፡
ትላንት ማታ… ነገ በአዳማ ከተማ ለሚደረገው ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ለአባቶች እና ለተማሪዎች አዳማ ደርሶ መልስ በነፃ የትራንስፖርት ቻሌንጅ ቲክቶክ ላይ በቀጥታ ላይቭ አስጀምረን በእናንተ ጊዮርጊሳዊያን ቤተሰቦች እርብርብ እና እገዛ በአጭር ሰዓት ለሁለት ባስ የደረሶ መልስ ዋጋ የሚሆን 48 000 ብር (አርባ ስምንት ሺ ብር) ሰብስበናል። በዚህም መሰረት ሁለት የነፃ አዳማ ደርሶ መልስ ባሶችን አዘጋጅተናል።
፡
ስለዚህም አባቶች እና ተማሪዎች ((አባቶች እና ሴቶች ይበረታታል ቅድሚያ እንሰጣለን)) ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24 /2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በስፖርት ማህበራችን መዝናኛ ክበብ እየመጣቹ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን።
፡
ሼር በማድረግ እንዲሁም ፌስቡክ ለማይጠቀሙ አባቶች እና ተማሪዎች በመደወል አድርሱልን 🙏 ጊዜው አጭር ስለሆነ እገዛቹ አይለየን