part 2
***
ከጋብቻ በፊት ከሚደረግ ወሲባዊ ሐጢያት እራሳችንና ጓደኛችንን እነዴት መጠበቅ እንችላለን?
እንዴት በወሲባዊ ንፅህና እስከ ጋብቻ መቆየት እንችላለን?፦
✅1, እጮኛሞች በግልም ሆነ አንድ ላይ ሲሆኑ እግዚአብሔርን መፍራት አለባቸው ። የትም እግዚአብሔር እንደሚያይ ማሰብ አለባቸው። ለእጮኝነታቸው መፀለይ ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠት።
✅2,በወሲባዊ ጉዳዮች ዙሪያ እጮኛሞች በግልፅ ሳይተፋፈሩ ለሐጢያትም በማይጋብዝ መልኩ ማውራት።
✅3, እጮኛሞች እርስ በርሳቸው ግልፅ ሊሆኑ ይገባል። ያለፈ የፍቅር ታሪክ ኖሮ በዛ ውስጥ ስተት ካለ በግለፅ መናገር። ይሄ ጥርጣሬ እንዳይኖርና ጓደኞች check ለማረግ የሚፈልጉት ነገር እንዳይኖር ይረዳል።
✅4, በቅርቡ የመጋባት እቅድ ከሌላቸው እንዲነፋፈቁ፣ እንዲፈላለጉ አዘውትረው ለመገናኘት የሚገፋፋቸውን ስሜታዊ ቃላትን አለመጠቀም።
✅5, በቅርብ ጊዜ የመጋባት እቅድ ከሌላቸው አዘውትሮ አለመገናኘት፤ ተመካክሮ ለሚገናኙበት ጊዜያት ገደብ ማድረግ።
✅6, ሲገናኙ ሁሌም ግልፅና ሰዎች በሚበዙበት ቦታ መገናኘት። ይሄም የወሲብ ሃሳብ አይምሯቸው ወስጥ እንዳይፈጠር ይረዳል
✅7, ወሲብ ቀስቃሽ የሆኑ photoችን በተለይ #ሴቶች አለመላክ (በስልክ) በአካልም ሲገናኙ መጠነኛ የሆነ አለባበስ መልበስ። ይሄም ጓደኛችሁ በዝሙት ሐጢያት እንዳይወድቅ ይረዳዋል፤ #ወንዶችም ጓደኛችሁን ለዝሙት የሚያነሳሳ ስጦታ አለመግዛት።
✅ 8,እጮኝነትን ለቤተክርስቲያን፣ ለቤተሰብ አንዲሁም ለቅርብ ሰዎች ማሳወቅ። ይህም በድብቅ የሚደረግ መገናኘት እንዳይኖር በዚህም ከዝሙት እንዲጠበቁ ይረዳል። በተጨማሪም የቤተክርስቲያን መሪዎችን ጥያቄ በሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ በግልፅ መወያያት።
✅ 9, ስለግንኙነታቸው ብቻ በማውራት ረጅም ጊዜን አለማሳለፍ። ይልቁን ስለስራ፣ ስለትምህርት፣ስለ አገልግሎት ማውራት።
✅ 10, በጋራ ቋሚ program አውጥቶ መፅሐፍ ቅዱስ ማንበብ።
✅ 11,በጋራ ቋሚ program አውጥቶ አብሮ መፀለይ።
✅ 12, የእጮኝነትን አላማ ማወቅ እሱም ትዳር እንደሆነ።
✅ 13, እጮኛ የሌለው ሰው ደግሞ ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ
✅14, በተቻለ መጠንም ትዳር መስርቶ አብሮ የሚኖርበትን መንገዶች መፈለግ እግዚአብሔርንም መጠየቅ። ምክንያቱም ጊዜ በሄደ ቁጥር ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ስለሚሆኑ።
*
የወሲብ ቅድስናን መጠበቅ የሚያስገኛቸው በረከቶች፦
1, በእግዚአብሔር ፈቃድና ትዕዛዝ ላይ የተመሠረተ እጮኝነት ለነፍስም ለስጋም እረፍትና በረከትን ይሰጣል። ፍርሃትና ጥርጣሬ የለበትም።
2, እግዚአብሔር ደስ የተሰኘበት ሁሉ ፍፁምና መልካም ነው። ነገ ይፈርሳል ተብሎ አይሰጋበትም። እግዚአብሔር ዋስ ይሆንለታል።
3, የወደፊት ትዳር የተረጋጋ ሰላም የሞላበት እዲሆን ያደርጋል።
4, እጮኛሞች አይምሯቸው፣ ሁለንተናቸው በእግዚአብሔር የተጠበቀ ይሆናል።
5, ወሲባዊ ንፅህናው በተጠበቀ ትዳር ውስጥ የሚወለዱ ልጆች በመንፈስ ብርቱዎች ይሆናሉ።
6, ቤተሰባዊ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ መከባበር፣ መስማማት፣ መረዳዳት በእግዚአብሔር ሃሳብ ይሆናል።
7, ልጆች ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው፣ለቤተክርስቲያን እንዲሁም ለሀገር ጠቃሚ ሆነው የሚያድጉበት ማንነት ይገነባሉ።
8, የህሊና ወቀሳ አይኖርም።
9, ቤቱም የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል።
10, የንብረት ብክነት አይኖርም።
11, ግራ መጋባት፣ አላማ ማጣት፣ተስፋ መቁረጥ አይኖርም።
***
ለእጮኝነት የምንመርጠው ሰው ለዘላለም ህይወታችን ወሳኝ ሰው ነው። ምክንያቱም ትዳር እስከመጨረሻው አብረን የምንኖረውን ሰው የመምረጥ ጉዳይ ነው።
ታዲያ በዚህ ትልቅ ምርጫ ወሲብ እንዴት መስፈርት ይሆናል?
ትዳር ቀልድ አይደለም የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል።
⚠️አስተውሉ የምታገቡት ሰው
ወይ ወደ ሲዖል
የሚወስዳችሁ ወይም ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መንግስት የሚወስዳችሁ ድልድይ ነው።
⚠️ ተጠንቀቁ!!
@behayluminilu
@behayluminilu
@behayluminilu