣ ዘምር አትዘምር አሸብሽብ አታሸብሽብ ቁጭ በል ተነስ፣ ስገድ አትስገድ የሚል ከሆነ የምታመልኩት ቭላድሚር ፑቲንን ወይንስ ኪም ጆንግ ኢንን ነው?

ፍልስፍና philosophy

14 Dec, 10:25


«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ[ኢ.ኦ.ተ] አዲስቷ የሮም ካቶሊክ አገዛዝ መገለጫ ሆናለች!»
[በኃይል እና ሥልጣን ስር]


                          [ትዝብት.   .   .   .]

        በምዕራባውያን የጽልመት ዘመን [Dark Age] ከሁሉም ኃይማኖቶች በላይ ዙፋኑን በእጁ ያስገባው የክርስትና ኃይማኖት በተለይ ደግሞ የምዕራቡ ካቶሊክ[ጣሊያናዊው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን] ነበር።በጊዜያዋም የተለያዩ ለመስማት የሚሰቀጥጡ የግድያ ሂደቶች[አማኝ ነኝ ከሚል የማይጠበቅ]፡በኃይማኖቱ ላይ ይሰጡ የነበሩ ትችቶችን በማስወገድ፡ከፖለቲካው ባለፈ ከፍተኛ የሆነ የሥልጣን ጥማትን፡የሀብት እና ቁስ ማጋበስ፡ለደሀው ክፍል «ከሞት በኋላ መንግስተ ሰማይ ካሳ[Heaven Consoling] አለህ»በሚል ለሀብታሙ እንዲበዘበዝ በር እስከመክፈት ደርሳ የነበረበት እና ኃይማኖት ሙሉ በሙሉ የሰውልጅ ልብ ውስጥ ሲፀና የሚፈጠረው ምን ሊመስል እንደሚችል ማሳያ ሆና አልፋለች።



ዘመናዊው የኦርቶዶክስ ኃይማኖት

          የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመካከለኛው ዘመን ያን ሁሉ ጉድ ስትሰራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወደ ሰሜን ሊስፋፋ የሚታገለው እስልምናዊ መንግስት ጋር ትግል ስትገጥም ነበር።በጦርነት ውስጥ ፃዲቅ ለመሆን መወሰን ሸምቀቆ በአንገት መክተት ይሆናልና ባላት ኃይል ካጣችም እየተበደረች ብዙ ፖለቲካው ጦርነት የምታካሄድበት የጦፈ ወቅት ነበር።አንዳንድ ገራሚ¡ የኃይማኖቱ ተከታይ የሆነ የታሪክ አጥኚዎች [Historians] ቤተክርስቲያኗ ልክ አማራጭ በማጣት እጇን የከተተችው ያክል ጭቆና እና ብዝበዛ ፀንቷባት ለነፃነቷ የታገለች ነገር አስመስለው ያቀርቡታል።ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ የበላይ ፖለቲካዊ ኃይልን ይናፍቃል።ኃይማኖት ራሱ በሰው ልጅ ውስጥ ያለው የኃይል ጥማት መግታት እንዳልቻለ መሳያዎች የታሪክ ሂደቶቻችን ናቸው።

   አሁኗዊው የቤተክርስቲያኗ ቅርፅ ቀድሞውኑ ከነበሩት የቫቲካን ቤተክርስቲያን አመራር እና የኃይማኖት አውቃቀር ጋር ከአመት አመት  እጅግ በጣም ተቀራራቢ እየሆነ እንደመጣ ነው የሚታየኝ።

መሰረታዊ ተመሳሳይ ባህሪያቸው፥
    °ያልተገታ  ሀብት የማጋበስ ፍላጎት
    °ለፖለቲካዊው በትረ መንግስት ማጎብደድ
    °ደሀውን ማህበረሰብ ከፖለቲካ፡ከማህበራዊ ከኢኮኖሚያዊ ስልጣኔ በመሸሽ ለበለጠ ብልፅግና እንዳይሰራ የማድረግ
     °ለኃይማኖታዊ ትችቶች ዝግ መሆን
     °ለሀብታሙ ክፍል የሚጠቅም የወንጌል ትምህርት
     °መንግስተ ሰማያትን የማይታይ መጭበርበሪያ ማድረግ
    °እምነት የሰው ልጅ ደካማ ጎን ነውና ይሄንን ስሜት ለገዛ ጥቅም ማዋል
    °የተለያዩ ብዛት እና ስፋት ያላቸው የመሬት ይዞታዎች በመያዝ ለእድገት እንቅፋት መሆን
    °ከእውነተኛው ወንጌል ያፈነገጠ ለዘመኑ የተመቸ ትምህርቶች
    °መንፈሳዊ ላሉት አለም ክሽፈት ማሳየታቸው
    °ለሥልጣን ፉክክር

እጅግ አጥብቆ የሚያመሳስላቸው ባህሪ ነው።በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን መቼ ሚካኤል፡ ገብርኤል እንዲሁም ሰማእታት Tiktok እና YouTube አካውንት እንደከፈቱ መረጃው ባይኖረኝም ነገርግን ለእነሱም ዋና ነገር «የኃይል ጥማት» እንደሆነ ማሳያዎች ሆነውልኛል [«አንዳንድ ሰው በሃይማኖት ከመጣ አምላኩን ራሱ አያዳምጠውም!!»አይነት ናቸው]።




ኃይማኖት የያዘው ወሳኝ ስሜት

   በሰውልጅ ብዙ መደብ ስሜቶች ውስጥ መሰረታዊ የሚባሉ ሰባቱ ደስታ፣ድንጋጤ፣ ሀዘን፣ፍርሃት፣ ጥላቻ ፣ ንቀት እና ቁጣ መካከል ውስጥ በዋናነት ኃይማኖት ፍርሃትን በመአከልነት ይይዛል።ይሄንን እንዲቆጣጠር ያስቻለው የሰውልጅ ለተጠየቁ አለም በሙሉ ቁርጥ ያለ መልስ አለማግኘት እና የማያወቀውን አጠቃሎ ከመፍራት አኳያ የመነጨ ስነልቦናዊ ግፊት ነው።ሌላኛው የስነልቦና ግፊቱ ደግሞ ቅይጥ ድብቅ ሀሳቦች[collective Unconscious] የሰውልጅ ስነልቦና ጥልቅ ነው ለሥልጣና እና ኃይል ከፍተኛ ቦታ አለው ሰይጣን ከነበረበት የጣለው የኃይል ፍላጎት ነው፡አዳምን ያስባረረው የኃይል ሂደት፡ክሮኖስን ልጆቹን እንዲገድል ያደረገው ኃይልን ፍለጋ ነው፡ሚካኤል ዘንዶውን ላይ መፈንቅለ ማዕረግ ያደረገው ለሥልጣን[ኃይል]¹ ነው። ወደ ጫካው ህግ ብንመለስ እንኳን  የተሻለ በተፈጥሮ ተመርጦ ለመቆየት የተማረውን[ሥልጣን]  ለዘርማንዘሩ ማስተላለፍ መቻል ወሳኝ ቁልፉ ነገር ነው፤ነገርግን የዚህ እውቀት የጎንዮሽ ጉዳት መሰረታዊ ኃይማኖትን ፈጠረ።
ኢየሱስ ክፍለዘመናትን ቢሻገር ኖር ሶስት ጊዜ ስቅላቱን ያይ ነበር፦
     አንድ በአይሁዶች[ይኸኛውን አየ አዘነላቸው አዘነባቸው!]
    ሁለትም በሙስሊሞች
    ሶስትም በክርስቲኖች


ከጲላጦስ በላይ አይሁዶች ለሞቱ ተጠያቂ ናቸው

ከኒሮ በላይ ክርስቲያኖች ለሞቱ ተጠያቂ ናቸው

ከቁረይሾች በላይ ሞሀመዳዊያን ለሞቱ
ተጠያቂዎች ናቸው።

መስቀሉን ይሸከማሉ ተብለው የተጠበቁት መስቀል አሸካሚ ሆነው አረፉት።የዚህ ደም ኃጢያታቸው በገዛ ራሳቸው ንሰሀ ውኃ የሚለቅ አልሆን ሲላቸው ለግፋቸው አምላካዊ ፈቃድ ያገኘ ክንውን ነው በሚል ሊሸፍኑት ይጥራሉ።ጊዜያት ሲያልፉ እና ስህተታቸው ማስተባበያ ሲያጣ
የገደሉትን ያመልካሉ ይሄ የኃይማኖት ሀተታ ፍፃሜ ነው።የአብርሃም ኃይማኖቶች ገድላቸውም ሆነ ግድያቸው ማብቂያ የለውምና .  .  .
ትዝብቴን አባ ተስፈስላሴ ሞገስ በቃላቸው ይቋጩልኝ ፥

«ኃይማኖትም ፖለቲካ፤ፖለቲካም ኃይማኖት ነው»

ፍልስፍና philosophy

12 Dec, 20:44


የአማርኛው መዝገበ ቃላት "ዘረኝነት" ለሚለው ቃል "ከቀለም ወይም ከዘር ልዩነት የተነሣ ራስን የተሻለ አድርጎ በመገመት ሌላውን መናቅ መጨቆን የበታች አድርጎ ማየት” የሚል ትርጓሜ ሰጥቶታል።
እስኪ እራሳችሁን ፈትሹ⁉️

ፍልስፍና philosophy

10 Dec, 18:18


ጉድ ነዉ⁉️
••••••••
ሰሞኑን ለጓደኛየ የምስክርነት ቃል ለመስጠት ፍርድ ቤት ዳኛ ፊት ቀርቤ በየትኛው መፅሀፍ ነው የምትምለው አሉኝ ክቡር  ዳኛው መፅሀፍ ቅዱስ እና ቁርአን ከፊቴ ጠረምጴዛ ላይ ደርድረዉ አንዱ ላይ እጄን ጭኜ የምምል መስሎዋቸው ነበር!

አይ እኔ ሐይማኖት የሌለኝ ኢ-አማኝ ሞርሞን ስለሆንኩ ቅዱስ ቡክ ኦፍ ሞርሞን ( The Book of Mormon) አምጡና በሱ ልማል አልኩኝ በጭዋ ደምብ! ዳኛው ያልኳቸዉ  መፅሀፉ  ምን እንደሆነ እንኳን አያቁም ። ተቆጡና ትምል እንደሆነ ባንዱ ማል ግዜዬን አታጥፍ ።ብለው አፈጠጡብኝ!

እኔም በጣም ደሜ ፈላ እንዴ ታዳ ምን ያናድድሀል ይረጋጉ እንጂ ክቡር ፍርድ ቤት? በቃ እሱ ከሌለ ፍቅር እስከ መቃብር መፅሀፍ ላይ ቢሆንም  እጄን ጭኜ ልማል ስላቸው ከችሎቱ ግቢ በፖሊስ እብድ ነዉ ብለዉ ገፍትረው አባረሩኝ።

ጎበዝ ያየነው የሰማነውን መመስከር አልቻልንም እኮ!?

አልገባቸዉም እንጂ መፅሐፍ ቅዱስ፣ቁራን  ላይ እጅ መጫን እውነት ቢያናግር ኖሮ፣ መፅሐፍ  ላይ እጃቸውን ጭነው በማሃላ ስልጣን ያያዙት ወሮ በላ ነፍሰ ገዳይ የሀገራችን ባለ ስልጣናት ሁሉ የመብረቅ ሲሳይ ይሆኑ ነበር።

ፍልስፍና philosophy

09 Dec, 03:54


ሶቅራጠስ፡ «እውነት ኃይል ነው»

ፕሌቶ፡«እውነት ከኃይል በላይ አስፈላጊ ነው»

አርስቶትል፡ «እውነት በኃይል አይረጋገጥም»

ዲዮጋን፡ «እውነት በቂ ነው! »

ኤፒክቴተስ፡«እውነት ለመልካም ህይወት መሰረት ነው»

ዘረያዕቆብ፡ «እውነት ሁለንተናዊ ነው»

ቶማስ አኳይነስ፡«እውነት ከመልካምነት እና በጎነት ጋር የተቆራኘ ነው»

ኒቼ፡«ኃይል የፈለገውን እውነት ማድረግ ይችላል!»

ካንት፡«የሞራል ህግ ምክኑይ እውነት ነው»

ሾፐንሀወር፡«ፈቃደ ኃይል በሚዘውረው ሰው ልጅ ህይወት ውስጥ እውነት የደረጃ ልኬት ነው»

ፖል ሳርተር፡«የኃይልንም ጉልበት የእውነትንም ኃያልነት ከማንሳት በፊት መኖር ይቀድማል»

ሲኦራል፡«ለትርጉም አልባ ሕይወት እውነት ጊዜያዊ ውጤቷ ነው»

ዶስቶቭስኪ፡«እውነት ልዕለ ኃያል ነው»

ዴካርት፡«እውነት ራሷን ለማግኘት እውቀት እና ኃይል አስፈላጊ ቢሆንም ከስህተት ለማዳን ኃይል በእውቀት ሊገራ ይገባል»

አልበርት ካሙ፡«እውነት የማንደርስባት ነገርግን ተራራዋን መውጣት ያለብን ናት»

አለን ዋት፡«በእውነት ውስጥ ያለው እውቀት በኃይል ውስጥ ካለው እውቀት በላይ ተሻጋሪ ነው»

ማካቬሌ፡«እውነት ከፖለቲካዊ ኃይል በታች ነው»

ዳርዊን፡«ኃይል ያለው እውነትን ከያዘ በላይ ለህይወት የተገባ ነው »

ካፍካ፡«እውነት ኃይልን ለመቀየር እጅግ ብዙ መልፋት ይኖርበታል»

አየን ራንድ፡«እውነት ለሚፈልጓት ብቻ ናት»

ፉኮ፡«እውነት የኃይል ውጤት ነው!»

ሄግል፡«እውነት በአእምሮ የሚቀረፅ ነው»

ማርክስ፡«ኃይል እውነትን መደበቅ ይችላል»

ቮልቴር፡«እውነት የሚገኘው ሁሉንም ነገር በመጠየቅ ብቻ ነው እናም የማመዛዘን ሃይል ሁሉንም ኃይል ለመቃወም መዋል አለበት»

በርናልድ ረስል፡«የፍልስፍና ዋጋ እውነት ነው»

ፍልስፍና philosophy

08 Dec, 08:17


ያኔ ሐይማኖተኛ ሳለሁ የነፍስ አባቴ ሳይቀር "ስካርህን ካላቆምክ አልባርክህም "እግዜር ያውጣህ!" ብለው ለቁም ገሃነም ጥለውኝ ሄደዋል...!
የሚገርመው ነገር ግን ከኔ በፊት እሳቸው ቀድመው ሞቱ⁉️

ፍልስፍና philosophy

04 Dec, 15:09


የአዲስ አበባን ህዝብ አትመነው⁉️
•••••••••••••••••••••••••••••
የአዲስ አበባ ህዝብ አጨብጫቢ ነው። የፖለቲካ ፍልስፍና ምን እንደሆነ አያውቅም። ነገር ግን ፖለቲከኛ ሲታሰር ይጮሀል። ሲፈታ ይቦርቃል። የአዲስ አበባ ህዝብ አጨብጫቢ ነው።  መሪዎች ከስልጣን ሲወርዱ እያጨበጨበ ይሸኛቸዋል። ሌላው ስልጣን ላይ ሲወጣ ያጨብጭባል። አንድ ሰሞን ለፓስተር ዐብይ ሲያጨበጭብ ነበር ዛሬ ዞሮ ደም እያለቀሰ ነው!

አጨብጭቦ የተቀበለው ከስልጣን ሲወርድ እንደገና አጨብጭቦ ይሸኘዋል። የአዲስ አበባ ህዝብ አትመነው። የአእምሮውን ዝገት የሚያፀዳው በእጁ ጭብጨባ ነው።

የአዲስ አበባ ህዝብ ወሬኛ ነው። ቱሪናፋ ነው። የሚያወራልህ መረጃ ለማስተላለፍ አይደለም። የወሬ ሱሱን ሊወጣብህ ነው። እንድትረዳለት የሚፈልገው እሱ ራሱ ያልተረዳውን ነው። የሚያሳውቅህ እሱ በሚገባ ያላወቀውን የተሳሳተ እውቀት ነው።

የአዲስ አበባ ህዝብ ባለጌ ነው። ጥፍራም። የአዲስ አበባ ወጣት ብሄር የለኝም ይልሀል። ግን ዞሮ  ትግሬውን ፂላ ብሎ ያገላል አማራውን ሎተሪ አዙሮ ሰርቶ በበላ ቆምጬ ኦሮሞውን አርሶ ባበላው ቦቲያም ጋላ ጉራጌው ከሱ ተሽሎ ጫማ ጠርጎ ገንዘቡን በአግባቡ ስለቆጠበ ስግብግብ ብሎ ይሳደባል።

የአዲስ አበባ ወጣት ኢትዮጵያዊ አይደለም። ብሄር የለው። ኦሮሞ አትለው ትግሬ። አማራ አትለው ጉራጌ። የአዲስ አበባ ማንነት የለውም። የአዲስ አበባ ወጣት የብሔር ፌዴራሊዝም እየተቸ ግን ያልታወቀበት እጅግ በጣም ሲበዛ ዘረኛ ነው።

የአዲስ አበባ ወጣት የመንግስት ባለስልጣናት ሲሳደብ ይውልና እነ ሰይፉ ፋንታሁንን ሴሌብሪቲ ያመልካል። የልማት ታጋይ ጠልቶ ዘፋኝ አዝማሪ የሚወድ ፣ የፊዚክስና ማትስ ፍልስፍና አስተማሪውን አልሰማም ብሎ ገጣሚ እና ቧልት ፀሀፊ እውቀት ሰጠኝ ብሎ የሚመፃደቅ ከብት ትውልድ ነው።

የአዲስ አበባ ህዝብ በላተኛ ህዝብ ነው። ከድሮ ጀምሮ እዚች አገር ላይ የአዲስ አበባ ህዝብ ከመብላት ውጪ የጨመረው እሴት የለም። የአዲስ አበባ ህዝብ ትልቁ እሴት መብላት ብቻ ነው። ገበሬ ያመርታል እሱ ይበላል። መንግስት ቀለበት መንገድ ይሰራል።ባለሀብቱ ሲሽከረከር ይውላል።  እግረኛው ዜብራ እያለለት በብረት ላይ ሲዘል ይውላል። ከዛ በኋላኮ አያፍርም። የሆነ ነገር ሲጎድልበት እሱ ከመብላት ውጪ  ምንም አስተዋፅኦ ያለደረገበት ጉዳይ ላይ አንደኛ መብት ጠያቂ ይሆናል።

የዚች አገር ውድቀት መነሻ የአዲስ ህዝብ ነው። እንዳታየው ሾካካ ነው። እንዳታምነው አስመሳይ ነው። እንዳትቀርበው ከአንተ ወደ ኋላ በጣም የራቀ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ ካልጠፋ የዚች አገር ችግር ይቀረፋል ማለት ዘበት ነው።

ፍልስፍና philosophy

03 Dec, 05:06


ባለቤትሽ ለእንቅልፍ በተኛበት ውድቅት ሌሊት ተነስተሽ ፓስዋርዱን ሰርቀሽ ስልኩን ትጎረጉሪያለሽ? ነገር ግን የልጆችሽን ቦርሳ ፈትሸሽ የቤት ስራቸውን ለመስራት ስንፍናሽ መከራ ነው?
የኔ እመቤት በጣም የምታሳዝኝ ሴት ነሽ!

ፍልስፍና philosophy

30 Nov, 10:31


አስተውል⁉️
•••••••••
ትላንት እርቃናችንን ዛሬም እርቃናችንን!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሰው ልጅ ድክመት የፈጣሪን አላማ ቀለበሰ፡፡
ሰው እውነትን የመሸከም አቅም የለውም፡፡ ስለዚህ ፈጣሪ እውነተኛውን ደስታ ትቶ ሰው መኖር የሚፈልገውን መከራ አሸከመው፡፡ ሰውም በሆነው ሳይሆን መሆን በሚፈልገው መኖር ሲጀምር እርቃኑን መንዘላዘል ጀመረ፡፡ ትናንት ስንፈጠር እርቃናችንን ነበርን ፡፡ ዛሬም ስንኖር እርቃናችንን ነን፡፡

ሁለቱ ግን አንድ አይነት ገላ አይደሉም፡፡ የመጀመሪያው በፈጣሪ የተሰጠ ትክክለኛ ገላ ነበር፡፡ ሁለተኛው ግን የሚያሳክክ ገላ ሆነ፡፡ አዳም በራሱ የብቃት ችግር ገላውን መኖር ቢያቅተው ኢዮብ በመከራ እከክ ለብሶ ለዘመናት ኖረ፡፡  ገላውን ያገኘው ትክክለኛ ማንነቱን ፍለጋ እርቃኑን ሲንከራተት ነው፡፡ እከክ የለበሰ ገላ ቆዳው በጥፍር የተገፈፈበት የሞራ እርቃንነት ነው፡፡ ገላ ከነማንነቱ የሰው ልጅ የክብር ውበት ነው፡፡ ብዙ ሰው ማንነነት ብሎ የተቀበለው የሆነውን ሳይሆን የመሰለውን ነው፡፡ “ሰው  በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠረ”  ብሎ ሲስብክ የነበረ ፓስተር ከሰበከበት ፑልፒት ላይ ሲወርድ “ አይ! የሰው ልጅማ ድሀ ነው” ይላል፡፡ በአንድ ቤተክርስቲያን ሁለት የተለያየ እውነት፡፡ ፑልፒቱ ጋር ሌላ እውነት፣  ለአግዳሚ ወንበር ሌላ እውነት፡፡ በእግዚአብሔር አምሳል ቢፈጠርም ሀብቱ እግዚአብሔር ጋር እንጂ ሰውየው ጋር አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው በሀብታም ፈጣሪ አምሳል ቢፈጠርም እርሱ ግን ድሀ ነው፡፡ ስለዚህ ችግሩ የአምሳያው ሳይሆን የኦርጂናሉ ነው ማለት ነው?

ሰው ሲፈጠር እርቃኑን ነበረ፡፡ ልብስ ቢያስፈልግ ኖሮ እግዚአብሔር ለአዳም ቆዳው ላይ ጂንስ ለጥፎ መፍጠር አቅትቶ ነው?? ትክክለኛ ማንነነት ከእከክ ድሪቶ የተሻለ ነው፡፡ የሠው ልጅ የሚያከው ገላ ካልኖረው “እርቃኔን ነኝ” ይላል፡፡ እርቃን የመሆን የማንነነት ንፅህና ለምን ይፈራል?? ሰው እውነትን የሚሸከምበት የስሜት አቅም የለውም፡፡ ያጎጠጎጠ ጡት ካየ ልናከስ ይላል፡፡ ዳሌ ሲመለከት ልጠልጠል ይላል፡፡ ስለዚህ ውሻው ራሱን መቆጣጠር ካልቻለ ተፈጥሮን መሸፈን አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ፡፡ እንጂማ ስሜቱን መቆጣጠር የሚችል አርፎ የሚቀመጥ ውሻ ባይበዛ ጡትና ዳሌ የፈጣሪ እውነተኛ ፍጥሮች ነበሩ፡፡ ጡት መንጠልጠሉ፣ ዳሌ መውረግረጉ ስህተት ከሆነ የተሳሳተው የፈጠረው  እግዜር ነው፡፡

ችግሩ ይህ ነው፡፡ የሞራል ማንነነት የተፈጥሮ ማንነትን ሲሸፍን ሰው የአካሉን ትቶ የአሳቡን  መኖር ጀመረ፡፡ የሞራል ማንነት ከንቱ ስሜት የፈጠረው ነው፡፡ ፈላስፋው ሳርተ እንዳለው ነው፡፡ ካፌ ውስጥ ስትሰራ ሌላው ሰው የሚለውን ተፈጥሯዊ ማንነት ትቶ “ አስተናጋጅ”  የሚለውን የሞራል ማንነነት ይሰጥሀል፡፡ አንተም አምነህ ትቀበላለህ፡፡ ስለዚህ ሰው መሆንህ ቀርቶ የአስተናጋጅ ሕይወት ትኖራለህ፡፡ ለሌላው ማሸርገድ አጎንብሶ መሄድ ካልቻልክ የሞራል ማንነቱን ትነጠቃለህ፡፡ ሌላ የማንነነት አማራጭ ነበረ፡፡ ሰው ግን መረዳ አልቻለም፡፡

ችግሩ ሌላ ነው፡፡ መፍትሄው ሌላ ነው፡፡ ለችግሩ መፍትሄ የተባለው በራሱ ሌላ ችግር ነው፡፡   ሰው ቤተክርስቲያን ሲገባ ልብስ የሚመረጠው እግዜር በውበት እንዳይወሰወስ ነው??  ወይስ የእሱ ፍጡር የሆነ ገላ የተሳሳተ  ነው??  ውበት አይቶ ማድነቅ መቻል የማን ፍጥረት ነው?? ይህ ሰው ሰራሽ የድሪቶ ማንነነት ነው፡፡ የዲማ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሚገኝበት መንደር ብዙ ድሀ ህዝብ መኖሩ ግን ሀፍረት አይደለም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኝበት መንደር ውስጥ በቀን ሶስት ጊዜ መብላት ያልቻለ ሰው መኖሩ ፀጋ ነው፡፡ ኩክየለሽ ማሪያም ያለችበት መንድር ውስጥ ለ3ሺ አመት በአንድ መርፌ እየጫረ የሚያርስ ገበሬ መኖሩ ነውር አይደለም፡፡ እስኪ ወደ ዉጪ ተመልከቱ፡፡  በግብፅ አሌክሳንደሪያ ቤተ መፀሀፍት ባለበት መንደር ውስጥ ድሀ የለም፡፡ በእንግሊዝ ዩንቨርስቲ በሚገኝበት የገጠር መንደር ለማኝ የለም፡፡ ስለዚህ የትኛው እርቃንነት ነው የሚያሳፍረው??  እግዜር የሰጠንን “መሆን” ሆኖ መኖር ወይስ እከክ ድሪቶ መደረብ??

ፍልስፍና philosophy

28 Nov, 10:13


ሶስቱ የነፃነት መንገዶች
(ግመል፣አንበሳ፣ህፃን)
ኒቼ

አንተ ታላቅ ነህ ራስህንስ ስለምን ከመንጋዎች መሃል ትፈልገዋለህ? ሰዎች ባሰመሩልህ መስመር ላይስ ስለምን ትኖራለህ? ከልጅነትህ እስካሁን የተነገሩህ እና የተጻፉልህን ትርጓሜዎችን መርመራቸው ፤  አውላላ ሜዳ ላይ የታሰሩ መስሏቸው ከቆሙ በጎች ጋርስ ምን ታደርጋለህ?
መንጋዎች መነጠልን አይፈልጉም፤ በራሳቸውም የሚወስኑት ውሳኔ የለም - እንዲሁ ከመንጋው ጋር በመጓዝ ደህንነታቸውን (ምቾታቸውን)ማስጠበቅ ብቻ ይፈልጋሉ፡፡

መንጋዎች አብረው አንድ ላይ ይሰበሰባሉ፤ ለእነሱ መልካም የሆነውን እንዲያሳያቸውም እረኛውን ይከተሉታል፡ ከመንጋው ተነጥለህ ነጻነትህን ማወጅ ከፈለግኽ መንገድህ ይህ ነው - ግመል - አንበሳ - ህጻን


ግመል - (እውቀትን፣ እውነት እና ጥበብን ፍለጋ)

አንዳንድ ሰዎች እንደ በግ መንጋው ውስጥ አይወሸቁም፤ ሃላፊነትንም ከመሸከም አይሸሹም፤ በሃሩር በረሃ ውስጥ ከባድ ሸክምን ተሸክመው ያልፋሉ፡፡ በመንጋ ቢጓዙም፣ ሸክሙ የየግላቸው ነው፡፡ ማንም ግመል የሌላኛውን ሃላፊነት ሸክም አይጋራም፡፡ የመጀመሪያው የነጻነት መንገድ “ግመል" መሆን ነው፡፡
ግመል መሆን የምንጀምረው እውነታውን ከመጋፈጥ ነው። እውቀትን እና ጥበብን ከእያንዳንዱ ጥጋት መለቃቀም  ጀምር፤ እውነታውንም እወቅ፡፡ ግመል እንዲህ ይጠይቃል፡-

“ምን ያህል ይከብዳል፣ ከባዱና ሊያስደስተኝ የሚችለው ሸክምስ የትኛው ነው?

ታላቁን ሸክም መሸከም ይኖርብናል፤ የግመል መንፈስ ደስታውን የሚያገኘው በጥንካሬው ውስጥ ነው፡፡ ከባዱን ሸክም እንደተሸከመ ወደ በረሃው ይጣደፋል፡፡ ከባድ ሃላፊነቶች ታላቅ እና መልካም ናቸው። ሸክማችን በበዛ ቁጥር ማወቃችን ይጨምራል ግመል- ሕይወት ከእርሱ ላይ የምትወረውራቸውን ነገሮች (ፍርሃት፤ አስፈሪ እውነት፤ ፍቅር ወዘተ) መቻል ይኖርበታል።


አንበሳ - (ማድረግ እችላለሁ)

አዲሱ ማንነት በረሃውን መቆጣጠር እና መምራት ይኖርበታል፤ ነገር ግን ይህን ለማድረግ ከግዙፍ እና አስፈሪ ድራጎን ጋር መጋፈጥ አለበት፡፡ የድራገኑም ስም “ይህን አድርግ/አታድርግ” ይባላል። ድራገኑ እውነተኛ ነጻነትን እንዳታገኝ ይጋርድሃል።

“ይህን አድርግ/አታድርግ” ማህበረሰቡ ያስቀመጠልህ መስመሮች ናቸው፡፡ እንዴትም መሆን እና ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነግሩሃል። ይህ ዋናው ጠላትህ ነው፤ ድራጎኑንም ልትገድለውም ይገባሃል።

አንበሳው በድራገኑ ፊት በቀረበ ጊዜ “እችላለሁ፤ አደርገዋለሁም” አለው። ድራገኑም መልሶ “ማንም እንደዚህ አድርጎ አያውቅም፤ አንተ ማነህና ነው?
አንበሳው ነጻነቱን ለማግኘት የበረሃውን ድራጎን ማሸነፍ ይኖርበታል።
አጓራ “እኔ ማንም አይደለሁም፤ እንዲሁ ያለፍቃዴ የተጫነብኝን ስርዓት አልቀበልም”

ኒቼ ይህንን The Sacred No' (ቅዱስ አይ) ይለዋል፡፡ አይነኬ ተብለው በማህበረሰቡ ውስጥ የተቀመጡ ህግ፣ ደንብ ወግ እና ባህሎችን ይቃወማል።ማንም ቢሆን የሚመሩትን የራሱን ስርዓት እና ደንቦች ለራሱ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ አይሆንም እያሉ ድራጎኑን በመፋለም ሂደት ውስጥ ደስታ
የለም፤ ሆኖም ነጻነትን የፈለገ የግድ ይህን ማድረግ ይኖርበታል::

ህጻን - (አዲስ ጅማሮ)

አሁን ፍቃድህ ባንተ እጅ ነው᎓᎓ ድራጎኑ ሞቷል፡፡
አንዲት ከተማን አስብ - በዚህች ከተማ ውስጥ ህግ፣ ስርዓት፣ ደንብ እና ወግ የሚባሉ ማሰሪያዎች የሉም፡፡ ሁሉም እንደየራሱ ይኖራል:: ይህቺ ከተማ ማንን ትወክላለች? ምንስ የሚሆንባት ይመስልሃል?
ከተማዋ የህጻናት ከተማ ናት፤ ህግን የማያውቁ ህጻናት እንዲሁ ተፈጥሮ እንዳዘዘቻቸው የሚኖሩ ህጻናት ሞልተውባታል፡፡

ኒቼ ይህንን The Sacred Yes” (ቅዱስ አዎ) ይለዋል፡፡
“ህጻናት ንጹህ እና ዝንጉ ናቸው፡፡ አዲስ ጅማሮ፣ አዲስ ጨዋታ በራሱ የሚሽከረከር ጎማ፣ የተቀደሰ አዎ”

እውነተኛ ነጻነት ያለው በጫወታ ውስጥ ባሉ ህጻናት ላይ ነው ይለናል ኒቼ። ህጻናት ዓለምን ከማንም አልተረከቧትም፡፡ በአግራሞት እና አዲስ ነገርን በመፈለግ ውስጥም ይኖራሉ፡፡ ህጻን በሚያደርጋቸው ተግባራት ውስጥ ትርጉሞችን በራሳቸው ፍቃድ ይፈልጋሉ፡፡ ማንም ሕይወት እንዲህ ናት፣ ዓለም ይህቺ ናት ብሎም የተረጎመላቸው የለም፡፡
ሰው-ማህበረሰቡ የሰጠውን ሁሉንም
ትርጓሜዎች አልቀበልም (The
Sacred No) ካለ በኋላ፣ ሕይወት የምትሰጠውን ትርጉም ይቀበላል (The Sacred Yes) የራሱን ህግ እና ደንቦች ያረቃል፤ የራሱን እሴቶች ይገነባል᎓᎓ ተፈጥሯዊ የሆነውን ማንነቱንም ይኖራል፡፡

በኒቼ ፍልስፍና ሰው ነፃነቱን ከፈለገ ከግመልነት ጀምሮ ህፃን እስኪሆን ድረስ መጓዝ ይኖርበታል።


መፅሀፍ-የፍልስፍና ማዕድ

ፍልስፍና philosophy

23 Nov, 20:30


በጣም ናፈቁኝ⁉️
••••••••••••••
ኢትዮጵያዊውን የገደለው ፣  ይሄን ቡኒ ህዝብ " ድሀ ነህ፣ ለማኝ ነህ፣ ደደብ ያልተማርክ ነህ፣ ኋላቀር ነህ" ብሎ ግልፁን የሚነግረው ሙሁር ጠሀፊ ስለሌለ ነው። ሌላው ቢቀር  በኢህአዴግ የትምህርት ፖሊሲ ፕሮፌሰር የሆነ ሙሁር ህዝቡን እየደለለ የሚኖር መሀይም ነው።

እኔ ሳይማር ያስተማረኝን ህዝብ ካልተማረ ትክክል ነህ አልለውም። ድሀ ከሆነ ሀብታም ነህ አልለለውም። በፍፁም። ሊያገለኝ ይችላል። የዊስኪ መጠጫ ባጣ አረቄ ጠጥቼ እተኛለሁ እንጂ ዊስኪ ልጠጣ ብዬ ያልሆነውን በመንገር አልደልለውም።

የኢትዮጵያ የደን ሀብት ቁልቁል ተመናምኖ ድሮ በየ 10 አመቱ ይከሰት የነበረ የዝናብ እጥረት ድርቅ ዘንድሮ ግን በየ ሁለት አመቱ ይከሰታል! ለምለሚቱ አገሬ እያለ ግጥም የሚሰልቅ ደደብ ደራሲ ለኔ ጣሳ ራስ ነው!

እኔ የምበላው ባጣ ፒያሳ አደባባይ ላይ ጨው እየላስኩ እኖራለሁ እንጂ ደንቆሮን ትሰማለህ አልልም።

በፍፁም! የአበሻ ሙሁር ታሪክ ከመጠየቅ የአክሱም ሀውልትን ማናገር ይሻላል። ቢያንስ አበሻ ሙሁር እያስመሰለ ከሚዋሽህ የድንጋይ ዝምታ የሚነገርህ እውነት ይሻላል።

የኢትዮጵያ ሙሁራን እነ ብላታ፣ የነፊታዉራሪ ልጆች፣ እነዚያ ለመጀመሪያ ጊዜ አሜሪካን የሄዱት በመጀመሪያ ስደት እውቀታቸው ተልክቶ አዋቂ የተባሉት ፣ ለህዝባቸው ጥገኝነትን አስተምረው ለማኝ ህብረተሰብ የፈጠሩት የኢትዮጵያ ሙሁራን፣ ቁጥብነትን አስርፀው በአገር ጉዳይ ላይ የህዝብ ተሳትፎን የሸረሸሩት ፣ ሰማያዊ አላማ እንጂ ምድራዊ ራዕይ የሌላቸው፣ ለነጭ መላዓክት ሲሰግዱ ፣ ሰውነት የከዳቸው፣ ያልባላቸውን ሲያኩ ማንነታቸውን የላጡት የኢትዮጵያ ሙሁራን..እነዚያ ሙሁራን ድጓ ተምረው ፣ ቅኔ ዘርፈው ፣ የቆሎ ተማሪ ተብለው ፣ የተማሩትን ንድፈ ሀሳብ ስንዴ ቆሎ በመለመን ወደ ተግባር የቀየሩ ጂኒየሶች፣ ስምንት ቋንቋ ተምረው አንድም ሳይናገሩ የሞቱት ፣ በቀለም የጠገበ ብዕራቸውን ያባከኑ ፣ የተራበ ህዝብን ስራ ሳይሆን  ልመና ያስተማሩ ዛሬ አዉሮፓና አሜሪካ የሚገኙት የኢትዮጵያ ሙሁራኖች፣ ምን ሆኑ? በጣም ናፈቁኝ!

ፍልስፍና philosophy

23 Nov, 15:10


ፈላስፋዉ ጭሰኛ ማን ነዉ⁉️
•••••••••••••••••••••••••
በህይወቴ በነበረው የኑሮ ሂደት በደመ ነፍስ ከፈጠርኳቸው የህይወት መርሆች በሌላው ዘንድ እንደ እብድ መጥፎ ቢታዩም ለኔ ግን ጠቅመውኛል፡፡ የምኖረው ህይወቴን ሆን ብዬ በማዝረክረክ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ህይወት እኔ ጋር ሁልጊዜ አዲስ ናት ፡፡ ምክንያቱም ህይወቴን የማዝረከርከው አሮጌውን በድጋሜ አስተካክዬ አዲስ ነገር ለመፍጠር ነው፡፡ ከእውነት አንፃር አዲስ ነገር የለም፡፡ ሁሉም አስቀድሞ የተፈጠረ ነው፡፡ አዲስ ነገር በሌለበት አለም እየኖርን ግን በህይወት ለመቆየት አዲስ ነገር ያስፈልጋል፡፡ አዲስ ህይወት ከሌለ ሊኖር የሚችለው ሞት ነው፡፡ ስለዚህ እንደመፍትሔ የወሰድኩት ሁል ጊዜ የምኖረው አንድ አሮጌ ህይወትን በማዘበራረቅ በተለያዬ መንገድ በማስተካከል ነው፡፡

ሁልጊዜ ገንዘብ ካለኝ ህይወት አስልቺ ነው፡፡ አስልቺ ከሆነ እየተሞትኩ ነው፡፡ ምክንያቱም እድሜ ማለት አመታት መጨመር ሳይሆን ብዙ አዳዲስ ህይወቶችን መኖር መቻል በመሆኑ ነው፡፡  ስለዚህ ላለመሞት አዲስ ህይወት መኖር አለብኝ ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ ማግኘት አሰልቺ ከሆነ ማግኘቴ ሲዘበራረቅ አጣለሁ ፡፡ ያጣሁትን ሳገኝ እንደገና አዲስ ህይወት እኖራለሁ፡፡ ያገኘሁትን ሳጣው እንደገና አዲስ ህይወት እኖራለሁ፡፡ እንግዲህ አለም አሮጌ ከሆነች አዲስ ህይወት ያለው የደስታና ስቃይ ቅንብር ላይ ነው ማለት ነው፡፡ ኤፒከረሳዊያን እንደሚያምኑት ነገ ለመደሰት ዛሬን በስቃይ ትኖራለህ፡፡ እየቆጠብክ ካልኖርከው ደስታም ያልቃል፡፡ የዚህ ጊዜ ህይወት ትርጉም አልባ ሆኖ አስልቺ ይሆናል፡፡ ያለመኖርም ስሜት ይፈጠራል፡፡ ያለመኖሩ ስሜት ከንቱነት ነው፡፡ ሁሉም ነገር አሮጌ ሆኖ አዲስ ህይወት ሲጠፋ ሰው በቁሙ ይሞታል፡፡ ከንቱነት ይኼ ነው፡፡ በቁም ላለመሞት አዲስ ህይወት አስፈላጊ ከሆነ መንገዱ አንድ ነው፡፡ አሮጌውን እያዘበራረቁ በማስተካከል እንደ አዲስ መኖር፡፡

ደንታ ቢስ ነኝ፡፡ሰዎች ቸልተኛ መሆን እንደሌለብኝ ይመክሩኛል፡፡ ለምን የሚለው ላይ ግን የኔ አርጊውመንት ከነሱ የተሻለ ነው፡፡ የነሱ አርጊውመንት ደንታ ቢስ ከሆንክ ትጎዳለህ ነው፡፡ የኔ አርጊውመንት ደግሞ እስከአሁን ያልተጎዳሁት ደንታ ቢስ በመሆኔ ነው ፡፡ የሁሉታችንም መደምደሚያ አለመጎዳት ከሆነ ደንታ ቢስ የሆንኩት ላለመጎዳት ነው፡፡ በእርግጥም ቸልተኛ መሆኔ ከብዙ ጉዳት ጠብቆኛል፡፡ በደል በበዛበት የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ እየኖርኩ እንደተበደልኩ አይሰማኝም፡፡ ካልተሰማኝ አልተጎዳሁም፡፡ ክህደት የእምነት ማጠንከሪያ በሆነበት ማህበረሰብ ውስጥ ብኖርም መካዴ ክህደት አልሆነም፡፡ እያመንኩት የሚክደኝ ጓደኛ ቢኖር ለኔ ክህደት አይደለም፡፡ አደራውን ከበላ ለሱ ሸክም ፣ ለኔ ደግሞ ችግር የመገላገል ያህል ነው፡፡ እኔ እንደተካድኩ ስለማይሰማኝ ከስቃይ ነፃ ነኝ፡፡ የስሜት ሸከሙ ከባድ የሚሆነው አደራ ለሰጠ ሳይሆን አደራውን ለተሸከመ ነው፡፡ ቢጉዳኝም፣ ስሜቱን ካልፈጠርኩ አልጎዳም።

ገንዘብ ቢነጥቁኝ እንደተቀማሁ አይሰማኝም፡፡ ባጣ የማጣት ስሜት የለም፡፡ ምክንያቱም መጀመሪያም እንዳገኘሁ አይሰማኝም፡፡ ካልተሰማኝ አላጣውም፡፡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመዋሸት እና በማጭበርበር የሞራል ህይወት መኖር የምችልበት ሰፊ እድል ነበር፡፡ ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ ቅንጦት ስቃይ ሆነ፡፡ የሚያስደስተኝ በስቃይ ውስጥ በማለፍ የሚገኝ እርካታ ሆነና የሞራል ህይወት ለኔ ወይ የማልመጥነው ፣ ወይ የማይመጥነኝ ኑሮ ሆነ፡፡ በዚህ የተነሳ በደመ ነፍስ ያዳበርኩት ልማድ ምን ሆነ ??  ደስተኛ ህይወት ለመኖር በስቃይ ውስጥ ማለፍ፡፡ ስቃዩ ሲያቆም ደስተኛ ህይወት መጀመር , ደስተኛ ህይወት ሲያቆም እንደገና መሰቃየት …

ምንም የለኝም፡፡ ምንም የሌለኝ ከሌላ ሰው ስለተለየሁ አይደለም፡፡ ቢጠፋ ቢጠፋ እንደሌላው ሰው እንዳለው ሆኖ መታየት አያቅተኝም፡፡ ምንም የሌለኝ ግን ምንም ስለማልፈልግ ነው፡፡ አሁን ያለኝ ፈልጌው የመጣ አይደለም፡፡ ከመጣ በኋላ እኔ የፈለኩት ነው፡፡ ካልመጣ አልፈልገውም፡፡ እኔ ጋር ካልመጣ የማልፈልገው ደግሞ የማልፈልገውን ህይወት መኖር ስለማልፈልግ ነው፡፡  ስለዚህ ምንም ባይኖረኝ ድሃ እንደሆንኩ አይሰማኝም፡፡  በመሰረቱ ድሃ የሚባል ሰው የለም፡፡ ሀብታም የሚባል ሰው የለም፡፡ ምክንያቱ፡  ድሀ የሚባል ሰው የለም፡፡ ሀብታምና ድሃ የሚል ክፍፍል የተፈጠረው በሰዎች  የተሳሳተ ግምት ነው፡፡

ሰዎች ከቁስ ሀብት ውጪ የሆነውን ሀብት መረዳት የሚችል  ብቃት የላቸውም፡፡ በዚህ የተነሳ  ዋጋውን መረዳት  የቻሉት የቁስ ሀብት ያለው ሲሆን የሀብቱን ዋጋ መረዳት ያልቻሉት ደግሞ ድሃ ነው፡፡ ለሀብታሙ ዋጋ እንደሰጠነው ፣ ለድሀውም ዋጋ መስጠት ብንችል የሰው ልጅ በሙሉ ሀብታም ነው፡፡   በዚህ መሰረት ስለቸገረህ የሚሰጡህ ሰዎች መልካም ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም መቸገርህ መጥፎ ከሆነ እንዳትቸገር ማድረጋቸው መልካም በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ የተለዩ ሰዎች ደግሞ መኖራቸውን አስተዋልኩ፡፡

እነዚህ ሰዎች የሆነ ነገር የሚሰጡህ ስለቸገረህ አይደለም፡፡ አንተ ጋር ያለውን ሀብት ትልቅ ዋጋ ሰጥተው ነው፡፡ የሚሰጡህ ምክንያት ስለቸገረህ አለመሆኑ ለምን መሰለህ ?? መጀመሪያም የቸገረህ ችግረኛ ስለሆንክ ሳይሆን የአንተን ሀብት ዋጋ መስጠት የሚችል ሰው ያለመኖሩ ችግር አስቸግሮህ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ቸግሮህ የሰጡህም መልካም ሰዎች ፣ ዋጋህ ገብቷቸውም የረዱህ ትክክለኛ ሰዎች  ናቸው- መመስገን አለባቸው!

ይቀጥላል...

ፍልስፍና philosophy

21 Nov, 07:27


በጊዜ ወደ ኋላ መመለስ (Time machine)

አብዛኛዎቹ ፈላስፎች ጊዜ ቀጣይነት ያለው ነገር እንደሆነ ይስማማሉ፣ እንዲሁ ደስ ባለው ጊዜም የሚቋረጥ እና የሚቀጥልም ነገር አይደለም፡፡ እናም ወደፊት ብቻም ይተማል እንጂ ወደ ኋላ አይመለስም፡፡ ቁርስ ላይ እንቁላል ፍርፍር ለመስራት የሰበርከው እንቁላል፣ ተመልሶ ያልተሰበረ እንቁላል አይሆንም፤ ጊዜ ምንም ያህል ወደ ኋላ እንዲመለስልን ብንፈልግም፣ አይመለስም፡፡

በጊዜ ወደ ፊት መሄድ ከፈለግን በሰከንዶች እና በቅጽበቶች መጓዝ ይቻላል። ለዚህም እኔ እና አንተ ምስክር ነን፤ ትናንትናም ከነበርንበት የጊዜ ስፍራ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ በጊዜ ወደ ኋላ መመለስ እንዲሁ በተግባር ከባድ ቢሆንም፣ በሳይንሳዊ ጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ይቻላል፡፡ ሆኖም ትኩረታችን ፍልስፍና ላይ ነውና ሳይንሱን እንደተከደነ እንተወው፡፡

ሳይንስ ያለው እውነት ቢሆን እና በጊዜ ወደ ኋላ መመለስ አልያም ወደ ፊት መሄድ ብንችል ምን አይነት አጣብቂኝ ውስጥ እንገባለን? የሚለውን ከፍልስፍና አንጻር የተለያዩ ሁለት ምሳሌዎችን በመስጠት እንመርምር፡፡

የአያት አያዎ (The grandfather paradox)

“አንድ የጊዜ ተጓዥ በጊዜ ማሽን ወደ ኋላ አባቱ ከመወለዱ በፊት ወዳለ ጊዜ ተመለሰ፤ እናም አያቱን አገኘው፡፡ አያቱንም ገደለው፡፡"

በጊዜ ወደ ኋላ ተመልሰህ አያትህን ብትገድለው ምን የሚከሰት ይመስልሃል? አባትህ አይወለድም፤ አባትህ ካልተወለደም አንተ አትወለድም፡፡ ተቃርኖው የሚነሳው አንተ ባለመወለድህ ላይ አይደለም።

አንተ ካልተወለድክ ምን ይከሰታል? የሚለው ጥያቄ ውዥንበር ውስጥ ይከተናል፡፡ አንተ ካልተወለድክ ምን ይከሰታል?... የጊዜን ማሽን ተጠቅመህ ወደ ኋላ አትመለስም፡፡ ወደ ኋላ ካልተመለስክም አያትህን አትገድለውም፤ አያትህን ካልገደልከው፣ አባትህ ይወለዳል፤ አባትህ ከተወለደ ደግሞ አንተም ትወለዳለህ፤ አንተ ከተወለድክ የጊዜ ማሽን ተጠቅመህ ወደ ኋላ ትመለሳለህ... አያትህንም ትገድለዋለህ...። የማይፈታ እንቆቅልሻዊ አዙሪት ውስጥ ይከተናል።

አዙሪታዊ አያዎ (Bootstrap paradox)

ሰው ወይም ዕቃ አልያም መረጃን በጊዜ ወደ ኋላ መላክ ብንችልስ? ለምሳሌ ለደራሲ በዓሉ ግርማ፣ በጊዜ ወደ ኋላ ተመልሰህ “ኦሮማይ” የተባለውን መጽሐፉን ለራሱ ብትሰጠውስ? ይህንንም መጽሐፍ እንዳለ ምንም ሳይቀይር በስሙ ቢያሳትመው ምን ይፈጠራል? ኦሮማይን ማን ጻፈው? በአሉ ግርማ እንዳትል ለእሱም መጽሐፉን የሰጠኸው አንተ ነህ፡፡ እኔ ነኝ የጻፍኩትም እንዳትለኝ፣ ተጻፈ በበአሉ ግርማ የሚል መጽሐፍ ሶስት መቶ ብርህን ከፍለህ ገዛኸው እንጂ አንተ አልጻፍከውም። ብቻ ይህ ፓራዶክስ፣ ዞረህ ዞረህ መልስ የማታገኝበት ክብ አዙሪት ውስጥ ይከትሃል።

አዙሪታዊ አያዋ በምናባችንን ወደማናውቀው አለም ወስዶ የእውነታዎቻችንን መሰረት እንድንጠራጠር አድርጎናል፤ ያለፈውን እና የወደፊቱን ውስብስብ በሆነ ዳንስ ውስጥ... ወደፊት እና ወደኋላ እያልን፣ ጊዜ የማይሽረውን የበዓሉ ግርማን ኦሮማይን አጣቅሰን የፍልስፍና ተረካችን እንጨርሳለን። ራሳችንንም ያለፈውን፣ የአሁንና የወደፊቱ የሚገናኙበት መስቀለኛ መንገድ ላይም አግኝተነዋልም፡፡

የፍልስፍና ማዕድ

ፍልስፍና philosophy

19 Nov, 08:56


ይድረስ ለአቶ አክሱም‼️
••••••••••••••••••••
ይቅርታ ‘አቶ’ አልኩህ
ስልጣንህን አላውቅም
ዘመኑ ራቀና ስላንተ ሚናገር ሰው አላገኘሁም
ንጉስ ትሆን አሽከር
ጠቢብ ወይንስ ደደብ
ታሪክ አዋቂዎች ጠቢባን ብጠይቅ
አክሱም ማን ነው ብየ ብይዛቸው ላሳር
እሱማ ቁላ ነው የወሲብ ምሳሌ
የዛ ዘመን Big Dick የህንደኬ አሞሌ
ንግስቷን ያረካ የምትልሰው ሁሌ

የህንደኬ ባሏ ንጉሱ ሞተና
አልጋ ላይ ብታጣው ወሲቧ ቢጠና
ፍትወት ቢያሰቃያት ቢፈጃት እንደ እሳት
ባሪያዋን አክሱምን ላልጋ መረጠችው
ዙፋን ላይ፣ ምንጣፍ ላይ፣ አልጋ ላይ ጣለችው
ከታች ፣ ከላይ ፣ ከጎን ፣ ከኋላ ሰጠችው
ንግስቲቷ ረካች አመለጣት ሲቃ
ፍፁም ተማረከች ላሽከሯ ፎንቅቃ
ለዚ ውድ ባሪያ ዳምጦ ላባዘታት
ቂንጥሯን ፈግፍጎ ፈትጎ ላሸላት
አክሱም ለተባለው ጉልበተኛ ወጣት
ወሲብ ባይነት ባይነት ሰቶ ላማረጣት
ዝቅ ብላ ሰገደች አረገችው ጣዖት
አዋጅ አስነገረች ተላለፈ መልዕክት
ድንጋይ ተፈልፍሎ ተሰንጥቆ ዓለት
ለባሪያዋ ብልት እንዲሰራ ሃውልት
ውስጧን ለገሸረው ለዛ ግዙፍ ቁላ
ባ‘ልጋ አልበቃ ብሏት ቆሞ ልየው ብላ
           
ብለው ሊቃውንቶች ሳያፍሩ ቢነግሩኝ
ፈገግ አደረገኝ በጣሙን ገረመኝ
ጠቢባን ሰብስቤ ስላንተ ጠይቄ
አሁን ገና ቆጨኝ ፀፀተኝ ማወቄ
ዳር ድንበር ያሰፋህ መስለኸኝ ንጉሥ
ብልት ነበርክ እንዴ የተሰራህ ለ'እምስ?

ፍልስፍና philosophy

18 Nov, 07:23


ምክር ለሴቶች ከፈላስፋው ጭሰኛ⁉️
•••••••••••••••••••••••••••••••
ንገስተ ሳባ እስራኤል አገር ሄደች፡፡ ከሶሎሞን ጋር ወሲብ ፈፀመች፡፡ ከፈረንጅ ልጅ አርግዛ ተመለሰች ስሙንም ምኒልክ አለችው፡፡ ንግስተ ሳባ አገር ቤት ከሰራችው ታሪክ ይልቅ እንደ ስኬት የሚነገርላት ውጪ አገር ሄዳ የፈፀመችው ወሲብ ነው፡፡

የአሁኑ ትውልድ ሴቶቻችን የንግስተ ሳባን ታሪክ ሲማሩ ታሪክ የሚሰራው ውጪ አገር በመሄድ እና ከፈረንጅ ጋር በመዋሰብ እንደሆነ አወቁ፡፡ ስለዚህ ትዳር አገር ቤት የለም፡፡ ትዳር የሚገኘው አውሮጳ አሜሪካ በመሄድ ነው፡፡

በባዕድ አገር ልጅ ይወልዱና ዜግነቱን ከቀየሩ በኋላ " ልጄን ኢትዮጵያዊ አንዲሆን ቋንቋ እያስተማርኩት ነው ይላሉ"፡፡ ፈረንጅ አገር ፈረንጅ አግብታ ስለኖረች  "ጌታ እየረዳኝ ነው" ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ ከመሰረቱ ጌታ አይረዳም ማለት ነው?? 

ጉድ እኮ ነው! አዲስ አበባ ላይ በአገራዊ ኩራት ትዳር ከመመስረት ይልቅ ለንደን እና አትላንታ ላይ ነጭ አግብቶ በባርነት መኖር የህይወት ስኬት አድርገው የሚመለከቱ ብዙ ሳባዎች አሁንም እየተፈጠሩ ነው፡፡

ብዙ ሴቶች የሌላ ሰው ዓላማ ነው የሚያስፈፅሙት፡፡ የጎረቤቷን ሕይወት መድገም የምትፈልግ ነው በየቤቱ ያለችው፡፡ የወዳጅ ዘመዷን እቅድ ለመተግበር የምትሯሯጥ ብኩን ሴት ሀገሩን ሞልታዋለች፡፡ የራሷ ዓላማ፣ ግብ፣ ትልምና እቅድ ያላት ሴት ማግኘት አዳጋች ሆኗል፡፡ እንደ ‹‹እከሊት›› ነው መኖር የምትፈልገው፡፡ የሌላው ሰው ደስታ የእሷም ደስታ የሚሆን እየመሰላት የሕይወት ዘመኗን በሌላ ሰው የሕይወት ዘይቤ የምታባክን ነፍ ነች፡፡

ጓደኛዋ ሐብታም ባል ስላገባች እሷም በደንብ የማታውቀውንና የማትወደውን ሐብታም የምታገባ ኮልኮሌ ሴት ሞልታለች፡፡ የህይወት ዘመኗንና ደስታዋን በገንዘብ የምትሸጥ ቀላል ርካሽ ሴት በየሰፈሩ አለች፡፡ የሚያሳዝነው አብዛኛው ሴቶች የተመኙትን ገንዘብ ቢያገኙም ደስታ ግን የላቸውም፡፡ ብዙዎቹ ሴቶች የውሸት ሕይወት ነው የሚኖሩት፡፡ የባከነ ሕይወት! የከሠረ የሕይወት ዘመን!

ለዚህ ነው አንቺ ቅንዝራም ‹‹Your time is limited, so do not waste it living someone else’s life ስሚኝ አዎ ዕድሜሽ ውስን ነው! የሌላ ሰውን ኑሮ በመኖር የህይወት ዘመንሽን አታባክኚው፡፡ የራስሽ ዓላማና ግብ ይኑርሽ! የሌላ ሰው ሕይወት እንደ ትምህርት ቤት ፈተና አይኮረጅም፡፡ የነውር ነውር ነው!››

ፍልስፍና philosophy

17 Nov, 12:00


ሴቶች ሲባሉ ገንዘብ ያለው ወንድ ብቻ ነው የሚወዱት አለኝ አንዱ ፎከታም ደደብ⁉️
እሰይ እንኳን ደግ አደረጉ እና ካንተ ጋር የድህነት ማሲንቆ ይገዝግዙ?ወይ አትማር ወይ ጠንክረህ አትሰራ ቁጭ ብሎ መቆዘም ብቻ ደንቆሮ ደደብ!

ፍልስፍና philosophy

17 Nov, 11:49


ማሳሰቢያ⁉️
••••••••••
Sorry to say this! እኔ የምፅፈው ለአንባቢ ብዬ  አይደለም። የምፅፈው የማሰብ ሱሴን ለመወጣት ነው። በዚህ ምክንያት በመጠንም በይዘትም አንባቢ ማንበብ የሚፈልገውንም የማይፈልገውን ፖስት አደርጋለሁ።

ከመጠን አንፃር ረጅም ፅሁፎች ፖስት አደርጋለሁ።  ከይዘት አንፃር ፖስት የማደርጋቸው የተለየ አስተሳሰብ የያዙ ፅሁፎችን ናቸው። እናም ብትችል በትዕግስት ብታነብ እወዳለሁ። ካልሆነ ይቅርብህ። በይዘታቸው የተለዬ አስተሳሰብ ያላቸውንም በአንድ ወቅት እንዳስቀመጥኩት " እፍፍ! እፍፍ!" እያልክ እያቀዘቀዝክ ብታነብ እመክራለሁ። ካልሆነ ተወው። ከዚህ ውጪ እኔ ለላይክ እና ለኮሜንት ጋጋታ ብዬ ፅፌ አላውቅም ወደ ፊትም አልፅፍም እኔ የምፅፈው ሀሳብ አእምሮዬን እየበላ ሲያሳክከኝ ነው።

ፅሁፎቼ ካልተመቸህ ይቅርብህ። የኔ ጌታ! በምድርም በሶሻል ሚድያም ተሳቅቄ አልችልም። በምድር የስጋ ፍላጎቴን እያረካሁ የምኖረው የሀብታም መኪና እንዳይገጨኝ ፣ ጥጋበኛ ባለስልጣን እንዳያስረኝ፣ የሴቶች ውበት እንዳይነድፈኝ  ተሳቅቄ በጥንቃቄ ነው የምኖረው።

ቴሌ ግራም  ላይ ግን በማሰቤ መሳቀቅ አልፈልግም። የምድር ላይ የስጋ ህይወቱን ትቼላችኋለሁ። ሶሻል ሚድያ  ላይ መሳቀቅ አልፈለግም። የፈለኩትን እንደፈለኩ እፅፋለሁ። ከተመቸህ ታነባለህ። ካልተመቸህ ብሎክ አድርገኝ። አሁንም ካልተመቸህ ስምህን ኮሜንት ላይ ፃፍልኝ ራሴ ብሎክ አደርግሀለሁ።

( በስጋም በማሰብም ህይወቴ ተሳቅቄ መኖር አልችልም።  ((ቢያንስ ቴሌግራም )) በአንዱማ  እኔም ሌላውን ማሳቀቅ እፈልጋለሁ። ማን ተሳቅቆ ማን ይቀራል!? )

ፍልስፍና philosophy

16 Nov, 19:21


መሳለሚያ ጋሽ ደበበ አረቄ ቤት ነኝ!
ኑ...? ቤት ያፈራትን ካቲካላ እንቃመስ? 🙂

ፍልስፍና philosophy

16 Nov, 19:13


📌የአማራ ልጆች የሀሰት ክስ⁉️

የጥንት አማራዎች የዮቶር ልጆች ናቸው። ዮቶር የዛሬ 5000 ዓመት ቤጌምድር የሚኖር በግ አርቢ ነው። ለንግድ እና ለተለያዩ ተግባራት ወደባህሩ በመጠጋት መንግሥታቸውን መሠረቱ። ይህም የደ አማት (ዘ አማራ) መንግሥት ነው። የመጀመሪያው ንጉሣቸውም አክናሁስ ይባላል። የግዛታቸው ድንበር እጅግ ሰፊ እየሆነ ሲመጣ የንጉሱ መጠሪያ ‘የአገር ሹም ‘ (አግ ሹም ፣ አክ ሹም በጊዜ ሂደት አክሱም) ይባል ነበር። ንጉሱ በዚህ ስም መጠራት የጀመሩት ክርስቶስ ሊወለድ 500 ዓመት ሲቀረው ነው። ስለዚህ ከ ሰሜን ቀይባሕር እስከ በናዲር (የአሁኑ ሞቃዲሾ ) የእነሱ ግዛት እንደነበር የታወቀነው።

ምጭ
Professor Richard Pokres
እናም
የአብይ አህመድ ብልጽግና መር መንግስት የሰሜኑን ጦርነት ካጠናቀቀ በኃላ ከፍተኛ ስጋት ያደረበት ከአማራ ሀይሎች ነበር በተለይም የአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖዎች በሰሜኑ ጦርነት ያሳዩት ጀግንነት መንግስትን እረፍት ነስቶታል::  ከጦርነቱ ማግስት ትጥቅ ለማስፈታት እና ልዩ ሀይሉን ለመበተን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የፀጥታ ግብረ ሀይል ተሰብስቦ በእቅዱ ላይ ቢስማማም አፈፃፀሙን ሊቃወሙ የሚችሉ ምሁራንን: ጋዜጠኞችን: ፖለቲከኞችን እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ቀድመን እንሰር ወይም እናሶግድ የሚል አማራጭ ቀረበ:: በመጨረሻም ገና ለገና ሊቃወሙን ይችላሉ በሚል እናሶግድ መባሉ ተገቢ አይደለም የሚለው ሀሳብ ተቀባይነት አግኝቶ የክልሉ መንግስት እና ብሔራዊ ደህንነት የሚታሰሩ ሰዎችን ስም ዝርዝር እንዲያቀርቡ በአቶ ፈቃዱ ፀጋ መሪነት ጠቅላይ አቃቤ ክስ እንዲያዘጋጅ የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ጌዲዮን ጢሞጢዎስ እንዲያስፈጽም ተደረገ::

የፌደራል ፖሊስ እና የደህንነቱ መስሪያ ቤት አፋኝ ግብረሀይል ከመጋቢት 22/2015 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ውድ የአማራ ልጆች ከየቤታቸው ታፍነው ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታጎሩ:: ቀሪዎች በገላን : በአዋሽ አርባ: በወታደራዊ ካምፖች እና በግል ሼዶች ተሰውረው ግፍ ተፈፀመባቸው::

የአማራ ተወላጆች ሀሰተኛ ክስ አናዘጋጅም በማለታቸው አቶ ፈቃዱ ፀጋ አማራ ያልሆኑ የጠቅላይ አቃቤ ህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ ከዚህ ቀደም ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች የተከሰሱበትን መዝገብ አገላብጣችሁ ዋስትና የሚያስከለክል ክስ አዘጋጁ 217 ሰዎች እንደሞቱ 297 ሰዎች እንደቆሰሉ ከ1ቢሊዮን በላይ ንብረት  ወድሟል ብላችሁ ክስ አዘጋጁ ይህንን ለመስራት የ45 ቀን አበል ተፈቅዷል ጊዮን ሆቴል ተቀምጣችሁ እንድትሰሩ አቶ ኢዮሲያድ አበጀ  ይህንን ቡድን እንዲመራ ተመደበ:: የምስክር ጉዳይ ሲነሳ አቶ ፈቃዱ አታስቡ እኔ አዘጋጃለሁ አላቸው::  በመጨረሻም ከ78 ቀን በኃላ እነ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ 309200 በሚል መደበኛ ክስ ተመሰረተ::

በመጨረሻ የአማራ ተወላጅ አቃቤ ህግ ባለሙያዎች የሀሰት ክሱን ይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ከአቶ ፈቃዱ ታዘዙ አቶ ፈቃዱም እሾህን በሾህ በሎ መቀለዱን ወስጣዋቂው  በቁጭት ተናግሯል::

በአቶ ፈቃዱ ፀጋ የተዘጋጀው የሀሰት ክስ በፍርድ ቤት እንዲሻሻል በህዳር 12/2016 ዓ.ም ቢታዘዝም  መዝገቡን በምክንያቶች በማሳገድ ለ1አመት ሙሉ አላሻሽልም በማለት  ቆይቶ በህዳር 3/2017 ዓ.ም አሻሽያለሁ በማለት እንዳዲስ ክሱን አስቀጠለ::

በተሻሻለው ክስ ተከሳሾች በእስር ላይ እያሉ የተገደሉ ሰዎችን በብሔር ግጭት በጅሌ ጥሙጋና አካባቢው በሸኔ እና በጁንታ የተገደሉትን እንዲሁም የቀድሞ አማራ ክልል ብልጽግና ሀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ 75 ሰዎች ገድላችኃል 48  ሰዎች አቁስላችኃል ከ1ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት አውድማችኃል በሎ አዲስ ክስ አሻሽሎ አመጣ::  የሚገርመው በፈቃዱ ፀጋ የተተካው አቶ ተስፋዬ ዳባ በወለጋ አንገር ጉትን በመከላከያና በሸኔ የተገደሉ 14 ሰዎችን ገድለዋል ብሎ ክሱ ውስጥ እንዲካተት አደረገ::

እጅግ የሚገርመው የአማራ ተወላጆች የተከሰሱባቸው 14ቱም መዝገቦች ከሰው ቁጥር መለያየት ውጭ ተመሳሳይ ክስ መሆናቸው ነው::  አቶ ተስፋዬ ዳባ ከዚህ በኃላ የሚመጡ የአማራ ተወላጆች ተመሳሳይ ክስ እንዲከሰሱ ትዕዛዝ አስተላልፏል::

ፍትህ ለአማሮች!!!

ፍልስፍና philosophy

15 Nov, 19:10


" ስለጋብቻ ምን ትላለህ"



"የተወለዳችሁት አብራችሁ ነው ። አብራችሁም ለዘለአለም ትኖራላችሁ ። የሞት ነጫጭ ክንፎች ቀናችሁን ባጨለሙባችሁ ጊዜም አብራችሁ ትሆናላችሁ።
አዎን ሌላው ቀርቶ በፀጥተኛው የእግዚአብሄር ዝክር ውስጥ እንኳ አብራችሁ ትኖራላችሁ…

"ነገር ግን በአብሮነታችሁ ውስጥ ክፍት ስፍራወች ይኑሩ ።
እርስ በእርስ ተፋቀሩ እንጂ የፍቅር ሰንሰለት አታብጁ። ይልቅስ በነፍሶቻችሁ ዳርቻዎች መካከል የሚንቀሳቀስ ባህር ይኑር…

"እርስ በእርሳችሁ ፅዋችሁን ተሞላሉ እንጂ ከአንድ ፅዋ አትጠጡ ።
ከዳቦወቻችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ ስጡ እንጂ ከአንድ ቁራሽ ዳቦ አትብሉ ። በአንድነት ዘምሩ፣ በአንድነት ጨፍሩ ።
ደስም ይበላችሁ ። ነገር ግን እያንዳንዱ ለብቻው ይሁን። የክራር ክሮች እንኳን በአንድ ሙዚቃ አብረው ቢርገበገቡም የታሰሩት ለየብቻ አይደለምን?…

"ልቦቻችሁን ስጡ እንጂ አንዳችሁ የሌላችሁን ልብ አትያዙ።
ልቦቻችሁን ሊይዝ የሚችለዉስ የህይወት እጅ ብቻ አይደለምን?…

"ደግሞም አብራችሁ ቁሙ እንጂ በጣም ተቀራርባችሁ አትቁሙ ። የቤተ መቅደስ ምሰሶዎችም ተራርቀው ነውና የሚቆሙት ።
ደግሞስ የባሉጥ ዛፍና ጥድ አንዳቸው በሌላኛው ጥላ ስር ተሸፍነው ያድጋሉን?"


Zephilosophy

ፍልስፍና philosophy

15 Nov, 06:44


ጣፋጩ ገዳይ መርዝ⁉️

በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል።

ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም።

ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው:: በተቻለህ መጠንም ከስራህ እና ከማሰብ ከሚያስተጓጉሉህ ነገሮች ሁሉ ለማራቅ ሞክር።

ፍልስፍና philosophy

15 Nov, 06:19


ስብሀት ገብረግዝአብሄር እውነት ስለሚናገር አንዳንድች እንደ እብዲ ያዩት ነበር ለምን አበሻ አስመሳይ ሾካካ ነው።
ሴክስ አማረኝ አይባልም⁉️
መባዳት አማረኝ፤ ወሲብ አማረኝ ፤ ነው የሚባለው። የራሳችን ቋንቋና ፊደል አለን እያላችሁ ፤ ሴክስ ስትሉ አይደብራችሁም?  መባዳትን ሳትፈራ እንባዳ የሚለውን ክቡር ቃል ትፈራለህ። አስመሳይ ሁላ⁉️

ፍልስፍና philosophy

14 Nov, 18:40


ልተኛ ነው? ዛሬ ጉዞ ላይ ነዉ የዋልኩት! መቼስ ፈላስፋ እና ሴተኛ አዳሪ እንቅልፉቸዉ ከመደበኛዉ ሰዉ የተገላቢጦሽ ነዉ እስኪ ይሁን!!! በተኛ  ትውልድ መሃል ቆሜ አንገላጀሁ፡፡ በተኛች አገር ላይ ብቻየን ቆሜ ምን እሰራለሁ?

ፍልስፍና philosophy

14 Nov, 05:31


የአረብ ኢምፔሪያሊዝም እና የአለም ፖለቲካ⁉️
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ትንታኔ  ልጀምር ነው ተከተለኝ

ሀ. የመሀመድ ጥንስስ
      ••••••••••••••••
ምስራቅ አፍሪካውያን ነብዮ መሀመድ በጠነሰሰው የአረብ ኤምሪያሊዝም እየተወረርን ነው፡፡ አሁን ላይ በቀጠናው ያለው የፖለቲካ አንቅስቃሴ አይን ያወጣ የአረብ ኢምፔሪያሊዝም ነው፡፡ ከታሪካዊ ገፅታው ካየነው የአረብ ኤምፔራለዝም መስራቹ ነብዩ መሀደመድ ነው፡፡ መሀመድ የአላህ መልዕክተኛ ነው የሚባለው ሀይማኖታዊ ሽፋን ለመስጠት ነው፡፡ የግለሰቡ አላማ በእስልምና ማዕቀፍ ውስጥ  ታላቁን የአረብ ኤምፔራሊዝም መመስረት ነው፡፡ መሀመድ ከሀይማኖት መስራች ይልቅ የፖለቲካ መሪ የሆነበት ገፅታ ጎልቶ የሚወጣ ነው፡፡ ነብይ መባል ያስፈለገበት ምክንያት በአካባቢው በነበረ የነብይ ባህል መሰረት ነብይ የሚከበር ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ፖለቲካውን ለመቆጣጠር ነብይ ነኝ ማለት ነበረበት፡፡ የግለሰቡ አነሳስ ግን ታላቁን የአረብ የግዛት አንድነት መፍጠር ነው፡፡ የአሁኑ የአረብ ኤምፔራሊዝምም መነሻም ይሄው ነው፡፡

ለ. የአረብ ኢምፔሪያሊዝም መነሻው ምንድን ነው ?
     •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የአረብ ኢምፔሪያሊዝም መነሻው ምንድን ነው ከተባለ ሀብትን መቆጣጠር ነው፡፡ አንደምታውቁት የአረብ መሬት ያለው ነዳጅ ብቻ ነው፡፡ የአረብ መሬት ለምግብ ፍጆታ የሚሆን ምርት ማምረት አይችልም፡፡ የአረቡ አለም የኤኮኖሚ ምሰሶ ነዳጅ ነው፡፡ አረቡ አለም ሌላ ሀብት የለውም፡፡ አንደ ቻይና ህዝብ ላይ የተመሰረተ ኤኮኖሚ አንዳይገነባ ህዝቡ ጮማ ራስ ነው፡፡ የቱሪዝም ሀብቱም ቢሆን በውጪ ዜጎች ፍላጎት ላይ የሚወሰን በመሆኑ አስተማማኝ አይደለም፡፡ ለአረቡ አለም ብቸኛ የኤኮኖሚ አውታር ነዳጅ ነው፡፡ ይሁንና አሁን ላይ ነዳጅ ከገበያው መዋዠቅ እና ነዳጅን አላስፈላጊ በሚያደርጉ የቴክኖሎጂ እድገቶች የተነሳ ነዳጅ አስተማማኝ አይደለም፡፡   ነዳጅ ዳቦ አይሆንም፡፡ ነዳጅ እየሸጡም ቢሆን አስተማማኝ የሆነ የምርት ምንጭ ካላገኙ ሆዳሙን የአረብ ህዝባቸውን መመገብ እንደማይችሉ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ የምግብ ፍጆታቸውን የሚያሟሉበት የመሬት ሀብት መቆጣጠር አለባቸው፡፡  አረብ ኤምፔራሊስቶች ምስራቅ አፍሪካ ላይ እየተሸኮቱ የሚገኙትም ይህንን የሀብት ጥያቄ ለመመለስ ነው፡፡

ሐ. ምስራቅ አፍሪካን ለምን መረጡ ?
      ••••••••••••••••••••••••••••••
እውነት ለመናገር አረብ ከራበው የማይበላው ነገር የለም፡፡ የአረቡ ኤምፔራሊዝም ከምስራቅ አፍሪካ ውጪ ሌሎች አካባቢዎችን ሞክሮ የተሳካለት አይመስልም፡፡ ለምን ከተባለ ሌላው አለም እነሱ ለሚፈልጉት የሀብት ጥያቄ አመቺ አልሆነም፡፡ ፊታቸውን ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያዞሩበትም ምክንያት ይሄ አካባቢ ለአረብ ኤምፔሪያሊዝም አመቺ ስለሆነ ነው፡፡ አንደኛ ምስራቅ አፍሪካ ለአረቡ አለም ቅርብ ነው፡፡ በፖለቲካ ለመቆጣጠርም አመቺ ነው፡፡ ለትራንስፖርትም በተመሳሳይ አመቺ ነው፡፡ ሁለተኛ ድሀ ነው፡፡ በትንሽ ገንዘብ ብዙ ነገር ማድረግ ይችላሉ፡፡ የገንዘብ አቅም ስሌለው ሀብታም ሲመጣ የሚደሰት ነው፡፡ በዛ ላይ በፖለቲካ ደካማ ስለሆነ አንደፈለጉት ማሽከርከር ይችላሉ፡፡ ሶስተኛ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ለሰብል ልማት አመቺ ነው፡፡ ከአየር ንብረት አንፃር ከታየ ይሄ አካባቢ የአረብን ሆድ መሙላት የሚችል ነው፡፡ በዛ ላይ የምስራቅ አፍሪካ አርሶ አደሮ ሰነፍ ስለሆነ፥ በትንሽ ነገር ለመደለል አመቺ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የሆነ የውሀ ሀብት ባለቤት ነው፡፡ ስለዚህ ይሔን አካባቢ መቆጣጠር አረቡ ኤምፔሪያሊዝም ዋና አላማ ነው፡፡

መ. የአረብ ኢምፔሪያሊዝም የሚኖረው ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ምንድን ነው ?

የአረብ ኢምፔሪያሊዝም የራሱን መስመር ተክትሎ በአለም ፖለቲካ ላይ የራሱን የሀይል ሚዛን መፍጠር ይፈልጋል፡፡ በፊት በአለም ፖለቲካ ላይ የነበረው አሰላለፍ ምዕራቡ /አሜሪካ እንግሊዝ ወዘተ/ እና ምስራቁ/ሩስያ ቻይና ወዘተ/  ነበር፡፡ አሁን የአረቡ ኤምፔሪያሊዝም እየተጨመረ ነው፡፡ ስለዚህ የአረብ ኢምፔሪያሊዝም የሚኖረው ፖለቲካዊ ተፅዕኖ የአለምን ፖለቲካ አሰላለፍን መቆጣጠር ነው፡፡ ሁለተኛ የአረብ ኤምፔራሊዝም ስግብግብ አለማውን ለማሳካት የሚፈርሱ ስርዓቶች ይኖራሉ፡፡ የአረብ ኤምፔሪያሊዝም የቀጠናውን ሀብት ለመቆጣጠር አና ያለማንም ከልካይነት ለመዝረፍ የአገር ምሰሶ የሆነው የፖለቲካ ስርዓት በማዳከም ሊያጠፋ ይችላል፡፡  ለምሳሌ ኤርትራ ጅቡቲ ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምትነት በአረብ ኤምፔሪያሊዝም የፖለቲካ ስርዓታቸው ሊፈርስ የሚችሉ አገራት ናቸው፡፡



ይቀጥላል......

ፍልስፍና philosophy

13 Nov, 18:33


ጋብዣችሁ አለሁ።

ፍልስፍና philosophy

12 Nov, 19:11


10,000 ቤተ-ክርስቲያን 10,000 መስጊድ አለ አንዲት ጠብታ ፍቅር ሽራፊ የሰላም ዋስትና ግን የለም።  ቤተ-ክርስቲያንና መስጊድ  መሰራቱ በፍቅር የሚኖር ማህበረሰብ ካልፈጠረ ከሐይማኖት ያተረፍነው የብሎኬት እና ሲሜንቶ ብክነት ነው!

ፍልስፍና philosophy

12 Nov, 19:09


https://t.me/Atruetraditionalmedicin

ፍልስፍና philosophy

11 Nov, 16:51


በህልሜ ፈጣሪ ተገለጠልኝ!!

ሙላ ናሱሩዲን እና ሁለት የሱፊ መምህራን ወደ መካ ጉዞ ጀመሩ። አንድ መንደር ውስጥም ገቡ፡፡ ይሄ የጉዟቸው የመጨረሻ ምዕራፍ ነበር። ገንዘባቸው በሙሉ አልቆ፣ ትንሽ ብቻ ቀርቷቸዋል። በቀራቸው ብርም ሃላዋ የተባለ ጣፋጭ ምግብ ገዙ፡፡ ነገር ግን ለሶስቱም የሚበቃ አልነበረም፤ በጣም ርቧቸዋል፡፡ ምን ያድርጉ? ለመከፋፈል አልቻሉም፤ ከተከፋፈሉ  ማንኛቸውንም አያጠግባቸውም፡፡

እናም ሁሉም “እኔ ከእናንተ አንጻር መኖሬ ጠቃሚ ነው፤ የእኔ ሕይወት መትረፍ አለበት” መባባል ጀመሩ።
የመጀመሪያው መምህር “ጾሜያለሁ፤ እድሜዬን ሙሉ ጸልያለሁ፤ እንደ እኔ ኃይማኖተኛ እና ቅዱስ የለም፡፡ እናም ፈጣሪ በኔ መትረፍ ይደሰታል። ሃላዋውን ስጡኝ” አላቸው።

ሁለተኛው መምህርም “አዎ! ልክ ነህ ልክ ነህ አውቃለሁ፡፡ አውቃለሁ። ታላቅ ኃይማኖተኛ ነህ። ግን እኔ ከሁላችሁም የላቀ እውቀት አለኝ። ሁሉንም መጽሐፍት አጥንቻለሁ። ሕይወቴን ሙሉ እውቀት ስፈልግ ኖሬያለሁ፡፡ ይህቺ ምድር ጿሚዎች አያስፈልጓትም᎓᎓ ምን ታደርግላታለህ፤ ልትጾምላት? ገነት ውስጥ ሆነህ መጸለይ ትችላለህ። ዓለም እውቀት ያስፈልጋታል። ዓለምን ድድብና ሞልቷታል፤ እኔን ማጣት የለባትም:: ሃላዋው ለእኔ መሰጠት አለበት::” አለ፡፡

ሙላ ናስሩዲንም እንዲህ አለ “እኔ እንደናንተ ቅዱስ አይደለሁም። እውቀትም የለኝም፡፡ ተራ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡ እንደሰማሁት ፈጣሪ ለኃጢአተኞች ያዝናል፡፡ እናም ሃላዋው ለኔ ይገባኛል፡፡”

ሁሉም ሊስማሙ አልቻሉም። በመጨረሻም በአንድ ነገር ተስማሙ፡ ፡ “ሶስታችንም ሃላዋውን ሳንበላ እንተኛ እናም ፈጣሪ ይፈርዳል። ፈጣሪ ጥሩ ህልም ያሳየው በጥዋት ይበላዋል።” ተባባሉና ተኙ፡፡

በጠዋት የመጀመሪያው መምህር እንዲህ አለ “ከእኔ ጋር ማንም ሊወዳደር አይችልም᎓᎓ ሃላዋውን ስጡኝ፤ በህልሜ የፈጣሪን እግር ስሜያለሁ። ማንም ከዚህ በላይ አይመኝም፤ ምን ያህል የሚያስደስት ህልም ነው?”

ሁለተኛውም ባለእውቀት መምህሩም እየሳቀ እንዲህ አለው “ይሄ ምንም አይደለም፤ ፈጣሪ አቅፎ ስሞኛል:: አንተ እግሩን ነው የሳምከው? እኔን ግን አቅፎ ስሞኛል:: ሃላዋው የታለ? የኔ ነው።”

ሁለቱም ናስሩዲንን እያዩ “አንተስ፤ ምን አይነት ህልም አየህ?” አሉት።

ናስሩዲንም መለሰላቸው “እኔ ምስኪን ኃጢአተኛ ነኝ መነገር የማይገባው ህልም ነው ያየሁት። ንገረን ካላችሁ ግን ልንገራችሁ:: በህልሜ ፈጣሪ ተገለጠልኝ እና እንዲህ አለኝ አንተ ሞኝ ምን ትሰራለህ? ተነስ ሃላዋውን ብላ::

እናም ተነስቼ ሃላዋውን በላሁት፤ ማንስ የእሱን ትዕዛዝ ይጥሳል? አሁን ምንም ሃላዋ የለም::”
😂😂😂😂


@Zephilosophy

ፍልስፍና philosophy

11 Nov, 07:34


ፓስተሩ በቦዲ ጋርድ ታጅቦ አትፍራ እግዚአብሔር ይጠብቅሀል በሰው አትተማመን ይልሀል!
ቄሱ V8ቱን አቁሞ ምድራዊ ቁሳቁስ ከንቱ ነው ለሱ አትድከሙ ይልሀል ስብከቱን ሲጨርስ አንተ በእግርህ ስትኳትን እሱ በመኪናው ላጥ!

ፍልስፍና philosophy

10 Nov, 06:44


ምን ይሻለኛል ግን⁉️
•••••••••••••••••
አንድ አንባቢ “ሴት ባየሁ ቁጥር ቁላየ እየቆመ አስቸግሮኛል። ምን ይሻለኛል?” የሚል ጥያቄ በውስጥ መስመር አቅርቦልኛል።

የኔ መልስ አጭር ነው።

1ኛ – የጻፍከው ነገር ለሴቶች ስድብ ነው። ምን ያህል ለሴት ልጅ ክብር እንደሌለህ ያሳያል። የሴትን ልጅ ባየህ ቁጥር ቀድሞ የሚታሰብህ ወሲብ ከሆነ ችግር አለብህና የስነልቦና ህክምና ጠይቅ። የሴት ልጅ ያንተ ቁላ ማስነሻ ዕቃ አይደለችም። ክብር ያላት ፍጡር ነች። ስለዚህ ራስህን ገምግም።

2ኛ – ቁላህን ቆንጥጠው። ስሜትህን ልትገዛው እንጂ ስሜትህ ሊገዛህ አይገባም። በጭንቅላትህ ሳይሆን በቁላህ ብቻ እያሰብክ ስለሆነ ራስህን ግዛ።

3ኛ – እህት አለህ? የሴት ዘመድስ አለህ? እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ። የሆነ ወንድ “እነዚህ ዘመዶችህን ባየሁ ቁጥር ቁላዬ ይቆማልና ምን ላድርግ” ቢልህ ምን አድርግ ብለህ ትመክረዋለህ? ያዙኝ፣ ልቀቁኝ፣ እገድለዋለሁ እንደምትል እርግጠኛ ነኝ። ያንተንም ሁኔታ በዚሁ መልኩ እየውና ራስህን ታዘበው።

በነገራችን ላይ እንዳንተ ያሉ ወንዶች እንደዚህ ዓይነት ሐሳብ የምታስቡት ሴትን ልጅ ከወሲብ ማርኪያነት ውጭ አርቆ የሚያስብ አዕምሮ ስለሌላችሁ ነው። ያቺ የምታያትና ቁላህ የሚቆምላት ሴት ግን የሌላ ሰው እህት፣ እናት፣ አክስት፣ ሚስት፣ ፍቅረኛ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ ልጅ ነች። በወሲብ ዕቃነቷ ሳይሆን በሰውነቷ እያትና አክብራት። በህይወቷ ለማሳካት የምትፈልጋቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ጣር። ያቺ ሴት ከወሲብ ቀስቃሽ ገላዋ በፊት የሚያስብ አዕምሮና የሚያፈቅር ልብ የያዘች ሰው መሆኗን ተረዳ። ያኔ በሰውነቷ ልትተዋወቃት ትችላለህ። ሴትነቷን ካከበርክ ማን ያውቃል ወዳህ ተዋዳችሁ ልብህ እስኪወልቅ ድረስ ልትበዳህ ትችላለች። ቅድሚያ ግን ማንነቷን ከወሲብ ጋር ብቻ አታያይዝ።

4ኛ – የምታስበው ነገር ሁሉ ወሲብ ብቻ ከሆነ ሴተኛ አዳሪዎች አሉልህ ገንዘብህን ከፍለህ ብዳ። እነሱንም ቢሆን ልታከብራቸው ይገባል። ሰውነታቸውን ስለሚሸጡልህ ከሰውነት በታች ልታያቸው አይገባም። ኤድስንና ሌሎች በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎችንም አትርሳ!

ህይወትህን ስለወሲብ ብቻ እያሳሰብክ ቀፎ አታድርገው።

ፍልስፍና philosophy

08 Nov, 14:49


የአማራ ወጣት ከልደቱ አያሌው የፖለቲካ ፍልስፍና እና ትንታኔ በበለጠ የአዝማሪው ፋሲል ደሞዝ ታማኝ በየነ መሀሪ ደገፋው፥ ሽመልስ አበራ ጆሮን ቀረርቶ እና ሽለላ የሚያደምጥ አሳዛኝ የአዝማሪዎች መጫወቻ የሆነ ምስኪን ህዝብ ነው

ፍልስፍና philosophy

08 Nov, 04:40


ጉድኮ ነው‼️
••••••••••
የቀድሞ የፍቅር ጓደኛዬ አንድ ሊንክ በሜሴንጀር አቀበለችኝ፣ ሊንኩን ስጫነው Youtube ላይ አድርሶ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፈተልኝ:- እንዲህም ይላል ግጥሙ!

ካለፈው ህይወቴ ተምሪያለሁ፣
ተፀፅቻለሁ
አንተ ትሻለኛለህ፣
ቤትህ እገባለሁ፣
በእጆችህ ዳብሰኝ፣
ደረትህ ላይ ለጥፈኝ

ምናምን የሚል ግጥም አለው፣ በጣም flattering ነው፣ አገረሸባት ማለት ነው እያልኩ ቀብረር ኮራ ብዬ ማዳመጤን ቀጠልኩ፣ "ኢየሱሴ" ስትል አይደል እንዴ መዝሙር መሆኑን ያወቅኩት፣ በጣም በንዴት ደሜ ፈልቶ በብሎክ አሰናብቻታለሁ፣

ኧረ ጴንጤዎች ግዴላችሁም አምልኮታችሁን መልክ አሲዙት፣ ከኢየሱስ ጋር ፆታዊ ነው መለኮታዊ ፍቅር የያዛት?

ፍልስፍና philosophy

01 Nov, 18:16


ሐበሻ ማለት እኮ Degree ፎርጅድ አሰርቶ ወይንም ከግል ኮሌጅ በብር ገዝቶ ቤተክርስቲያን ሔዶ አውደ ምሕረት ላይ ቆሞ
"ፈጣሪ ረዳኝ... እስኪ እግዜርን አመስግኑልኝ እልል በሉ የሚል ፈጣጣ ህዝብ ነው⁉️

ፍልስፍና philosophy

01 Nov, 06:26


የተራራው ስብከት፣ ክርስትናና ዲሞክራሲ
*
***
‹‹ለዲሞክራሲ መምጣትና መስፋፋት አመቺ ሁኔታን የፈጠረው ክርስትና ነው››
**
ኒቸ በፍልስፍና ውስጥ ይበልጥ የሚታወቀው የግብረገብነትን ታሪካዊ አመጣጥ ያሳየበት መንገድ ነው፡፡ ኒቸ ሞራሊቲን ‹‹የጌትነት ሞራሊቲ›› እና ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› (Master Morality and Slave Morality) በማለት በሁለት ይከፍለዋል፡፡ ይሄም ማለት ጠንካሮችና ደካሞች በግብረገባዊ እሴት ይለያያሉ፡፡ የጠንካሮቹ (የጌትነት ሞራሊቲ ያላቸው ሰዎች) ልዕልናዎች ደፋርነት፣ ጀብደኛነት፣ ስኬታማነት፣ አይበገሬነት፣ ደስታ፣ ክብር፣ ኩራትና ዝና ሲሆኑ፣ ምድራዊ ህይወታቸውንም ያፈቅራሉ፡፡ ‹‹የጥንት ግሪኮችና ሮማውያን እንደዚህ ዓይነት እሴት የበለፀገባቸው ህዝቦች ናቸው›› ይላል ኒቸ፡፡
***
‹‹የጌትነት ሞራሊቲ›› ያላቸው እነዚህ ህዝቦች ከደካሞች የፈለጉትን እየወሰዱ፣ የፈለጉትን እያደረጉ ሲኖሩ ደካሞቹ ህዝቦች ቁጭ ብለው ከማየት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡ በዚህም ‹‹የደካማ ሞራሊቲ›› ያላቸው እነዚህ ህዝቦች ውስጣቸው በጥላቻ እና በበታችነት ስሜት እየተሞላ ሄደ፡፡ ስለዚህ፣ ያላቸው አማራጭ ምንድን ነው እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ከመግለፅ (define ከማድረግ) ይልቅ ለእነሱ የሚያዋጣቸው እነዚያን ብርቱዎቹንና ጠንካራዎቹን define ማድረግ ነው፡፡ ብርቱዎቹን define ማድረግ ማለት ደግሞ አዲስ ሞራሊቲ ፈጥሮ የብርቱዎቹን እርኩስነት ማሳየት ማለት ነው፡፡ በዚህም የጠንካሮችን ልዕልናዎች እርኩሰት አደረጓቸው፡፡ ለምን?
***
ምክንያቱም፣ መቼም ቢሆን እነዚህ ደካማ የሆኑ ሰዎች ጠንካሮችን ማሸነፍ አይችሉም፡፡ ስለዚህ፣ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ጠንካሮችን መብለጥ ሳይሆን በአዲስ ሞራሊቲ ማሰርና ማንበርከክ ነው፡፡ እነዚህን የበላይ የሆኑትን ሰዎች ሊያምበረክኩ የሚችሉበት ብቸኛው መሳሪያቸው ደግሞ መንፈሳዊ ብቀላ ነው፤ አካላዊ ብቀላን መፈፀም ስለማይችሉ፡፡ ‹‹መንፈሳዊ ብቀላ›› ማለት ደግሞ የብርቱዎችን የሞራል እሴቶች (ደፋርነት፣ ክብር፣ ኩራት፣ ጀግንነት፣ ምድራዊ ህይወትን ማፍቀር፣ ምድራዊ ስኬት…) በእርኩስነት መፈረጅ ነው፡፡ በዚህ መንገድ፣ ደካሞቹ የጠንካሮችን የሞራል እሴቶች ‹‹እርኩሰት›› በማድረግ በሂደት ሙሉ ለሙሉ አንበረከኳቸው፡፡ በመሆኑም፣ ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› የበቀል ሞራሊቲ ነው፤ ምንጩም ጥላቻ ነው፤ የበደል ስሜት ነው፡፡
***
ይሄንን የደካሞች ሞራሊቲ በግልፅ በአይሁዳውያን ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ አይሁዳውያን በተለያየ ጊዜ በባቢሎናውያን፣ በፐርሺያኖች፣ በግሪኮች፣ በሮማውያንና በግብፆች በምርኮ ተይዘው ነበር፡፡ ለዚህም ነው ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› መነሻው የአይሁድ እምነት የሆነው፡፡ ምንም እንኳ፣ ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› በአይሁድ እምነት ቢጀመርም ወደ ፍፁምና ያመጣው ግን ክርስትና ነው ― የአይሁድ እምነት ወራሽ፡፡
***
ኒቸ እንደሚለው ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ››ን በዝርዝር የምታገኙት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስም ውስጥ በተለይ ማቴዎስ ምዕራፍ አምስት ላይ የተጠቀሰው የእየሱስ የተራራው ስብከት (Sermon on the Mount) ላይ ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ››ን በግልፅ ታገኙታላችሁ፡፡
***
* በመንፈስ ድሆች የሆኑና የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤
* ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጠው፤
* ሁለት ኮት ካለህ አንዱን ኮት ስጠው፤
* ሸሚዝህን ለሚቀማህ ሹራብህንም ጨምርለት፤
* አምስት ሜትር አብረኸኝ ሂድ ለሚልህ አስር ሜትር አብረኸው ሂድ፤
***
‹‹ይሄ የመጨረሻ ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› ነው›› ይላል ኒቸ፡፡
***
በታሪክ ውስጥ ‹‹የጌትነት ሞራሊቲ›› ሙሉ በሙሉ የተሸነፈው ክርስትና በመላው ታላቁ የሮማን ኤምፓየር ሲስፋፋ ነው፡፡ በዚህም መላው አውሮፓ ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› መናኸሪያ ሆነ፡፡ የዚህ ጉልህ ማሳያው ደግሞ የክርስትና የመንፈስ ውርስ የሆነው የዲሞክራሲ ፅንሰ ሐሳብ መምጣት ነው፡፡ በክርስትና አማካኝነት ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› አውሮፓ ላይ ድል መቀዳጀቱ በኋላ ላይ ለተነሳው የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ ደካማውንም ጠንካራውንም እኩል የሚያየው ዲሞክራሲ በመላው አውሮፓ መስፋፋቱ ‹‹አጠቃላይ የሰው ልጅ የሞራል ንቅዘት ነው››፡፡ ምክንያቱም፣ ክርስትናና ዲሞክራሲ ጠንካሮች ልቀው እንዳይወጡ በመገደብና ሁሉንም ሰው ደካማ በማድረግ ሁሉንም ሰው እኩል ማድረግ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡
***
በመሆኑም፣ ለኒቼ ያለ ክርስትና ዲሞክራሲ ሊኖር አይችልም፡፡ ክርስትና ሁሉንም ሰው እኩል በማድረግ ለዲሞክራሲ አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ይሄም ማለት ‹‹ሰዎች ሁሉ እኩል ናቸው›› የሚለው መርህ ክርስትናንና ዲሞክራሲን አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ በመሆኑም፣ ዲሞክራሲ ‹‹የደካሞች ሞራሊቲ›› ፖለቲካዊ መገለጫው ነው፡፡

ፍልስፍና philosophy

31 Oct, 14:24


#የፍልስፍና_ሀሁ
          እና
#የለት_ፍልስፍና

#እውነት_ምንድን_ነው? የሚለው ጥያቄ የምንጊዜም እንቆቅልሽ ጥያቄ ሆኖ ኖሯል፡፡ ከግሪክ እስከ ሮም፣ ከህንድ እስከ ጃፓን፣ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ድረስ በተለያዩ ዘመናት የኖሩ አያሌ ፈላስፎች ይህን ጥያቄ ለመመለስ እድሜያቸውን ሰውተዋል፡፡

ከሰዎች ተለይተው በየዋሻውና በየምኩራቡ እውቀትን ክፉኛ ቢሹም፣ እስካሁን ሁሉንም የሚያስማማ መልስ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይሁን እንጂ የሁሉም መልስ ደግሞ ስህተት ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ሁሉም የየራሱ እውነት አለውና፡፡ ፍለጋው አሁንም ቀጥሏል፡፡ ሁለቱም መጽሐፍት #የፍልስፍና_ሀሁ እና #የለት_ፍልስፍና ደግሞ አብረውን እውነትን ይፈልጋሉ፡፡

ፍጥረትና ህይወት ከየት ተገኘ?

የምንኖረው ለምንድን ነው?

የህይወት የመጨረሻው አላማ ምንድን ነው?

ለምን ወደዚህ ምድር መጣን?

ወዴትስ እንሄዳለን?

እነዚህና ሌሎች አያሌ ጥያቄዎች የእውነትን እውነተኛ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ዴስካሬት በፕላቶ መልስ ቢስቅም፣ ሩሶ በስፒኖዛ ፍልስፍና ቢበሳጭም፣ ፓይታጎራውያን በኢፒስኩሮሶች ቢያፌዙም፣ ሁሉም ግን በአንድ ነገር ብቻ ፈጽሞ ይስማማሉ፡፡

#የመጨረሻው_የጥበብ_ፍለጋ ፍልስፍና መሆኑን፡፡

#የፍልስፍና_ሀሁ እና #የለት_ፍልስፍና መጽሐፍት ስለ ፍልስፍና አስደናቂና አዝናኝ ጉዞ ይተርካሉ፡፡

ከአቴንስ እስከ ኤፌሶን፣ ከለንደን እስከ ፓሪስ በተለያየ ዘመን የኖሩ አለምን የቀየሩ ፈላስፎችን በር ያንኳኳል፡፡ መሰረታዊ ፍልስፍናን ማወቅ አለብኝ ለሚልና የስቶይሲዝም ፍልስፍናን ለተጠማ አንባቢ እነዚህ መጽሐፍት ትልቅ ገጸ በረከቶች ናቸው፡፡

አራት ምርጥ_ምርጥ የፍልስፍና መጽሐፎች በገበያ ላይ-

#የለት_ፍልስፍና 2ተኛ  ዕትም
#የፍልስፍና_ሀሁ_5ኛ ዕትም
#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ 2ተኛ ዕትም
#የፍልስፍና_ማዕድ

#በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች_እጅ_ያገኟቸዋል፡፡

ፍልስፍና philosophy

30 Oct, 19:28


ሐበሻ ማለት እኮ የተሰረቀ ስልክ ገዝቶ መዝሙር እና መንዙማ አስጭኖ የሚያንጎራጉር
አሳፋሪ ነውረኛ ህዝብ ነው⁉️

ፍልስፍና philosophy

30 Oct, 10:43


አስተውል⁉️
••••••••••
ድህነት በፀሎት እና በ ዱአ ከተረታ የ3 ሺ አመት ልመናችሁ ምን አመጣ? አጅህን ወደ እግዚአብሄር ወደ አላህ  ዘርግተህ "ስጠኝ" ስትለው እሱም እጁን ወደ መሬት ዘርግቶ የሰጠህን የተፈጥሮ ሃብት ፀጋ ሲያሳይህ።

የማይገባህን ደመና ፣ የሚተን ጉም ጨብጠህ። በባዶ የመለስካት መዳፍህ ራስህን ኩም አደረገችህ።

አባይ በደጃፍህ ሲያልፍ ተዘፍዝፈህ ማሲንቆ እየገዘገዝክ እያየኸዉ፣ ጉሮሮህ በውሀ ጥም ተቃጠለ።

ለልመና ወደላይ  መዘርጋት እንጂ መቆፈር እና ማረስ መስራት ያላስለመድከው እጅህ የሚበላው ሲያጣ ያንተኑ ማንነነት በላብህ! ለማኝ አድርጎ የሰው መሳቂያ አደረገህ።

ኢትዮጵያ ተወልደን በልጅነታችን በነበረን ልዩ ፍላጎት አንደ ሰው አልተቆጠርንም፡፡ በልጅነታችን አንደ ትልቅ ሰው በማሰባችን ያደግነው ያለ ጓደኛ ነው፡፡

የሚመጥነን ሰው ጠፍቶ መፅሐፍትን ጓደኛ ብናደርግ ወረቀት ለቃቃሚ የሚል ቅፅል ስም አወጡልን!

ኋላ-ቀር አስተሳሰብ እንዲቀየር በመጠየቃችን ያደግነው እንደ ባንዳ እየታየን ነው፡፡

በልጅነታችን የፊዚክስ ጥያቄ በመጠየቃችን ያደግነው ሀጥያተኛ እየተባልን  ነው፡፡

ኦርቶዶክስ ብንሆን መባው መከራ!

ጴንጤ ብንሆን የማሪያም ጠላት!

ሙስሊም ብንሆን የአረብ ሞራል ሰለባ!

መቻቻልን በመስባክችን ፈሪ!

ለሰላም ባለን አቋም ቦቅቧቃ እየተባልን ነው ያደግነው፡፡

ካደግንም በኋላ ስለቢግ-ባንግ ፍልስፍና በመፃፋችን የስድብ ናዳ የሚወርድብን ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነኝ በሚለው ነው፡፡

የጎጆ ኢንዱትሪን ቀጥቃጭ እያላችሁ አታግልሉ  በማለታችን ማንነታችን የተቀማን ሆነናል፡፡
ቆዳ ፋቂ ቡዳ አይደለም በማለታችን ስንት ነገር አሳልፈናል፡፡

ለሳይንሳዊ ማህበረሰብ መፈጠር ባደረግነው ጥረት በትምክህተኝነት ነግደው ከሚያተርፉ የአጀንዳ ነጋዴዎች ብሔራችን ተቀምቷል፡፡ በየጫት ቤቱም የጭቅጭቅ አጀንዳ ሆነን ተሰላችተናል፡፡

የመንጋ ፖለቲካ ባለመከተላችን በሰው አገር ለስደት ተዳርገናል፡፡ እነዚህን የመሳሳሉ ችግሮች የሚሳዩት ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው እኛን እየበደለ መሆኑን ብቻ አይደለም፡፡ ቀድሞ ነገር የኢትዮጵያ ችግር የሚነሳው ከኢትዮጵያ ነው፡፡

ትልቁ ችግር ደግሞ የኢትዮጵያ ችግር ኢትዮጵያዊያን አራሳቸው መሆናቸው  አለመቀበል ነው፡፡

ብልፀግና ወያኔ ኦነግ ግምቦት 7 ሸኔ አሜሪካ ጃማይካ ብትል ምን ብትል ዋጋ የለውም፡፡  የኢትዮጵያ  ችግር የተቆለፈበት ከውስጥ በኩል ነው፡፡ በራሱ በኩል ራሱ ላይ የቆለፈውን ቤት መክፈት የሚችለው ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው፡፡

እንዲያው አንበልና እኔ እንዳግዛችሁ ብትፈልጉ አንኳን ማድረግ የምችለው በሩን ማንኳኳት ብቻ ነው፡፡ እጀታውን ከራስህ በኩል አድርገህ የዘጋኸውን በር መክፈት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፡፡ ካልከፈትክ ቤቱ ውስጥ ሆነህ እድሜ ልክህን ስትጮህ ትኖራለህ ማለት ነው አንተ ደደብ፡፡

ጉራጌ ሲተርት "ጎረምሳ ላስደስት ብላ ዲቃላ ወለደች!" ይላል!  አንዳንድ ሰዎች 'ንፁህ ኢትዮጵያዊ' ለመባል ሲጋጋጡ እያየን ነው! እነርሱ የሚሉንን የውሸት 'ኢትዮጵያዊነት' ኖረንበታል እጅግ በጣም ጠንቅቀን እናውቀዋለን! እንፀየፈዋለንም!

ፍልስፍና philosophy

29 Oct, 19:25


ሐበሻ ማለት እኮ...⁉️

"የገብርኤልን ፅላት ለመስረቅ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሔዶ ወርቅ ጥላ የሚሳል መሰሪ ህዝብ ነው"

እውነትን ተናግሮ የመሸበት ማደር።

ፍልስፍና philosophy

29 Oct, 07:05


ዝም በል ⁉️
•••••••••••••••
አንድ የምዕራባውያን ተወላጅ ማንነቱን ብትጠይቀው የሚመልስልህ መልስ በሚኖርበት ማህበረሰብ የመፍትሔ ሚና የሚጫወትበትን ማንንት ነው። ማንነቱን  ሲነግርህ እኔ ዶክተር ነኝ ፈላስፋ ነኝ፣ መምህር ነኝ።ነርስ ነኝ: ኢንጂነር ነኝ ፖሊስ ነኝ: መካኒክ ነኝ፣አናፂ ግምበኛ ነኝ ይልሀል።መፍትሄ የሆነ ማንነት ማለት ይሔ ነው ።

ኢትዮጵያዊን ግን ማነህ ብለህ ብትጠይቀው የሚነግርህ ችግር ነው። አማራ ነኝ።ኦሮሞ ነኝ። ትግሬ ነኝ። ኦርቶዶክስ ነኝ ጴንጤ ነኝ።ሙስሊም ነኝ። የችግር መአት። እኛ እና እነሱ በጣም ተራርቀናል።

ሶስት ምእራባውያንን አንድ  ክፍል ውስጥ አስገብተህ በሩን ከውጪ ብትዘጋባቸው ሶስቱም የሚያስቡት በጋራ ተባብረው በሩን መክፈት ላይ ነው።

እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያዊ ቢሆኑ ብለህ አስብ። ሶስቱ ሰዎች ኢትዮጵያዊ ቢሆኑ የሚያስቡት ተባብረው ተረዳድተው በሩን ስለመክፈት ሳይሆን  የተዘጋው ቤት ውስጥ ለብቻ ለብቻ ክፍል ሰርቶ ለመኖር እርስ በርስ ለመጨራረስን ነው።

እንኳንም ሐበሻ አልሆንኩ ።

ፍልስፍና philosophy

28 Oct, 10:21


ኑ እንወያይ⁉️
••••••••••
በ ማህብረሰባዊ ሳይንስ ወይንም (sociology Science) እሳቤ መሰረት የአንድ አገር ወይንም ማህበረሰብ ጤናማ አኗኗርን ለመመዘን ከሚቀርቡ መስፈርቶች መካከል ጥቂቶቹን ላካፍላችሁ!

• አገሪቱ ያላት የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር እና አመታዊ የጉዲፍቻ መጠን?

•አገሪቱ ያላት የሴተኛ አዳሪዎች ቁጥር?

• አገሪቱ ያላት አመታዊ የውልደት የጋብቻ የፍች የሞት ቁጥር?

•ኤች ኤይቪ ን ጨምሮ የተለያዩ ውሀ ወለድ እና አየር ወለድ በሽታዎች ተጋላጭነት ቁጥር?

•የምግብ እና መጠጥ አቅርቦት በነፍስ ወከፍ?

•በአገሪቱ ያለ የፍትህ እና የሙስና ሁናቴ?

•በአገሪቱ ያለ የዝርፊያ ግድያ እና ተዛማጅ የወንጀል መጠን?

ሌሎችም......

በዚህ መመዘኛ መሰረት እስኪ ኢትዮጵያን እንቃኛት? ትዝብቱን ለአንባቢ ልተው?

ፍልስፍና philosophy

27 Oct, 18:37


በሚዛን ተመዘንክ፣ ቀለህም ተገኘህ ⁉️
•••••••••••••••••••••••••••••••••
በታላላቅ ቅዱሳን መፃሕፍት ላይ እንደተጠቀሰው የእግዜር እጅ የብልጣሶር ግድግዳ ላይ መልዕክት አስቀመጠች!

እንዲህም ትላለች ‹‹ማኔ | ቴቄል | ፋሬስ›› ይላል ይሔ ቃል የንጉሱን የወገብ ጅማት የፈታ ኃያል ፅሑፍ ነው፣ ነብዩ ዳንኤል እንደተረጎመው ከሆነ "ማኔ" ማለት እግዚአብሔር መንግሥትህን ቈጠረው ፈጸመውም ማለት ነው፣ "ቴቄል" ማለት በሚዛን ተመዘንህ፣ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው፣ "ፋሬስ" ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው፣

አብይ አህመድ ብቻውን አይደለም፣ ህዝብን የናቁ፣ እግዜሩን ያልፈሩ፣ ህዝብ የሚልሰውና የሚቀምሰው ባጣበት ጊዜ በእልፍኛቸው ሰርግና ምላሻ ያደረጉ፣ የህዝብ ለቅሶ ሙዚቃ ይሆነላቸው፣ በህዝብ ዋይ ዋይታ እስክስታ የወረዱ፣ በህዝብ ገንዘብ ለምቾታቸው የሰሩ ....ብዙ ባይሆኑም በዘመናት መካከል መጥተው አልፈዋል፣

ከባቢሎን ንጉስ ብልጣሶር እስከ ሮማው ንጉሰ ኔሮ፣ ከፈረንሳዩ ንጉስ ቻርለስ VI (በቅፅል ስሙ "እብዱ") እስከ ንግስት ማሪያን አንቶውኔት፣ ከላይቤሪያው ሳሙኤል ዶ እስከ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ቦካሳ ሁሉም ታድመውበት የነበረውን በእንግዳ ብዛትና በወጪ እስከዛሬ  አቻ ያልተገኝለትን የሶስት ቀን ድግስ ከደገሰው ከኢራኑ ንጉሰ መሐመድ ሪዛ ሻህ እስከ ሰባተኛው ንጉስ አብይ አህመድ ..... ...

ከላይ የተጠቀሱትን ሰዋች ተመሳሳይነታቸው ይገርማል፣ ከአንዱ (ከ ፓስተር አብይ አህመድ) በስተቀር ሌሎቹ በህይወት የሉም፣ መጨረሻቸው ሰቅጣጭ ነበር፣

አንዱ የብልፅግና ካድሬ እዚህ ቴሌግራም ላይ ላይ ስለ ፓስተር ዐብይ በተነፍስኩ ቁጥር "ወሬውን ተውና ወንድ ከሆንክ ስለ ኢኮኖሚክስ ፃፍ፣ ኢኮኖሚክስ አውቃለሁ ብለሀል እኮ" የሚለኝ ልጅ አለ፣ አውቃለው እንኳን ብዬ አላውቅም፣ አውቃለሁ ያላልኩት ስለማላውቅ ሳይሆን humble ለመሆን ያህል ነው ለማንኛውም ለዚህ ኮልኮሌ ልጅ ምላሽ ልሰጠው እፈልጋለሁ፣

ይሄ  የብልፅግና ካድሬ ስለ ኢኮኖሚክስ ያልገባው ነገር እንዳለ ይሰማኛል፣ ኢኮኖሚክስን እንደ እውቀት እንዲደራጅና ሙያ ያደረጉት ነገሮች ሁለት ጉዳዬች ናቸው፣

(1) የሰው ፍላጎት ወሰን አልባ መሆን (unlimited wants) እና (2) የሀብት ውስንነት (limited resources) ናቸው፣

የኢኮኖሚክስ ስራ ፍላጎትን ማመቻመችና ማጣጣም ነው፣ ኢኮኖሚክስ ፍላጎትህን ቅደም ተከተል ያሲዝልሀል፣ ከቅደም ተከተሉ ላይ ትመርጣለህ፣ እንደውም ኢኮኖሚክስን "the science of choice" ብለው ነው define የሚያደርጉት፣

የአብይ አህመድ መንግስት በኢኮኖሚክስ ሀዲድ ላይ የለም፣ ዙሪያ ገባውን ፈትሸን አጥተነዋል፣ ቢሮ የሚያስውብ፣ ፓርክና ፓርኪንግ ሎት የሚገነባ ሰው ነው የገጠመን፣ ያንንም እንደ ስኬት ቆጥሮ ራሱ የሚሳተፍበት ዘጋቢ-ፊልም (documentary) እያሰራ ነው፣ የሚመራት ሀገር:-

25% ስራ-አጥ ተሸክማለች

80% በላይ በገጠርና በግብርና ይኖራል

56% ህዝብ የቀን ገቢው 1.25 USD በታች ነው

60% ከድህነት ወለል በታች ይኖራል፣ በአለም ባንክ ሪፖርት መሰረት ዛሬ ያሉት ደሀዋች የዛሬ 10 ዓመት የተሻለ ድህነት ውስጥ ነበሩ፣ ዛሬ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ማለት ነው፣

45% ለትምህርት ቢደርስም ትምህርት አላገኝም፣

65% የቧንቧ ውሀ አያገኝም

75% መብራት የለውም፣

በ35% የዋጋ ግሽፈት አሳሯን እየበላች ነው፣

የውጭ ገበያ ሚዟን ከዜሮ በታች (-) $12.41b ነው፣

ከ1,000 ህጻናት ውስጥ 80 ህጻናት የአምስተኝ አመት ልደታቸው ሳያከብር ይሞታሉ፣ እጅግ በጣም ብዙ እና ጥልቅ ችግር ያላት ሀገር ናት፣

እብዱ አብይ አህመድ የዝችን ሀገር ችግር (ፍላጎት) ቅደም ተከተል ሲያሲዝ ፓርክና ፓርኪንግ ሎት መጀመሪያው ረድፍ መጥተውለታል፣ እና የሌለ ኢኮኖሚክስ ላይ፣ ምንድን ነው ስለ ኢኮኖሚክስ የምናወራው?

ፍልስፍና philosophy

27 Oct, 18:17


በሕይወት ዘመኔ እጅግ በጣም ክፉ አረመኔ እና ባለጌ ሰዎችን የመተዋወቅ አጋጣሚ የገጠመኝ ቦታዎች 2 ናቸው!
ዩኒቨርሲቲ⁉️
እና
ቤተክርስቲያን⁉️

ፍልስፍና philosophy

27 Oct, 11:30


Live stream finished (2 minutes)

ፍልስፍና philosophy

27 Oct, 11:28


Live stream started

ፍልስፍና philosophy

27 Oct, 08:06


ሰንበት🙏
"...ሰዎች ለዘመናት እያዳበሩ በመጡት አስተሳሰቦች ከህያው የእውቀት ውቅያኖስ ደርሰዋል።ዛሬ ለብዙዎች ስለተፈጥሮ ማወቅ እስከፈለጉ ድረስ የማወቅ ነፃነት እና አቅም አላቸው።በየትኛውም ዘርፍ እውቀትን ለሚሻ መምህራን መፃሕፍት አሉለት።.... ሁሉም የሰው ልጅ በአስተሳሰብ ጥራዙ በሚከተሉት አራት ምሰሶዎች ይኖራል።
፩) በፍልስፍና (Philosophy)
፪)በጥበብ (Art)
፫)በሳይንስ (Science)
፬)በሃይማኖት(Religion)
👉እነዚህ አራት ግንዛቤዎች በበላይነት የሚ'መሩት በፍልስፍና ነው።ፍልስፍና በሁሉም አካሄድ የመላቅ ጥበብ ነው።እውቀትን ራስን ወይም ተፈጥሮን መገንዘብ መቻል ነው።ጥበብም ሆነ ሳይንሱ የሚቀዱት ከፍልስፍና ነው።
👉የሃይማኖት አስተሳሰቦች ምክንያታዊ ምንነታቸውን የሚያገኙት በፍልስፍና ነው።ፍልስፍና ስለምንኖረውም ሆነ ስለምናጠናው ድርጊት እውነት ሁሉ ምክንያታዊ ትርጉም መስጠት ወይም መተንተን ነው። ...
👉ፍልስፍናን ለመረዳት በመጀመሪያ የተዘጋውን የአስተሳሰብ በር በራሳችሁ መክፈት አለባችሁ።ለዘመናት ከልቅና ጥበብ አርቋችኋልና በሩ መከፈት አለበት።ልቦናችሁን ከከፈታችሁት ወዲህ በፍልስፍና ጥልቅ አተናተን የሚገኝ ምርጥ እምነት እንዳለ ትረዳላችሁ።ፍልስፍና ኮ ስለምናከናውናቸው ነገሮች ምክንያታዊ መሆን እንጂ ሌላ አይደለም።ታድያ ይህ ምርጥ የመላቅ ሂደት እንዴት ሊጠላ ይችላል?ፍልስፍናን እንደመጥላት ለሰው ልጅ አሳፋሪ ተግባር የለም።ፍልስፍና የተወሳሰበ የህይወትን ችግር ለመፍታት ቁልፍ የምናገኝበት ነውና ሊወደድ ይገባል።"
ሻሎም🙏

ፍልስፍና philosophy

26 Oct, 18:10


ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሳለን ዶርም ውስጥ እኛ የዶርሙ ልጆች እንቅልፍ እስክንተኛ ድረስ ጠብቆ በብርድ ልብስ ውስጥ ተሸሽጎ ዳቦ ቆሎውን የሚቆረጥመው ስስታም ልጅ
አሁን ላይ ፓስተር ሆኖ ዱባይ ላይ ሲሰብክ በፌስቡክ አየሁት! 🤣

ፍልስፍና philosophy

26 Oct, 11:36


#Rationalism / ምክኖአዊ #Rene_Descartes
*****
አንድ የማይጠረጠር ዕውነታ አሳዩኝ.
አንድ ሊጠረጠር የማይችል ዕውነታ ንገሩኝ.
አንድ ለቀልድ ተብሎ እንኳን የማይጠረጠር ነገር ስጡኝ....ከዛ የዕውቀትን መሰረት አሳያችዋልሁ ይላል ዴካርት።
***
የሬነ ዴካርት የስነ ዕውቀት ቀደምት ዘይቤው በ ‘Methodic doubting ‘ መሰረት የማይጠረጠር ነገር ላይ እስክንደርስ ድረስ፣ ሁሉንም ጠርጥር የሚል ነው። ይህን ዘዴ እራሱ ላይ ሞከረው፣ በሚከተለው ሂደት……
***
- አለው? #Do_I_existበህይወት ካለው ምን ዓይነት ፍጥረት ነኝ
- በህይወት መኖሬን እንዳምን፣ የትኛውን የእኔን ምንነት በፍፁም ልቤ ልመን
- ከሁሉም ነገሬ ማሳቤን ማመን አለብኝሆኖም ይህን ማሰቤንም ግን እጠራጠረዋልሁ። ግና ይህ ጥርጣሬዪ ደግሞ በህይወት መኖሬን ያረጋግጥልኛል። ምክንያቱም ለመጠርጠር ማሰብ ያስፈልገዋል። ስለዚህ ካሰብኩ አልሁ።

#I_think_there_for_I_am.

I exist because I think.

I am because I think.
***
ህልው / existence በማሰባችን ይወሰናል። የማያስብ እንደ ሞተ ይቆጠራል ማለት ነው። በህይወት አለሁ? አዎ አልሁ።ምን አይነት ፍጥረት ነኝ? የሚያስብ ፍጥረት ነኝ። I am a being whose essence/identity is to think.
ሬነ ዴካርት የ Analytical geometry አባት ነው። የዚህ የሂሳብ ዕውቀቱ ነው ፍልስፍና ውስጥ የዶለው ይላሉ የፍልስፍና ምሁራን።
***
አለን ለማለት የስሜት ህዋሳታችንን ማንቃት ያስፈልጋል። ምክንያቱም እነሱ በሰጡን መረጃ ነው የምናውቀው። ነገር ግን የስሜት ህውሳቶቻችን ብዙውን ጊዜ አሳሳቾች ናቸው።
***
ለምሳሌ ... ውሃ በተሞላ ብርጭቆ ውስጥ የተቀመጠን እርሳስ ወይም ቀጭን እንጨት ስንመለከት ከውሃው በላይ ቀጥ ያለ ሲሆን ውሃው ውስጥ ያለው ቀጥ ብሎ ሳይሆን ተጣሞ ነው የሚታየን። ሆኖም ይህንን በአንደዜ ቀጥ ያለና የተጣመመ የመሆንን ሁኔታ አዕምሮአችን ያስተካክለዋል, ይላል።
***
አመሰግናልሁ

ፍልስፍና philosophy

25 Oct, 14:56


#ፍርሃት ፦ ሁሉን ነገር እንዳታውቁ የሚጋርድ ፣ሁሉን ነገር እንዳትረዱ የሚከልል የአእምሮ ጥቁር በርና የልማድ መጋረጃ ነው።

የፍቅር አካል ስትሆኑ ፍርሃት እዚያ አይኖርም ፤ ንቃተ ህሊና ሲደረጅ #ልበ_ሙሉነት_ይከሰታል ።
ስትፈሩ የተዘጋ የሚመስለውን በር አልፋችሁ አዲስ ነገር ለመረዳት አትችሉምና ከፍርሃት ነፃ ሁኑ ።

#ኦሾ/OSHO

ፍልስፍና philosophy

24 Oct, 10:09


ምክር ለሴቶች⁉️
•••••••••••••
በጅንጀና ወቅት የወንዱን የፍቅር ጥያቄ በይሁንታ ከማፅደቅሽ በፊት ልብ ልትያቸው የሚገቡ ነገሮች እንዳሉ አስቢ። አብዛኛውን ጊዜ ከውበትና ተክለ ሰውነት ምዘና ባሻገር ግለሰቡን የገነቡት ማንነቶች ከእኔ ማንነት ጋር ውህደት መፍጠር ይችላሉ ወይ የሚለው ላይ ትኩረት ሰጥተሽ ለመረዳት ሞክሪ። ውበት ለፍቅር ግንኙነት መግቢያ በር ቢሆንም ብቻውን መኖሪያ ሊሆን እንደማይችል አስቢ። ውበት በር እንጂ ቤት አለመሆኑን አስቢ። በበር ላይ በመቆም ጊዜ አታጥፊ። ማንነቱን ወደ ገነቡት ጥልቅ የስነ ልቦና ግብአቶች ዘልቀሽ ለመሄድ ጥረት አድርጊ።ለቅፅበታዊ ውሳኔ የሚያጋልጡ ክስተቶችን ለማለፍ ሞክሪ።

በአካላዊ ውበት ላይ ብቻ መሰረት በማድረግ ብቻ ወደ ግንኙነቱ አትግቢ። የሱ መሰረታዊ ማንነቶች አንቺ የምትፈልጊው አይነት መሆኑን ተረጂ።ወንዶች የጅንጀናው መጀመሪያ ደረጃ ላይ ብዙ ጉዳዮች ሊደብቁ እንደሚችሉ አስቢ። ከውሳኔሽ በፊት ግለሰቡ የደበቃቸው ጉዳዮች ካሉ ምን እንደሆኑ ጠንቅቀሽ ለማወቅ ሞክሪ።በህይወትሽ ክፍተት የፈጠርሽባቸው ጉዳዮችን እንደ ድክመት በማየት በሚፈጠር ጫና የሚደረግ የፍቅር ጥያቄን አታስቀድሚ። ደካማ ሴቶች አስቸጋሪ  ጊዜን ለመጋፈጥ የሚጠቀሙት የመጀመሪያው አቅም ውበታቸውን እንደሆነ አስቢ። በህይወትሽ ያጋጠሙ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለመፍታት ውበትሽን ከማጋፈጥ የተሻሉ ሌሎች አማራጮችን ለማጤን ጥረት አድርጊ።

ከእድሜ፣ ተክለ ሰውነትና የሀብት ፍላጎት በተለየ መልኩ በአንቺና በእርሱ መካከል የማንነት ውህደት መፍጠር የሚያስችሉ የስነ ልቦና ግብአቶች መኖራቸውን አረጋግጪ። ዘለቄታዊ ለሆነ ጣፋጭ የፍቅር ግንኙነት ከአካላዊ ውበት ይልቅ የስነ ልቦና ውህደት አስፈላጊ መሆኑን ተገንዘቢ። በባህሪ፣ በአመለካከት ወይም በአስተሳሰብ ደረጃ የምትፈልጊው ማንነት ይዞ መገኘቱን ፈትሺ። የመለያየት ምክንያቱ የውበት ችግር ሳይሆን የስነ ልቦና ውህደት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች መሆናቸውን አትርሺ። ውበትና ተክለ ሰውነትን የመሳሰሉ ፈታኝ የሆኑ ቅፅበታዊ ግብአቶችን ለጊዜው ለውሳኔሽ አትጠቀሚ። የግለሰቡ ያለፈ ታሪክ አስፈላጊ ቢሆንም ወቅታዊ አቋሙን በመፈተሽ ላይ ትኩረት ስጪ።

በስሜት የሚገኙ መረጃዎችን ለውሳኔሽ ከመጠቀም ተቆጠቢ። "ልጁ በጣም  ያሳዝነኛል፣ ልጁ በጣም ኩራቱ ይማርከኛል" በሚሉና በመሳሰሉ ተልካሻ የስሜት መረጃዎች በመመርኮዝ ወደ ይሁንታ ውሳኔ ለመመራት አትቸኩይ። የግለሰቡን የህይወት መርህ፣ አስተሳሰብ፣ የወደፊት ራዕይ ለመረዳት ሞክሪ። ጫፍ የወጣ ፍቅር ከመስጠት ተቆጠቢ። ወንድ ልጅ በማስመሰል ሊጫወታቸው የሚችሉ ጊዚያዊ ባህሪያትን ሊያንፀባርቅ እንደሚችል አስቢ። ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ሳትደርሽ መባዳት መተሻሸት፣ መተቃቀፍና የስሜት ምንጭ የሆኑ ንኪኪዎችን በተቻለ መጠን ለመቀነስ ሞክሪ። በፍቅር መጀመሪያ ወንዶች ከፍተኛ መስዋዕትነት ፣ በፍቅር መጨረሻ ደሞ ሴቶች መራራ መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ አስቢ። የመጀመሪያው መስዋእት አንቺን ለማግኘት ሲሆን የመጨረሻው መስዋእትነት ደግሞ አንቺን ለመክዳት የሚደረግ መሆኑን አስቢ።

ይቀጥላል....

ፍልስፍና philosophy

23 Oct, 15:51


በታሪክ "ፍልስፍና" (philosophy) የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተጠቀመበት የሚታመነው ፓይታጎረስ ነው። በዘመኑ የነበሩ ገዢዎች ማንነቱን ሲጠይቀት "እኔ ፈላስፋ ነኝ" ብሏቸው ነበር። ከጥበብ ጋር በፍቅር የወደቅሁ ነኝ ማለቱ እንደሆነ ይታመናል።

በዚህም ምክንያት ገዢዎቹ 'ፈላስፋ' ምን ማለት እንደሆነ እንዲያብራራላቸው ጠየቁት፤ እርሱም የፈላስፋን ትርጉም ለማብራራት የኦሎምፒክ ጨዋታን ለመመልከት የተሰበሰበን ህዝብ ፥ እንደ ምሳሌ በመጠቀም እንድ ፍላጎታቸው ዓይነት በሦስት ጎራ የከፈላቸው ሲሆን፦

የመጀመሪያዎቹ ተፎካካሪዎች ሲሆኑ፤ ፍላጎታቸው አንድም ቁሳዊ ካልሆነም ግላዊ ዝናና ክብር ነው። ሁለተኛዎቹ ከውድድሩ ትርፍ ለማግኘት የተሰበሰቡ ነጋዴዎች ሲሆኑ ፥ ብቸኛ ፍላጎታቸው ትርፍን በሽያጭ ማግኘት ነው። በሦስተኛው የሚገኙት ደግሞ ከየትኛውም የማይወግኑ ተመልካቾች ናቸው። ቁሳዊ ጥቅምም ሆነ ግላዊ ክብር ፥ አልያም ከሚሸጡት ለማትረፍ የሚገኙ ሳይሆኑ፤ ምን እየተደረገ እንደሚገኝ ለመመልከት የተሰበሰቡ ናቸው፤ በአጭሩ እዉነትን ለመረዳት ተገኝተዋል።

እንዲሁ ፈላስፋ ማለት በሕይወት ጨዋታ ላይ የተገኘ ተመልካች፤እውቀትን(እውነትን) በመከተል የሚደክም ሰው ነው፤ በማለት ነበር ያብራራላቸው።
ጥበብ ከጲላጦስ

ፍልስፍና philosophy

22 Oct, 18:37


ይድረስ ለኢትዮጵያውያን⁉️
••••••••••••••••••••••
ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር እፈራለሁ፣ የምፈራው መንግስትን አይደለም፣ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ወይም ቀስት የወደረ ሰው አያስፈራኝም፣ የምፈራው ማህበረሰቡን ነው፣ እንደ ማህበረሰብ የገባንበት የሞራል ዝቅጠት መለኪያ የለውም፣ የትየ ለሌ ነው፣ ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ ብለው ባሊስትራ የሸጡ፣ እንጀራ በሚል ሥም ሳጋቱራ የሚጋግሩ፣ ሙዝ ለውሰው ቂቤ ነው ብለው የሚሸጡ በርበሬ ብለው ሸክላ የሚፈጩና ከማምታታት ውጭ ምንም ሙያ የሌላቸው የዛሬ አራት/አምስት ወራት ገደማ ጀሶ ከጤፍ ጋር ቀላቅሎ እንጀራ ጋገረ ስለተባለ ድርጅት በዜና ስሰማ መሀል አናቴን በቆላ ዱላ የገመሱት እስኪመስለኝ ሰማይና ምድር ዙሮብኝ ነበር፣ እኔ ደግሞ ዜናው ላይ አላቆምም፣ ሳልወድ በግድ ብዙ ጥያቄዋች ጭንቅላቴን ወጥረው ይይዙታል፣ ስለታወቀው ትቼ ያልታወቀው ያሳስበኛል፣ እፈራለሁ፣

ሌላውን ቀርቶ የግል ሆስፒታሎች ያኔ ከኮቪድ ጋር በተገናኝ የሚፈፅሙት ግፍ አደንዝዞኛል፣ ሁለት መቶ ሺህ ብር ካላስያዝክ አናክምም ብለው ሞት አፋፍ የደረሰ በሽተኛን የሚመልሱ ሀኪሞች፣ ቀሪ ገንዘብ አለብህ ብለው አስከሬን የሚከለክሉ ሆስፒታሎች በአለም ላይ መኖራቸውን እጠራጠራለሁ፣ ግማሽ ሰውነቱ በእሳት አደጋ የተቃጠለን ሰው ቅድሚያ ሕይወት ማትረፍ ሲገባ ስለ ተያዥ ገንዘብ ንዝንዝ ውስጥ ይገባል?

በባእድ ሀገር እንግዳ-ደራሽ ሁነህ እንደ ኮቪድ ያለ ድንገተኛ በሽታ ቢያገኝህ እንኳን ገንዘብ ስምህን ሳይጠይቁ ነው ነብስህን ለማትረፍ የሚረባረቡት፣ በየትኛውም አለም የህክምና መርህ አንድ ነው:- patient-first/ ቅድሚያ ለታካሚው፣ እንኳን ገንዘብ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው በሽተኛን እንዲታደጉ ሙያው ግድ ይላቸዋል፣ የት አለ ኢትዮጵያውያዊነት መልካምነት ሐይማኖተኛ ህዝብ? ቅድስት አግር? ቅብርጥስ ሲባል የተኖረው?

አብይ አህመድ የሚመራ ቡድን መንግስት ነው ብዬ አላስብም እሱን እርሱት፣ ይህ የሆስፒታሎች ተግባር public outrage አለመፍጠሩ ግን ገርሞኛል፣ ህዝብ እንዴት በዚህ አይቆጣም? ህዝቡ ትክክል ነው ብሎ ተቀብሎት ነው የሚኖረው? ምናልባት ከዚህ የከፋ አይቷል ማለት ነው? እንዲህ ያለ ነገር ነው የሚያስደነግጠኝ፣ የሚያስፈራኝ፣

የግለሰቦች ዝቅጠት ማህበረሰባዊ ሲሆን በአይናችን እየተመለከትን ነው፣ ነውርን የሚፀየፍ ትውልድ ጠፍቷል፣ ሌባ ህዝብን እንደ ጠበቃ መግዛት ጀምሯል፣

Anyways I truly enjoy and cherish the public morality of my host country, than anything else. እኔ የማቴሪያል ሰው አይደለሁም፣ እንደ ሰው መኖር ነው ትልቁ ነገር፣ አንተ ላይ ሊደረግብህ የማትፈልገውን ሰዋች ላይ ሳታደርግ መኖር ነው ቁልፍ

ሁሉን ማወቅ መልካሙን መያዝ።

ፍልስፍና philosophy

22 Oct, 18:36



ፍልስፍና philosophy

22 Oct, 10:25


"አልችልም" የማለት ችሎታ
***
ይህ የአይንስታይን ሌላኛው እውቀት ነው። የማይችሉትን አልችልም ማለት።
አልበርት አንስታይን የእስራኤል ኘሬዚዳንት እንዲሆን ተጠይቆ እንደነበር ታውቃላችሁ?
እስራኤል በጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ስሌት በ1948 ነው የተመሰረተችው። በወቅቱ አገሪቱን እንዲመሩ ተመርጠው የመጀመሪያው የእስራኤል ኘሬዚዳንት ሆነው ስልጣን ላይ የወጡት ዶ/ር ሀይም ዋይዝማን ናቸው። ሩሲያ የተወለዱት ባዮ ኬሚስቱ ዋይዝማን አሲቶንን የተለያዩ ጥራጥሬዎችና ድንችን በማብላላት ያበለፀጉ ሳይንቲስት ናቸው።
እስራኤል አገር ሆና እንድትቆም ካደረጉ ምሰሶዎች መካከል አንዱ የሆኑት እኒህ ሰው በ1952 ህይወታቸው ሲያልፍ በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዴቪድ ቤን-ጉሪዮን በአሜሪካው አምባሳደራቸው አማካኝነት ለይሁዲው ሳይንቲስት አንድ ደብዳቤ ላኩ።
"የእስራኤል ኘሬዚዳንት እንድትሆን እንፈልጋለን"
አይንስታይን መልሱን በወረቀት ጽፎ አደረሰ።
እንዲህ በማለት፦
"ፕሬዝዳንት ሆኜ እንዳገለግል በቀረበልኝ ጥያቄ በጣም ተነክቻለሁ፤ ይህንን በቀላሉ የማይታለፍ እድል ልቀበለው ባለመቻሌ ግን አዝኛለሁ፤ አፍሬያለሁ። ህይወቴን በሙሉ የሚጨበጡ ጉዳዮችን ስመለከትና ስመረምር ነው የኖርኩት። ከሰዎች ጋር ስለሚኖረኝ ግንኙነትና ተግባቦት የመለማመድ ተፈጥሯዊ ችሎታ እና ልምድ የለኝም። በነዚህ ምክንያቶች ብቻ ለዚህ ታላቅ ሀላፊነት ብቁ አይደለሁም። "
Philosophy-ፍልስፍና
ሁሉን ማወቅ መልካሙን መያዝ።

ፍልስፍና philosophy

21 Oct, 17:53


ፍልስፍና ጨው ነው፤ ሕይወትን ያጣፍጣል፡፡ ፍልስፍናን የሚፈሩ ሰዎች ሃሳብን የሚፈሩ ናቸው፡፡ ፍልስፍና ዩንቨርስቲ ውስጥ ብቻ አይደለም መገኛው፡፡ ፍልስፍና ቢሮም፣ ጠጅ ቤትም፤ ግሮሰሪም፣ ካፌ ውስጥም፤ አረቄ ቤትም አለ፡፡ ፍልስፍና በመስጊድም በቤተክርስቲያንም አይጠፋም፡፡ ፍልስፍና ሰው ባለበት ሁሉ ይኖራል፡፡ ነፍሱን ይማረውና ታላቁ ሳይንቲስት ስቴፈን ሆውኪንግ በፈረንጆቹ 2010 ላይ ባቀረበው ትልቁ ስራው በሆነው “The Grand Design” ጥናቱ የፍልስፍና አስፈላጊነት ሙሉ በሙሉ በሳይንስ ስለተተካ ፍልስፍና ሞቷል ብሎ አውጆ ነበር፡፡ ነገር ግን የፍልስፍናን ሞት ሳያረጋግጥ፣ በቀብሩ ላይ ሳይገኝ እሱ ራሱ ቀድሞት ሞተ፡፡

በዚህ ዘመንም ፍልስፍና ህይወት አልባ ሆኗል የሚሉ አሉ፡፡ በሰሞኑ የእስራኤልና የሃማስ ግጭቶች እንኳን ፍልስፍና (philosophy) በርዕዮትዓለም (ideology) መሸነፉን የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ የኢየሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ በድረገፁ በግል-ሃሳብ (opinion) አምዱ ላይ ከትናንት በስቲያ ባወጣው ዘገባ መሰረት የምዕራባውያን ፍልስፍና የሃማስን ርዕዮት ዓለም ማሸነፍ አልቻለም (Israel’s Western philosophy can’t beat Hamas ideology) ብሏል፡፡ ፀሐፊው በዚህ ሃሳቡ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን አትቷል፡፡ ሆኖም ግን ሌላውን ትተን ፍልስፍናዊ ሃሳቡን ብቻ ነቅሰን ስናወጣ ‹‹ሰዎች ከተነጋገሩና ከተወያዩ ያ ፍልስፍና ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች እርስበርሳቸው ከተዋጉ ያ ርዕዮት ዓለም ነው (If peoples are discussing, it;s philosophy፤ if they are fighting, it is ideology)›› የሚለው ንግግሩ የፍልስፍናንና የርዕዮት ዓለምን ልዩነት በቀላሉ ያሳያል፡፡

ፍልስፍና በሃሳብ ውይይት የሚያድግና የሚዳብር ነው፡፡ ርዕዮት ዓለም ግን እንደእምነት የሚቀበሉት ነው፡፡ ሰው ለፍልስፍና ሲል አንዲት እርምጃ አይሄድም፤ ለርዕዮት ዓለሙ ሲሆን ግን ህይወቱን ሳይሳሳ ይሰጣል፡፡ በመላው ዓለምም ይሁን በሐገራችን የምናየው ይሄንኑ ነው፡፡ የሐገራችን ፖለቲከኞችም በሃሳብ ውይይት አያምኑም፡፡ ጥይት መተኮስ እንጂ ሃሳብ መተኮስ አይችሉበትም፡፡ አዲስ የጦር መሳሪያ መታጠቅ እንጂ አዲስ ሃሳብ መታጠቅ አልተማሩም፡፡ እንደእምነት ለተቀበሉት ርእዮት ዓለማቸው ሲሉ ግን የምስኪኖችን ደም በከንቱ ያፈስሳሉ፡፡

ባልና ሚስትም የትዳራቸውን ግድግዳ በፍልስፍና ማገር አልማገሩም፡፡ ወደድኩሽ ወደድኩህ ተባብለው በስሜት የጀመሩት ትዳር ስሜቱ ጋብ ባለ ጊዜ፣ ፍቅሩ የቀዘቀዘ ቀን ተነጋግሮ መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አለመግባባት መሰለቻቸትን፤ መሰለቻቸት መጣላትን፤ መጣላት መለያየትን ያመጣል፡፡ በፍልስፍና ያልዳበረ ፍቅር መጨረሻው አያምርም፡፡ መከራከር፣ መነጋገርና መወያየት የሌለበት ወዳጅነትም ይሁን ዝምድና ዕድሜው አጭር ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ ሰው ማሰብ እስካላቆመ ድረስ ፍልስፍና አይሞትም! ማንም ሃሳብን መግደል እንደማይቻለው ሁሉ ፍልስፍናንም መግደል አይችልም፡፡ ፍልስፍና የነፍሳችን ጥሪ ነው፡፡ እውነትን ፈልገኝ የምናገኘው በፍልስፍና መንገድ ነው፡፡ ፍልስፍና የሌለበት ሕይወት አይጣፍጥም፤ አልጫ ነው፡፡

ሁሉን እንወቅ መልካሙን አንያዝ።

ፍልስፍና philosophy

21 Oct, 14:29


ታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ እና እንጦጦ ፓርክ
******
ታላቁ ፈላስፋ ፕለቶ የሰው ልጅ ከተፍጥሮ ውበት ጋር ያለው መስተጋብር ሰዎች ለማህበራዊ ፍትህና የፖለቲካ መረጋጋት ካላቸው ፍላጎት ጋር ይያዛል ይላል። በዚህም ለተፈጥሮ ውበት እና ይህን ፀጋ በማጎልበት ተዝናኖትን ለመፍጠር የሚሹ ሠዎች ስብዕናቸው ከፀብና ከአምባጎሮ የራቀ እንዲሁም ለፍትህና ፖለቲካዊ መረጋጋት ቀናዎች መሆናቸውን ይገልፃል።
***
ይህ ትስስር በጣም አስፈላጊና ጉልህ መሆኑን የገለፀው ፈላስፋው ፕሌቶ ስለ ፍትህ እና መልካም ምግባር በጎ አመለካከት ከሌለን ተፈጥሮአዊ አካባቢያችንን ለመጉዳት አንደማንመለስ ይገልፃል።
****
በመሆኑም የሰው ልጅ ለተፈጥሮ ውበት ያለውን ዕይታን ለማስተካከል የአሳቢዎችና የአክቲቪስቶች ዋና ስራ መሆን አለበት ይላል።

እንደ መውጫ
**
በትናትናው ዕለት በተመረቀው የእንጦጦ ፓርክ ጥቂት የማይባሉ ሠዎች ነቀፌታ እና ተቃውሞ ማሰማታቸውን ታዝበናል። ከነዚህ መካከል ጥቂቶቹ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ባህል በገነገነው መልካም ነገርን ያለማድነቅ አባዜ የተለከፉ እና የመንግስትን ወይም የጠ/ሚር አብይ ስኬቶች የማይስማማቸው ናቸው, ለርካሽ እና ጊዚያዊ ፖለቲካዊ ትርፍ።
***
ሌሎቹና አብዛኛዎቹ ደግሞ ሁለት አይዶል ሾው አይተው በሶስተኛው ሾው እራሳቸው ለዳኝነት የሚያጩ "ሁሉ አወቅ" የሆኑ የሚመስላቸው ናቸው።
***
ብርሃን ስታይ ተከተል🌅🌅🌅

አመሰግናለሁ

ፍልስፍና philosophy

21 Oct, 03:59


4ቱ ልዕልናዎች The Four Cardinal Virtues
📚📚📚
ልዕልናዎች (Virtues) አመክንዮ ላይ የተመሰረቱ የአእምሮ ባህርያት ሲሆኑ እነዚህም ልዕልናዎች የሰውን ልጅ ደስታ እንደሚያጎናፅፉ ይታመናል፡፡ በታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ መሠረት ደስታን የሚያጎናፅፉ የህይወት ልዕልናዎች አራት ናቸው፤ እነሱም፣
📚
1) ጥበብ Wisdom/Prudence
ለትክክለኛ ድርጊት ትክክለኛ ጊዜና ትክክለኛ ቦታ ማወቅ፣ ‹‹ምን?―እንዴት?―መቼ?―የት?―ማን?›› የሚሉትን ጥያቄዎች የማቀናጀት ችሎታ፤ ይሄ እሴት በተለይ ህዝብን ለሚመሩ ሰዎች እጅግ የሚያስፈልግ እሴት ነው እንደሆነ ይታመናል፤
📚
2) ታጋሽነት Temperance/Moderation
ስሜትን የመቆጣጠርና የመግራት ችሎታ፤ ይህ ልዕልና ለሁሉም የህብተሰብ ክፍል አስፈላጊ ቢሆንም፣ በተለይ ግን ለአምራቹ የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ነው፤
📚
3) ጉብዝና/ደፋርነት Courage
ፍርሃትን ማሸነፍ፣ በአስቸጋሪ ጊዜ መፅናት፣ አቋም ያለው፣ በወቅታዊ ማዕበል በቀላሉ አለመናወፅ፤ ይሄ ደግሞ ለወታደሮች እጅግ ጠቃሚ የሆነ እሴት ነው፡፡
📚
4) ፍትሐዊነት Justice
ፍትሐዊነት ለአንድ የህብረተሰብ ክፍል ተለይቶ የሚሰጥ እሴት ሳይሆን፣ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከት ነው፡፡
📚
አሪስቶትል እነዚህን የፕሌቶ አራት ልዕልናዎች ይቀበልና እንደ "ጓደኝነት" ያሉ ሌሎች ልዕልናዎችንም ይጨምርበታል።

ቶማስ አኳይነስ ግን እነዚህን የፕሌቶና አሪስቶትል ልዕልናዎች ‹‹..የዚህ ምድር ልዕልናዎች ናቸው›› ይላቸዋል፡፡
አጅሬ ግን፣ ያሉን ልዕልናዎች እነዚህ ምድራዊ ልዕልናዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ሦስት የሰማያዊው ዓለም ልዕልናዎችም እንዳሉነ ቅዱስ ጳውሎስን በ1ቆሮ 13:13 ይጠቅሳል።

በዚህም.....
እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር ― faith, hope and love, በአኳይነስ አመለካከት ዘላለማዊ ህይወት እና ደስታን ለመጎናፀፍ እነዚህን ሰማያዊ ልዕልናዎች የግድ ማሟላት እንዳለብነ ይነግረናል።
🙏🙏🙏
አመሠግናለሁ